AAUFC | Addis Ababa University Federalism Club
285 subscribers
155 photos
14 files
43 links
Welcome to AAU Federalism Club. We aim to promote knowledge, tolerance, and unity among our diverse students.
Let's embark on this journey towards a stronger and more inclusive Ethiopia.
aaufc01@gmail.com
@aaufc01
linkedin.com/company/aau-federalism-club
Download Telegram
AAUFC | Addis Ababa University Federalism Club
Photo
ሀገራችን ለሁሉም የምትመች ለማድረግ መስራት ያስፈልጋል፡-ዶ/ር ኃይለየሱስ ታዬ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 20፣ 2017 (ህፌአማ) ሀገራችን ብዙ ብሔሮች የሚኖሩባት ሀገር ስለሆነች ለሁሉም ብሔር የምትመች ለማድረግ መስራት ያስፈልጋል ሲሉ ዶ/ር ኃይለየሱስ ታዬ ገለፁ፡፡

የህገ መንግስትና ፌደራሊዝም አስተምህሮ ማዕከል ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የፌደራሊዝም እና አስተዳደር ጥናት ማዕከል ጋር በመተባበር ለፌደራሊዝም ክበባት አባላት መሰረታዊ የፌደራሊዝም ፅነሰ ሀሳቦች ዙሪያ ለተከታታይ አራት ሳምንታት ሲሰጥ የነበረው የግንዛቤ ማጨበጫ ስልጠና መድረክ ዛሬ ተጠናቋል።

በማጠናቀቂያ መድረኩ ላይ የተገኙት ዶ/ር ኃይለየሱስ ታዬ እንደተናገሩት፤ ሀገራችን ለሁሉም የምትመች ለማድረግ መወያየት፤መነጋገር እና ትክክለኛውን መንገድ መያዝ እንደሚገባ ጠቁመው፤ ለዚህ ደግሞ ፌደራሊዝም የተሻለ አማራጭ ነው ብለዋል፡፡

የፌደራል ስርዓት ላይ የሚታዩ ችግሮችን በየጊዜው እየፈቱ መሄድ ያስፈልጋል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ማዕከሉ በፌደራሊዝም ዙሪያ የተዛባ ግንዛቤ ያላቸውን አካላት ተገቢውን እውቀት በመፍጠር ግንዛቤን የማሳደግ ስራ እየሰራ እና በተወሰነ ደረጃም ለውጦች እየተስተዋሉ ነው ሲሉ ዋና ዳይሬክተሩ ተናግረዋል፡፡

በቀጣይም ማዕከሉ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የፌደራሊዝም ክበብ ጋር በእቅድ የተደገፍ ቅርብ ግንኙነት በመፍጠር በተለያዩ ጉዳዮች ላይ እንደሚሰራ ጠቁመው፤ የፌደራሊዝም ክበባት በሌሎች ዩኒቨርስቲዎች የማቋቋም እና የማጠናከሩ ስራ በቀጣይ በትኩረት ይሰራል ብለዋል፡፡

የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የፌደራሊዝም እና አስተዳደር ጥናት ማዕከል ዲን ዶ/ር ከተማ ዋቅጅራ በበኩላቸው፤ የጥናት ማዕከሉ በፌደራሊዝም ዙሪያ ተለያዩ ተግባራትን እያከናወነ መሆኑን ጠቅሰው፤ በቀጣም ከአስተምህሮ ማዕከሉ ጋር በቅርበት እንደሚሰሩ አሳውቀዋል፡፡

ስልጠናው እንዲሳካ የተለያዩ ድጋፍ ያደረጉ የአስተምህሮ ማዕከሉ፣ የክበቡ፣ የጥናት ማዕከሉ እና የአዲስአበባ አበባ ዩኒቨርስቲ መምህራን ፣አመራሮች እና ሙያተኞችን አመስግነዋል ።

በመጨረሻም ከተማሪዎች የተለያዩ አስተያየቶች በመቀበል እና የስልጠና ተሳትፎ ምስክር ወረቀት በመስጠት ስልጠናው ተጠናቋል ።

ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት
በዩትዮብ፡- https://www.youtube.com/channel/UCqSFrJ1EpIhLiECdtRwL23g
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/centerforconstitutionandfederalism
ቲክቶክ :- https://www.tiktok.com/@federalismconstit
ቴሌግራም:- @Center4constitutionandfederalism በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

ለሕገ-መንግስታዊነት እና ፌደራላዊ አስተሳስብ መዳበር እንተጋለን !!!

©️ ከ FDRE Center for Constitution and Federalism Training የFacebook ገፅ የተወሰደ
AAUFC | Addis Ababa University Federalism Club pinned «ሀገራችን ለሁሉም የምትመች ለማድረግ መስራት ያስፈልጋል፡-ዶ/ር ኃይለየሱስ ታዬ አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 20፣ 2017 (ህፌአማ) ሀገራችን ብዙ ብሔሮች የሚኖሩባት ሀገር ስለሆነች ለሁሉም ብሔር የምትመች ለማድረግ መስራት ያስፈልጋል ሲሉ ዶ/ር ኃይለየሱስ ታዬ ገለፁ፡፡ የህገ መንግስትና ፌደራሊዝም አስተምህሮ ማዕከል ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የፌደራሊዝም እና አስተዳደር ጥናት ማዕከል ጋር በመተባበር ለፌደራሊዝም…»
የፕሮግራም ጥቆማ

እሁድ መጋቢት 28/2017 ከረፋዱ 5፡10 ጀምሮ ‹‹ፌደራሊዝም ፤ ብዝሃ እና ተመጋጋቢ ማንነቶች›› በሚል ርዕሰ ጉዳይ ከዶ/ር ኃይለየሱስ ታዬ ጋር በፋና ኤፍ ኤም 98.1 የሚደረግ ቆይታን ይከታተሉ

ፕሮግራሙን የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የሕገ-መንግስትና ፌደራሊዝም አስተምህሮ ማዕከል ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት አ.ማ ጋር በመተባበር ያቀርቡታል፡፡

ይከታተሉ! ይሳተፉ!
በ09-88-88-50-51 ላይ ጥያቄዎን በመልዕክት ይላኩ
ለሕገ-መንግስታዊነት እና ፌደራላዊ አስተሳስብ መዳበር እንተጋለን !!!


📌Follow the Federalism Club's social media Address: -
● Telegram channel: @AAU_FC
● LinkedIn: http://linkedin.com/company/aau-federalism-club
✨️እንኳን ለትንሣኤ በዓል በሰላም በጤና አድረሳችሁ!✨️

May this special day be filled with peace, blessings, and reflection.

🥀Wishing you and your loved ones a joyful Easter 🥀