የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን Addis Ababa Housing Development Corporation
6.68K subscribers
14K photos
48 videos
8 files
885 links
Download Telegram
1447ኛው የዒድ አል-ፈጥር በዓል የዒድ ሰላት በከተማችን ሃይማኖታዊ ትውፊቱን ጠብቆ በታላቅ ድምቀት ተካሂዷል ።

መርሐ ግብሩ በስኬት እንዲከናወን ያደረጋችሁ የሃይማኖት አባቶችን፣ የፀጥታ አካላትን፣ ህዝበ ሙስሊሙንና አጠቃላይ የከተማችን ነዋሪዎችን በራሴና በከተማ አስተዳደሩ ስም ከልብ አመሰግናለሁ።

በድጋሚ ዒድ ሙባረክ!

ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ!

ከንቲባ አዳነች አቤቤ
8
1447ኛውን የኢድ አል-ፈጥር በዓል ምክንያት በማድረግ፣ በከተማችን በሁሉም ክፍለ ከተሞች በሚገኙ 28ቱም የተስፋ ብርሃን የምገባ ማዕከላት አቅመ ደካሞችን፣ አካል ጉዳተኞችን፣ አረጋውያንና ለከፋ ማህበራዊ ችግር ተጋላጭ ለሆኑ ወገኖቻችንን ማእድ የማቋደስ መርሃ ግብር ተከናውኗል።

እኔም በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ በሚገኘው 6ኛው እና በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ በሚገኘው 21ኛው የተስፋ ብርሃን የምገባ ማዕከላት በመገኛት ማዕድ በማቋደስ እንኳን አደረሳችሁ ብያለሁ።

ማዕከላቱ በዐቢይ ጾም እና በረመዳን ወቅትም ጭምር ለጾመኞች እንደየ እምነታቸዉ የአፍጥር እና የፆም ምገባ አገልግሎት ሲሰጡ ቆይተዋል።
ያደረግንላችሁን ጥሪ በመቀበል በማዕከላቱ እየመገባችሁ ለምትገኙ ባለሀብቶች፣ አጋሮች እና አስተባባሪዎች በተጠቃሚዎቹ ስም ከልብ የመነጨ ምስጋናዬን አቀርባለሁ።

በዓሉ የደስታና አብሮነት የሚጎለብትበት ይሁንልን!!
ዒድ ሙባረክ!

ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ!

ከንቲባ አዳነች አቤቤ