ለኢራን የጦር መሳሪያ ስታሻሽጥ የነበረችው ሴት በሎስ አንጀለስ አየር ማረፊያ በቁጥጥር ስር ዋለች
በኢራን የተወለደችውና የአሜሪካ ቋሚ ነዋሪ የሆነችው የ44 ዓመቷ ሻሚም ማፊ፣ ለቴህራን መንግስት የጦር መሳሪያ ድርድር ስታመቻች ነበር በሚል ክስ፣ በሎስ አንጀለስ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ተያዘች። ኒው ዮርክ ፖስት የካሊፎርኒያ አቃቤ ህግን ጠቅሶ እንደዘገበው፣ ግለሰቧ ድሮኖችን፣ ቦምቦችንና ጥይቶችን ለሱዳን መንግስት ለመሸጥ ስታደራድር ነበር። ማፊ በኦማን የተመዘገበ ድርጅትን በመጠቀም እስከ 2025 ድረስ ይህንኑ ህገ-ወጥ የንግድ እንቅስቃሴ ስታከናውን እንደነበረ በክሱ ተመልክቷል።
ከእነዚህ የጦር መሳሪያ ድርድሮች መካከል ከኢራን መከላከያ ሚኒስቴር የተገዙና "ሞሃጀር-6" የተሰኙ የታጠቁ ድሮኖችን ለሱዳን ለማቅረብ የተደረገው የ70 ሚሊዮን ዶላር ስምምነት ይገኝበታል። አቃቤ ህግ እንዳስታወቀው፣ የማፊ ስልክ ግንኙነቶች እንደሚያሳዩት ከታህሳስ 2022 እስከ ሰኔ 2025 ባለው ጊዜ ውስጥ ከኢራን የመረጃና ደህንነት ሚኒስቴር ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ነበራት። ይሁን እንጂ ተከሳሽዋ በበኩሏ፣ በዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ማንኛውንም አይነት ተልዕኮ ከኢራን መንግስት ተቀብላ እንደማታውቅ ለመርማሪዎች ተናግራለች።
የካሊፎርኒያ ማዕከላዊ ዲስትሪክት አቃቤ ህግ ቢል ኢሳሊ በኤክስ ገጹ ላይ እንደገለጸው፣ ማፊ የቀረበባት የወንጀል ክስ ከተረጋገጠባት እስከ 20 ዓመት የሚደርስ የፌዴራል እስራት ይጠብቃታል። "ማፊ በኢራን የተመረቱ ድሮኖችን፣ ቦምቦችንና በሚሊዮን የሚቆጠሩ ጥይቶችን ለሱዳን ለመሸጥ በማደራጀቷ በአሜሪካ ህግ ተጠያቂ ትሆናለች" ብሏል። ተከሳሽዋ ሰኞ ከሰዓት በኋላ በሎስ አንጀለስ በሚገኘው የዩኤስ ዲስትሪክት ፍርድ ቤት ለመጀመሪያ ጊዜ ትቀርባለች ተብሎ ይጠበቃል።
@Zena_maezen

❤13👍3😢2
❤5👍4
ፕሬዝዳንት ትራምፕ የባህር ላይ ከበባውን ጥሳ ለማለፍ የሞከረችውን የኢራን 'ቱስካ' (TOUSKA) የጭነት መርከብ አሜሪካ በቁጥጥር ስር ማዋሏን ገለጹ።
"መርከቧን ሙሉ በሙሉ ተቆጣጥረናል፣ በውስጧ ምን እንዳለ እያየን ነው።"
via:- brics news
@Zena_maezen
@Zena_maezen
"መርከቧን ሙሉ በሙሉ ተቆጣጥረናል፣ በውስጧ ምን እንዳለ እያየን ነው።"
via:- brics news
@Zena_maezen
@Zena_maezen
❤5👍4😁4
ኢራን በሀገሪቱ ውስጥ ጥቃት ለማድረስ አቅደዋል በሚል "የእስራኤል ሞሳድ ወኪሎች ናቸው" ብላ የከሰሰቻቸውን 2 ሰዎች በሞት ቀጣች።
@Zena_maezen
@Zena_maezen
@Zena_maezen
@Zena_maezen
❤7👍7
ህወሓት ምክር ቤቱን ዳግም ማቋቋሙን ገለጸ
በትግራይ ክልል ያለው የሥልጣን ፍትጊያ ወደ አዲስ ምዕራፍ ተሸጋግሯል። በዶ/ር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል የሚመራው ህወሓት፣ የፌዴራል መንግሥቱ የጊዜያዊ አስተዳደሩን የሥልጣን ዘመን ማራዘሙን በመቃወም፣ ከጦርነቱ በፊት የነበረውን የክልል ምክር ቤት (ባይቶ) ዳግም ማቋቋሙን በይፋ አውጇል።
በፌዴራል መንግሥቱና በክልሉ የሽግግር መዋቅር መካከል ከፍተኛ ውጥረት የፈጠረ ሲሆን፣ የፕሪቶሪያውን የሰላም ስምምነት አደጋ ላይ ሊጥል እንደሚችል ስጋት ተፈጥሯል።

❤4😁4👍3
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በዩክሬን የድሮን ጥቃት ምክንያት በሩሲያው ቱአፕሴ (Tuapse) የነዳጅ ማጣሪያ ፋብሪካ ላይ ከፍተኛ የእሳት አደጋ ተከሰተ።
@Zena_maezen
@Zena_maezen
@Zena_maezen
@Zena_maezen
❤3👍3
ዩናይትድ አረብ ኤሚሬትስ (UAE) ለጦርነት ጊዜ የሚሆን የፋይናንስ ድጋፍ እንዲደረግላት አሜሪካን ጠየቀች ሲል WSJ ዘገበ።
"ከኢራን ጋር እየተካሄደ ያለው ጦርነት በነዳጅ የበለጸገችውን የፋርስ ባህረ ሰላጤ አገር ወደ የከፋ ቀውስ ውስጥ ከከተታት በሚል፣ ዩናይትድ አረብ ኤሚሬትስ የፋይናንስ ዋስትና (backstop) ለማግኘት ከአሜሪካ ጋር ንግግር ጀምራለች።"
@Zena_Maezen

❤6😁3
16 የእስራኤል ወታደሮች ሲገደሉ፣ 690 ቆስለዋል: - የእስራኤል ጦር
ከየካቲት 21 ጀምሮ ከኢራንና ከሊባኖስ ጋር በተያያዙ ጥቃቶች 16 የእስራኤል ወታደሮች ሲገደሉ፣ 690 ያህሉ ደግሞ መቁሰላቸውን የጦር ሰራዊቱ መረጃ አመልክቷል። ካለፉት 24 ሰዓታት ወዲህ ብቻ 37 ወታደሮች በአብዛኛው "በፈንጂ መሳሪያዎች" ምክንያት መቁሰላቸው የተገለጸ ሲሆን፣ እስራኤል በጥቃቶቹ የሚደርሰውን ጉዳት በሚመለከት ጥብቅ የመረጃ ቁጥጥር ስታደርግ ቆይታለች። በአሁኑ ወቅት 149 ወታደሮች በሆስፒታል ውስጥ በህክምና ላይ እንደሚገኙ ተነግሯል።
በደቡብ ሊባኖስ "ቢጫ መስመር" ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በፈንጂ መሳሪያዎች በተከሰቱ ሁለት የተለያዩ አደጋዎች ሁለት የእስራኤል ወታደሮች መገደላቸውንና 12ቱ መቁሰላቸውን ማዕሪቭ ጋዜጣ ዘግቧል። ይህ "ቢጫ መስመር" በሊባኖስ ግዛት ውስጥ ከ4 እስከ 10 ኪሎ ሜትር ዘልቆ የሚገባ መደበኛ ያልሆነ ድንበር ሲሆን፣ በሊባኖስ የሚቀበሩ ፈንጂዎች እ.ኤ.አ. በ1980ዎቹ እና 90ዎቹ የእስራኤል ጦር በሊባኖስ በነበረበት ወቅት ለወታደሮቹ ትልቅ "ቅዠት" እንደነበሩ ጋዜጣው አስታውሷል።
አሁን ያለው ግጭት ተባብሶ የቀጠለው ከአሜሪካና እስራኤል ጥምር ወታደራዊ ዘመቻ በኋላ ሲሆን፣ ኢራን እና ሄዝቦላህ ሚሳይሎችንና ድሮኖችን በመጠቀም የእስራኤልን ይዞታዎች እንዲሁም በአካባቢው የሚገኙ የአሜሪካ የጦር ሰፈሮችን ኢላማ በማድረግ ምላሽ ሰጥተዋል። ምንም እንኳን በዋሽንግተን እና በቴህራን መካከል ከሚያዝያ 1 ጀምሮ ለሁለት ሳምንታት የሚቆይ የተኩስ አቁም ስምምነት ቢደረግም፣ ጦርነቱን በዘላቂነት ለማቆም እስካሁን የመጨረሻ ስምምነት ላይ አልተደረሰም።

❤6
ዜና ማዕዘን - Breaking
ፕሬዝዳንት ትራምፕ የባህር ላይ ከበባውን ጥሳ ለማለፍ የሞከረችውን የኢራን 'ቱስካ' (TOUSKA) የጭነት መርከብ አሜሪካ በቁጥጥር ስር ማዋሏን ገለጹ። "መርከቧን ሙሉ በሙሉ ተቆጣጥረናል፣ በውስጧ ምን እንዳለ እያየን ነው።" via:- brics news @Zena_maezen @Zena_maezen
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የአሜሪካ የባህር ሃይል ኮማንዶዎች (Marines) የኢራንን ቱስካ (Touska) የተሰኘች የጭነት መርከብ በቁጥጥር ስር ሲያውሉ የሚያሳይ ቪዲዮ ይፋ ሆኗል።
@Zena_maezen
@Zena_maezen
@Zena_maezen
@Zena_maezen
😢6👍4😁3💔2
በጃፓን በሬክተር ስኬል 7.4 የተለካ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከሰተ
አስር ኪሎሜትር ጥልቀት መፍጠሩን የጃፓን አየር ንብረት ኤጀንሲ አስታውቋል።
በአደጋው የደረሰው የጉዳት መጠን እስካሁን ማወቅ አለመቻሉ ተገልጿል።
አደጋው የተከሰተው ከዋና ከተማዋ ቶኪዮ በመቶ ኪሎሜትር ርቃ በምትገኘው የሰሜን የኢዋቴ ግዛት ነው።
የአካባቢው ነዋሪዎችን የማስወጣት ስራ እየተሰራ እንደሚገኝ ጠቅላይ ሚኒስትር ሳናዔ ታካቺ ተናግረዋል።
በአንፃሩ ከፍተኛ ሱናሚ በተቀሰቀሰባቸው አካባቢዎች አደጋው እስኪቆም ድረስ ባሉበት እንዲቆዩ ኤጀንሲው ጥሪ አቅርቧል።
በጃፓን በ2011 ከተከሰተው እና ከ18,000 በላይ ሰዎችን ህይወት ከቀጠፈው የ9.0 የተለካ የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ በኋላ ከባድ አደጋ ሲከሰት የአሁኑ የመጀመሪያ ሆኗል።

👍3😢2❤1
ደቡብ ኮሪያ፦ አብዛኞቹ ዜጎች ከቤታቸው ውጭ መሞት እንደማይፈልጉ ተገለጸ
የደቡብ ኮሪያ ፖሊስ ባደረገው ጥናት አብዛኞቹ የሀገሪቱ ዜጎች ከቤታቸው ውጭ መሞት እንደማይፈልጉ አረጋግጧል። በጥናቱ መሠረት 67.5% የሚሆኑት ዜጎች በቤታቸው ውስጥ መሞትን ሲመርጡ፣ 8.3% የሚሆኑት ደግሞ በሆስፒታል ውስጥ የመሞት ፍላጎት እንዳላቸው ተገልጿል።
የነገሩ መነሻ በሆስፒታል የሚሰጥ የህክምና አገልግሎት ላይ የሚፈጠሩ ስህተቶች በዜጎች ላይ ጥርጣሬ መፍጠሩ እንደሆነ ተጠቁሟል። ይህን ተከትሎ ፖሊስ በየቤቱ ምርመራ ያደረገ ሲሆን፣ የዜጎቹን በቤት ውስጥና በሆስፒታል የመሞት ፍላጎት ከላይ በተጠቀሰው መልኩ መሆኑን አረጋግጧል። እንደ መረጃው ከሆነ፣ በሆስፒታል የታገዘ ሞትን የመረጡት እድሚያቸው የገፉ ሰዎች ናቸው።
የደቡብ ኮሪያ መንግስት ይህንን የዜጎች ምርጫ ከግምት በማስገባት በ2025 "የህይወት ፍፃሜ እንክብካቤ" የተሰኘ የጤና ስርዓት ማሻሻያ ፖሊሲ ይፋ ማድረጉ ይታወሳል።

❤8
የኮንጎ ሪፐብሊክ ጠቅላይ ሚኒስትር እና የካቢኔ አባላት የሥልጣን መልቀቂያ አቀረቡ
በኮንጎ ሪፐብሊክ (ኮንጎ-ብራዛቪል) ጠቅላይ ሚኒስትር አናቶል ኮሊኔት ማኮሶ እና የካቢኔ አባሎቻቸው በዛሬው ዕለት የሥልጣን መልቀቂያቸውን ለፕሬዝዳንት ዴኒ ሳሱ ንጌሶ አቅርበዋል።
ይህ የሥልጣን መልቀቂያ የቀረበው ፕሬዝዳንት ሳሱ ንጌሶ በመጋቢት 15 ቀን 2026 በተካሄደው ምርጫ ከ94 በመቶ በላይ ድምፅ አግኝተው ካሸነፉ በኋላ፣ ለ5ኛ የሥልጣን ዘመን በቅርቡ ቃለ መሐላ መፈጸማቸውን ተከትሎ ነው።
በሀገሪቱ የፖለቲካ ሥርዓት መሠረት ፕሬዝዳንቱ አዲስ መንግሥት እንዲያዋቅሩ ዕድል ለመስጠት የቀድሞው ካቢኔ መልቀቁ የተለመደ አሠራር ሲሆን፣ አዲስ ካቢኔ እስከሚሰየም ድረስም የወጡት ሚኒስትሮች የዕለት ተዕለት የመንግሥት ሥራዎችን ማከናወናቸውን ይቀጥላሉ።

❤9
አሜሪካ የኢራንን መርከብ መጥለፏን ተከትሎ ቴህራን የድሮን ጥቃት ሰነዘረች
በአሜሪካና በኢራን መካከል ያለው ውጥረት ወደ አደገኛ ደረጃ ተሸጋግሯል። ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ "ቱስካ" የተሰኘውና የኢራን ባንዲራ የሚያውለበልበው ግዙፍ የጭነት መርከብ የአሜሪካን የባሕር እግድ ጥሶ ለመጓዝ በመሞከሩ በአሜሪካ ባሕር ኃይል ቁጥጥር ስር መዋሉን አስታውቀዋል። ትራምፕ በሰጡት መግለጫ፤ መርከቡ ማስጠንቀቂያ ባለማክበሩ ኢንጅን ክፍሉ ላይ ተመትቶ እንዲቆም መደረጉንና በአሁኑ ወቅት በአሜሪካ ሙሉ ቁጥጥር ስር እንደሚገኝ ገልጸዋል።
ይህንን እርምጃ ተከትሎ ኢራን "በትጥቅ የታገዘ የባሕር ላይ ውንብድና" ስትል ድርጊቱን ያወገዘች ሲሆን፣ ወዲያውኑ የአጸፋ እርምጃ መውሰድ ጀምራለች። ከእስላማዊ አብዮታዊ ዘብ ጋር ግንኙነት ያለው ታስኒም የዜና ወኪል እንደዘገበው፤ ቴህራን በኦማን ባሕረ ሰላጤ ላይ በሚገኙ የአሜሪካ ጦር መርከቦች ላይ የድሮን ጥቃቶችን ፈጽማለች። የኢራን ጦር ማዘዣ ጣቢያ አሜሪካ የተኩስ አቁም ስምምነቱን ጥሳለች ሲል የከሰሰ ሲሆን፣ ጥቃቱ የዚህ ድርጊት ቀጥተኛ ምላሽ መሆኑን አስታውቋል።
ይህ ግጭት የተከሰተው ምክትል ፕሬዝዳንት ጄዲ ቫንስ ጦርነቱን ለመቋጨት ፓኪስታን ውስጥ በሚደረገው ድርድር ላይ የአሜሪካን ልዑክ እንደሚመሩ ዋይት ሀውስ ባረጋገጠበት ወቅት ነው። ይሁን እንጂ ኢራን በማዕቀብና በእገዳ ሁኔታ ውስጥ ድርድር ውስጥ እንደማትሳተፍ እየገለጸች ትገኛለች። በአሁኑ ወቅት በአሜሪካ የጦር መርከቦች ላይ ተፈጸመ በተባለው ጥቃት የደረሰው ጉዳት በዝርዝር ባይታወቅም፣ ሁኔታው ቀጣናውን ወደ ከፋ የጦርነት ቀውስ ሊከተው እንደሚችል ተሰግቷል።

ኳታር ዓለምአቀፍ የበረራ አገልግሎት ጀመረች
ኳታር የበረራ አገልግሎት የጀመረው ወቅታዊ የደህንነት ግምገማ ከተደረገ በኋላ ሲቪል አቬሽኗ አስታውቋል።
የሀገሪቱ አቬሽን ዝግጅት እና ስራ የመጀመር አቅም ላይ ውይይት ከተደረገ በኋላ በከፊል ሲተገበሩ የነበሩ በረራዎች ሙሉ በሙሉ እንዲጀምሩ ወስኗል ተብሏል።
ውሳኔው በጦርነቱ ምክንያት ተቀዛቅዞ ለቆየው የኳታር አቬሽን እና ቱሪዝም ዘርፍ መነቃቃትን እንደሚፈጥር ተስፋ ተደርጓል።
እስራኤል እና አሜሪካ ኢራን ላይ ጥቃት ማድረሳቸውን ተከትሎ የገልፍ ሀገራት የሀገር ውስጥ እና አለማቀፍ በረራዎችን ለመቆም ተገደዋል።
በጦርነቱ ምክንያት በረራዎችን አግዳ የነበረችው ኳታር፣ አሜሪካ እና እስራኤል ለ15 ቀን የሚቆይ የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ መፈጸማቸውን ተከትሎ ነው የአየር ክልሏን ለበረራ ክፍት ያደረገችው።