Zemedkun Bekele (ዘመዴ)
269K subscribers
22.3K photos
3.47K videos
10 files
1.42K links
"ይህ የቴሌግራም ቻናሌ ግንቦት1/2011ዓም የተከፈተ ነው። የእኔን የስልክ ወጪ ጨምሮ አገልግሎቴን መደገፍ የምትፈቅዱ ጓደኞቼ በ
👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia እና
👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል ማገዝ ትችላላችሁ። በተረፈ ለቤተ ክርስቲያኔና ለኢትዮጵያ ሀገሬ የሚጠቅመውን ሁሉ አበረክት ዘንድ አብዝታችሁ ጸልዩልኝ።
Download Telegram
ወግተዋል። አሁንም ድረስ ሁለት የሰንበት ተማሪዎች ታስረዋል። ማኅበሩ በአስቸኳይ ከዐቢይ ጋሻ ጃግሬ ከቤተ መንግሥቱ የእልፍኝ አስከልካይ ከአሽከር ዳንኤል ክብረት ጋር ተነጋግረው። ዳንኤልም ከጓደኞቹ ከእነ ዐቢይና ከኦሮሚያ ፕሬዘዳንት ከአቶ ሽመልስ አብዲሳ ጋር ተነጋግሮ ያስፈታቸው ብዬ እጠይቃለሁ። ፈሪዎች አፈር ደቼ ብሉና እናንተ በመግለጫ አምልጣችሁ የደሃ ልጅ ስታስደበድቡ ትኖራላችሁ። አይደረግም፣ አይሆንምም። እኔም አልፋታችሁም። በተለይ ብርሃኑ አድማስን የመሰለ ጀዝባ ህዝቡን በይፋ ይቅርታ እስኪጠይቅ ድረስ አልፋታቸውም። ነውረኞች።

•••
እነ ባህሩንና እነ ፈቃዱ ደንገሎጥን እንኳን እርሷቸው። ቂምም አትያዙባቸው። ዝርክርክ ሁላ ራሱን የማይመራ ሰልፍ ልምራ ሲል ነው ነገሩ ያከተመለት።

•••
ምስጋና ፦ እስከ መጨረሻው ድረስ ለተሟገታችሁ የቴዮሎጂ ኅብረት ሊቀ መንበር ቀሲስ ምትኩ፣ የአዲስ አበባ የጥምቀት ተመለሾች መሪ እነ ፌቨን፣ የማኅበረ ፋኑኤሉ ሱራፌል። ብድራቱን መድኃኔዓለም ይክፈላችሁ። ልዩነታችሁን አስመዝግባችሁ የወጣችሁ በሙሉ አሸናፊዎች ናችሁ።

#ማስታወሻ_ማሳሰቢያም
•••
ለነገ መስከረም 4/2012 ዓም ማኅበረ ቅዱሳንን አምናችሁ ሰልፍ የጠራችሁ በተለይ በዐማራ ክልል የምትገኙ የሰልፍ አስተባባሪዎች በመድኃኔዓለም ይሁንባችሁ ሰልፋችሁን ሰርዙ። ለጽንፈኛ ፖለቲከኞች የፖለቲካ ግብአት የሚሆን የማዳበሪያ ሃሳብ አታመንጩ። አውቃለሁ፣ ደፋሮች ናችሁ፣ ሞትን የማትፈሩ ሰማዕታት የሰማዕታት ልጆች ናችሁ። እባካችሁ ማኅበረ ቅዱሳን አንዴ አስበልቶናል። እናም ጉዳዩ ከዐማራ ጋር ብቻ እንዳይያያዝ ልለምናችሁ። ሰልፉን ተዉት። ወደ ቅዳሴ ሂዱ። እዚያም ዘምራችሁ፣ ምህላ አድርጋችሁ፣ ንስሃም ገብታችሁ ተለያዩ። በእመ አምላክ፣ በወላዲተ አምላክ ብዬ ልለምናችሁ። ከታላቅ አክብሮት ጋር።

•••

ሻሎም ! ሰላም !

ዘመድኩን በቀለ ነኝ።
መስከረም 3/2012 ዓም
ከራየን ወንዝ ማዶ።
ይሄም አንደኛው ስጋቴ ነው።
*★★★*

• በተለይ ዐማሮች ይህችን የእኔንና የታደለ ጥበቡን ምክር ስሙ። ግድየላችሁም ስሙ። አልረፈደም፣ እልኸኞች አትሁኑ።

#ETHIOPIA | ~ የተዋሕዶ ልጆች ተጠንቀቁ። ድጋሚ እንዳትሸወዱ።

•••
ፊት አውራሪ ማኅበረ ቅዱሳን የመስከረም 4ቱ ሰልፍ ወደ ጥቅምት 30 አዞረዋለሁ ማለቱ ይታወሳል። ለዚህም ደግሞ እነ ራዲዮ ፋና በደንብ እየዘገቡለትም ነው። ይሄን ይሄን በደንብ መጠርጠር ነው። ወዳጄ ከእንግዲህ ማኅበረ ቅዱሳንን አምናችሁ ለጥቅምት 30 ሰልፍ አለ ብላችሁ አደባባይለመውጣት እንዳትሞክሩ።

•••
ልብ በሉ ህዳር 3 የሲዳማ ህዝብ ሪፈረንደም እንዲያደርግ እነ ራዲዮ ፋና ቀጠሮ የያዙበት ዕለት ነው። ጥቅምት 30 ደግሞ መልስ ካልተሰጠን ሰላማዊ ሰልፍ እንወጣለን ብለው የማህበረ ቅዱሳኖቹ እነ ፋንታሁን ዋቄ ቀጠሮ የስያዙበት ዕለት ነው። እነ ብርሃኑ አድማስ ደግሞ ሰልፉ እንዲደረግ የሚወተውቱት የቲሸርት ነጋዴዎች ናቸው ብለው በአደባባይ ህዝብን በግልጽ እየሰደቡ ያለበት ሁኔታ ነው ያለው።

•••
እንደኔ እንደእኔ ማኅበሩ ወይ ተጠልፏል። ወይ ሆን ብሎ ክፍት አፎች አፋቸውን እንዲከፍቱ ፈቅዷል። እግረ መንገዳቸውንም ቤተ ክርስቲያንን ሊያስፈጇት ካልሆነ በቀር የጥቅምት 30ውም ሰልፍ ይለፋችሁ።

•••
ፈሪና ራስወዳድ ነጋዴ አይደለም ሰልፍ ቤቱን መምራት እንኳ አይሆንለትም እኮ። ማኅበረ ቅዱሳን በትልቁ ማኖ ነክቷል። ፋውል ሠርቷል። ቤተ ክርስቲያንን የአህዛብ መሳቂያ መሳለቂያ አድርጓል። በታሪክ ይቅር የማይባል ስህተት ሠርቷል። አንገታችንን አስደፍቷል። እንደ ብርሃኑ አድማስ ዓይነት ጎጤ ጎጠኛ የማኅበሩ አፈጉባኤ ዓይነቱ ደፋር ወፍራም ወራዳ ህዝብን በአደባባይ ይቅርታ ሳይጠይቅ መላቀቅ የለም። እኔ በበኩሌ አልፋታችሁም።

•••
ያዘናችሁ፣ ዘመዴ ችግሩ አደባባይ አይውጣ በውስጥ ተነጋገሩ የምትሉ ሁላ በጓዳ ንግግር ብሎ ነገር የለም። ቅዱሳን ፓትሪያርኮቻችን ላይ አፌን ስከፍት፣ በዘርም በሌብነትም የሳቱትን በአደባባይ ስንወቅስ ለራስህ ጥቅም አፍህን ለጉመህ የነበርክ ሁላ ዛሬ ማኅበሩ ፋውል ሰርቶ ቢጫ ካርድ ሊሰጠው ሲል የምን ማለቃቀስ ነው?

•••

እኔጋ እገሌ ወእገሌ ብሎ ነገር የለም። ባንዳው የድል አጥቢያ አርበኛው ብርሃኑ አድማስን የመሰለ ጎጠኛ በአደባባይ ይቅርታ እስኪጠይቅ ሙግቴን እቀጥላለሁ። ከኑመ ጋ ዱቢን። ሃላስ፣ አከተመ።

•••
★ አንት ድንባዣም አዋራጅ ማኅበር ሆይ አንተን አምነው ሰልፍ እንወጣለን ብለው በጅማ የታሰሩትን ሁለቱን ብርቅዬ የሰንበት ትምህርት ቤት ተማሪዎች እንዲፈቱ አድርግ። ለጨካኝ አክራሪ እስላም ከንቲባና ፖሊስ አዛዥ አሳልፈህ ሰጥተህ ትተኛለህ እንዴ? ሆዳም ሁላ። የታሰሩት በአስቸኳይ ይፈቱ።

•••
#ማስታወሻ_ማሳሰቢያም
•••
ለነገ መስከረም 4/2012 ዓም ማኅበረ ቅዱሳንን አምናችሁ ሰልፍ የጠራችሁ በተለይ በዐማራ ክልል የምትገኙ የሰልፍ አስተባባሪዎች በመድኃኔዓለም ይሁንባችሁ ሰልፋችሁን ሰርዙ። ደግሜ ደጋግሜ ተማጽኜያችኋለሁ። ለጽንፈኛ ፖለቲከኞች የፖለቲካ ግብአት የሚሆን የማዳበሪያ ሃሳብ አታመንጩ። አውቃለሁ፣ ደፋሮች ናችሁ፣ ሞትን የማትፈሩ ሰማዕታት የሰማዕታት ልጆች ናችሁ። እባካችሁ ማኅበረ ቅዱሳን አንዴ አስበልቶናል። እናም ጉዳዩ ከዐማራ ጋር ብቻ እንዳይያያዝ ልለምናችሁ። ሰልፉን ተዉት። ወደ ቅዳሴ ሂዱ። እዚያም ዘምራችሁ፣ ምህላ አድርጋችሁ፣ ንስሃም ገብታችሁ ተለያዩ። በእመ አምላክ፣ በወላዲተ አምላክ ብዬ ልለምናችሁ። ከታላቅ አክብሮት ጋር። እኔን ካላመናችሁ ወንድማችሁ ታደለ ጥበቡን ስሙት።

•••
ታደለ ጥበቡ:
*በፍጥነት መስተካከል ያለባቸው 2 ጉዳዮች፦

1.በአማራ ክልል ብቻ ተነጥሎ እንዲካሄድ የተፈለገው ሃይማኖታዊ ሰልፍ ሁለት conspiracy (ሴራ) አለበት።

ሀ~ጥያቄውን የአማራ ሕዝብ ብቻ ነው ያነሳው በሚል የአማራን ፖለቲካ ከሃይማኖት ጋር ለማቡካት፥ለመጋገር የቋመጡ "መንጋዎች" ቀዳዳ መስጠት በመሆኑ በፍጹም መካሄድ የለበትም።ሰልፉን አካሄዳለሁ የሚል ኮሚቴ ካለ አርፈህ ቁጭ በል በሉት።

ሁ~የአደባባዩን ሰልፍ እንዳጋጣሚ በመጠቀም በሌላው ሃይማኖት አባሎች ላይ አላስፈላጊ ትንኮሳ በማድረግ ወደ ግጭት እንዲያመራ የሚፈልጉ አካላት ስለሚኖሩ አሁንም በፍጹም አማራ ክልል ላይ ሰልፉ መደረግ የለበትም።

ይልቁንስ ነገ ጧት ሁሉም ቤተ ክርስቲያን ተገኝቶ ፀሎት ያድርግ።ቆሞ ያስቀድስ።ሲመለስ በዝማሬ ወደየቤቱ ይመለስ።

2.ሰሞኑን ጃዋር ኦዲፒን "ነፍጠኛ" በቀለ ገርባ "ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይውረድ" የሚለው ፕሮፖጋንዳ አብይ አህመድ በአማራ ክልል ያጣውን ተቀባይነት እነርሱ የገፉት በማስመሰል ከአማራ ሕዝብ ድጋፍ እንዲያገኝ የተሸረበች ዘዴ ናት።ጃዋር፣በቀለ ሆነ ግርማ ጉተማ አብይ አህመድ ድጋፍ ለመሸመት ወሬ እንዲነዙ ያሰማራቸው መንጋዎች መሆናቸውን እወቁባቸው።

*በተረፈ መስከረም 30 ቀን ነው ፌስቡክ አካውቴን የሚለቀው ያኔ በሚገባ እናወጋለን።በድጋሜ መልካም በዓል። ብሏችኋል እንደ እኔው ፌስ ቡክ ፔጁን የጠረቀመበት ወንድማችን ታደለ ጥበቡ። እናም ሳትንቁን ስሙን።

•••

ሻሎም ! ሰላም !

ዘመድኩን በቀለ ነኝ።
መስከረም 3/2012 ዓም
ከራየን ወንዝ ማዶ።
እንኳን ደስስስ አለን !!
*~★★~*

• ይሄ ዜና ለኢትዮጵያ ትንሣኤ ምልክቱ ነው።

#ETHIOPIA |~ ቀጣዩን መከራ ካሳጠረልን የኢትዮጵያ ትንሣኤ ቅርብ ይሆናል ብለን እናምናለን። እልልልልልልልልል እሰይ እሰይ እሰይ። ደስስስ ሲል በአዛኚቷ።

… በመጨረሻም ለ30 ዓመታት ያህል በህወሓት ኮሚኒስታዊ አስተዳደር ቁጥጥር ስር ወድቆ በካድሬዎቿም ፍዳ መከራውን ይበላ የነበረው ታላቁ የዋልድባ አብረንታንት ገዳም በዐማራ ፋኖና በዐማራ ልዩ ኃይል ተጋድሎ ከአራጇ ህወሓትና ከአረመኔ ካድሬዎቿ ነፃ ወጥቷል። ይሄንንም ደውዬ እነ አባን በስልክ አነጋግሬ አረጋግጫለሁ። እግዚአብሔር ይመስገን።

… የሕወሓት አሽከሮች እና ካድሬዎች ገና አባ ገብረ ኢየሱስ አዲአርቃይ መጥተዋል ሲባሉ ነው ጥርግርግ በለው ከዋልድባ ገዳም ወጥተው ወደ ማይጸምሪ የፈረጠጡት ተብሏል። አሁን በዋልድባ ምድር ላይ እየተንቀሳቀሰ ያለው የዐማራ ፋኖ ብቻ ነው። ባለማዕተቡ ፋኖ።

… ማሀርገጽ ቅዱስ ጊዮርጊስ፣ ዕጣኑ ማርያም፣ ደለሳቆቃ አቡነ አረጋዊ፣ ቤትሙሉ ቅዱስ ሚካኤል(ማይጋባ)፣ እባነጻ፣ በሙሉ ከህወሓት ከትግራይ ነፃ አውጪ ወንበዴ ቡድን ነፃ ወጥተዋል። ግድቡ አካባቢ ደግሞ የዐማራ ልዩ ኃይል እና የዐማራ ፋኖ ተቆጣጥረውታል። በአጠቃላይ የዋልድባ ገዳምን ከሕወሓት እጅ አስለቅቆ የዐማራ ልዩ ኃይልና ፋኖ ተቆጣጥሮታል። የአባቶቻችን አምላክ እግዚአብሔር ይመስገን።

… በዋልድባ ጉዳይ የአንበሳውን ድርሻ የሚወስዱት አንድ አባት ግን አሉ። ለእኔ ለዘመዴ አባቴ፣ ወንድሜም፣ ደግሞም ጓደኛዬ፣ የልጆቼም የቤተሰቤም ጠያቂ አባ ገብረኢየሱስ ወልደ ሰሙኤል። አዎ አባ ገብረ ኢየሱስ በዚህ ዘመን ዋልድባ ሲነሣ አብረው ይነሣሉ። ይወሳሉ። ይዘከራሉ።

… እነ አባ ገብረ ኢየሱስ በዋልድባ ምክንያት ተሰድደዋል። ታስረዋል። ተገርፈዋል፣ ተዋርደዋል፣ ተሰድበዋል። መሬት ለመሬት ተጎትተው በህወሓት ቅልብ ወታደሮች ተወቅጠዋል። ውኃ እንዳይነካቸው፣ ልብሳቸውን እንዳይቀይሩ ተደርገው በብዙ ተቀጥተዋል። በሰንሰለት ተጠፍረው እንደ ሌባ እንደ ወንበዴ ተጎሳቅለዋል። በመጨረሻ ግን አሳሪዎቻቸው ወድመው እነሱ ነፃ ወጥተዋል።

… ዋልድባ አይደፈር ባሉ፣ አይታረስም ባሉ፣ አይርከስ አይቃጠል፣ አይውደምም ባሉ ነው መከረ ፍዳቸውን ያዩት። ዋልድባን የደፈረው መለስ ተቀስፏል፣ ምላሽ አልሰጥ ያሉት ሁሉ ተቀስፈዋል። ኢህአዴግም ህወሓትም ዕድል ፈንታዋ፣ ፅዋዕ ተርታዋ የተቆረጠው ዋልድባን በተዳፈረች ጊዜ ነበር። ህወሓትም በዕድሩ ድክመት እንጂ የሞተችው ዋልድባን የደፈረች ጊዜ ነበር፣ ቀባሪ አጥታ ነበር ስትንከላወስ የከረመችው።

... በዚህ ጉዳይ ላይ፣ በዋልድባ ጉዳይ ላይ፣ በዋልድባ ገዳም ዙሪያ በሰነድ የተደገፈ እና በመረጃም በማስረጃም የታጨቀ መጽሐፍ አባ ገብረ ኢየሱስ አዘጋጅተውም አቅርበውልናል። ስለ ዋልድባ ይዞታና ታሪክ ማወቅ የሚፈልግ ሰው በሙሉ ይህን መጽሐፍ ገዝቶ በቤቱ ማስቀመጥ ግድ ይለዋል። አጠቃላይ የዋልድባ ስቃይና መከራ የተመዘገበበት መጽሐፍም ነው።

… የመጽሐፉ ዋና አከፋፋይ ፍሬው መጻሕት መደብር 4ኪሎ አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ህንጻስር ሲሆን መጽሐፋ በሌሎች መጻሕፍት መደብሮችም ይገኛል። ሜክሲኮ ጃፋር መጽሐፍ መደብር፣ ናዝሬት መናኸሪያ ጀርባ፣ አርባምንጭ፣ ባህርዳር ቀበሌ 6 ካሰች መጽሐፍ መደብር፣ ጎንደር አራዳ ዮሐንስ ቤተ ክርስቲያን ጎን ካሰች መጽሐፍ መደብር፣ ፒያሳ ኢትዮጵያ ሆቴል ፊት ለፊትም ይገኛል። ገዝታችሁ አንብቡት። ለታሪክም አስቀምጡት።

... ሰሞኑን ከዚያው ከዋልድባ በመረጃ ቲቪ በኩል ዝግጅት ይኖረኛል። እነ አባንም አስገብቼ የምሥራቹን አሰማችኋለሁ። ቪድዮም ይኖረኛል።

#ማስታወሻ | ማሳሰቢያም | ማስጠንቀቂያም የዐማራን ፋኖ ድንቅ ተጋድሎ ለማራከስ ፌስቡክ ላይ ክላሽ ይዘህ የምትደነሰር አጭበርባሪና ዘራፊ ሌባ የከተማ ወንበዴዎች ከድርጊታችሁ ብትታቀቡ መልካም ነው። ግርግር ለሌባ ያመቻል የሚለውን አባባል ተጠቅማችሁ፣ በዳንሻና በሁመራ አካባቢ ውርውር የምትሉ ዘራፊ የከተማ ወፈፌዎች ተጠንቀቁ። ጀግና በግንባር ይዋደቃል። አንተ ፌስቡክ ላይ አስፋልት ላይ ቆመህ ክላሽ ይዘህ ፎቶ ተነሥተህ በመለጠፍ ትቀፍላለህ፣ ትዘርፋለህ። ማፈሪያዎች ተጠንቀቁ። በዐማራ ልዩ ኃይልና በዐማራ ፋኖ ደም ላይ መቀለድ ነውርም፣ ኃጢአትም፣ ወንጀልም ነው። የፌስቡክ ላይ አርበኞች ተጠንቀቁ።

… በተለይ ሽሬ፣ ሽራሮ ተቀጥረው ሲሠሩ የነበሩ፣ በሁመራና ዳንሻ የግለሰብና የመንግሥት መኪኖችን እየሰረቁ ወደ አዲስ አበባ እየሾለኩ ነውና በዚህ በኩል ክትትል እንዲደረግ ለመንግሥት አካላትም እንዲደርስ ይደረግ ዘንድ የፋኖ አመራሮች አሳስበዋል። እኛ እንዋደቃለን ሌላው ወንበዴ ይዘርፋል። ይሄ ልክ አይደለም። የአንድም ሰው ንብረት በዱርዬና በአስመሳይ የፌስቡክ ላይ የፎቶ ጀግና መዘረፍ የለበትምም ብለዋል። ብራቮ ፋኖ። እምቢ ካለ እራሱን ይሄን አስመሳይ ዠልጠህ ወደ ከተማ ላከው። ሌባን፣ የንፁሐን ሃብት ዘራፊውን ልክ እንደ ህወሓት ተዋጊ ቆጥረህ ጠብሰህ አሳርፈው። የፋኖ ስም በዚህ የከተማ አውደልዳይ ሌባ ምክንያት መጥፋት የለበትም። ፋኖ ሰምተሃል። ሌባ ዘራፊውም ሰምተሃል። እኔም ተናግሬአለሁ። መንግሥትም ህዝብም ሁላቸውም ሰምተዋል።

• አንተም አንቺም ሰምታችኋል። የአሐዱ ባንክን ከፍተኛውን ቦንድ የገዛችሁት አሐዱ ፒኤልሲ፣ አቶ ወርቁ አይተነው፣ ማኅበረ ቅዱሳኖችም ሰምታችኋል። ባለ አልሙኒየም ቤቱም ሶዬ ሰምተሃል። ይሄ አሐዱ ባንክማ ነገር ገና ብዙ ጉድ ነው የሚያሳየን።

… በማኅበረ ቅዱሳን ካባ የተጠቀለለው የአሐዱ ባንክ ጁንታ ቡድንም በመጨረሻ ከፍተኛውን ሼር የገዙትን ግለሰቦችና ድርጅቶች ስም ዝርዝር የያዘውን ሰነድ ለቦርዱ ኦዲተርና ለዋና ጸሐፊው መስጠት ቢከለክልም። ፓስወርዱ ጠፍቶብኛል ቢልም። እኔ ዘመዴ ግን እንደምንም ብዬ ሙሉ በሙሉ አክስዮን የገዙትን ግለሰቦችና ድርጅቶች ስምዝርዝር የያዘው ፋይል እጄ አስገብቸዋለሁ። ባለአክስዮኖቹ የተዘረፈ ብር ሕጋዊ ለማድረግ አምጥተው እዚህ ጎስጉሰውት ይሁን አይሁን እሱ መንግሥት የሚያጣራው ይሆናል። እኔ ግን የእያንዳንዳቸውን የአክስዮን የግዢ መጠን እለጥፈዋለሁ። የሁሉንም እለጥፈዋለሁ። አከተመ። ጧ በል።

•••

ሻሎም ! ሰላም !

ዘመድኩን በቀለ ነኝ።
ህዳር 12/32013 ዓም
ከራየን ወንዝ ማዶ።