Zedo News
2.48K subscribers
5.96K photos
263 videos
4 files
181 links
🚨 Breaking News Daily
🇪🇹 Ethiopia | 🌍 Global
Facts First. Always.
Download Telegram
24 ቢሊዮን ዶላር‼️
እስካሁን ከህወሃት የተያዘው የጦር መሳሪያ መጠን 24 ቢሊዮን ዶላር እንደሆነ የአሜሪካ እና የአውሮፓ ወታደራዊ አባሪ ዛሬ በተደረገ ጉብኝት ላይ ተናግረዋል።

⚠️ የተያዙ መሳሪያዎች
📍ሞሃጀር ድሮኖች፣ የካሚካዜ ድሮኖች፣ የድሮን ተተኳሽ
📍ረጅም እና አጭር ርቀት ሚሳኤሎች
📍ትላልቅ እና መካከለኛ መድፍ እና ተተኳሾች
📍ሞርታሮች፣ ፀረ-ታንክ፣ኮርኔት ሚሳኤሎች
📍ጠመንጃዎች፣ የእጅ ቦምቦች፣ ስናይፐር፣ፀረ ተሽከርካሪ ፈንጂዎች...ይገኙበታል።
አዩዘሀበሻ
👍2😁1
ትግራይ ባለአደራ ምክር ቤት ተቋቋመላት‼️
ፌደራል መንግሥት የትግራይ ክልል ባለአደራ ምክር ቤት መቋቋሙን ጠቅላይ ሚኒስቴር ጽ/ቤት አስታውቋል፡፡
👉ህወሃት ለአራተኛ ጊዜ የከፈተው ጦርነት ለአራተኛ ጊዜ በህወሓት ተሸናፊነት መጠናቀቁን የጠቅላይ ሚኒስቴር ፅህፈት ቤት አስታውቋል።
የስድት ወር ዕድሜ ያለውን የትግራይ ባለአደራ ምክር ቤትን የሚመሩ ባለሥልጣናትም ሹመት ተሰጥቷል፡፡

የባለአደራ አስተዳደሩ ዋና አስፈጻሚዎች

1. አቶ አሰፋ አብርሃ ሐጎስ የአስተዳደር እና የሕዝብ አገልግሎት ዋና አስፈጻሚ
2. ⁠ዶክተር ቴዎድሮስ አረጋይ  ወ/ሥላሴ - የኢኮኖሚ እና መልሶ ግንባታ ዋና አስፈጻሚ
3. ⁠ብ/ጄ ገብረ እግዚአብሔር በየነ ኃይሉ(ወዲ አንጥሩ)- የጸጥታና ሰላም ዋና አስፈጻሚ
4. ⁠አቶ ረዳኢ ኃለፎም ወ/ሥላሴ - የፖለቲካ እና ሕዝብ አደረጃጀት ዋና አስፈጻሚ
5. ⁠ዶክተር ሽሻይ አማረ - የመቐለ ከተማ ከንቲባ በመሆን ተሹመዋል።
የድሮን ጥቃት‼️
በዛሬው ዕለት ጥቅምት 6/2019 ዓ.ም ከረፋዱ 5፡10 ጀምሮ በትግራይ ክልል ተንቤን አካባቢ በሚንቀሳቀሱ የህወሓት ታጣቂዎች ላይ ተደጋጋሚ የድሮን ጥቃት መፈፀሙን ምንጮች ለአዩዘሀበሻ ገልፀዋል። በትናንትናው ዕለት በዚሁ አካባቢ ውጊያ እንደነበር ታውቋል።
አዩዘሀበሻ
❤1
የአስክሬን ሳጥን እንደሚከራይ ያውቃሉ?

​በአዲስ አበባ ከተማ የአስክሬን ሳጥን የመሸጥ ብቻ ሳይሆን የኪራይ አገልግሎት ለበርካታ ዓመታት ሲሰጥ መቆየቱን በዘርፉ የተሰማሩ ነጋዴዎች ገለጹ።

​የኪራይ አገልግሎቱ በዋናነት በሰሌን መቀበር በሚፈልጉ መነኮሳት እና ሰዎች ለሽኝት ሥነ-ሥርዓት ብቻ ጥቅም ላይ የሚውል ሲሆን፣ እንደ ሳጥኑ ደረጃ የሀገር ውስጥ ሳጥኖች ከ2 ሺህ እስከ 15 ሺህ ብር፣ የውጭ (የአሜሪካ) ሳጥኖች ደግሞ እስከ 25 ሺህ ብር እንደሚከራዩ ተገልጿል።

​ነጋዴዎች አገልግሎት ላይ ውለው የተመለሱ ሳጥኖችን በፕላስቲክ፣ ጨርቅ በመቀየር እና ኬሚካል በመርጨት ድጋሜ እንደሚያከራዩ ወይም እንደሚሸጡ የተናገሩ ሲሆን፣ ደንበኞች ይርቁናል በሚል ፍርሃት እናከራያለን ብለው በግልጽ እንደማያስተውቁ ጠቁመዋል።(via ቲክቫህመጋዚን)
😁2
የትግራይ ቴሌቪዥን የፌስቡክ ገጽ መመለሱ ታውቋል።

​እስከ ትላንትናው ምሽት ድረስ በሕወሓት አመራሮች ቁጥጥር ስር የነበረው የትግራይ ቴሌቪዥን የፌስቡክ ገጽ፣ አሁን ላይ አዲስ ወደ ተመሰረተው የትግራይ ክልል ባለአደራ አስተዳደር መተላለፉ ተነግሯል።

​ገጹ እንዴት ሊተላለፍ እንደቻለ እስካሁን በዝርዝር የታወቀ ነገር ባይኖርም በኢንሳ ሳይሆን እንዳልቀረ ተጠቁሟል።
ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ ታሪካዊ ድል አስመዘገበች!

የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ኮሚቴን በሰብሳቢነት እንድትመራ ተመረጠች!"


ኢትዮጵያ የተባበሩት መንግስታት የዓለም ስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን ዋና ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ 78ኛውን መደበኛ ክፍለ ጊዜ በሰብሳቢነት እንድትመራ በድምፅ ተመረጠች።

ሚሊዮን ለሚጠጉ ስደተኞች መሸሸጊያ በመሆን የምትታወቀው ኢትዮጵያ፤ ይህንን ዓለም አቀፍ ኃላፊነት መረከቧ በዓለም አቀፍ መድረክ ያላት ዲፕሎማሲያዊ ተሰሚነት እጅግ ማደጉን የሚያሳይ ትልቅ ምዕራፍ ነው።
Forwarded from Safe 2+ Odd
.
Forwarded from Betting Society
.
Forwarded from Betting House
.
Forwarded from Bet squad
.
Forwarded from quality botton
ተማርዎች አሁን ምን ያስፈልጋቹሃል?
በእነዮሐንስ ቧያሌው የክስ መዝገብ የሚገኙና መንግስት ያቀረበው የይቅርታ ሰነድ ላይ ለመፈረም ፈቃደኛ ያልሆኑ አራት ተከሳሾች ክሳቸውን እንዲከላከሉ ፍርድ ቤቱ ውሳኔ ማሳለፉን ጠበቃቸው ለአዲስ ማለዳ ገለጹ

በእነ ዮሐንስ ቧያሌው የክስ መዝገብ ውስጥ 52 ውስጥ 36ቱ በሌሉበት፣ 16ቱ በችሎት ተገኝተው ሲከታተሉ ነበር። ከ16ቱ ውስጥ 12ቱ በመንግስት የቀረበውን የይቅርታ ሰነድ በመፈረም የተፈቱ ናቸው።

በዚሁ የክስ መዝገብ ፍርድ ቤቱ እንዲከላከሉ ብይን የተሰጠባቸው 4 ተከሶሾች፤ ዮሐንስ ቧያሌው፣ ዶክተር ዘሪሁን ባህሪው፣ ጋዜጠኛ ዓባይ ዘውዱ እና ደሳለኝ እጅጉ ናቸው።

የ2019 አዲስ ዓመትን ምክንያት በማድረግ የፌደራሉ መንግስት በኢትዮጵያ በሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን(ኢሰመኮ) ጥረት በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ከእስር እንዲፈቱ የተደረገ ቢሆንም 30ዎቹ ግን ለመፈረም ፍቃደኛ ባለመሆናቸው ከእስር አልተለቀቁም፡፡

በእነ ዮሐንስ ቧያሌው የክስ መዝገብ ሥር ፊርማ ለመፈረም ፈቃደኛ ባለመሆናቸው በእስር ላይ የሚገኙ አራት ተከሳሾች ክሳቸውን እንዲከላከሉ የከፍተኛ ፍርድ ቤት መወሰኑን ጠበቃቸው ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል።

እነዚህ አራት ተከሳሾች ክሳቸውን በፍርድ ቤት የመከላከል መብታቸውን ለመጠቀም ይግባኝ ያቀረቡ ሲሆን፣ በዛሬው የከፍተኛ ፍርድ ቤት ችሎትም ይግባኛቸው ተቀባይነት ማግኘቱን ጠበቃ ሰለሞን ገዛኸኝ ገልጸዋል።

በዚሁ መሠረት አራቱ ተከሳሾች በቀረበባቸው ክስ ላይ መከላከያቸውን እንዲያቀርቡ መወሰኑን ጠበቃቸው አስረድተዋል።

ውሳኔው ተከሳሾቹ ክሳቸውን የመከላከል እድል እንዲያገኙ የሚያስችል ሲሆን፣ በጉዳዩ ላይ የሚቀጥለው የሕግ ሂደት ምን እንደሚሆን በቀጣይ የፍርድ ቤት ሂደቶች የሚታይ ይሆናል። 
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ህውሃት ተዘረፍኩ እያለ ነው።

📌ዛሬ የትግራይ ቴሌቪዥን የፌስቡክና የዩቱብ ገጾችን መንግስት መቆጣጠሩን ተከትሎ ነው ህወሃት ተዘረፍኩ እያለ ያለው።

📌በሌላ በኩል ህውሃት ጥሎት የሸሸውና የውጊያ ድሮኖች በትግራይ የሰላም ኃይል አሰሳ መያዛቸው ተነግሯል።

አሁን ላይ በትግራይ ክልል የተለያዩ ቦታዎች የተደበቁ የጦር መሳሪያዎች በህብረተሰቡ ጥቆማ እየተያዙ ነው ተብሏል።
Forwarded from quality botton
Are You Struggling? College or University?
Forwarded from quality botton
Which University Is  Best in Ethiopia ?
🤷‍♂1
10 ሚሊየን ብር ያላቸው ኢትዮጵያውያን የዳንጎቴ ነዳጅ ማጣሪያን አክሲዮን መግዛት ይችላሉ

ኢትዮጵያውያን ባለሀብቶች በዳንጎቴ የነዳጅ ማጣሪያ አክሲዮን ግዢ ላይ ለመሳተፍ መኪናቸውንና ቤታቸውን ሳይጨምር ቢያንስ 10 ሚሊዮን ብር ሀብት ሊኖራቸው እንደሚገባ የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለሥልጣን አስታውቋል።

አዲስ አበባ ላይ በተዘጋጀው የባለሀብቶች መድረክ ይፋ እንደተደረገው፣እያንዳንዱ አክሲዮን 74 ብር ከ90 ሳንቲም ዋጋ የወጣለት ሲሆን፣ ሽያጩም እስከ ጥቅምት 17 ቀን 2019 ዓ.ም. ድረስ ክፍት ሆኖ ይቆያል።

ይሁን እንጂ ይህ ዕድል ለሁሉም ክፍት የተደረገ ሳይሆን፣ ከ100 ለማይበልጡ ብቁ ባለሀብቶችና ተቋማት ብቻ የተወሰነ ነው።

በናይጄሪያ የሚገኘውና በአፍሪካ ትልቁ የሆነው የዳንጎቴ ነዳጅ ማጣሪያ ፋብሪካ፤ የነዳጅ ማጣራት አቅሙን በእጥፍ ለማሳደግ 1 ነጥብ 6 ቢሊዮን ዶላር ለማሰባሰብ ይህንን አክሲዮን ይፋ አድርጓል።

ፋብሪካው በ2026 የመጀመሪያ አጋማሽ ብቻ 13 ነጥብ 6 ቢሊዮን ዶላር ገቢ እና 1 ነጥብ 78 ቢሊዮን ዶላር ትርፍ ማግኘቱ ተገልጿል።
❤1
📢 Looking for more customers? Pick a Telegram channel and put your ad in front of its readers.
🔗 Earn 50% affiliate fee
ፖለቲከኛው አቶ አበበ አካሉ ከእስር ተፈቱ‼

​ በወቅታዊ ጉዳዮች ትንታኔ በመስጠትና በፓርቲ ፖለቲካ እንቅስቃሴያቸው የሚታወቁት አቶ አበበ አካሉ ዛሬ ጥቅምት 6 ከእስር መፈታታቸው ታውቋል።