ዛZalaላ
409 subscribers
601 photos
6 videos
2 files
69 links
We bring news that matters to you with an in depth analysis
Download Telegram
ንግድ ባንክን ምን አጋጠመው?

ከትናንት ለሊት ጀምሮ ተመሳሳይ መልዕክቶች እየደረሱኝ ነበር፣ መልዕክቶቹም "በርካታ ሰዎች፣ በተለይ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ከንግድ ባንክ ከኤቲኤም እና ከኦንላይን ትራንስፈር በነፃ ገንዘብ ወስደዋል ወይም ትራንስፈር አርገዋል" የሚል ነው።

አንድ ተማሪ እንደጠቆመኝ "እኛ ጋር ጓደኞቻችን ከ100 ሺህ እስከ 50 ሺህ  የሰሩ አሉ። 435ሺ ብር የሰራ ተማሪ አለ በዛች ቅፅበት ምክንያቱም ለሊት ላይ ንግድ ባንክ የፃፍክለትን ብር ያወጣ ነበር። ይህ የሆነው ለሊት ከ6 ሰአት እስከ 9 ሰአት አከባቢ ነበር።"

ሌላ ተማሪ ሲያስረዳ "ለምሳሌ እኔ ጋር 500 ብር ቢኖረኝ  ዝም ብዬ ወደ አንተ 50,000 ብር ፅፌ በሞባይል ባንክ ብልክ ዝም ብሎ ይልክ ነበር" ብሏል። ወደ ኢ-ብር የላኩት ልጆች ግን አካውንታቸው ወዲያው እንደታገደባቸው ታውቋል።

አንድ መምህር ደግሞ "እኔ በምሰራበት ዩኒቨርሲቲ የሚማሩ ተማሪዎች ለሊቱን ሙሉ በዛ ያለ ገንዘብ በኤቲኤምና በትራንስፈር ገንዘብ ሲያስተላልፉ እንደነበር ሰምቻለሁ። ይህም ነገር በአንዳንድ የሀገሪቱ አካባቢዎችም እንደነበር ስለሰማሁ ጥቆማ ልስጥህ በሚል ነው የጻፍኩልክ" ብለዋል።

ይህን ተከትሎ ባንኩ "በሲስተም ችግር ምክንያት" አገልግሎቶቹ ላይ ማለትም በቅርንጫፎች፥ በኢንተርኔት ባንኪንግ፥ በሞባይል ባንኪንግ፥ እንዲሁም በሲቢኢ ብር የአገልግሎት መቋረጥ አጋጥሟል ብሏል።

የባንኩን የስራ ሀላፊዎች በስልክ ለማግኘት ያደረግኩት ሙከራ አልተሳካም፣ ባንኩ ግን ምን እንደተከሰተ ዝርዝር መረጃ ለህዝብ እንደሚሰጥ ይጠበቃል።

Via Elias meseret
በስፔን የ10 ኪሎ ሜትር ሩጫ ውድድር ዮሚፍ ቀጄልቻ አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 7፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በስፔን ላሬዶ ከተማ በተካሄደ የ10 ኪሎ ሜትር ሩጫ ውድድር ኢትዮጵያዊው አትሌት ዮሚፍ ቀጄልቻ አሸንፏል፡፡

አትሌት ዮሚፍ ርቀቱን 26 ደቂቃ ከ36 ሰከንድ በሆነ ሰዓት በማጠናቀቅ ነው ቀዳሚ የሆነው፡፡

**
አሰደናቂውን ብቃት የሚያሳየውን ቪዲዮ ከቆይታ በኋላ ወደ እናንተ እናደርሳለን
አሰደናቂውን ብቃት የሚያሳየውን ቪዲዮ ከቆይታ በኋላ ወደ እናንተ እናደርሳለን
በስፔን የ10 ኪሎ ሜትር ሩጫ ውድድር ዮሚፍ ቀጄልቻ አሸነፈ

በስፔን ላሬዶ ከተማ በተካሄደ የ10 ኪሎ ሜትር ሩጫ ውድድር ኢትዮጵያዊው አትሌት ዮሚፍ ቀጄልቻ አሸንፏል፡፡

አትሌት ዮሚፍ ርቀቱን 26 ደቂቃ ከ36 ሰከንድ በሆነ ሰዓት በማጠናቀቅ ነው ቀዳሚ የሆነው፡፡

https://youtu.be/warVauG54rE?si=BPJa4yK1nQKd0FIW
አረንጓዴውን ጎርፍ ውድድሩን ለመመልከት https://youtu.be/vZJa7jSv_G4?si=YDxtAkAbhJFLNova
በሁለተኛ ቀን የጋና አክራ 13ኛው መላ አፍሪካ ጨዋታዎች በርካታ የማጣሪያና የፍፃሜ ውድድሮች የሚካሄዱ ሲሆን ምሽት ላይ ተጠባቂ የፍፃሜ ውድድሮች መካከል፦

በ800 ሜትር ሴቶች ፍፃሜ ምሽት 4:05 አስቴር አሬሬ እና ፅጌ ዱጉማ

በ10000 ሜትር ወንዶች ፍፃሜ ምሽት 4:35 ኃ/ማርያም አማረ፣ ንብረት መላክ እና ገመቹ ዲዳ የሚሳተፋ ይሆናል።

መልካም እድል ለውድ አትሌቶቻችን!
ህብረተሰቡ ጥንቃቄ ያድርግ ተብሏል ⚠️

#Ethiopia | ከፖርክ የወጡ 12 ዝሆኖች በሰዉ እና በንብረት ላይ ጉዳት ማድረሱን የዳዉሮ ዞን ፖሊስ አስታወቀ።

የዝሆን መንጋ ጉዳት ያደረሰው በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በዳዉሮ ዞን ከጪ ወረዳ ኦዳ ጎፋ ቀበሌ ዝግና ተብሎ በሚጠራው ስፍራ ነዉ።

እንደ ፖሊስ ሪፖርት የዱር እንስሳቱ መጋቢት 09 ቀን 2016 ዓ.ም ከምሽቱ 12:00 ሰዓት ከጨበራ ጩርጩራ ብሄራዊ ፖርክ የወጡ በቁጥር

* 12 የሚሆኑ ዝሆኖች በሰው እና በንብረት ላይ ጉዳት አድርሰዋል።

በሃያዎች ዕድሜ ክልል የምትገኝ ወጣት ከትምህርት ቤት ወደ መኖሪያ ቤቷ በመሄድ ላይ የነበረች የዘጠነኛ ክፍል ተማሪ በዝሆኑ መንጋ ሆዷ ላይ ተረግጣ ጉዳት ደርሶባት ታርጫ ሆስፒታል እየተደረገላት እንደሚገኝ ተጠቁሟል።

የዝሆን መንጋዉ በንብረት ላይ የደረሰዉን የጉዳት መጠን እየተጣራ እንደሚገኝና ዝሆኑ ወደፖርኩ አለመመለሳቸዉን ፖሊስ ገልፆ ህ/ሰቡ ተጨማሪ ጉዳት እንዳይደርስበት ጥንቃቄ እንዲያደርግ መልዕክቱን አስተላልፏል ሲል የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነትና ግንኙነት ዘግቧል።
ዛሬ ምሽት ፅጌ ድጉማ ትጠበቃለች።

እንደተለወደው ውድድሩን @Shegerplusnews ዩቲዩብ ላይ ያገኙታል

**

በሁለተኛ ቀን የጋና አክራ 13ኛው መላ አፍሪካ ጨዋታዎች በርካታ የማጣሪያና የፍፃሜ ውድድሮች የሚካሄዱ ሲሆን ምሽት ላይ ተጠባቂ የፍፃሜ ውድድሮች መካከል፦

በ800 ሜትር ሴቶች ፍፃሜ ምሽት በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር 3:05 አስቴር አሬሬ፣ አዳኑ ኔንቆ እና ፅጌ ዱጉማ

በ10000 ሜትር ወንዶች ፍፃሜ ምሽት በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር 3:35 ኃ/ማርያም አማረ፣ ንብረት መላክ እና ገመቹ ዲዳ የሚሳተፋ ይሆናል።

መልካም እድል ለውድ አትሌቶቻችን!
በጋና አክራ በ10ሺህ ወንዶች አራተኛው ወርቅ ለኢትዮጵያ ተመዝግቧል

Ghana 10000 men Final / Ethiopia won gold and silver in Accra Ghana / Ethiopia athletics federation
https://youtu.be/n1LJtvgfeBU
115 ሰዎች በላይ ከሞቱበት የትላንቱ በሩሲያ ሞስኮ ከተፈፀመው ጥቃት ጀርባ ISIS ወይስ ዩክሬን?
****

ታጣቂዎች በሞስኮ አቅራቢያ በሚገኘው ታዋቂው የክሮከስ አዳራሽ ላይ በከፈቱት ተኩስ የተገደሉ ሰዎች 115 መድረሱን እና 100 ሰዎች መቁሰላቸውን የሩሲያ የደኅንነት አገልግሎት አስታወቀ።
ቢያንስ አራት ወታደራዊ የደንብ ልብስ የለበሱ ታጣቂዎች የበርካቶችን ሕይወት በቀጠፈው ጥቃት ውስጥ መሳተፋቸውንም ቢቢሲ ያረጋገጠው ቪዲዮ ያሳያል።

ዝርዝር ትንታኔውን ለማግኘት

https://youtu.be/kTFO_zoerRc?si=8mbfcWkzhLfSuD0z
እንደ ሲጋራ ተጠቅልሎ አንድ ሁለቴ ሲሳብ የገዛ ነፍስን ማስጠፋት፣ የራስ ጉሮሮን በስለት መቁረጥ አልያም በቆሻሻ ቱቦ ውስጥ መዋኘት … ሌላም ሌላም አስከትሏል

የአደንዛዥ እፁ ስም ኩሽ ይባላል

ከተፈጨ የሰው አጥንት ጋር ተቀላቀሎ ይሰራል

ለዚህም ሱሰኞቹን በሌሊት መቃብር እያስቆፍረ ያሳድራል

ሙሉሙን ከታች ባለው ሊንክ ይመልከቱ

https://youtu.be/QokPBeHlPGI?si=bWh2yX0wnzGR_gr9
ኢራን ላይ ይህ ሁሉ ለምን ይሆናል።
ይህን ለመረዳት የግድ ከአምስት አስርት ዓመታት በፊት የነበረውን የአኢራን ሁኔታ ማወቅ ያስፈልጋል። ይህን የሚያሳይ ጥልቅ ትንተና በዩቲዩብ ላይ በRedSeapost_netsanetlakew በሚለው ገፅ ያገኛሉ።

ይቺን ሊንክ ኮፒ አድርገው በቀጥታ መግባት ይችላሉ።

https://youtu.be/E-zfXXyD_Lo?si=hArdLtyxZ5bXfg7R

በ1951 መሐመድ ሞሳዴቅ ብሪታንያ በኢራን ላይ የነበራትን የበላይነት ለማቆም ሞከረ። ሞሳዴቅ ከአርባ ዓመታት በላይ በአንድ የብሪታንያ ኩባንያ ብቻ ተይዞ የነበረውን የኢራንን ድፍድፍ ዘይት የሀገር ሀብት አደረገ (ብሔራዊ አደረገው)። ለእሱ ይህ የድፍድፍ ዘይት ሀብት የሀገር ንብረት መሆኑ -ነፃ እና ገለልተኛ ኢራንን ለመመሥረት አስፈላጊ ነበር።

በዚህ ድርጊቱም ሞሳዴቅ በጠላቶቹ መካከል - ፍቅርን፣ ጥላቻን፣ መሳለቂያን እንዲሁም አክብሮትን ጭሮ ነበር። በርካቶች በቢጃማ ሆኖ ጋደም ካለበት አልጋ ሳይነሳ በሚያደርጋቸው ጠንከራና ስሜት ኮርኳሪ ንግግሮቹ ሲነኩ አንዳንዶቸ‍እ ደግሞ ይስቁበት ነበር።

ሞሳዴቅ የውጭ እና የሀገር ውስጥ ጠላቶች ፥ በስልጣን ሽሚያ እና በድፍድፍ ዘይት ቁጥጥር ፍልሚያ ውስጥ እሱን ለማዳከም ከፈጠሩት ጥምረት ጋር መታገል ነበረበት።

ከአምስት አስርት ዓመታት በኋላ፣ የሞሳዴቅን ድሎች እና ውድቀቶች ሳይረዱ ኢራንን መረዳት የማይቻል ነው። የእሱ ዝና (ተረት) ዛሬም በኢራን ሕይወት እና ፖለቲካ ላይ ተጽዕኖ ማሳደሩን ቀጥሏል።