Yop Poem ️
7.7K subscribers
55 photos
5 videos
25 files
43 links
፨Yop Poem
አዳዲስ እና የቆዩ ግጥሞችና ወጎችን በቀላሉ ያገኙበታል። 🤲
እርስዎም የግጥም ተሰጥዖ ካልዎት መልቀቅ ይችላሉ።👐
Our main channale :- @Utophiainfo

ቻናላችንን #share ያድርጉ👍

for promo & cross 👉 @Yared642
Download Telegram
Forwarded from Yop Poem ️ (Death💀)
አባቶች እናቶች
በፍቅር ተጋግዘው ፣ ያቆሙልን እውነት
በዘመን ጠልሽቶ...
ለእኛ ለልጆች ፣ ይመስለናል ተረት፡፡
።።።።።።
የኛ ትልቅ ችግር ፣ የኛ ትልቅ ህመም
"ተረት ተረት"ሲባል
መሰረት ሳንይዝ
"የመሰረት" ብሎ ፣" እሺ" እያሉ ማዝገም፡፡
።።።።።።፣
ተረት ተረት
"የመሰረት"
አንድ ሀገር ነበረች
"እሺ"
እምነትን ከፍቅር ፣ ገምዳ ያስተማረች፡፡
"እሺ"
አናም በዚች ሀገር...
ሙስሊሞች በእምነት ፣ መስጅድ ሲገነቡ
ክርስቲያኖች በፍቅር...
ይታዩ ነበረ ፣ ምሶሶ ሲያቀርቡ፡፡
"እሺ"
፡፡፡፡፡፡፡፡፡
እናም በዚች ሀገር...
ክርስቲያኖች በምነት ፣ ቤተስኪያን ሲያንፁ
ሙስሊሞች በፍቅር...
ይታዩ ነበረ ፣ ጉልላት ሲቀርፁ፡፡
"እሺ"
እናም በዚ መልኩ ፣ ሲኖሩ ሰኖሩ
እንደተዋደዱ እንደተፋቀሩ
እንደተጋገዙ እንደተባበሩ
መሰረት እንድናይ...
አንዋር ከራጉኤል ፣ ተጎራብተው ቀሩ
"እሺ"
"እሺ" ማለት ጥሩ
መሰረት ሳይዙ ...
የመሰረት ብሎ ፣ መኖር ነው ችግሩ!!!
።።።።።

By Belay Bekele Weya

@Yoppoem
በዚህ ሙቅ ከተማ
በዚህ ደማቅ መንገድ
ሺ አምፖል በበራበት
ፀሐይ ቀንና ሌት ፥ በማትጠልቅበት
ለሰው የማይታይ
አለ ብቸኝነት ።

አለ ብቸኝነት
በስንት እግሮች መሐል
ያደፈ ኮት ለብሶ
አይኑ ማዶ ፈዞ
የታክሲ ጥሩንባ የሚያደነቁረው
ሰው ገፍትሮት እንኳን
"ይቅርታ" የማይለው
ስሙ ፥ ማይነሳ
መኖሩ ፥ የተረሳ
ቢሞት ፥ ልብ የማይባል
አለ ብቸኝነት
እዚሁ ፥ እኛው መሐል ።

አለ ብቸኝነት
አንድ ጊዜ ተራምዶ
ብዙ ጊዜ የሚቆም
በፋሲካ በአል ፥ ብቻውን የሚጾም ።

አለ ብቸኝነት
ቢያውቀው ወይ ባያውቀው
የሚገላምጠው
(ወይ በመተያየት)
ፈገግታ 'ሚሰጠው
አንድ አይን የናፈቀው ።

አለ ብቸኝነት
ዕንባውን የዋጠ
ሳቁን የመጠጠ
ስሜቱን ያፈናት ፥ ልውጣ ባለች ቁጥር
ልቡ እንደ ድመት ሆድ ፥ ትር ትር የምትል ።

አለ ብቸኝነት
ወዴትም የማይሄድ ፥ ዝም ብሎ የሚራመድ
እንኳንስ ሰውና ፥ ልቡ ያልሆነው ዘመድ
ጭር ያለ ባይተዋር
በሰው ጎርፍ መሐል
ትንፋሹ የሚታየው
እርምጃ የሚመትር
ጠብታ የሚቆጥር
ወዴትም ሳንርቅ ፥ እዚሁ አፍንጫችን
እዚሁ ልባችን ስር
አለ ብቸኝነት ።

@Yoppoem
Messages in this channel will no longer be automatically deleted
ተመልሰናል ቤተሰብ 😊😊
ጥቁር ነጭ ግራጫ
(ነብይ መኮንን)

...ሰው እያለ አጠገባችን
ቅንነቱን ማየት ሲያመን
ከኛ አብሮ በሕይወት ቆሞ ፤ መልካሙን ስምን
መጥራት ሲያንቀን
"ሰው ካልሞተ ወይ ካልሄደ አይነሳም" እንላለን
እንዲህ እያልን፤
ስንቱን ጠቢብ እየሸኘን፤
አበባውን ቀጥፈን ጥለን፤ አበባ (እ)ናስቀምጣለን።



@Yoppoem
አድሚኖች ፖስት ካደረጋችሁ በኋላ የፖሰታችሁትን እራሳችሁ አጥፉ🙏🙏
Yop Poem ️ pinned «አድሚኖች ፖስት ካደረጋችሁ በኋላ የፖሰታችሁትን እራሳችሁ አጥፉ🙏🙏»
መሔጃ የለኝ !
ካይኖችሽ ብሸሽ ፥ ቅንድብሽ ስር ነኝ ።
ወዴትም ብዞር
ገላሽ ብቻ ነው ፥ የሚያዋስነኝ ።
ቅርቤም - ሩቄ
ኩነኔም - ጽድቄ
ከህጎች በልጦ ፥ ልብሽ የሚያዘኝ
ሙዚቃሽ ብቻ የሚያስደንሰኝ ።

ጠዋት ብጠላሽ ፥ ማታ ምወድሽ
ምንም ቢሰማኝ ፥ የማላመልጥሽ
ወስልቼ ብሄድ ከገላሽ ምሕዋር
ተኝቼ ምገኝ ፥ ከትዝታሽ ጋር ፥
ወዲህም ሳራ ፥ ወዲህም አጋር !

አይንሽ እንደ ጥላ
ከኋላ ከኋላ
ሳይከታተለኝ
እምነትሽ ብቻውን ሸብቦ  'ሚያስቀረኝ
ያንቺው ግዞተኛ ፥ ያንቺው ታሳሪ ነኝ !

Habtamu Hadera
@Yoppoem
Forwarded from Utopia ዩቶጵያ (Clandestine)
ስለምን ይቅረብ ?

Inbox me
@Yared642
Forwarded from Mic tech solution 🔧 (Clandestine)
አንዱ ጀለሴ ሰጋቶራ የተቀላቀለበት
እንጀራ አብዝቶ ከመመገቡ የተነሳ
ሲተኛ,ሲነሳ,ሲቀመጥ,ሲራመድ ቀጥ
ብሎ ነው
:
እኔ ደሞ ላስቀው ብዬ ቀልድ ስነግረው
:


ቀልድህ ሁሉ አያስቅም እንጨት
እንጨት ነው የሚለው አላለኝም
😂😂😂

Join
@Nu_fresu
Messages in this channel will be automatically deleted after 1 day
Messages in this channel will no longer be automatically deleted
እዚህ ቻናል ላይ አድሚን መሆን የሚፈልግ ያናግረኝ
@Yared642
Messages in this channel will be automatically deleted after 1 day
Forwarded from ኑ ፍረሱ
ሀይ ኢትዮጵያ 😂

@Nufresu
Messages in this channel will no longer be automatically deleted
በሰዉ ዘንድ መገፋት፤
ደግ ፊት መነሳት፤
እስከ ጥግ አዉቃለሁ.....
ክፉ ደግ ያሳለፍን፤
ጎረቤቶቼ እንኳን፤
ያለፍኩ እንደሆነ ድንገት በበራቸዉ፤
እንደዚህ ይሉኛል ቃል እያጠራቸዉ፤
ምኑን ቢያቀምሷት፤
በምን ቢመርዟት፤
አልባሷን ቀዳዳ ጎዳና የወጣች፤
ከሰዉ ተነጥላ ብቻዋን ያወራች፤
እርሷ እኮ እንዲህ ነች እያሉ፤
ምኑንም ሳያዉቁ ፍርድ ይበይናሉ፤
ፍፁም ሰላምና ጤንነትን ሽቼ፤
ራሴን አገኘሁ  ከገዳም ሰንብቼ፤
እናም አካላቴ እዉነት ናፍቀኸኛል፤
በክንድህ መሸሸግ እቅፍህ ያሻኛል፤
ትዝ ይልሃል አይደል......
የኔ ልብ ካንተ ያንተም ልብ ከኔ፤
በፍፁም ተጋምዶ በፍቅራችን ቅኔ፤
ለሰርጋችን ድምቀት እቅድ ስናወጣ፤
ነጠላ አጣፍተን ተሳልመን ስንመጣ፤
ትዝ ይልሃል አይደል......
ለዚህ ያደረሰኝ ቤተሰብ ጓዳዬ፤
ስንት የደከምኩበት ፍቅርና አላማዬ፤
ትናንት በጉያዬ በእጄ የነበረ፤
ተስፋ ያደረኩት መና ሆኖ ቀረ።
ማነዉ ተጠያቂ ልቤ ለመድማቱ
እዉነተኛ ደስታ ከእኔ ለመጥፋቱ
ማነዉ ተጠያቂ?????
......................................
በዔደን ታደሰ


@Yoppoem
እኔ እና ሚስቴ(ከ "ሀ" እስከ"ፐ")
====================
ክፍል 1
👇👇👇
ከእለታት በአንድ ቀን...
         እረፍት ስለፈለኩ
       ከአልጋየ ተጋደምኩ
ግና ምን ያደርጋል
               ቀኝ አይኔን ሸከከኝ
                   ግራ ጎኔን ወጋኝ
ከአልጋየ ወርጄ ከቤቴ ወጣሁኝ
መንገድ ዳር
      ቁጭ ብየ በሀሳብ ነጎድኩኝ

      የወጋኝን ጎኔን በእጄ ስዳብሰው
ጎሏል አንድ ነገር ጎሎኛል አንድ ሰው
ፈለኩኝ ሄዋኔን
ከሞላው ህዝብ ላይ ከሚተራመሰው
የሸከከኝ አይኔን ወረወርኩት እሩቅ
የወጋኝን ጎኔን
መድሀኒት እስኪአገኝ ደባበስኩት በጥብቅ
አፌንም ነገርኩት
           ሄዋኔን ለመሳብ  ብዙ ቃላት ሰንቅ
ጥርሴንም መከርኩት
     ሄዋኔን ለማስመጥ ልመድ ብዙ መሳቅ

ይኧው ...ከምክሩ በሗላ ሁሉን አሟልቸ
  አይኔ እስኪአመጣልኝ ቆየሁ ተጎልቼ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
ይቀጥል?  👍👍👍👍

belaya(ዝምተኛው ፀሀፊ)

@Yoppoem
🚨🚨🚨 ተመልሰናል 🚨🚨🚨