Yeshua Apologetics Ministry
2.17K subscribers
56 photos
3 videos
6 files
85 links
➟የሹዋ ዐቅበተ እምነት አገልግሎት አላማ

ከክርስትና እምነት አንጻር ደርዛቸውን የጠበቁ ስነ መለኮታዊ ፍልስፍና፤ አመክንዮአዊና ታሪካዊ ጽሑፎችን ማቅረብ

በክርስትና ላይ የሚነሱ የተቃውሞ ሀሳቦችንና የኑፋቄ ትምህርቶችን መመከት

የሌላውን እምነተ መርህ ከሎጂክና ከታሪካዊ ዳራዎች አንጻር መመርመር



@Yeshua_Apologetics_Ministry

Download Telegram
« Inerrancy & Sola Scriptura »

«ቅዱሳት መጻሕፍት ሁሉ #የእግዚአብሔር_መንፈስ_ያለባቸው ናቸው፤ ለማስተማር፣ ለመገሠጽ፣ ለማቅናት በጽድቅም መንገድ ለመምከር ይጠቅማሉ» ----2ኛ ጢሞ 3፥16 (አዲሱ መ.ት)

Sola scriptura ለክርስትና እምነተ መርሕ(Principle) መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ inerrant & infallible authority እንዳለው confess የሚያደርግ ክርስቲያናዊ principle ነው። ይሄንን ሐሳብ ብርሐነ አለም ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ለመንፈሳዊ ልጁ ለጢሞቴዎስ በጻፈለት መልዕክት ላይ <<ቅዱሳት መጻሕፍት ሁሉ>> እስትንፋሰ እግዚአብሔር (ቴዎኔዩስቶስ/θεόπνευστος) መሆናቸውን ሲነግረው እንመለከታለን። ቅዱሳት መጻሕፍት እስትንፋሰ እግዚአብሔር (ቴዎኔዩስቶስ/θεόπνευστος) ወይም አፊዎተ እግዚእ ማለትም በቀጥታ divinely inspired መሆናቸውን እና ከዚህም የተነሳ እውነተኛ እና ሕጸጽ አልቦ ናቸው ብለን እናምናለን። የቤተ ክርስቲያን አበው ይህንኑ ሐሳብ ሲደግፉ ይስተዋላል። የአራተኛው መቶ ክፍለ ዘመን አባት ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ(John Chrysostom) ክፍሉን በድርሳኑ ላይ ሲያብራራ ቅዱሳት መጻሕፍት አፊዎተ እግዚእ መሆናቸውን እና ለአማኞች ትክክለኛ የቅድስና እና የህይወት መንገድ መሮች መሆናቸውን ይናገራል(Homilies on 2 Timothy)። ቅዱስ ሔሬኔዎስ ዘሊዮን(Irenaeus of Lyons) በመድፍነ መናፍቃን መጽሐፉ ላይ ቅዱሳን መጻሕፍት እስትንፋሰ እግዚአብሔር እና የበላይ ባለስልጣን መሆናቸውን በመግለፅ እውነተኛው የክርስትና አስተምህሮ መሠረት የሆኑ  እና ሐሰተኛውን አስተምህሮ የምንከላከልባቸውም (የምንመክትባቸው) ጭምር እንደሆኑ ይገልጻል (Against Heresies)።  ቅዱሳት መጻሕፍት Inspiration of God በመሆናቸው ስለ እውነት ፤ ክርስትያናዊ የሕይወት መርህ እና ድነት አስፈላጊ የሆኑትን Doctrinal issue ሁሉ በውስጡ ያካተቱ በመሆናቸው Sufficiency of Scripture ባህሪዎት እንዳላቸው እንመለከታለን። ቅዱስ አትናቲዎስ (Athanasius of Alexandria) ስለSufficiency of Scripture ሲናገር፦

"The Holy Scriptures, given by inspiration of God, are of themselves sufficient toward the discovery of truth."
(Against the Heathen, 1:3)


ነገር ግን Sufficiency of Scripture በራሱ ትውፊትን የሚያገልል ወይም የሚቃወም ተደርጎ በፍጹም መታሰብ የለበትም። ለTradition, ለLiturgical practice ሆኑ ለCouncils አስተምህሮ እና እውነተኝነት ትክክለኛው መመዘኛ መጽሐፍ ቅዱስ መሆኑን የሚናገርም ነው። በተጨማሪም ሁሉም Highest Authority ላለው ለመጽሐፍ ቅዱስ መገዛት እና ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር alignment መፍጠር እንዳለባቸው የሚያመላክትም ጭምር ነው። ምክንያቱም Tradition, Liturgical practice ሆኑ Councils inerrant ስላልሆኑ ማለትም fallible በመሆናቸው ምክንያት መመዘን ያለባቸው infallible እና inerrant በሆነው በመጽሐፍ ቅዱስ ነው። ይህንን ሐሳብ ቅዱስ አውግስጢኖስ ዘሒፖ(Augustine of Hipo) በመደገፍ መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ inerrant እና infallible እንደሆነ ይናገራል፦

I have learned to yield this respect & honour #only to the scripture, of these #alone do I most firmly believe that completely #inerrant (free from error)----Letters, 82:3

Tradition, Liturgical practice ሆኑ Councils ስህተት ሊገኝባቸው ይችላል። ምክንያቱም የትውፊት transmissionን በተመለከትን ጊዜ በHuman interpretation, fallibility እና በculture influence የታሰረ በመሆኑ original መልዕክቱ distort ሊሆን ይችላል። በተለይም Tradition እና Liturgical practice በዘመናት መሐል የተለያየ ብርዘት እና ለውጥ ሊገባባቸው የሚችሉ ናቸው። ለምሳሌ ያክል በካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የጳጳሳቱ መብት እያደገ እየተሻሻለ በመምጣት ወደ papal Infallibility በመጨረሻም ወደ ስህተት መምጣታቸው የሚዘነጋ አይደለም። በተጨማሪም በነገረ ማሪያም ያላቸውን ዶክትሪን እጅጉን እየለጠጡ በመምጣታቸው ወደ Immaculate conception(አንዳንድ ኦርቶዶሳውያንም ይህንኑ አስተምሮ ይቀበላሉ) እንዳመሩ እንመለከታለን። የMonastic practice እና Ascetic tradition, የPurgatory concept ሌላው የሚጠቀሱ ጉዳዮች ናቸው። በኦርቶዶክሱም ሆነ በካቶሊኩም የሚስተዋለው የመጽሐፍ ቅዱስ የቀኖና ችግር ስንመለከት ትውፊት በዘመናት መካከል ሊቀያየር እና ሊበከል የሚችል ጉዳይ ሁኖ እናገኘዋለን። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም በማቴዎስ ወንጌል 15:3 ላይ በdivine revelation ላይ rooted ያልሆነውን የአይሁዳውያንን ትውፊት criticize ሲያደርግ እንመለከታለን። የSola Scriptura Concept እነዚህ ሁሉ Tradition እና Liturgical practice በሕጸጽ አልቦው እና በአይለወጤው በእስትንፋሰ እግዚአብሔር ቃል መሠረት ተመዝነው መጥራት ያለባቸው ጉዳዮች መሆናቸውን የሚገልጽ ክርስቲያናዊ መርህ ነው። ስለዚህ Traditions are subject to scrutiny against God's Word, implying that they are not inerrant so inerrant የሆነው መጽሐፍ ቅዱስ ትክክለኛው ሚዛን እና Highest Authority ያለው አፊዎተ ቃል ነው።

በሚቀጥለው Consensus of fathers conceptን እና የSola scriptura Interpretation of scripture Framework የምንዳስስ ይሆናል። ተባረኩ!

@Yeshua_Apologetics_Ministry