Yeshua Apologetics Ministry
2.47K subscribers
62 photos
4 videos
6 files
89 links
➟የሹዋ ዐቅበተ እምነት አገልግሎት አላማ

ከክርስትና እምነት አንጻር ደርዛቸውን የጠበቁ ስነ መለኮታዊ ፍልስፍና፤ አመክንዮአዊና ታሪካዊ ጽሑፎችን ማቅረብ

በክርስትና ላይ የሚነሱ የተቃውሞ ሀሳቦችንና የኑፋቄ ትምህርቶችን መመከት

የሌላውን እምነተ መርህ ከሎጂክና ከታሪካዊ ዳራዎች አንጻር መመርመር



@Yeshua_Apologetics_Ministry

Download Telegram
መዝሙር 9
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ አቤቱ፥ በልቤ ሁሉ አመሰግንሃለሁ፥ ተአምራትህንም ሁሉ እነግራለሁ።
² በአንተ ደስ ይለኛል፥ ሐሤትንም አደርጋለሁ፤ ልዑል ሆይ፥ ለስምህ እዘምራለሁ

መልካም እለተ ሰንበት
@Yeshua_Apologetics_Ministry
ትንሽ ቆየት ብሏል

ከአንድ ሙስሊም ጋር ውይይት ገጠምንና መጽሐፍ ቅዱስ ይጋጫል አለ። የድሮ ማስታወሻዬን አወጣሁና ዘርዝር አልኩት ዘረዘራቸው።(በሰዓቱ ገና ወደ ውይይቱ ዓለም መቀላቀሌ ነበርና የምችለውን መለስኩና ገሚሱን ለሌላ ጊዜ አስተላለፍኩ😁)

እንደ እኔ የነበረ ጓደኛዬ ሙስሊሞች ከ100 በላይ ግጭት አለ፤ መጽሐፍ ቅዱስ ይጋጫል ብለው የሚጠቅሷቸው ጥቅሶች ሁሉ ግን መልስ መስጠት ይቻላል ወይ? አለኝ። በደንብ!

በቅርቡ ብቅ የምናደርጋት _ _ _ _ አለች ለማለት ነው😊
@Yeshua_Apologetics_Ministry
የዮሃንስ ወንጌል አጭር ሐተታ
መግቢያ

➥የዮሃንስ ወንጌል በዘመናት መሐል በቤተክርስቲያን ተወዳጅነቱን ጠብቆ የቆየ መጽሃፍ ሲሆን በሌሎች ለዘብተኛ ምሁራን ደግሞ “አራተኛው ወንጌል” በመባል ይጠራል። ከጥንታዊት ቤተክርስቲያን አባቶች መካከል አንዱ የሆነው ቀለሜንጦስ ዘእስክንድሪያ ደግሞ መንፈሳዊ ወንጌል በማለት አቆላምጦታል [1]፤ ይህንን ያለበትም ምክኒያት ዮሃንስ ወንጌሉን የጻፈው በመንፈስ ቅዱስ አነሳሽነት ነው ብሎ ስላመነ እንደነበር የአውሳብዮስ ዘቂሳርያ ዘገባ ያሳያል። ወንጌሉ ምንም ያህል አከራካሪ ጉዳዮች ቢኖሩበት፤ ከዘመናውያኑ ሥነ መለኮት ምሁራን አንዱ የሆነው ኮሊን ክሩዝ ደግሞ “ኁልቆ መሳፍርት ለሌላቸው የክርስትና ትውልዶች መነሳሳት የፈጠረና በስርዓት ላጠኑት ሁሉ ታላላቅ ሽልማቶችን ያስታቀፈ” [2] በማለት መስክሮለታል።

የጸሃፊው ማንነት

➥የወንጌሉን ትክክለኛ ጸሃፊ በተመለከተ የተለያዩ አመለካከቶች ቢኖሩም በሐዋርያው ዮሃንስ ስለመጻፉ የሚቀርቡ ሃሳቦች ከሌሎች ይልቅ ተጨባጭነት አላቸው። በቅድሚያ የመጽሃፉን ውስጣዊ ማስረጃዎች (internal evidences) እንመልከት። ጸሃፊው የአረማይክ ቋንቋ ችሎታ ያለው አይሁዳዊ ስለመሆኑ ለሚጠቅሳቸው አንዳንድ የእብራይስጥና አራማይክ ቃላት ትርጉም ማስቀመጡ ምስክር ነው፤ የአይሁድን ወግና ስርአት ጠንቅቆ የሚያውቅ ሰው መሆኑን የገዛ ጽሁፉ ያሳያል (ዮሃ 4፡ 9፣ 20)፤ ስለ መጀመሪያው ክፍለ ዘመን የእስራኤል መልክአ ምድራዊ አቀማመጥ በትክክል እንደሚያውቅም ከወንጌሉ ላይ መረዳት ይቻላል (ዮሃ 1፡44፣ 2፡1፣ 4፡5፣ 4፡21፣ 9፡7፣ 11፡18፣ 18፡1)፤ እንደዚሁም የአይን ምስክርና የኢየሱስ የቅርብና ተወዳጅ ሰው እንደነበርም ይናገራል (ዮሃ 1፡14፣ 19፡35) [3]።ከኢየሱስ የቅርብ ደቀ መዛሙርት መሃል ያዕቆብ ብዙም ሳይቆይ ስለሞተ፤ እንዲሁም ጴጥሮስ ቶማስና ፊሊጶስ በሶስተኛ መደብ እየተጠሩ ስለተዘገቡ የጸሃፊው ማንነት ዮሃንስ የመሆኑ እውነታ የበለጠ ተአማኒነት አግኝቶአል። ከመጽሐፍ ቅዱስ ውጪ ያሉ ማስረጃዎችን (External Evidences) በአጭሩ ስንዳስስ ደግሞ የጥንት የቤተክርስቲያን አባቶችን ምስክርነት እናገኛለን።ከላይ እንደተመለከትነው አውሳብዮስ ዘቂሳርያ በዘገበው መሠረት የእስክንድርያው ቀለሜንጦስ ይህንን ወንጌል መንፈሳዊ ወንጌል ብሎ ጠርቶታል። ቀለሜንጦስ ወንጌሉን በዚህ ስም የጠራውም ዮሐንስ ወንጌሉን የጻፈው በደቀ መዛሙርት ተገፋፍቶና በመንፈስ ቅዱስ ተነሳስቶ እንደሆነ በማመኑ እንደነበረ አውሳብዮስ ጨምሮ ዘግቧል [4]። በመሆኑም ቀለሜንጦስ አራተኛው ወንጌል የተጻፈው በሐዋርያው ዮሐንስ እንደሆነ ያምን ነበር። 200 ዓ.ም አካባቢ እንደጻፈ የሚገመተው ኢራኒየስ ወንጌሉን የጻፈው የተወደደው ደቀ መዝሙር ዮሐንስ መሆኑንና የጻፈውም በኤፌሶን ሳለ እንደነበረ ተናግሯል [5]። በተጨማሪም የተወሰኑትን የአዲስ ኪዳን መጻሕፍት ዝርዝር ይዞ የተገኘውና ከ 180-200 ዓ.ም ድረስ እንደተጻፈ የሚገመተው የሙራቶሪያን ጽሁፍ አራተኛውን ወንጌል በዮሐንስ እንደተጻፈ ይመሰክራል። ዮሐንስ ወንጌሉን እንዴት ጻፈው? ለሚለው ጥያቄ ይህ ጽሁፍ ተአማኒ ዝርዝር ባይኖረውም ወንጌሉ በተጻፈባቸው አመታት ውስጥ ጸሃፊው ዮሐንስ መሆኑ ይታመንበት እንደነበር ያሳያል [6]። በመሆኑም ከውስጣዊ ማስረጃዎች ጸሃፊው ፍልስጤም ምድር ውስጥ የሚኖር አይሁዳዊ መሆኑን፣ የኢየሱስ የአይን ምስክር መሆኑን፣ከአስራ ሁለቱ ደቀ መዛሙርት አንዱ መሆኑንና ከጽሁፉ ዝርዝሮች በመነሳት ጸሃፊው ዮሐንስ እንደሆነ መገመት እንደሚቻል ስንረዳ ከውጫዊ ማስረጃዎች ደግሞ ወንጌሉ ለተጻፈበት ዘመን የሚቀርቡ አባቶችና ተጨማሪ ጽሁፎች የዮሐንስን ጸሐፊነት እንደሚደግፉ መገንዘብ ይቻላል። የዮሐንስ ወንጌል በራሱ በዮሐንስ መጻፉን የሚጠራጠሩ ምሁራን ቢኖሩም ከላይ ባነሳናቸው ማስረጃዎች መሠረት ጸሃፊው ሐዋርያው ዮሐንስ መሆኑን ተቃውሞ በብቃት የሚቆምና ተለዋጭ ጸሃፊ በርግጠኝነት የሚያቀርብ መከራከሪያ ግን ሊገኝ አልቻለም።

የተጻፈበት ዘመንና ስፍራ

➥ልክ እንደ ጸሃፊው ማንነት ሁሉ በዘመናችን ምሁራን ዘንድ ወንጌሉ መቼ እንደተጻፈ የማያባራ ክርክር ይደረጋል። አንዳንዶች የተጻፈው በ2ኛው ክፍለ ዘመን መካከለኛ አመታት፤ ማለትም 150 ዓ.ም አካባቢ እንደሆነ በማንሳት ይከራከራሉ። ይሁን እንጂ የሥነ ቁፋሮ (Archaeology) ጥናቶች የሚያሳዩት የዮሐንስ ወንጌል የተጻፈው በመጀመሪያው ክፍለ ዘመን መገባደጃ ላይ መሆኑን ነው። የዮሐንስ ወንጌል የመጀመሪያው እደ-ክታብ Papyrus 52 የሚባል ሲሆን የምዕራፍ 18ን የተወሰኑ ክፍሎች የያዘና በ130 ዓ.ም አካባቢ እንደተጻፈ የሚገመት ቁራጭ ብራና ነው። ቀጥሎም ከምዕራፍ 1-14 ድረስ ያለውን አብዛኛውን ክፍልና የቀሩትን ምዕራፎች በከፊል የያዘው Papyrus 66፤ እንዲሁም ከምእራፍ 1-11 እና ከ12-15 ድረስ የያዘው Papyrus 75 ከጥንታዊ እደ ክታባት ይመደባሉ። እነዚህ
እደ ክታባት ከሁለተኛው ክፍለ ዘመን መጨረሻ ይመዘዛሉ [7]። እንግዲህ እስካሁን የሚታወቀው የመጀመሪያው የወንጌሉ ቅጂ (P 52) የተጻፈው እንደተገመተው በ 130 አካባቢ ከነበረ የመጀመሪያው ጽሁፍ የተጻፈው በመጀመሪያው ክፍለ ዘመን መሆኑ ግድ ነው። ወንጌሉ የት ተጻፈ? ለሚለው ጥያቄ ደግሞ በቀለሜንጦስ ዘእስክንድርያንና በኢራንየስ ትውፊቶች ላይ መደገፍ ግድ ይለናል። ቀለሜንጦስ እንደጻፈው ዮሐንስ ከፍጥሞ ደሴቱ ስደት ወደ ኤፌሶን የተመለሰው ንጉሡ ዶሚሽያን ከሞተ በኋላ (ከ 81-96) ሲሆን ኢራኒየስ ደግሞ ሐዋርያው እስከ ትራጃን ንግስና ዘመን ድረስ (ከ98-117) እዚያው ኤፌሶን እንደነበረ ይናገራል [8]። ይህም ወንጌሉን በዚያ ጊዜ (በመጀመሪያው ክፍለ ዘመን መጨረሻ) በኤፌሶን ሳለ ጽፎታል የሚል ግምትን አሳድሯል። ስለዚህም የዮሐንስ ወንጌል ከ80-90 ዓ.ም ሐዋርያው ዮሐንስ በኤፌሶን ሳለ የጻፈው ወንጌል መሆኑ በብዙዎች ዘንድ ተቀባይነት አለው።

የዮሐንስ ወንጌል ዋና ዋና ይዘቶች

➥በመጀመሪያው ምእራፉ ስለዋና ገጸ ባህርዩ ማንነት በዝርዝር ይናገራል። ይህም ገጸ ባህርይ በመጀመሪያ ከእግዚአብሔር ጋር
የነበረው በፍጥረት ስራ ላይ ተሳታፊ የነበረውና በኋላም ሰው ሆኖ የመጣው ኢየሱስ መሆኑን ይናገራል።

➥እስከ ምእራፍ 12 ድረስ ሰፋ ባሉ ንግግሮችና በተአምራት የተገለጠውንና በልጁ ለሚያምኑ ሁሉ የዘለአለም ህይወት የሚሰጥ
አባቱን የተረከውን ኢየሱስን በተዋበ የመክፈቻ ንግግር መልክ እናገኛለን።

➥ከምእራፍ 13 – 20 ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን ለቀጣይ ዘመናት ሲያዘጋጅ፣ ሲመክራቸውና ሲጸልይላቸው፣ እንዲሁም ስቃዩን፣ ስቅለቱንና ሞቱን እንዲሁም ትንሳኤውን ያስቃኘናል።

➥ምእራፍ 21 ተጨማሪ የትንሳኤውን ምስክርነቶች፣ ለጴጥሮስ የተሰጠውን ተልአኮ ከሞቱ ትንበያ ጋር፣ እንዲሁም የተወደደውን ደቀ መዝሙር ምስክርነት ያስቃኘናል [9]።

የዮሃንስ ወንጌል ልዩ ባህርያት

➥በሶስቱ ተመሳሳይ ወንጌላት ዘገባ የኢየሱስ አገልግሎት ትኩረት ያደረገው በገሊላ ሲሆን የዮሃንስ ወንጌል ግን በብዛት የኢየሱስን የይሁዳና የኢየሩሳሌም አገልግሎት ያስቃኘናል።
ተመሳሳዮቹ ወንጌላት የኢየሱስን ምሳሌያዊ ንግግሮች፣ የእግዚአብሔርን መንግስት የተመለከቱ ስብከቶቹን፣ እንዲሁም በተለያዩ ርእሰ ጉዳዮች ላይ ያደረጋቸውን ንግግሮች (ለምሳሌ ስለ ምጽዋት፣ ስለጋብቻና ፍቺ፣ ስለግብር ስለጭንቀት፣ ስለሃብት፣ ወዘተ...) ሲያስነብቡን የዮሃንስ ወንጌል ግን “እኔ... ነኝ” በሚሉ ሃረጋት በሚጀምሩ ኢየሱስ ስለራሱ በተናገራቸው ንግግሮች ይታወቃል። የዮሃንስ ወንጌሉ የኢየሱስ ንግግር ከሶስቱ ተመሳሳይ ወንጌላት በተለየ ከላይና ከታች፣ ብርሃንና ጨለማ... ወዘተ በሚል ሁለት ነገሮችን በተነጻጻሪነት በሚመለከት አጻጻፉ ይታወቃል። በዮሃንስ ወንጌል በተዘገበው የኢየሱስ አገልግሎት የሚገኙት ክስተቶች በሌሎቹ ወንጌላት ውስጥ አይገኙም። ማለትም የወይኑ ተአምር (2: 1-11)፣ ከኒቆዲሞስ ጋር ያደረገው ጭውውት (3:1-13)፣ የሳምራዊቷ ሴት ታሪክ (4:1-42)፣ የቤተዛታው ኩሬ ፈውስ (5:1-18)፣ የሰሊሆም መጠመቂያው ፈውስ (ምእራፍ 9)፣ የአላዛር ከሞት መነሳት (ምእራፍ 11)፣ ኢየሱስ የደቀ መዛሙርቱን እግር ማጠቡ (13: 1-11)፣ እንዲሁም ኢየሱስና ጲላጦስ ያደረጉት ዘለግ ያለ ንግግር (18:28-19:22) የሚገኙት በዮሃንስ ወንጌል ብቻ ነው [10]

የዮሐንስ ወንጌል ስነ መለኮት

➥የዮሐንስ ወንጌል በውስጡ ብርሃንና ጨለማ፣ ሞትና ህይወት የሚሉ ሐሳቦች በተነጻጻሪነት ተደጋግመው ተነስተዋል፤ ይህም የኖስቲክ እሳቤን የያዘ ወንጌል እንደሆነ እንዲታሰብ ምክንያት ሆኗል። ነገር ግን የኖስቲክ መምህራን ስጋን ሁሉ እንደ እርኩስ ነገር ስለሚቆጥሩ አምላክ በስጋ እንደመጣ የሚናገረው የዮሐንስ ወንጌል ከእነርሱ አስተምህሮ በተቃራኒ እንደሚቆም ለመረዳት አይከብድም[11]። ይህ ወንጌል ልዩ የሆነ ነገረ ክርስቶስን ይዟል፤ ይህንንም ኢየሱስ አባቱን ለመተረክ ከሰማይ የመጣ፤ ተግባሩንም ተወጥቶ ወደመጣበት የተመለሰ የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ በአግባቡ በማሳየት ገልጦታል። (ዮሐ 1:18፣ 3:13፣ 6፡33፣ 38)። በስጋ የተገለጠ አምላክ የሚልን ነገረ ክርስቶስ በዋናነት የምናገኘውም እዚሁ ወንጌል ውስጥ ነው። መንፈስ ቅዱስ በታሪካዊው ክርስቶስ (Historical Jesus) የተገለጠውን እውነት ወደ አማኞች በማምጣት ተግባሩ ተገልጧል። የዩሐንስ ወንጌል በቃልና በስራ ለእግዚአብሔር የመታዘዝን ስነ ምግባር በኢየሱስ በኩል ያስተምራል። ዋናውን የኢየሱስን ትእዛዝ ፍቅርንና ትህትናን በአማኞች መሃል ያስተዋውቃል (ዮሐ 13:14)። ይህንንም ኢየሱስ ራሱ በተግባር በማድረግ አስተምሯል (ዮሐ 15:12-14) [12]

ወንጌሉ የተጻፈበት አላማ
 
➥ለዚህ ጥያቄ እንደ መልስ የሚቀርበው የመጀመሪያው መላ ምት ዮሐንስ ወንጌሉን የጻፈው ለሶስቱ ወንጌላት ተጨማሪ ድጋፍ ይሆን ዘንድ ነው ይላል። በዚህ መላ ምት መሠረት ሐዋርያው ከእርሱ በፊት የተጻፉትን ሶስቱን ወንጌላት በተመለከተ ጊዜ ይዘታቸው አላረካውም፤ ስለዚህም ወንጌሉን በዚህ መልኩ ጻፈው። ነገር ግን ወንጌሉ በሶስቱ ወንጌላት ላይ ጥገኝነት ባለማሳየቱ ይህ መላ ምት ብዙውን ጊዜ ውድቅ ይደረጋል። ሌሎች ደግሞ ስጋ ሁሉ ርኩስ ነው የሚለውን የኖስቲካውያን ትምህርት ለመዋጋት እንደተጻፈ ይናገራሉ። ነገር ግን የኖስቲክ ትምህርት የሁለተኛው ክ/ዘ ትምህርት እንደመሆኑ በመጀመሪያው ክፍለ ዘመን የተጻፈውን ወንጌል እንደ ውጊያ መሳሪያነት እንዳንመለከተው ይገዳደራል። ሌላው ታሳቢ አላማ ደግሞ ዮሐንስ ወንጌሉን የጻፈው የማያምኑ አይሁዳውያንን ለመዋጋት ነው ይላል። እንደ ማስረጃም “አይሁድ” የሚለው ቃል ከሌሎች ጸሃፊያን ይልቅ በዮሐንስ ጥቅም ላይ መዋሉን ያቀርባሉ። ነገር ግን ይህ የወንጌሉ አንድ ትኩረት እንጂ ዋና አላማ አይደለም በማለት ውድቅ የሚያደርጉት ምሁራን ይበዛሉ [13]። የወንጌሉ አላማ በዚህ ደረጃ የሚያመራምር ሆኖ ቢገኝም ጸሃፊው ግን ለአንባቢያኑ ሊናገር የፈለገውን ነገር በግልጽ አስቀምጧል። ኢየሱስ እርሱ በአባቱ ተልኮ ከሰማይ የመጣ፤ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ መሆኑን ማስረዳት የዮሐንስ ወንጌል ዋናው አላማ ነው (ዮሐ 20:30-31)።

ለዛሬዎቹ አማኞች የዮሐንስ ወንጌል የሚሰጠን ጥቅም 

➥ልክ ቀድሞ ለመጀመሪያዎቹ ተደራሲያን ጠቅሞ እንደነበረው ለኛ ለዛሬዎቹ አንባቢዎችም የኢየሱስ ክርስቶስን የእግዚአብሔር ልጅነት በማስረዳት ነገረ ክርስቶሳችንን እንድንቃኝ ያስችለናል። እንደዚሁም ከእግዚአብሔር ጋር ትክክለኛ ግንኙነት መመስረት የሚቻልበትን የመታዘዝ ልብ ዛሬም ከኢየሱስ አገልግሎት እየተማርን እንድንተገብረው ያግዘናል። በተጨማሪም አማኞች እርስ በርሳቸው የመዋደዳቸውንና በአንድነት የመኖራቸውን ጥቅም ሲያስተምረን መንፈስ ቅዱስ በእኛ ህይወት ውስጥ የሚሰራውን ታላቅ ስራም በየእለቱ ያስገነዝበናል።

ዋቢ መጻሕፍት
[1] Eusebius of Caesarea, Ecclesiastical History Book 6, Chap. 14, Verse 7
[2] Kolin J. Kruse; TNTC Vol. 4, John: an introduction and commentary; 2003; page 20
[3] የአዲስ ኪዳን ቅኝት፤ ሜሪል ሲ. ቴኒ (የአማርኛው ትርጉም)፣ የኢትዮጵያ ቃለ ህይወት ቤተክርስቲያን፤ 1998 ዓ.ም
[4] THE GOSPEL ACCORDING TO JOHN (REVISED); Leon Morris: 1971: page 53
[5] JOHN THE NIV APPLICATION COMMENTARY; GARY M. BURGE, 1973: Page 28
[6] Exposition of the Gospel according to John; William Hendriksen; Baker book house: 1953: page 29
[7] The Gospel according to John- The pillar New Testament commentary ; D.A Carson; Page 31
[8] Kolin J. Kruse; TNTC Vol. 4, John: an introduction and commentary; 2003; page 36
[9] Kolin J. Kruse; TNTC Vol. 4, John: an introduction and commentary; 2003; page 20
[10] [John: a commentary; Marianne Meye Thompson: The New Testament library: 2015; page 2-3]
[11] The Gospel of John: a commentary; Rudolf Bultmann: 1971: page page 8
[12] D. Moody Smith; John - Abingdon New Testament Commentaries; 1999 page 46
[13] THE GOSPEL ACCORDING TO JOHN (REVISED); Leon Morris: 1971: page 49

@Yeshua_Apologetics_Ministry
ምሳሌ 8:22
. እና
ኒቂያ ጉባኤ

ኢየሱስ ፍጡር ነውን? ከጽርዕ ትርጓሜና ታሪካዊ ዳራው

Uploading.....
@Yeshua_Apologetics_Ministry
ተለቋል!

ኢየሱስ ፍጡር ነውን?

ምሳሌ 8:22 እና ጉባኤ ኒቂያ

ዩቱዩብ፦
https://youtu.be/BNROfoMjfZg?si=JhcJZWRdZy1Fh04j

ሼር ይደረግ
@Yeshua_Apologetics_Ministry
ዛሬ ደሞ!

አንዱ የኦርቶዶክ አቃቤ በድጋሚ
መጽሐፍ ቅዱስ የሚሳሳት ነው፤
በእጃችን ያለው መጽሐፍ ኮራፕት ነው።
(የተበረዘ የሚል ድምዳሜ ያለው ንግግር)
አዳልጦት ነው ስል ድጋሚ ደገመው።
ደግሞ እንወያይ ብሎ ጥሪ እያረገ ነው።
ሙስሊም ነኝ ብሎ የሚያምን ከሆነ
በTextual Criticism ላይ የምንወያየው ይሆናል!

ጥሪውስ ይሁን እሺ ቆይ ተሟጋቾቹ
ኦርቶዶክሱ አቃቤ እርሱ መጽሐፍ ቅዱስ ተበርዟል ሲል...

ተሟጋች ያላቸው ሰዎች አልተበረዘም እያሉ ነው የሚወያዩት?

what?😂

ወይ ሃይ በሉት(ኢትዮጲያዊው ባርት ሄርማን) ልለው ነው። ከማለቴ በፊት ወይ አድርሱለት!😂😂
@Yeshua_Apologetics_Ministry
የአዲስ ኪዳን እደክታባት(MSS) ተዓማኒ አይደሉምን? የአቃቤውን ንግግር ላስተላለፉ ሙስሊም አቃቤያን

ክፍል ፩

ጥያቄ፦ አንድ ጽሑፍ ጥንታዊ ነው፣ እናም ተዓማኒ ነው የሚባለው እንዴት ነው? የአዲስ ኪዳንስ መጽሐፍ እንተማመንበታለን?

መልስ፦ ምሑራን የአንድን ጥንታዊ መጽሐፍ ተዓማኒነት ለማረጋገጥ ነፃ በሆነ መንገድ የተገለበጡትን ኮፒዎች ብዛት፣ ጥራትና በመካከላቸው የሚገኘውን ስምምነት ይገመግማሉ እንጂ የመጀመርያው ጽሑፍ የግድ መገኘት አለበት አይሉም፡፡ እንደርሱ ዓይነት መመዘኛ ቢጠቀሙ ኖሮ ከጥንት መጻሕፍት መካከል አንዱም ተዓማኒ ባልሆነ ነበር፡፡ በኮፒዎች ብዛት አዲስ ኪዳን ከእርሱ በፊትም ሆነ በኋላ ከተጻፉት ጥንታውያን ጽሑፎች ጋር ሊነፃፀር በማይችልበት ሁኔታ በእጅጉ የላቀ በመሆኑ ለተዓማኒነቱ አስተማማኝ ዋስትና ነው፡፡

ይህንን በተመለከተ ዕውቅ ክርስቲያን አቃቤ ዕምነት የሆኑት ፕሮፌሰር ጆሽ ማክዱዌል እንዲህ ይላሉ፡-

"...ከ5,686 በላይ የሚሆኑ የታወቁ የአዲስ ኪዳን የግሪክ ጥንታውያን የእጅ ጽሑፎች አሉ፡፡ በተጨማሪም 10,000 የላቲን ቩልጌቶችና ሌሎች 9,300 ቀዳሚያን ቅጂዎች፣ በአጠቃላይ ከዚያ ካልበለጡ ወደ 25,000 የሚሆኑ ጥንታውያን የእጅ ጽሑፎች አሉ፡፡ ከጥንት መዛግብት መካከል አንዱም እንኳ ይህንን ያህል ቁጥርና የማረጋገጫ ብዛት ወደ ማስመዝገብ የቀረበ የለም፡፡ በንፅፅር 643 የእጅ ጽሑፎች ብቻ ያሉት የሆሜር ኢሊያድ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡...."

Josh McDowell, Evidence That Demands a Verdict, p. 34

ከነዚህ እውነታዎች በመነሳት ለጠያቂዎቻችን ተከታዮቹን ጥያቄዎች እናቀርባለን፤ በማስረጃ የተደገፈ ምላሽም እንዲሰጡን እንጠይቃቸዋለን፡-

1) የመጽሐፍ ቅዱስን ያህል ዕድሜ ያለው በኩረ ጽሑፉ (autograph) ተጠብቆ ያለ አንድ መጽሐፍ ይጥቀሱልን፡፡

2) በእጅ ጽሑፎች ሥልጣን ከመጽሐፍ ቅዱስ የላቀ ጥንታዊ ጽሑፍ የሚያውቁ ከሆነ ይጥቀሱልን፡፡

3) የመጀመርያው ጽሑፍ መኖሩ ተመራጭ መሆኑን ከማመን በዘለለ አንድ ጥንታዊ መጽሐፍ ተዓማኒ ለመሆን የመጀመርያው ጽሑፍ መኖሩን እንደ ቅድመ ሁኔታ የሚያነሳ አንድ የታሪክ ምሑር ይጥቀሱልን፡፡

4) በመሐመድ ዘመን ከተጻፉት ቀዳሚያን የቁርአን ጽሑፎች መካከል እስከ እኛ ዘመን የኖረ አንድ ቁራጭ እንኳ ካለ ያሳዩን፡፡

5) በመሐመድ ዘመን የተጻፉትን ማሳየት ካልቻሉ ጥያቄውን ቀለል እናድርገውና በአቡበከር ዘመን ተሰብስቦ በሐፍሷ ቤት ተቀምጦ የነበረው ሙሳሒፍ ካለ ያሳዩን፡፡

6) እርሱንም ማድረግ ካልቻሉ አሁንም እናቅልልላችሁና ከኡሥማን አምስቱ ኮፒዎች መካከል እስከዚህ ዘመን የዘለቀ ካለ ያሳዩን፡፡
------
🔥 ነጥብ አንድ፣ ሁለትና ሦስት ለኦርቶዶክሱም አቃቤ ይሁንልን።
------

እመለስበታለን! ለዛሬ ይቺ ትሁነን።

@Yeshua_Apologetics_Ministry
ጥሩ መጽሐፍ እናጋራችሁ😊 Defending Inerrancy: Affirming the Accuracy of Scripture for a New Generation የNorman Geisler እና የWilliam Roach የመጽሐፍ ቅዱስን ሕጸጽ አልቦነት(the Bible, in its original manuscripts, is without error in everything it affirms, whether doctrinal, historical, or scientific.) በtraditional evangelical belief የዳሰሱበት ድንቅ መጽሐፍ ነው። ኮምኩሟት በተለይ ለሆነ ሰው ላኩለት ማወቅ የሚሻ ከሆነ😁

@Yeshua_Apologetics_Ministry
Defending_Inerrancy_Affirming_the_Accuracy_of_Scripture_for_a_New.pdf
4.2 MB
አጠር ያሉ ጽሑፎች የምናጋራችሁ ይሆናል!
እስከዛው ይቺን pdf እያነበባችሁ ተባረኩበት።(እንደው ሃርድ ኮፒ ቢኖራችሁ ከሸልፋችሁ ላይ አይጥፋ ስልን አበሰርን😁)

soon.....

@Yeshua_Apologetics_Ministry
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ወገናችን አኬ Matthew Barrett ጠቅሶ ስለInerrancy of Scripture scholastic interpretationኑን ሲናገር እንመለከታለን። በመጀመሪያ Matthew Barrett biblical inerrancy ላይ ድምጻቸውን ከሚያሰሙ from prominent theologian ጥብቅ ተሟጋቾች መሃል አንዱ ነው። ስለoriginal manuscripts ጥበቃ እና ምንባባዌ ሕያሴም ላይ እንዴት ወደ Autograph writings መድረስ እንደምንችል ሰፋ ያለ ትንታኔን እና ማብራሪያዎችን የለገሰ ፕሮቴስታንት ስኮላር ነው። በተጨማሪም The Authority of Scripture ላይም ያለው አቋም የጠነከረ ነው። Matthew Barrett የChicago Statement on Biblical Inerrancy support የሚያደርግ እና ከዚሁ መርህ ጋር ሀሳቡን እና አመለካከቱን align ያደረገ scholar ነው። ነገር ግን ወንድማችን አኬ ይህንን ሰው ይጠቅስ እና "To believe in inerrancy is to affirm that the true God has breathed out a true Word" የምትለዋን ሐሳብ ብቻ ቆርጦ በማውጣት ሙሉውን የMatthew Barrett ሐሳብ በቁንጽል ለማሳየት ይሞክራል😊 በተጨማሪም አኬ "vast majority of textual variants መኖሩ አሁን ላይ inerrant የሆነ ቅዱስ መጽሐፍ እንደሌለ የሚያሳይ ማስረጃ ነው" በማለት ይናገራል። እንዴ አኬ ምን ሁኖ ነው የBarrett  መጽሐፍ አንብቦ የለ እንዴ ይሄንን እንዴት መረዳት አቃተው😁 Barrett እጅጉን ጥርጣሬ የሌለው እውነት ከሚለው ነገር መሐል አንዱ  በtextual criticism ጥናት ድጋፍ ወደ original text of Scripture መቅረብ እንደምንችል ነው። ይህ ማለት original text of Scripture (may be አኬም የሚያምን ይመስለኛል😊በinerrancyነቱ ላይ የሚያጠራጥረን ጉዳይ የለም። ስለዚህ በtextual criticism ጥናት ድጋፍ ወደ original text of Scripture መቅረብ የምንችል ከሆነ variation of manuscript ምንም ስጋት ሊሆንብን አይገባም። በተጨማሪም በbiblical inerrancy ላይ የሚቀርብ issue መሆን የለበትም።

@Yeshua_Apologetics_Ministry
Barrett, Matthew. God's Word Alone: The Authority of Scripture. Zondervan, 2016

« textual variations in the copies do not imply that the original manuscripts contained errors. These variations are seen as part of the natural process of transmission over time, but they do not undermine the truthfulness of Scripture as it was originally given. the existence of textual variants should not shake one's confidence in the inerrancy of the Bible, as the original text remains reliable and intact, even if minor discrepancies exist in the copies »

—-Matthew Barrett—-
በዚህ ሳምንት ከሚለቀቁ ቪዲዮዎች መካከል
ለመኮምኮም ተዘጋጅታችኋል?😊

ሲለቀቅ እንዲደርሳችሁ፦ "ይጫኑ"

@Yeshua_Apologetics_Ministry
« Inerrancy & Sola Scriptura »

«ቅዱሳት መጻሕፍት ሁሉ #የእግዚአብሔር_መንፈስ_ያለባቸው ናቸው፤ ለማስተማር፣ ለመገሠጽ፣ ለማቅናት በጽድቅም መንገድ ለመምከር ይጠቅማሉ» ----2ኛ ጢሞ 3፥16 (አዲሱ መ.ት)

Sola scriptura(መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ) ለክርስትና እምነተ መርሕ መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ የማይሳሳትና ሊሳሳት የማይችል ባለሥልጣን እንዳለው የሚገልጽ ክርስቲያናዊ መርሕ ነው። ይሄንን ሐሳብ ብርሐነ አለም ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ለመንፈሳዊ ልጁ ለጢሞቴዎስ በጻፈለት መልዕክት ላይ <<ቅዱሳት መጻሕፍት ሁሉ>> እስትንፋሰ እግዚአብሔር (ቴዎኔዩስቶስ/θεόπνευστος) መሆናቸውን ሲነግረው እንመለከታለን። ቅዱሳት መጻሕፍት እስትንፋሰ እግዚአብሔር (ቴዎኔዩስቶስ/θεόπνευστος) ወይም አፊዎተ እግዚእ ማለትም በቀጥታ መለኮታዊ ግልጠት መሆናቸውን እና ከዚህም የተነሳ እውነተኛ እና ሕጸጽ አልቦ ናቸው ብለን እናምናለን። የቤተ ክርስቲያን አበው ይህንኑ ሐሳብ ሲደግፉ ይስተዋላል። የአራተኛው መቶ ክፍለ ዘመን አባት ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ(John Chrysostom) ክፍሉን በድርሳኑ ላይ ሲያብራራ ቅዱሳት መጻሕፍት አፊዎተ እግዚእ መሆናቸውን እና ለአማኞች ትክክለኛ የቅድስና እና የህይወት መንገድ መሮች መሆናቸውን ይናገራል(Homilies on 2 Timothy)። ቅዱስ ሔሬኔዎስ ዘሊዮን(Irenaeus of Lyons) በመድፍነ መናፍቃን መጽሐፉ ላይ ቅዱሳን መጻሕፍት እስትንፋሰ እግዚአብሔር እና የበላይ ባለስልጣን መሆናቸውን በመግለፅ እውነተኛው የክርስትና አስተምህሮ መሠረት የሆኑ  እና ሐሰተኛውን አስተምህሮ የምንከላከልባቸውም (የምንመክትባቸው) ጭምር እንደሆኑ ይገልጻል (Against Heresies)።  ቅዱሳት መጻሕፍት የእግዚአብሔር እስትንፋስ በመሆናቸው ስለ እውነት ፤ ክርስትያናዊ የሕይወት መርህ እና ድነት አስፈላጊ የሆኑትን ሥነመለኮታዊ አስተምህሮ ሁሉ በውስጡ ያካተቱ በመሆናቸው ለዚህም አስተምህሮ ብቁ ባህሪዎት እንዳላቸው እንመለከታለን። ቅዱስ አትናቴዎስ (Athanasius of Alexandria) በክታቡ እንዲህ ሲል ይናገራል፦

"The Holy Scriptures, given by inspiration of God, are of themselves sufficient toward the discovery of truth."

(Against the Heathen, 1:3)


ነገር ግን የእግዚአብሔር ቃል ለክርስቲያን ሥነመለኮት ብቁ ነው ስንል በራሱ ትውፊትን የሚያገልል ወይም የሚቃወም ተደርጎ በፍጹም መታሰብ የለበትም። ለትውፊት, ለአምልኮ ሥርዓት ሆኑ ለጉባኤያት አስተምህሮ እና እውነተኝነት ትክክለኛው መመዘኛ መጽሐፍ ቅዱስ መሆኑን የሚናገርም ነው።

በተጨማሪም ሁሉም ከፍተኛ ባለሥልጣን ለሚለው ለመጽሐፍ ቅዱስ መገዛት እና ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር ህብረት መፍጠር እንዳለባቸው የሚያመላክትም ጭምር ነው። ምክንያቱም ትውፊት, የአምልኮተ ሥርዓት ሆኑ, ጉባኤዎች የማይሳሳቱ ስላልሆኑ ማለትም ሊሳሳቱ የሚችሉ በመሆናቸው ምክንያት መመዘን ያለባቸው አይሳሳቴና የእግዚአብሔር እስትንፋስ በሆነው በመጽሐፍ ቅዱስ ነው። ይህንን ሐሳብ ቅዱስ አውግስጢኖስ ዘሒፖ(Augustine of Hipo) በመደገፍ መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ ዝንፈተ እውነት የሌለበት እንደሆነ ይናገራል፦

I have learned to yield this respect & honour #only to the scripture, of these #alone do I most firmly believe that completely #inerrant (free from error)----Letters, 82:3

ትውፊትም, የአምልኮ ሥርዓቶች ሆኑ ጉባኤያት ስህተት ሊገኝባቸው ይችላል። ምክንያቱም የትውፊት አስተላለፋቸውን በተመለከትን ጊዜ በሰዋዊ አተረጓጎም, በተፈጥሮዋቸው የሚሳሳቱ ስለሆኑ እና በculture influence የታሰረ በመሆኑ original መልዕክቱ distort ሊሆን ይችላል። በተለይም Tradition እና Liturgical practice በዘመናት መሐል የተለያየ ብርዘት እና ለውጥ ሊገባባቸው የሚችሉ ናቸው። ለምሳሌ ያክል በካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የጳጳሳቱ መብት እያደገ እየተሻሻለ በመምጣት ወደ papal Infallibility በመጨረሻም ወደ ስህተት መምጣታቸው የሚዘነጋ አይደለም። በተጨማሪም በነገረ ማሪያም ያላቸውን ዶክትሪን እጅጉን እየለጠጡ በመምጣታቸው ወደ Immaculate conception(አንዳንድ ኦርቶዶሳውያንም ይህንኑ አስተምሮ ይቀበላሉ) እንዳመሩ እንመለከታለን። የMonastic practice እና Ascetic tradition, የPurgatory concept ሌላው የሚጠቀሱ ጉዳዮች ናቸው። በኦርቶዶክሱም ሆነ በካቶሊኩም የሚስተዋለው የመጽሐፍ ቅዱስ የቀኖና ችግር ስንመለከት ትውፊት በዘመናት መካከል ሊቀያየር እና ሊበከል የሚችል ጉዳይ ሁኖ እናገኘዋለን። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም በማቴዎስ ወንጌል 15:3 ላይ በdivine revelation ላይ rooted ያልሆነውን የአይሁዳውያንን ትውፊት criticize ሲያደርግ እንመለከታለን። የSola Scriptura Concept እነዚህ ሁሉ Tradition እና Liturgical practice በሕጸጽ አልቦው እና በአይለወጤው በእስትንፋሰ እግዚአብሔር ቃል መሠረት ተመዝነው መጥራት ያለባቸው ጉዳዮች መሆናቸውን የሚገልጽ ክርስቲያናዊ መርህ ነው። ስለዚህ Traditions are subject to scrutiny against God's Word, implying that they are not inerrant so inerrant የሆነው መጽሐፍ ቅዱስ ትክክለኛው ሚዛን እና Highest Authority ያለው አፊዎተ ቃል ነው።

በሚቀጥለው Consensus of fathers conceptን እና የSola scriptura Interpretation of scripture Framework የምንዳስስ ይሆናል። ተባረኩ!

@Yeshua_Apologetics_Ministry
Just so that you all know, there is no early church father MANUSCRIPT older than p52 or p75. That means, The earliest primary evidence for christianity is scripture itself.

@Yeshua_Apologetics_Ministry
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
"..እውነት ነው እግዚአብሔር ሁሉን የፈጠረ ነው። አይመረመሬውን እንመርምር ብንል ትርፉ ድካም ነው። ይህ ማለት ግን ከቶ አናቀውም ማለት ግን አይደለም። እርሱ ራሱን በቃሉ ላይ በገለጠልን ልክ እንረዳውም ዘንድ ዛሬም በመንፈሱ በኩል ከእኛ ጋር አለና።.."

የሹዋ ዐቅብተ እምነት
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
እነሆ ጥቂቷን!

የዮሐንስ ወንጌል ዳሰሳ ላይ እየሰራን ካለነው ቪዲዮ ቅምሻ እናካፍላችሁ እስኪ..😁😁

ተቃውሚያንን ምንሞግትባቸው ነጥቦች፦

ጸሐፊው ማነው? ጸሐፊው አይታወቅምን? እና ሌሎችም... ሙሉውን ሳምንት ዩቱዩብ ቻናላችን ላይ ይጠብቁን፦
https://youtube.com/@yeshuaapologetics?si=cN_dgAZysZ45n7vh

ተባረኩ!
@Yeshua_Apologetics_Ministry