YeProtocol Guday/የፕሮቶኮል ጉዳይ
363 subscribers
105 photos
15 videos
51 links
A Radio Show on Social, Business and International Protocol and Etiquette. Tune to Arada FM 95.1 every Saturday from 4 to 5 PM to listen to the show.
Download Telegram
ይህን ያውቁ ኖሯል?
ለበለጠ መረጃ
📞 +251911424957
📧 info@proeventsaddis.com

#ProEventsAddis #businesscard #Appointment #Gift #Preparation #InternationalMeeting
#protocol #Ethiopia #AddisAbaba
👍21
እንኳን ለጥቁር ህዝቦች ኩራት ለሆነው የአድዋ 129 የድል በዓል ቀን አደረሳችሁ!

#proevents #Ethiopia #victory #ADWA #አድዋ #ድል #Ethiopiavictory #AdwaHeroes
👍1
Meet&Greet Services of Pro Events Addis
1
ከአቶ መላኩ ደሴ ጋር የነበረን ቆይታ ይህንን ይመስላል። ተከታተሉት
👍1
“ጓድ የሥልጣን ተዋረድ ሊቅ”
“ሚስተር ቲቪ!” አለኝ አንዱ የኪነት ሰው፡፡
“ወዲህ!ወዲህ!” አለኝ የፕሮቶኮል ሹሙ፡፡
በጥድፊያ ተከተልኩት፡፡ የሊቀመንበሩ መምጫ ሰዓት ሲቃረብ መቁነጥነጥ ያበዛል፡፡ ተካልቦ ሰው ያካልባል፡፡ ወደ አንደኛ ማእረግ ወስዶ ከደርግ ቋሚ ኮሚቴና ከኢሠፓአኮ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባሎችና ከሚኒስትሮች ጋር አስቀመጠኝ፡፡
“ጓድ፣ ፕሮቶኮል ተሳስቶ እንደሆነ?” አልኩት፡፡
“አርፈሽ ቁጭ በይ” አለኝ፡፡ አንዳንድ የሚወዳቸውን ሰዎች ‘አንቺ’ እያለ መጥራት ይወዳል፡፡
“እውነቴን ነውኮ...”
“ቦታሽ ነው፡፡”
ጓድ ተድላ ረጋሳ የፕሮቶኮል አቀማመጥ የሚያሳስት ሰው አይደለም፡፡ ስለ ፕሮቶኮል አቀማመጥ በጣም ተጠቦ ይጨነቃል፡፡ የያንዳንዱን ሰው ፖለቲካዊ ክብደት መዝኖ የሚያውቅ በመሆኑ “ጓድ የሥልጣን ተዋረድ ሊቅ” ይሉታል አንዳንድ የደርግ አባሎች፡፡ ነገሩ ቀልድ አይደለም፡፡ ከደርግ አባሎች ጀምሮ ብዙ ባለሥልጣኖች የከርሞ ፖለቲካዊ ክብደታቸውን የሚመዝኑት በእሱ ዓይን ነው፡፡ ካገሪቱ ከፍተኛ ባለሥልጣኖች ጋር ጎን ለጎን መቀመጥ ወይም ትከሻ ለትከሻ መጋፋት ልብ ያሳብጣልና እኔም ትንሽ ክብደት ብጤ ተሰማኝ፡፡...
አዳራሹ በሰው ተሞልቷል፡፡ ሁሉም እንደፕሮቶኮሉ ነበር የተቀመጠው - በተዋረድ፡፡ ስም ስማችንን የያዘ ካርድ ከፊት ከፊታችን ተቀምጧል፡፡ ስሜ የተጻፈበትን ካርድ አይቼ ተቀመጥኩ፡፡ የተያዘልኝ ቦታ የመጨረሻው ወንበር ነበር፡፡ ‘ቀይ ኮከብ’ ዓርማ ያለበት የሁገአዘ ልዩ ማስታወሻ ደብተር ከያንዳንዳችን ፊት ጠረጴዛ ላይ ተደርድሯል፡፡ የሚያጨስ የለም፡፡ ከረባት ያላሰረ ሰው የለም፡፡ ሁሉም እንደ አቅሙ ታንቋል፡፡ ለውጥ ይታያል፡፡ ....ሥነ ሥርዓት ሰፍኗል፡፡
ኦሮማይ፤ በዓሉ ግርማ
2
ሻለቃ ፍስሓ ገዳ እንደ ተድላ ረጋሳ

“በበዓሉ ግርማ- ኦሮማይ ገጸ-ባህሪያት በእውነታው ዓለም የሚታወቁበት ስም በመጽሐፉ ውስጥ ተቀይሯል፡፡ ከነርሱ መካከል ተድላ ረጋሳ ሆኖ የተሳለው ገጸ-ባህሪ ሻለቃ ፍሰሓ ገዳ (የኢሠፓ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባልና የደርግ መንግሥት የፕሮቶኮል ሹም ነበር)።
ሻለቃ ፍስሓ ገዳ የሰው አለባበስና አቀማመጥ ብቻ ሳይሆን የእቃ አደራደርም የሚያውቅ ጠንቃቃ ሰው ነው ይሉታል።
መንግስቱ ሃይለማርያም መስቀል አደባባይ ላይ የከሰከሳቸውን በቀይ ቀለም የተሞሉ ፋሽኮ ጠርሙሶች ቆሞ የሚያቀብለው ሻለቃ ፍሰሓ ገዳ ነው፡፡ በወቅቱ የፕሬስና የሕዝብ ግንኙነት ክፍል ሃላፊ ነበር። በኋላ ላይ የተዋጣለት የፕሮቶኮል ሰው ሆኗል፡፡ የት እንደተማረ ግን አላውቅም፡፡” ብሎ በውስጥ መልዕክት ልኮልኛል። ለመረጃው እጅግ አመሰግናለሁ!
👍1
Dear All,
Wishing you a joyful and peaceful Fasika filled with love, reflection and time well spent with family.
Have a splendid celebration!
👍2
የፕሮግራም ቀንና ሰዓት ለውጥ ጥቆማ፡ የፕሮቶኮል ጉዳይ የሬዲዮ ፕሮግራም የበለጠ ተደራሽ ለመሆን በአራዳ ኤፍ ኤም 95.1 ላይ ዘወትር ቅዳሜ ከ10-11 የሚቀርብ ይሆናል።
👍2