ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ለመናፍቃንና ለአህዛብ መልስ አላት!
1.98K subscribers
328 photos
21 videos
6 files
109 links
እዚህ ቻናል ውስጥ አህዛብ እና መናፍቃን ለሚያነሷቸው ጥያቄዎች በክርስቶስ አምላካችን ፣ በቅዱሳኑ ትሩፍት እና በስርዓተ ቤተ ክርስትያን ላይ ስለ ሚነሱ የስህተት ና የቅሰጣ ትምህርቶች ሙሉ መልስ የሚሰጥበት ቻናል ነው። በተመሳሳይ፦
* የቤተ ክርስትያን ቀኖና፣ዶግማ፣ትውፊት፣ታሪክ
* ነገረ ቅዱሳን
ይዳስሳሉ ይነገራሉ።

ለማንኛውም አስተያየት በዚህ ታገኙናላችሁ
@Selamawitttttttt
Download Telegram
@#ጌታቺን ኢየሱስ ክርስቶስ ትንቢት በብሉይ ኪዳን ፍጻሜውን በሀዲስ ኪዳን እናገኛለን//

ለሴቱቱ የተነገር ትንቢት ዘፍ 3፥15 በብሉይ ኪዳን
@#ፋጻሜው ሉቃ 2፥7
ገላ 4፥4
ራዕ 12፥5
ለአብርሀም ዘር የተሰጠ የተስፋ ትንቢት ዘፍ 18፥17-18 ዘፍ 12፥2-3
@#ፍጻሜው ሀዋስራ 3 ፥ 35 እናገኛዋለን
ለይሳሀቅ ዘር የተሰጠ የተስፋ ትንቢት ዘፍ 17፥19
@#ፍጻሜው ማቴ 1፥2
በይሁዳ ነገድ መወለዱን የሚናገር ትንቢት ጌታቺን ከመወለዱ በፊት ዘፍ 49፥10
@#ፍጻሜው ሉቃ 3፥33
የሚወለድበትን የሚናገር ትንቢት ት፡ሚኪ 5፥2
@#ፋጻሜው ማቴ 2፥1 ሉቃ 4፥2-7
የሚወለድበትን ግዜ የተነገር ትንቢት ዳን 9፥25
@#ፋጻሜው 2፥1-5
ከድንግል ስለመወለዱ የሚናገር ትንቢት ኢሳ 7፥14
@#ፋጻሜው ማቴ 1፣23
እናቱ ዘላለማዊ፡ድንግክ ስለመሆኖ የሚናገር ትንቢት ሕዝ 44፥1
@#ፋጻሜው ማቴ 4፥18
ሉቃ 11፥27
የህጻናት መታርድ ትንቢት ኢሳ 31፥15
@#ፍጻሜው ማቴ 2፥17
ወደ ግብጽ መሰደድ ትንቢት ሆሴ 11፥1
@#ፍጻሜው ማቴ 2፥14
ጌታቺን ስለ ገሊላ ስብከቱ ኢሳ 9፥1-2
@#ፍጻሜው ማቴ 4፥12-17
ማር 1፥14-15
ሉቃ 4፥14-15
የነብዩ መምጣት ትንቢት ዘጸ 18፥5
@#ፍጻሜው ማት 9፥7
ካህን፡ከመልከጼዲቅ እንደሚመጣና እንደ መለከጼዲቅ እንደሆነ መዝ110፥4
@#ፍጻሜው ዕብ 6፥20
በአይሁድ እንደሚገርፍ የሚናገት ትንቢት ኢሳ 53፥3
@#ፍጻሜው ዩሀ 1፥11
ስለ፡ክርስቲስ መለያ ስጦታዎች የተሰጠ የተነገር ትንቢት ኢሳ 11፥2
@#ፍጻሜው ሉቃ2፥52
በይባቤ ኢየሩስአሌም መግባቱ የሚናገር ትንቢት ዘካ 9፣9
@#ፍጻሜው ማቴብ21፥1-11
ሉቃ 19፥28-40
በወዳጁ ይሁዳ ስለመካዱ የተነገር ትንቢት መዝ 41፥9
@#ፍጻሜው ማር 14፥10
ጌታቺን በ30 ብር መሸጡን የሚናገር ትንቢት ዘካ 11፥12 ተረፈ ባሮክ 1፥2-3
@#ፍጻሜው ማቴ 26፥6-7 ማር 14፣10 ሉቃ 22፥36
በሸክላ ሰሪ የተሰጠ፡ትንቢት ዘካ 11፥13
@#ፍጻሜው ማቴ 26፥6-7 ማር 15፥1 ሉቃ 23፥1-3
ስለ ውሸታሞች ሀሰተኛ፡ምስክር ትንቢት መዝ 27፥12፥(35፥11
@#ፍጻሜው ማቴ 26፥57-62 ማር 14፣53-65 ሉቃ 22፥54-55
ሲከሱት ዝም ስለ ማለቱ፡የተነገር ትንቢት ኢሳ 53፣7
@#ፍጻሜው ማቴ 26፥62-67 ማቴ 27፥12-14 ሉቃ 23፥13-15
ተነታ ተገፋ ምርቅ ተተፋበት ተብሎ የተነገር ትንቢት ኢሳ 50፥6
@#ፍጻሜው ማር 14፥35 ማር 15፥17 ዩሀ 19፥1-3 ዩሀ 18፥22
ያለ፡ምክንያት፡ለመጠላቱ የተነገር ትንቢት መዝ 69፥4 (109፥3-5
@#ፍጻሜው ዩሀ 15፥23-25
አለምን አለማዳን ተሰቃየ የሚክ ትንቢት ኢሳ 53፥4-5
@#ፍጻሜው ማቴ 8፥1-17 ሮሜ 4፥25 1ቆሮ 3፥5
አለምን፡ለማዳም፡ከሐጢያተኞች ጋር ተቆጠር ትንቢት ኢሳ 53
@#ፍጻሜው 7፥38 ማር 15፥27-28 ሉቃ 23፥33
እጅና እግሮቺን እንደተቸነከር የተነገር ትንቢት መዝ 22፥16 ዘካ 12፥16
@#ፍጻሜው ዮሀብ20፥27 ዮሀ 19፥37 (20 25-26
ይሰደባል ይቀለድበታም ተብሎ የተነገር ትንቢት መዝ22፥7-8
@#ፍጻሜው ማቴ 27፣39-40 (41፥44)ማር 15፥29-32
መራራ ሀሞት መጣጣና ሀሞት ለመሰጠቱ የተነገር ትምቢት መዝ 68፥21
@#ፍጻሜው ማቴ 27፥34-48 ዩሀ 19፣29
ጎኑን እንደየሚወጋ የተነገር ትንቢት ዘካ 12፥10
@#ፍጻሜው ዩሀ 19፥34
ከወንብዴዎች ጋር ይቀበራል የሚክ ትንቢት ኢሳ 53፣9
@#ፍጻሜው ማቴ 27፥57-69
ስለ ትንሳኤው የተነገር ትንቢት መዝ 16፣10
@#ፍጻሜው ፡ማቴ 28፥16 ማር 14፥18
ስለ ይሁዳ የተነገር ትንቢት መዝ 109፥7-8@#ፍጻሜው ሀዋ ስራ 11፥18-20
እናገኛዋለን


@YEMEREJAWECHSIBESEBCHANNEL
#በእርሱ #ቊስል #እኛ #ተፈወስን

ጲላጦስም የካህናት አለቆችንና መኳንንትን ሕዝቡንም በአንድነት ጠርቶ እንዲህ አላቸው ሕዝቡን ያጣምማል ብላችሁ ይህንን ሰው ወደ እኔ አመጣችሁት እነሆም በፊታችሁ መርምሬ ከምትከሱበት ነገር አንድ በደል ስንኳ በዚህ ሰው አላገኘሁበትም፡፡ ሄሮድስም ደግሞ ምንም አላገኘም ወደ እኛ መልሶታልና እነሆም ለሞት የሚያደርሰው ምንም #አላደረገም፡፡ እንግዲያስ ቀጥቼ እፈታዋለሁ አላቸው (ሉቃ. ፳፫፥፲፬‐፲፮)

ጲላጦስ የጌታችንን ንጹሕ መሆን ካወቀ በኋላ ቀጥቼ #እፈታዋለሁ አለ፡፡ ንጹሕ በመሆኑ ምክንያት የተቀጣ #ከጌታችን በቀር ማን አለ? ጲላጦስ አይሁድን ደስ ለማሰኘት ስለፈለገ ያን ሁሉ ጥያቄና መልስና ሕጋዊውን የፍርድ ሒደት ማስፈጸም ትቶ በንጹሑ ጌታ ላይ ግርፋት እንዲወርድበት ፈረደ፡፡

ነቢዩ ኢሳይያስ #በውርደቱ ፍርዱ #ተወገደ ብሎ #እንደተናገረው ትንቢት ጲላጦስ በእርጋታ ጀምሮት የነበረውን ሕጋዊ የምርመራና የፍርድ ሒደት አሽቀንጥሮ ጥሎ (አስወግዶ) ከሕግ ውጪ በዚያች ቀን በአይሁድ እጅ የተዋረደውን ጌታ ያለ ፍትሕ እንዲገረፍ ወሰነበት፡፡ (ሐዋ. ፰፥፴፫)

ጲላጦስ #ኢየሱስን ይዞ #ገረፈው (ዮሐ. ፲፱፥፩) የጲላጦስ አሳብ #በመሰቀሉ ፈንታ ግርፋት ቢገረፍ ሕይወቱን ካዳንኩለት #ቢቆስል ምንም አይደለም የሚል ነበር፡፡ አይሁድም የግርፋቱን ጽናት አይተው ይሙት ማለታቸው እንደሚቀር ተስፋ አድርጎ ነበር፡፡ በዚህ ምክንያት ከትናንት ምሽት ጀምሮ ታስሮ ሲንገላታ ያመሸውን ፣ በሐናና ቀያፋ ግቢ ውስጥ ሲደበደብና በጡጫ ሲመታ ያደረውን ጌታ በምሕረት የለሾቹ የሮም ወታደሮች እጅ እንዲገረፍ አሳልፎ #ሠጠው፡፡

የሮማውያን ግርፋት እንደ አይሁድ ግርፋት በጅራፍ ብቻ አይደለም፡፡ የቤተ ክርስቲያን ታሪክ ጸሐፊው አውሳብዮስ ዘቂሣርያ እንደገለጠው ጅራፉ በቆዳ ከተሠራ በኋላ በላዩ ላይ ስለታማ የሆኑ የብረት ኳሶች ሾለው የተሳሉ የአጥንት ስብርባሪዎች ይደረጉበታል፡፡ በዚህ አሰቃቂ የግርፋት መሣሪያና በጨካኞቹ ወታደሮች እጅ ወድቀው ሥቃዩን መቋቋም ተስኖአቸው የሞቱም ብዙዎች ናቸው፡፡

በጅራፉ ላይ የተሠሩት የብረት ኳሶችና የአጥንት ስብርባሪዎች በሚገረፈው ሰውነት ላይ ሲያርፉ ሥጋውን እየነጩ የሚነሡ ስለሆኑ ጅራፉ በሰውነት ላይ ማረፉ ብቻ ሳይሆን ከሰውነት ላይ የሚነሣበትም ቅጽበት እጅግ ለመግለጽ የሚከብድ ሥቃይ የሚያደርስ ነው፡፡ የግርፋቱ መጠን በጨመረ ቁጥር የደም ሥሮችና #አጥንቶች እስከሚታዩ ድረስ የሚጎዳ ፣ የጎድን አጥንቶችን መሰባበር ፣ ከፍተኛ የሆነ ውጪያዊና ውስጣዊ የደም መፍሰስ ፣ የሳንባ መጎዳት የሚያስከትል አሰቃቂ ሒደት ነው፡፡😢

በዚያች ቀን #ጌታችንን ለመግረፍ የተመደቡት ወታደሮች እስራኤልን በብርሃን ዓምድ በሌሊት የመራቸውን #አምላክ #ሙሴና #አሮንን #በደመና ዓምድ ያነጋገራቸውን አምላክ በድንጋይ ዓምድ ላይ ለመግረፍ ዕርቃኑን #አሰሩት፡፡ የካህናት አለቆችን ደስ ለማሰኘት ሲሉም በሙሉ ኃይላቸው በታላቅ ጭካኔ እጅግ ብዙ ግርፋትን አዘነቡበት፡፡ አንድ ገጣሚ እንዳለው በሙሴ አድሮ #የፈጣሪን ክብር ለማየት የለመነው የሰው ልጅ ፈጣሪ በጊዜው #ጀርባዬን #ታያለህ ብሎ የገባለትን ቃል ቢፈጽምለትና ጀርባውን ቢያሳየው ግርፋትን አዘነበበት፡፡ (ዘጸ. ፴፫፥፳፫) በእርግጥም ቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ #ከጲላጦስ ግርፋትን ይቀበልበት ዘንድ ጀርባን ፈጠረ እንዳለው አምላክ ሰው የሆነውና ጀርባን ለራሱ ያዘጋጀው ስለ ሁላችን #ኃጢአትን #ግርፋትን ሊቀበልበት ነበር፡፡ 😭

የሮማውያን ግርፋት ቅዱስ ጳውሎስ እንደተገረፈው እንደ አይሁድ ግርፋት በመጠን ተወስኖ አንድ ሲጎድል አርባ ግርፋት አምስት ጊዜ ገረፉኝ› እያለ የተገረፈው ሰው በሕይወት ተርፎ እያስታወሰ የሚናገረው ዓይነት ግርፋት አይደለም፡፡ (፪ቆሮ. ፲፩፥፳፬)
ቤተ ክርስቲያናችን #የጌታችን ግርፋት #ስድስት #ሺህ #ስድስት #መቶ #ስድሳ #ስድስት ጊዜ እንደሆነ ስታስተምር አምስት ሺህ ነው ፣ አራት ሺህ ነው የሚሉም አሉ፡፡ ይህን አሰቃቂ ግርፋት በሺህ ለሚቆጠር ጊዜ መገረፉን ግን ሁሉም ሊቃውንትና የታሪክ ሰዎች ተስማምተውበታል፡፡ ጌታችን እጅግ መገረፉን የሚያሳየን መስቀሉን ባሸከሙት ጊዜ በየሥፍራው እስኪወድቅ ድረስ አቅም ማጣቱ ነው፡፡

የጌታን ግርፋቱንስ መቁጠር ቢቻልም እንኳን ሥቃዩን ግን እንዴት ልንቆጥረው እንችላለን? ቤተ ክርስቲያናችን ከሥጋው አልፎ አጥንቶቹ እስከሚታዩ ድረስ ስለ ተገረፈው አምላክ በዕለተ ዓርብ የምታነበውና የምታዜመው ራሱ #ክርስቶስ አስቀድሞ በነቢዩ ዳዊት አድሮ ስለሕማሙ የተናገረው የትንቢት ቃል የሥቃዩ መጠን ጥቂትም ቢሆን ለማሰብ ያግዘናል፡-

‹‹እንደ ውኃ ፈሰስሁ #አጥንቶቼም ሁሉ ተለያዩ ፤
ልቤ እንደ ሰም ሆነ #በአንጀቴም መካከል ቀለጠ…
#አጥንቶቼ ሁሉ #ተቈጠሩ እነርሱም አዩኝ #ተመለከቱኝም
#አጥንቶቼ #ተነዋወጡ (መዝ. ፳፪፥፲፬፣፲፯፤፴፩፥፲)

ቅዳሴያችን እንዲህ ይላል #የወልድን መከራውን የሚናገር ምን ዓይነት አፍ ነው? ምን ዓይነት #ከንፈር ነው? ምን ዓይነት አንደበት ነው? #የፍቅር #ጌታ #ሕማማቱ በተነገረ ጊዜ ልብ ይለያል ፤ ሕሊናም ይመታል #ነፍስም #ትንቀጠቀጣለች #ሥጋም #ይደክማል በእውነትም #የጌታችንን ሥቃይ ለመግለጽ ምንም ዓይነት ቋንቋ ምንም ያህል ቅኔ አቅም አይኖረውም፡፡

ቅዱስ ኤፍሬምም :-
#በክርስቶስ #የተወደዳችሁ ሆይ ኑ! ወዲህ ቅረቡ በዚች ዕለት በዳዊት ከተማ የሆነውን አብረን እንይ #በተስፋው ቃል ሲጠበቁ የነበሩት የተመረጡት #የአብርሃም #ዘሮች ዛሬ ምን እንዳደረጉ እንመልከት! ጌታ ሆይ ረዥሙን ሥቃይህን ማን ሊገልጸው ይችላል?›› ይላል፡፡

ይህ ሁሉ የሆነው #ስለ #እኛኃጢአት ነበር፡፡ ኦሪት የሚገረፍ ሰው ‹‹የግርፋቱም ቊጥር እንደ ኃጢአቱ መጠን ይሁን›› ትላለች፡፡ (ዘዳ.፳፭፥፪) ጌታችን ማንም ስለ ኃጢአቱ ሊወቅሰው የማይችል ንጹሕ ቢሆንም #እግዚአብሔር #የሁላችንን #በደል #በእርሱ ላይ #አኖረ ስለተባለ ግርፋቱም በተሸከመው የእኛ ኃጢአት መጠን ሆነ፡፡

እርሱ #ስለመተላለፋችን #ቈሰለ ስለ በደላችንም ደቀቀ #የደኅንነታችንም ተግሣፅ #በእርሱ ላይ #ነበረ በአጋንንት እጅ ልትገረፍ የጸጋ ልብስዋን አውልቃ ዕርቃንዋን በሲኦል የወደቀች ነፍሳችንን ነጻ ያወጣት ዘንድ እርሱ በጨካኝ ወታደሮች እጅ #ዕርቃኑን #ተገረፈ፡፡

እኛን #ከሚገባን #ግርፋት ያድነን ዘንድ #ኢየሱስ የማይገባውን ግርፋት #ተገረፈ የተገረፈባቸውም አለንጋና ገመድ በደም ታለሉ ተነከሩ ከግርፋቱ ጽናት የተነሣ ሥጋው ሁሉ አለቀ #ሐዋርያው #ጴጥሮስ በመገረፉ ቊስል ተፈወሳችሁ በማለት እንደተናገረ በእርሱም ቊስል እኛ ተፈወስን (፩ጴጥ. ፪፥፳፬፤ኢሳ. ፶፫፥፭)

#ህማማት #በዲያቆ #ሄኖክ #ሀይሌ

@YEMEREJAWECHSIBESEBCHANNEL
#በእውነት #ደዌያችንን #ተቀበለ ሕመማችንንም #ተሸክሞአል እኛ ግን እንደ ተመታ #በእግዚአብሔርም እንደ #ተቀሠፈ እንደ ተቸገረም #ቈጠርነው😭
እርሱ ግን ስለ መተላለፋችን ቈሰለ፥ ስለ በደላችንም ደቀቀ የደኅንነታችንም ተግሣጽ #በእርሱ ላይ ነበረ #በእርሱም #ቍስል እኛ #ተፈወስን
እኛ ሁላችን እንደ በጎች #ተቅበዝብዘን ጠፋን ከእኛ እያንዳንዱ ወደ ገዛ መንገዱ አዘነበለ #እግዚአብሔርም #የሁላችንን በደል #በእርሱ ላይ አኖረ።

ትንቢተ ኢሳያስ 54,4-6

#እርሱ #በእግዚአብሔር #መልክ #ሲኖር👈 ሳለ #ከእግዚአብሔር #ጋር #መተካከልን #መቀማት #እንደሚገባ ነገር አልቈጠረውም፥

ነገር #ግን #የባሪያን መልክ ይዞ #በሰውም #ምሳሌ👈👀 ሆኖ ራሱን #ባዶ አደረገ☝️
#በምስሉም እንደ #ሰው #ተገኝቶ ራሱን #አዋረደ #ለሞትም ይኸውም የመስቀል ሞት እንኳ የታዘዘ ሆነ

ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 2,6

#በወንድማችን #ሀብተወልድ🎙🌺

@YEMEREJAWECHSIBESEBCHANNEL
“አቃጥሏት ግዴለም “
⛪️⛪️⛪️

ቤተ ክርስቲያን ቅድስት እመ ኵሉ
የወንጌል ማኅደር የጸናብሽ ቃሉ!
ስብከትሽ ሰላም ነው ለዓለም በሙሉ
አፅራረ ሰላም ግን አንቺን ይጠላሉ!

ተልእኮሽ ፈውስ ነው ለታመሙ ኹሉ
መዳን የማይወዱ ከአንቺ ይሸሻሉ!
ጭራሽ ሊያሳድዱሽ ይመካከራሉ
አጥፍቶ ጠፊዎች ሊያጠፉሽ ይሻሉ።

የጥፋት ልዑካን ለጽድቅ ያልታደሉ
ሕንፃሽን በእሳት አቃጠሉት አሉ!
ጣሪያ ግድግዳዉን አፈረሱት አሉ
ባያውቁት ነው እንጂ ቢጠፋቸው ውሉ
በአንቺ እሳትነት አብረው ይጨሳሉ!
በማገዱት እንጨት ኋላ ይነዳሉ
ዛሬ እንዳፈረሱሽ ነገ ይፈርሳሉ
በሠፈሩት መጠን ዋጋን ያገኛሉ

አብዳን ግብዞች ሆይ የሰይጣን ፈረሱ
ደስ ካሰኛችሁ እሳት መለኮሱ!
አቃጥሏት ግዴለም ጣሪያዋን አፍርሱ
ግድግዳ ወለሉን ብሎኬቱን አንሡ
ለጊዜውም ቢኾን ቅፅሮቿን ደምስሱ
ልጆቿን በሙሉ ደም ዕንባ አስለቅሱ።

ነገር ግን ጌታዋ ሲቆጣ ንጉሡ
መቃጠላችሁን ፈጽሞ እንዳትረሱ
ጽዋ ተርታችሁን ዘወትር አስታውሱ፡፡

ጌታ ችሎ ችሎ መዓቱን ሲያመጣ
ቅፅሩን ለማስከበር ሲፈርድ በቁጣ
በተራ መንደድ ነው የሁላችሁ ዕጣ፡፡

እስከዚያው ድረስ ግን እስኪመጣ ጌታ
የዓለምን መድኀኒት የሕዝብን አለኝታ
ቤተ ክርስቲያንን አፍርሷት በአንድ አፍታ
አቃጥሏት ግዴለም አንድዷት በተርታ፡፡

እርሷ በትረ ወንጌል የሾለ ብረቱ
ብትቆሙ ደፍራችሁ በኃያል ስለቱ
ደዌው ለእናንተ ነው ሕመሙ ጉዳቱ።

ጣሪያና ግድግዳው አካሏ ቢደማ
ብትነድ ብትቃጠል በክፉዎች ፊርማ
መቅደስ ማኅሌቱ ቢመስልም ባድማ
አትፈርስም በፍጹም በግብዞች ዐድማ
እሳት የሚያነዳት አይደለችም እማ
በክርስቶስ ፍቅር ተቃጥላለች ቀድማ፡፡

ቤተ ክርስቲያን ይቺ ምድራዊቷ
መለኮት እሳት ነው ጥንትም መሠረቷ
የክርስቶስ ደም ነው እስትንፋስ ሕይወቷ አቃጥሏታልና ክርስቶስ እሳቷ
አጽንቷታልና አምላክ ባለቤቷ
በፍጹም አትፈርስም ጽኑ ነው ዐለቷ
በጠላት ዘመቻ አይኾንም ኅልፈቷ፡፡

እግዚአብሔር አምላክ ሆይ ሀገረ ኢትዮጵያን ሠላም አድርግልን🙏
💚💛❤️

@YEMEREJAWECHSIBESEBCHANNEL
#ክርስቶስ #አምላክ ነው!

ተወው አታምልከው እኔ አመልከዋለው!
👇
#በሰማይና በምድር ያሉት #ሁሉ በእርሱ #ተፈጥረዋልና ከፍጥረት ሁሉ በፊት በኵር ነው። #ሁሉ #በእርሱና #ለእርሱ #ተፈጥሮአል።"

(ወደ ቆላስይስ ሰዎች 1:15-16)

@YEMEREJAWECHSIBESEBCHANNEL
ዮሐንስ 1 (John)
14፤ #ቃልም #ሥጋ #ሆነ፤ $ጸጋንና እውነትንም ተመልቶ በእኛ አደረ፥ አንድ ልጅም ከአባቱ ዘንድ እንዳለው ክብር የሆነው ክብሩን አየን።
15፤ #ዮሐንስ #ስለ #እርሱ መሰከረ እንዲህም ብሎ ጮኸ፡— ከእኔ በኋላ የሚመጣው እርሱ ከእኔ በፊት ነበረና ከእኔ ይልቅ የከበረ ሆኖአል፤ ስለ እርሱ ያልሁት ይህ ነበረ።
16፤ እኛ ሁላችን ከሙላቱ ተቀብለን በጸጋ ላይ ጸጋ ተሰጥቶናልና ሕግ በሙሴ ተሰጥቶ ነበርና፤
17፤ ጸጋና እውነት ግን በኢየሱስ ክርስቶስ ሆነ።
18፤ መቼም ቢሆን እግዚአብሔርን ያየው አንድ ስንኳ የለም፤ በአባቱ እቅፍ ያለ አንድ ልጁ እርሱ ተረከው።
ዮሐንስ
9፤ #ለሰው #ሁሉ #የሚያበራው እውነተኛው ብርሃን ወደ ዓለም ይመጣ ነበር።
10፤ #በዓለም #ነበረ#ዓለሙም #በእርሱ ሆነ፥ #ዓለሙም #አላወቀውም
11፤ የእርሱ ወደ ሆነው መጣ፥ የገዛ ወገኖቹም አልተቀበሉትም።
12፤ #ለተቀበሉት #ሁሉ #ግን#በስሙ #ለሚያምኑት #ለእነርሱ የእግዚአብሔር ልጆች ይሆኑ ዘንድ ሥልጣንን ሰጣቸው፤
13፤ እነርሱም ከእግዚአብሔር ተወለዱ እንጂ ከደም ወይም ከሥጋ ፈቃድ ወይም ከወንድ ፈቃድ አልተወለዱም።

ኤፌሶን 2 (Ephesians)
10፤ እኛ ፍጥረቱ ነንና፤ እንመላለስበት ዘንድ እግዚአብሔር አስቀድሞ ያዘጋጀውን መልካሙን ሥራ ለማድረግ #በክርስቶስ #ኢየሱስ #ተፈጠርን

#መቼም #ቢሆን እግዚአብሔርን ያየው አንድ ስንኳ የለም፤ #በአባቱ እቅፍ ያለ አንድ ልጁ እርሱ ተረከው።
—ዮሐንስ 1: 18

#በወንድም #ፍቅረ🌺

@YEMEREJAWECHSIBESEBCHANNEL
ነህምያ 9
13፤ #ወደ #ሲናም #ተራራ #ወረድህ#ከሰማይም #ተናገርሃቸው#ቅኑን ፍርድና እውነቱን ሕግ መልካሙንም ሥርዓትና ትእዛዝ ሰጠሃቸው፤
መዝሙር 139
7፤ #ከመንፈስህ #ወዴት እሄዳለሁ? ከፊትህስ ወዴት እሸሻለሁ?
8፤ #ወደ #ሰማይ #ብወጣ#አንተ በዚያ አለህ። ወደ ሲኦልም ብወርድ፥ በዚያ አለህ።
9፤ #እንደ ንስር የንጋትን ክንፍ ብወስድ፥ እስከ ባሕር #መጨረሻም ብበርር፥
10፤ በዚያ እጅህ ትመራኛለች፥ ቀኝህም ትይዘኛለች።

ምሳሌ 15 (
3፤ #የእግዚአብሔር #ዓይኖች #በስፍራ ሁሉ ናቸው፤ ክፉዎችንና ደጎችን ይመለከታሉ።
ኢሳይያስ 66
1፤ #እግዚአብሔር #እንዲህ #ይላል፡— #ሰማይ #ዙፋኔ ነው፥ #ምድርም #የእግሬ መረገጫ ናት፤

#በወንድም #ፍቅረ🌺

@YEMEREJAWECHSIBESEBCHANNEL
#ክርስቶስ #አልተሰቀለም ብለው ለሚቀጥፊት #ኢአማኒያን #ሙስሊም ወገኖቻችን #የተሰጠ ምላሽ!
በመጀመርያ በመፀሀፍ ቅዱስ መነፀር ሆነን ቁርአንን ካየነው ብዙ ስህተት አለበት እንዳለው ኡስታዝ አቡሀይደር
በተሳሳተው ቁርአን እይታ መፀሀፍ ቅዱስን ላይ ኢየሱስ አልተሰቀለም ያለው ኡስታዝ ሙሀመድ ከድር ሁለት ጥቅሶችን አንስቷል እነሱም;

1⃣የዮሃንስ ወንጌል 7፣32
ፈሪሳውያንም ሕዝቡ ሰለ ርሱ እንደዚህ፡ሲያንጐራጕሩ ሰሙ የካህናት፡አለቃዎችም ፈሪሳውያም፡
ሊይዙት ሎሌዎችን ላኩ።
ኢየሱስም ገና ጥቂት ጊዜ፡ከእናንተ፡ጋራ እቈያለኹ ወደላከኝም እኼዳለኹ።
ትፈልጉኛላችኹ አታገኙኝምም እኔም፡ወዳለኹበት እናንተ ልትመጡ አትችሉም፡አለ።
2⃣የዮሃንስ ወንጌል 8፣21
ኢየሱስም ደግሞ እኔ እኼዳለኹ፡ትፈልጉኛላችኹም በኀጢአታችኹም፡ትሞታላችኹ እኔ፡
ወደምኼድበት እናንተ ልትመጡ፡አትችሉም አላቸው።
አይሁድም እኔ ወደምኼድበት እናንተ፡ልትመጡ አትችሉም ማለቱ፡ራሱን፡ይገድላልን እንጃ አሉ።
እናንተ ከታች ናችኹ እኔ ከላይ ነኝ እናንተ፡ከዚህ ዓለም ናችኹ እኔ ከዚህ ዓለም፡
አይደለኹም።
እንግዲህ በኀጢአታችኹ ትሞታላችኹ አልዃችኹ እኔ እንደኾንኹ ባታምኑ፡ዳ በኀጢአታችኹ
ትሞታላችኹና አላቸው።

እነዚህን ጥቅሶች ብቻ በመንሳት ሙሉ መፀሀፉ ሳያነብ #ክርስቶስ #አልተሰቀለም በማለት #ለቀጠፈው #ቅጥፈት መልስ ተሰጥቶበታል።
👉በመጀመርያ ክርስቶስ አምላካችን #እንደሚሰቀል ሲያስተምር ነበር
ከዚያን ቀን ጀምሮ #ኢየሱስ ወደ ኢየሩሳሌም ይሄድ ዘንድ ከሺማግሌወችና #ከካህናት አለቆች ከፃፊወችም #ብዙ #መከራ ይቀበልና #ይገደል ዘንድ #በሶስተኛውም ቀን #ይነሳ ዘንድ እንዲገባው #ለደቀመዛሙርቱ ይገልጥላቸው ጀመር።


ማቴወስ ወንጌል 16፣21 ከዚያን ቀን ዠምሮ ኢየሱስ ወደ #ኢየሩሳሌም #ይኼድ ዘንድ ከሽማግሌዎችና ከካህናት አለቃዎች
ከጻፊዎችም ብዙ #መከራ #ይቀበልና #ይገደል ዘንድ #በሦስተኛውም ቀን ይነሣ ዘንድ እንዲገባው ለደቀ
መዛሙርቱ #ይገልጥላቸው ጀመር።
👇👇👇
ማቴወስ ወንጌል 20፣18
እንሆ ወደ ኢየሩሳሌም እንወጣለን #የሰው #ልጅም ለካህናት አለቃዎችና ለጻፊዎች #ይሰጣል #የሞት
#ፍርድም #ይፈርዱበታል👈
ሊዘባበቱበትም ሊገርፉትም #ሊሰቅሉትም #ለአሕዛብ #አሳልፈው ይሰጡታል #በሦስተኛውም ቀን ይነሣል አላቸው።
በዚያን ጊዜ የዘብዴዎስ ልጆች እናት ከልጆቿ ጋራ #እየሰገደችና አንድ ነገር እየለመነች ወደ ርሱ #ቀረበች

የዮሃንስ ወንጌል 7፣33
#ኢየሱስም #ገና #ጥቂት ጊዜ ከእናንተ ጋራ #እቈያለኹ ወደላከኝም እኼዳለኹ።
ትፈልጉኛላችኹ #አታገኙኝምም እኔም፡ወዳለኹበት እናንተ ልትመጡ አትችሉም
እዚጋ እየተናገር ያለው ለአይሁዶች ነው።
ጥቂት ጊዜ👈 እቆያለው ወደላከኝም እሄዳለው ትፈልጉኛላችሁ አታገኙኝም ወዳለሁበትም ልትመጡ አትችሉም ብሎ ለአይሁድ ነው የተናገረው።።
👇👇👇👇👇
የዮሃንስ ወንጌል 13፣33
አስቀድሞ ለአይሁድ ይነግራቸው ነበር።

ልጆች ሆይ ገና ጥቂት ጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ ትፈልጉኛላችሁ #ለአይሁድም እኔ #ወደምሄድበት እናንተ #ልትመጡ አይቻላችሁም #እንዳልኋቸው አሁን #ለእናንተ ደግሞ እላችኋለሁ።
እዚህ ጋ እየተናገረ ያለው ደግሞ በሶስተኛው ቀን ሞትን ድል አድርጎ እንደሚነሳና #እንደሚያርግ ነው እየነገራቸው ያለው።

#ሞትን #ድል #አድርጎ ወደ አባቱስ አርገ ወይ ለሚለው!
👇👇

የሐዋርያት ስራ 1፣9
===
ይህንም ከተናገረ በዃላ እነርሱ እያዩት #ከፍ #ከፍ አለ #ደመናም #ከዐይናቸው #ሰውራ #ተቀበለችው
ርሱም ሲኼድ ወደ ሰማይ ትኵር ብለው ሲመለከቱ ሳሉ እንሆ #ነጫጭ #ልብስ የለበሱ ኹለት
ሰዎች በአጠገባቸው ቆሙ
ደግሞም የገሊላ ሰዎች ሆይ ወደ ሰማይ እየተመለከታችኹ ስለ ምን ቆማችዃል ይህ ከእናንተ
ወደ ሰማይ የወጣው #ኢየሱስ ወደ ሰማይ #ሲኼድ #እንዳያችኹት እንዲሁ #ይመጣል #አሏቸው። ለምንድነው ድጋሜ የሚመጣው? #ለፍርድ🙏
ስለዚህ ካረገና ከሄደ በሁዋላ አይሁድ እንደማያገኙት ነው የዮሃንስ ወንጌል 7፣33 ላይ ያለው ቃል የሚናገረው። ክርስቶስ አታገኙኝም ያላቸው ለዚህ ነው እንጂ አትይዙኝም አልሰቀልም እያላቸው አይደለም ምክንያቱም ከላይ እንደሚይዙትና እንደሚሰቀል ስለተናገረ።

#አይሁድ #እንደያዙት👇
የማቴወስ ወንጌል 26፣48-57
=====
#አሳልፎ #የሚሰጠውም #የምስመው #ርሱ ነው #ያዙት #ብሎ ምልክት ሰጥቷቸው ነበር።
ወዲያውም ወደ ኢየሱስ ቀረበና መምህር ሆይ ሰላም ለአንተ ይኹን ብሎ #ሳመው
ኢየሱስም ወዳጄ ሆይ ለምን ነገር መጣኽ አለው።በዚያን ጊዜ #ቀረቡ #እጃቸውንም #በኢየሱስ
ላይ #ጭነው #ያዙት
#ኢየሱስን #የያዙትም #ጻፊዎችና ሽማግሌዎች #ወደተከማቹበት ወደ ሊቀ ካህናቱ ወደ ቀያፋ #ወሰዱት
👇👇👇
የማርቆስ ወንጌል 14፣44
===
አሳልፎ የሚሰጠውም የምስመው እርሱ ነው #ያዙት #ተጠንቅቃችሁም #ውሰዱት ብሎ ምልክት ሰጥቶአቸው ነበር።#ይህን ያለው ማነው? #እሁዳን

#እነርሱም #እጃቸውን #በእርሱ ላይ #ጭነው #ያዙት

በተጨማሪም የሉቃስ ወንጌል 22፣63
#ኢየሱስንም #የያዙት ሰዎች #ይዘብቱበትና #ይደበድቡት #ነበር

የሐዋርያት ስራ 1፣16
======
ወንድሞች ሆይ ኢየሱስን ለያዙት መሪ ስለኾናቸው ስለ ይሁዳ መንፈስ ቅዱስ አስቀድሞ በዳዊት
አፍ የተናገረው የመጽሐፍ ቃል ይፈጸም ዘንድ ይገ፟ባ፟ ነበር፤

ስለዚህ #አልያዙትም የሚለው #የሰይጣን #የዳቢሎስ #አስተምህሮ እንጂ #የመፀሀፍ ቅዱስ አስተምህሮ #አይደለም

(አልሰቀሉትም ወይ የሚለውን ደግሞ እንመልከት )
👇👇👇👇
የማቴወስ ወንጌል 28፣5
=======
መልአኩም መልሶ #ሴቶቹን አላቸው እናንተስ #አትፍሩ #የተሰቀለውን #ኢየሱስን #እንድትሹ
#ዐውቃለኹና
ስለዚህ የክርስቶስን መሰቀል መልአኩ እራሱ መስክሮለታል።

የማርቆስ ወንጌል 16፣6
====
ርሱ ግን አትደንግጡ የተሰቀለውን የናዝሬቱን ኢየሱስን ትፈልጋላችኹ #ተነሥቷል በዚህ #የለም
ስለዚህ ክርስቶስ አምላካችን ተሰቅሏል ማለት ነው።
የዮሃንስ ወንጌል 19፣20
ክርስቶስ አምላካችን የተሰቀለበትን ስፍራ ይናገራል።
አሁንም የዮሃንስ ወንጌል 19፣32
ጭፍራዎችም መጥተው የፊተኛውን ጭን ከርሱም ጋራ #የተሰቀለውን የሌላውን ጭን ሰበሩ።
የዮሃንስ ወንጌል 19፣41
#በተሰቀለበትም #ስፍራ #አትክልት #ነበረ👈
ሮሜ 6፣6
===
ከእንግዲህስ ወዲያ ለኀጢአት እንዳንገዛ #የኀጢአት #ሥጋ #ይሻር ዘንድ አሮጌው ሰዋችን ከርሱ ጋራ
እንደ #ተሰቀለ #እናውቃለን
የሞተስ #ከኀጢአቱ #ጸድቋልና
እንግዲህ መፀሀፍ ቅዱስ እንደተሰቀለ እየተናገረ ኢአማንያን ግን አልተሰቀለም ማለታቸው የዳቢሎስ ምርኮኞች በመሆናቸው ነው።
1ኛቆሮ 1፣13
====
ክርስቶስ ተከፍሏልን ጳውሎስስ ስለ እናንተ #ተሰቀለን ወይስ #በጳውሎስ ስም ተጠመቃችኹን።
እኛ ግን #የተሰቀለውን #ክርስቶስን #እንሰብካለን ይህም #ለአይሁድ#ማሰናከያ #ለአሕዛብም #ሞኝነት ነው።
ክርስቶስን አልተሰቀለም እሚል ሞኝና አህዛብ ነው።

1ኛ ቆሮ 2፣2
====
በመካከላችኹ ሳለኹ ከኢየሱስ ክርስቶስ፡በቀር #ርሱም አንደ #ተሰቀለ ሌላ ነገር እንዳላውቅ ቈርጬ ነበርና።
ገላቲያ 3፣1
====
የማታስተውሉ የገላትያ ሰዎች ሆይ በዐይናችኹ ፊት #ኢየሱስ #ክርስቶስ እንደ #ተሰቀለ ኾኖ #ተሥሎ
ነበር #ለእውነት #እንዳትታዘዙ #ዐዚም ያደረገባችኹ ማን ነው?
ክርስቶስ አልተሰቀለም እያሉ በደረቁ እሚሞግቱት አህዛብ ለእውነት እንዳይታዘዙ አዚም ያደረገባቸው ሰይጣን ዳቢሎስ ነው።
አሁንም ወደ ገላቲያ ሰወች 6፣14
====
ገር ግን ዓለም ለእኔ የተሰቀለበት #እኔም ለዓለም #የተሰቀልኹበት ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ
#መስቀል #በቀር ሌላ #ትምክሕት #ከእኔ #ይራቅ
ስለዚህ ክርስቶስ አምላካችን ተሰቅሏል።
ሙስሊም ወገኖቻችን መፀሀፍ ቅዱስን ስታነቡ ከኦሪት ዘፍጥረት እስከ ራዕይ ዮሃንስ ነውና ሙሉውን አገላብጡ።
ኡስታዝም የአላህን አጭበርባሪነት ለመደበቅ ክርስቶስ አልተሰቀለም ለማለት ሁለት ጥቅሶችን አንጠልጥለህ ብቻ ለትችት አትሩጥ።

#ከወንድም #ፍቅረ ት/ት የተወሰደ

@YEMEREJAWECHSIBESEBCHANNEL
ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ለመናፍቃንና ለአህዛብ መልስ አላት! pinned «#ክርስቶስ #አልተሰቀለም ብለው ለሚቀጥፊት #ኢአማኒያን #ሙስሊም ወገኖቻችን #የተሰጠ ምላሽ! በመጀመርያ በመፀሀፍ ቅዱስ መነፀር ሆነን ቁርአንን ካየነው ብዙ ስህተት አለበት እንዳለው ኡስታዝ አቡሀይደር በተሳሳተው ቁርአን እይታ መፀሀፍ ቅዱስን ላይ ኢየሱስ አልተሰቀለም ያለው ኡስታዝ ሙሀመድ ከድር ሁለት ጥቅሶችን አንስቷል እነሱም; 1⃣የዮሃንስ ወንጌል 7፣32 ፈሪሳውያንም ሕዝቡ ሰለ ርሱ እንደዚህ፡ሲያንጐራጕሩ…»
የጥያቄ መልስ

" እኔ ከራሴ አንዳች ላደርግ አይቻለኝም፤ እንደ ሰማሁ እፈርዳለሁ ፍርዴም ቅን ነው፥ የላከኝን ፈቃድ እንጂ ፈቃዴን አልሻምና።"
(የዮሐንስ ወንጌል 5:30)

ጌታ ይህን ቃል የተናገረው የአምላክነት ብቃት ሳይኖረው ቀርቶ ሳይሆን ስለ ሦስት ነገር ነው።

አንደኛው ትህትናን ለማስተማር ነው በተለይ ለመምህራን። የወንጌል መምህራን መጽሐፍትን አመስጥረው ቢተረጉሙ የሰዎችን ልቡና በትምህርታቸው ቢማረኩ በእውቀቴ በችሎታዬ ይህን አደረኩ ብለው እንዳይመጻደቁ ይህን ከእግዚአብሔር በተሰጠኝ ጸጋ ነው ብለው ራሳቸውን በትህትና ዝቅ ማድረግን እንዲማሩ ነው። ለዚህም በእግዚአብሔር ቸርነት መሆኑን አውቀው እኔ ከራሴ አንዳች ላደርግ አይቻለኝም ማለትን እንዲማሩ ነው።

ሁለተኛው፡- ደካማ ስጋ መልበሱን ለማስረዳት ነው ። አይሁድ ኢየሱስን ይመለከቱት የነበረው እንደ ተራ ሰው ነበር እንጅ መለኮት የተዋህደውን ሥጋ ለብሶ በመካከላቸው የሚመላለስ አምላክ መሆኑን አላወቁም ነበር። " አውቀውስ ቢሆን የክብርን ጌታ ባልሰቀሉት ነበር እንደተባለ" 1ቆሮ 2፣8 ኃይልና ስልጣኑ መለኮታዊ ማንነቱ ላይ መሆኑን ሲገልጽላቸው።

ሦስተኛ፡- ሥላሴ በፍቃድ አንድ መሆናቸውን ለማስረዳት ነው። በተለየ አካሉ ሥጋ ለብሶ በምድር የተገለጠው ወልድ ነው። ቢሆንም ወልድ ሥጋ የለበሰው በራሱ ፍቃድ ብቻ ሳይሆን በአባቱም ፍቃድ በርሱም ፍቃድ በመንፈስ ቅዱስም ፍቃድ መጥቶ አዳነን።

ያለ ልብ ፍቃድ የሚወጣ ቃል የለም ለዚህም ይህን ቃል ተናግሯል

@YEMEREJAWECHSIBESEBCHANNEL
#ሆሳዕና #አጭር #ግጥም🌿

አንቺ ኢየሩሳሌም ጌታ የመረጠሽ
አለምሽ ዛሬ ነው ክርስቶስ መጣልሽ
አንቺ የፂዮን ልጅ እጅግ ደስ ይበልሽ
ቅዱስ ትሁት ሆኖ ንጉስሽ መጣልሽ

ቀድሞም ነግሮሽ ነበር በትንቢታዊ ቃል
በአህያ ግልገል ላይ ተቀምጦ ይመጣል
ብሎ ዘካሪስ እንደተናገረ
በማቴወስ ወንጌል ትንቢቱን ፈፀመ
ጼጥሮስን ዮሃንስን ላከና ኢያሪኮ
በትዕዛዝ አስመጣት እሷን አስፈትቶ

ኪሩቤል ሱራፌል የሚፈሩት ጌታ
ፍቅርን ትህትና ሊያስተምረን ለኛ
ተቀምጦ መጣ በአህያ ሁርንጫ

ልብስ ሰውነትን እምደሚሸፍነው በደላችን ሸፈንክ በማለት ያለው ሰው ያነጥፍ ነበረ እንዳይቆረቁረው

ፀሀፍት ፈሪሳዊን እስኪደንቅ ድረስ
ህፃናት ዘመሩ ሆሳዕና ብለው ጌታን በማወደስ

እነዛም ፀሀፍታን በህፃናት መዝሙር እጅጉን ቀኑና በክርስቶስ ምግባር በጣም ተከፉና በቃል ከሰሷቸው ድንገት ተነሱና
ክርስቶስም አለ እኔማ እሰማለው

በመዝሙረ ዳዊት ከህፃናትና ከሚጠቡት አፍ ላይ ምስጋና ለራስህ አዘጋጅ ይል የልወይ ብሎም ጠየቃቸው?

እነዛም ፈሪሳዊ በግርምት ዝምታን ተውጠው ቀሩና ጌታም ነገራቸው ጥቅሱን አወጣና።

በንፁህ አንደበት ዘንባባውን ይዘው አመስግነውታል ሆሳዕና እያሉ ህፃናት በእልልታው

አህዛብ ሆይ ንቁ መዳን በክርስቶስ መሆኑን አትዘንጉ ተቀበሉ እውነቱን ከባርነት ውጡ!


ወስብሀት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክብር🙏🌿🌿

@YEMEREJAWECHSIBESEBCHANNEL
በሰሞነ ህማማት #የአብይ ፆም #መጨረሻ #ሶስተኛ #ክፍል #ስምንተኛ #ሳምንት ነው።
#ከሰኞ እስከ #እሁድ ያሉት የእለታቱ #ስያሜወች👂

#ሰኞ #መርገመ #በለስ

ማለዳም ሲያልፉ #በለሲቱን #ከሥሯ #ደርቃ አይዋት።
#ጴጥሮስም ትዝ ብሎት #መምህር ሆይ እንሆ #የረገምኻት #በለስ #ደርቃለች አለው።
የማርቆስ ወንጌል 11፣20

#ማክሰኞ #የጥያቄ #ዕለት

ወደ መቅደስም ገብቶ ሲያስተምር የካህናት አለቃዎችና የሕዝብ ሽማግሌዎች ወደ ርሱ
ቀረቡና በምን ሥልጣን እነዚህን ታደርጋለኽ ይህንስ ሥልጣን ማን ሰጠኽ አሉት።
ኢየሱስም መልሶ እኔ ደግሞ አንዲት ነገር እጠይቃችዃለኹ እናንተም ያችን ብትነግሩኝ እኔ
ደግሞ እነዚህን በምን ሥልጣን እንዳደርግ እነግራችዃለኹ።
የማቴወስ ወንጌል 21፣23
#ሮብዕ #ምክረ #አይሁድ
#ሀሙስ #የፀሎት ስርአትን ያስተማረበት
#አርብ በእለተ አርብ የተፈጠረው አዳም ባጠፋው ጥፋት አርብ ለፈጠረው የሰው ልጅ አርብ ቀን ቤዛ ሆነለት
#ቅዳሜ የተሻረች ቅዳሜ
ይባላሉ

@YEMEREJAWECHSIBESEBCHANNEL
#ሰሞነ #ህማማት😭
#ጌታችን #የተቀበላቸው
#13ቱ #ህማማተ #መስቀል
ሰሞነ ህማማት ከሌሎች እለታት እንዴት ይለያል?👆👂

ትንቢተ ኢሳያስ 53፣1-4
======
#የሰማነውን #ነገር ማን #አምኗል #የእግዚአብሔርስ #ክንድ ለማን #ተገልጧል
በፊቱ እንደ #ቡቃያ #ከደረቅም መሬት እንደ ሥር አድጓል #መልክና #ውበት #የለውም ባየነውም ጊዜ
#እንወደ፟ው ዘንድ #ደም ግባት #የለውም
#የተናቀ #ከሰውም #የተጠላ #የሕማም ሰው #ደዌንም #የሚያውቅ ነው ሰውም ፊቱን እንደሚሰውርበት
የተናቀ ነው እኛም አላከበርነውም።

#በእውነት #ደዌያችንን #ተቀበለ #ሕመማችንንም ተሸክሞአል እኛ ግን እንደ ተመታ በእግዚአብሔርም እንደ ተቀሠፈ እንደ ተቸገረም #ቈጠርነው
እርሱ ግን ስለ #መተላለፋችን #ቈሰለ #ስለ #በደላችንም #ደቀቀ የደኅንነታችንም ተግሣጽ በእርሱ ላይ ነበረ #በእርሱም #ቍስል #እኛ #ተፈወስን
እኛ ሁላችን እንደ በጎች ተቅበዝብዘን ጠፋን ከእኛ እያንዳንዱ ወደ ገዛ መንገዱ አዘነበለ #እግዚአብሔርም #የሁላችንን #በደል #በእርሱ #ላይ #አኖረ😭😭

#የሰው #ልጅ #የጠፋውን #ሊፈልግና ሊያድን #መጥቶአለና አለው።
(የሉቃስ ወንጌል 19፣10)

#በመጋቤ #ሀዲስ #ሮዳስ #ታደሰ🌺🎙

@YEMEREJAWECHSIBESEBCHANNEL
#ሺሕ #ዓመት በፊትኽ #እንዳለፈች/እንደ #ትናንት ቀን እንደ #ሌሊትም ትጋት ነውና።
===
መዝሙረ ዳዊት 89፣4

እናንተ ግን #ወዳጆች ሆይ በጌታ ዘንድ #አንድ ቀን እንደ #ሺሕ #ዓመት #ሺሕ #ዓመትም እንደ #አንድ #ቀን እንደ #ኾነ ይህን አንድ ነገር #አትርሱ
ለአንዳንዶች #የሚዘገይ #እንደሚመስላቸው ጌታ ስለተስፋ ቃሉ #አይዘገይም ነገር ግን ዅሉ ወደ
ንስሓ እንዲደርሱ እንጂ ማንም እንዳይጠፋ ወዶ ስለ እናንተ ይታገሣል።
===
2ኛ ጴጥሮስ

#ይህን ቤተ መቅደስ #አፍርሱት #በሦስት ቀንም #አነሣዋለሁ አላቸው።
ስለዚህ #አይሁድ ይህ ቤተ #መቅደስ #ከአርባ #ስድስት #ዓመት ጀምሮ ይሠራ ነበር አንተስ በሦስት ቀን #ታነሣዋለህን? አሉት።
#እርሱ ግን #ስለ #ሰውነቱ #ቤተ #መቅደስ ይል ነበር።
===
የዮሃንስ ወንጌል 2፣19

#በወንድም #ፍቅረ🌺

@YEMEREJAWECHSIBESEBCHANNEL
ብዙ #ውሻዎች #ከበ፟ውኛልና #የክፋተኛዎች ጉባኤም ያዘኝ #እጆቼንና #እግሮቼን #ቸነከሩኝ
#ዐጥንቶቼ #ዅሉ #ተቈጠሩ #እነርሱም አዩኝ #ተመለከቱኝም
#ልብሶቼን #ለራሳቸው #ተከፋፈሉ #በቀሚሴም ላይ ዕጣ #ተጣጣሉ

(መዝሙረ ዳዊት 22፣16)

#ከዐሥራ #ኹለቱ አንዱ #ዲዲሞስ የሚሉት #ቶማስ #ኢየሱስ በመጣ ጊዜ ከነርሱ ጋራ አልነበረም።
ሌላዎቹም ደቀ #መዛሙርቱ #ጌታን አይተነዋል አሉት።ርሱ ግን #የችንካሩን #ምልክት #በእጆቹ
ካላየኹ #ጣቴንም #በችንካሩ ምልክት ካላገባኹ እጄንም በጐኑ ካላገባኹ አላምንም አላቸው።
#ከስምንት ቀን በዃላም ደቀ መዛሙርቱ ደግመው በውስጥ ነበሩ #ቶማስም ከነርሱ ጋራ
ነበረ።#ደጆች ተዘግተው ሳሉ #ኢየሱስ መጣ #በመካከላቸውም ቆሞ ሰላም ለእናንተ ይኹን አላቸው።
ከዚያም በዃ #ቶማስን #ጣትኽን ወደዚህ #አምጣና #እጆቼን እይ #እጅኽንም #አምጣና #በጐኔ
አግባው #ያመንኽ እንጂ ያላመንኽ አትኹን አለው።
ቶማስም ጌታዬ አምላኬም ብሎ መለሰለት።

(የዮሃንስ ወንጌል 20፣25-26)

#በወንድም #ፍቅረ🌺

@YEMEREJAWECHSIBESEBCHANNEL