Bilaluna Edris
558 subscribers
3.35K photos
276 videos
50 files
2.3K links
♡_ወደ መልካም ነገር ያመላከተ ሰው የሰራ ሰውን አጅር ያህል ያገኛል"(አመላካች የሰሪውን ምንዳ ያገኛል)(ﷺ)

« ከናንተም ወደ በጎ ነገር የሚጠሩ ፣ በመልካም ስራም የሚያዙ ከክፉ ነገርም የሚከለክሉ ሕዝቦች ይኑሩ» ﷻ
                 ቁርኣን[ 3:104 ]


መወያያ ግሩፓችን ☞ https://t.me/+1qmNqy265XoyNGY0
Download Telegram
በአፋር ክልል የሰው ሰራሽ እግር እና እጆች የመግጠም ስራ ተጀመረ።
****

የአፋር ክልል ሴቶች እና ህፃናት ቢሮ ከ ሰመራ ዪኒቨርሲት ጋር በመተባበር አርተፍሻል (የሰው ሰራሽ) እግር እና እጆችን ለአካል ጉዳተኞች የመስራት እና የመግጠም ስራን በዛሬው ቀን አስጀምረዋል።

በተፈጥሮም ወይም ከግዜ በኋላ በተለያዩ ምክንያቶች እና አደጋዎች አካለ ጎደሎነት ደርሶባቸው የነበሩ ሆነው የአደጋው ቁስል ለደረቀላቸው አካል ጉዳተኞች በሙሉ አሁን የሰው ሰራሽ (አርቴፊሻል ) እግር እና እጅ የመግጠም ስራ እንዲሁም የ ፊዝዮቴራፒ አገልግሎትን የክልሉ ሴቶች እና ህፃናት ቢሮ እና የሠመራ ዪኒቨርስቲ በኢትዮጵያ የህንድ ኢሚባሲ እና የፌዴራል ሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚንስቴር ጋር በጋራ በመሆን በሰመራ ዪኒቨርሲት ስር በሆነው በሎግያ ከተማ በሚገኘው የሎጊያ ሆስፒታል ቅጥር ግቢ ውስጥ በተዘጋጀው ግዜያዊ አገልግሎት መስጫ ላይ አገልግሎት መስጠቱ ተጀምሯል።

ስለሆነም የአገልግሎቱ ተጠቃሚ መሆን የሚፈልግ በክልሉ የሚገኝ ማንኛውም አካል ጉዳተኛ ከላይ ወደተጠቀሱት ተቋሞች በመሄድ በመመዝገብ እና የተመዘገቡበትን ማስረጃ ወደ ሎግያ ሆስፒታል ይዞ በመሄድ እና በመቅረብ አገልግሎቱን ማግኘት እንደሚችሉ ተቋሞቹ በጋራ በሰጡት ማቦራሪያ ገልፀዋል። በተጨማሪም ከዚህ በፊት ተመዝግበው እየተጠባበቁ የነበሩ አካል ጉዳተኞች በአሁኑ ግዜ የአገልግሎቱ ተጠቃሚ እንዲሆኑ እየደረገ እንደሆነ ገልፀው ከዚህ በፊት ምዝገባ ያላደረጉ ደግሞ ምዝገባ እያደረጉ የአገልግሎቱ ተጠቃሚ መሆን እንደሚችሉ ተገልጿል።

የቴሌግራም ቻናሌን በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ 👇
@ https://t.me/Xuqal
የሸዋልን Vibe ከምናጣ...😊

ኢብን አጧኢላህ አስከንደሪ ራህመቱላህ አለይህ በሒከማቸው ላይ ለሩሕ ስንቅ የሚሆንን ንግግር ያሰፍራሉ: "አላህ አንድ ነገር ከሰጠህ በኃላ በተመሳሳይ ሁኔታ ከሌላ ነገር ደግሞ ሊከለክልህ ይችላል። ከዛ ደግሞ አቆይቶ ሊሰጥህ ይችላል! አላህ ይህንን የሚያደርገው ፀጋውን ለመቆጠብ ብሎ ብሎም ስላልቻለ አይደለም። አላህ ከዚህ የፀዳ ሉዓላዊ ጌታ ነው! ግን አላህ ከአንድ ነገር የሚከለክለን እሱን የጠየቅነው ጉዳይ ላለንበት ሁኔታና ተጨባጭ የማይሆን እንደሆነ ስለሚያውቅ ነው። አውቆም አይዘነጋንም! ጊዜው ምንም ያክል ይርዘም ለኛ የተሻለ የሚሆንበት ሰአት ላይ የጠየቅነውን ይሰጠናል። በየትኛውም ሁኔታ ላይ አላህን እንመነው!" ይላሉ! 😊

ውስጥን አያረጋጋም?! ሰላም አለው! የጌታዬ ነገር እንዲህ ነው። 🩵

ሰይዲና ኡመር ኢብኑል ኸጣብ ረዲየላሁ አንህ'ም አንድ ምርጥዬ ንግግር አለቻቸው።

"አላህ በመከራዎች ውስጥ እንዳልፍ ሲያደርገኝ በነዚህ ችግሮች ውስጥ እርሱ ለኔ የዋላቸው ሶስት ፀጋዎች ይታዩኛል ይላል

1ኛ የገጠመኝ መከራ ቀለል እንዲለኝ ማድረጉና ከዚህ የከፋ ችግሮች ውስጥ መክተት እየቻለ በዚህ ብቻ መተዉ ከዋለልኝ ፀጋዎች ውስጥ ነው! ...

2ኛ የመከራው መንስዔ የዱንያ ሐጃዎቼ ላይ መሆኑና፤ በእምነቴ ላይ እንዲሆን ማድረግ እየቻለ በዲን ጉዳይ ላይ መከራ ውስጥ አለመክተቱ ከኒዕማዎቹ ውስጥ ነው! ...

3ኛ የኔ በመከራዎቹ ውስጥ መታገስና በእርሱ መተማመን አላህ ለገባሁበት መከራ የውመል አኺር ላይ መሸለሙ በችግሮቹ ውስጥ ከዋለልኝ ፀጋዎች ሁሉ የበለጠው ነው።" ይላሉ አሚረል ሙዕሚኒን! 😊

አላህ በመከራዎቻችን ውስጥ የምንታገስ፤ በእርሱ ውሳኔዎች ሙሉ ለሙሉ የምንተማመንና የምናምን ባሮች ያድርገን! 🤲

@ https://t.me/Xuqal
"አላህ ሆይ ጨለማን ገፈህ በብርሀን እንደምትተካው ፤ በወንጀል ብዛት የጨለሙ ቀልቦቻችንን በኑርህ አብራልን" 🤲
«ከበደሎች ሁሉ ትልቁ በደልና ከድንቁርና ሁሉ ትልቁ ድንቁርና ማለት ሰዎች እንዲያልቁህና እንዲያተልቁህ እየፈለክ፤ የአንተ ልብ ግን አላህን ከማተለቅና ከማላቅ ባዶ ከሆነ ነው።»

ኢብኑል ቀዪም ረሒመሁሏህ
“አብዛኛው የአደም ልጅ ስህተት በምላሱ የሚፈፅመው ነው።”
ረሱል (ﷺ)
ልቡ ውስጥ የአኼራ ቤቱን አሳምሮ እየገነባ ያለን ጀግና የዱንያ ቤቱን ቢያፈርሱበት ምን ሊጎድልበት? ምንም!☝️
,,,,,,,,
"አሏህ አዩብን የአንበጣ ወርቅ ሲያወርድላቸው እሱን ሲሰበስቡ ከወቀሳቸው ማይገባውን ጥቅም የሰውን ሃቅ ሀራሙን ሀላሉን ሚያግበሰብሰውስ እንዴት ይሆን?"

ሸይኽ ኢልያስ አወል
በዙሪያህ የነበሩ የትላንትና ሰዎችን አስታውስ!!
የትሄዱ ብለህም ጠይቅ?
“የአደም ልጅ ባነጋ ጊዜ የሰውነት አካላት በጠቅላላ ለምላስ እጅ ይሰጣሉ። እንዲህም ይሏታል፦ በኛ ጉዳይ ላይ አላህን ፍሪ በጥሩም ሆነ በመልካም አንቺን ተከታይ ነንና። አንቺ ከተስተካከልሽ እኛም እንስተካከላለን ከተበላሸሽ ግን እኛም እንበላሻለን ይሏታል።”
ረሱል ﷺ
ለሪል ስቴት በሊዝ የገዛውን መሬት ፡  ለሌላ  ጥቅም ያዋለው ናይጄሪያዊ ኳስ ተጫዋች ።

ጄጄ ኦካቻ ፡ ከቀድሞ የናይጄሪያ ቡድን ተጫዋችነቱ በተጨማሪ ፡ ብዛት ባላቸው የአውሮፓ ክለቦች ያሳይ በነበረው ድንቅ ብቃት አለም ያወቀውና ተደናቂነትን ያተረፈ ዝነኛ ኳስ ተጫዋች ነበር ።

ጄጄ ፡ ከእግር ኳስ አለም በይፋ ከተሰናበተ በኋላም በሀገሩ ናይጄሪያ ውስጥ በተለያዩ ቢዝነሶች ላይ ተሰማርቶ የቆየ ሲሆን ፡ በቅርቡ ባደረገው ነገር መነጋገሪያ ሆኗል ።

ኦካቻ  በሚኖርበት ከተማ. .. ለራሱና ለቤተሰቡ የሚሆን እጅግ ዘመናዊ መኖሪያ ቤት ሰርቶ ካጠናቀቀ በኋላ ፡ ለዴልታ ስቴት ማዘጋጃ ቤት ብዛት ያላቸው ቤቶችን ለመስራት ጠይቆ ሰፊ መሬት በሊዝ ይገዛል ።

በዚህ በወሰደው መሬት ላይም ባጠቃላይ ብዛታቸው መቶ የሚሆኑ  የተለያዩ ባለአንድና ሁለት መኝታ ቤት መኖሪያ ቤቶችንና ኮንደሚኒየሞችን ካሰራ በኋላ.....
በዴልታ ስቴት ለሚኖሩ በእድሜ ገፋ ላሉ .. ችግረኞችና የጎዳና ተዳዳሪዎች ሁሉንም ቤቶች ፡ በነጻ ሰጥቶ ሰውን አስገርሟል ።

ጄጄ  ሙሃመድ ያቪዝ ኦኮቻ ቤቶቹን ለነዚህ ሰወች ካስረከበ በኋላ እንደተናገረው. ..

እኔ ሚሊየን ዶላር  የፈጀ ቪላ ውስጥ እየኖርኩ ፡ ለጎዳና ተዳዳሪዎችና ችግረኞች ምንም ማድረግ አለመፈለግ እና አለማድረግ ሀጢያት (ወንጀል) ይሆናል ነገ አላህ ፊትስ ምን መልስ ይኖረኛል? ሲል ገልጿል።

( ናይጄሪያ በአለም የታወቁ ሀብታሞች ያሉባት ሀገር ብትሆንም ፡  ለመስጠት በራሱ የሚሰጥ ልብ ይፈልጋልና. ..  እነሱ ያላሰቡትን ኦካቻ አድርጎ አሳይቷቸዋል ።

@ https://t.me/Xuqal
መልክተኛው ﷺ

ተደበደቡ...ተንገላቱ .... ደሙም...🥺

እንባቸውን....ከተከበረው ውብ ፊታቸው እያበሱ... እንዲህ ነበር ያሉት ...ጌታዬ ሆይ ህዝቦቼን አላዋቂ ናቸውና ማራቸው 😞

أي رحمة سكنت قلبك يا رسول الله 🥰
صلى الله عليه وسلم 💕

لَقَدْ جَاءَكُمْ رَسُولٌ مِّنْ أَنفُسِكُمْ عَزِيزٌ عَلَيْهِ مَا عَنِتُّمْ حَرِيصٌ عَلَيْكُم بِالْمُؤْمِنِينَ رَءُوفٌ رَّحِيمٌ

ከጎሳችሁ የሆነ ችግራችሁ በእርሱ ላይ ጽኑ የሆነ፣ በእናንተ (እምነት) ላይ የሚጓጓ፣ በምእምናን (ላይ) ርኅሩኅ አዛኝ የኾነ መልክተኛ በእርግጥ መጣላችሁ፡፡

(ሱረቱ ተውባ :128)

ጁምዓ 🥰
@ https://t.me/Xuqal
እጅግ ልብ ሰባሪ ዜና 😏
የእስራኤል የብሔራዊ ደህንነት ቢሮ ኃላፊ ኢተማር ቢን ገፊር በደረሰበት ከባድ የመኪና አደጋ ወደ ሆስፒታል ተወስዷል።በአደጋው ልባቸው ለተሰበረ የኤምሬትና ጆርዳን መንግስታት እንዲሁም የአብረሐሚያ አባላት መፅናናትን እንመኛለን።🥴
ከቀናት በፊት ቢንገፊር:-"እስር ቤቶቻችን እየሞሉ ስላስቸገሩን፤ታሳሪዎችን በሞት መቅጣት አለብን።" የሚል መግለጫ አውጥቶ ነበር።
ከወራት በፊትም:-"ጋዛን በኒውክሌር መሳሪያ ማጥፋት ብቸኛው መፍትሄ ነው።" ሲል ተደምጦ ነበር።
"ያቅዳሉ አላህም ያቅዳል። ከእቅዶች ሁሉ ደግሞ የአላህ እቅድ በላጭ ነው"....ሱብሀነክ ☝️

@ https://t.me/Xuqal
"የዓይን ከእንባ መድረቅ ምልክቱ የልብ መድረቅ ነው፤ የልብ መድረቅ ምልክቱ ደግሞ ከመልካም ስራ ይልቅ ወንጀሎች ሚዛን መድፋታቸው ነው፤ ይህ የሚያስከትለው በአኼራ ቅጣትን ነው።"