Bilaluna Edris
558 subscribers
3.35K photos
276 videos
50 files
2.3K links
♡_ወደ መልካም ነገር ያመላከተ ሰው የሰራ ሰውን አጅር ያህል ያገኛል"(አመላካች የሰሪውን ምንዳ ያገኛል)(ﷺ)

« ከናንተም ወደ በጎ ነገር የሚጠሩ ፣ በመልካም ስራም የሚያዙ ከክፉ ነገርም የሚከለክሉ ሕዝቦች ይኑሩ» ﷻ
                 ቁርኣን[ 3:104 ]


መወያያ ግሩፓችን ☞ https://t.me/+1qmNqy265XoyNGY0
Download Telegram
ለአቅመ አዳም ስደርስ ማግባት እመኝ ነበር'ና በርግጥም ደርሼ አገባሁ። ግና ትዳር ያለ ልጆች አይጥምም ነበር። ልጅ ተመኘሁ፤ ልጆችንም ወለድኩም።

ለኔም ለልጆቼም ሚበቃን ቪላ እንዲኖረን ተመኘሁ። ተግቼ ሰርቼ ገንዘብ ያዝኩ'ና ቪላውን ገነባሁ።

ልጆቼ አድገው ጎረመሱ። ልድራቸው እና የልጅ ልጅ እንዲያሳዩኝ ተመኘሁ፤ በርግጥም ዳርኳቸው።

ግና አሁን ሰውነቴ ይደክም ጀመር፤ እድሜዬም ስራ ትቼ ቤት እንድቀመጥ ያስገድደኝም ያዘ። ስራዬን ሰው ተክቼ ቤት ጠቅልዬ ለመግባት ተመኘሁ፤ በርግጥም ቤት ገባሁ።

ያኔ ስራ አጥ ሆኜ ቤት እውል እንደነበረ ሁላ በተመሳሳይ መልኩ በስተርጅናዬም ላይ ቤት መዋል ጀመርኩ።

ግና ምኞት አሁንም ያማልለኝ ይዟል።

ቁርአንን መሐፈዝ ተመኘሁ፤ ግና አዕምሮዬ ዝሏል።
የሱና ፆሞች ላይ ለማተኮር ተመኘሁ፤ ግና ጤንነቴ ከድቶኝ ኑሯል።
የለይል ሰላት ላይ ለመበርታት ወሰንኩ፤ ግና እግሮቼ ሊሸከሙኝ ተሳናቸው።

ነቢ ሰዐወ ያሉት ነገር አሁን ገባኝ።

5 ነገር ሳይቀድምህ በ5 ነገር ተጠቀም
- ወጣትነትህን እርጅና ሳይቀድምህ
- ጤንነትህን በሽታ ሳይቀድምህ
- ሀብትህን ድህነት ሳይቀድምህ
- ነፃ ግዜህን የግዜ እጥረት ሳይገጥምህ
- ህይወትህን ሞት ሳይቀድምህ

የአዛውንቱ ማስታወሻ

@ https://t.me/Xuqal
አንተ አላህ ዘንድ ያለህን ቦታ ማወቅ ከፈለግክ አላህ አንተ ዘንድ ያለውን ቦታ ተመልከት !
ኡመር ኢብን ኸጣብ ረ.ዐ አምርን ረ.ዐ  በሾሙት ግዜ እንዲህ አሉት "አንድ ሌባ የመጣህ ግዜ ምን ታደርገዋለህ? አምርም "እጁን እቆርጠዋለኋ" ብሎ መለሰ ኡመርም ረ.ዐ መለሱ "እንግዲያውስ እኔም አንድ  ችግርተኛ ወደ እኔ መጥቶ እሮሮውን ካሰማ ያንተን እጅ እቆርጠዋለሁ።" አሉት
#ፍትህ #መሪነት #ሀቀኝነት
     
@ https://t.me/Xuqal
ሲራቸዉን ከምወደዉ ዑሰታዝ አንደበት 😍

የሰው ዘር አይነታ የሆኑትን ታላቅ ነቢይ ታሪክ በተከታታይ የማቅረብ ሃሳብ ሰንቂያለሁ፤ ኢንሻአላህ።
የዚህ ትምህርት ዓላማ፡-

🔘ነቢዩ ሙሐመድን(ሰዓወ) በዝርዝር መተዋወቅ፣

🔘ልባችንን በፍቅራቸው ማነፅ፣

🔘በርሳቸው ህይዎት ውስጥ ኢስላምን በጥልቅ መገንዘብ፣

🔘በዱንያ ጊዚያዊ ቆይታችን የርሳቸውን ፈለግ በመከተል የደስታ ህይዎት መኖር፣

በመጨረሻም፡-

🔘በዘለዓለማዊው ዓለም የርሳቸውን ጉርብትና ማግኘት ይሆናል።

አዛኙ ጌታችን ሆይ! ታላቁን ነቢይ የማወቅን፣ የመውደድን፣ የመከተልን ፀጋ ለግሰን። በዘለዓለማዊው ዓለምም ሸፋዓቸውን ከሚያገኙት፣ ከሐውዳቸው ከሚጠጡትና የርሳቸውን ጉርብትና ከሚቸሩት ደጋጎች ተርታ አሰልፈን።
አላሁመ አሚን🤲🤲🤲

🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹
መስታዎሻ፡
ትምህርቶቹ በሳምንት አንድ ቀን -ዘወትር ሰኞ- በሚከተሉት የማህበራዊ ሚዲያ ገፆች የሚተላለፉ ይሆናሉ👇

Telegram:- https://t.me/UstazBedruHussein
Facebook:- Engr/Ustaz Bedru Hussein - በድሩ ሁሴን
Tiktok፡- @ustazbedruhussein
#ዕውቀት እና #ጥበብ በጀሰድ 👌
በአፋር ክልል የሰው ሰራሽ እግር እና እጆች የመግጠም ስራ ተጀመረ።
****

የአፋር ክልል ሴቶች እና ህፃናት ቢሮ ከ ሰመራ ዪኒቨርሲት ጋር በመተባበር አርተፍሻል (የሰው ሰራሽ) እግር እና እጆችን ለአካል ጉዳተኞች የመስራት እና የመግጠም ስራን በዛሬው ቀን አስጀምረዋል።

በተፈጥሮም ወይም ከግዜ በኋላ በተለያዩ ምክንያቶች እና አደጋዎች አካለ ጎደሎነት ደርሶባቸው የነበሩ ሆነው የአደጋው ቁስል ለደረቀላቸው አካል ጉዳተኞች በሙሉ አሁን የሰው ሰራሽ (አርቴፊሻል ) እግር እና እጅ የመግጠም ስራ እንዲሁም የ ፊዝዮቴራፒ አገልግሎትን የክልሉ ሴቶች እና ህፃናት ቢሮ እና የሠመራ ዪኒቨርስቲ በኢትዮጵያ የህንድ ኢሚባሲ እና የፌዴራል ሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚንስቴር ጋር በጋራ በመሆን በሰመራ ዪኒቨርሲት ስር በሆነው በሎግያ ከተማ በሚገኘው የሎጊያ ሆስፒታል ቅጥር ግቢ ውስጥ በተዘጋጀው ግዜያዊ አገልግሎት መስጫ ላይ አገልግሎት መስጠቱ ተጀምሯል።

ስለሆነም የአገልግሎቱ ተጠቃሚ መሆን የሚፈልግ በክልሉ የሚገኝ ማንኛውም አካል ጉዳተኛ ከላይ ወደተጠቀሱት ተቋሞች በመሄድ በመመዝገብ እና የተመዘገቡበትን ማስረጃ ወደ ሎግያ ሆስፒታል ይዞ በመሄድ እና በመቅረብ አገልግሎቱን ማግኘት እንደሚችሉ ተቋሞቹ በጋራ በሰጡት ማቦራሪያ ገልፀዋል። በተጨማሪም ከዚህ በፊት ተመዝግበው እየተጠባበቁ የነበሩ አካል ጉዳተኞች በአሁኑ ግዜ የአገልግሎቱ ተጠቃሚ እንዲሆኑ እየደረገ እንደሆነ ገልፀው ከዚህ በፊት ምዝገባ ያላደረጉ ደግሞ ምዝገባ እያደረጉ የአገልግሎቱ ተጠቃሚ መሆን እንደሚችሉ ተገልጿል።

የቴሌግራም ቻናሌን በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ 👇
@ https://t.me/Xuqal
የሸዋልን Vibe ከምናጣ...😊

ኢብን አጧኢላህ አስከንደሪ ራህመቱላህ አለይህ በሒከማቸው ላይ ለሩሕ ስንቅ የሚሆንን ንግግር ያሰፍራሉ: "አላህ አንድ ነገር ከሰጠህ በኃላ በተመሳሳይ ሁኔታ ከሌላ ነገር ደግሞ ሊከለክልህ ይችላል። ከዛ ደግሞ አቆይቶ ሊሰጥህ ይችላል! አላህ ይህንን የሚያደርገው ፀጋውን ለመቆጠብ ብሎ ብሎም ስላልቻለ አይደለም። አላህ ከዚህ የፀዳ ሉዓላዊ ጌታ ነው! ግን አላህ ከአንድ ነገር የሚከለክለን እሱን የጠየቅነው ጉዳይ ላለንበት ሁኔታና ተጨባጭ የማይሆን እንደሆነ ስለሚያውቅ ነው። አውቆም አይዘነጋንም! ጊዜው ምንም ያክል ይርዘም ለኛ የተሻለ የሚሆንበት ሰአት ላይ የጠየቅነውን ይሰጠናል። በየትኛውም ሁኔታ ላይ አላህን እንመነው!" ይላሉ! 😊

ውስጥን አያረጋጋም?! ሰላም አለው! የጌታዬ ነገር እንዲህ ነው። 🩵

ሰይዲና ኡመር ኢብኑል ኸጣብ ረዲየላሁ አንህ'ም አንድ ምርጥዬ ንግግር አለቻቸው።

"አላህ በመከራዎች ውስጥ እንዳልፍ ሲያደርገኝ በነዚህ ችግሮች ውስጥ እርሱ ለኔ የዋላቸው ሶስት ፀጋዎች ይታዩኛል ይላል

1ኛ የገጠመኝ መከራ ቀለል እንዲለኝ ማድረጉና ከዚህ የከፋ ችግሮች ውስጥ መክተት እየቻለ በዚህ ብቻ መተዉ ከዋለልኝ ፀጋዎች ውስጥ ነው! ...

2ኛ የመከራው መንስዔ የዱንያ ሐጃዎቼ ላይ መሆኑና፤ በእምነቴ ላይ እንዲሆን ማድረግ እየቻለ በዲን ጉዳይ ላይ መከራ ውስጥ አለመክተቱ ከኒዕማዎቹ ውስጥ ነው! ...

3ኛ የኔ በመከራዎቹ ውስጥ መታገስና በእርሱ መተማመን አላህ ለገባሁበት መከራ የውመል አኺር ላይ መሸለሙ በችግሮቹ ውስጥ ከዋለልኝ ፀጋዎች ሁሉ የበለጠው ነው።" ይላሉ አሚረል ሙዕሚኒን! 😊

አላህ በመከራዎቻችን ውስጥ የምንታገስ፤ በእርሱ ውሳኔዎች ሙሉ ለሙሉ የምንተማመንና የምናምን ባሮች ያድርገን! 🤲

@ https://t.me/Xuqal
"አላህ ሆይ ጨለማን ገፈህ በብርሀን እንደምትተካው ፤ በወንጀል ብዛት የጨለሙ ቀልቦቻችንን በኑርህ አብራልን" 🤲
«ከበደሎች ሁሉ ትልቁ በደልና ከድንቁርና ሁሉ ትልቁ ድንቁርና ማለት ሰዎች እንዲያልቁህና እንዲያተልቁህ እየፈለክ፤ የአንተ ልብ ግን አላህን ከማተለቅና ከማላቅ ባዶ ከሆነ ነው።»

ኢብኑል ቀዪም ረሒመሁሏህ
“አብዛኛው የአደም ልጅ ስህተት በምላሱ የሚፈፅመው ነው።”
ረሱል (ﷺ)
ልቡ ውስጥ የአኼራ ቤቱን አሳምሮ እየገነባ ያለን ጀግና የዱንያ ቤቱን ቢያፈርሱበት ምን ሊጎድልበት? ምንም!☝️
,,,,,,,,