Bilaluna Edris
545 subscribers
3.35K photos
276 videos
50 files
2.3K links
♡_ወደ መልካም ነገር ያመላከተ ሰው የሰራ ሰውን አጅር ያህል ያገኛል"(አመላካች የሰሪውን ምንዳ ያገኛል)(ﷺ)

« ከናንተም ወደ በጎ ነገር የሚጠሩ ፣ በመልካም ስራም የሚያዙ ከክፉ ነገርም የሚከለክሉ ሕዝቦች ይኑሩ» ﷻ
                 ቁርኣን[ 3:104 ]


መወያያ ግሩፓችን ☞ https://t.me/+1qmNqy265XoyNGY0
Download Telegram
በመጨረሻም!!! "በዱንያ ላይ የኖረ ከሞት እና ከትዳር የሚያመልጥ የለም" ይል ነበር አንዱ...😁
Masha Allah Mabruk qarus Acmad Mohammad Saqid Xigiib Xalaayay Qafiyatay baraka leh yan digiib koh abay

Mabruk 🙌

ሀቢቢ ባረከላሁ ለክ ወባሪከ አለይክ
አልፍ አልፍ መብሩክ ወንድሜ
ክብራችሁ እንደ መድሃኒት ነው። ሕፃናት ከማይደርሱበት ቦታ አርቃችሁ አስቀምጡት።
ምንም አይነት ወንጀል ውስጥ ብትሆን...ወደ አላህ ተመለስ እሱ መሀሪ ነውና
በአስቸጋሪ ሁኔታ በርሀብና በሚሳኤል እየተደበደቡም አይደክማቸውም። አንደበታቸው አላህን ከመዘገር አይቦዝንም። ምላሳቸውስ ብትሉ አላህ አላህ ከማለት አይዘናጋም። ትንሽ ፋታ ያግኙ እንጂ ቁርአንን መቅራትና መሐፈዝ ስራቸው ነው ፈፅሞ አይሰለቹም።

እነሆ ዛሬም ከጋዛ በስተ-ምዕራብ የባህር ዳርቻ በአንድ ትምህርት ቤት ውስጥ የተጠለሉ 100 ተማሪዎች የአላህን ቃል ቁርአንን ሐፍዘው ተመርቀዋል።

እንዲህ ናቸው እነርሱ አያርፉም። አጋጣሚውን ሁሉ ወደ አላህ መቃረቢያ ያደርጉታል። የአንድ ቀን ዕድላቸውን ይጠቀሙበታል። ሲደክሙ በአላህ ቃል ይበረታሉ። በሞት አፋፍ ላይ ሆነው እንኳ የጌታቸውን ቃል ታቅፈው እርሱኑ ይገናኙታል። 

ከቀናት በፊትም 500 ሀፊዞች ከጋዛ በስተምስራቅ በሚገኘው አጥ-ጡፋህ መጠለያ ካንፕ ውስጥ ተመርቀዋል።

@ https://t.me/Xuqal
አሳዛኝ ዜና
የቀለም ቀንድ ተሰበረ!

እኛ የአላህ ነን፡፡ እኛም ወደ እርሱም ተመላሾች ነን፡፡
ኢና ሊላሂ ወዒና ኢለይሂ ራጂዑን

የመናዊው እውቅ አሊም የነበሩት ሼይኽ አብዱልመጂድ ቢን አዚዝ አዘንዳኒ በ82 አመታቸው ወደ አኼራ ሄደዋል::

ሼይኽ አብዱልመጂድ ቢን አዚዝ አዘንዳኒ  የቁርዓን ተዓምራትን ከሳይንስ አንፃር በመተንተን እና በተለይም የፅንስ እድገትን በተመለከተ የቁርዓንን አስተምህሮ ሙስሊም ያልሆኑ የዘርፉ ተመራማሪዎች ሳይቀር ተመራምረው እውነታውን እንዲደርሱበት በማድረግ እስልምናን እንዲቀበሉ ማድረግ የቻሉ አሊም ነበሩ::

ሼይኽ አብዱልመጂድ ቢን አዚዝ አዘንዳኒ አላህ ይዘንላቸው፣ ማረፊያቸውንም በጀነተል ፊርደውስ ያድርግላቸው 🤲

@ https://t.me/Xuqal
ለአቅመ አዳም ስደርስ ማግባት እመኝ ነበር'ና በርግጥም ደርሼ አገባሁ። ግና ትዳር ያለ ልጆች አይጥምም ነበር። ልጅ ተመኘሁ፤ ልጆችንም ወለድኩም።

ለኔም ለልጆቼም ሚበቃን ቪላ እንዲኖረን ተመኘሁ። ተግቼ ሰርቼ ገንዘብ ያዝኩ'ና ቪላውን ገነባሁ።

ልጆቼ አድገው ጎረመሱ። ልድራቸው እና የልጅ ልጅ እንዲያሳዩኝ ተመኘሁ፤ በርግጥም ዳርኳቸው።

ግና አሁን ሰውነቴ ይደክም ጀመር፤ እድሜዬም ስራ ትቼ ቤት እንድቀመጥ ያስገድደኝም ያዘ። ስራዬን ሰው ተክቼ ቤት ጠቅልዬ ለመግባት ተመኘሁ፤ በርግጥም ቤት ገባሁ።

ያኔ ስራ አጥ ሆኜ ቤት እውል እንደነበረ ሁላ በተመሳሳይ መልኩ በስተርጅናዬም ላይ ቤት መዋል ጀመርኩ።

ግና ምኞት አሁንም ያማልለኝ ይዟል።

ቁርአንን መሐፈዝ ተመኘሁ፤ ግና አዕምሮዬ ዝሏል።
የሱና ፆሞች ላይ ለማተኮር ተመኘሁ፤ ግና ጤንነቴ ከድቶኝ ኑሯል።
የለይል ሰላት ላይ ለመበርታት ወሰንኩ፤ ግና እግሮቼ ሊሸከሙኝ ተሳናቸው።

ነቢ ሰዐወ ያሉት ነገር አሁን ገባኝ።

5 ነገር ሳይቀድምህ በ5 ነገር ተጠቀም
- ወጣትነትህን እርጅና ሳይቀድምህ
- ጤንነትህን በሽታ ሳይቀድምህ
- ሀብትህን ድህነት ሳይቀድምህ
- ነፃ ግዜህን የግዜ እጥረት ሳይገጥምህ
- ህይወትህን ሞት ሳይቀድምህ

የአዛውንቱ ማስታወሻ

@ https://t.me/Xuqal
አንተ አላህ ዘንድ ያለህን ቦታ ማወቅ ከፈለግክ አላህ አንተ ዘንድ ያለውን ቦታ ተመልከት !
ኡመር ኢብን ኸጣብ ረ.ዐ አምርን ረ.ዐ  በሾሙት ግዜ እንዲህ አሉት "አንድ ሌባ የመጣህ ግዜ ምን ታደርገዋለህ? አምርም "እጁን እቆርጠዋለኋ" ብሎ መለሰ ኡመርም ረ.ዐ መለሱ "እንግዲያውስ እኔም አንድ  ችግርተኛ ወደ እኔ መጥቶ እሮሮውን ካሰማ ያንተን እጅ እቆርጠዋለሁ።" አሉት
#ፍትህ #መሪነት #ሀቀኝነት
     
@ https://t.me/Xuqal
ሲራቸዉን ከምወደዉ ዑሰታዝ አንደበት 😍

የሰው ዘር አይነታ የሆኑትን ታላቅ ነቢይ ታሪክ በተከታታይ የማቅረብ ሃሳብ ሰንቂያለሁ፤ ኢንሻአላህ።
የዚህ ትምህርት ዓላማ፡-

🔘ነቢዩ ሙሐመድን(ሰዓወ) በዝርዝር መተዋወቅ፣

🔘ልባችንን በፍቅራቸው ማነፅ፣

🔘በርሳቸው ህይዎት ውስጥ ኢስላምን በጥልቅ መገንዘብ፣

🔘በዱንያ ጊዚያዊ ቆይታችን የርሳቸውን ፈለግ በመከተል የደስታ ህይዎት መኖር፣

በመጨረሻም፡-

🔘በዘለዓለማዊው ዓለም የርሳቸውን ጉርብትና ማግኘት ይሆናል።

አዛኙ ጌታችን ሆይ! ታላቁን ነቢይ የማወቅን፣ የመውደድን፣ የመከተልን ፀጋ ለግሰን። በዘለዓለማዊው ዓለምም ሸፋዓቸውን ከሚያገኙት፣ ከሐውዳቸው ከሚጠጡትና የርሳቸውን ጉርብትና ከሚቸሩት ደጋጎች ተርታ አሰልፈን።
አላሁመ አሚን🤲🤲🤲

🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹
መስታዎሻ፡
ትምህርቶቹ በሳምንት አንድ ቀን -ዘወትር ሰኞ- በሚከተሉት የማህበራዊ ሚዲያ ገፆች የሚተላለፉ ይሆናሉ👇

Telegram:- https://t.me/UstazBedruHussein
Facebook:- Engr/Ustaz Bedru Hussein - በድሩ ሁሴን
Tiktok፡- @ustazbedruhussein
#ዕውቀት እና #ጥበብ በጀሰድ 👌