Bilaluna Edris
545 subscribers
3.35K photos
276 videos
50 files
2.3K links
♡_ወደ መልካም ነገር ያመላከተ ሰው የሰራ ሰውን አጅር ያህል ያገኛል"(አመላካች የሰሪውን ምንዳ ያገኛል)(ﷺ)

« ከናንተም ወደ በጎ ነገር የሚጠሩ ፣ በመልካም ስራም የሚያዙ ከክፉ ነገርም የሚከለክሉ ሕዝቦች ይኑሩ» ﷻ
                 ቁርኣን[ 3:104 ]


መወያያ ግሩፓችን ☞ https://t.me/+1qmNqy265XoyNGY0
Download Telegram
#Breaking!
ኒው ዮርክ ታይምስ የእስራኤል ባለስልጣናትን ጠቅሶ እንደዘገበው እስካሁን ባለው ሂደት #ኢራን:
√185 ሰው አልባ አውሮፕላኖች፣   √36 ክራይዝ ሚሳኤሎች እና
√110 ከመሬት ወደ ላይ የሚወነጨፉ ሚሳኤሎችን አስወንጭፋለች!
- አብዛኛወቹ በቀጥታ ከ #ኢራን ሲሆኑ ጥቂቶቹ ከየመን እና ከኢራቅ የተላኩ ናቸው!
#አልጀዚራ

@ https://t.me/Xuqal
#Breaking!
በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የኢራን ተወካይ ለፀጥታው ምክር ቤት ባስተላለፉት መልእክት፡-
√ጥቅማችንን እና የግዛት አንድነትን ኢላማ ያደረገ ማንኛውም ጥቃት በህጋዊ መንገድ ምላሽ ለመስጠት #ቃል_እንገባለን!
√እስራኤልን ከማንኛውም ወታደራዊ እርምጃ #እናስጠነቅቃለን!ለማንኛውም ጥቃት ምላሽ ለመስጠት #ቁርጠኞች ነን!
√አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ህጋዊ የመከላከል መብታችንን ከመጠቀም ወደኋላ አንልም!!
#endeed!
@ https://t.me/Xuqal
“እስራኤል በኛ ላይ ማንኛውንም አይነት ወታደራዊ እርምጃ ከወሰደች ምላሻችን የበለጠ ጠንካራ ይሆናል!”
በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የኢራን ተወካይ ለፀጥታው ምክር ቤት ያስተላለፉት መልእክት!

@ https://t.me/Xuqal
እስራኤል ያረፋባትን ብትር እንዲህ ገልፀዋለች

እስራኤል እንደስታወቀችው ከ300 በላይ ድሮኖች አና ሚሳዔሎች ከኢራን፣ የመን እና ኢራቅ ውስጥ ወደ እስራኤል ተተኩሰዋል።
ኢራን ጥቃትና ያስከተለው ጉዳት
የእስራኤል ጦር ቃል አቀባይ አድሚራል ዳንኤል ሀግሪ፤ ወደ እስራኤል ከተተኮሱ ከ300 በላይ ድሮኖና ሚሳኤሎች ውስጥ 99 በመቶውን ማክሸፍ እንደተቻለ ተናግሯል።
በአሜሪካ፣ በብሪታኒያ እና ፈረንሳይ እርዳታ በመቶዎች የሚቆጠሩ የኢራን ድሮኖችና ሚሳዔሎች ድንበር ላይ ተመትተው ወድቀዋል።
እስራኤል ተከላከልኩ ትበል እንጂ የኢራን ሚሳኤሎች የእስራኤል አየር መከላከያዎችን ጥሰው በመግባት በርካታ ኢላማዎችን መምታታቸው ሲጠቃለል ኢራን ከአራት አገራቶች ጋር ገጥማለች ማለት ይቻላል አሁን ተራኛዋ እስራኤልናት በ48 ሰዓት ዉስጥ የምትፈልገው ጦር ያቀደችውን ለመተግበር ተዘጋጅታለች ጀርመን መጨመራ የማይቀር ነዉ የኢራን ሀሉተኛ ምቷ ከባድ እንደሚህን ይጠበቃል።

@ https://t.me/Xuqal
ብታምኑም ባታምኑም የኢራን ሮኬት የክሩስ ሚሳኤል ድሮንስ ተጠቅማ የሀማስን ያክል ወራሪዋ እስሬኤል አልቆሰለችም ኦክቶበር 7 ከድልም በላይ ድል ነዉ ።ለማንኛውም ገ'ዛ ሰማይ ሰከን ፀጥ ረጭ ብሏል የሰላም አየር ነዉ

@ https://t.me/Xuqal
ቴህራን ጥቃቱን የመቀጠል ፍላጐት የለኝም ማለቷን ፕሬስ ቴሌቪዥን  ዘግቧል።

የኢራን አብዮታዊ ዘብ ኮማንደር በእስራኤል ላይ የተደረገው ዘመቻ "ከተጠበቀው በላይ ስኬታማ" ነበር ሲል አስታውቋል።

ጥያቄዉ  አሁን እስራኤል ዝም ትላለች ወይ የሚለው ነዉ ?በፍፁም የመልስ ምት አላት ካላት ደሞ የኢራን አፀፋ አንጀት የሚያርስ ነዉ የሚሆነዉ ብዬ አስባለሁ ።ለግዜዉ ገ'ዛ እፎይ ብላለች ኢራን ቢዚ አድርጋቸዋለች ።

@ https://t.me/Xuqal
በኢራን የሚሳኤል ጥቃቶች የእስራኤል ኔቫቲም የአየር ማረፊያ ሙሉ በሙሉ ወድሟል። ኢራን የአየር ማረፊያውን ያወደመቺው በ15 ሚሳኤሎች ከደበደበቺው በኋላ ነበር።

የኔቫቲም አውሮፕላን ማረፊያ በወራሪዋ እስራኤል ደቡባዊ ግዛት በቤየር ሼቫ አቅጫ የሚገኝ ስትራቴጂካዊ የጦር ማረፊያ ሲሆን የእስራኤል F-35 ጀቶች ዋና ማዘዢያ ጣቢያ ነው። ይህ የወራሪዋ እስራኤል የጦር ማረፊያ በኢራን አዳሩን ከወደመ በኋላ ሙሉ ለሙሉ ስራ ማቆሙ ታውቋል።

ምንም እንኳ እስራኤል አሜሪካና እንግሊዝ የኢራንን ጥቃት መመከት ችለናል ብለው ለመፅናናትና ለመዋሸት ቢሞክሩም ጉዳቱ እያደር እየለበለባቸው ይገኛል። የኢራን ሚሳኤልችም እስራኤልን አሳማሚ ጥፊ እንደሰጧት ተረጋግጧል።

በኢራን የሚደርስብኝ ጥቃት መጠነኛ ከሆነ አፀፋ አልመልስም ብላ የነበረው እስራኤልም ጉዳቱ ገዘፍ ስላለባት በኢራን ላይ የአፀፋ እርምጃ ለመውሰድ እየመከረች ትገኛለች። የቡድን ሰባት አባል ሀገራትንም ድረሱልኝ ብላለች።

@ https://t.me/Xuqal
ኢራን ምን አለች ?

- በተቀናጀ እርምጃ በእስራኤል ወታደራዊ ኢላማዎችን መተናል።

- እንቅስቃሴያችን ውስን ነበር።

- የወሰድነው እርምጃ አገዛዙን ለመቅጣት ያለመ እንደነበር ዛሬ ለዋይት ሀዋስ አስታውቀናል።

- በዚህ ዘመቻ ኤፍ-35 አውሮፕላኖች የሚቀመጡበትን የጦር ሰፈር በትክክለኛ ስሌት እና ሰው አልባ አውሮፕላኖችን እና ሚሳኤሎችን በመጠቀም ኢላማ አድርገናል።

- ኃይላችን የትኛውም ህዝባዊ ይሁን የኢኮኖሚ ቦታዎች ላይ አላነጣጠረም።

- በአካባቢው ያሉ የአሜሪካን ሰዎች እና መሠረቶችን ኢላማ አላድረግንም። ውጥረቱ እንዲብስም አልፈለግንም።

... ነገር ግን አሜሪካ ቴል አቪቭን ለመከላከል ስትል ኢላማ ውስጥ ያሉ ሀገራት ግዛትን ከተጠቀመች በዚያች ሀገር ያለው የአሜሪካ ጦር ኢላማ መደረጉ የማይቀር ነው። ይህን አስረግጠን ነው የምንናገረው።

@ https://t.me/Xuqal
ለመጥፋትህ አላህ ሱ.ወ. አንተን ላንተ መተዉ ብቻ በቂ ነው። አንተን ለራስህ ከተወህ አለቀልህ። ሰው አላህን ትቶ በዕውቀቱ፣ በገንዘቡ፣ በብልሃቱ፣ በወገኑ፣ በጦሩ .. ከተማመነ መጥፊያው ፈጠነ ማለት ነው።

"ለቅጽበት እንኳን እኔን ለኔ አትተወኝ።" ይሉ ነበር የአላህ መልዕክተኛ ﷺ.

ከነፍሴ በላይ ለኔ ጠላት ማን አለ!??

@ https://t.me/Xuqal
ከጋዛ አንዱ ሲመልስ

ወራሪዎች በተራቸው በፍርሃት ሲብረከረኩ

ድሮን እኛን አልፎ ጠላት ላይ ሲወድቅ
ባየሁ ጊዜ

የለይለተል ቀድር ዱዓአችን ተቀባይነት እዳገኘ ተሰማኝ

ይኸው 24 ሰአት ሆነው ቦምብ ሳይወድቅብን በጋዛ አንድም ነፍስ ሸሂድ ሳይሆን ለመጀመሪያ ጊዜ አሳለፍን

@ https://t.me/Xuqal
የልብ ደግነቱ ልብ እንደ ልብስ አለመሆኑ
ሲያድፍ ሲያድፍ ሲቆሽስ አለመታየቱ
በኢራን የተፈፀመብን ጥቃት ከጠበቅነው በላይ የከፋ ነው በማለት ወራሪዋ እስራኤል ገልፃለች።
የእስራኤል መከላከያ ሚኒስትርን ዋቢ አድርጎ አልጀዚራ ባወጣው መረጃ በኢራን የተፈፀመው የሚሳኤል ጥቃት ከጠበቅነውና ካሰብነው በላይ ነው ማለቷን ዘግቧል።

አነስተኛ ውድመት ብቻ እንደደረሰባት ወራሪዋ እስራኤል ማስተባበያ ስትሰጥ ብትውልም የኢራን ጥቃት አሳማሚ እንደነበር ለማመን ተገዳለች።
ግዙፉ የእስራኤል የጦርጀቶች ማዘዣና አየር ማረፊያ ኔቫቲም airbase መውደሙ የተረጋገጠ ሲሆን ሌሎች በርካታ ጉዳቶችም በወራሪዋ እስራኤል ወታደራዊ ተቋማት ላይ ደርሰዋል።

በኢራን ላይ ጥቃት ለመፈፀም ወራሪዋ እስራኤል ምእራባውያንን እየተማፀነች ትገኛለች። ኢራን በበኩሏ ወራሪዋ እስራኤል በኢራን ላይ ጥቃት የምትፈፅም ከሆነ ትፀፀታለች አፀፋውም ከአሁኑ በእጅጉ የከፋ ይሆናል በማለት ማስጠንቀቂያ ሰጥታለች።

https://t.me/Xuqal
ሁሉም የዓለም ድሮኖች የሚላኩት በሚስጥር ነው።የኢራን ድሮኖችና ሚሳኤሎች ሲቀሩ። መነሻ ሰአታቸው  ተገልጿል 😊 ብዛታቸው ፣ ስንት ሰአት እንደሚወስድባቸው ሁሉ። 😊

ይሄን ሚስኪን ኡማ ታድያ ይህ ጦርነት እንደሆነ  ይነግሩታል። ኡማውም ተቀብሎ ድል ለኢራን እያለ ይፎክራል።

ዐረቦች አንድ አባባል አላቸው። 
«أهل مكة أدرى بشعابها»
«የመካ ሰዎች ስለሸንተረሮቿ ይበልጥ አዋቂዎች ናቸው»

አንድን ጉዳይ በቅርብ ርቀት ከሚከታተለው ባለቤቱ  የበለጠ የሚያውቅ የለም ማለታቸው ነው። ይህ ጂሃድ ሐለስ የተባለ ጋዛ የሚኖር ፀሃፊና ዳዒ ከታች በምስሉ እንዳያያዝኩት እንዲህ ይላል፦

«የግምታችሁን ጣራ በጣም ከፍ አታድርጉት፤ የተስፋ መቁረጥ እንዳያጋጥማችሁ።በ190ቀናት እሽክርክሪት ውስጥ አሳልፎ የሰጠን ዛሬ ሊረዳን አይችልም። »

ኢራን ጋዛን የመርዳት ፍላጎቷ እውነት ቢሆን ባለፉት 6ወራት ተጨባጭ የሚባል ጥቃት ትሰነዝር ነበር።ነገር ግን አንድም ተጨባጭ ጥቃት አልፈፀመችም ።

ያሁኑም ቢሆን ኢስራኢል በሶሪያ ኢምባሲዋ ላይ ለፈፀመችው  አፀፋ ምላሽ እንጅ ለጋዛ እገዛ የተደረገ ካለመሆኑ ጋር አንድም ተጨባጭ ጉዳት አልተመዘገበም።

ኢላማዎቹም በብዛት ኢስራኢል በወረራ በያዘቻቸው የሶሪያና የፊለስጢን ግዛቶች ላይ የተደረጉ ናቸው።ጠላትህን ከሌሊቱ 5 ሰአት ጀምሬ 200 ድሮን እልክብሀለሁ ተብሎ የሚጀመር ጦርነት አስቡት።

በኢራንና በኢስራኢል መካከል ምንም አይነት ሃይማኖታዊ ፀብ የለም። ስለሆነም ሃይማኖታዊ ጦርነት አይኖራቸውም። የሁለቱ ሀገራት ምልልስ አሜሪካ የምታደርገው የውክልና ጦርነትን ወካይ ነው።
ሶፈዊይ ስለ ኢስላም ብሎ ሶህዩኒን የሚዋጋበት አጀንዳ የለውም። ለግል የዱንያ ጥቅሞቻቸው ቢዳቀቁ ደስታችን እጥፍ ነው። 

@ https://t.me/Xuqal
የእስራኤል የመልስ ምት የከፋ ይሆናል ይለኛል። ወዳጄ ስለሞሳድ እና እስራኤል ኃያልነት እንድታስብ ተፅእኖ ያደረጉብህ በአይሁዶች ቁጥጥር ስር ያሉት ፊልሞች፣ ሚዲያዎችና በእነርሱ የተፃፉት የስለላ መፅሃፎች እንጂ ኦክቶበር 7 የታገቱባትን ዜጎቿንና የአለም መሳቂያ የሆነውን ይህንን ጀነራል እንኳን ማስፈታት አልቻለችም።

@ https://t.me/Xuqal
Bilaluna Edris
Photo
"የአንዷ ዲናር ደስታ ከቪላው ደስታ በላይ ነበር።"
የሳዑዲው ቢሊየነር አር-ራጂሂይ

እጅግ በጣም ድሃ ነበርኩ።በተማሪነት ዘመኔ በትምህርት ቤት የተማሪዎች የጉዞ ፕሮግራምን ልቀር የነበረበት ክስተት እስካሁን አይረሳኝም።

ጉዞውን ለማድረግ የሚያስፈልገውን አንድ ዲናር በማጣቴ ነበር የቀረሁት።ቤተሰቦቼን አልቅሼ ብለምንም ገንዘቡን ሊያገኙልኝ አልቻሉም።
ጉዞው ከመደረጉ ከአንድ ቀን በፊት  በትምህርት ክፍል ውስጥ ፍልስጤማዊው መምህር አንድ ጥያቄ ጠየቀኝ።እኔም ለጥያቄው ትክክለኛ ምላሽ ሰጠሁት።

እሱም መልሱን በመመለሴ ተደስቶ አንድ ዲናር ሸለመኝ።ለሳምንታት የቆየው እምባዬም ታበሰ።እጅግ ተደስቼ ወደ ጓደኞቼ ጋር ሄድኩ።የጉዞውም አካል መሆኔን አበሰርኳቸው።
ጊዜያት አልፈው የትምህርት ዘመኔ አበቃ፤ወደ ስራው አለምም ተቀላቀልኩ።

ደህና የሚባል ገንዘብም ካካበትኩ ወዲህ በበጎ ተግባራት ላይ መሳተፍ ጀመርኩ።ከቆይታም በኋላ ያ በታዳጊነት ዘመኔ እምባዬን ያበሰልኝ መምህር ትዝ አለኝ።

ያኔ አንድ ዲናሩን የሰጠኝ በሽልማትነት ነው ወይስ በምፅዋትነት ነው ስል ራሴን መጠየቅ ጀመርኩ።ምንም ሆነ ምን ግን ያኔ ማንም ሳያውቅ ትልቅ ምለው የነበረን ችግሬን ቀርፎልኛል ብዬ ለራሴ ምላሽ ሰጠሁ።

ወዲያውም እሱን ፍለጋ ወደ ቀድሞ ትምህርት ቤቴ ሄድኩኝና የመኖሪያ አድራሻውን ጠይቄ አገኘሁ።
ወደ ቤቱም ስሄድ እጅግ ከባድ በሆነ ሁኔታ፤ ያለ ስራ ተቀምጦ አገኘሁት።ወደሌላ ሀገር ለመሰደድ በማሰብ ላይ እንዳለ ደረስኩበት።
ወደሱም ቀረብ ብዬ:-
"የተከበርክ መምህሬ! ያንተ ትልቅ እዳ አለብኝ።" አልኩት።እሱም ግራ ተጋብቶ:-

"እኔ በማንም ላይ እዳ የለኝም።" ሲል መለሰ።
እኔም ማንነቴን ነገርኩት:-

"ያኔ በትምህርት ቤት ጥያቄ ጠይቀኸኝ አንድ ዲናር የሰጠኸኝ ትዝ አይልህም?" ስል ይበልጥ ስለራሴ አሳወቅኩት።እሱም እየሳቀ፦"አዎ አዎ።እና አንድ ዲናሩን ለመመለስ እያፈላለከኝ ነበር?" አለኝ።

እኔም አዎ ብዬው፤በመኪናዬ ከቤቱ ይዤው ወጣሁ።አዲስ የሰራሁት ወደነበረው ቪላ በመውሰድ:-

"መምህሬ ይህ ያበደርከኝ ብድር ምላሽ ነው።ይህች መኪናም ያንተው ናት።የሚያስፈልግህን ነገር በሙሉ የምችልህ ይሆናል" አልኩት።እጅግ በጣም ተደስቶ:-
"ኧረ ይሄ ሁላ ይበዛብኛል።"አለኝ።እኔም መለስኩለት:-
"ያኔ በአንድ ዲናሯ የተደስትኩት ደስታ አንተ ዛሬ በቪላውና በመኪናው ከተደስተከው በላይ ነበር።"


@ https://t.me/Xuqal
ወደ ቤተሰቦቿ ሽምግልና ልትልክ ያሰብካት ልጅ አባት የሚሰግድበት መስጂድ ላይ ሄደህ ስትሰግድ...