Bilaluna Edris
558 subscribers
3.35K photos
276 videos
50 files
2.3K links
♡_ወደ መልካም ነገር ያመላከተ ሰው የሰራ ሰውን አጅር ያህል ያገኛል"(አመላካች የሰሪውን ምንዳ ያገኛል)(ﷺ)

« ከናንተም ወደ በጎ ነገር የሚጠሩ ፣ በመልካም ስራም የሚያዙ ከክፉ ነገርም የሚከለክሉ ሕዝቦች ይኑሩ» ﷻ
                 ቁርኣን[ 3:104 ]


መወያያ ግሩፓችን ☞ https://t.me/+1qmNqy265XoyNGY0
Download Telegram
“ሱብሃነላሂ ዓል-ዓዚም ወቢሃምዲህ ያለ በጀነት ውስጥ የተምር ዛፍ ይተከልለታል።”
ረሱል ﷺ
Bilaluna Edris
Photo
ያለ አንዳች ተጨማሪ ማብራሪያ ሰይዳችንﷺ "እንደኛው ሰው ናቸው!"  ማለቱ በአንዳንድ ሰዎች አስተሳሰብ ላይ ስሁት ግንዛቤን ሲፈጥር ይታያል።ይህ ንግግር የቀደምት ህዝቦች ለነቢያቶቻቸው ካቀረቡት መሞገቻ ጋር ተመሳሳይ ሆኖ እናገኘዋለን።

قَالُوا مَا أَنتُمْ إِلَّا بَشَرٌ مِّثْلُنَا
"እናንተ መሰላችን ሰዎች እንጂ ሌላ አይደላችሁም፡፡"

አሏህ የሰይዳችንንﷺ ሰውነት ሲገልፅ በሱረቱል-ከህፍ እንዲህ ይላል:-

قُلْ إِنَّمَا أَنَا بَشَرٌ مِّثْلُكُمْ يُوحَىٰ إِلَيَّ

« ወደኔ ራዕይ የሚወረድልኝ ቢጤያችሁ ሰው ብቻ ነኝ።"

አንቀፁን በማስተዋል የተመለከተ አሏህ ሰውነታቸውን እንዲሁ ያለ አንዳች የተለየ ማሰሪያ አልገለፀውም።እሱም "ወደኔ ራዕይ የሚወርድልኝ!" የሚል ቃል ነው።ይህ የሳቸውና የመሰል ወንድሞቻቸው ከሌሎች ሰዎች መለያ ባህሪይ ነው።ስለዚህ አንድ ሰው እንዲሁ ተነስቶ "ሰይዳችን እንደኛው ሰው ናቸው!" ማለቱ " لا تقربوا الصلاة" የሚለውን አንቀፅ ሳያሟላ እንደማንበብ ነው።
"እኔ አምሳያቹህ ሰው ነኝ" የሚለውን ሰውነት ከሚያስፈርደው ነገራት ጋር መስክሮ፤"ወደኔ ራዕይ የሚውርድልኝ" የሚለውን የሳተ ከባድ በሆነ የመታወር ግርዶ ይሸፈናል።

"እኔ አምሳያቹህ ሰው ነኝ" በሚለው የተፈለገው አምላካዊ ባህሪን የተላበስኩ አይደለሁም፤መልአክም አይደለሁም።እንደናንተው የተወለድኩ፣የማገባ፣የምመገብ፣የምጠጣ እንዲሁም የምሞት፤ከናንተው ዘር የሆንኩ ሰው ነኝ ለማለት ነው።
ይህ ማለት ግን በሁሉም ሰዋዊ መገለጫ እንደናንተ ነኝ ማለት አይደለም።ይህን ለማረጋገጥ የተወሰኑ አሓዲሶችን እንመልከት።

1.ሰይዳችንﷺ ሁለት ቀናትን በማከታተል ይፆሙ ነበር።ይህ ፆም "ዊሳል" በመባል ይጠራል።ሰሐቦቹ ይህን ፆም ለመፆም ሲሞክሩም ሰይዳችንንﷺ
ከልክለዋቸው የሚከተለውን ብለዋል:-
"እኔ እንደናንተ አምሳል አይደለሁም።እኔ ጌታዬ እያበላኝና እያጠጣኝ ነው የማድረው።"
ቡኻሪና ሙስሊም የዘገቡት።

2.ከኃላቸው ተከትለው ለሚሰግዱ  ሰሐቦች እንዲህ ብለዋል:-
"ወላህ! ኹሹዓቹና ሩኩዓቹህ ከኔ አይሰወርም።እኔ በጀርባዬ እመለከታቹሃለሁ።"
ቡኻሪ የዘገቡት።

3.አሏህ እስከለተ ትንሳኤ ድረስ ለኡመታቸው የገባላቸውን ቃል አይተዋል።
"አሏህ ለናንተ ቃል የገባው አንዳች ነገር ሳይቀር በዚህ ሰላቴ ውስጥ አይቼዋለሁ።"
በዚህ ውስጥ ጀነትና እሳትን ማየታቸውንም መክተት እንችላለን።

4."አይኔ ይተኛል፤ልቤ ግን አይተኛም።"

እነዚህና መሰል ሐዲሶች ሰይዳችን እንደማንኛውም ሰዎች፤"ሰው" ብቻ ተብለው የሚገለፁ እንዳልሆነ የሚያሳዩ ናቸው።እሳቸው በምሽት ጉዞ ሰውም ሆነ መልዐክ ያልደረሰበት ስፍራ የደረሱ ናቸው፤እሳቸው ማንም ያላየወን ታላቁን የአሏህ ተዓምር ያዩ ናቸው።እሳቸው የታላቁ ምልጃ ባለቤት ናቸው።እሳቸው የምስጋና ሰንደቅ አውለብላቢ ናቸው።እሳቸው የጀነት በር ከፋች ናቸው።እሳቸው የሰዎች አይነታ የፍጡራን ሁሉ እንቁ ናቸው።እሳቸው በመጨረሻው መለኮታዊ ራዕይ እስከተለ-ትንሳኤ ድረሰ የሚቆይ ህግን አንግበው የመጡ ናቸው።
ኢማም አል-ቡሲሪይ አሳቸውን የገለፁበት መንገድ እጅግ ድንቅ ነው:-

مُنَـزَّهٌ عـن شـريكٍ في محاسِــنِهِ .. فجَـوهَرُ الحُسـنِ فيه غيرُ منقَسِـمِ

ያልተከፈለን የውበት እንቁ ከላይ ችሯቸው
በምግባር ውበት...
እንኳን ሊመስል የቀረበ እንኳን አጣንላቸው።

اللهم صل على سيدنا ومولانا محمد وآله وسلم

የቴሌግራም ቻናሌን follow በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ
@ https://t.me/Xuqal
“ሶስት ሰዎች በትንሳዔ ዕለት አይናቸው እሳት አይነካውም። አላህን በመፍራት ያለቀሰች አይን፤በአላህ መንገድ ላይ ዘብ የቆመች አይንና አላህ ከከለከለው የታቀበች አይን”
ረሱል ﷺ
"ልባችሁ ቢጠራና ንጹህ ቢሆን የጌታችሁን ቃል በቃኝ ባላላችሁና ባልጠገባችሁት ነበር።"

ዑሥማን ኢብኑ ዐፋን ረ.ዐ
...«ምኞት ኣያልቅም። ዛሬ ላይ የተመኘኸውን ወደፊት ስታገኝ ደስታ ኹሉ ሚሞላ ይመስልሕና፤ ኣሳካሑ ብለሕ ገና ሳታርፍ ሌላ ምኞት - ሌላ ሐሳብ ሲተካ ታያለሕ። ያሰብነውን ስናገኝ ለዚያ ነገር የነበረን ፍላጎትና ጉጉት ቀስ በቀስ ይወርዳል፣ ይለመዳል። ሌላ ኣዲስ ነገርም ይወለዳል። መሔድ ሔዶ ኣያልቅም ኣይነት ጫፍ ደርሰን ከጫፍ ተነሳትን መሄድ ኣለማቆም። በመልመድ፣ መላመድ ደስታን ማገድ፤ ለሁሉም ሰው ነፍስ የታደለ ምድራዊ ሕግ ነው።»

የቴሌግራም ቻናሌን follow በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ
@ https://t.me/Xuqal
የአሹራ ቀን ፆም!

ለመልካም ስራ አስተዋሽ እንሁን

ከኢብኑ አባስ (ረ.ዐ) ተይዞ፡ ነቢዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦

﴿فَإِذَا كَانَ الْعَامُ الْمُقْبِلُ - إِنْ شَاءَ اللَّهُ - صُمْنَا الْيَوْمَ التَّاسِعَ﴾

“የሚቀጥለው ዓመት ከደረስኩ በአላህ ፍቃድ የአሹራን ቀን ፆም ዘጠነኛውን ጨምሬ እፆማለሁ።”

ሙስሊም ዘግበውታል: 1134


ከአቢ ቀታዳ (ረ.ዐ) ተይዞ፡ ነቢዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦

﴿صيامُ يومِ عاشوراءَ، إنِّي أحتَسِبُ على اللَّهِ أن يُكَفِّرَ السَّنةَ الَّتي قبلَهُ﴾

“የአሹራ ቀን ፆም ያለፈውን አመት ኃጢአት እንደሚያብስ ከአላህ እጠብቃለሁ።”

ሙስሊም ዘግበውታል: 1162

የቴሌግራም ቻናሌን follow በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ
@ https://t.me/Xuqal
አላህ ብልሕ የሆኑ ባሮች አሉት፣
ፈተናዋን ሸሽተው ዱንያን መመለስ በሌለው ፍች የፈቷት፣

እርሷን አስተውለው በሚገባ አውቀው፣
ሀገር እንዳልሆነች ሕያው ለሆነ ሰው፣

እርሷንም....
ጥለዋት ተጓዙ በባሕር መስለው ፣
መልካም ሥራቸውን በዱንያ ባህር ላይ እንደ ጀልባ ይዘው።

[ ኢማሙ ሻፊዒይ (ረሒመሁል'ሏህ) ]

👉በነዚህ አድራሻዎች ይከታተሉን፦

Telegram 👉 https://t.me/Xuqal

Facebook 👉https://www.facebook.com/share/w44LtDj2agVEKiPU/?mibextid=qi2Omg

Instagram 👉 https://www.instagram.com/bilaluna_edris

Twitter👉 https://x.com/bilal17_idris

Tiktok👉 https://www.tiktok.com/@xuqal11
#የዓሹራ_ፆም ያለው ትሩፋት
فضل صوم يوم عاشوراء
ኢብኑ ዐባስ (ረዲየላሁ አንሁ) በዘገቡት ሀዲስ ነቢዩ (ሷለላሁ አለይሂ ወሰለም) ወደ መዲና በመጡ ግዜ የሁዶች ዓሹራን ሲፆሙ አይተዋቸው ለምን እንደሚፆሙት ሲጠይቋቸው "ይህ ቀን መልካም ቀን ነው፣ አላህ በኒ ኢስራኢልን ከጠላታቸው ነፃ ያወጣበት ቀን ነው፣ በዚሁ ምክንያት ሙሳ (ዐለይሂ አሰላም) ፆሙት" በማለት መለሱላቸው። ነቢዩም (ሷለላሁ አለይሂ ወሰለም) "እኔ ለሙሳ ከናንተ ይበልጥ የተገባው ነኝ" በማለት ፆሙት ሌሎችም እንዲፆሙት አዘዙ። (ቡኻሪ) በሌላ
በሙስሊም ዘገባ "ይህ ታላቅ ቀን ነው። ሙሳንና ህዝቦቹን ነፃ ያወጣበትና ፈርኦንንና ህዝቦቹን ያሰመጠበት" በማለት ተዘግቧል።
عن ابن عباس رضي الله عنهما قال: قَدِمَ النَّبِيُّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وآله وَسَلَّمَ المَدِينَةَ فَرَأَى اليَهُودَ تَصُومُ يَوْمَ عَاشُورَاءَ، فَقَالَ: «مَا هَذَا؟» قَالُوا: هَذَا يَوْمٌ صَالِحٌ، هَذَا يَوْمٌ نَجَّى اللهُ بَنِي إِسْرَائِيلَ مِنْ عَدُوِّهِمْ، فَصَامَهُ مُوسَى، قَالَ: «فَأَنَا أَحَقُّ بِمُوسَى مِنْكُمْ»، فَصَامَهُ، وَأَمَرَ بِصِيَامِهِ. أخرجه البخاري في صحيحه.
وفي رواية مسلم- ((هذا يوم عظيم أنجى الله فيه موسى وقومه وغرّق فرعون وقومه))

فعَنْ ابْنِ عَبَّاسٍ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُمَا قَالَ : مَا رَأَيْتُ النَّبِيَّ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ يَتَحَرَّى صِيَامَ يَوْمٍ فَضَّلَهُ عَلَى غَيْرِهِ إِلا هَذَا الْيَوْمَ يَوْمَ عَاشُورَاءَ وَهَذَا الشَّهْرَ يَعْنِي شَهْرَ رَمَضَانَ . " رواه البخاري

ኢብኑ ዐባስ (ረዲየላሁ አንሁ) "ነቢዩ (ሷለላሁ አለይሂ ወሰለም) ከዓሹራእ እና ከረመዳን ሌላ አንድንም ፆም ከሌላው አስበልጠው ትኩረት የሰጡበት አላየሁም" ብሏል። (ቡኻሪ)

فعن عَبْدِ اللهِ بْنِ عَبَّاسٍ رَضِيَ اللهُ عَنْهُمَا قال: حِينَ صَامَ رَسُولُ اللهِ صَلَّ اللهُ عَلَيْهِ وآله وَسَلَّمَ يَوْمَ عَاشُورَاءَ وَأَمَرَ بِصِيَامِهِ قَالُوا: يَا رَسُولَ اللهِ، إِنَّهُ يَوْمٌ تُعَظِّمُهُ الْيَهُودُ وَالنَّصَارَى، فَقَالَ رَسُولُ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وآلِهِ وَسَلَّمَ: «فَإِذَا كَانَ الْعَامُ الْمُقْبِلُ إِنْ شَاءَ اللهُ صُمْنَا الْيَوْمَ التَّاسِعَ» قَالَ: فَلَمْ يَأْتِ الْعَامُ الْمُقْبِلُ حَتَّى تُوُفِّيَ رَسُولُ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وآلِهِ وَسَلَّمَ. أخرجه مسلم في "صحيحه"

አብደላህ ኢብኑ አባስ (ረዲየላሁ አንሁ) የአላህ መልእክተኛ ሷለላሁ አለይሂ ወሰለም የአሹራን ቀን ፁመው ሰሀባዎቻቸውንም እንዲፃሙ ባዘዙ ጊዜ፦ ይህ ቀን እኮ አይሁዶችና ነሳራዎች የሚያልቁት ቀን ነው አሉዋቸው። እሳቸውም፦ "የአላህ ፍቃድ ሆኖ ቀጣይ አመት ከደረስን ዘጠነኛውንም ቀን እንፃማለን" አሉ። ነገር ግን የቀጣዩ አመት አሹራ ሳይደርሱ ሞቱ።" (ሙስሊም)

ዘጠነኛውን ቀን መጨመር የተፈለገበት ምክንያት ከአይሁዶችና ከነሳራዎች ለመለየት ነው።

وقال رسول الله صلى الله عليه وسلم : " صِيَامُ يَوْمِ عَرَفَةَ أَحْتَسِبُ عَلَى اللَّهِ أَنْ يُكَفِّرَ السَّنَةَ الَّتِي قَبْلَهُ وَالسَّنَةَ الَّتِي بَعْدَهُ وَصِيَامُ يَوْمِ عَاشُورَاءَ أَحْتَسِبُ عَلَى اللَّهِ أَنْ يُكَفِّرَ السَّنَةَ الَّتِي قَبْلَهُ " رواه مسلم

የአላህ መልክተኛ ( ሷለላሁ አለይሂ ወሰለም) "የዐረፋ ቀን ጾም ያለፈውን አመትና የቀጣዩን አመት ወንጀል እንደሚያብስ ከአላህ እጠብቃለሁ። የዓሹራ ፆም ደግሞ ያለፈውን አመት ወንጀል እንደሚያብስ ከአላህ እጠብቃለሁ" ብለዋል። (ሙስሊም)

በነዚህ ፆሞች የሚታበሱት ወንጀሎች ትናንሽ (ሰጋኢር) ወንጀሎች ናቸው። ትላልቅ ወንጀሎች የተለየ ተውባ ይፈልጋሉ።

በዘንድሮ አመት 1446 አመተ ሂጅራ ዘጠነኛው ቀን ሰኞ ሲሆን አስረኛው ማክሰኞ ስለሆነ ሁላችንም እንዳያመልጠን በጉጉት እንጠባበቅ ።
★ በእነዚህ ቀናት ጾም ከመጾም ውጭ ከወትሮው ለየት ያለ የሚደረግ ኢባዳም ሆነ የሚኬድበት ቦታ የለም ።

አላህ ደርሰው ከሚፆሙት ያድርገን

👉በነዚህ አድራሻዎች ይከታተሉን፦

Telegram 👉 https://t.me/Xuqal

Facebook  👉https://www.facebook.com/share/w44LtDj2agVEKiPU/?mibextid=qi2Omg

Instagram 👉 https://www.instagram.com/bilaluna_edris

Twitter👉 https://x.com/bilal17_idris

Tiktok👉 https://www.tiktok.com/@xuqal11