Bilaluna Edris (Xuqal.X.Qafarey)
474 subscribers
3.13K photos
208 videos
46 files
2.15K links
♡_ወደ መልካም ነገር ያመላከተ ሰው የሰራ ሰውን አጅር ያህል ያገኛል"(አመላካች የሰሪውን ምንዳ ያገኛል)(ﷺ)

« ከናንተም ወደ በጎ ነገር የሚጠሩ ፣ በመልካም ስራም የሚያዙ ከክፉ ነገርም የሚከለክሉ ሕዝቦች ይኑሩ» ﷻ
                 ቁርኣን[ 3:104 ]


መወያያ ግሩፓችን ☞ https://t.me/+1qmNqy265XoyNGY0
Download Telegram
Bilaluna Edris (Xuqal.X.Qafarey)
Photo
በአላህ ፍቃድ ቅዳሜ ዙልሒጃህ 9 እንይዛለን። ዙልሂጃ 9 ወይም የአረፋ ቀን በዱንያ ላይ ካሉ ቀናቶች ሁሉ የበለጠች ቀን ናት።

ሑጃጅ ዐረፋ ላይ የሚቆሙበት ቀን እንደመሆኑም ይህ እለት የዐረፋ ቀን ይባላል። ዐረፋ ላይ መቆም ከሐጅ ምሰሶዎች ውስጥ አንድ ምሰሶ ነው።

ነብዩ ﷺ “ሐጅ ማለት ዐረፋ ነው” ማለታቸው ይህንን እውነታ ያሳያል።

በዚህ ቀን አላህ የወፈቃቸው ሑጃጆች ሱብሕን ሚና ላይ ከሰገዱ በኋላ ፀሐይ ስትወጣ ተልቢያ፣ ዚክር እያደረጉ ወደ ዐረፋ ለኢባዳቸው ይጓዛሉ።

አላህ የሚመጣውን ሀጅ ይወፍቀን እና እንደኛ ይሄን ቦታ ለኢባዳ መዘየር ያልቻለ ምን ያድርግ፦

1ኛ. እለቱን በፆም ያሳልፍ

ይህን ቀን መፆም ያለውን ምንዳ አስመልክቶ የአላህ መልዕክተኛ(ሰዐወ) እንዲህ ብለዋል፦

"የዐረፋ እለት የፆመ ሰው ያለፈውን አንድ አመት እና የሚመጣውን የአንድ አመት ወንጀሉን ያስምረታል ብየ እከጅላለሁ" ማለታቸው ተዘግቧል። (ሙስሊም)

2ተኛ. በዱዐ ይበራታ

የአላህ መልዕክተኛ(ሰ•ዐ•ወ) "በላጩ እና ምርጡ ዱዓ በአረፋ ቀን ውስጥ የተደረገ ዱዓ ነው"ብለዋል።(ቲርሙዚ ዘግበውታል) 

በዚህ ቀን የትኛው ዱዐ ነው ይበልጥ ተወዳጅ ?

ነብዩ ﷺ እንዲህ አሉ፦ እኔም ከእኔ በፊትም የነበሩት ነብያት በዚህ ቀን የምንለው ይህን ዱዐ ነው ብለዋል።

لا إِلَهَ إِلَّا اللهُ وَحْدَهُ لا شَرِيكَ لَهُ، لَهُ الْمُلْكُ وَلَهُ الْحَمْدُ وَهُوَ عَلَى كُلِّ شَيْءٍ قَدِيرُ،

ከአላህ በቀር ሌላ አምላክ የለም። አንድ ነው። አጋርም የለውም። ስልጣን የርሱ ብቻ ነው። ምስጋናም የሚገባው ለርሱ ብቻ ነው።

በተቻለን መጠን ከዙሁር ቡሃላ አፋችንን በዚህ ዱዐ ልንጠምዳት ይገባል።

3ተኛ. ሰደቃ መስጠት

ሰደቃ የተዘጋ ሲሳይን ትከፍታለች፣ የመጣ በላዕ ታባርራለች፣ ከእሳት ቅጣት ትከላከላለች፣ ድብቅ ወንጀልን ታባርራለች፣ በዚህ ታላቅ ቀን እጃችን ላይ ባለው ነገር ከመልካም ንግግር ጀምረን ሰደቃ ልናረግ የተገባ ነው።

4ተኛ. እውነተኛ ተውበትን ማድረግ

ረሱል (ሰ•ዐ•ወ) "አላህ (ሱ•ወ) ባሪያውን ከእሳት ነፃ የሚያወጣበት ቀን ከአረፋ ቀን በላይ የለም" ማለታቸው በሙሰሊም ተዘግቧል። እኛም በዚህ ቀን አላህ (ሱ•ወ) ከእስት ነጃ ካላቸው ሰዎች ያደርገን ዘንድ ፤ ለክብሩ ተናንሰን፣ ለትእዛዙ እጅ ሰተን፣ ከልባችን እያለቀስን መሃርታውን ይቅር ባይነቱን እንዲሰጠን እየለመንን ከሰራናቸው ወንጀሎች በመጸጸት ወደ አላህ (ሱ•ወ) መመለስ ይገባናል።

አላህ (ሱ•ወ) እንዲህ ብሏል፦

ምእምናኖች ሆይ! ትድኑ ዘንድ ሁላችሁም ወደ አላህ (በመመለስ) ተጸጸቱ። [ሱረቱል-ኑር-31]

5ተኛ. ከወንጀል መራቅ

የአላህን ትእዛዛት መፈጸም ወደርሱ እንደሚያቃርብ ሁሉ የከለከላቸውን እና እርም ያደረጋቸውን ነገሮች መዳፈር ከርሱ መራቅን እና ከእዝነቱ ለመባረር ምክንያቶች ናቸውና በዚህም ቀን ሆነ በሌሎች ቀናት ከወንጀል መራቅ ግድ ይለናል።

ቁርአንን መቅራት፣ ሱና ሰላቶችን መስገድ፣ አላህን ማውሳት (ዚክር ማድረግ)፣ ወላጆችን መርዳት፣ ድሆችን መመገብ፣ ዱዓን ማብዛት፣ የታሰረን ወይም የታመመን ሰው መጠየቅ፣ ዝምድናን መቀጠል በዚህ ቀናት ልናረጋቸው የምንችላቸው መልካም ስራዎች ናቸው።

ከሁሉም በላይ አላህ አዋቂ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ ፣ የቴሌግራም ቻናሌን follow ያድርጉ
@ https://t.me/Xuqal
ለተጨማሪ መረጃ ፣ የቴሌግራም ቻናሌን follow ያድርጉ
@ https://t.me/Xuqal
ለተጨማሪ መረጃ ፣ የቴሌግራም ቻናሌን follow ያድርጉ
@ https://t.me/Xuqal
ስራህ ምንድን ነው?
ለዚህ አይነት ጥያቄ የተለየ የሚያኮራና ልብን የሚያሞቅ ምላሽ ሊገኝ የሚችለው ከዚህ ብርሃናማ ስፍራ የክብር ካባ ከደረቡት አገዋቶች አንደበት ብቻ ነው።

አገዋቶች የመስጅደ ነበዊ ኻዲሞች፣ የማረፊያቸውን ቁልፍ ጠባቂዎች፣ የሁለቱ ሃረም እንግዶች ኻዲም ናቸው። ለብዙ መቶ አመታት እየተፈራረቁ አገልግለዋል። አሁን የቀሩት ጥቂቶች ቢሆኑም አንደኛው ባለ እጣ አጋ ኑሪ ሙሐመድ አህመድ ዓሊ በመስጅደ ነበዊ የአገዋቶች ሸይኽን አግኝተን የመዘየሩን እድል ተወፍቀናል።

ከመልእክተኛው (ሰዐወ) ጋር የተገናኘ የትኛውም አገልግሎት ሽልማቱ የደረጃዎች ሁሉ ከፍታ መሆኑ ግልፅ ነው።

የሐበሻ መገለጫ የነቢ ማረፊያ ጠባቂ የቁልፉ ባለአደራዎች የመስጅደ ነበዊ ኻዲም የሆኑትን አገዋት ያለፉትንም ጨምሮ አላህ መልካም ስራቸውን ይቀበላቸው።

by አቡሐኒፋ - ሙሀመድ ሰዒድ

ለተጨማሪ መረጃ ፣ የቴሌግራም ቻናሌን follow ያድርጉ
@ https://t.me/Xuqal
“ኒዕማ ወደ አንተ ትመጣለች፤ የአላህ ውሳኔ የጣፋጭ ፍሬ ቅርንጫፏን ወደ እጅህ ያቀርብልሃል፤ አንተ ግን የስሩን ምንነት አታውቅም፣ አቅምም የለህም፡፡ ከዛም ኒዕማዋ ትገለበጥና እጅህ መራር የሆነው ፍሬ ቅርንጫፍ ላይ ያርፋል፤ ይህም ሲሆን አንተ አታውቅም፤ አቅምም የለህም፡፡ አዋጅ! ኢማን ማለት እርግጠኝነት (የቂይን) መሆኑን እወቅ፡፡ ሁለቱም ቅርንጫፎች አላህ ዘንድ ያደርሱሃል የጣፋጩ ቅርንጫፍ አምልኮቶች የምላስና የተግባር ምስጋናዎች ናቸው፤ ይህ በስሜት ህዋስህ ስታቀምሰው እጅግ ጣፋጭ ነው፡፡ የመራሩ ቅርንጫፍ አምልኮቶች ደግሞ ትዕግስት (ሶብር) እና ወዶ መቀበል (ሪዷ) ናቸው፤ ይህንንም በሩህህ ስትቀምሰው እጅግ ጣፋጭ ነው፡፡” (ሙስጦፋ ሷዲቅ አልሪፋዒ)
.
ለተጨማሪ መረጃ ፣ የቴሌግራም ቻናሌን follow ያድርጉ
@ https://t.me/Xuqal
"አላህ በባሪያው ላይ መልካምን ከፈለገለት ቅጣቱን በዱንያ ያፈጥንለታል፤ አላህ በባሪያው ላይ መጥፎን ከፈለገለት ወንጀሉን ዝም ይለውና የቂያማ ቀን በወንጀሉ ይይዘዋል፡፡"
ረሱል صلى الله عليه وسلم
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
عليه افضل الصلاه والسلام ياحبيب يارسول الله صلى الله عليه وسلم ياحبيب يارسول الله صلى الله عليه وسلم ياحبيب يارسول الله صلى الله عليه وسلم ياحبيب يارسول الله صلى الله عليه وسلم ياحبيب يارسول الله صلى الله عليه وسلم ياحبيب يارسول الله صلى الله عليه وسلم ياحبيب يارسول الله صلى الله عليه وسلم ياحبيب يارسول الله صلى الله عليه وسلم ياحبيب يارسول الله صلى الله عليه وسلم

ለተጨማሪ መረጃ ፣ የቴሌግራም ቻናሌን follow ያድርጉ
@ https://t.me/Xuqal
ያ ረቢ

ወደ ወንጀሎቼ እመለከትና እፈራለሁ! የጥፋቴ ግዝፈት ያሸማቀኛል!?

ወደ እዝነትህ ስመለከት ደግሞ ተስፋ አድርጌ እደሰታለው:: እዝነትህ ከቁጣህ የቀደመች ናትና ተስፋዬ ይለመልማል

ግና እራሴን ስመረምር በስራዬ በመሸማቀቅ አንተን መጠየቅ አፍራለው

እንዴትስ አንተን ባመፀ ምላስ ልጠይቅህ??

ወይስ አንተን ባጠራህ፣ባላቀህ እና ባስታወስህ ምላሴ ደፍሬ ልማፀንህ?

ውዱ አምላኬ ሆይ

አንተን ማስታወስ በዘነጋ ምላሴ አንተን መለመን ይቻለኝ ይሆን ?

ወይስ ባንተ ፍቅር በሰመጠው ተናናሽ ልቤ ልማፀንህ ?

ኢላሂ

በልቅናህ እና በሀያልነትህ ይሁንብኝ

ያንተን ይቅርታና መሀርታን ለመጠየቅ እደጅህ ላይ ጠዋት እና ማታ ሳልታክት እቆማለው:: እዝነትህን እከጅላለው::

ጌታዬ ይኸው እኔ ልክ እንዳዘዝከኝ ለመንኩህ ኃያሉ ጌታዬም ቃል እንደገባህልኝ አንተም ልመናዬን ተቀበለኝ

እንደ ባህር አረፋ የበዛውን ወንጀሌን ሁሉ እጠብልኝ፣ የጠየኩህን ልመና ሁሉ ተቀበለኝ:: በዚህችም አለም፤ በመጪዋም አለም ስኬትን አጎናፅፈኝ

አሚን

ለተጨማሪ መረጃ ፣ የቴሌግራም ቻናሌን follow ያድርጉ
@ https://t.me/Xuqal
በዓለም ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ …

#Ethiopia | ሳኡዲ አረቢያ በሐጅ ወቅት የመጀመሪያዉን በሰማይ ላይ ማሽከርከር የአየር ታክሲ በይፋ በዛሬ ዕለት ይፋ አድርጋለች ።
Towards Mina!
ሁጃጆች ወደ #ሚና ጉዟቸውን ጀምረዋል!
#hajj #hajj1445

ኢላሂ እኛንም ወፍቀን 🤲 አሚን
ሳሊህ የሆነች ሚስት የፈለገ
ሳሊህ የሆኑ ልጆችን የፈለገ
አፊያ፣ ሀላል ሪዝቅን የፈለገ
ወንጀሉ እንዲማርለት የፈለገ
ዱንያ የከለከችውን ነገር ማግኘት የፈለገ… የነገዋን እለት በዱዐ ሙጢኝ ይበል። አህባቢ ያው እንደ ዱንያ ነዋሪ ብዙ ሀጃዎች አሉኝና በመልካም ዱዐቹ አስታውሱኝ።🙏

ለተጨማሪ መረጃ ፣ የቴሌግራም ቻናሌን follow ያድርጉ
@ https://t.me/Xuqal
መስጂድ አል ኸይፍ ሚና በተርዊያህ ቀን በሺህ የሚቆጠሩ ሰጋጆች መስጂድ ተጨናንቋል ።
ኃጥያቴ ቢበዛም ለበይከ ጌታዬ… አንተን የተጠጋ ልብ እድለቢስ ሆኖ አያውቅምና። በቅዱሱ ስፍራ ከሁጃጆች መሀል ሆኜ ባልጠራህም … ካለሁበት ቦታ አቤቱ እልሃለሁ። ልቤ ደርቆ ስምህን ደጋግሜ ባላነሳም… መመለሻዬ አንተ ብቻ ነህና ለበይከ ረቢ። ቤትህን ከሚወዱን ከምንወዳቸው ጋር የምንዘይርም አድርገን ያ አላህ። 🥹 🤲