Bilaluna Edris
543 subscribers
3.35K photos
275 videos
50 files
2.3K links
♡_ወደ መልካም ነገር ያመላከተ ሰው የሰራ ሰውን አጅር ያህል ያገኛል"(አመላካች የሰሪውን ምንዳ ያገኛል)(ﷺ)

« ከናንተም ወደ በጎ ነገር የሚጠሩ ፣ በመልካም ስራም የሚያዙ ከክፉ ነገርም የሚከለክሉ ሕዝቦች ይኑሩ» ﷻ
                 ቁርኣን[ 3:104 ]


መወያያ ግሩፓችን ☞ https://t.me/+1qmNqy265XoyNGY0
Download Telegram
#BREAKING!
የኢራኑን ፕሬዝደንት ጭኖ በነበረ ኮንቮይ ላይ የነበረ ሄሊኮፕተር አደጋ ደረሰበት!
#ኢራን ቲቪ
የኢራን ባለስልጣን ለሮይተርስ እንደተናገሩት የሄሊኮፕተር አደጋውን ተከትሎ የፕሬዚዳንቱ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ህይወት አደጋ ላይ ነው።
#አልጀዚራ
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በምስራቅ አዘርባጃን ግዛት አደጋ በደረሰባት ሄሊኮፕተር ላይ የኢራኑ ፕሬዝዳንት ከውጪ ጉዳይ ሚኒስትሩ እና ከበርካታ ባለስልጣናት ጋር #የመጨረሻ እይታ!
#አልጀዚራ

ኢና ሊላህ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን !

በጎንደር በግፍ የተገደሉት የመስጂድ ኢማም ሸይኽ ሲራጅ አብድሬ እኚህ ናቸዉ!

በአማራ ክልል በማዕከላዊ ጎንደር ደንቢያ ወረዳ አየንባ ቀበሌ የመስጂድ ኢማም የሆኑት ሸይኽ ሲራጅ አብድሬ በግፍ ተገድለዋል::

አላህ(ሱ.ወ) ይዘንላቸዉ። አሚን🤲

የቴሌግራም ቻናሌን በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
@ https://t.me/Xuqal
“በአስቸጋሪ የአየር ሁኔታ እና በቀላሉ ሊደረስበት በማይችል ተራራማ አካባቢ የፍለጋው ስራ ቀጥሏል!
- ተጨማሪ የነፍስ አድን ቡድኖች ወደ አደጋው ቦታ እየላክን ነው!”

የኢራን መንግስት ቃል አቀባይ!
#አልጀዚራ

የቴሌግራም ቻናሌን በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
@ https://t.me/Xuqal
የኢራኑ ፕሬዝዳንት ሄሊኮፕተር የወደቀችው በመጥፎ የአየር ሁኔታ ምክንያት ሲሆን ተሳፋሪዎቹ መቁሰላቸውን ወይም መሞታቸውን ማረጋገጥ አልተቻለም።
በሄሊኮፕተሩ ላይ የተሳፈሩት ሰዎች ሞተዋል ወይም ቆስለዋል የሚሉ ዘገባዎች ያልተረጋገጡ ስለሆኑ አስተማማኝ አይደሉም!”
#መህርአጄንሲ(ኢራን)

የቴሌግራም ቻናሌን በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
@ https://t.me/Xuqal
▪️የኢራኑ ፕሬዝዳንት ራይሲ ከሄልኮፕተር አደጋው ጥቂት ቀደም ብሎ የነበሩበትን የሚያሳይ ቪዲዮ፤ እንዲሁም
    - ከአደጋው በኋላ ለአደጋ ጊዜ ሰራተኞች የሄልኮፕተር ፍለጋ ስራቸውን አስቸጋሪ ያደረገው የአየር ሁኔታ

#Ethiopia #Raisi
#Iran #Helicoptercrash #SearchOperation
#RescueOperation

የቴሌግራም ቻናሌን በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
@ https://t.me/Xuqal
🇮🇷🇺🇸 የአሜሪካ አየር ኃይል ካርጎ የሆነው C-17 ግዙፍ ወታደራዊ አይሮፕላን ከዓመት በላይ ጊዜ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ አዘርባጃን ባኩ በዛሬው ዕለት ማረፉ ተሰምቷል።

  የአሜሪካው ወታደራዊ ካርጎ የኢራኑ ፕሬዝዳንት ራይሲ የተሳፈረበት ሄሊኮፕተር አዘርባጃንን ከመልቀቁ እና ከተከሰከሰበት ጊዜ ጋር መገጣጠሙ ጥያቄዎችን እየፈጠረ ይገኛል።

#Ethiopia #Raisi
#Iran #Helicoptercrash #SearchOperation
#RescueOperation

የቴሌግራም ቻናሌን በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
@ https://t.me/Xuqal
#BREAKING
የኢራኑ ፕሬዝዳንት ኢብራሂም ራይሲ፣የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ሁሰይን አሚር አብዱላሂ እና አብሯቸው የነበረው የልዑካን ቡድን በሙሉ በሄሊኮፕተር አደጋው መሞታቸውን የኢራን መንግስት ቴሌቭዥን አስታውቋል!
#አልጀዚራ

የቴሌግራም ቻናሌን በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
@ https://t.me/Xuqal
የአፋልጉኝ ጥሪ......

በአፋር ክልል ከወላጆቹ ጋር በሎጊያ ከተማ የሚኖረው ህፃን አፍረሂም ሙሀመድ አብዱ ዛሬ ጠዋት አካባቢ ወላጆቹ ለመልእክት ወደ ሱቅ ልከውት እስካሁን አልተመለሰም። ህፃን አፍረሂም ሙሀመድን ያየ ካለ ከታች ባለው ስልክ ቁጥር (+251910090080)ደውላችሁ ብታሳውቁን ወሮታውን ከፋይ ነን። ቤተሰቦቹ
ሼር ሼር ሼር
«አንድ ሰው  ከሚኖረው መልካም ነገራት ሁሉ  በላጩ በመከራ የማይንበረከክ ልብን ማግኘት  ዋነኛው ነው»
©أدهم شرقاوي
በስም ሳይሆን በመሆን፤በምላስ ሳይሆን በተግባር እንዴት ወንድ እንደሚኾን ያሳዩ ድምቅ መሪ።ሰዎች ግማሾቹ በዐረባዊ ብሔረተኝነት፤ሌሎቹንም በቡድናዊ ወገንተኝነት ተቆላልፈው በታሰሩበት ሰዓት ፐርሺያነታቸውና የሺዓ ቡድን ተከታይነታቸው ዐረብና የሱና ተከታይ የሆኑት የገዛ ወንድሞቻቸውን ከመርዳት እንደማያግዳቸው ያሳዩ ድንቅ ህዝቦች ሐገር መሪ!
ሰይድ ኢብራሂም ከስማቸው ድርሻቸውን የወሰዱ ናቸው።በአንዱ ሞት የማይሞት የኡመት ስም ነው!
አሏህ በሰፊው ራሕመቱ ይቀበሎት ሰይድ ኢብራሂም ረኢሲ

የቴሌግራም ቻናሌን በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
@ https://t.me/Xuqal
ለተባበራችሁ ወንድም እና እህቶች ሁሉ አላህ ምንዳችሁን በሰፊው ይክፈላችሁ እናመሰግናለን
እውቀት ማለት የተሸመደደ ሳይሆን የተጠቀምክበት ነው !
       ኢማሙ ሻፊዒይ ረሂመሁላህ
Bilaluna Edris
Photo
ልዩ “ኸበር” - ከ6 ዓመት ሕፃን ዕድሜ የጀመረ የሐጅ ትዝታ

ኤንዶኔዥያዊቷ እናት መርየም ሙሐመድ ሙኒር፣ ከሰሞኑ ሳዑዲ ዐረቢያ ተገኝተዋል፡፡ እናት መርየም ሳዑዲ የተገኙት ለዓመታዊው የሐጅ ሥርዐት ክንውን ነው፡፡ የ66 ዓመት ዕድሜ ያላቸው እናት፣ ከ60 ዓመት በፊት በ6 ዓመታቸው በተመሳሳይ አሁን የተገኙት ሥፍራ ላይ ነበሩ፡፡

ያን ጊዜ ግን ዕድሜያቸው 6 ዓመት ብቻ ነበር፡፡ ክፉ እና ደግ የሚለዩም አልነበሩም፡፡ ወላጆቻቸው ለሐጅ ሲያቀኑ አስከትለዋቸው ነው፡፡

እናት መርየም በ6 ዓመት ዕድሜያቸው ጀምረው በተደጋጋሚ ለሐጅ እና ዑምራ ሳዑዲ ዐረቢያ ተመላልሰዋል፡፡ የሳዑዲ ዜና አገልግሎት እንዳለው ከሆነ ኢንዶኔዥያዊቷ እናት የዘንድሮው ጉዟቸው ለ22ኛ ጊዜ የተከናወነ ነው፡፡

እናት መርየም በእነዚህ ስድስት ዐስርት ዓመታት የቆየ የሐጅ ትዝታቸው ውስጥ፣ የሚያስገርሟቸው ነገሮች ምን እንደሆኑ ተጠይቀው ነበር፡፡ ኢንዶኔዥያዊቷ እናት አንደኛው ጉዳይ ከሀገራቸው ወደ ሳዑዲ ዐረቢያ ለመጓዝ የመንገዱ ማጠር እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

እናት መርየም ከ60 ዓመት በፊት ከወላጆቻቸው ጋር ወደ ሐጅ ሲጓዙ አሁን እንዳደረጉት በአውሮፕላን አልበረሩም፡፡ ባይሆን አነስተኛ መጠን ያላቸው መርከቦች እየተፈራረቁ አድርሰዋቸዋል፡፡ መርከቦቹ ከኢንዶኔዥያ ተነስተው ሳዑዲ ለመድረስ ሕንድን፣ ዐረቢያ እና ቀይ ባህርን ማቋረጥ ነበረባቸው፡፡ እንደ እናት መርየም አገላለጽ ያን ጊዜ የነበረው ከአምስት እስከ ስምንት ሰዓት የሚፈጅ የሐጅ ጉዞ፣ ከሚበላው ገንዘብ እና ጊዜ በተጨማሪ አደገኛ እና አስፈሪ ነበር፡፡

እናት መርየም ከ60 ዓመት በኋላ ከጃካርታ ሳዑዲ ዐረቢያዋ ቅድስት ከተማ መዲና ለመድረስ 9 ሰዓት ከ45 ደቂቃ ብቻ በአየር ላይ በአውሮፕላን በርረዋል፡፡

የእናት መርየም ሀገር ኢንዶኔዥያ፣ በዘንድሮው ዓመት የሐጅ ሥነ ሥርዐት እርሳቸውን ጨምሮ 241 ሺሕ ምዕመናንን ወደ ሐጅ ሥነ ሥርዐት ትልካለች፡፡

የቴሌግራም ቻናሌን በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
@ https://t.me/Xuqal
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ቁርአን ልባችን ላይ እንዲቀመጥ ከፈለኝ አካላችንን ብቻ ሳይሆን ልባችንንም ማጽዳት አለብን! ቁርአን የሚነበብ ብቻ ሳይሆን ለሁለት ዓለም ስኬት የሚያበቃ የህይወት መንገድ ነው።

የቴሌግራም ቻናሌን በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
@ https://t.me/Xuqal
Bilaluna Edris
Photo
ልዩ “ኸበር” - የሳዑዲ ዐረቢያ የሐጅ ሽር ጉድ በመጨረሻው ሰዓት

ከመላው ዓለም ለሐጅ ሥነ ሥርዐት ክንውን ወደ ሀገሯ ይገባሉ ተብለው የሚጠበቁትን ከሁለት ሚሊዮን የሚልቁ ምዕመናንን መቀበል የጀመረችው ሳዑዲ ዐረቢያ፣ የአላህ እንግዶች ከቤት የወጡበትን ውጥን እንዲሞሉ ሽር ጉድ ማለቷን ቀጥላለች፡፡ ሳዑዲ እንግዶችን መቀበል የጀመረችው ግንቦት 1/2016 ነበር፡፡ እስካሁን ከተቀበለቻቸው ውስጥ ከእኛዋ ኢትዮጵያ የተነሱ ምዕመናን ይገኙበታል፡፡ 12 ሺሕ ኢትዮጵያውያን እስከ ሰኔ 2/2016 ድረስ ሳዑዲ ዐረቢያ ተጠናቀው ይገባሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

በርግጥ ሳዑዲ ዐረቢያ ሑጃጆችን መቀበል ጀምራም ቢሆን ለዑምራ እና ሌላ ጉዳይ (ለምሣሌ ለጉብኝት) በተለይ መካ ከተማ የሚጓዙ የሀገሯን ሰዎችም ሆነ እንግዶችን ስታስገባ ቆይታለች፡፡ ሆኖም ከዛሬ ሐሙስ ግንቦት 15/2016 አንስቶ ለሐጅ ካልሆነ በስተቀር የከተማዋን በር መቆለፏን እወቁት ብላለች፡፡ በዚህም ወደ ቅድስቲቱ መካ ከተማ የሚያስገቡ የፍተሻ ጣቢያዎች፣ ከሑጃጅ ውጪ ሌላ ሰው ወደ ውስጥ እንዳይዘልቅ ጥብቅ ቁጥጥር እያደረጉ ይገኛሉ፡፡ ሳዑዲ ዐረቢያ ከሚቀጥለው ሳምንት ግንቦት 25/2016 ጀምሮ ደግሞ፣ በድንገት ያለ ሐጅ ቪዛ ወደ መካ ከተማ ዘልቆ ያገኘችውን ግለሰብ እንዲሁ አትለቀውም፤ 10 ሺሕ ሪያል መቀጮ እንደምታስከፍለው ቀድማ አሳውቃለች፡፡ ቅጣቱ በዚህ ብቻ ላይቆም ይችላል፤ ከተደጋገመ ከምድሯ ያስባርራል፡፡

ሳዑዲ ዐረቢያ ወደ ሐጅ ቀናት ስትቃረብ፣ ከሐጅ ቪዛ ውጪ የያዙ ምዕመናንን ወደ መካ እንዳይገቡ ከማገድ ጎን ለጎን ሐጅ መድረሱን ጠቋሚ የሆነውን የካዕባን ልብስ ከፍ አድርጋለች፡፡ ሳዑዲ በየዓመቱ የሐጅ ቀናት ሲቃረቡ ይህን የምታደርገው በጥንቃቄ ነው፡፡ ዘንድሮም ኪስዋውን ከመሬት ከፍ ለማድረግ 36 ባለሞያዎችን ከአስር “ክሬን” ጋር መድባለች፡፡ ባለሞያዎቹ ልብሱን ከፍ አድርገው በአራቱም ማዕዘን በነጭ የጥጥ ጨርቅ እንዲሸፈን (ኢህራም) አድርገውታል፡፡

ኢህራም የተደረገው ኪስዋ በየዓመቱ የሚቀየር ነው፡፡ ከዚህ ቀደም ከሁለት ሳምንት በኋላ በሚጀምረው በዙልሒጃ ወር 9ኛው ቀን ይቀየር የነበረ ቢሆንም በቅርብ ጊዜያት በአዲሱ ዓመት መግቢያ ሙሐረም ወር የመጀመሪያው ምሽት እንዲቀየር ተወስኗል፡፡

ኪስዋ የዓለማችን ውዱ ልብስ ነው፡፡ የልብሱ ክብደት 850 ኪሎ ግራም ሲመዝን፣ ወጪው ደግሞ 6.5 ሚሊዮን ዶላር ይገመታል፡፡ ኪስዋ ሲዘጋጅ ቢያንስ 200 ባለሞያዎች ይሳተፋሉ፡፡ የኪስዋ 670 ኪሎ የሚመዝነው ጥቁር ሀር ነው፡፡ በዚህ ሀር ላይ ለሚጻፉ የቁርኣን አንቀፆች 120 ኪሎ 21 ካራት ወርቅ እንዲሁም 100 ኪሎ ግራም ብር ጥቅም ላይ ይውላል፡፡

የቴሌግራም ቻናሌን በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
@ https://t.me/Xuqal