Bilaluna Edris (Xuqal.X.Qafarey)
466 subscribers
3.04K photos
187 videos
46 files
2.1K links
♡_ወደ መልካም ነገር ያመላከተ ሰው የሰራ ሰውን አጅር ያህል ያገኛል"(አመላካች የሰሪውን ምንዳ ያገኛል)(ﷺ)

« ከናንተም ወደ በጎ ነገር የሚጠሩ ፣ በመልካም ስራም የሚያዙ ከክፉ ነገርም የሚከለክሉ ሕዝቦች ይኑሩ» ﷻ
                 ቁርኣን[ 3:104 ]


መወያያ ግሩፓችን ☞ https://t.me/+1qmNqy265XoyNGY0
Download Telegram
ከጥቂት ቀናት በፊት በግብፅ ብሄራዊ ደህንነት ኢንተለጀንሶች በኩል አንድ መልዕክት ተላከ። ከዋሽንግተን ነበር። ለቀሳሙ መሪ ለየህያ ሲንዋር።
  ለግሉ 15 ቢሊዮን ዶላር ስጦታ፣ ምቹና ቅንጡ መኖርያ፣ ጋዛ ከተማን መልሶ ለመገንባት ቃል የሰፈረበት ደብዳቤ! በምትኩ የህያ ሲንዋር ቀሳሞችን ከውስጥ በኩል ሰርስሮ በመናድና በመሰነጣጠቅ ህብረታቸውን እንዲንድላቸው ይጠይቃል።

አደራ ይላል መልዕክቱ መጨረሻ ላይ "አደራ ከግብፅ አስታራቂዎች በኩል የቀረበውን ልዩ ጥያቄ ተጠቀምበት ይህ እድል እንዳያመልጥህ" በማለት ይቋጫል።

የህያ ሲንዋር ከአራት ቀናት በኋላ ለዚህ ጥያቄ በአንድ አንቀጽ ምላሽ ሰጠ እንዲህ ይላል፡-

فَلَمَّا جَاءَ سُلَيْمَانَ قَالَ أَتُمِدُّونَنِ بِمَالٍ فَمَا آتَانِيَ اللَّهُ خَيْرٌ مِّمَّا آتَاكُم بَلْ أَنتُم بِهَدِيَّتِكُمْ تَفْرَحُونَ

"ሱለይማንንም በመጣው ጊዜ አለ «በገንዘብ ትረዱኛላችሁን አላህም የሰጠኝ ከሰጣችሁ የበለጠ ነው፡፡ ይልቁንም እናንተ በገጸ በረከታችሁ ትደሰታላችሁ"
                   [አን-ነምል 36]

@ https://t.me/Xuqal
Bilaluna Edris (Xuqal.X.Qafarey)
Photo
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ                           
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
የሐጅ ቪዛ ሳይይዙ ሐጅ ማድረግ እንደማይቻል የሳዑዲ የሐጅ ሚኒስቴር አስጠነቀቀ።
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••

ሚያዝያ 21፣ 2016 (አዲስ አበባ) - የሳዑዲ አረቢያ የሐጅ እና ዑምራ ሚኒስቴር፣ የሐጅ ቪዛ ሳይይዙ ሐጅ ማድረግ እንደማይቻል በመግለጽ ዘንድሮ ሐጅ የማድረግ ኒያ ያላቸው ምዕመናን "ሐጅ እናስደርጋለን" በሚሉ የግል ኩባንያዎች እንዳይታለሉ በጥብቅ አስጠነቀቀ።

ሚኒስቴሩ ይህን ማስጠንቀቂያ ይፋ ያደረገው፣  በተለያዩ ሀገራት በማኅበራዊ ትስስር አውታሮች የሐጅ ቪዛ እንሰጣለን የሚሉ ሐሰተኛ ኩባንያዎች በስፋት የሚያሰራጩት ማስታወቂያ መበራከቱን ከተመለከተ በኋላ መኾኑን በመግለጫው ጠቅሷል።

ሐጅ ለማድረግ ሳዑዲ አረቢያ ከመገባቱ በፊት የሐጅ ቪዛ ማግኘት የግድ አስፈላጊ መኾኑን የጠቀሰው ሚኒስቴሩ፣ በጉብኝት ቪዛ፣ በሥራ ቪዛ፣ በቱሪስት ቪዛ፣ በትራንዚት እና በመሳሰሉት ቪዛዎች ሳዑዲ አረቢያ በመግባት ሐጅ ማድረግ እንደማይቻል አሳስቧል።

ሚኒስቴሩ አክሎም፣ ሐጅ ማድረግ የሚቻለው ጉዳዩ የሚመለከተው የሳዑዲ አረቢያ ሚኒስቴር በየሀገራቱ የሐጅና ዑምራ ጉዳይ ከሚመለከታቸው ተቋማት ጋር በመተባበር በሚሰጠው የሐጅ ቪዛ እና፣ እነዚህ ተቋማት በሌሉባቸው ሀገራት ደግሞ "ኑሱክ ሐጅ" በሚሰኘው ፕላትፎርም አማካይነት ብቻ መኾኑን መረዳት ያስፈልጋል ብሏል።

ሐጅ ለማድረግ፣ ሳዑዲ አረቢያ ከመገባቱ በፊት ራሱን የቻለ የሐጅ ቪዛ ማግኘት የግድ አስፈላጊ እንደኾነ የጠቀሰው የሚኒስቴሩ መግለጫ፣ ከሳዑዲ የሐጅና ዑምራ ሚኒስቴር ጋር ግንኙነት ካላቸው የየሀገራቱ የሐጅና ዑምራ ተቋማት ውጪ የሐጅ ቪዛን ማግኘት እንደማይቻል በመግለጽ ምዕመናን ከመታለል እንዲጠነቀቁ አሳስቧል።

"ሐጅ እናስደርጋለን" በሚሉ አጭበርባሪ ኩባንያዎች መታለል ከሚያስከትለው የገንዘብ ኪሳራ በተጨማሪ፣ የጓጉለትን ሐጅ ለማድረግ አለመቻልን በማስከተል ከባድ ሐዘን ላይ ሊጥል እንደሚችል ሚኒስቴሩ አሳስቧል።

@ https://t.me/Xuqal
“አላህ ዘንድ መልካም ጎደኛ ማለት ለጎደኛው መልካም የሆነው ነው። አላህ ዘንድ መልካም ጎረቤት ማለት ለጎረቤቱ መልካም የሆነው ነው።”
ረሱል ﷺ
"እውነተኛ ታማኝ ነጋዴ አኸራ ላይ ከነብያቶች ፣ ከሲዲቆች እና ከሰማእታት ጋር ነው"
ረሱል ﷺ
#አላሙዲን_በገባው_ቃል_መሠረት_ስራውን_ጀምረዋል

ለ27 አመታት ግንባታው ተቋርጦ የነበረው የሱልጣን አሊሚራህ ኢስላማዊ ኮለጅ ግንባታ ሸህ መሀመድ ሁሴን አላሙዲን በሰኔ 06/2013 ቃል በገቡት መሠረት የፕሮጀክቱን ግንባታ በይፋ ጀምረዋል። ከወራት በፊት ግንባታ የተፈቀደው ለመስጅድ ብቻ ነው የሚለው ሀሳብ ደስታች ጎዶሎ አድርጎት ነበር። ዛሬ ደግሞ  የመድረሳው ግንባታ አብሮ እንዲቀጥል አላሙዲን መፍቀዳቸውና በቀጣይ ሳምንት ስራ እንደሚጀመር  ስንሰማ ተደስተናል። አላሙዲን በገቡት ቃል መሠረት በቃላቸው በማገኘት ግንባታው ተጀምረዋል ከወራት ቡሗላ ይጠንቀቅ ተብሎ ይጠበቃል።

  አሁን የቀረው የክልሉ መንግስታችን የገባልን ቃል ብቻ ነው። እሱም በፕሮጀክቱ ላይ የሚገኘው 25 ሚሊዮን ብር እዳ ጉዳይ ነው። የክልሉ መንግሥት የኮንትራክተሩን ክፍያ በሰኔ 06/2013 ልክ እንደአላሙዲን ለአሳይታ ህዝብ እዳውን እንደሚከፍል በመድረኩ ቃል ገብተዋል። እዳውን ለማክፈል ድርሻውን ወስደዋል። እስካሁን የክልሉ መንግስት በገባው ቃል መሠረት የኮንትራክተሩን ክፊያ አልከፈለም። መንግሥታችን በመስጅዱ ላይ ያለው እዳ በገባው ቃል መሠረት እንደሚከፍል ተስፋ አለን። እዳው ተከፍሎ ከእዳ ነፃ ስንሆን እና  የፕሮጀክቱ ግንባታ ስጠናቀቅ ያኔ ደስታችን ሙሉ ይሆናል። አላህ የዛ ሠው ይበለን!

Via @Aloyayyo
@ https://t.me/Xuqal
"የነቢዩ (ﷺ) ሰሃባዎች (ስራቸውን አላህ ይውደድላቸው) ገንዘባቸውንና ቤታቸውን ለአላህ ሲሉ በመተዋቸው…አላህ ዱንያን ሙሉ በሙሉ በእጃቸው አደረገላቸው፡፡"

#ኡስታዝ_በድሩ_ሁሴን
Bilaluna Edris (Xuqal.X.Qafarey)
Photo
የመጀመሪያዎቹ ኢትዮጵያውያን ሑጃጆች ወደ ሳዑዲ ዐረቢያ በረራ የሚያደርጉበት ቀን ታወቀ

#Ethiopia |~ መጅሊስ ለተጓዦች ስለ ሐጅ አፈፃፀም የሚሰጠው ሥልጠና በዛሬው እለት ይጀምራል ።

ለ1445 ዓ.ሂ የሐጅ ሥነ ሥርዐት ከተመዘገቡ ኢትዮጵያውያን ውስጥ የመጀመሪያዎቹ ተጓዦች በረራ የሚያደርጉበት ቀን ታወቀ። “ሚንበር ቲቪ” ከኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት (መጅሊስ) የሐጅ እና ዑምራ ዘርፍ እንደሰማው የመጀመሪዎቹ ተጓዦች በረራ የሚከናወነው ግንቦት 13፣ 2016 ነው።

ምክር ቤቱ ለዘንድሮው ዓመት የሐጅ ሥነ ሥርዐት ለመላክ በእቅድ የያዘው የምዕመናን ቁጥር መጠን 12 ሺሕ መሆኑን መዘገባችን ይታወሳል። “ሚንበር ቲቪ” ከመጅሊስ ኃላፊዎች ማረጋገጥ እንደቻለው በተያዘው ዓመት ለሐጅ ክንውን ወደ ሳዑዲ የሚጓዙ ኢትዮጵያውያን ምዕመናን ቁጥር ከአምናው በ1 ሺሕ 62 ብልጫ ያለው ነው።

መጅሊስ ለጉዞው የመዘገባቸውን ምዕመናን ከዛሬ ማክሰኞ ሚያዝያ 22/2016 አንስቶ ሥልጠና መስጠት እንደሚጀምር ታውቋል። ይህ ሥልጠና ለስድስት ቀናት የሚቆይ ነው።

የዘንድሮው ዓመት የሐጅ ሥነ ሥርዐት ሰኔ 7/2016 ይጀመራል ተብሎ ይጠበቃል። በመላው ዓለም የሚገኙ ወደ 2 ሚሊዮን ገደማ የሚቆጠሩ ምዕመናን ሥነ ሥርዐቱን ለመፈፀም ከግንቦት 1/2016 ጀምሮ ወደ ሳዑዲ ዐረቢያ መግባት እንደሚጀምሩ የሀገሪቱ መገናኛ ብዙኃን ዘገባ ያመለክታል።

ምንጭ  = ሚንበር ቲቪን
ኢላሂ እኛንም ወፍቀን 🥹 🤲
የቴሌግራም ቻናሌን በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
@ https://t.me/Xuqal
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ፍቅር ጥግ …… ፊዳከ አቢ ወኡሚ ያ " ረሱለሏህ !
Bilaluna Edris (Xuqal.X.Qafarey)
Photo
አቡ ዑበይዳ (አሚር ኢብኑ አብዱላህ ኢብኑ አል-ጀራህ)

በዱንያ ሳሉ በነብያችን ሰ•ዐ•ወ አማካኝነት በጀነት ከተበሸሩ ሰሃባዎች መሃከል አንዱ ነው። "በኑል ሃሪሳ" ተብሎ የሚጠራው የቁረይሽ ጎሳ አባል የሆነው የአል-ሀሪስ ኢብኑ ፊህር ጎሳ አባል ነበር።  ቤተሰቡ በሂጃዝ (በምእራብ አረቢያ) ውስጥ የቁረይሽ መገኛ በሆነችው ዝቅተኛ የመካ ስፍራ ነው።

የአቡ ኡበይዳ አባት አብደላህ በ6ኛው መቶ ክፍለ ዘመን መገባደጃ ላይ በሃዋዚን ዘላኖች ላይ በተደረገው የፊጃር ጦርነት ከቁረይሾች አለቆች ውስጥ አንዱ ነበር። እናቱም ቁረይሻዊ ነበረች።

አቡ ኡበይዳህ የተወለዱት በዚሁ ስፍራ እ.ኤ.አ በ583 ዓ.ል አካባቢ ሲሆን። እስልምናን ከመቀበላቸው በፊት ከቁረይሽ መኳንንቶች ውስጥ አንዱ እንደሆኑ ይቆጠሩ የነበሩ ሲሆን በጎሳቸዉ ሰዎች ዘንድም በጨዋነታቸው እና በጀግንነታቸው የሚታወቁ ዝነኛ ሰው ነበሩ።

እ.ኤ.አ በ611 ዓ.ል ነብያችን ሙሀመድ (ሰ•ዐ•ወ) ለመካ ሰዎች፣ ለቅርብ ባልደረቦቻቸው እና ዘመዶቻቸው በግል እና በመነረገድ ላይ ዳዕዋ የአላህን አንድነት ይሰብኩ በነበረበት ጊዜ አቡበክር ረ•ዐ ከሰለሙ ከአንድ ቀን በኋላ በ28 አመታቸው ኢስላምን ተቀበሉ።

አቡ ዑበይዳ ሙስሊሞች በመካ ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ ባሳለፉት ከባድ እንግልት እና መከራ ውስጥ ኖረዋል። በአንድ ወቅት መኳንንት የነበሩት እኒህ ሰው ለኢስላም ሲሉ ከሌሎች ቀደምት ሙስሊሞች ጋር  ሆነው የቁረይሾችን ስድብና እንግልት ተቋቁመው አልፈዋል።

ነብያችን ሙሀመድ (ሰ•ዐ•ወ) ከመካ ወደ መዲና በተሰደዱ ጊዜ አቡ ኡበይዳም እንዲሁ ወደ መዲና ተሰደዱ። ነብያችን ሙሀመድ (ሰ•ዐ•ወ) መዲና በደረሱ ጊዜ ሙሃጅሩን ከአንሷሪዩ ጋር በወንድማማችነት ሲያጣምሩ ከሙሀመድ ኢብኑ መስለማህ ጋር በወንድማማችነት ተጣመሩ።

አቡ ዑበይዳህ የሙስሊሞች ጀግና የጦር አዛዥ ሆነው ካለፉ የነብያችን (ሰ•ዐ•ወ) ድንቅ ባልደረባዎች መሃል አንዱ ነበሩ። ከቁረይሽ ሙሽሪኮች ጋር በተደረገው የበድር ዘመቻ ወላጅ አባታቸውን ለኢስላም ሲሉ በሰይፋቸው መቅላታቸው የሚታወስ ነው። በዚህ ቆራጥ ተግባራቸው ሰበብ አላህ ሱ.ወ የቁርአን አንቀፅ ሊያወርድላቸው ችሏል።

በሁለተኛው ኸሊፋ በኡመር ረ.ዐ ዘመን የጦር ሰራዊት አዛዥ ሆነው ኢስላምን አገልግለዋል። ኡመር ረ.ዐ እኔን ይተኩኛል ብለው በዝርዝር ከያዟቸው ሹማምንቶች ውስጥ አንዱ የነበሩት አቡ ዑበይዳህ ኢብኑ ጀራህ ረ•ዐ እ.ኤ.አ በ639 ዓ.ል በዑመር የአገዛዝ ዘመን ከነብያችን (ሰ•ዐ•ወ) ዘንድ ቃል ወደ ተገባላቸው አኼራ አለፉ።

የAthamina, Khalil, "አቡ ኡበይዳ ኢብን አል-ጀራህ" ከሚለው መፅሀፍ የተወሰደ

ከሁሉም በላይ አላህ አዋቂ ነው።
ውበታቸውን በአኽላቃቸው የሚያበለሹ እና
ውበታቸው አኽላቃቸው የሆኑ ሰዎች አሉ።ቆንጆ የሚያደርግህ መልክህ ወይም አለባበስህ ሳይሆን...በውስጥህ ያለው አኽላቅክ/ስብዕናህ ነው።
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
۞ إِنَّ اللَّهَ لَا يَسْتَحْيِي أَن يَضْرِبَ مَثَلًا مَّا بَعُوضَةً فَمَا فَوْقَهَا ۚ

አላህ ማንኛውንም ነገር ትንኝንም ኾነ (በትንሽነት ወይም በትልቅነት) ከበላይዋ የኾነንም ምሳሌ ለማድረግ አያፍርም፡፡
ሁሉም ስብራቶች የነገራችን መጨረሻ አይደሉም ...አንዳንድ ስብራቶች ለአድስ ሂወት ብስራቶች ናቸዉ።
'ዱዓ አርግልኝ' አልኩት
'ምን ሆንክ?' አለኝ ።
'ምንም ካልሆንኩ ዱዓ አታደርግልኝም?' ማለት ነው ? አልኩት።
'እሺ በቃ' አለኝ ።

አዎ ምንም ሳይሆኑም ዱዓ ይደረጋል ፣ ያስፈልጋልም።

እንዲህም ሆኖ
ምንም እንኳ እንደጉዳዩ ባለቤት ጉዳዩን ለአምላኩ የሚናገር የሌለ መሆኑን ባውቅም፤ ከራሴ እጅ ይልቅ በሌሎች እጅ የሚደረግልኝን ዱዓ እመርጣለሁ ።

#እጄ #በእጅጉ #ቆሽሿል

ወንድም እህቶች ሆይ ይህን ደካማ ባርያ በዱዓችሁ አስታውሱት።


የቴሌግራም ቻናሌን በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
@ https://t.me/Xuqal
«የፈጠርናችሁ ለከንቱ መኾኑን እናንተም ወደኛ የማትመለሱ መኾናችሁን ጠረጠራችሁን»
سورة المؤمنون
አንድ ቀን ሰይዳችን ረሱል ﷺ ከእንቅልፋቸው ደስ ብሏቸው ተነሱ "ምን አስደሰተሁ አንቱ የአላህ መልእክተኛ" ብላ ጠየቀቻቸው ባለቤታቸው አዒሻ ረ.ዓንሀ እሳቸውም "አንድ ሰው ሲራጥ ላይ ሲንደፋደፍ በህልሜ አየሁት ከዚያ ግን በኔ ላይ ያወረዳት ሰለዋት ደግፋ ሲራጥን አሻገረችው ይህ ነው ያስደሰተኝ" አሉ ሀቢቢ 🥹

فداك أبي و أمي و روحي يا رسول الله
اللهم أني أسألك أن تجمعنا برسول الله في الجنه
فنحن أمته نحبه كما يحبنا و نفديه بأرواحنا و بكل ما نملك
يارب صلِّ وسلم وزد وبارك على الحبيب المصطفى محمد صل الله عليه وسلّم تسليما كثيراً 💚 صلى الله عليه وسلم💚
የቴሌግራም ቻናሌን በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
@ https://t.me/Xuqal