Bilaluna Edris
528 subscribers
3.3K photos
266 videos
46 files
2.24K links
♡_ወደ መልካም ነገር ያመላከተ ሰው የሰራ ሰውን አጅር ያህል ያገኛል"(አመላካች የሰሪውን ምንዳ ያገኛል)(ﷺ)

« ከናንተም ወደ በጎ ነገር የሚጠሩ ፣ በመልካም ስራም የሚያዙ ከክፉ ነገርም የሚከለክሉ ሕዝቦች ይኑሩ» ﷻ
                 ቁርኣን[ 3:104 ]


መወያያ ግሩፓችን ☞ https://t.me/+1qmNqy265XoyNGY0
Download Telegram
ሠው ለሰው ደራሽ ጋሻ ከለላ
መሆን ካልቻለ የዋርካ ጥላ
ለሥጋ ሐሴት ሰርክ እየለፉ
ነፍስ አዝሎ መኖር ምንድነው ትርፉ!!

ጥር 19/2016 በአፋረ በጦርነቱ የተጎዱ ወገኖቻችን ለመልሶ ለመቋቋም ልዩ ልዩ ፕሮጀክት ይፋ የሚሆኑበት ቀን ነው። የፊታችን እሁድ በአፋር ሰመራ ብሔር ብሔረሰቦች አዳራሽ ጥር 19/2016 ለትልቅ አለማ በተዘጋጀው ፕሮግራም ላይ አብረን እንታደም።

#ሒራ_በጎ_አድራጎት_ድርጅት
#ሠመራ_ጥር_19
#በብሔር_ብሔረሰቦች_አዳራሽ
#የማይቀርበት

" ሁሉም ሠው በጎ ነው!!!!!

https://t.me/Xuqal 
https://ummalife.com/BilalunaEdris1
ሰሀባዎች ረሱልን ሰዐወ ከመሀል አድርገው የሚናገሩትን በተመስጦ በማዳመጥ ላይ ናቸው፦‹‹የቂያማ ለት መጀመርያ ሱጁድ ለማድረግ እሚፈቀድልኝ ለኔ ነው።›› በማለት ወደ መጪው ዘመን በምናብ አከነፏቸው።

ረሱል ሰዐወ ንግግራቸውን ቀጥለዋል፦‹‹ፍጥረት ሱጁድ ባደረገ ግዜም የዝያን ለት ራሴን ቀና እንዳደርግ ቅድምያ ለኔ ነውም እሚፈቀድልኝ።

ሱጁድ ካደረግኩበት ስፍራ ራሴን ቀና ሳደርግ እፊት ለፊቴ የተለያዩ ህልቆ መሳፍርት ህዝቦችን እመለከታለሁ። ከነዝያ ህዝቦች መካከልም ኡመቶቼን ለይቼ አውቃቸዋለሁ።

እዝያው ከቆምኩበት ሆኜ ኋላዬን ስመለከት በህዝብ ከተሞላው አድማስ ውስጥ የኔን ኡመቶች እያየሁ እለያቸዋለሁ።  ግራ ቀኜንም ስመለከት ከህዝቦች  መሀል ፍንትው ብላችሁ ትታዩኛላችሁ።››

ይህንን ንግግር ሲያዳምጡ ከነበሩ ስሀባዎች መካከል አንዱ ብድግ ብሎ፦‹‹ያ ረሱለሏህ! ከኑሕ ጀምሮ እስከ አሁን ድረሱ የተፈጠሩ ህዝቦች በዝያ ቦታ ላይ ተበትነው ሳለ በዝያ ሁሉ የህዝብ ብዛት ኡመትዎን እንዴት ነው እሚለይዋቸው?›› ሲል ጠየቀ።

‹‹ኡመቶቼን አውቃቸዋለሁ፤ እፊቶቻቸው እና እጆቻቸው ላይ እሚስተዋለው የዉዱእ ምልክት ጌጣቸው ነው፣ ከነሱ ሌላ በዚህ ያጌጠ ኡመት የለም።

ኡመቶቼን አውቃቸዋለሁ፤ መፅሐፎቻቸውን በቀኝ እጆቻቸው ይዘዋል፣ ኡመቴቼን አውቃቸዋለሁ እፊት ለፊቶቻቸው ላይ ዝርዮቻቸውም ይገኛሉ ››
ሲሉ መለሱለት።

ጌታችን ሆይ! በነብይህ የምንታወቅ ህዝቦች አድርገን🤲

https://t.me/Xuqal 
https://ummalife.com/BilalunaEdris1
ለ እሁድ ጥር 19/2016 በውቢቷ ሰመራ ቀጠሮ የተያዘለት የ #ከፍታ_ጉዞ ✌️ ታላቅ የሙሀደራ ፕሮግራም ድግስ የዋዜማ ፕሮግራም ጥር 18/2016 (ቅዳሜ) እለት በእደል መግሪብ ወል ኢሻ ተዘጋጅቷል።

➛ በ ሠመራ ሀጂ ሰአድ (ሰልሀዲን አል-አዩቢ) መስጂድ በ Engr/Ustaz Bedru Hussein - በድሩ ሁሴን

➛ በ ሎጊያ አቡዘር መስጂድ በ Ustaz Abubeker Ahmed/ ኡስታዝ አቡበከር አህመድ.

➛ በ ዱብቲ ሰላም መስጂድ በ Ustaz Yassin Nuru / ياسين نورو ......

በይነል መግሪብ ወል ኢሻ ተዘጋጅቷል። ሁሉም ሰው ይታደም ዘንድ ተጋብዟል።

https://t.me/Xuqal 
https://ummalife.com/BilalunaEdris1
#Breaking
የማእከላዊ ላቲን አሜሪካዊቷ ሃገር #ኒካራጓ🇳🇮 ደቡብ አፍሪካ በእስራኤል ላይ ፍርድ ቤት ቀርቦ በነበረው የዘር ማጥፋት ወንጀል ክስ ላይ ለመሳተፍ ለአለም አቀፍ ፍርድ ቤት ጥያቄ ማቅረቧን አስታወቀች።
መንግስት በመግለጫው ላይ “ኒካራጓ በጋዛ ሰርጥ የተባበሩት መንግስታት የዘር ማጥፋት ስምምነትን በመጣስ ደቡብ አፍሪካ በእስራኤል ላይ ባቀረበችው የዘር ማጥፋት ክስ ውስጥ እንዲትካተት ለአለም አቀፍ የፍትህ ፍርድ ቤት አመልክታለች!”ብሏል።
በማስስከተልም ኒካራጓ ከፍርድ ቤት ሊሰጡ  ሚችሉት የህግ ውጤቶች ሁሉ አካል መሆን ትፈልጋለች፤እናም #የዘር_ማጥፋት ወንጀልን ለመከላከል ያለብንን #ግዴታ ለመወጣት እና የዘር ማጥፋት ወንጀል የፈጸሙትን #ለመቅጣት የበኩሏን አስተዋፅኦ ለማድረግ ትፈልጋለች።”ይላል።
መግለጫው በተጨማሪም #ኒካራጓ ጥያቄዋ ተቀባይነት ካገኘ በጠቅላላው የክስ ሂደት ውስጥ እንደ ሀገር ጣልቃ ለመግባት እንደምትፈልግ ለአለም አቀፍ የፍትህ ፍርድ ቤት ማሳወቋን ገልጿል።  “ኒካራጓ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ እንደገለጸው፣ የእስራኤል ድርጊት የዘር ማጥፋት ስምምነትን ህግጋት እንደሚጥስ ያምናል” በማለት አብራርተዋል በመግለጫቸው።
መግለጫው አክሎም “የእስራኤል ወታደራዊ ጥቃት በፍልስጤም ህዝብ ላይ የሚደርሰውን ጥቃት #በአስቸኳይ እንዲያቆም የእስራኤል ከፍተኛ ባለስልጣናት በፍልስጤም ህዝብ ላይ የሚሰነዝሩት የዘር ማጥፋት ድርጊት እና የእስራኤል ከፍተኛ ባለስልጣናት በፍልስጤም ህዝብ ላይ የሰጡት ኢሰብአዊ መግለጫዎችም አመላካች ናቸው” ብሏል።
በጃንዋሪ 11, የአለም አቀፍ የፍትህ ፍርድ ቤት ችሎት ደቡብ አፍሪካ በጋዛ ሰርጥ "የዘር ማጥፋት" ወንጀል በእስራኤል ላይ ባቀረበችው ክስ የተጀመረ ሲሆን፣
ባለ 84 ገፆች ማስታወሻ ላይ ጠበቆቹ እስራኤል "በጋዛ ውስጥ የምታደርገውን ወታደራዊ እንቅስቃሴ በአስቸኳይ እንድታቆም" ዳኞች እንዲያዝዙ አሳስበዋል።
ምንጭ፡RT

ለወቅታዊ ሃገር አቀፍና አለምአቀፍ መረጃዎች ይሄን የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ!👇
https://t.me/Xuqal 
https://ummalife.com/BilalunaEdris1
እስራኤል ለዓለም አቀፉ ፍርድ ቤት የ"ዘር ማጥፋት" ክስ ባቀረበችበት ወቅት በደቡብ አፍሪካ ላይ የመጀመሪያውን "የቅጣት" እርምጃ አስታውቃለች።
የእስራኤል ቻናል 12 አርብ እንደዘገበው የእስራኤል አየር መንገድ ኤልአል ወደ ደቡብ አፍሪካ ትልቋ ከተማ ጆሃንስበርግ በሚያዝያ1 የሚያደርገውን የበረራ መስመር ይሰርዛል።
RT እንደዘገበው! በሷ ቤት መአቀብ መጣሏኮ ነው ደቡብ አፍሪካ ጉድ አደረኳት ማለቷኮ ነው¡
😂😂😂

ለወቅታዊ ሃገር አቀፍና አለምአቀፍ መረጃዎች ይሄን የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ!👇
https://t.me/Xuqal 
https://ummalife.com/BilalunaEdris1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በደቡብ አፍሪካ በእስራኤል ላይ የቀረበው “የዘር ማጥፋት” ክስ ICJ ውሳኔ ነገ የሰወሰናል ከወዲሁ ነፍልስጤም ደጋፊ በሪአይኤ ኖቮስቲ   በሄግ ባቡር ጣቢያ ያላባራዉ የእስራኤል ድብደባ  ተቃውመዋል ዛሬ ፍትህ ይገኝ እያሉ ነዉ።
የእስራኤል ሜጀር ጄኔራል (ሬቲ.) ናምሩድ ሸፈር፡-

" ናታንያሁ ጦርነቱ እንዲያበቃ ስለማይፈልግ የእስረኞች ልውውጥ ውል ለሌላ ጊዜ አራዝሟል። ይህ ማለት እስረኞችን በሃማስ ዋሻዎች ለማስፈታት እና የወታደሮቻችንን ህይወት በማጥፋት ስልጣኑን ለማስቀጠል ስሜቱ ነዉ

ለወቅታዊ ሃገር አቀፍና አለምአቀፍ መረጃዎች ይሄን የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ!👇
https://t.me/Xuqal 
https://ummalife.com/BilalunaEdris1
ዓለም አቀፉ የፍትህ ፍርድ ቤት ደቡብ አፍሪካ በእስራኤል ላይ ያቀረበችውን የዘር ማጥፋት ወንጀል ክስ ላይ የአስቸኳይ ጊዜ ርምጃ ላይ ዛሬ ከደቂቃዎች በኋላ ጀምሮ ብይን ይሰጣል።

ፍርድ ቤቱ እስራኤል የዘር ማጥፋት እየፈፀመች ነው ወይ የሚለውን ዋና ጥያቄ ዛሬ ይመለከታል ተብሎ አይጠበቅም ነገር ግን እስራኤል በጋዛ ሰርጥ የምታደርገውን ወታደራዊ ዘመቻ እንድታቆም መፍረድን ጨምሮ ደቡብ አፍሪካ የጠየቀችውን ጊዜያዊ እርምጃዎችን ይመለከታል።

የፍርድ ቤቱን ውሎ ከጁሙዓ በኋላ እየተከታተልኩ አቀርብላችኋለሁ ኢንሻ-አላህ

ለወቅታዊ ሃገር አቀፍና አለምአቀፍ መረጃዎች ይሄን የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ!👇
https://t.me/Xuqal 
https://ummalife.com/BilalunaEdris1
Bilaluna Edris
ዓለም አቀፉ የፍትህ ፍርድ ቤት ደቡብ አፍሪካ በእስራኤል ላይ ያቀረበችውን የዘር ማጥፋት ወንጀል ክስ ላይ የአስቸኳይ ጊዜ ርምጃ ላይ ዛሬ ከደቂቃዎች በኋላ ጀምሮ ብይን ይሰጣል። ፍርድ ቤቱ እስራኤል የዘር ማጥፋት እየፈፀመች ነው ወይ የሚለውን ዋና ጥያቄ ዛሬ ይመለከታል ተብሎ አይጠበቅም ነገር ግን እስራኤል በጋዛ ሰርጥ የምታደርገውን ወታደራዊ ዘመቻ እንድታቆም መፍረድን ጨምሮ ደቡብ አፍሪካ የጠየቀችውን…
ተጨማሪ

ዓለም አቀፉ የፍትህ ፍርድ ቤት ደቡብ አፍሪካ በእስራኤል ላይ ያቀረበችውን የዘር ማጥፋት ወንጀል ክስ ላይ አስቸኳይ እርምጃዎች ላይ ልክ 8፡00 ሲል ብይን መስጠት ይጀምራል፡፡

ጊዜያዊ እርምጃዎቹ እስራኤል በጋዛ ሰርጥ የምታደርገውን ወታደራዊ ዘመቻ እንድታቆም ማዘዝን ያጠቃልላል አንዳንድ ተንታኞች እንደሚሉት በፍርድ ቤቱ ላይ በበዛው ጫና ምክንያት ጦርነቱ እንዲቆም ሳይሆን ሰብአዊ እርዳታ በበቂ ሁኔታ እንዲገባ እስራል እንድትፈቅድ ብይን ሊሠጥ ይችላል።

ለወቅታዊ ሃገር አቀፍና አለምአቀፍ መረጃዎች ይሄን የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ!👇
https://t.me/Xuqal 
https://ummalife.com/BilalunaEdris1
ሰበር

ሮይተርስ እንደዘገበው ጀርመን የዓለም አቀፉ የፍትህ ፍርድ ቤት (ICJ) ውሳኔን እንደምታከብር ተናግራለች።

ጀርመን ምን አስባ ነው ዛሬ ፀባይ አበዛች

ለወቅታዊ ሃገር አቀፍና አለምአቀፍ መረጃዎች ይሄን የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ!👇
https://t.me/Xuqal 
https://ummalife.com/BilalunaEdris1
ሰበር

የብሪታንያ የባህር ንግድ ስራ ድርጅት (UKMTO) ከየመን በኤደን ደቡባዊ ምዕራብ 60 ናቲካል ማይል ርቀት ላይ በምትገኝ መርከብ ላይ ጥቃት መፈጸሙን ዘግቧል።

ድፍድፍ ዘይትና የነዳጅ ምርቶችን ከጫነ መርከብ በአንድ ማይል ርቀት ላይ ፍንዳታ መኖሩም ተነግሯል።

ለወቅታዊ ሃገር አቀፍና አለምአቀፍ መረጃዎች ይሄን የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ!👇
https://t.me/Xuqal 
https://ummalife.com/BilalunaEdris1
አል-ቃሳም ብርጌድም ፍርድ እየሰጠ ነው!

አል-ቃሳም ብርጌድ ተዋጊዎቹ በደቡብ ምዕራብ ጋዛ በሚገኘው ሼክ አጅሊን አካባቢ 8 ወታደሮችን ባቀፈው የጽዮናውያን እግረኛ ጦር ጋር በመዋጋት ላይ ሲሆኑ የጠላት ወታደሮችን ሙት እና ቁስለኛ ማድረግ መቻላቸውን አስታውቋል።

ለወቅታዊ ሃገር አቀፍና አለምአቀፍ መረጃዎች ይሄን የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ!👇
https://t.me/Xuqal 
https://ummalife.com/BilalunaEdris1
ፍርድ ቤቱ ጉዳዩን ማየት ጀምሯል!

የእለቱ መሪ ዳኛ ዶንጉዌ ንግግሯን የጀመረችው እ.ኤ.አ ኦክቶበር 7 በእስራኤል ውስጥ ሐማስ የፈፀመውን ጥቃት በመጥቀስ ነው።

ቀጥላም እስራኤል በጋዛ ላይ በመሬት፣ በአየር እና በባህር መጠነ ሰፊ ወታደራዊ ዘመቻ መክፈቷን፣ ይህም ከፍተኛ የሲቪሎች ጉዳት ማድረሱን፣ የሲቪል መሰረተ ልማቶችን ማውደሙን እና አብዛኛው የጋዛ ህዝብ መፈናቀሉን ገልጻለች።

ፍርድ ቤቱ በቀጠናው እየደረሰ ያለው የሰው ልጆች ሰቆቃ ምን ያህል እንደሆነ ጠንቅቆ እንደሚያውቅና ቀጣይነት ያለው የህይወት መጥፋትና የሰው ሰቆቃ በእጅጉ እንዳሳሰበው ተናግራለች።

ከፍርድ ቤቱ 17 ዳኞች መካከል 16 ዳኞች በችሎቱ ውስጥ ይገኛሉ።

"በሁለቱም የውይይት እና የመጨረሻ ድምጽ ላይ በትክክል የተሳተፈው ዳኛ ሮቢንሰን ዛሬ መገኘት ያልቻለበት ምክንያት ተነግሮኛል" ሲል ዳኛ ዶንጉዌ ተናግሯል።

ዳኛ ዶንጉዌ ፍርድ ቤቱ በጉዳዩ ላይ አስቸኳይ እርምጃዎችን የመወሰን ስልጣን እንዳለው ተናግረዋል ።
ፍርድ ቤቱ እስራኤል በጋዛ የዘር ማጥፋት ወንጀል የተከሰሰችበትን ክስ አይተወውም ብለዋል ሰብሳቢው ዳኛ።

ለወቅታዊ ሃገር አቀፍና አለምአቀፍ መረጃዎች ይሄን የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ!👇
https://t.me/Xuqal 
https://ummalife.com/BilalunaEdris1