Bilaluna Edris
529 subscribers
3.3K photos
267 videos
46 files
2.24K links
♡_ወደ መልካም ነገር ያመላከተ ሰው የሰራ ሰውን አጅር ያህል ያገኛል"(አመላካች የሰሪውን ምንዳ ያገኛል)(ﷺ)

« ከናንተም ወደ በጎ ነገር የሚጠሩ ፣ በመልካም ስራም የሚያዙ ከክፉ ነገርም የሚከለክሉ ሕዝቦች ይኑሩ» ﷻ
                 ቁርኣን[ 3:104 ]


መወያያ ግሩፓችን ☞ https://t.me/+1qmNqy265XoyNGY0
Download Telegram
" የቁርኣን ሰዎች ልዩ የአላህ ቤተሰቦች ናቸው "

ረሱልﷺ
ሂዝቦላህ ዛሬ ከባድ ጥቃት እየፈፀመ ነው!

የኢስላማዊ ተቃውሞው ተዋጊዎች ቅዳሜ ዛሬ ከጠዋቱ 3፡40 ላይ “መቱላ” ቦታ ላይ ተበገቢውን መሳሪያ በቀጥታ ጥቃት ሰንዝረዋል።

የኢስላማዊ ተቃውሞው ተቃውሞ ተዋጊዎች ዛሬ ከጠዋቱ 3፡55 ላይ በሁኒን ጦር ሰፈር አቅራቢያ የተሰበሰበውን የጠላት “እስራኤል” እግረኛ ሃይል ላይ በተገቢው መሳሪያ በቀጥታ መምታት ችለዋል።

የኢስላማዊ ተቃውሞው ተዋጊዎች፣ ዛሬ ማምሻውን 9፡40 ላይ ባያድ ብሊዳ ቦታን በሮኬት መሳሪያ ኢላማ በማድረግ ቀጥተኛ ጥቃት አደርሰዋል።

https://t.me/Xuqal 
https://ummalife.com/BilalunaEdris1
እድሳት ላይ የነበረው ኑር (በኒን) መስጂድ እድሳቱ ተጠናቋል። መስጂዱ በዚ መልኩ አዲስ ውብ እና ማራኪ እይታን ተላብሷል።

https://t.me/Xuqal 
https://ummalife.com/BilalunaEdris1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ጥር 19/2016 አ.ል ሰመራ በ ብሔር ብሔረሰቦች አዳራሽአይቀርም
#ያለንን_ብናውቅ_የጎደለን_የለም!
                        
ሁለት የሚዋደዱ ጓደኛሞች ጉዞ ላይ ሳሉ አንደኛው ያማረ ቪላ ቤቶችን ያይና ለጓደኛው እንዲህ አለው።

«ፈጣሪ ይህን ሁሉ ሀብት ለእነዚህ ሰዎች ሲያድል እኛ የት ነበርን?»

ጓደኛውም አጠገቡ ነበረና ና ብሎ ወደ ሆስፒታል ይዞት ሔዶ እንዲህ አለው።

«ለእነዚህ ሰዎች ሁሉ ፈጣሪ በሽታን ሲያድል እኛ የት ነበርን?»

"ያለንን ብናውቅ የጎደለን የለም!!"
"ምንግዜም ባለን ነገር እናመሥግን።"
الحمدلله ثم الحمدلله 🙏

https://t.me/Xuqal 
https://ummalife.com/BilalunaEdris1
#BREAKING
ከሸይኽ አብዱ ያሲን ግድያ ጋር ተያይዞ የመጀመሪያው ተጠርጣሪ ነው የተባለው የባለቤታቸው ልጅ የሆነው መሀመድ ሽኩር እየተፈለገ ነው ።

መሀመድ ሽኩር ይኖርበት ከነበረው መኖሪያ ቤት መሰወሩ ተነግሮዋል ያያችሁት በአከባቢ ለሚገኝ ፖሊስ ጥቆማ ስጡ!

https://t.me/Xuqal 
https://ummalife.com/BilalunaEdris1
አባቴ ሆይ!አንተ ታጋሽ ነህ! ስለዚህ መቸም ተስፋ አትቁረጥ! ፈፅሞ ከአሏህ ምህረት ተስፋ አትቁረጥ!
አሏህ ለታጋሽነትህ መልካም ጀዛእ እንደሚሰጥህ እርግጠኛ ሁን!”
😔😔

ከወር በፊት ባለቤቱን እና ብዙ ቤተሰቦቹን በወራሪዋ የቦንብ ጥቃት በሞት ያጣው እና ከ3ሳምንታት በፊት እርሱም በስራ ላይ እያለ ጉዳት ደርሶበት ስራውን በትግስት የቀጠለው ታዋቂው የአልጀዚራ ጋዜጠኛ #ዋኢል_አልዱህዱህ ዛሬ ደግሞ አብሮት በአልጀዚራ ቻናል ላይ በጋዜጠኝነት ይሰራ የነበረውን ልጁን ጋዜጠኛ #ሃምዛን በሞት ያጣ ሲሆን ሀምዛ ሸሂድ ከመሆኑ በፊት ለአባቱ ያስተላለፈው የመጨረሻ መልእክት!!

https://t.me/Xuqal 
https://ummalife.com/BilalunaEdris1
የ ሂዝቦላህ መግለጫ
-
በጋዛ ሰርጥ ውስጥ ያለውን ጽኑ የፍልስጤም ሕዝብ ለመደገፍ እና ያላቸውን ክቡር ተቃውሞ ለመደገፍ, እስላማዊ ተቃውሞ ሀማስ ያለውን አቋም እና የሊባኖስ-ፍልስጤም ድንበር ላይ "በርካታ ገድሎችን ተሰርቷል

- የምስራቃዊ ዘርፍ የነበረው ሁኔታ

1- ምሽት 3፡40 ላይ "መቱላ" የተባለውን ቦታ በተገቢው የጦር መሳሪያ ኢላማ በማድረግ እና ቀጥታ በወራሪዋ ላይ ጉዳት መድረስ ችለናል ተብለዋል ።

2-ምሽት 3፡55 በሁኒን ሰፈር አቅራቢያ በተሰበሰበው የ"እስራኤል" ጦር እግረኛ ቡድን ላይ ተገቢውን መሳሪያ በመያዝ  ደምስሰናቸዋል ብለዋል ።

3- ምሽት 6፡40 ባያድ-ብሊዳ ቦታን በሮኬት መሳሪያዎች ኢላማ በማድረግ እና ቀጥታ መምታቱ በወራሪዋ ጉዳት አድርሰዋል ።

4- 17፡15 ላይ በመናራ ቦታ አቅራቢያ በተሰበሰቡት የ"እስራኤል" ጦር ወታደሮች ላይ ተገቢውን የጦር መሳሪያ በማነጣጠር እና ቀጥተኛ ጥቃትን ማሳካት።

- ቀምዕራባዊ  ግንባር

1-ምሽት 1፡50 ላይ የሜሮን"ን  በተያዘች ፍልስጤም (ጀባል አል-ጃርማቅ) በሰሜን በኩል የአስተዳደር፣ የክትትል እና የአየር መቆጣጠሪያ ብቸኛ ማእከል ሆኖ የሚያገለግለውን አየርን የሚመለከት በክልሉ (ሶሪያ፣ ሊባኖስ፣ ቱርክ፣ ቆጵሮስ፣ ወዘተ) በ62 ሚሳኤሎች ጥቃት አድርሰዋል የሀማሱ መሪ፣ ታላቁ መሪ ሼክ ሳሌህ አል አሩሪን እና ሰማዕታቸውን ለመግደል ወንጀል የመጀመሪያ ምላሽ ሆኖ የተረጋገጠ ቀጥተኛ ድብደባ ፈፅመናል ብለዋል ።

2- ምሽት 5:40 በ"አቪቪም" የ"እስራኤል" ጦር ወታደሮችን በተሰበሰበበት ተገቢ መሳሪያ በማነጣጠር እና ቀጥተኛ ጥቃትን በማድረስ ማሳካት ችለናል ይላል በመግለጫው ።

3- 6፡05 ላይ ጃል አል-አላም ቦታ አጠገብ በተሰበሰቡ የ"እስራኤል" ጦር ወታደሮች ደምስሰናል ብለዋል ሄዝቦላህ ከበፊቱ የተሻለ ሀይሉን እየጨመረ ነዉ ።

https://t.me/Xuqal 
https://ummalife.com/BilalunaEdris1
ሀማስ መግለጫ አዉጥቷል

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው።

የፕሬስ መግለጫ

በአልዳህዱህ እና በሶራያ ጋዜጠኞች ላይ ወራሪዋ እስራኤል በማነጣጠር ሆን ተብሎ የተፈፀመ የጽዮናውያን የጦር ወንጀል ሲሆን ጋዜጠኞች እውነትን እንዳይዘግቡ እና ወንጀላቸውን እንዳይዘግቡ ለማድረግ ነው ይላል

በጋዛ ሰርጥ ወንጀለኛው ጽዮናዊት የፍልስጤም ጋዜጠኞች ላይ ያደረሰው ሆን ተብሎ የተፈፀመበት ኢላማ፣ የቅርብ ጊዜውም በሚከተሉት ኢላማዎች ላይ ነው።

ሰማዕቱ ጋዜጠኛ ሃምዛ አልዳህዱህ የጋዜጠኛ ዋኤል አልዳህዱህ ልጅ

እና ሰማዕቱ ጋዜጠኛ ሙስጠፋ ቱራያ

ጋዜጠኞች እውነትን እንዳይዘግቡ እና በጋዛ ሰርጥ ጽዮናውያን በሰው ልጆች ላይ ያደረሱትን ዘግናኝ ወንጀሎች እንዳይዘግቡ ለማድረግ ያለመ ሽብርተኝነት እና የጽዮናውያን የጦር ወንጀል ነዉ።

በጋዜጠኞች ላይ በደረሰው አሰቃቂ ወረራ ጠላት እስካሁን 109 ጋዜጠኞችን ከገደለበት እና በሰላማዊ ዜጎች፣ ህጻናትና ሴቶች ላይ እየደረሰ ያለውን አሰቃቂ ግድያ ከግምት ውስጥ በማስገባት አለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ተቋማት በህዝባችን ላይ የሚፈፀሙትን ወንጀሎች ለህግ እንዲያቀርቡልን እንጠይቃለን። ይህ አጭበርባሪ አካል።

ለጋዜጠኛ ዋኤል አልዳህዱህ እና ለቤተሰቦቹ፣ ለጋዜጠኛ ሙስጠፋ ቱራያ ቤተሰቦች፣ ለሞቱት ሰማዕታት ጋዜጠኞች ቤተሰቦች እና ለታጋቹ የፍልስጤም ህዝባችን አል ሙራቢት የተሰማንን ጥልቅ ሀዘንና ሀዘን እየገለፅን መፅናናትን እንመኛለን። እኛ የአላህ ነን ወደርሱም ተመላሾች ነን።

የእስልምና ተቃውሞ ንቅናቄ - ሃማስ

እሑድ፡ 25 ጁማዳ አል-አኺራህ 1445 ሂጅራ
07 ጃንዋሪ 2024 ዓ.ም

https://t.me/Xuqal 
https://ummalife.com/BilalunaEdris1
ከኪታብ ጋር ኖረው ከኪታብ ጋር ያረጁ ባለመነፅሩ ሸይኽ ይሏቸዋል። በእርግጥም አንደበተ ርቱዕ ናቸው ሲያስቀሩ ፈትፍተው የሚያጎርሱ። ከመስጂድ ቤት ከቤት መስጂድ እንጂ የማይታዩ ኸጢብም ይሏቸዋል በቅርበት የሚያውቋቸው ሁሉ።

ዒልምን ለማድረስ የሚተጉ! ኡማውን ለማስተማር እንቅልፍ ያጡ የሕይወት አቅጣጫን አመላካች ዛሂድና ዓቢድ! የአስኮ በድር መስጅድ ኢማም ሸይኽ አብዱ ያሲን!

ትላንት ከዒሻ ሰላት በኋላ ማንነቱ ባልታወቀ ግለሰብ በተተኮሰባቸው ጥይት ተመተው ከመሬቱ ወደቁ። ህይወታቸውን ለማትረፍ ወደ አቤት ሆስፒታል ቢወሰዱም ከሰዓታት በኋላ ይህን አለም ተሰናብተው ወደ አኼራ ተሸጋገሩ።

አላህ ቀብራቸውን ኑር ማረፊያቸውንም ጀነተል ፊርደውስ ያድርግላቸው!

ዛሬ ከዙሑር ሰላት በኋላ እዚያው በድር መስጂድ ሰላተል ጀናዛ ተሰግዶባቸው ኮልፌ ቀብራቸው ተከናውኗል።

https://t.me/Xuqal 
https://ummalife.com/BilalunaEdris1
ኪታባቸውን ተንተርሰው ለልጃቸው የገዙት ዳቦ በደማቸው ጨቅየቶ ዱንያን የተሰናበቱት ሸይኽ አብዱ ያሲን!

ሳኡዲ በነበሩበት ወቅት የሸህ ዑሰይሚን ደረሳ፣ ሱደይስን ተጅሪድ ያቀሩ ታላቅ ዓሊም ናቸው። ወደ ሀገር ከተመለሱ ወዲህ አፍንጮ በር በሚገኘው አቅሷ መስጅድ ያስቀሩ፣ በኋላም የአስኮ አዲስ ሰፈር በድር መስጂድ ኸጢብና ሸይኽ ነበሩ።

ትናንት ምሽት ኪታባቸውን ተንተርሰው የገዙት ዳቦ በደም ጨቅይቶ ከመሬቱ ወደቁ። ከመግሪብ እስከ ኢሻ ተፍሲር ሲያቀሩ ያውም ሱረቱ ዙመርን ሲያብራሩ አምሽተው ሁሌም እንደሚያደርጉት መስጂድ በር ላይ ሲዋክ የሚሸጠውን አይነ አዕማውን አረቡን ለመሸት ከመስጂዱ በር ላይ ቆሙ። አረቡ ሁሌም "ኡስታዝ  አይጠብቁኝ ይሂዱ" ይላቸዋል። እሳቸው ግን እሺ አይሉም። ከኢሻ በኋላ ለአረቡ ምርኩዝ ናቸው። እንጀራ አይበላም ለሚሉት ልጃቸው ዳቦ ገዝተው አረቡን ቤቱ እየመሩ አስገብተው ነው ወደቤታቸው የሚገቡት።

ትናንትም ከአረቡ ጋር ወደቤታቸው በማቅናት ላይ ሳሉ መታጠፊያ አሳቻ ቦታ ላይ ከቅርብ ርቀት በተተኮሰ ሽጉጥ ከጀርባቸው በኩል ተመተው ሲወድቁ አረቡም ራሱን ስቶ ከመሬቱ ተዘረረ። በአካባቢው መብራት ጠፍቶ ስለነበር ማንነቱ ያልታወቀው ገዳይ የልቡን አድርሶ ከቦታው ተሰወረ።

እዳ ያስጭንቃቸዋል በሽማግሌዎችም የተሰጣቸው ጊዜም አጭር በመሆኑ ያሳስባቸው ነበር። የተወሰነውን ገንዘብ ተበድረው ከፍለው ቀሪውን ለመክፈል ቤታቸውን ለመሸጥ እንዳሰቡ ነገር ግን የበድር መስጂድ ጀመዓዎች ቤቱ ከመሸጡ በፊት ትላንት ፈጅር ላይ ለመስጂዱ ጀመአ ዛሬ እሁድ ገቢ ለማሰባሰብ እቅድ ተይዞ ነበር። ግና የአላህ ውሳኔ ቀደመ። በቅርብ ጊዜ ወደ አኺራ ወደተሻገረችው ባለቤታቸው ጉርብትና ተጓዙ። አላህ ይዘንላቸው። 

ከቀብራቸው በፊት እዳ ለመክፈል እየተንቀሳቀሱ ያሉ ኮሚቴዎች አካውንት ከፍተው ሁሉም ሙስሊም እዳቸውን እንዲከፍል ጥሪ አቅርበዋል።

የአካውንት ስም:- ጀሚል ሁሴን ፣ ሲሩ ሀሰን እና አብዱ ዑስማን 
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ:- 1000592716309

via mahi mahisho

https://t.me/Xuqal 
https://ummalife.com/BilalunaEdris1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ጥር 19 በሠመራ ከተማ ብሔር ብሔረሰቦች አዳራሽ ታላቅ የዱአ ድግስ 👌 መቅረት ራሱ የማይቀርበት ሙሀደራ 👌
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ጥር 19 በሠመራ ከተማ ብሔር ብሔረሰቦች አዳራሽ ታላቅ የዱአ ድግስ 👌 መቅረት ራሱ የማይቀርበት ሙሀደራ 👌