Bilaluna Edris
549 subscribers
3.35K photos
276 videos
50 files
2.3K links
♡_ወደ መልካም ነገር ያመላከተ ሰው የሰራ ሰውን አጅር ያህል ያገኛል"(አመላካች የሰሪውን ምንዳ ያገኛል)(ﷺ)

« ከናንተም ወደ በጎ ነገር የሚጠሩ ፣ በመልካም ስራም የሚያዙ ከክፉ ነገርም የሚከለክሉ ሕዝቦች ይኑሩ» ﷻ
                 ቁርኣን[ 3:104 ]


መወያያ ግሩፓችን ☞ https://t.me/+1qmNqy265XoyNGY0
Download Telegram
“የትኛው ምድር ፣ የትኛው ልብና የትኛው ውሳኔ ለኛ የተሻለ እንደሆነ አናውቅም። ነገር ግን ምርጥ የሆነው አላህ ለኛ በመረጠው ነገር ውስጥ እንዳለ እርግጠኞች ነን። ”
ኢማም ሙተወሊ ሸዕራዊ
የሞሳድ ሃላፊ የነበረው ዳኒ ያቶም ከእሰራኤል ጋዜጣ ያድዖት አህረኖት ጋር ከቀናት በፊት ባደረገው ቀለ ምልልስ
"ምንድን ነው እየተፈጠረ ያለው? የሙሴ ፈጣሪ ረሳን ተወን ማለት ነው? ይህ እንዴት ሊሆን ቻለ። 170 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር አፍስሰን የሰራነው። የራሳችን ምርት የሆነችው በአለም ፊት ስንመካበት የከረምነው ሜርካፋ የምትሰኘው ታንክ የሃማስ ተዋጊዎች በቀላል መሳሪያ በአርቢጂ እንዳልነበረች አመድ ሲያደርጓት ማየት ለማመን ይቸግራል ከነሱ ጋር ሁኖ የሚዋጋ ነገርማ አለ አለዚያማ በፍፁም እነዚህን ታንኮቻችንን በቀላሉ ማቃጠል ከቶ አይቻልም። እነዚህ ሰዎች የተኮሱት ሁሉ መሬት ላይ አይወድቅም ያለ የሙሴና የሃሮን ፈጣሪማ ከድቶናል አበቃ ሌላ የምለው የለኝም"

https://t.me/Xuqal
https://ummalife.com/BilalunaEdris1
አሁን ከጋዛ ወደ ቴልአቪቭ የተተኮሰ ሮኬት ኢላማውን ጠብቆ እንዲህ ውድመት አድርሷል።

አላሁመ ዚድ ወሰዲድ። ጌታዬ ሆይ የሙጃሂዶቻችንን ተኩስ ኢላማውን የሚመታ አድርግላቸው ፅናትና ብርታቱንም ወፍቃቸው 🤲

https://t.me/Xuqal
https://ummalife.com/BilalunaEdris1
[| አንድ ሰው የሆነ ንግግርን ብዙም ሳይብራራለት(ትኩረት ሳይሰጣት) ይናገራል ፤ በዛች ንግግር ምክንያት በምስራቅ እና ምዕራብ መካከል የራቀ የሆነን ውርደት እሳት ውስጥ ይዋረዳል |] ረሱል - ﷺ
🛑 ታላቅ የምስራች
🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉

📌 https://onelink.to/quvuv3

በሀገራችን ፋና ወጊ የሆነውንና የመስገጃ ቦታዎችን የሚያመላክት መተግበሪያ(Application) ይፋ ሆነ!

አፕሊኬሽኑ "Musalla" የሚሰኝ ሲሆን ለአንድሮይድና ለ IPhone (IOS) ተጠቃሚያዎች የተዘጋጀና መተግበሪያው በአማርኛ፣ በአፋን ኦሮሞ፣ በአረብኛና በእንግሊዘኛ ቋንቋ አማራጮች መስራት የሚችል ነው።

🚩 አፕሊኬሽኑ ዋና ዋና መስጂዶችን ፣ በንግድ ማዕከላት እና በሆቴሎች ውስጥ የሚገኙ መስገጃ ቦታዎችን የት እንደሚገኙ ይጠቁማል

🚩 በመስገጃ ቦታዎቹ ውዱእ ማድረጊያ ቦታ መኖሩን እና አለመኖሩን ይገልፃል

🚩መስጂዶቹ የሴቶች መስገጃ ቦታ እንዳላቸው እና እንደሌላቸው ይገልፃል

🚩 ከተማው ውስጥ የሚገኙ የቀብር ቦታዎችን፣ የመጅሊስ ፅህፈት ቤቶችንና ቂብላ ይጠቁማል። እንዲሁም የመስጂዶችን አድራሻ በቪዲዮና በምስል ጭምር ማሳየት የሚችል አፕሊኬሽን ነው ይፋ የሆነው።

የፈጠራው ባለቤቶች በነሱ አቅም ማካተት የቻሏቸውን መስጂዶች ያሰገቡ ቢሆንም እርሰዎ ክፍለ አገርም ሆኑ አዲስ አበባ በየጉራንጉሩ ያሉ የሚያውቋቸውን መስጂዶች እና ተያያዥ መረጃዎች በአፕሊኬሽኑ ውስጥ ማስገባት እንዲችሉ ክፍት ተደርጓል። በጣም ደስ የሚለው ነገር ያልተካተቱ መስጂዶችን እርሰዎ ካስገቡ በኋላ አፕሊኬሽኑ ላይ ባስገቡት መስጂዶች ላይ ሰዎች ሲገለገሉ ለእርሰዎ ይኼን ያህል ሰው በመስጂዱ ሰግዷል የሚል ብዙ ምንዳ የሚያዝቅ መረጃ በየጊዜው ይልክልዎታል።

አፕሊኬሽኑን ከታች ባለው ሊንክ ገብታችሁ አውርዳችሁ መጠቀም የምትችሉ ሲሆን ሌሎች እንዲጠቀሙበትም ሼር በማድረግ እንድታጋሩ እንጠይቃለን።

የአፕሊኬሽን መገኛ ሊንክ:- https://onelink.to/quvuv3

የቲክቶክ አድራሻቸው 👉 https://t.ly/i8Tkc
የሙስሊሞች ምሽግ
>>>ነብዩ(ሰ.አ.ወ) ስለ >>ጁምአ ቀን
ታላቅነት ሲናገሩ
የጁምአ ቀን የቀኖች ሁሉ ንጉስ ነዉ እነዚህ
5ነገሮች የጁምአ
ቀን ተከስተዋል ብለዋል
>>1.አላህ አደምን የፈጠረዉ በጁምአ ቀን
ነዉ
>>2.አደም ከጀነት የወጡትም በጁምአ ቀን
ነዉ
>>3.አደም የሞተዉም በጁምአ ቀን ነዉ
>>4.ቂያማ የምትቆመዉ በጁምአ ቀንነዉ
>>5.በጁምአ ቀን የሆነች ሰአት አለች አንድ
የአላህ ባሪያ
አላህን የጠየቀዉን ነገር ይሰጠዋል ያችን ሰአት
ካገኛት,ሀራም
ነገር እስካልጠየቀ ድረስ አላህ ይቀበለዋል::
>>>በሌላ የሀዲስ ዘገባ አንድ ሰዉ ታጥቦ
ያለዉን ጥሩ ልብስ
ለብሶ ሽቶ ተቀብቶ ወደ መስጂድ ሄዶ ማንንም
አዛ ሳያደርግ
ኢማሙ ቁጥባ ሲያደርጉ ዝም ብሎ ከሰማ
ጁምአዉንም
ከሰገደ
አላህ ከባለፈዉ ጁምአ እስከ እስካሁኑ ጁምአ
ያለዉን ወንጀሉን
ያብስለታል
>>>በሌላ የሀዲስ ዘገባ የጁምአ እለት
በመጀመሪያዉ ሰአት
ወደ መስጂድ የገባ ግመል ሶደቃ እንዳደረገ
ይጻፍለታል
ከዚህ አርፍዶ የመጣ የቀንድ ከብት ሶደቃ
እንዳደረገ ይጻፍለታል
ከዚህ አርፍዶ የመጣ በግ/ፍየል ሶደቃ
እንዳደረገ ይጻፍለታል
ከዚህ አርፍዶ የመጣ ዶሮ ሶደቃ እንዳደረገ
ይጻፍለታል
ከዚህ አርፍዶ የመጣ እንቁላል ሶደቃ እንዳደረገ
ይጻፍለታል
ኢማሙ ሚንበር ላይ ሲወጡ የሚመዘገቡት
መላኢኮች
የኢማሙን ቁጥባ ለመስማት መስጂድ
ይገባሉ::
*ታድያ ይህን ሁሉ ጥቅም የሚያስገኘዉንና
ይሄን ሁሉ ቱሩፉት
የሚያስገኘዉን የጁምአን ሶላት በሙሉ ሸርጡ
ከሰገድን ከላይ
የተጠቀሱትን ጥቅሞች እናገኛለን......
[ ከእናንተ ውስጥ አንድኛችሁ ዱዓ በሚያደርግበት ጊዜ በዱዓ ላይ ይቁረጥ(ቆራጥ ይሁን) ፤ አላህ ሆይ! ከፈለክ ስጠኝ አይበል ፤ ምክንያቱም ለአላህ አስገዳጅ የለውምና ] ረሱል - ﷺ
#አልጀዚራ_ሰበር!
የእስራኤል ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን“የአሜሪካ ሰው አልባ አውሮፕላኖች በጋዛ ሰርጥ ላይ ለአንድ ሳምንት ያህል በሀማስ የተያዙትን ሰዎች ለማወቅ ሲበሩ ነበር!”ሲል አስታወቀ!!
ሀማስማ ጉድ ችሏል!

https://t.me/Xuqal
https://ummalife.com/BilalunaEdris1
የአልቃሳም ብርጌዶች ቃል አቀባይ አቡ ዑበይዳ ከተናገሩት ዋና ዋና ነገሮች፡-

- ሙጃሂዶቻችን በአስር ግንባሮች ከጽዮናውያን ጦር ጋር እየተፋለሙ ይገኛል።

- ታንኮችን አውድመናል የጦር መሪዎችን ማርከናል የበዙ የጠላት ወታደሮችን ገድለናል አቁስለናልም።

- ከጠላት ኋላ ተነስተን ከመከላከል ወደ ማጥቃት ተሸጋግረናል።

- ዛሬ ማምሻውን ከጋዛ ከተማ በስተሰሜንና በስተምዕራብ በኩል የመልሶ ማጥቃት ዘመቻ ከፍተን 6 ታንኮችንና ሁለት የሰው ኃይል አጓጓዥ መኪናዎችን አውድመናል።

- የሟቾች ቁጥር የጽዮናዊያኑ ሚዲያ ከጠቀሰው እጅግ የላቀ ነው።

-"ነብር" የተሰኘውን የጠላት የሰው ኃይል ተሸካሚ ጦር ለማውደም በሚሳኤሎቻችን ባደረግነው የመጀመሪያ ሙከራ ዶግ አመድ ማድረግ ችለናል።

- በርካታ ወታደሮቻችሁ በጥቁር ከረጢት ተሸፍነው ሲመለሱ ጋዛን በጽዮናዊያኑ ላይ የታሪክ እርግማን እናደርግባቸዋለን የሚለው ንግግራችንን በሚገባ ታስታውሱታላችሁ።

- በሺዎች የሚቆጠሩ ወገኖቻችንን በሞት ማጣታችንና በሰማዕትነት መገደላቸው ህመማችንን ዋጥ አድርገን ለከባድ መስዋዕትነት እንድንዘጋጅ ጉልበት ሆኖናል።

https://t.me/Xuqal
https://ummalife.com/BilalunaEdris1
IMG_7511.MP4
6.3 MB
ይህ አክሽን ፊልም፣ አሊያም የቦሊዩድ ልብ አንጠልጣይ ድርሰት አይደለም

ይህ የቀሳም ሙጃሂዶች "ወጀአልና ሚን በይኒ አይዲሂም ሰደን..." የሚለውን አንቀፅ እያነበቡ የፈፀሙት የጀግንነት ገድል እንጂ!

አሁን ከደቂቃዎች በፊት የቀሳም ሙጃሂዶች ይፋ ያደረጉት ተንቀሳቃሽ ምስል ነው።

https://t.me/Xuqal
https://ummalife.com/BilalunaEdris1
IMG_7589.MP4
6.9 MB
አሁን ከሰሜን ምዕራብ የጋዛ ሰርጥ ከአር-ራሺዲያ ጎዳና በኩል የወራሪዋ እስራኤል ታንኮች ወደ ኋላ በማፈግፈግ ላይ መሆናቸውን የጋዛ ምንጮች ዘግበዋል።

https://t.me/Xuqal
https://ummalife.com/BilalunaEdris1
አቡ ኡበይዳህ (ረ.ዐ) የታላቁ ሶሓብይ አሚር ቢን አል_ጀራህ (ረ.ዐ) ቅፅል ስም ነው።

የአላህ መልእክተኛ ﷺ ስለእርሱ እንዲህ ብለዋል፡- ለሁሉም ህዝብ አደራ ተረካቢ አለው፣ የኔ ህዝብ አደራ ተረካቢ አቡ ዑበይዳ ነው።
ስማቸው እንኳን የትንቢት ብርሃን ውጤት አለው።♥️

https://t.me/Xuqal
https://ummalife.com/BilalunaEdris1
IMG_7592.MP4
2 MB
ወራሪዋ በጦር ሜዳ በሚደርስባት ውርደትና ሽንፈት ከሰሜን ምዕራብ ጋዛ ሰርጥ በአር-ራሺድያ የባህር ዳርቻ መንገድ በኩል ታንኮቿን ስታፈገፍግ በተፈናቀሉ ንፁሐን ሰዎች ላይ አዲስ እልቂት ፈፅማለች ቪድዮውን ተመልከቱ።

https://t.me/Xuqal
https://ummalife.com/BilalunaEdris1
[ባሪያዎች የሚያነጉበት የሆነች አንድም ቀን የለችም ሁለት መላኢካዎች የሚወርዱ ቢሆን እንጂ ፤ ከዛም አንድኛቸው ይላል፦ አላህ ሆይ! ሰጪን አካል ምትክ ስጠው ፤ ሌላኛው ደግሞ ይላል ፦ አላህ ሆይ! ጨባጭን(ከልካይን) አካል ጥፋትን ስጠው]

ረሱል - ﷺ

https://t.me/Xuqal
https://ummalife.com/BilalunaEdris1
ፊትን በአማኢም መሸፈን የጀግንነት ምልክት ነው። ለዘመናት የተሻገረ የሙስሊም ሙጃሂዶች ልብስ

አብዛኞቹ ሰሐቦች ወደ ጦር ሜዳ ሲገቡ ይጨነበላሉ። ዙበይር በቢጫ አቡ ሐምዛና ሚህጀንም በቀይ ጥምጥም ፊታቸውን ይሸፍኑ ነበር። ማነው አቡ ሚህጀን?!

እርሱ የአላህንና የነቢን ጠላት በማሸበር ወደር ያልተገኘለት ጀግና። ወደ ጦር ሜዳ ሲገባ ጭንቅላቱ ላይ የሚጠመጥማት ቀይ አማይማን የተመለከተ ከሐዲ በፍርሐት ይርዳል። አንድ መሰረታዊ ችግር ግን ነበረበት። ሁሌም ይጠጣል። ጭንብስ ብሎ ይሰክራል። የአላህን ህግ በተደጋጋሚ እየጣሰ አስቸግሯልና በአደባባይ ብዙ ጊዜ ተገርፏል። ከዚህ ተግባሩ ባለመላቀቁ በእግረ ሙቅ ተጠፍሮ በግዞት ወደ እስር ቤት ተወርውሯል።

ዕለቱ የቃዲሲያ ዘመቻ ወቅት ነበር። አቡ ሚህጀን የታሰረው ጦርነቱ ከሚካሄድበት ቦታ ብዙም አይርቅም። የፈረሶችን ማሽካካት የሰይፍ ግጭቶችና የተክቢራ ድምፆችን ሲሰማ መታሰሩን አምርሮ ጠላ። ከተጋጋለው ጦር ገብቶ የአላህን ጠላቶች አንገት በሠይፍ መሸልቀቅን በእጅጉ ናፈቀ። ከአይኖቹ እንባን እያረገፈ ውስጡ ክፉኛ ተረበሽ። የጂሃድ ናፍቆት እንደነበልባል እያንገበገበ አላስችል ቢለው የታሰረበትን ክፍል በር ደብድቦ ለጦር መሪው ሚስት መልዕክትን ላከ። እንዲህም አላት "ካቴናዬ ተፈቶ የጦር መሳሪያና ፈረስ አዘጋጅተሽ የናፈኩትን ጂሃድ እንድካፈል አድርጊኝ። እባክሽ እፋለም ዘንድ እርጂኝ። በህይወት ከተረፍኩ ራሴ መጥቼ የእስር ቤቱን በር በላዬ ላይ እከረችማለሁ" አላት።

ንግግሩን ስትሰማ አዘነች የመጣው ይምጣ ብላ በራሷ ወሰነች። ፈረስና ሠይፍ ሰጥታ ለቀቀችው። አቡ ሚህጀን ፊቱን በጨርቅ ሸፍኖ ከጦር ሜዳው መሐል ሰፈረ። የአላህ ጠላቶች የበላይነትን ለመቆጣጠር ቀርበዋል። የሙስሊሙ ጦር ተዳክሟል። በዚህ ቅፅበት አቡ ሚህጀን ከመሐላቸው ተከሰተ። አንዱን በአንዱ ላይ አነባበረ። ድል ወደ ሙስሊሞች ማዘንበል ጀመረ። አቡ ሚህጀን የአላህንና የሙስሊሙን ጠላቶች አረገፋቸው። ከፊቱ የቀረበን የጠላት ጦር አንገቱን ቀንጥሶ መሬት ላይ እየጣለ፣ ያገኘውን እየገነዳደሰ ወደመሐል ገሰገሰ።

የጦር መሪው ሰዕድ የዚህን ተዋጊ ገድል እየተመለከተ ነው። እንዲህ በፅናት የአላህን ጠላቶች አመድ የሚያደርገው ማን ነው ሲል ይጠይቃል። የሚያውቀው ሰው ጠፋ። አቡ ሚህጀን ነው እንዳልል እሱን አስሬዋለሁ ይላል።
ጦርነቱ በሙስሊሞች ድል አድራጊነት ሲጠናቀቅ ወደ እስር ቤቱ ተመለሰ። እነዛን በጦርነት የደከሙ እግሮቹንና እጆቹን በካቴና ጠፍሮ አሰራቸው። ሰዕድ ወደ ቤት ሲመለስ ሚስቱ ውሎውን ጠየቀችው።

ሰዕድም የሽንፈት ማቅ ልንከናነብ በተቃረብንበት ወቅት አላህ አንድ ልዩ ተዋጊ ላከልን። ያ የመነመነ የድል ተስፋ ተቀልብሶ ለማሸነፍ በቃን። አቡ ሚህጀንን አስሬው ባልሄድ ኖሮ ያ ጀግና ተፋላሚ እሱ ነው ብዬ እጠረጥር ነበር። የጦር ስልቱ የእሱን ይመስላል በማለት ተናገረ።

ሚስቱም በአላህ ይሁንብኝ እራሱ አቡ ሚህጀን ነው ብላ የተከሰተውን አስረዳችው። በሁኔታው በእጅጉ የተደሰተው ሰዕድ አቡ ሚህጀንን አስጠርቶ ከዛሬ ጀምሬ አልገርፍህም። አላስርህም በነፃ ለቅቄሀለው አለው።
አቡ ሚህጀንም እንግዲያውስ እኔም ከዛሬ ጀምሬ አልጠጣም አልሰክርም በማለት መለሰ።

ረድየላሁ አንሁም አጅመዒን


https://t.me/Xuqal
https://ummalife.com/BilalunaEdris1
#አንኳር_ዜናዎች!
▶️ አልቃሳም ብርጌዶች“ሙጃሂዲኖቻችን ከ “ኢሬዝ” በስተምዕራብ በጋዛ ሰርጥ የሚገኘውን የጽዮናውያን የእግር ሃይል ከርቀት በኢላማ ውስጥ አስገቡት!”ብሏል።

▶️ ክሬምሊን“የሩሲያ የአየር መከላከያ ዘዴን ወደ ሄዝቦላህ መላክን በተመለከተ በዎል ስትሪት ጆርናል ዘገባ ላይ የተነገረው ውሸት ነው” በማለት አጣጥሏል።

▶️ የተባበሩት መንግስታት በዌስት ባንክ ያለው ሁኔታ አሳሳቢ እና አፋጣኝ እርምጃ ያስፈልገዋል ሲል አሳስቧል።ወሬብቻ!

▶️ የሩስያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በመካከለኛው ምስራቅ ያለውን ተኩስ በአስቸኳይ ማቆም እና ሰብአዊ እርዳታን በጋዛ ለሚገኙ ሲቪሎች ማስተላለፍ አስፈላጊ ነው ያለ ሲሆን፣ጋዛን በተመለከተ የፀጥታው ምክር ቤት ውሳኔዎችን ተግባራዊ እንድያደረግ እንጠይቃለን፣በተለይ የተኩስ አቁምን፣ ሰብዓዊ ቀውስን ለመፍታት እና የታፈኑትን መመለስን በተመለከተ ብሏል።
በተጨማሪም ግብፅ ፍልስጤማውያንን ወደ ሲና በማፈናቀል የፍልስጤምን ጉዳይ የመፍታት ዘዴን እንደማትቀበል አረጋግጣለች በማለት አክሏል።
በመጨረሻም ፍልስጤማውያንን ለማፈናቀል እና የፍልስጤም መንግስት ምስረታን ለማጥፋት የታቀደው ሴራ አስከፊ መዘዞችን የሚያስከትል ሲሆን በአካባቢው ያለውን ቀውስ የበለጠ ያሰፋዋል ሲል አስጠንቅቋል።

▶️ የኩዌት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጦርነቱን በአስቸኳይ ማቆምና የሰብአዊ እርዳታ ወደ ጋዛ ህዝብ እንዲገባ መፍቀድን በተመለከተ ከሩሲያ ጋር ተመሳሳይነት ያለው አቋም አለን ያለ ሲሆን፣400 ቶን ሰብአዊ እርዳታን የጫኑ 11 አውሮፕላኖችን በጋዛ ላሉ ወገኖቻችን ልከናል ብሏል።በመጨረሻም የፀጥታው ምክር ቤት በጋዛ ያለውን ጦርነት በተቻለ ፍጥነት ለማስቆም ኃላፊነቱን ሊወጣ ይገባል በማለት አሳስቧል።

▶️ የእስራኤል ጦር የኛ የምህንድስና ቡድን በጋዛ ሰርጥ የተገኙትን ዋሻዎች ለማፍረስ እየሰሩ ነው ብሏል!
አፍራሽ መሀንዲስ! 🙄

▶️ የእስራኤሉ ፕሬዝዳንት እራሳቸውን እንድከላከሉ 6 ሚሊየን የጽሁፍ መልእክቶችን እና 1.2 ሚሊየን በራሪ ወረቀቶችን በጋዛ ለሚገኙ ሲቪሎች አሰራጭተናል ብሏል!
ድንቄም አዛኝ! 😎

▶️ አል-ቃሳም ብርጌዶች ከቤቴላሂያ በስተሰሜን ምዕራብ በሚገኝ ሕንፃ ላይ በቲፒጂ ዛጎሎች የተጠለፈውን የጽዮናውያን ኃይል ኢላማ አድርገናል ብሏል።

▶️ CNN በመረጃ የተደገፈ ምንጭን ጠቅሶ እንደገለጸው የአሜሪካ ባለስልጣናት ነዳጅ ለሰብአዊነት ሲባል ወደ ጋዛ እንዳይገባ ስጋት አድሮባቸዋል ያለ ሲሆን፣ባይደን እና ከፍተኛ አማካሪዎቹ የአለም ማህበረሰብ ቁጣ እየተባባሰ በመምጣቱ እስራኤልን ወታደራዊ ግቦቿን የማሳካት ችግር እንዳለባት አስጠንቅቀዋል በማለት ዘግቧል።

▶️ አል ቁድስ ብርጌዶች በ"ሱፋ"፣"ሁሊት" እና "ኒር ሻቅ" የተሰበሰበውን ወራሪ ሀይል በሚሳኤል ፈንጅ ደበደብናቸው በማለት አስታውቋል።

▶️ NBC በዩኤስ ባለስልጣናት ላይ ባወጣው መረጃ እስራኤል ጦርነቱን እንዴት እየፈፀመች እንደሆነ በBiden አስተዳደር ውስጥ ባሉ ከፍተኛ ባለስልጣናት መካከል ያለው ስጋት እየጨመረ ሲሆን፣የጋዛ ሰብአዊ ቀውስ እየተባባሰ ሲሄድ የባይደን አስተዳደር በእስራኤል ውስጥ የመቆጣጠር ችሎታ ያሳስበዋል ብሏል።

▶️ አልቃሳም ብርጌዶች ከኤሬዝ በስተ ምዕራብ በነበሩ የጠላት መኪናዎች በጋዛ ኤንቨሎፕ ውስጥ በተሰበሰቡ ከባድ የሞርታር ዛጎሎች ደበደብን ሲል፣ ሒዝቦላህ በበኩሉ በደቡብ ሊባኖስ ርሜይሽ ከተማ ትይዩ በሚታት ቦታ አቅራቢያ በተሰበሰቡ የጠላት ወታደሮች ላይ ኢላማ ያደረግን ሲሆን በጦር ሠራዊታቸው ላይ ጉዳት መድረሱን አረጋግጠናል ብሏል!
እነዚህን እርኩሳኖች በሏቸው አቦ አሏህ ይርዳችሁና!

▶️ የቱርክ መንግስታት ድርጅት #የመጨረሻ ባለው መግለጫው አስቸኳይ የተኩስ አቁም ተፈፃሚ እንድሆን፣ለሲቪሎች ጥበቃ እንድደረግ እና በመላው ጋዛ ሰብአዊ እርዳታ እንዲሰጥ እንጠይቃለን ብሏል።

▶️ ፑቲን ማንኛውም ኖርማል ሰው በጋዛ ውስጥ በደም የተሸፈኑ ሕጻናት ምስሎችን በማየቱ እጅግ ያዝናል፣ይበሳጫልም በማለት የእስራኤልን፣አሜሪካንና ምዕራባዊያንን ጭራቅነት ጠቁሟል።

https://t.me/Xuqal
https://ummalife.com/BilalunaEdris1
مـاكتبتُ الشعرَ في أروقة القصور طالباً الأُجور

عـنـدما تنفجِرُ الدماء أو تثور تُكتَب السطور

تـقـلع السجادة الحمرا من الجذور عندما تفور

ثـمـن الحرية الحمرا دم النحور في مدى العصور

https://t.me/Xuqal
https://ummalife.com/BilalunaEdris1