Bilaluna Edris (Xuqal.X.Qafarey)
472 subscribers
3.13K photos
207 videos
46 files
2.15K links
♡_ወደ መልካም ነገር ያመላከተ ሰው የሰራ ሰውን አጅር ያህል ያገኛል"(አመላካች የሰሪውን ምንዳ ያገኛል)(ﷺ)

« ከናንተም ወደ በጎ ነገር የሚጠሩ ፣ በመልካም ስራም የሚያዙ ከክፉ ነገርም የሚከለክሉ ሕዝቦች ይኑሩ» ﷻ
                 ቁርኣን[ 3:104 ]


መወያያ ግሩፓችን ☞ https://t.me/+1qmNqy265XoyNGY0
Download Telegram
#Breaking
አሁን ከሶሪያ ድንበር በኩል ሚሳኤል ወደ ወራሪዋ መተኮስ ጀምሯል። የቀሳም ሙጃሂዶች በየከተማዋ ዘልቀው ገብተው ወታደሮቿን እየቀጠፉ ይገኛል። አስቀላን እየነደደች ነው። ከጋዛ ከሉብናን ከሶርያ ድንበር በተምዘግዛጊ ሮኬቶች እየተደበደበች ነው። አላሁመ ዚድ

https://t.me/Xuqal
ዓለም አቀፉ ኢንዲቴክስ የስፔን ኩባንያ በእስራኤል የሚገኙትን 84 የንግድ ማዕከል መዝጋቱን ይፋ አደረገ።

https://t.me/Xuqal
በዚህ የአለም መንግስታት ውሳኔ ላይ ኢትዮጵያ ድምጿን ለማን የሰጠች ይመስላቹሀል?(ቅድሚያ ገምታቹ ወደ ንባቡ ግቡ)
.
.
1947 የአለም መንግስታት ፓለስታይን ሁለት ቦታ ትከፈል ፣ አትከፈል (እስራኤል የምትባል ሀገር ትፈጠር ፣ አትፈጠር) ለሚለው በመላው አለም ያሉ ሀገራት ድምጽ ሰጥተው ነበር።
የሚያሳዝነው በዛን ሰአት አለም ፓለስታይን የምትባል ሀገር እንዳለች ያውቃል። ከዚያ የድምጽ መስጠት ቀን አንስቶ ዛሬ ድረስ ፓለስታይን ሀገር የመሆን መብቷን እንዳገደው ይገኛል።

የአለም ሀገራት ድምጽ ሲሰጡ ዛሬ አስራኤል ከያዘችው መሬት ለ20/100 ብቻ ነበር። የተቀረውን 80/100 በጉልበት የወሰደችው ነው።

ይህንን እውነታ ሁሉም ሊያውቀው ይገባል። ነገሩን ያልተረዳም ስለሚኖር ለግንዛቤ ያህል አድርሱልኝ።

@AmmarAli75
የእስራኤል እና የፍልስጤም ሃማስ ጦርነት፤ ምን አዳዲስ ክስተቶች አሉ?

በእስራኤል 900 ሰዎቸ በጋዛ ደግሞ 700 ፍልስጤማውያን እስካሁን በጦርነቱ ሞተዋል
ሃማስ ባሳለፍነው ቅዳሜ በእስራኤል ላይ ያለተጠበቀ እና ድንገተኛ ጥቃት መሰንዘረሩን ተከትሎ በእስራኤልና በፍልስጤም መካከል የተጀመረው ጦርነት ዛሬ አራተኛ ቀኑን ይዟል።
በሃማስ ጥቃት እና በእስራኤል የአየር ድብደባ ከሁለቱም ወገኖች የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከ1 ሺህ 600 ማለፉ ተነግሯል።
የእስራኤል መከላከከያ ኃይል ባወጣው መረጃ መሰረት በሃማስ ጥቃት የሞቱ እስራኤላውኝ ቁጥር 900 የደረሰ ሲሆን፤ ከ2 ሸህ በላይ ሰዎች ደግሞ ቆስለዋል።
በእስራዔል ከተገደሉ ሰዎች መካከል የአርጀንቲና፣ የካምቦዲያ፣ እና የአሜሪካን ጨምሮ የሌሎች ሀገራት ዜጎችም እንደሚገኙበት ተገልጿል።
አሜሪካ በሃማስ ጥቃት 11 ዜጎቿ እንደተገደሉባት ትናንት አስታውቃለች።
የፍልስጤሙ ሃማስ ቡድን እስራኤል ላይ ለምን ጥቃት ከፈተ? ማወቅ ያለብን ነጥቦች
የፍልስጤም ባለስልጣናት በሰጡት መረጃ ደግሞ በእስራኤል የአየር ድብደባ የሞቱ ፍልስጤማውያን ቁጥር 700 መድረሱን የገለጹ ሲሆን፤ ከእነዚህም ውስጥ 143 ህጻት እና 105 ሴቶች ይገኙበታል።
የተመድ የስደቶች ኤጀንሲ እንዳስታወቀው በእስራኤል የአየር ድብደባ 187 ሺህ ሰዎች ከጋዛ መፈናቀላቸውን እና ከእነዚህም 137 ሺህ ሰዎች በ84 ትምህርት ቤቶች ውስጥ መጠለላቸውን አስታውቋል።
እስራኤል በጋዛ የምታካሂደውን የአየር ድብደባ የቀጠለች ሲሆን፤ አዳሩን በካሄደችው የአየር ድብደባ ሁለት የፍልስጤም ጋዜጠኞች ተገድለዋል።
እስራኤል በተትናትናው እለት ብቻ በጋዛ ውስጥ በሚገኝ 1 ሺህ የሃማስ ኢላማዎች ላይ የአየር ድብደባ መፈጸሟ ተነግሯል።
የእስራዔል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ትናት ምሽት በሰጡት መግለጫ፤ በጋዛ እየተካሄደ ያለው የአየር ድብደባ ገና ጅማሮ ነው ብለዋል።
በጋዛ የምታዩት ውድመት ገና የመጀመሪያው ነው ያት ኔታንያ፤ የአየር ድብደባው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቀዋል።
የአሜሪካ የጋራ ግብረ ኃይል ዋና አዛዥ ጄንራል ቻርልስ በሮወን፤ ኢራን በጦርነቱ ውስጥ ከመሳተፍ እንድትቆጠብ አሳስበዋል።
ኢንዶኔዤያ ዜጎቿ በአስቸኳይ እስራዔልን ለቀው እንዲወጡ ማሳሰቢያ ሰጥታለች።


https://t.me/Xuqal
የቀድሞው የስፔን ብሔራዊ ቡድን ተጫዋች እና የአሁኑ የባርሴሎና ክለብ አሰልጣኝ ዣቪ ሄርናንዴዝ በፅዩናዊቷ እስራኤል የግፍ በትር እየተሰቃዩ ያሉትን ፍሊስጢኖች ጎን እንደሚቆም በትዊተር ገፁ አስነብቧል።

https://t.me/Xuqal
4_5848342192552153259.mp4
1005.4 KB
ከፍልስጤም መንግስት እና ከፍልስጤም ህዝብ ጋር እንቆማለን። ጽዮናውያን ፍልስጤምን ከመውረራቸው በፊት አይሁዶች ከሙስሊሞች ጋር በሰላምና በስምምነት ይኖሩ ነበር።"
የቶራ አይሁዶች ቡድን  መሪ

https://t.me/Xuqal
ፅዮናዊቷ እስራኤል ከሶርያ በመድፍ በሞርታርና በሮኬት እየተደበደበች ነው ጥቃቱ አስክሮ ያንገዳግዳት ይዟል።

ጸሃፊና ጋዜጠኛ ሰኢድ አስ-ሱኒ
"የማይቀለበስ ክብር" በሚል ርዕስ በአልጀዚራ ኔት ላይ ባሰፈረው ፅሑፍ "የአል-አቅሳ አውሎ ንፋፍ ከባድና አስፈሪ መንቀጥቀጥ ሆኖ መጣ። ለወራሪዋ አስደንጋጭና አስፈሪ ተለዋዋጭ ገፅታ ለስለስ ብሎ ሰከን መለስ ብሎ እንደ አውሎ ንፋስ የሚጠራርግ የፍልስጤም ብርጌዶች እንደስከዛሬው መደበኛ ባልሆነ መንገድ የጓዙ ጎርፎች ሆነው መጥተዋል። እስራኤል ከሁሉም ነገር በላይ የምትፈራው እንደ ቂጣ ተገላቢጦሽ የሆነውን ስደት ነው" ይላል።

https://t.me/Xuqal
4_5850471465538818397.mp4
1.9 MB
🇵🇸🇮🇱🚨 የእስራኤል ወታደሮች ወደ ጋዛ ነዋሪዎች የሚያስተላልፈውን የውሃ አቅርቦት ሲቆርጡ..

በሮም ስምምነት መሰረት "ሆን ብሎ የሲቪሎችን ረሃብ እንደ ጦርነት ዘዴ በመጠቀም ለህይወት አስፈላጊ የሆኑትን እንደ የመጠጥ ውሃ አቅርቦትና ውሃውን መመረዝ እንደ የጦር ወንጀል ይቆጠራሉ።" ሲል ይደነግጋል።

#Gaza #ጋዛ #Palestine #Israel #ፍልስጤም #እስራኤል #peaceandlove

Via esleman abay

https://t.me/Xuqal
በጭንቀት እና በፍራቻ የጠወለገ ፊት....ብለው በመግለፅ የእስራኤል ሚዲያዎች ኔታንያሁ ከጆ ባይደን ጋር በስልክ በሚወያዩበት ግዜ የኔታንያሁ ፊት ምስልን ለቅቀውታል
#AlAqsaFlood
#Gaza

https://t.me/Xuqal
የቀሳም ሙጃሂዶች ነሃል ኦዝ የተሰኘውን የወራሪዋን ወታደራዊ ካንፕ መቆጣጠራቸውን ይፋ አደረጉ።
الله اكبر
#AlAqsaFlood
#Gaza

https://t.me/Xuqal
"የምዕራቡ አለምና አውሮፓ ፍልስጤምን ለማፍረስ ሲሰባሰቡ እያየን እንዴት በጋራ አንዳች ነገር ማድረግ አቃተን?"
የቺቺኒያው መሪ ራምዛን ቀዲሮፍ

https://t.me/Xuqal
በጋዛ ሰሜናዊ ምዕራብ በሚገኘው የወተት ፋብሪካ ላይ ባደረሰው ጥቃት የእስራኤል ወታደሮች በአለም አቀፍ ደረጃ የተከለከሉ ነጭ ፎስፎረስ ቦምቦችን ተጠቅመዋል።

https://t.me/Xuqal
"ሁለት ከፍተኛ አመራሮቻችን ጀዋድ አቡ ሸማላ እና ዘከሪያ አቡ ሙአመር ደም እየፈሰሳቸው ሰውነታቸውን በጨርቅ ጠቅልለው መሳርያቸውን እንደሰበቁ ግንባር ላይ ስናያቸው ወኔና ሞራላችን ከፍ ብሎ ጥንካሬ ሆነን።  ቁርጠኝነታችን ጨመረ።

በዚያው የእሾህ መንገድ ላይ እንዘልቃለን የወራሪዋ ትዕቢት እስኪተነፍስ የጡፋን አል አቅሳ ዘመቻችን ይቀጥላል። ጠንካራ እና ጥልቅ ምላሽ እንሰጣለን። ፍልስጤምንና እስረኞቻችንን ነፃ ሳናወጣ አንቆምም"    የሃማስ ንቅናቄ ግንባር

https://t.me/Xuqal
ባለን የማንረካ ከሆነ ተመኝተን ኋላ ላይ አላህ ቢሰጠንም አንረካም። ዱንያ ብትጨመርልንም ያው ትሆንብናለች። መብቃቃት፣ መርካት፣ አልሐምዱ ሊላህ ማለት ሀብት ነው። ሰባሀኩም 😍
የተባረከው የፍልስጤም ምድር 4
—————————————————


የአይሁድ ሠፋሪ ታጣቂዎች ዴር-ያሲን የምትባል ከኢየሩሣሌም አቅራቢያ የምትገኝ ፀጥተኛ መንደር ላይ ከበባ አደረጉ፡፡ ዕድሜና ፆታ ሳይለዩ ፊለፊት ያገኙትን ሁሉ በጥይት ቆሉት፡፡ በስለትና በመጥረቢያ ጨፈጨፉት፡፡ ለማምለጥ የሚሞክረውን መግቢያ መውጫውን ዘግተው በመጠበቅ ደፉት፡፡ በመጨረሻም 256 ነዋሪዎችን ጭፍጭፍ አድርገው አንድም እንዳልተረፋቸው እርግጠኛ ሲሆኑ ቤት ንብረቱ ላይ (የፍየልና የግመል ማደሪያ፣ የጥራጥሬ ማከማቻ ሳይቀር) እሣት ለቀቁበት፡፡ ይህ የኾነው ሜይ 15 ቀን 1948 ነው፡፡

ፍልስጤማውያን ይህን ቀን ´አን-ነክባ’ ይሉታል፡፡ በታላቅ ምሬትም ያስታውሱታል፡፡ የሐዘንና የዕልቂት ቀን ማለት ነው፡፡
አይሁዶች ግን በዚህ አልበቃቸውም፡፡ ´ታንቱራ’ በተባለች መንደር ተመሳሳይ ጥቃት ሠንዝረው 200 ነዋሪዎችን ፈጁ፡፡

ፍልስጤማዊያን በዴር-ያሲን ወገኖቻቸው ላይ በተፈጸመው ጅምላ ፍጅት ክፉኛ ተናወጡ፡፡ ተረበሹ፡፡ በገዛ ቤት ቀያቸው ላይ ውለው ለማደር ደህንነት አልሰማቸው አለ፡፡ ባፋጣኝ ቀያቸውን እየለቀቁ በቀንና በለሊት ተሰደዱ፡፡ ምንም አልያዙ፡፡ ምንም አልቋጠሩ፡፡ አልሰነቁ- ብቻ ነፍሳቸውን ይዘው እግር ወደመራቸው ጎረፉ፡፡ አንፃራዊ ሰላም እናገኛለን ወዳሉበት ርቀው ሄዱ፡፡

ድርጊቱ ዓለም አቀፍ ውግዘት አስከትሎ ተኩስ አቁም ሲደረግ 800,000 ፍልስጤማዊያን ቤተሰቦች የትውልድ ቀያቸውን ለቀው ተሰደዋል፡፡ ገሚሱ የዮርዳኖስን ወንዝ ተሻግረው ኡርዱን ገቡ፡፡ ገሚሱ በረሃ አቋርጠው ሉብናን ደረሱ፡፡ ገሚሱ እስከዚህ ጊዜ ድረስ የዐረቦች ጠንካራ ይዞታ ወደነበረው የምዕራብ ዳርቻ (ዲፋ-ገርቢያ) እና የጋዛ ሠርጥ ሄደው ሜዳ ላይ ፈሰሱ፡፡ የተቀሩት ወደ ማዕከላዊ ፍልስጤም ተራራማ ቀበሌዎች በመሄድ ተገን ያዙ፡፡ በጊዜው 160,000 የሚሆኑ በገሊላ ነዋሪ ዐረቦች ብቻ እዚያው የመጣ ይምጣ ብለው ሲቀሩ ሌላው ተበታተነ፡፡

ተኩስ አቁም ተደርጓል ተብሎ አገር አማን የሆነ ሲመስል ተሰዳጆቹ ፍልስጤማዊያን ሌላ ያልጠበቁት ነገር ገጠማቸው፡፡ ወደየነበሩበት ቀየ አትመለሱም ተባሉ፡፡ ተከለከሉ፡፡ የኢስራኤል ጦር መንገዱን ሁሉ በከባድ መሣሪያና ፀረ-ሰው ፈንጂ አጥሮ አላስገባ አላቸው፣ አሳደዳቸው፣ ተኮሱባቸው፡፡ ይህን ጊዜ የተባበሩት መንግሥታት ልዩ ኮሚሽን ተቋቁሞ ፍልስጤማውያኑ እዚያው ተሰደው ባሉበት ወደ 50 የሚሆኑ ጊዜያዊ መጠለያ (እነሱ ሙኸየማት ይሏቸዋል) በማቋቋም ተፈናቃዩን ህዝብ ማስተናገድ ጀመሩ፡፡

በአይሁዶች ላይ ጫና አሳድሮ ተፈናቃዩን ህዝብ ወደ ቀየው የማስመለሱ ዲፕሎማሲያዊ ጥረት ከዐረብ መንግሥታት በኩል ለረጅም ጊዜ ቢቀጥልም ውጤት አላመጣም፡፡ የፍልስጤማዊያኑ ከዛሬ ነገ ወደ ቀያችን እንመለሳለን ተስፋም የሩቅ ምኞት ብቻ ሆኖ ቀረ፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ በኢስራኤል ቁጥጥር ሥር ባሉት ከተሞች የሚገኙ ፍልስጤም ዐረቦች ሌላ አመፅ በማስነሣት የ1953ቱን የግዲያ ርምጃ ጀመሩ፡፡

ከአይሁዶችም በኩል ተመሳሳይ ጥቃት በዐረቦቹ ላይ ሲፈጸም ነገሩ ተቀጣጠለ፡፡ በግጭቱ የተገደሉት ሥርዓተ-ቀብራቸው ሲፈጸም በዐረቦችና በአይሁዶች መካከል ሌላ ዙር ረብሻ ተቀሰቀሰ፡፡ አመፁ እየተባባሰ ቀጥሎ ማዕበሉ ሌሎች ከተሞችንም አዳረሰ፡፡ የብሪትሽ ወታደራዊ ባለሥልጣናት በጃፋና በቴልአቢብ ከተሞች የሠዐት እላፊ ገደብ እስከመጣል ደረሱ፡፡ በናብሉስ ከተማም አስተባባሪ ኮሚቴ ተቋቁሞ አጠቃላይ የህዝብ አድማ ተጠራ፡፡

ሁኔታውን ተከትሎ የብሪትሽ ጦር ወደ 20,000 የወታደር ኃይል ከፍ ከተደረገ በኋላ በፍልስጤም የፊዳአይን ንቅናቄ አባላትና በብሪትሽ አይሁድ ጣምራ ኃይላት መካከል ኖቬምበር 1953 ላይ ደም አፋሳሽ ውጊያ ተካሄደ፡፡ የነዚህ ተከታታይ አመፆችና ግጭቶች ድምር ውጤት ብዙ እንግሊዞችና ሠፋሪ አይሁዶች የተገደሉበትና የአካል ጉዳት ያገኙበት ሲሆን ከዐረቦቹም በኩል 145 ሰዎች የተሰዉበትና በመቶዎች የሚቆጠሩ የተጎዱበት ሁኖ ተመዘገበ፡፡

የፍልስጤሞች መነሳሳት እንደገናም በመቀጠል የእንግሊዝ መንግሥት እስከዛ ጊዜ ድረስ ይዞት የነበረውን አይሁድ ዘመም አቋም እንደገና እንዲያጤነው የተገደደበትን ርምጃ ወሰዱ፡፡ የጀሊል ከተማን እንግሊዛዊ አስተዳዳሪ ገደሉ፡፡ በዚህም የተነሳ እንግሊዞች ካንዳንድ አቋሞቻቸው በማፈግፈግ አገሪቱን በአይሁዶችና በፍልስጤሞች መካከል የመክፈል ሃሳብም ለማቀንቀን ተገደዱ፡፡

ባንድ በኩል ምንም ውጤት ያለመገኘቱ ነገር እንዳለ ሁኖ ውስጥ ውስጡን ደሞ የኢስራኤል ሠፋሪ መንግሥት ድንበር እየገፋ ሠፈራውን የማስፋፋቱ ድርጊት የተጎራባች ዐረብ መንግሥታትን ቁጣ እያስነሣ ቁርቋሶና ወታደራዊ ግጭቶች ተካሂደዋል፡፡ በ1956 ሲናይ ምድር ላይ ከግብጽ ጋር የተደረገው ውጊያ ተጠቃሽ ነው፡፡ አይሁዶች በሲናይ ድንበር በኩል ከግብጽ የሚደርስባቸውን ወታደራዊ ጫና ለማርገብና እስከ ወዲያኛው ከግብጽ ተከታታይ ጥቃት ለመጠበቅ ሲሉ ከፈረንሳይና ከእንግሊዝ ጎን በመሆን ግብጽን ወጉ፡፡ የሲናይን ምድር ለመቆጣጠር የነበራቸው ሃሳብ ግን አልሠመረም፡፡ በ1967 የስድስቱ ቀን ጦርነት ተሳክቶላቸው ከግብጽ የሲናይን ምድር፣ ከሶሪያ የጎላንን ኮረቦታዎች፣ የደቡብ ሊባኖስን ከፍታማ ቀበሌዎች መያዝ ቻሉ፡፡

በዐረቦች ይዞታ ሥር በሚገኙት የምዕራብ ዳርቻና የጋዛ ሠርጥ ላይ ቁጥጥር ማጥበቅ የሚያስችላቸውን ገዢ መሬትም ተቆናጠጡ፡፡ ይህንንም አዲስ ጥቃትና ወረራ ተከትሎ ተጨማሪ ፍልስጤሞች ለስደት ተዳረጉ፡፡ የተባበሩት መንግሥታት የስደተኛ ኮሚሽንም ተጨማሪ 10 መጠለያዎችን በማቋቋም የመጠለያውን ቁጥር ወደ 60 ከፍ አደረገው፡፡

ከቀያቸው ላይ በግፍ ከተፈናቀሉበት ጊዜ አንስቶ እስካሁንም ድረስ በምዕራብ ዳርቻ፣ በጋዛ ሠርጥና በጎረቤት ዐረብ አገራት በስደተኛ ካምፖች እየኖሩ ይገኛሉ፡፡ በጎረቤት አገራት የምጣኔ ሀብትና የማኅበራዊ ህይወት መዋቅር ውስጥ መቅለጥና ሟምተው መጥፋት አልፈለጉም፡፡ የማንነት ጉዳይ ነው፡፡ ወደ አገር ቤት ለመመለስ ያላቸውን ቁርጠኝነት የሚያሳይ፡፡ በመሠረቱ ይህ የፍልስጤማዊያን ወደ አገር ቤት የመመለስ ቁርጠኛ አቋም ነው እስካሁንም አይሁዶችን ዕንቅልፍ እየነሣ ያለው፡፡

Mahi Mahisho
https://t.me/Xuqal