Woy AddisAbeba ወይአዲስ አበባ በሸገር
7 subscribers
4 photos
17 links
woy Addis Abeba ወይ አዲስ አበባ በሸገር ሬድዮ
Download Telegram
ይህ ትክክለኛ የወይ አዲስ አበባ በሸገር የዩቱዩብ ቻናል ነው ማስፈንጠርያውን በመጫን ሰብስክራይብ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ እናመሰግናለን…🙏
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇

https://www.youtube.com/channel/UC8dZQi3xN8mP2dF25bq2sAg
ይህ ትክክለኛ የወይ አዲስ አበባ በሸገር የዩቱዩብ ቻናል ነው ማስፈንጠርያውን በመጫን ሰብስክራይብ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ እናመሰግናለን…🙏
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇

https://www.youtube.com/channel/UC8dZQi3xN8mP2dF25bq2sAg
ቶሎሳ ሰፈር ክፍል 1 - በጀሚል ይርጋ

https://youtu.be/Xu1gNZGFUVY
በዛሬው ዕለት october 1 በእኛ በኢትዮጵያውያን አቆጣጠር መስከረም 21 ዓለም-አቀፍ የቡና ቀን በዓለም ዙርያ ይከበራል:: ቡና ዓለም ላይ ነግሳ የምትውልበት ቀን ነው!

ቡና ሲነሳ... ቡና ሲከበር የቡና የትውልድ ቦታ የሆነችው ኢትዮጵያ አብራ ትነሳለች። ቡና ለመጀመሪያ ጊዜ የተገኘውን ኢትዮጵያ ውስጥ "ካልዲ" በተባለ እረኛ አማካኝነት እንደሆነ ይነገራል። እረኛው "ካልዲ" ፍየል ለግጦሽ አሰማርቶ በሚያግድበት ወቅት ፍየሉ የቡናውን ቅጠል እና ፍሬ በሚበላበት ሰዓት እንቅስቃሴው ሲጨምርና ፍጥነት ሲያሳይ አስተዋለ። ይህም አስተውሎቱ ለቡና ግኝት ምክንያት ሆነው:: ፍየሉን እንዲያ ያነቃው ቡና ለሰው በሚስማማ መልኩ ቢቀርብ ለኃይል እና ለንቃት የሚኖረውን ጥቅም መረዳቱ ቡናን እስካሁን ድረስ በዓለም ዙሪያ ተወዳጅ እና ተመራጭ እንዲሆን አድርጎታል።

ለኢትዮጵያውያን ደግሞ ቡና መጠጥ ብቻ አይደለም ማህበራዊ ሕይወትን ማጠናከርያ፣ ወዳጆችን ማሰባሰቢያ፣ ደስታ፣ እና ሐዘንን መጋሪያ፣ መወያያም ጭምር እንጂ!

ለኢትዮጵያውያን ዓለም አቀፍ የቡና ቀንን ማክበር .. ታሪካችንን ማወቅ፣ ባህላችንን ማክበር እንዲሁም ቡና በሀገራችን ኢኮኖሚ ላይ ያለውን ወሳኝ ሚና ማወደስም ጭምር ነው!

ለቡና ውዳጆች በሙሉ መልካም የቡና ቀን!

የቡና ስባቱ መፋጀቱም አይደል ፉት በትኩሱ!
👍2
ሰላም ለእናንተ ይሁን፤ የተወደዳችሁ አድማጮቻችን :-

ዛሬ (ሐሙስ) መስከረም 22/2018 ዓ.ም. … “ወይ አዲስ አበባ” የሬድዮ ዝግጅት በሸገር FM 102.1 ላይ … ከ8:00 እስከ 10:00 ሰዓት ድረስ መሰናዶዎቹን ያቀርባል።

☞ "ሰፈራችን" በተሰኘው መሰናዶአችን ዛሬ የምናመራው ወደ መርካቶ ነው - "መርካቶ፡ የኢትዮጵያ የንግድ ልብ፤ የማይበገረው የአዲስ አበባ መንፈስ" ርዕሱ ነው። የመጀመሪያው ክፍል ይቀርብላችኋል።

☞ ዛሬ በ“ጉዞ አፍሪቃ” ዝግጅታችን የምንጓዘው ወደ ምዕራብ አፍሪቃዊቷ አገር ኮትዲቯር ነው - ወደ "ድሮግባ አገር"።። … አዘጋጅቶ የሚያቀርብላችሁ፤ .. ኃይሉ ውድነህ ነው!

☞ ከወዲያና ወዲህ ያሰባሰብናቸው የከተማ ወሬዎችም አሉን።

ለአስተያየቶቻችሁ በ011 -1- 27 5454 ደውሉልን።

አጫጭር መልዕክቶቻችሁንም :- በ8101 እና በ0939-939393 አኑሩልን!