Forwarded from ከፍልስፍና ዓለም ™ (Peter)
#Objectivism
ተፈጥሮ በማንም የአዕምሮ ምኞት አይለወጥም። አይዲያሊስቶች እንደሚሉት ሳይሆን፤ አዕምሮ አካባቢውን በማስተዋል ተፈጥሯቸውን የማወቅ አቅም አለው፤ አቅሙን የመጠቀምና ያለመጠቀም ምርጫም የራሱ ብቻ ነው። ነፃ ምርጫ አለው፤ ማቴሪያሊስቶች እንደሚሉት ሮቦት አይደለም።
የሚኖረን ነገር ሁሉ (Existence) የራሱ የሆነ የማይቀየር ተፈጥሮ (dentity) ነው፡፡ ብረት ሁልጊዜ ብረት ነው - ከውሃ ጋር ሲገናኝ ይዝጋል፣ በተወሰነ መጠን ካርበንና ነሃስ ሲጨመርበት ይጠነክራል፣ 1500 ዲግሪ ሴንቲ ግሬድ በሆነ ሙቀት ይቀልጣል፤ ኃይል ሲጫነው ወደ ቆርቆሮነት ይለወጣል። ወይም ሽቦ ይሆናል ወዘተ... ። ብረት እስካለ ድረስ ዝንተ ዓለም ተፈጥሮው ይሄው ነው። እንጨት፣ ውሃ፣ ድንጋይ፣ እስካሉ ድረስ የማይቀየሩ ተፈጥሮ ናቸው፤ በምኞት የማይቀየሩ ባህርያት።
አየን ራንድ እንዲህ ትላለች፦
To be is to be something !
በሌላ እይታ ተፈጥሮ የሌለው ተፈጥሮ የለም እንደማለት ይሆናል። መሆን ማለት፣ የሆነ ነገር መሆን ነው፡፡ የአዕምሮ ስራ ደግሞ ማወቅ ብቻ ነው። ተፈጥሮን መፍጠር፣ መቀየር ፣ መለወጥ አይችልም ይላል የኦብጀክቲቪዝም ፍልስፍና መሠረታዊ እሳቤ።