Wegagen Bank
17.3K subscribers
2.91K photos
125 videos
2 files
1.84K links
Offcial Page
Download Telegram
የወጋገን ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ እና ማኔጅመንት ከከፍተኛ ባለአክሲዮኖች ጋር በባንክ ኢንዱስትሪው እየተከሰቱ ባሉ ለውጦች ዙሪያ ውይይት አካሄዱ

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 7 ቀን 2017 ዓ.ም
የወጋገን ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ እና ማኔጅመንት በባንክ ኢንዱስትሪው እየተከሰቱ ያሉ ፈጣን ለውጦች በባንኩ አፈፃፀም ላይ የሚያስከትሉትን ተግዳሮቶች በመቋቋም እና መልካም እድሎችን በመጠቀም ባንኩን ለማሳደግ እና በዘርፉ ተወዳዳሪ ሆኖ እንዲቀጥል ለማስቻል እየተከናወኑ ያሉ ተግባራትን አስመልክቶ ከከፍተኛ ባለአክሲዮኖች ጋር የግማሽ ቀን የምክክር መድረክ በስካይ ላይት ሆቴል አካሄዱ፡፡
በምክክር መድረኩ ላይ በባንክ ኢንዱስትሪው እየተከሰቱ ባሉ አጠቃላይ ነባራዊ ሁኔታዎች ዙሪያ ለባለአክሲዮኖች ገለፃ የተደረገ ሲሆን የካፒታል ገበያ ስርዓት መጀመር፣ የውጪ ባንኮች ወደ አገር ውስጥ መግባት እና ብር ከውጭ ምንዛሬ አንፃር ያለው ዋጋ በገበያ እንዲተመን መደረጉን ጨምሮ አዳዲስ በወጡ የብሔራዊ ባንክ መመሪያዎች ዙሪያ ማብራሪያ ተሰጥቷል፡፡ በተመሳሳይም የባንኩ የ2023/24 በጀት ዓመት አፈፃፀም እንዲሁም የ2024/25 የመጀመሪያ ሩብ ዓመት አፈፃፀም ቀርቧል፡፡
በዕለቱ የቀረበውን ገለፃ ተመርኩዞ ሰፊ ውይይት የተደረገ ሲሆን በቀጣይም ባንኩ በዘርፉ ተወዳዳሪ ሆኖ እንዲቀጥል ለማስቻል ካፒታል ማሳደግ፣ ሃብት ማሰባሰብ፣ የዲጂታል ባንክ አማራጮችን ማስፋፋት፣ የባንኩን የብድር አሰባሰብ እና ትንተና ማጠናከር፣ የደንበኛ እርካታ ማሳደግ፣ የሰለጠነ የሰው ኃይል ማፍራት እንዲሁም ገቢ እና ትርፍን ማሳደግ ላይ ትኩረት ተሰጥቶ እንደሚሰራ ተገልጿል፡፡
ወጋገን ባንክ ሸሪዓውን ተከትሎ በሚሰጣቸው የተለያዩ ከወለድ ነፃ የቁጠባ ሂሳብ አገልግሎቶች፣ ቆጥበው ትርፍ በሚጋሩባቸው ሙዳረባህ የቁጠባ ሂሳብ፣ ሙዳረባህ የኢንቨስትመንትና ሙዳረባህ የጊዜ ገደብ ተቀማጭ የሂሳብ ዓይነቶች እንዲሁም የሙራባሃ ፋይናንሲንግ እና ከፋላ የዋስትና አገልግሎቶች ዛሬውኑ ወደሚቀርብዎ የባንካችን ቅርንጫፍ በመሄድ የአገልግሎቱ ተጠቃሚ እንዲሆኑ እንጋብዝዎታለን፡፡
#WegagenBank #Amana
Follow us and get more information...
https://linktr.ee/WegagenBank
ጉዳይሽ ሰምሮ ማጀትሽ እንዲሞላ እፎይ የምትይበት እኛ ጋር አለ መላ

ወጋገን ባንክ በእፎይታ ዲጂታል የብድር አገልግሎት በጥቃቅን፣ አነስተኛ እና መካከለኛ ንግድ ስራ ላይ ለተሰማሩ ሴቶች መለኛ እና እድገት የተሰኙ  የስራ ማስፋፊያ ብድሮችን ያዘጋጀ መሆኑን እያበሰረ በአገልግሎቱ እንድትጠቀሙ  ይጋብዛል፡፡
የእፎይታ ዲጂታል ብድር ተጠቃሚ ለመሆን በቅድሚያ በወጋገን ሂሳብ ከፍተው እፎይታ መተግበሪያን ከኘሌይ ስቶር በማውረድ በአምስት ቋንቋ አማራጮች  አገልግሎቱን ማግኘት ይችላሉ፡፡

Download now:👉 https://play.google.com/store/apps/details?id=com.qena.efoyta

#WegagenBank #bank #EmpoweringWomenEntrepreneurs #Efoytawegagen #DigitalLending
የወጋገን ባንክ ንጋት፣ አጋር እና አማና ካርዶችን በመጠቀም ጊዜ ሳይገድብዎ ሂሳብዎን በቀላሉ ያንቀሳቅሱ ፣ግብይትዎን ያቀላጥፉ፡፡

ለተጨማሪ መረጃ በ866 ነፃ የስልክ መስመር ወደ ደንበኞች ግንኙነት ማዕከል ይደውሉ፣ ይስተናገዱ:: 
#WegagenBank #CardBanking
Follow us and get more information...
https://linktr.ee/WegagenBank
ወጋገን ባንክ በአሜሪካ ኢንተርፕነር መፅሄት ልዩ ሽፋን ተሰጠው

የወጋገን ባንክ ዋና ስራ አስፈፃሚ አክሊሉ ውበት (ዶ/ር) ከታዋቂው የኢንተርፕነር መፅሄት እና ዌብሳይት አዘጋጅ ጋር ባደረጉት ሰፊ ቆይታ፣ ባንኩ ከምስረታ ጀምሮ ያሉ የባለድርሻ አካላት ሚና፣ የባንኩን ካፒታል ዕድገት፣ የሰው ሀይል እና የቴክኖሎጂ ልህቀት እንዲሁም ለውጭ ሀገር ዲያስፓራ እና ድርጅቶች ከባንኩ ጋር ለመስራት የሚያስችሉ ምቹ ሁኔታዎችን ገልፀዋል።

የቃለ መጠይቁን ዝርዝር መረጃ ከስር የተቀመጠውን ሊንክ በመጫን ይመልከቱ
https://assets.entrepreneur.com/static/4_Entrepreneur_International_Spotlight_Wegagen_Bank_ET_SeptOct_2024.pdf