WeeMuslims
128 subscribers
502 photos
373 videos
9 files
733 links
⚫️ የስኬቶች ሁሉ መሠረት አላህን ማስታወስ ሲሆን የውድቀቶች ሁሉ ሰበብ አላህን መርሳት ነው።
Join 👇👇
Download Telegram
Forwarded from DEEN MODE
«አብዛሃኛዎቹ ሰዎች የጠፉት የሰዎችን ወቀሳ በመፍራትና ሙገሳቸውን በመሻት መሆኑን አውቃለሁ። ሁሉም እንቅስቃሴያቸው የሰዎችን ውደታ በሚገጥም መልኩ ሆነ፤ ሙገሳቸውን መሻትና ወቀሳቸውን መፍራት! ይህ ከአጥፊ ነገሮች መካከል ነው። መታከም ይገባዋል።»

ኢብኑ_ቁዳማህ ረሒመሁሏህ


📚 مختصر منهاج القاصدين【212】
Forwarded from DEEN MODE
قُلْ إِنِّي أَخَافُ إِنْ عَصَيْتُ رَبِّي عَذَابَ يَوْمٍ عَظِيمٍ
(سورة الأنعام)
ጌታችን ያዘጋጀልንን ነገር ብናውቅ ለመሶበር  ባልተቸገርን ነበር🥹

ኢላሂ .. እየጠበቅንህ ነው❤️‍🩹


https://t.me/WeeMuslims
👌2
عيدكم مبارك وكل عام وانتم بألف خير وصحة وسلامة وعافية 🎊🎉
احبابي😊

🖋 እየሰራው ባልሆነ ነገር ላይ እራሱ ሆኖ ቢመክረህ ምክሩ እውነተኛ እስከሆነ ድረስ ጠቀበለው Habibi ሰለሌላው ማንነቱ አያገባህም 🙌


«የተናጋሪውን ሰው ማንነት ሳይሆን የሚነገረውን መልዕክት ልብ ብለህ አስተውል »

(አልይ ኢብን አቢ ጣሊብ)😊


#عبدالحفظ_عمر
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
1
« ፀሀይ የተውበትን ያህል አታበራም። ፀሀይ ብርሀኗ ውስጥ ማቃጠል አለው፣ ተውበት ግን አያቃጥልም፣ ይልቁኑ ምንም በማይጎረብጥ መልኩ ይሞቃል፣ ያሞቃል። የፀሀይ ብርሀን የሚደርስበትን የርቀት መጠን የሰው ልክ ተመራምሮ ሊያውቅ ይችላል። ተውበት ግን ረቂቅ ነው የሚደርስበትን ርቀት ከአላህ በቀር ማንም አያውቅም! ፀሀይ ልብ ውስጥ አትበራም። ተወበት ግን ሁሉም ነገር በሚመሰጠርበትና አላህ ብቻ በሚመለከተው ልብ ውስጥ በርቶ ሰዎች መመልከት በሚችሉት ገፅታ ላይ ይንፀባረቃል። ፀሀይ እጅ የምትሰጥለት ጽልመት አለ፣ ተውበት ግን ድል የማያደርገው አንድም ጽልመት የለም።
በምንም ነገር ውስጥ አልፈው፣ በስተመጨረሻ ወደ አላህ ተመልሰው ንፅህናን በደረቡ፣ ውበትን በጨመሩ፣ በመልካሙ መንገድ ላይ በፀኑ ላይ ሁሉ የአላህ ሰላም ይስፈን። »
[ አብዱልሀኪም ሰፋ ]
:
@Venuee13
አሥሩ የዚልሂጃ ቀናት- ከዱኒያ ቀናቶች ሁሉ በላጮች

ይህን ጠቃሚ ትምህርት ሼር በማድረግ ላልደረሰው እናዳርስ

ከዱኒያ ቀናቶች ሁሉ እጅግ በላጮች የሆኑት የመጀመሪያዎቹ አሥሩ የዚልሂጃ ወር ቀናት ናቸው። እነሆ እነኚህ ምርጥ ቀናት ከፊት ለፊታችን ተደቅነዋል። ለዚህም ይመስላል ሙስሊሙ የአላህን ቤት ከዕባን ለመጎብኘት ያለው ጉጉቱ ድንበር አልፏል፤ በከዕባ ዙሪያ ጠዋፍ ለማድረግ፣ በሶፋና መርዋ መካከል ለመሮጥ እና ዐረፋ ላይ ቆሞ አላህን ለመለመን ያለው ስሜት ጣሪያ ነክቷል። የታላቁን ነቢይ መስጅድ መስጅደ-ነበዊን ለመጎብኘትና በመስጅዱ ውስጥ በተከበረው ቦታ ረውደቱ ሸሪፋ ላይ ለመስገድ ያለው መነሣሣት ውስጥን ይነቀንቃል፤ በሀሣብ ያምሣል፣ ክንፍ ቢኖር “ምነዋ ወደዚያ ወደተቀደሰው ምድር በበረርኩ!” ያስብላል።

ወዳጆቼ! እኛስ እነኚህ እጅግ የተባረኩና የተከበሩ ቀናቶች ከያዙት ምንዳ ለመቋደስ ምን ማድረግ እንችል ይሆን?

አላህ ሱብሃነሁ ወተዓላ ዘወትር በትእዛዙ በመገኘት ለቋሚው ሀገራቸው ለሚሰንቁ መልካም ባሮቹ በነኚህ በተባረኩ ቀናት ውስጥ ምን ዓይነት ትልቅ ምንዳ ይሆን ያዘጋጀላቸው?

የዚልሂጃ ወር የመጀመሪያዎቹ አሥር ቀናት ታላቅነት

1. አላህ ሱብሃነሁ ወተዓላ የማለባቸው ቀናት መሆናቸው

አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ አለ

وَالْفَجْرِ ﴿١﴾ وَلَيَالٍ عَشْرٍ ﴿٢﴾ وَالشَّفْعِ وَالْوَتْرِ ﴿٣﴾

“በጎህ እምላለሁ። በዐሥር ሌሊቶችም። በጥንዱም በነጠላውም።” (አል-ፈጅር 89፤ 1-3)

ከጃቢር ኢብኑ ዐብዱላህ (ረ.ዐ) እንደተዘገበው የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እነኚህ አሥር ቀናቶች የትኞቹ እንደሆኑ በሚያመላክተው ሀዲሣቸው ውስጥ እንዲህ ብለዋል፡-

العشر عشر الأضحى، والوتر يوم عرفة، والشفع يوم النحر

“አሥሩ ማለት አሥሩ የአድሃ ቀናት ናቸው። ‘ወትር’ /ጥንዱ/ የተባለው የዐረፋ ቀን ሲሆን ‘ሸፍዕ’ /ነጠላው/ ማለት ደግሞ የነህር /የእርዱ/ ቀናት ናቸው።” ብለዋል። ሀዲሱን ኢማም ነሣኢ እና ሃኪም በሙስሊም መስፈርት መሠረት ሰሂህ ትክከለኛ ሀዲስ ነው ብለውታል።

ኢማም በይሀቂ ከዐብዱላህ ኢብኑ ዙበይር እንደዘገቡት ደግሞ:-

ليالٍ عشر، العشر الثماني، وعرفة، والنحر

“አሥርቱ ሌሊቶች የመጀመሪያዎቹ ስምንቶቹ፣ የዐረፋ ቀን እና የእርድ ቀን ናቸው።” ብለዋል።

2. እነኚህ ቀናት “አያም መዕሉማት” /የታወቁ ቀናት/ም ይባላሉ

ይህም በሚከተለው የቁርዓን አንቀፅ ውስጥ የተጠቀሠ ነው።

وَيَذْكُرُوا اسْمَ اللَّهِ فِي أَيَّامٍ مَّعْلُومَاتٍ [٢٢:٢٨]

“በታወቁ ቀኖችም ውስጥ የአላህን ስም ያወሱ ዘንድ” (አል-ሀጅ 22፤ 27)

“የቁርዓን ተርጓሚ” በመባል የሚታወቁት ታላቁ ሰሃባ ዐብዱላህ ኢብኑ ዐባስ እነኚህ ቀናት “አሥርቱ ቀናት” ናቸው ያሉ ሲሆን በነኚህ ቀናት ውስጥ ታላቁን ጌታ አላህ ሱብሃነሁ ወተዓላን በብዛት ማውሳት የተወደደ ነው።

3. ከዱኒያ ቀናቶች ሁሉ በላጮቹ

ይህም በሚከተለው ሀዲስ ውስጥ ተነግሯል። ከጃቢር (ረ.ዐ) እንደተዘገበው የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡-

أفضل أيام الدنيا أيام العشر، يعني: عشر ذي الحجة، قيل: ولا مثلهن في سبيل الله؟، قال ولا مثلهن في سبيل الله إلا رجل عفر وجهه في التراب، وذُكر عرفة، فقال يوم مباهاة ينزل الله تبارك وتعالى إلى سماء الدنيا، فيقول: عبادي شعثًا غبرًا ضاحين، جاءوا من كل فجٍّ عميق يسألون رحمتي، ويستعيذون من عذابي ولم يروا، فلم نر يومًا أكثر عتيقًا وعتيقة من النار

“ከዱኒያ ቀናቶች ሁሉ በላጮቹ አስሩ ቀናት ናቸው። ማለትም አሥሩ የዚልሂጃ ቀናት። በአላህ መንገድ ላይ መውጣትም ቢሆን የነሱ አምሣያ የለምን? ተብለው ተጠየቁ። እርሳቸውም ‘በአላህ መንገድ ላይም ቢሆንም እነሱን የሚመስል የለም። ፊቱ ከአፈር የተገናኘ ሰው (በአላህ መንገድ ላይ የሞተ) ሲቀር።’ አሉ። ስለ ዐረፋም ተወሳና መልእክተኛው (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ ‘እሱ የሙባሃት /አላህ በባሮቹ የሚኩራራበት/ ቀን ነው። አላህ ወደ ቅርቢቱ ዓለም ይወርድና ባሮቼ ተንጨፋረው፣ አቧራ የለበሱ ሆነውና ተጎሣቁለው እሩቅ ከሆነ አቅጣጫ ሁሉ እዝነቴን ሊጠይቁ እሷን ያላዩ ሲሆን ከእሣቴም በኔ ሊጠበቁ መጡ። ወንድም ሆነ ሴት በብዛት ከእሣት ነፃ የሚወጡበት እንዲዚህ ቀን አላየንም’።” (በዛር ሀዲሱን ዘግበውታል)

4. በርካታ የሀጅ ሥራዎች የሚሠሩት በነኚህ ቀናት ውስጥ ነው

ከነኚህም መካከል የዚልሂጃ ስምንተኛ ቀን በሙዝደሊፋ ይታደራል፤ በዘጠነኛው ቀን በዐረፋ ላይ ይቆማል፤ ከዚህም በተጨማሪ ለመስዋእት የሚሆን እንሠሳት መንዳት፣ ጠጠር መወርወር፣ ፀጉር መላጨት አሊያም ማሣጠር፣ በዚልሂጃ አሥረኛው ቀን ጠዋፍ ማድረግንና የመሳሰሉትን ያጠቃልላል።

5. የአምልኮ ዘርፍ የሆኑት ዋና ዋናዎቹ የሚሰበሰቡባቸው ቀናቶች ናቸው

ኢማም ሃፍዝ ኢብኑ ሀጀር ፈትሁልባሪ በተሠኘው ታዋቂ ኪታባቸው ውስጥ እንዲህ ይላሉ

والذي يظهر أن السبب في امتياز عشر ذي الحجة لمكان اجتماع أمهات العبادة فيه، وهي الصلاة والصيام والصدقة والحج، ولا يتأتى ذلك في غيره

“የዚልሂጃ አሥርቱ ቀናትን ለየት ከሚያደርጉ ነገሮች መካከል ቦታው ከአምልኮ ተግባራት ዋና ዋና የሚባሉት በአንድ ላይ ተሰባስበው የሚሠሩበት መሆኑ ነው። ይሀውም ሰላትን፣ ፆምን፣ ሰደቃን (ምጽዋትን) እና ሀጅን ያጠቃልላል። ከነኚህ ቀናት ውጭ እነኚህ ሁሉ ነገሮች አንድ ላይ የሚሰባሰቡበትን አጋጣሚ አናገኝም።” (ፈትሁልባሪ ቅጽ 2፣ ገጽ 462)

በነኚህ ቀናት ውስጥ ከሚወደዱ ሥራዎች መካከል

1. ሐጅና ዑምራ ማድረግ

በነኚህ ቀናት ውስጥ የሚሠሩ ምርጥ የአምልኮ ሥራዎች ናቸው። ምክኒያቱም የነኚህ አምልኮ ሥራዎች ትክክለኛ ወቅቱ ይህ ነውና። ከአቢሁረይራ (ረ.ዐ) እንደተዘገበው የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ)እንዲህ አሉ:-

العمرة إلى العمرة كفارة لما بينهما، والحج المبرور ليس له جزاء إلا الجنة

“አንደኛው ዑምራ እስከ ሌላኛው ዑምራ በመካከላቸው የተሰራ ወንጀልን ያብሣል፤ መብሩር /የተሟላ/ የሆነ ሀጅ ምንዳው ጀነት ብቻ እንጂ ሌላ አይደለም።” (ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል)

2. በበጎ ሥራዎች ላይ መበርታት

ከዐብዱላህ ኢበብኑ ዐባስ (ረ.ዐ) እንደተዘገበው የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ፡-

ما مِن عمل أفضل من عمل فى هذه الأيام العشر، قالوا: ولا الجهاد؟ قال ولا الجهاد إلا رجل خرج بماله ونفسه فلم يرجع منه بشيء

“በነኚህ አሥር ቀናት ውስጥ የሚሠራ ሥራን የሚበልጥ ምንም የለም። ‘ጅሃድም ቢሆን?’ አሏቸው። እርሣቸውም ‘አዎን ጅሃድም ቢሆን ገንዘቡንና ነፍሱን ይዞ ወጥቶ ያልተመለሰ ሰው ብቻ ሲቀር።’ አሉ።” (ኢማም አህመድና ቱርሙዚ ዘግበውታል)

እንዲሁ በሌላ ዘገባም:-

لا تطفئوا سرجكم ليالي العشر

“በአሥርቱ ቀናት ለሊቶች ውስጥ መብራታችሁን አታጥፉ።” የሚል ዘገባ የመጣ ሲሆን ይህም ትርጉሙ “በነኚህ ቀናት ውስጥ ቁርዓን ቅሩ፣ በሰላትም በርትታችሁ ቁሙ ለማለት ነው” ተብሏል።

3. ዚክር ማብዛት
🥰1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
اللهم إني ظلمت نفسي ظلماً كثيراً ولا يغفر الذنوب إلا انت فاغفرلي مغفرة من عندك وارحمني إنك أنت الغفور الرحيم

يا رب، إننا نرجع إليك بعد ذنوب كثيرة، فارحمنا.🤲
https://t.me/WeeMuslims
👍1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
القارئ جابر القيطاني سورة الرحمن

ربي ارحمني يوم لا ينفع مال ولا بنون🤲

https://t.me/WeeMuslims
🥰1
This media is not supported in the widget
VIEW IN TELEGRAM
📚 የ2026 የክረምት የደርስ መርሃ-ግብር 📚

​"ታዳጊ ወጣቶችን በኢስላማዊ እውቀት በማነፅ፣ አርአያ የሚሆን ስነ-ምግባር ያላቸው ሰብዕናዎችን መገንባት!"

​አሰላሙዓለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱህ 👋

​ውድ የሀይስኩል ተማሪዎች እና ወላጆች፤ የዘንድሮውን የክረምት እረፍት ጊዜያችሁን በዒልም የምታደምቁበት፣ እውቀታችሁን የምታሳድጉበትና ከዘመኑ ፈተናዎች ራሳችሁን የምትጠብቁበት ታላቅ የደርስ መርሃ-ግብር በኹለፋኡ ራሺዲን መስጂድ ተዘጋጅቶ ይጠብቃችኋል።
📌 በፕሮግራሙ የሚሰጡ ዋና ዋና ደርሶች እና ኡስታዞች፦

🛡️ ዓቂዳ (እምነት): ዓቂደቱል ዋሲጢያህ በኡስታዝ አብዱረሂም ግራኝ

⚖️ ፊቅህ : መባዲኡል ፊቅህ በኡስታዝ ሳዲቅ ሁሴን

​​⚖️ ፊቅህ(በኦሮምኛ) ሰፊነቱ ነጃህ በኡስታዝ አብዱረህማን

💖 ተዝኪየቱ ነፍስ (ስነ-ምግባር):  ሙኽተሰር አዳእ ወደዋእ በኡስታዝ አብዱረህማን ኸድር

📜 ቃኢደቱ ኑራኒያ : በኡስታዝ ዚያድ ሚፍታህ

🎤 ልዩ ወቅታዊ የውይይት መድረኮች (ከተጋባዥ እንግዶች ጋር)፦

ከወንድም አፖሎጀቲክስ ኢብራሂም ጋር
​"(ንፅፅር) ክርስትና በእውነት ሚዛን"

ከኡስታዝ ቃልአሚን ፀጋዬ ጋር
​"የዘመኑ ርዕዮተ በኢስላም አውድ"

📅 የፕሮግራሙ ዝርዝር መረጃ፦

🗓️ የሚቆይበት ጊዜ: ከሐምሌ 1 እስከ ነሐሴ 30 ቀን 2026 ዓ.ም
ሰዓት: በየቀኑ ከሰዓት ከ 10:00 - 12:00
📍 ቦታ: ኹለፋኡ ራሺዲን መስጂድ(ድሬ ዳዋ)

📝 የመመዝገቢያ ሊንክ:-
https://forms.gle/RkFg8jZeSsrHoAom7

📞 ለበለጠ መረጃና ምዝገባ በእነዚህ ስልኮች ያግኙን፦
📱 +251920696464 (@professor_mu)
📱 +251902899242 (@Adu_garip5)

የቴሌግራም ግሩፓችንን ይቀላቀሉ:-
https://t.me/winterforilm

🏆 ማሳሰቢያ
​በፕሮግራሙ ማጠናቀቂያ ላይ ደርሱን ላጠናቀቁ ተማሪዎች በሙሉ የምስክር ወረቀት (ሰርተፍኬት) ያዘጋጀን ሲሆን፤ በጥሩ ውጤት ለጨረሱ ተማሪዎች ደግሞ ልዩ ሽልማት አዘጋጅተናል።

🌟 ይህንን ሁሉ የምትረከቡት በክብር እንግድነት ከሚመጡት ከመጅሊስ ኡስታዞች እጅ የሚሆን ይሆናል!
♻️ አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱሁ

🔔 የአድስ ደርስ ማስታወቂያ

📒 የትምህርት ቤቶች መዘጋትን ተከትሎ ተማሪዎች የክረምት እረፍታቸውን በጠቃሚ የዲን እውቀት ላይ እንዲያሳልፉ ኡስታዛችን ልዩ የክረምት ኮርስ አዘጋጅቶላችኋል።

📖 አዲስ የሚጀመረው ደርስ ሁለት አይነት ኪታቦችን ያካተተ ሲሆን ስማቸውም [الموطأ في الإعراب] እና [ نظم الورقات للعمريطي ] በመባል የምታወቁ የሆኑ ክታቦች ናቸው

🔖  በኡስታዝ :- አብዱረሒም ግራኝ አላህ ይጠብቀው

📆 ደርሱ የሚጀመረው [የፊታችን ሰኞ ነው ]

ደርሱ የሚሰጥበት ሰዓት [ከመግሪብ---ኢሻዕ]

🕌 ቦታ:- አሸዋ ቢላል መስጂድ[ ድሬዳዋ

🛑 ለነባርም ሆነ ለአዳዲስ ተማሪዎች:
ይህ የትምህርት እድል ለሁሉም ክፍት ነው። አዳዲስ መማር የምትፈልጉ ተማሪዎች ካላችሁ ከመጀመሪያው ቀን ጀምራችሁ እንድትገኙ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።
የክረምት ጊዜን በኸይር ስራ እናሳልፍ!

👉 መልዕክቱ ለሌሎች እንዲደርስ ሼር ያድርጉ ! #ባረከሏህፊኩም

🌱 « አላህ መልካም የሻለት ሰው ዲኑን(እምነቱ) ያስገነዝበዋል ። » (ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል )

ወሰላሙ አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱሁ

👇 👇 👇

https://t.me/abdurehimgragn
احبابي gn

⚫️ልክ ጥዋት እስፖርት ዜና አያለው ብለህ በሌላም video እዝናናለው ብለህ ስልክህን ስትከፍት

⚫️አከሌ. ባልታወቀ ምክንያት አክስቱን ቆራርጦ ገደላት

⚫️አከሌ. ባልታወቀ ምክንያት እህቱን በአሰቃቂ ሁኒታ ገደላት

⚫️እንተናን *** ገደላት

⚫️አባቱን ለዘመኑ ቢዝነስ ስራ አትመጥንም ብሎ ገደለው

⚫️እናቱን . ባልታወቀ ምክንያት በአሰቃቂ ሁኒታ ገደላት

ምን ጉድ ነው ቆይ ምንድ ነው የምንሰማው በአላህ እእእ ወላጆች ግን ስለ ልጆቻቹ ምን ታስባላቹ ልጆቻቹን በዲን ላይ አንጿቸው walahi የቂያማ ቀን እኮ  ከባድ ጥያቄ አለባቹ   ነብያችን 🕋

قال 🕋  كُلُّكُمْ رَاعٍ، وَكُلُّكُمْ مَسْؤُولٌ عَنْ رَعِيَّتِهِ

ሁላችሁም እረኞች (ኃላፊዎች) ናችሁ እያንዳንዳችሁም በተሰጣችሁ ኃላፊነት ላይ ትጠየቃላችሁ

⚫️እንኳን በልጆቻቹ አይደለም እና በምትበሉት ምግብ እራሱ እንደምትጠየቁ እንዳረሱ

﴿ثُمَّ لَتُسْأَلُنَّ يَوْمَئِذٍ عَنِ النَّعِيمِ﴾

🤲 ጌታዬ walahi ለአንተ ፍቅር ኖሮን ሳለ ከአንተ አታርቀን

#عبدالحفظ_عمر
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
« በሰው ሀዘን ድንበር አይታለፍም ነውር ነው። ያጣ ሰው፣ የሚወደውን የተለየ ሰው በትኩስ ሀዘኑ ላይ ስለተለየው ሰው ፍፃሜ ማማር ማውጋት አላዋቂነት ነው። ሰውየው እኮ ጎድሎበታል፣ ናፍቆትና ትዝታ እየጠበሰው እየተሰቃየ ባለበት ገና ከሀዘኑ ሳይላቀቅና ሳይሰክን መልካም የመሰለንን ነገር ሁሉ መቀደድ ይበልጥ ያደማዋል። ስድ አፅናኞች እረፉ፣ የተገኝቻለሁ ስደተኞች በሀዘንተኞች ቁስል የመልካምነት ጎጆ ለመቀለስ ጠብ እርግፍ አትበሉ።
ምንም ነገር ካለቦታው ክብር የለውም! ሁሉንም መልካም የተባለን ነገር ሰውየው በትክክለኛው የአረዳድ አቅሙ ላይ መሆን አለመሆኑን ሳያስተውሉ መናገር አግባብ አይደለም። ከጎን መሆን፣ ዝምታን ማክበር፣ ሰውየው ደንዝዞ ባለበት ሲነቃ ብዙ የተመሰቃቀለ ነገር ኖሮ ይበልጥ ሀሳብ እንዳይገባው  ብክነትን ለመቆጣጠር መሞከር ፍቅርም፣ ክብርም የመልካም ምግባር መገለጫም ነው። »
[ አብዱልሀኪም ሰፋ ]
:
@WeeMuslims