ፍቅር ለምን ያስፈራል? ......
ፍቅር ሁልጊዜ ያስፈራል። አንድን ሰው ፍቅር ለምን እንደሚያስፈራው ምክንያቶች አሉ፡፡ ፍርሀቱ የሚመጣው ከያልነቃው የአእምሮ ክፍል ነው፡፡ እናም ሁሉም ብቃቶቻችሁ - ሁሉም ክህሎታችሁ ፣ ሁሉም እውቀታችሁ የሚገኙት በያልነቃው የአእምሮ ክፍል ውስጥ ነው፡፡
ፍቅር የሚመጣው ከያልነቃው የአእምሮ ክፍል ነው፡፡ እናም እንዴት ፍቅር ጋር መስመር እንደምትችሉ ፣ በፍቅር ምን እንደምታደርጉ ደግሞ አታውቁም፡፡ ፍቅር ደግሞ ህልቆ መሳፍርት የሆነ ክስተት ነው፡፡
ያልነቃው አእምሮ ከነቃው አእምሮ ዘጠኝ እጅ ይልቃል፡፡ ስለሆነም ከያልነቃው አእምሮ የሚመጣው የትኛውም ነገር ሊቋቋሙት በማይቻል መንገድ ታላቅ እና የሚያጥለቀልቅ ይሆናል፡፡ ለዚያ ነው ሰዎች ስሜቶችን የሚፈሩት፡፡ እነዚህ ስሜቶች ሰዎችን እንዲያመነቱ ያደርጓቸዋል፡፡ ስሜቶቹ ትርምስን ይፈጥራሉ ብለው ያስባሉ፡፡
ስሜቶችም ትርምስን ይፈጥራሉ ፤ ትርምስ ግን ውብ የሆነ ነገር ነው፡፡ ሥርዓት አስፈላጊ ነው ፤ ትርምስም እንዲሁ፡፡ ስርዓተ በሚያስፈልግ ጊዜ ሥርዓትን - የነቃው አእምሮን ተጠቀሙ። ትርምስ በሚያስፈልግ ጊዜም ያልነቃው አእምሯችሁን ተጠቀሙ፤ ትርምስ ይኖር ዘንዳም ፍቀዱ፡፡ ምልኡ ሰው፣ አጠቃላዮ ሰው ሁለቱንም የመጠቀም ብቃት አለው፡፡ ምልኡ ሰው የነቃው አእምሮ በያልነቃው አእምሮ ወይም ያልነቃው አእምሮ በነቃው አእምሮ አንዳች አይነት ጣልቃ እንዲገባ አይፈቅድም፡፡
በህይወት ምሉእነት ... በቀናቶቿ ፣ በሌሊቶቿ፣ በጸሃያማ ቀናቶቿ እና በዳመናማ ሌሊቶቿ .... እናምናለን፡፡ በህይወት ውስጥ ያለው እያንዳንዱ ነገር ዘና ሊባልበት ይችላል፡፡ የሚያስፈልጋችሁ ጥቂት ተጨማሪ ግንዛቤ ብቻ ነው፡፡ የሚያስፈልጋችሁ እየሆነ ባለው ነገር ላይ የበለጠ ንቃት ብቻ ነው፡፡
እናንተ አእምሮን አይደላችሁም፡፡ አካላችሁንም አይደላችሁም፡፡ በውስጣችሁ አእምሮን፣ ስሜቶችን፣ አካላዊ አጸፋዎችን ቀጣይነት ባለው ሁኔታ የሚመለከት ታዛቢ አለ፡፡ ምስክሩም/ታዛቢውም እናንተ ናችሁ፡፡ እናም አንድ ጊዜ እዚያ ማእከላችሁን እስካደረጋችሁ ድረስ ያ...ታዛቢ እያንዳንዱን ነገር ዘና ማለት ይችልበታል፡፡
አእምሯችሁ መከራ፣ ስቃይ ይሰማዋል፡፡ አእምሮ ሁሉም አይነት ስሜቶች፣ ተጣብቆዎች፣ ምኞቶች እና ጠንካራ ናፍቆቶች ይሰሙታል፡፡ እነዚህ ሁሉ ነገሮች ግን የአእምሮ ነጸብራቅ ናቸው፡፡
ከአእምሮ ባሻገር የትም የማይሄደዉ እውነተኛ ማንነታችሁ አለ። ይሄ ማንነታችሁም ሁልጊዜ እዚህ እና እዚህ አለ።

👍1
አፍቅሩ - አትፍሩ::
አነሰም በዛም የእያንዳንዱ ሰው ህይወት የሚገዛው በፍርሃት ነው፡፡ ምክንያቱም ሁለት የመኖሪያ መንገዶች ብቻ ስላሉ ነው፡፡ አንድም ህይወት በፍቅር ልትገዛ / ልትመራ ትችላለች አልያም ደግሞ በፍርሃት የተገዛች ትሆናለች፡፡ ተራ በሆነው መንገድ ለማፍቀር ካልተማራችሁ በስተቀር ህይወታችሁ በፍርሃት የተመራ ይሆናል፡፡
ከፍቅር ውጪ ፍርሃት መኖሩ ግድ ነው፡፡ ፍርሃት የፍቅር አለመኖር ነው፡፡ ፍርሃት በውስጡ አንዳችም አዎንታዊ ነገር የለውም፡፡ ፍርሃት በቃ የፍቅር እጦት ነው፡፡ ነገር ግን ማፍቀር ከቻላችሁ ፍርሃት ይጠፋል፡፡ በፍቅር ቅጽበት ውስጥ ሞት እንኳን አይኖርም፡፡
በህይወት ውስጥ ካሉ ነገሮች ሞትን በብቸኝነት ሊያሸንፈው የሚችለው ነገር ፍቅር ብቻ ነው፡፡ ሁሉም ፍርሃት የሚያጠነጥነው በሞት ላይ ነው እናም ሞትን ሊያሸንፈው የሚችለው ነገር ደግሞ
ፍቅር ብቻ ነው፡፡
ስለዚህ ማለት የምፈልገው አንድ ነገር ለፍርሃት ብዙም ትኩረት አትስጡት ነው፡፡ ምክንያቱም ፍርሃቱ ግላዊ ሰመመን ይሆናል፡፡ በፍርሃት መኖራችሁን በቀጠላችሁ ቁጥር ፣ ህይወታችሁ በፍርሃት የሚገዛ መሆኑን በቀጠለ ቁጥር በፍርሃት ተጽእኖ ይደረግባችኋል። ከዚያ በኋላም ፍርሃትን የበለጠ ትረዱታላችሁ፡፡ ይህንን ልብ በሉ - ህይወታችሁ በፍርሃት የታጠረ መሆኑን እወቁ - አለቀ! ይህ ማለት ፍርሃት ይጠፋ ዘንዳ ፍቅር በበቂ ሁኔታ ሃያል አልሆነም ማለት ነው፡፡
ፍርሃት የበሽታ ምልክት እንጂ በራሱ በሽታ አይደለም፡፡ በሽታ ስላልሆነ ሊፈወስ አይችልም፡፡ ፈውስም አያስፈልገውም፡፡ ስለዚህ ፍርሃት ምልክት ነው እናም ምልክቱም በጣም ጠቃሚ ነው፡፡ ይህ ፍርሃትም ህይወታችሁን ማባከን እንደሌለባችሁ ያሣያል፡፡ ይህ የሚናገረው ብዙ ማፍቀር እንዳለባችሁ ነው።
ስለዚህ ስለ ፍርሃት አላወራም፡፡ የበለጠ አፍቃሪዎች ትሆኑ ዘንዳ እረዳችኋለሁ ፍርሃትም እንደ ውጤት ይጠፋል፡፡ በፍርሃት ላይ ቀጥታ መስራት ብትጀምሩ ፍርሃትን በይበልጥ ታጠናክሩታላችሁ የዚህ ምክንያቱም መላው ጥሞናችሁ በፍርሀት ላይ ስለሚያተኩር ነው፡፡ ይህም አንድ ሰው ጨለማን ለማጥፋት
እንደሚሞክረው አይነት ነገር ነው፡፡ ጨለማን በቀጥታ ማጥፋት አትችሉም፡፡ ምክንያቱም በመጀመሪያ ደረጃ ጨለማ የሚባል ነገር የለም፡፡ጨለማ እንዳለ ያለውን እውነታ እወቁት እና እንዴት ብርሃንን በማምጣት ጨለማን ማጥፋት እንደሚኖርባችሁ እወቁ፡፡
ፍርሃትን ለመዋጋት የምትጠቀሙት ተመሣሣዮ ሃይል ፍቅርን ለማሣደግ መጠቀም ይቻላል። ብዙ ጥሞናን ለፍቅር ስጡ፡፡ ስትነኩ ልክ መላው ሰብዓችሁ በእጃችሁ ውስጥ እየፈሰሰ እንደሆነ በሚሰማ ሁኔታ በሚቻለው መጠን በፍቅር ንኩ፡፡ ሃይል በእጃችሁ ውስጥ በመፍሰስ ሲያልፍ የሚሰማችሁ ይሆናል፡፡ ፍቅር የምትሰሩ ከሆነ ሁሉንም ስልጣኔ እርሱት እና የዱር ሁኑ። ስለፍቅር የተማራችሁትን ሁሉም ነገር እርሱት:: አንድ ጊዜ የፍቅር መኖር የፍርሃት መጥፋት መሆኑን ካወቃችሁ ነገሩ ገብቷችኋል ማለት ነው፡፡ እናም ምንም ችግር አይኖርም፡፡
የሰው ልጅ በፍርሃት ውስጥ በሚኖር ጊዜ ጠጣር ይሆናል፡፡ ይህን ጠጣርነት የሚፈጥረው ፍርሃት ነው፡፡ በፍርሃት ውስጥ ስንሆን ሁሉንም በሮች እና መስኮቶች እንዘጋለን፡፡ በጣም ትንሽ ፣ ጨለማ ጉድጓድ ውስጥ መኖር ጀምረናል፡፡ ህይወታችን ቀድሞውኑ ሞት ይሆናል፡፡ የተጠበቅን እንሆን ዘንዳ በዙሪያ ገባችን ጠንካራ ብረት የተሰራ ጥሩር / ጋሻ እንፈጥራለን፡፡
ይህ የህይወት መንገድ አይደለም፡፡ ይህ ራስ የማጥፊያ መንገድ ነው፡፡ ይህ እውነተኛው ራስ ማጥፋት ነው፡፡ ይህ ወደ መቃብራችሁ ውስጥ ገብታችኋል ማለት ነው፡፡ ምክንያቱም ይህ አይነቱ የተዘጋ ህልውና አንዳችም እውነትን፣ ውበትን፣ ፍቅርን፣ ቡራኬን፣ እግዚአብሔራዊነትን ማወቅ አይችልም፡፡ ምንም ነገር ለማስገባት ካልተፈቀደ ምን እንደከበባችሁ ልታውቁ ትችላላችሁ? እናም የከበባችሁ ምን እንደሆነ ካላወቃችሁ ራሳችሁን ፈጽሞ ማወቅ አትችሉም፡፡ አንድ ሰው ራሱን ማወቅ የሚችለው ከሌላው ሰው አንጻር ነው፡፡
የስነ-ልቦና ተመራማሪዎች እንደሚሉት -ህጻኑ በመጀመሪያ የሚያውቀው ሌሎችን ማለትም ፡- እናቱን፣ አባቱን፣ ወንድሞቹን፣ እህቶቹን፣ ቤተሰቡን፣ የከበቡትን ነገሮች፣ ክፍሉን፣ ግድግዳዎቹን፣ አሻንጉሊቶቹን ነው፡፡ ከዚያ በኋላ ቀስበቀስም በጣም እና በጣም እየቀረበ ይመጣል፡፡ ከዚያም አካሉን ማወቅ ይጀምራል፡፡ ከዚያም አንድ ቀን ራሱን እንደ ተነጠለ ግለሰብ ይሰማው ይጀምራል፡፡ በመጀመሪያ ሌላውን ያውቃል እናም ከዚያ በኋላ ራሱን ከሌላው በማነጻጸር ለራሱ ፍቺ ይሰጣል፡፡ ሌላውም ፍቺውን ይሰጣል፡፡
ነገሮችን የግሉ በማድረግ የሚኖር ሰው እውነተኛ ማንነቱን እያዉቅም፡፡ ምክንያቱም ይህ ሰው የሚኖረው በነገሮች ተከብቦ ነው እናም ሰዎች እናንተን ፍቺ የሚሰጧችሁ እንደ ነገር ነው፡፡ ሰዎች እናንተን እንደ ነፍስ ፍቺ ሊሰጧችሁ አይችሉም፡፡
አንድ ሰው በጥልቅ ፍቅር ውስጥ ብቻ ነው ነፍሱን ማወቅ የሚችለው ምክንያቱም በጥልቅ ፍቅር ውስጥ ሲሆን የሌላውንም ነፍስ የሚያውቅ ይሆናል፡፡ የሌላው ነፍስም በውስጣችሁ ምላሽን፣ ብቃትን ይፈጥራል፡፡ በድንገትም ከጊዜ እና ቦታ ባሻገር የሆነን አዲስ ልኬትን የምታውቁ ይሆናል፡፡

❤7👍1
Mastering Your mind & Thought
የተመስጦ ዋናውን ገጽታ የበለጠ እያሰላሰልክ ስትሄድ፤ አንተ አለቃ፣ አእምሮህ ደግሞ ባሪያ ይሆናል፤ ሁልጊዜም መሆን ያለበት እንደዚህ ነው። አእምሮ ማለቂያ በሌለው መከራ ውስጥ የሚያሳልፍህ አስፈሪ ጌታ ቢሆንም፣ በተወሰነ መንገድ ከያዝከው ግን የምትፈልገውን ማንኛውንም - ነገር ልታደርግበት የምትችል ድንቅ ባሪያ ይሆናል። በዚህ ጊዜ በደንብ ልትቆጣጠረው ትችላለህ
ማሰብ ከፈለግክ ማሰብ ትችላለህ፧ ማሰብ ካልፈለግክ ደግሞ አታስብም፡፡ መሆን የሚገባውም እንደዚህ ነው፡፡
አሁን እጄን ማንቀሳቀስ ከፈለግኩ እጄን አንቀሳቅሳለሁ፤ ካልፈለግኩ ደግሞ አላንቀሳቅስም፡፡ ሰውነትህ ሁልጊዜ ዝም ብሎ የሚንቀሳቀስ ፡ ከሆነ፣ እብድ እየሆንክ ነው ማለት ነው። በአእምሮህ ላይም ተመሳሳይ ነገር እየሆነ ከሆነ ማለትም ማሰብህን ማቆም እየፈለክ ደጋግመህ በማይረቡ ሀሳቦች ውስጥ የምተዘፈቅ ከሆነ ፣ ሰዎች ሊያዩት በቀላሉ ስለማይችሉ እብድ ሆኗል አትባልም እንጂ ፣በበቂ ሁኔታ ራስህን ስትመለከት ግን እያበድክ እንደሆነ ትገነዘባለህ።
አእምሮህ ተመስጦ አይወድም። መቀመጥና ማሰላሰል ስትፈልግ አእምሮህ ያንን እንዳታደርግ ሁሉንም ነገር ያደርጋል። በመጀመሪያ" ነገ ታደርገዋለህ” ይልሃል። “ነገ”t የአእምሮ ጥልቅ ማታለያ ነው።ነገ ደግሞ በፍጹም አይመጣም፡፡ ሰዎች በሕይወታቸው ውስጥ ሊያደርጓቸው የሚገቡ ብዙ ነገሮችን “ነገ” ብለዋል፡፡ ለራሳቸው ደስታ ሳይቀር “ነገ” ይላሉ፡፡
ለተመስጦ ወይም ለማሰላሰል ስትቀመጥ የአእምሮ “ነገ” የሚለው ዘዴ ካልትሳካና “አይ፣ ነገ አይሆንም፤ ዛሬ ለማድረግ ቆርጫለሁ” ካልክ፣ ሁለተኛ ዘዴውን ይሞክራል፡፡ ሳምንቱን ሙሉ ለማስታወስ ስትሞክር የነበረው የስልክ ቁጥር ድንገት ብልጭ ይልልህና ወደ ስልክህ ትሮጣለህ ተመስጦውም ያበቃል፡፡
ይህንንም - ከተቋቋምክና ወደ ስልኩ ሳትሮጥ ተመስጦህን ከቀጠልክ፣ በሁለት እና ሶስት ደቂቃዎች ደርዘን የሚሆኑ የተለያዩ የሰውነትህ ክፍሎች በድንገት ያሳክኩሀል፡፡ ለዚህ ምክንያቱ አእምሮ ሰውነት ከተረጋጋ እርሱም እንደሚረጋጋ ስለሚያውቅ ነው፡፡ አእምሮ ይህ እንዲሆን ከፈቀደ ደግሞ ባርያ እንደሚሆን ያውቃል፡፡
ራስህን ብታስተውል፤ ስትቆም፣ ስትቀመጥና ስትናገር ሰውነትህ ምን ያህል አላስፈላጊ እንቅስቃሴዎችን እንደሚያደርግ ታያለህ። ሕይወትህን ስትመለከት ምናልባት ከግማሽ በላይ ጊዜ የወሰዱት እነዚህ ነገሮች እንደሆኑ ትገነዘባለህ፡፡ በሰውነትህ ውስጥ አንተ ግድ የማትሰጣቸው ብዙ አላስፈላጊ ሀሳቦችና እንቅስቃሴዎች አሉ። ነገር ግን ሰውነት መረጋጋት ከቀጠለ፣ አእምሮም ቀስ በቀስ መርገብ ይጀምራል።
ይህን ማድረግ ከቻልክ፣ አእምሮ የሚያደርገውን የማያቋርጥ ሩጫ ገታህ ማለት ነው።እናም አእምሮ በድንገት የተለየና ድንቅ ባሪያ ይሆናል።

👍9
'የታጋቾች ሞት' ብሎ ብዙ ሺህ ኪሎ ሜትሮችን ሄዶ ስለ እስራኤል ከማውራት እዚሁ አማራ እና ኦሮሚያ ክልሎች ውስጥ እየተፈፀሙ ያሉ እገታዎች እና ግድያዎችን መዘገብ አይቀድምም?
ጎንደር ውስጥ ታግታ፣ ኋላም ትናንት ስለተገደለችው የ2 አመት ህፃን አልሰሙ ይሆን?

🕊15👍3❤1
የብቸኝነትና የባዶነትን ስሜት መጋፈጥ
በውስጣቸው ከራሳቸው ጋር ብቻቸውን የሆኑ፣ አዕምሮና ልባቸው ከብቸኝነት ስቃይ የፀዱ ሰዎች እውነተኞች ናቸው
አዝናኝና አስከፊ ነገር በሞላበት ዓለም ሁሉም ሰው ተሳታፊ ከመሆን ይልቅ ተመልካች መሆኑ አያስገርምምን? አብዛኞቻችን ትንሽ ነፃ ጊዜ ስናገኝ አንድ የሚያስደስተን ነገር እንፈልጋለን፡፡ ከተማ ውስጥ ከሆንን ቴሌቪዥን ወይም ሞባይል እንከፍታለን ወይም ወሬ እንጀምራለን፤ አለዚያም መፅሀፍ ወይ መፅሄት እናነሳለን፡፡ የመደነቅ የመዝናናት፣ ራሳችንን የመርሳት የማያቋርጥ ፍላጐት አለን፣ ብቸኝነትን፣ ጓደኛ ማጣትን፣ ሳይረበሹ መቆየትን እንፈራለን፡፡ ሳናወራ ወይም ሳንዘፍን በፀጥታ በመስክ ወይም በጫካ ውስጥ እየተራመድን ስለ ራሳችንና በውስጣችን ስላለው ነገር የምናስተውል ጥቂቶቻችን ነን፡፡ አብዛኞቻችን እንዲህ ማድረግ የሚሳነን ስልቹዎች ስለሆንን ነው፤ በመማር ወይም በማስተማር፣ በቤት ጣጣ ወይም በስራ ተጠምደናል፡፡ ስለዚህም ነፃ ጊዜ ስናገኝ በቀላሉ ወይም በከባዱ መደነቅን እንፈልጋለን፡፡ እናወራለን ወይም ወደፊልም ቤት እንሄዳለን - ወይ ወደ አንዱ ሃይማኖት እንዞራለን። ሃይማኖትም አንደኛው ዓይነት ከስልቹነት የማምለጫ መንገድ ሆኗል፡፡
ይህን ሁሉ ተገንዝባችሁ እንደሆነ አላውቅም:: አብዛኞቹ ሰዎች በአንድ ነገር ተጠምደዋል - የተወሰኑ ቃላትን በመደጋገም፣ በዚህ ወይም በዚያ ጉዳይ በመስጋት - ምክንያቱም ከራሳቸው ጋር ብቻቸው መሆንን ስለፈሩ። የሚረብሻችሁ ነገር ሳይኖር ብቻችሁን ለመሆን ብትሞክሩ ምን ያህል ከራሳችሁ መውጣት እንደምትፈልጉና ማንነታችሁን ለመርሳት እንደምትሹ ትገነዘባላችሁ። ለዛም ነው ይህ ግዙፍ የደስታ መዋቅር፣ ፈጣን ረብሻ ስልጣኔ የምንለው ነገር አካል የሆነው:: አስተዋዮች ከሆናችሁ የዓለም ህዝቦች ይበልጥ እየተረበሹ እንደመጡ፣ ውስብስብና ዓለማዊ እየሆኑ እንደሄዱ ትመለከታላችሁ። የደስታው መብዛት፣ አዲስ የሚወጡ ፊልሞች መብዛት፣ የጋዜጦች በስፖርታዊ ጉዳዮች መሙላት - እነዚህ ሁሉ ያለማቋረጥ መደሰትን እንደምንፈልግ ያመለክታሉ፡፡ ውስጣዊ ባዶነት ስላለብን ግንኙነቶቻችንና ማህበራዊ ለውጦቻችን ከገዛ ራሳችን ለማምለጥ እንደ መሳሪያ እንጠቀምባቸዋለን፡፡ ብቸኝነት የወረራቸው ብዙ ሰዎች እንዳሉ አስተውላችኋልን? ከብቸኝነታቸን ለማምለጥ ተሽቀርቅረን ፣ ግብዣ ወዳለበት እንሔዳለን፣ ቴሌቪዥን እናያለን፣ ሞባይል እንነካካለን፤ እናወራለን ወዘተ፡፡
ብቸኝነት ምን እንደሆነ ታውቃላችሁ? አንዳንዶቻችሁ ቃሉን ባታውቁም ስሜቱን በደንብ ታውቁት ይሆናል። ብቻችሁን ሽርሽር ስትወጡ ወይም ከሞባይል ስትላቀቁ ወይ ከሰው ጋር መነጋገር ስታቆሙ ይህ ሁሉ ነገር እንዴት አሰልችቷችሁ እንደነበር ትገነዘባላችሁ፡፡ ይህን ስሜት በደንብ ታውቁታላችሁ፣ ነገር ግን ለምን እንደሰለቻችሁ አታውቁም፤ ምን ብላችሁ ጠይቃችሁም አታውቁም:: ያን ስልቹነት በጥቂቱ ብትመረምሩት መንስኤው ብቸኝነት እንደሆነ ትገነዘባላችሁ፡፡ አብረን መሆን የምንፈልገው፣ መዝናናት የምንፈልገው፣ የሚረብሹንን መምህራን ወይም ምርጥ ፊልሞች የምንሻው ከብቸኝነታችን ለማምለጥ በማሰብ ነው፡፡ ውስጣዊ ብቸኝነት ሲሰማን የህይወት ተመልካች እንሆናለን ፤ ይህን ብቸኝነታችንን ተገንዝበን አልፈነው ስንሄድ ብቻ ተሳታፊዎች መሆን እንችላለን፡፡
ብዙ ሰዎች እንዴት በብቸኝነት መኖር እንደሚችሉ ስለማያውቁ ትዳር ይይዙና ሌላ አይነት ማህበራዊ ግንኙነት ይመሰርታሉ፡፡ ይህ ሲባል ግን አንድ ሰው ብቻውን መኖር አለበት አይደለም። መወደድ ስለፈለጋችሁ ብቻ የምታገቡ ከሆነ ወይም ሰልችቷችሁ ስራችሁን ራሳችሁን እንደ መርሻ ከተጠቀማችሁበት መላ ህይወታችሁ ረብሻን ፈላጊ እንደሆነ ትገነዘባላችሁ፡፡ ከዚህ ልዩ የብቸኝነት ፍርሃት በላይ የሚሆኑ ጥቂቶች ብቻ ናቸው፡፡ ነገር ግን ከዚህ ፍርሃት በላይ ሲኮን እውነተኛው ሀብት ይገኛልና ሁሉም ሰው ፍርሃቱን መብለጥ አለበት፡፡
በብቸኝነትና ብቻን በመሆን መካከል ከፍተኛ ልዩነት አለ፡፡ አንዳንድ ወጣት ተማሪዎች ብቸኝነት ምን እንደሆነ አያውቁ ይሆናል፤ በዕድሜ የገፉት ግን ይህን ጠንቅቀው ያውቃሉ። ብቸንነት ጨርሶ የመቆረጥ፣ ያለምንም ምክንያት በድንገት የመፍራት ስሜት ነው። አእምሮ የሚጠጋው ነገር ሲያጣ፤ የባዶነቱን ስሜት የሚያስወግድለት ነገር ሲያጣ ይህ ፍርሃት ይሰማዋል። ይህ ብቸኝነት ነው፡፡
ብቻን መሆን - ግን ፍፁም የተለየ ነገር ነው፤ በብቸኝነት ውስጥ አልፋችሁ ስትገነዘቡት የሚመጣ የነፃነት ሁኔታ ነው። በዚያ የብቻ መሆን ሁኔታ ውስጥ ስትሆኑ በስነ - ልቡና ረገድ የማንም ጥገኛ አትሆኑም፡፡ ምክንያቱም ደስታን፣ ምቾትን መፈለጋችሁ ያቆማል፡፡ ይህን ጊዜ ብቻ አዕምሮ ሙሉ በሙሉ ብቻውን ይሆናል፤ ፈጣሪ ይሆናል፡፡
የብቸኝነትን፣ የባዶነትን ልዩ ስሜት የመጋፈጡን፣ ያለ መፍራቱን፣ ስሜቱ ሲመጣ ሞባይል ያለመጠቀሙን፤ በስራ ያለመጠመዱን ወይ ወደሲኒማ ቤት ያለመሮጡን፤ ከዚህ ይልቅ ስሜቱን የመመልከቱን፣ የመገንዘቡን ነገር መፍጠር ያለበት ትምህርት ነው:: ስጋትን የማያውቅ ወይም ያላወቀ ሰው የለም፡፡ ይህንን ስሜት በወሲብ፣ በሀይማኖት፣ በስራ፣ በመጠጥ፣ ግጥሞች በመፃፍ ወይም በልባችን የተማርናቸውን ጥቂት ቃላት በመደጋገም ወዘተ ለማምለጥ ስለምንሞክር ፈፅሞ አንገነዘበውም።
ስለዚህም የብቸኝነት ህመም ሲመጣባችሁ ትታችሁት ከመሮጥ ይልቅ ተጋፈጡት፡፡ ትታችሁት ከሮጣችሁ ፈፅሞ አትገነዘቡትም፤ ሁልጊዜ በየጥጋጥጉ ቆሞ ይጠብቃችኋል። ስሜቱን ተገንዝባችሁ አልፋችሁት ብትሄዱ ግን ማምለጡ፣ መዝናናቱ አስፈላጊ እንዳልሆነ - ትረዳላችሁ፤ አዕምሯችሁ የማይበላሽ፣ የማይነጥፍ ብልፅግናን ይጎናፀፋል፡፡
ይህ ሁሉ የትምህርት አካል ነው፡፡ በትምህርት ቤት ፈተና ለማለፍ ብቻ የተወሰኑ ትምህርቶችን የምትማሩ ከሆነ ትምህርት ራሱ ፣ ከብቸኝነት የማምለጫ መንገድ ይሆናል፡፡ ትንሽ ብታስቡበት ይገባችኋል።
በውስጣቸው ከራሳቸው ጋር ብቻቸውን የሆኑ፣ አዕምሮና ልባቸው ከብቸኝነት ስቃይ የፀዳ ሰዎች እውነተኞች ናቸው- ምክንያቱም እውነታውን ከራሳቸው ይረዳሉ፣ ጊዜ የማይወስነውን መቀበል ይችላሉ፡፡

👍7❤6🙏5
ስለ ፍቅር
"ፍቅር ያልገባበት ልብ ፦ ሙት የኖረበት ፣ በድን የከረመበት ጥቁር የሬሳ ሳጥን ነው።ያለ ፍቅር ያለፈ እድሜም የጥላቻ ብል የሚበላው የከንቱ ነው።ሕይወታችሁ በዘላለማዊ ጥልቀት ውስጥ ሕያው ሆና ትቅጥል ዘንድ ፍቅርን ሁኑ!"
"ፍቅር እንደ ውቅያኖስ ማዕበል ብስለትን ተንተርሶ • በሰውነት የሚሰርፅ በልብ የሚቀረፅ በህሊና የሚታነፅ እንጂ እንደ መብረቅ ብልጭታ ታይቶ በቅፅበት ድርግም የሚል ሊሆን አይገባም"
"ፍቅር የሁሉ ነገር መነሻና መድረሻ ነው ። አንድን ቤት ስንሰራ ሁሉም ነገር ካልተዋደደና በአንድ ካልተዋሃደ እኮ ቤቱ ይወድቃል እንጂ አይቆምም ። ይቺ መሬታችንንም ብንወሥድ ቁጥር ስፍር የሌላቸው ብናኞች በፍቅር የመሰረቷት ህብር ናት ። እያንዳንዱ ግዙፍ ነገር ሁሉ ፍቅር የገለፀው የረቂቅ ብናኞች ህብር ነው።"
ያልታወቀ
"ፍቅር ከሚነደው የነፍስ ጉድጓድ በመመንጨት ምድሪቱን በብርሃን የሚሞላ አስማታዊ ጨረር ነው፡፡ፍቅር ሰው የአምላኩን ሀይል እንዲያይ የሚያስችለው ሰማያዊ ዕውቀት ነው፡፡"

👍15❤8💯1
እውነትን ፍለጋ
የሰው ልጅ እውነትን በመሻት ሂደቱ ውስጥ በተለያየ አቅጣጫ ሲያካሄድ የቆየው ውስጣዊና ውጫዊ ጉዞ የታሪኩን እኩሌታ አስቆጥሯል ለማለት ይቻላል። አንዳንዱ ሀይማኖትንና መንፈሳዊነትን መሰረት በማድረግ፣ ገሚሱ ፍልስፍናን በመንተራስ የተቀረውም ሳይንስን በመሞርኮዝ ሁሉም በየፊናው የህይወትን ትርጓሜ ለመረዳትና በዙሪያው ያለውን እውነታ ለመገንዘብ፣ ግንዛቤውንም በመሰሎቹ ዘንድ ለማስረጽ ታትሯል። ይህም ሆኖ ሁሉንም ከሚያስማማ፣ በሁሉም ሰው ዘንድ ተቀባይነት ካለው የጋራ ድምዳሜ መድረስ የተሳነው ይመስላል።
በመሆኑም በዚህ የረዥም ዘመን ሂደት እውነት በሶስት መልክ ተተርጉሞ ከሶስት የተለያዩ ድምዳሜዎች ተደርሷል። አንዳንዶች እውነት ከሁኔቶችና ከሰዎች አመለካከት ጋር የማይለዋወጥ ፍጹም ሀቅ ነው ሲሉ ሌሎች በበኩላቸው እውነት እንደየሰዉ አመለካከትና ግላዊ ስሚት የሚለያይ አንጻራዊ ክስተት መሆኑን ይጠቁማሉ። በሶስተኛው ጎራ የሚፈረጁት ደግሞ እውነት ከቶውኑ ሊታወቅ የሚችል አይደለም ከሚል ድምዳሜ ደርሰዋል።
ከዚህ አኳያ የእውነትን አንጻራዊነትና ፍጹማዊነት በተመለከተ ከሶቅራጥስ ጊዜ ጀምሮ ሲካሄድ የቆየው የማያባራ ሙግት አሁንም መቋጫ ያልተገኘለት ነው። በርግጥ ብዙዎች ነባር እንጂ አዲስ እውነት የለም እንደሚሉት በዚህ ዘመን ስለ እውነት አንጻራዊነት የሚካሄዱ ሰጣ ገባዎች የጥንቱን መሰረት ያደረጉ ቅጥያዎች ናቸው።
እውነት ከሰው ሰው የሚለያይ አንጻራዊ ክስተት ነው ብለው ከሚያምኑ ጥንታዊ ፈላስፎች ውስጥ በግምባር ቀደምትነት የሚነሳው የአፕዴራው ሱፊስት ፕሮታጎረስ ነው። የፕሮታጎረስ የአንጻራዊነት ድምዳሜ መሰረት ያደረገው የሰው ልጅ ስለ ገሀዱ አለም ያለው እውቀት በህጸጽ የተሞላ መሆኑ ላይ ነው።
ሰው የገሀዱን አለም እውነታዎች መገንዘብ የሚችለው በስሜት ህዋሳቱ አማካኝነት ነው። ሆኖም የሰው የስሜት ህዋሳት ከሰብአዊ የአፈጣጠር ገደብ አኳያ ነገራትን ሙሉ ለሙሉ መመልከት አይችልም። ቀጥ ያለ ብረት ውሀ ውስጥ ሆኖ ሲታይ የተጣመመ መስሎ ይገኛል። የብረቱን መጣመም የሚፈጥረው የሰዎች የእይታ ግድፈት ነው። ስለሆነም
የስሜት ህዋሶቻችን አቅምና ሀያል ነገራትን በትክክል ለመመልከትና ለመገንዘብ የሚያስችል አይደለም።
ነገራትን በትክክል ለመገንዘብ በሚል እሳቤ በሰው ልጅ የተፈበረኩ የተለያዩ ማሽኖች ቢኖሩም የነገራትን ትክክለኛ ህልውና ለማሳየት ብቁ አይደሉም። በርግጥ ማይክሮስኮፕና ቴሌስኮፕን የመሳሰሉ በሰው ልጅ የተፈበረኩ የማጉያ መነጽሮች ያለጥርጥር የእይታ አድማሳችንና አቅማችንን ያሰፋሉ። ድምጽን የሚያጎሉ ድምጽ ማጉያዎች የሰው ልጅ ከመስማት ችሎታው በላቀ እንዲያደምጥ ያስችሉታል። ይህም ሆኖ እነዚህ ሰው የፈበረካቸው መሳሪያዎች ፍጹምና እንከን የለሽ ባለመሆናቸው የነገራትን እውነተኛ ህልውና በትክክል የሚያመላክቱ አይደሉም።
በመሆኑም የሰው ልጅ በጎዶሎ ሀይሉ ማግኘት የሚችለው እውቀት ጎዶሎ ይሆናል" የሚያገኘውም እውቀት ሌሎች ከሚያገኙት የተለየ ነው ሁለት ሰዎች አንድን እውነት ፍጹም ተመሳሳይ በሆነ መልኩ ሊመለከቱ አይችሉም። በዚህ የተነሳ እውቀት እንደየሰዉ አተያይና ግላዊ ስሜት የሚለያይ ይሆናል" ለእኔ እውነት የሆነው እውነትነቱ ለእኔ ብቻ ሲሆን ለአንተ እውነት የሆነው እውነትነቱ ላንተ ብቻ ይሆናል።
ከዚህም ባሻገር የሊዮንቲየሙ ጆርጂየስ የፕሮታጎረስን የአንጻራዊነት አስተሳሰብ ይበልጥ በማስፋት ለኒሊዝምና ስኬፕቲዝም አመለካከት መሰረት ጥሏል። በኒሊዝም አራማጆች ዘንድ እውነት የሚባል ነገር ከነአካቴው የለም። እውነት የሚለው አስተሳሰብ በራሱ ውሽት ነው። ፈይራቤንድ እንዳስቀመጠው ‹‹ፍጹም የሆነው እውነት ፍጹም የሆነ እውነት አለመኖሩ ብቻ ነው›
ከስኬፕቲክስ ጎራ የሚፈረጁት ደግሞ እውነት የሚባል ነገር ቢኖር እንኳ ማወቅ አይቻልም ባይ ናቸው። እውነት የሚባል ነገር የለም ቢኖርም እውነትን ማወቅ አይቻልም የሚለው የነጆርጂየስ አመለካከት ፍሬድሪክ ኒቼንም የሚያስማማ ይመስላል። ኒቼ እውነተኛውን መንገድ አስመልክቶ እንዳስቀመጠው ‹‹እኔ የራሴ የሆነ መንገድ አለኝ፤ አንተም የራስህ መንገድ ይኖርሀል። ብቸኛውን፣ ትክክለኛውንና እውነተኛውን መንገድ በተመለከተ - የለም››
ከዚህ አመለካከት በመነሳት ጆርጂየስ ሶስት መሰረታዊ መርሆዎችን አስቀምጧል። አንድ - እውነተኛ ህልውና የለም። ሁለት - ሊኖር ቢችል እንኳ ሰው እውነታውን ማወቅ አይችልም። ሶስት በሆነ አጋጣሚ እውነትን ማወቅ ቢችል እንኳ ያወቀውን ለሌሎች ማሳመን አይችልም።
እነዚህን የኒሊዝምና ስኬፕቲዝም አመለካከቶች አጥብቀው የሚቃረኑ ፈላስፎች በበኩላቸው አመለካከቶቹ በራሳቸው መስፈርት ውድቅ የሚሆኑ፣ እርስ በርሳቸው የሚጻረሩ አመለካከቶች መሆናቸውን ይገልጻሉ። ምክንያቱም እውነት የሚባል ነገር ከሌለ የኒሊዝም እውነቶችም እውነት አይደለም ማለት ነው" ማንኛውንም ነገር ማወቅ አይቻልም ብለን ካሰብን ደግሞ ቢያንስ ማወቅ እንደማይቻል ማወቃችን በራሱ ምን ሊባል ነው?

👍6❤2🙏1
4ቱ የሕይወት መሪዎች
(1) ትግሰት
በሕይወት ዘመን ትግስት ውሳኝ ምህራፍ ነው፤ ታገሰ፦ በትግሰት ጊዜ ከሰጠይ ከባድ ነው ያልካቸው ሁኔታዎች ቀሎ ይገኛል፤ ተግዳሮቶችን ታገሰና እለፊ ያልፋል፤ ሁሉንም ነገር በትግሰት አድርገው።
ብዙዎች የዘላለም ጽኑ እሰራትን ያገኙት፥ ሕይወትን ያጡት ትግሰት አጥተው ነው። ለጥቅት ብታግሱ ለምያልፈው ችግር፥ ትንሸ ብቆዩና ብጠብቁ ለምሄድ ነገር በማይገባው ፈተናዎች ውሰጥ ገብተዋል። ታገሰ ሁሉም ያልፋል፤ ትግሰት የተላበሰ ማንነት ይኑርህ፤
እየገፉ ነው፥ እየተሳደቡ ነው፥ እየናቁ ነው፥ እያቋሸሹ ነው፥ እያሳሰቱ ነው፥ ወደ ሞት እየገፉ ነው አዎ! እነርሱ ይግፉ አንተ ግን ሰለ ምን ተናደህ በጸጸት ውሰጥ ትገባለህ፥ ብዙ ነገር ይጠብቃል ገና ታገሰና እለፉ እች ቀን በትግስት አሳልፊ ነገን ታያለ።
(2) መረጋጋት
ለየትኛውም ጉዳይ ከመውሰንህ በፍት ጊዜ ሰጥ፤ በተረጋጋ መንፈሰ አሰብ፥ ከማንም ጋር ሰትናገር በተረጋጋ መንፈሰ መልሰ ሰጥ፥ መረጋጋት ከሞት ያድናል፤ በመረጋጋት ውሰጥ ጊዜ ውሰድ፥ ለነገሮች ሁሉ አለመጨነቅ ረጋ ብሎ ማሰብ፤ በንደት አለመውሰን ረጋ ማለት፥ በሕይወት በምያጋጥሙ ደሰታም ይሁን ሐዘን ሲያጋጥሙ ረጋ ማለት የምሰጠው አዲሰ ሕይወት አለ።
በየትኛውም ቁምነገር መረጋጋትን ዘረጋው። ዘመንህን ለማየት ሁሉንም በማስተዋል ለመወሰን መረጋጋት ትልቅ ጥበብ ነው።
(3) እውነት
ሌላ ሰው ለመሆን አለመጣር፥ ከራሰ በላይ ሌላ ለመሆን አለማሰብ፥ እራሰ ሆኖ መኖር፥ እግዚአብሔር የሰጠውን ማንነት በደሰታ አምኖ መቀበልና በሱ በተሰጠ እውነተኛ ከሆነ ምክንያታዊ ሕይወት ጋር መኖር፤ የተሰጠውን ማንነት ማሳደግ፥ ማሰተማር፥ ማሠራት፥ ማለማመድ፥ መምራት፥ መቅጣት፥ መለየት፥ መወሰን፥ በራሰ ማንነት ማጸናት፤ አለማሰመሰል፦ ሌሎች ለመሆን አለመጣር። በተፈጥሮ እግዚአብሔር ማመሰገን ነው እውነት። እድሜን ሙሉ ሌላ ሰው ለመሆን በመጣር እራሰህን ሳትሆን ኖርኩ በለህ አትሙት። ሌላ ከመሆን በሸታ አድን።
(4) ንፅህና
ቅምና ጥላቻ፥ ጠማማነትና ክፋትን፥ ተንኮልና ግፍ ከሕይወት ላይ አሰወግድ። ንፅህ ትዉልድ ሁን፤ አእምሮህን ከምያቆሺሹ ነገሮች እራሰህን አሰወግድ፤
ለቅድሰትና ንፅህ ሁን፥ በአነጋገር ንፅህ ሁን፥ በአስተሳሰብ ንጻ፥ በአመለካከት ንፅህ ሁን፤ በአገማመት ንጻ፥ በማንነት ሁሉ ንፅህ ሁን፥ ክፉ አመል ክፊ ማንነትና መጥፎ አሰተሳሰብ ከራሰህ ላይ አሰወግድ፤ ከሱሰ አንጻ፥ ከዝሙት ንጻ፥ ከሐመት ንጻ፥ ለመምጣ ሕይወት ለዘላለማዊ ሕይወት ንፅህና ሰላማዊ እውነትና ትግስት የተላበሰ መረጋጋት ለጤነኛና ለሠላማዊ ሕይወት ውሳኝ ነገር ንፅህ መሆን ነው ።
ንፅህ ትዉልድ ሁን።
ንፅህና ትግሰተኛ
እውነተኛና የተረጋጋ ሰው ሁን።

🙏14👍9❤6
የጠፋውን የሰው ልጅ ፍለጋ (Search for the lost human soul)
ዘመኑ 1950ዎቹ ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ... ከሁለቱ የዓለም ጦርነቶች ስካር የባነነው ዓለም ለሌላ ዓይነት ባርነት ራሱን ሲያዘጋጅ ተገኘ፡፡ ሥልጣኔውም አገዘው፡፡ የሥልጣኔ ቀዳሚው ተልዕኮ የሰውን ልጅ እንሰሳዊ ደመነፍስ ማላመድ (taming human animalistic aggresion) ቢመስልም ውጤቱ ግን የተገላቢጦሽ ሆነ፡፡ ለኤሮፓዊ ፋውስታዊ የዛገ መዳዳቱ ስምረት ቴከኖሎጂው ረዳት ሆነለት፡፡
ዘመኑ ሰው ወደ አሻንጉሊትነት የሚያደርገውን የመምዘግዘግ ጉዞ አሀዱ ያለበት ሆነ፡፡ በአዲሱ ፈጠራ ቴሌቪዥን በመታገዝ "ፖፕ ከልቸር" ሰለጠነ፡፡ ሁሉም አብረቅራቂው ዘመን አመጣሽ ሳጥን ጋር ፍቅር ወድቆ ለአዲሱ ጊዜ ባርነት ራሱን አዘጋጀ፡፡ ዓመታት ተቆጠሩ፡፡ ቴክኖሎጂው በቀኝም በግራም እኩል ይመነደጋል፡፡ ቫይረሱ እና አንቲቫይረሱ፣ ሚሳኤሉና ጸረሚሳኤሉ እኩል ይበለጽጋሉ፡፡
ዛሬ ከሰባ ዓመታት በኋላ በዓለምአቀፍ ደረጃ ወደ ሁለት ቢሊዮን የሚጠጉ የቴሌቪዥኖች ዝግጅቶች ፣ ከ5 ቢሊዮን በላይ የሞባይል ስልኮች በሰው ልጆች እጆች ላይ ይገኛሉ። በአንጻሩ በሰው ልጆች የንባብ አትሮኖሶች ላይ እንደተዘረጉ የሚገመቱት መጻሕፍት ዓይነት ከ150 ሚሊዮን አይበልጥም፡፡
እነሆ ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ሞታችን ረክሶ ‹ላይቭ ስናየው ስንኳ ማስደንገጡ ቀንሷል፡፡ እንበላለን፤ ግን አናጣጥምም፡፡ እንዋሰባለን፤ ግን ፍቅርን ረስተናል፡፡ አብረን ሆነን ለብቻችንን ነን፡፡ አብረን እየኖረን አንዳችን ለሌላችን በዓድ፣ ሩቅ ነን፡፡ ወዳጅነት፣ ሣቅ፣ ፈገግታ፣ መታመን፣ ፍቅር፣ ፍትወት... ሸቀጥ ሆነው በገበያ ዋጋ ይቸበቸባሉ፡፡
ሰብዓዊት የማይቀለበስበት አስፈሪ ውጥንቅጥ ውስጥ ገብቷል፡፡ አንዳንዶች ይህ አረዳድ ጭፍንነት ሊመስላቸው ይችላል፡፡ አንዳንዶች ሀዘኑ ቤታቸው እስኪገባ ድረስ የመቃብር ደወሉ በየዕለቱ ለእነርሱ እንደሚደወል ይረሱታል፡፡
እናስ ኤሪክ ፍሮም እንዳስጠነቀቀው የሚቀጥለው ዘመን ሮቦቶች ለመሆን ምን ያክል ይቀረናል? በዚያ ዘመን (በ195oዎቹ አጋማሽ) የተነሱት እንደ ኤሪክ ፍሮም ዓይነት የሰው ልጅ ዕጣ ያስጨነቃቸው አሰላሳዮች ሰው ስለመዳረሻው እንዲጠነቀቅ አብዝተው ቢወተውቱም ሁሉም ከአጥበርባሪ ሳጥኗ ጋር ሲወዛወዝ ሰሚ አልነበራቸውም፡፡ ኤሪክ ፈሮም በ1955 እ.ኤአ በታተመ The Sane Society› በተሰኘ መጽሐፉ ላይ እንዲህ አለ፡፡
‹የ19ኛው ክፍለዘመን ጥያቄ፣ ትርክት ‹‹እግዚአብሔር ሞቷል›› ነበር፡፡ የሀያኛው ክፍለዘመን ፈተና ግን የሰው ልጅ ሞቷል› ሆነ፡፡ በ19ኛው ክፍለዘመን ኢ-ሰብዓዊነት ማለት ጭካኔ ነበር፡፡ በ20ኛው ክፍለዘመን ግን ኢሰብዓዊነት ማለት መደንዘዝ፣ ስሜት ማጣትና መነጠል ሆነ፡፡ የትናንት ስጋታችን የሰውን ልጅ ወደ ባርነት እንዳይገባ ነበር፡፡ የነገ ስጋታችን ግን የሰውን ልጅ ከሮቦትነት የመታደግ ሆኗል፡፡››
‹‹ሁላችንም በዘመናዊው የምዕራብ ዓለም የምንኖር ሰዎች እብደት ውስጥ ነን፡፡ ራሳችን እያታለልን ላለመሆናችን ምን ዋስትና አለን?››
ዓለም መልክ የሌለው መገማሸር ውስጥ ገብታለች፡፡ ልክ አንደ ሁልጊዜው!... በዚህ ሂደት ሰው የመሆናችን ቀለም አጥተናል፡፡ ሰው የመሆናችን ውሉ በምን ይረጋገጥ? ከቅድመ አያቶቻችን የሚያስተሳስረን ፈትለነገር ከተቋረጠ ሺህ ዘመናት አልፈዋል፡፡ በሕንጻ ሰንሰለቶች መካከል እየተመላለስን ስንኳ ሕልማችን የተራራ፣ የሸንተረር፣ የአደን፣ የለቀማ ነው፤ እንደ ግዞተኛ ነን፤ ፊሊፒናዊ፣ ቼካዊ፣ ቱርካዊ... መሆናችን፣ የመጽሐፍ ቅዱስ፣ የቅዱስ ቁርዓን፣ ወይም የማናቸውም ቅኝት ሥሪት መሆናችን እውነታውን አይቀይረውም፡፡
እኔ ግን የዓይኑ ቀለም ያላማራቸውን በጅምላ ኮንነው ሰልፊ እየተነሱ ዘቅዝቀው የሚሰቅሉ ሕዝቦች ሀገር ዜጋ ነኝ፡፡ ያ ሁሉ የሺህ ዘመናት ወንጌል፣ ሥነምግባር፣ ሀፊዝ፣ ሥርዓት፣ ትምህርት፣ ግብረገብነት በቅፅበት ውኃ በልቶት መቅላት፣ እስከነፍስ ማቃጠል፣ መደፍጠጥ፣ ማሳደድ... ሁሉም በሚያስደነግጥ ፍጥነት ሲከናወን አቅመቢስ ስዱድ፣ ዲዳ ሆኘ ተመልከቻለሁ፡፡ ታምሜያለሁ፡፡ ብዙ ኢፍትሃዊነት ባለበት ምንም ማድረግ ካለመቻል በላይ የሚያም ምንስ ነገር ይኖራል?
ለነገሩ በየትኛውም የዓለም ክፍል በሰብዓዊነት፣ በአጠቃላይ በስነፍጥረት ላይ የሚቃጣ በደል ካላመመኝ የስካሩ አካል ሆኛለሁ ማለትም አይደል? አንዳንዶች ለዚህ መድኃኒቱ ዜግነትን ማስረጽ፣ ሕገመንግስት መቀየር... ዓይነት _ ጨዋ ሐሳቦችን ሲሰነዝሩ እሰማለሁ፡፡ ምንኛ የዋሆች ሆነዋል ጃል! የታመመው በአጠቃላይ የሰው ልጅ (ሰብዓዊነት) መሆኑን ማየትስ እንዴት ይሳናቸዋል? ይህ የሰብዓዊነት ማሽቆልቆል፣ ስርዓት በመቀየር፣ ደንደሳም ዴሞክራሲ በማስረጽ፣ በአዋጅ በማስነገር፣ ኢትዮጵያን እንደ አሜሪካ በማበልጸግ ብቻ ሊሻሻል አይችልም፡፡ እንዲውም ሁላችንም ከጫፍ እስከ ጫፍ እንደ ሰው ካላሰብን አንተርፍም፡፡
ዘመናዊው የሰው ልጅ ከቅድመ አያቶቻችን አንጻር የሁሉም ነገር ውስጥ መትረፍረፍ ውስጥ ነው፡፡ ዛሬ የአንድ አሜሪካዊ ቤተሰብ አማካይ የመገልገያ ቁሳቁሶች ብዛት እስከ 300,000 ይገመታል፡፡ ከመቶ ዓመታት በፊት ከነበረው ጋር ሲነጻጸር 5000% እጥፍ ተመንድጓል፡፡ ዘመኑ በሁሉም ነገር የመትረፍረፍ (Abundance) ቅዠት ውስጥ የሚዳክር ይመስላል፡፡ ነገርግን መትረፍረፍ መቅሰፍት ሆኖብን ምኞታችን፣ እውነታችን፣ የሕይወት ትርጉማችን አሳክሮብናል፡፡ ምንም የማይፈይድልን የመረጃ ናዳ ያጥለቀልቀናል፡፡ በተሳከረ የመረጃ ቱማታ ተዋክበን እውነታችን ራሱ ዋጋ አጥቷል፡፡
ዘመኑ እንደየትኛውም ግልብ ዘመን ነበርና ኤሪክ ፍሮምና መሰሎቻቸው አድማጭ አላገኙም፡፡ እንደየትኛውም ዘመን... ዛሬ ለስሙ እንሰዋለን የሚሉ ቢሊዮናት ተከታዮች ያሉት መሲሁ በቁርጡ ቀን ከመስቀሉ ፊት ለፊት ለብቻው እንደነበረበት ዘመን፡፡ የሚያሳዝነው ዘመን ልብ መግዛት ሲጀምር ዕድሎች ቁጭት ሆነው ከተፍ ማለታቸው እኮ ነው፡፡
የሰው ልጅ የለየለት ዕብደት ውስጥ ገብቷል፡፡ ነጠል ብሎ ለሚታዘብ ተመልካች የሚታየው የሚሰማው ሁሉ አጃኢብ ነው፡፡ ሥልጣኔው ሁሉ በየዕለቱ የሚያስመዘግበው መካን፣ መራቀቅ የአውዳሚነት መሆኑ ተስፋ ያስቆርጣል፡፡ ከጦር መሣሪያ ጋር ያልተነካካው ቴክኖሎጂያዊ ፈጠራ ስንኳ በየዕለቱ ሰብዓዊነትን የሚያኮሰምን የመሆኑ ነገር ያስደነግጣል፡፡
ተመራማሪዎች በቅርቡ ሰው በማይደርስባቸው አስፈሪ የአርክቲክ አካባቢዎች ሳይቀር ብዙ ሺህ ቶን የሚመዝን የማይበሰብስ ቆሻሻ አግኝተዋል፡፡ የሰው ልጅ አሁን በተያያዘው ግዴለሽ ጎዳና ከቀጠለ ሩቅ በማይባል ዘመን ሕይወት ከውቅያኖሶችና ባህራት ተጠቃልሎ ሊጠፋ ይችላል፡፡

👍19❤2
"መሪ አስመሳይና አታላይ መሆን አለበት"
ወደ ላይ መውጣት ከፈለግክ የግድ የበታቾችህን መጨፍለቅ ይኖርብሃልን? ስኬት የሚመጣው ሰዎችን በማታለል እና በክፋት ውስጥ ብቻ ነውን? ስለምንድን ነው በአብዛኛው ዘርፍ ላይ ከላይ የሚሆኑ ባለ ስልጣናት ወይም ፖለቲከኞች የእብደት ጠባይ ያላቸው?
የዲፕሎማቱ እና ፈላስፋው ማኪያቬሊ መጽሐፍ የሆነው The Prince ለዚህ መልስ አለው፡፡ ይህ አጭር መጽሐፍ እንዴት አንድ መሪ የራሱን የስልጣን ዘመን ማራዘም እንደሚችል ያሳያል።ምርጥ መሪ ማለት መልካም መሪ የሚል ቀጥተኛ ትርጓሜ የለውም፡፡ ምርጥ መሪ በምንም አይነት መንገድ ስልጣኑን የሚያስጠብቅ መሪ ነው ይለናል። ይህ መሪ ስልጣኑን ለማስጠበቅ ያጭበረብራል፣ ይሰርቃል፣ ህዝቡን ያታልላል።
በመፅሀፍ ውስጥ እነዚህ ሀሳቦች ይንፀባረቃሉ።
1.መሪ ሥነ - ምግባርን አሽቀንጥሮ መጣል
አለበት፡፡
ህዝቡ በከፋበት ዘመን ከመሪ መልካምነት ሊጠበቅ አይገባም ይላል ማኪያቬሊ ።መሪው በባህሪው መጥፎነት ኖሮበት ሣይሆን መጥፎ ህዝብ መጥፎ መሪን ስለሚያመጣ ነው፡፡ ህዝቡ ሥነ ምግባር የጉደለውና ሥርዓት የሚያውቅ ከሆነ በዚህ ሁኔታ አንድ መሪ የራሱን ደህንነት መጠበቅ ግዴታ ውስጥ ይገባል፡፡ ለዚህ ያለው ብቸኛ አማራጭ ኃይልን በመጠቀም ጨካኝነቱን ማሳየት ነው፡፡ ህዝቡ ገልበጥባጣ በመሆኑ መሪ ህዝቡን ማመን የለበትም፤ ህዝቡን ከማመን ይልቅ የራሱን ማንነት እንደሁኔታው እየቀያየረ መኖር ያስፈልገዋል፡፡ በዚህ ሁኔታ ማካቬሌ ፖለቲካን ከሥነ - ምግባር የሚነጥል ፍልስፍናን አቀረበ፡፡
2.መሪ የሐይማኖተኛና የቅድስና ህይወት ሊኖር አይገባም፡፡
ማኪያቬሊ ሲናገር ሐይማኖትን ህዝብ ይከተለው እንጅ መሪ ሊከተለውና ሊኖርበት አይገባም፡፡ መሪ ሐይማኖተኛ ከሆነ ትሑት ይሆናል፤ ትህትና ደግሞ ደካማ ያደርጋል፡፡ መሪ ደካማ ከሆነ በዙሪያው ያሉት ጠላቶቹ ሰለባ ይሆናል::
3. መሪ ለስልጣኑ ሕጋዊነት መጨነቅ የለበትም፡፡
ለማኪያቪሊ ህጋዊ መንግስት የሚያስፈልገው መረጋጋት ባለበት ሀገር ውስጥ ነው፡፡ መረጋጋት ከሌለ ህግም ቢኖር ተግባራዊ አይሆንም፤ ህግ አልባነትንም በህግ መመለስ አይቻልም፡፡ ህግ በጠፋበት ዘመን ህጋዊ ሥርዓት መፍጠር የሚቻለው ጸጥ - ለጥ አድርጐ በጉልበት መግዛት ሲቻል ነው፡፡ “መልካም ህግ ያለመልካም ክንድ ሊኖር ስለማይችል ከህግ ይልቅ የበረታች ክንድን እመርጣለሁ” ይላል ማኪያቬሊ፡፡
"Since there can not be good laws with out good arms, I will not consider laws but speak of arms.”
መጥፎ ህዝብ የመንግስት ቅጣት ስለሚፈራ ሣይወድ በግድ ሥርዓት ይይዛል፤ ስለዚህ መሪ ለመወደድ ከመጣር ይልቅ ለመፈራት ቢጥር የተሻለ ነው፡፡መሪ ይላል ማኪያቬሊ የመንግስትን ሥልጣን ለመያዝ ህጋዊ መንገድ ከመጠበቅ ይልቅ በራሱ ኃይል መተማመን ይገባዋል፡፡
ማኪያቬሊ በዚህ አመለካከቱ የመንግስት ሥልጣንና ህጋዊ ሥርዓት የተሳሰሩበትን ገመድ በጥሶ ጣለው፡፡
4.መሪ አስመሳይና አታላይ መሆን አለበት
ያልተረጋጋን የፖለቲካ ሁኔታ ማለፍ የሚችሉት ተንኮለኛ ሰዎች ናቸው ብሎ ማኪያቬሊ ያምናል፡፡ ተንኮለኛነቱ ለደህንነቱ በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ ተንኮለኛነቱ የሚገለፀው ደግሞ ህዝቡን ለማሳሳት አስመሳይ ሁኖ ስለሚቀርብ ነው፡፡ መሪ ጥሩ ሰው ሳይሆን ነገር ግን ጥሩ ሰው መስሎ ህዝቡን መቅረብ አለበት፡፡ በዚህ ጊዜ አስመሳይነቱን ህዝቡ እንዳያውቅበት መጠንቀቅ አለበት፤ ለህዝቡ ሐቀኛ መስሎ ነው መታየት ያለበት፡፡ የህዝቡን ድጋፍ ለማግኘት ደግ መስሎ መታየት፤ ለፍትህ፣ ለእኩልነት፣ ለሰባዊነት የቆመ መስሎ መታየት አለበት፡፡ ነገር ግን በተግባር ከእነዚህ እሴቶች በተቃራኒ ሁኖ መኖር አለበት፡፡ ተቀናቃኞቹንና ደጋፊ መስለው በዙሪያው እየኖሩ ደባ የሚሠሩበትን ምቹ ሁኔታ ባገኘ ቁጥር ያለምንም ርህራሄ ማጥፋት አለበት፡፡ መሪ እንደ ተኩላ የራሱን እኩይነት በማይነቃ መልኩ ሸፍኖ መያዝ አለበት፡፡ ሊያጠቃቸው የሚፈልጋቸውንም የዋህ፣ ደካማና በእነርሱ ላይ ክፋት የማያስብ መስሎ በመታየት ሊያዘናጋቸውና ባላሰቡት ጊዜ ሊያጠቃቸው ይገባል ይለናል፡፡

❤11👍7🕊1
ስሜትን ማንፃት-1
ስሜቶች ከአካል እና ከሃሳቦች ይበልጥ ጥልቅ በሆነ ደረጃ ላይ ናቸው፡፡ የስሜቶች ንጹህነት በጣም አስፈላጊው ብቃት ነው፡፡ በመንፈሣዊው ጉዞ የስሜቶች መጽዳት ከአካል እና ከሃሳቦች የበለጠ ጠቃሚ ነው፡፡ ይህ የሆነበት ምክንያትም የሰው ልጅ እንደ ሃሣቦቹ ከመኖር ይልቅ እንደ ስሜቶቹ የሚኖር በመሆኑ ነው።
“የሰው ልጅ ምክንያታዊ እንስሳ ነው” ይባላል ግን ይህ እውነት አይደለም፡፡ በህይወታችሁ ውስጥ የምታደርጓቸው ብዙ ነገሮች የማሰብ ውጤቶች አይደሉም፡፡ የምታደርጉዋቸው ብዙ ነገሮች ተጽእኖ የሚደረግባቸው በስሜቶቻችሁ ነው፡፡ ጥላቻችሁ፣ ቁጣችሁ፣ ፍቅራችሁ - እነዚህ ሁሉ ከስሜቶቻችሁ ጋር እንጂ በብዛት ከሃሳቦችሁ ጋር የሚገናኙ አይደሉም፡፡
በህይወት ውስጥ ያሉት ብዙዎቹ እንቅስቃሴዎች የሚመነጩት
ከሃሣቦች ሣይሆን ከስሜቶች ነው፡፡ አንድ ነገርን አስባችሁ ሌላ ነገር
የምታደርጉበት ሁኔታም አስተውላችሁ የምታውቁ መሆን አለበት።የዚህ ጉዳይ መስረታዊው ምክንያት በሥሜቶች እና በማሰብ መካከል መስረታዊ ልዮነት ያለ መሆኑ ነው፡፡ ምናልባትም“አልናደደም” ብላችሁ ወስናችሁ ይሆናል ፣ ምናልባትም “ንዴት መጥፎ ነው” ብላችሁ ልታስቡም ትችላላችሁ፡፡ግን ንዴት ለቀም አድርጎ ሲይዛችሁ ማስብ ገለል ይል እና ትናደዳላችሁ፡፡
በስሜቶች አለም ውስጥ ሽግግር/ለውጥ እስካልተከሰተ ድረስ ማሰብ እና ቁዘማ ብቻውን በህይወት ውስጥ አብዮትን ሊያመጣ አይችልም። ለዚያ ነው ሥሜቶች በመንፈሳዊ ጉዞ ዋና ነጥብ የሆኑት።
ሥሜቶች የሚነጹባቸው አራት ገጽታዎች
1. ወዳጅነት(ፍቅር) 2. ርህራሄ
3. ደስተኛነት እና 4. ምስጋና
• እነዚህን አራቱን ስሜቶች በህይወታችሁ ውስጥ ብታካትቱ የስሜትን ንጽህና ትቀዳጃላችሁ፡፡
እነዚህ የሥሜት ገጽታዎች ሊገለበጡ እና ያልነጹ ስሜቶች ማህጸን ሊሆኑም ይችላሉ፡፡ አራቱ የስሜት ገጽታዎች እያንዳንዳቸው ተቃራኒ አላቸው፡፡
ወዳጅነት - ጥላቻ እና ጠላትነት
ርህራሔ - አረመኔነት፣ አንባጓሮ፣ ክፋት
ደስታ - ሃዘን ፣ መከራ ፣ ጭንቀት
ምስጋና - ምስጋና-ቢስነት
ህይወቱ እና ሥሜቶቹ በአራቱ ተቃራኒ ገጽታዎች ውስጥ ያለ ሰው ባልነጻው የስሜቶች ሁኔታ ውስጥ ሲሆን በመጀመሪያዎቹ የስሜቶች ገጽታዎች ውስጥ ስሩን የሰደደው ሰው ደግሞ በንጹህ ስሜቶች ውስጥ የጠለቀ ነው፡፡
ነፃ ስሜቶች
ይቀጥላል..

👍21❤5
ሁላችንም የተፈጥሮ አካላቶች ነን - ስፒኖዛ
በአጽናፈ ዓለም ውስጥ ብዙ ኃይላት አሉ፡፡ ምድር ወደ ላይ በረን እንዳንሄድ ስባ ታስቀረናለች፡፡ ጸሐይ ምድርን በክብ ምህዋር ላይ እንድትዞር ታስገድዳታለች... ብንዘረዝራቸው የማያልቁ ብዙ ኃይላትን በሁለንተና ውስጥ እናገኛለን፡፡ በእያንዳንዱ ቁስ አካል ውስጥም ይፈሳሉ፡፡ በዓለም ሁሉ ያለ ነገር በእነዚህ ሃይሎች ተይዟል፡፡ ሰዎች፣ በባህር ውስጥ ያለ አሳ፣ ከወፎች የሚወጣ ድምጽ... ሁሉም የዚህ ኃይል አካል ናቸው፡፡ ሁላችንም በእነዚህ ኃይላት ታስረናል፡፡
ይህ ሁለንተናን በሌላ መንገድ የመመልከቻ ሃሳብ የቀረበው ባሩክ ስፒኖዛ በተባለ ፈላስፋ ነው፡፡ የፍልስፍናውም ሃሳብ ሞኒዝም ተብሎ ይጠራል፡፡ ሞኒዝም ቃሉ “አንድ ብቻ” የሚል ትርጓሜ አለው፡፡ ይህም በሁለንተና ውስጥ ያለ ነገር ሁሉ እንደ “አንድ አካል” ነው የሚል አንድምታ አለው፡፡ እኔም አንተም፣ ጨረቃም ጸሐይም - ሁላችንም በአንድ አካል ውስጥ እንዳሉ ህዋሳቶች ነን፡፡
ስፒኖዛ በአብርሆት ዘመን በፊት የነበረ አውሮፓዊ ፈላስፋ ነው፡፡ ከእርሱ ጋር በአንድ ዘመን የነበረው ዴካርት በሁለንተና ውስጥ ያሉ ነገሮችን በሶስት ይከፍላቸዋል- አእምሯዊ፣ አካላዊ እና አምላክ (ያልተፈጠረ እና ሁለንተናን የፈጠረ)።
ነገር ግን ስፒኖዛ እንዲህ ይላል - ከሁላችንም በላይ የሆነ እና ሁላችንንም የሚያውቅ አምላክ ካለ፣ ይህ አምላክ በሆነ መንገድ ከሁላችንም ጋር ይገናኛል ማለት ነው፡፡
“አቤቱ፣ ፈትነኝ መርምረኝም፤ ኩላሊቴንና ልቤን ፈትን:: እንዳለው መዝሙረኛው ዳዊት፣ ልብ እና ኩላሊትን የሚመረምር አምላክ በልብም፣ በኩላሊትም ውስጥ መገኘት አለበት ይለናል ስፒኖዛ፡፡ የአካላቸው ክፍል የሆኑ ነገሮችን ብቻ ነው ልንመረምር የምንችለው... አምላክም እኛን ሊመረምር የሚችለው እኛ የእርሱ አካል እስከሆንን ድረስ ብቻ ነው፡፡ እግርህ ላይ ያለ ህመም የሚሰማህ እግርህ የአንተ አካል ስለሆነ ነው፡፡ አምላክም የእኛ ህመም የሚሰማው እኛ የእርሱ አካል ስለሆንን ነው፡፡
በተመሳሳይም በሁለንተና ውስጥ ያሉ ሁሉም ነገሮች እንደ አንድ አካል ናቸው፡፡ አእምሮም፣ አካላዊ ቁሶችም የአንድ ግዙፍ ስርዓት አካል ናቸው፡፡ እንደ አንድም ይንቀሳቀሳሉ። ሁሉም ነገር ስረ መሰረቱ አንድ ነው፡፡ ያንተ ህሊናም፣ የጉንዳኖች ጉዞም፣ የአንዲት የብርሃን ቅንጣት፣ አንዲት ጠብታ ውሃም መዳረሻቸው አንድ ነው ... ሞኒዝም፡፡
አንስታይን ስፒኖዛን ይወደው ነበር፡፡ የስፒኖዛ ፍልስፍና ለእርሱ ሒሳባዊ ቀመሮች የሚፈይድለት ነገር ኖሮ አይደለም፤ ነገር ግን ስፔኖዛ ተፈጥሮን እንደ አምላክ አድርጎ ስለሚገልጻት ነው። አንስታይንም ተፈጥሮን አምላክ ብሎ ይጠራት ነበር፡፡
ስፒኖዛ ከጥቃቅን ነገሮች ወይም ተፈጥሮን/አምላክን ለመረዳት መጓዝ አለብን ይለናል፡፡ በተፈጥሮ ሁነቶች ተነስተን ውስጥ ራሳችንን እያስመጥን ስንመጣና ከተፈጥሮ ጋር ፍጹም አንድ ስንሆን፣ መታበያችን ከእኛ ይርቃል። እኔ እንዲህ ነኝ ማለትንም እናቆማለን፡፡ ራሳችንንም ነጥለን የምንኮራበት አልያም የምንወቅስበት ምክንያት አይኖርም... ምክንያቱም “እኔ” የሚባል ማንነት
አይኖረንም...
ስፒኖዛ የሰው ልጆች ሕይወታቸውን አወሳስበው ይኖራሉ ይለናል። ልክ እንደ ህጻናትም በጸደይ አበባ መሃል ከመቦረቅ ይልቅ፣ በብዙ ጥቃቅን ጉዳዮች ራሳችንን አስረነዋል። ይህ የሚገባን ግን እድሜያችን ሲገፋ ብቻ ነው፡፡ በእርጅና ዘመናችን በወጣትነታችን የነበሩ አላስፈላጊ ጭንቀቶቻችን እና ፍርሃቶቻችን ይገለጡልናል። ሕይወታችን ውስጥ ያሉ ነገሮችንም መውደድ እና ማድነቅ እንጀምራለን፡፡

👍17❤3
የእመቤታችን ቅ/ድ/ማርያም ልደት ለምን ቂጣ ተጋግሮ፤ ንፍሮ ተቀቅሎ እየተበላ ይከበራል?
እመቤታችን በተፀነሰች ዕለት አይሁድ ቀንተው ተነሱባቸው፡፡ ቅናቱ እንዴት ነው? ቢሉ ሳሚናስ የሚባል የጦሊቅ ልጅ ከኤዶቅ ከአጎቱ ቤት ሔዶ ሞተ እነርሱም እንቀብራለን ብለው በአልጋ ይዘው ሲሄዱ ከመንገድ አሳረፉት፡፡ የሐናም የአጎቷ ልጅ ነበርና ለማልቀስ ብትደርስ ዘመዶቿ ሁሉ ተሰብስበው ሲላቀሱ ቆይዋት:፡፡ እርሷ አብራ ስታለቅስ ጥላዋ ቢያርፍበት መግነዝ ፍቱልኝ ሳይል የሞተው ልጅ ብድግ ብሎ ተነሳ፡፡ ሕዝቡ ሁሉ ተገረሙ ተደሰቱ አይሁድ አብረው ነበሩና ሳሚናስ ምን አየህ? ምን ትላለህ? ቢሉት ከሐና ማኅፀን የምትወለደው ሕፃን ሰማይ ምድርን እመቀ አየርን የፈጠረ አምላክን ትወልዳለች፡፡ እያሉ መላእክት ሁሉ ሲያመሰግኗት ሰማሁ፡፡ እኔንም ያስነሳችኝ ያዳነችኝ እርሷ ናት አላቸው፡፡ ያን ጊዜ አይሁድ እነዳዊት እነሶሎሞን አባቶቻችንን 40፣40 ዓመት እንደ ሰም አቅልጠው፤ እንደ ገል ቀጥቅጠው ገዙ፡፡ ከሐና የሚወለደውም እንዲሁ ሊገዛን ነውን? ብለው ሳይወለድ እንግደለው ብለው ሊገድሉ ያስቡ ነበር ፡፡ መልአኩም አይሁድ እንዳያገኟቸው ወደ ሊባኖስ እንዲሰደዱ ነገራቸው፡፡
እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምም በሊባኖስ ግንቦት 1 ተወለደች::
እመቤታችን በተወለደችበት ዕለት ደስታ ተደረገ፡፡ ቤታቸው በብርሃን ተመላው በስምንተኛውም ቀን ማርያም ብለው ስም አወጡላት:: በዚህ መሰረት የእመቤታችንን የልደት በዓል(ግንቦት ልደታ) በታላቅ ክብር ከሚያከብሩ አብያተ ክርስቲያናት መካካል ዋነኛዋ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ናት፡፡ የግንቦት ልደታ በዓል አከባበር በቤተ ክርስቲያናችን ትውፊት መሰረት ኢያቄምና ሐና ከአይሁድ ለማምለጥ ተሰደዉ ምግባቸው ንፍሮና ጥራጥሬ ስለነበር ይህንን ትውፊት መሰረት በማድረግ በቤተ ክርስቲያን በማኅሌት፣ በቅዳሴና ታቦታትን በማክበር፣ ከመኖሪያ ቤት ዉጭም ቂጣ ተጋግሮ፤ ንፍሮ ተቀቅሎ እየተበላ ይከበራል፡፡
የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ፍቅሯ አማላጅነቷ በሁላችን ይደር፡፡ አሜን

❤19👍4🙏3👏2🔥1
በወንዶች አለም ውስጥ አንዲት ሴት
“መለያየት ሞት ነው”
"የአዲስ አበባ ወንድ የመልበሻ ቤት መስተዋት ሆኗል፡፡ ሴቶቹ በሱ ፊት ላይ አለባበሳቸውን ያያሉ፤ የአዲስ አበባ መንገዶች፣ ካፌዎች፣ ባሮች፣ ቢሮዎች፣ ሆቴሎች፣ የፀሎት ቤቶች … አለባበስ ማሳያ መድረኮች ሆነዋል፡፡
ወንዱ የጥሞና ጊዜ ተነፍጓል፡፡ ሲበላ፣ ሲጠጣ፣ ሲሰራ፣ ሲፀልይ፣ ታክሲ ሲጠብቅ … በሞዴሎች ተከቦ ነው፡፡ ህይወቱ የናይት ክለብ ውስጥ እስረኛ ሆናለች፡፡ ሲወለድ ሳውና ባዝ የገባ ሲሞት ይወጣል፡፡ ኑሮው በላብ መጠመቂያ ስፍራው ሆናለች፡፡ አይኑ ሸሽቶ የትም አይደርስም፡፡ እድሜ ልኩን መስክ መካከል እንደቆመ ሁሉ በአበባ ተሰላችቷል፡፡ …ትቢያ… ናፍቆታል፡፡
ሴቶች፤ የወንዶች አገልግሎት አቅራቢ ድርጅት ሆነዋል፡፡ አይኑን ያገለግላሉ፣ ልቡን ያገለግላሉ፣ ስሜቱን ያገለግላሉ … የሴቶች የመጨረሻ አማራጭ … የወንዶች ገበያ .. እንደሚፈልገው ሆኖ መገኘት ነው። ህይወታቸው በወንዶች ህልም የተፈበረከ ነው፡፡ ከሰው የሚጠበቀው ከዘንድሮ ሴቶች አይገኝም፡፡ ወንድ የሚፈልገውን ግን አያጣም። አይኑ፣ ጆሮው፣ አፍንጫው፣ ምላሱ … በሴቶች ትጋት ሥር ተጠምዶ ተደናቅፏል፡፡ አንዲት ሴት ከአንዲት አበባ ጋር በንፅፅር ቆማለች፡፡ የወንድ ቀልብ እንደ ንብ ሲጠመድላት ከማየት ውጭ ሌላ ህልም የላትም፡፡
እንግሊዛዊው ደራሲ ዲ.ኤች ላውረንስ ይሄንን ታዝቦ አንዲት የመረረች መጣጥፍ አቅርቦ ነበር፡፡ “Give her a pattern” ይላል ርእሱ “The real trouble about women is that they must always go on trying to adapt themselves to men’s theories of women, as they always have done.” ብሏል፡፡ (የሴቶች ዋነኛ ችግር ወንዶች ስለሴቶች የሚኖራቸውን ፅንሰ ሃሳብ አሟልተው ለመገኘት ሁልጊዜም መጣራቸው ነው)
የዘንድሮ ሴቶች ሴት የመሆን መብት የላቸውም፤ ወንድ የሚፈልገው አይነት ሴት እንጂ፡፡ ሴቶች የወንዶችን ህልም ለመተርጎም ህይወታቸውን የሚሰዉ ጭዳዎች ናቸው። በመሰልጠን ስም እራሳቸውን ለፆታ ባርነት አጋልጠዋል፡፡ ኧረ እንዳውም ከባርነት ወርደው ለአሻንጉሊትነት ተዳርገዋል፡፡ ሁኔታውን “Living Doll” ይለዋል Cliff Richard የተባለ አቀንቀቃኝ፡፡ … ህያው አሻንጉሊት … እንደማለት ነው፡፡ “I got myself a sleeping, walking, crying, talking Doll” (እራሴን የምትተኛ፣ የምትሄድ፣ የምታለቅስ፣ የምታወራ አሻንጉሊት ሆኜ አገኘሁት) የዘንድሮ ሴቶች ሰው መሆናቸውu የሚረጋገጠው ስለሚተኙ፣ ስለሚሄዱ፣ ስለሚያለቅሱና ስለሚያወሩ ብቻ ነው፡፡ እንደ አበባ … ንብ.. መጥራት የህይወት ትርጉማቸው ሆኗል፡፡ "

❤41👍13🙏11