WSU National Volunteer Trainers
857 subscribers
224 photos
23 files
13 links
Download Telegram
Wolaita Sodo University:
#ማስታወቂያ

የዩኒቨርሲቲው አካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት ከደረጃ ጋር!!

ለ2017 ዓ.ም ተመራቂ ተማሪዎች በሙሉ

**         *

ንኳን ለ2017 የት/ም ዘመን በሰላም አደረሳችሁ እያለ  የወላይታ  ሶዶ ዩኒቨርሲቲ አካ/ጉ/ም/ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት ከደረጃ ጋር በመተባበር በአይነቱ ለየት ያለ የስልጠና አገልግሎት ዘመቻ ማዘጋጀቱን ስናበስራችሁ በታላቅ ደስታ ነው!!

ስለሚሰጡ አገልግሎቶች ገለፃ የፊታችን ረቡዕ ህዳር 4/2017 ዓ.ም ጠዋት እና ከሰዓት በኋላ በፖስተሩ ላይ በተጠቀሱት ካምፓሶችና አዳራሾች ይደረጋል። እንዲሁም አርብ 6/2017 ዓ.ም በዳውሮ ታርጫ ካምፓስ ፕሮግራሙ ይቀጥላል፡፡

በቆይታችን የተለያዩ የደረጃ ነባርና አዳዲስ አገልግሎቶች ገለጻ እና በተጋባዥ እንግዶች ንግግር ይደረጋል፡፡
ለተማሪዎች የተለያዩ ስጦታዎች እና በሚደረጉ ውድድሮች ላይ አሸናፊ ለሆኑ ተማሪዎች ሽልማቶችም ይኖሩናል።

የፊታችን ረቡዕ ህዳር 4 እና አርብ ህዳር 6/2017 ዓ.ም አይቀርም!!

ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ

Big News, Wolaita Sodo University!

In partnership with Dereja, we’re bringing exciting events to your campus from November 13-15!  Get ready to unlock your potential and elevate your career journey. Save the date! 

#Dereja

#WolaitaSodoUniversity

#CareerOpportunities

The Dereja Campaign is coming to multiple campuses at Wolaita Sodo University with exciting sessions lined up.

#Dates & Times:
Wednesday, November 13 | 1:30 PM Main and Health Campus at Graduation Hall

Friday, November 15| 9:00 A.M Dawro Tercha Campus at Council Hall.

ARE YOU #GC2025? Don’t miss out on the opportunity to elevate your career journey! 🚀

See you there!

Knowledge in Action!!

Wolaita Sodo
👍3
ሰላም እንዴት ናችሁ!!
ከታች ያለው ሊንክ የ "WSU Student's Career Development Club". ቴለግራም  ቻናል ሲሆን በቻናሉ የተለያዩ መረጃዎችን የሚናጋራ ይሆናል,  ለምሳል:-
1) የ Dereja.com የስልጠና መረጃ ሲኖር
2) የተለያዩ ቀጣሪ ድርጅቶች የቅጥር ማስታወቂያ ሲያወጡ
3) በግቢያችን የተለያዩ የግል እና  የመንግስት ድርጅቶች ስልጠና የሚሰጡ ከሆነ.... እነዚህንና የመሳሰሉ መረጃዎችን የምናጋራ ይሆናል።
ቴለግራም ቻናሉ የተከፈተው  ከDereja.com ጋር በመተባበር ነው።

Please share this link to your friends
https://t.me/WSUstudentscareerdevelopmentclub with Dereja.com
👎4
Forwarded from Tikvah-University
በሁሉም የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የተማሪዎች የምግብ በጀት ተመን ላይ ማሻሻያ ተደረገ።

በዚህም "የተማሪዎች የምግብ በጀት ተመን በቀን በአንድ ተማሪ የነፍስ ወከፍ ወጪ ብር 100.00 (አንድ መቶ) ሆኖ ከታህሳስ 1 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ሥራ ላይ እንዲውል" መንግሥት ወስኗል።

ማሻሻያው በትምህርት ሚኒስቴር የቀረበን የምግብ በጀት ተመን ማሻሻያ ጥናት ከወቅቱ የገበያ ዋጋና ከመንግሥት የመክፈል አቅም አኳያ በማየት የተወሰነ መሆኑን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ለትምህርት ሚኒስቴር በላከው ደብዳቤ ተገልጿል።

በሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች የተማሪዎች የምግብ አቅርቦት በወጥነት እንዲከናወንና ከምግብ በጀት ተመን ማሻሻያው ጋር የተጣጣመ ስታንዳርድ የምግብ ሜኑ በማዘጋጀት እንዲጠቀሙበትና በአግባቡ ስራ ላይ መዋሉን ትምህርት ሚኒስቴር ክትትል እንዲያደርግ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ኃላፊ ክና የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር አለምፀሐይ ጳውሎስ በቀን ህዳር 25/2017 ዓ.ም የተፈረመ ደብዳቤ ያሳያል።

ዩኒቨርሲቲዎች ከዚህ ቀደም በቀን አንድ ተማሪ ቁርስ፣ ምሳ እና እራት ለመመገብ በመንግሥት የሚመድብላቸው 22 ብር በጀት ብቻ እንደነበር ይታወሳል።

(የማሻሻያ ውሳኔው ለሁሉም የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች መነገሩን ቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ አረጋግጧል።)

@tikvahuniversity
👍2
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA
#MoE : በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የምግብ ሜኑ ተመሳሳይ እንዲሆን መወሰኑን ትምህርት ሚኒስቴር አሳወቀ።

የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የምግብ በጀት ማስተካከያ መደረጉንም ይፋ አድርጓል።

" ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተውጣጡ ባለሙያዎች የዩኒቨርስቲ ተማሪዎችን የምግብ ሜኑ ተቀራራቢ እንዲሆን እየሰሩ ነው " ሲል ትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል።

ወቅታዊውን የምግብ ዋጋ መጨመር መነሻ በማድረግ ትምህርት ሚኒስቴር ጥናት ማድረጉን በጥናቱ ውጤት መነሻነትም የከፍትኛ ትምህርት ተቋማት / የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የምግብ በጀት በቀን ወደ 100 ብር ከፍ እንዲል መደረጉን አሳውቋል።

በተደረገው የበጀት ማሻሻያ መሰረት በተቋማቱ የምግብ ሜኑ ተመሳሳይ እንዲሆን ይሰራል ተብሏል።

በአዲሱ የበጀት ተመን መሰረት ለዩኒቨርስቲዎቹ ባላቸው ተማሪ ቁጥር ልክ ገንዘቡ እንደሚለቀቅላቸው ተጠቁሟል።

ዩኒቨርሲቲዎች ከዚህ ቀደም በቀን አንድ ተማሪ ቁርስ፣ ምሳ እና እራት ለመመገብ በመንግሥት የሚመድብላቸው 22 ብር በጀት ብቻ እንደነበር ይታወሳል።

@tikvahethiopia
4👍1🖕1
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA
#MoE

በወጥነት ይተገበራል የተባለው የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ሜኑ ምን ይመስላል ?

የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ዕለታዊ የምግብ ወጪ ከታህሳስ 01/2017 ዓ.ም ጀምሮ 100 (መቶ ብር) እንዲሆን መወሰኑ ይታወቃል።

የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የምግብ ሜኑም ሁሉም ጋር ወጥ እንዲሆንብ እየተሰራ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር መግለጹ አይዘነጋም።

ይህንን ተከትሎ ፤ የተማሪዎች የምግብ አቅርቦት በሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች በወጥነት እንዲከናወን ትምህርት ሚኒስቴር ከምግብ ተመን ማሻሻው ጋር የተጣጣመ ስታንዳርድ የምግብ ሜኑ በማዘጋጀት ለሁሉም የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ልኳል።

የምግብ ሜኑው ዝቅተኛውን መስፈርት መሠረት በማድረግ መዘጋጀቱን የገለጸው ሚኒስቴሩ ተቋማት ከባቢያዊ ነባራዊ ሁኔታን ከግምት ውስጥ በማስገባት በአንድ ተማሪ ሳምንታዊ ወጪው ከ700 (ሰባት መቶ) ብር ባልበለጠ መልኩ ስራ ላይ መዋል እንዳለባቸው ማሳሰቢያ አስተላልፏል።

ለዩኒቨርሲቲዎች በተላከው የምግብ ሜኑ ከላይ የተያያዘ ሲሆን ፦

👉 ቁርስ ላይ ፦ እንጀራ ፍርፍር / ሩዝ + ዳቦ + በሻይ ፣ ቅንጬ ፣ ስልስ ፣ ማካሮኒ ተካተለዋል።

👉 ምሳ ላይ ፦ ምስር/አተር ክክ/ሽሮ / አተር / ባቄላ / ድንች / አትክልት ማለትም ጎመን ፣ድንች፣ ካሮት የመሳሰሉ / ፓስታ /  + እንጀራ / ዳቦ ፣ ከዚህ በተጨማሪም በሳምንት 1 ቀን ስጋ በምስር/በድንች/ በክክ (በዳቦ ወይም በእንጀራ) ተካተዋል።

👉 እራት ላይ ፦ ምስር/ክክ/ፓስታ / ሽሮ + በእንጀራ/ዳቦ ፣ ከዚህ በተጨማሪ በሳምንት 1 ቀን ስጋ በምስር/በድንች/ በክክ (በዳቦ ወይም በእንጀራ) ተካተዋል።


🔵 ለበለጠ መረዳት ከሰኞ እስከ እሁድ የተከፋፈለውን የምግብ ሜኑ ከላይ መመልከት ይቻላል።

አጠቃላይ ትምህርት ሚኒስቴር ለዩኒቨርሲቲዎች በላከው የምግብ ሜኑ መሰረት ለቁርስ ፣ ለምሳ፣ ለእራት ለአንድ ተማሪ የተመደበው 100 ብር ነው።

በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት / ለመንግሥት ዩኒቨርሲቲ ለተማሪዎች የተመደበው ዕለታዊ የምግብ በጀት በየጊዜው እየጨመረ ያለውን የምግብ ዋጋ ንረት ሊሽፍን ባለመቻሉ መንግሥት በፊት የነበረውን ዕለታዊ የተማሪ ምግብ ወጪ 22 ብር ወደ 100 ብር ከፍ አድርጎታል።

(በትምህርት ሚኒስቴር ዴኤታ ኮራ ጡሸኔ ተፈርሞ ለሁሉም የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የተላከው ሰርኩላር ከላይ ተያይዟል)

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
👍2🥰1👏1
መልካም ዜና ለወላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲ Freshman ተማሪዎች በሙሉ :-

በቅድሚያ እንኳን ደስ አላችሁ እያልን

  የወላይታ  ሶዶ የዩኒቨርሲቲ አካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት ከDereja ጋር በመተባበር  ለfreshman ተማሪዎች  ልዩ የስልጠና መርሃ ግብር  ስላዘጋጀ በሥልጠናው ላይ ለመሳተፍ ከስር ባለው ሊንክ እንድትመዘገቡ እናሳስባለን ።
https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLSe6RVteAe1bAwNMfE-zVllQZuvJ_L0NL25pasj3WhRDSevHKQ/viewform
ማሳሰቢያ፡- ያልተመዘገበ ተማሪ በስልጠናው ላይ አይሳተፍም!!
Some informations about career compass training:-
👇👇👇
Career Compass :- is a training tailored to assist First year University students in making informed department selection. It will allow them to get access to counselling and guidance to assess their skill, interest and passion before selecting department. 

Training to be held for: 1-month 
Sessions include Macro (once per week) and Micro Sessions/counselling individual and group (twice per week).

What you will get after the completing the training: 
    
  *Enhanced self-awareness:          you will discover your skills, and interests and personality.

  *Explore career options: you will get insight to different departments and possible career paths to pursue.

*Decision-making skill: you will get guidance on how to select a department that suits your skill, personality and interest.

*Develop Career Plan: you will develop a career plan to help you reach your career goals.

Trainees who successfully complete the program will be Certified. 
ሰላም ሰላም እንዴት ናችሁ የ10ኛው ዙር የሰላም ሚኒስትር   በጎ ፍቃደኛ ተማሪዎች  ::
የምስክር ወረቀት (certificate ) ስለመጣ ከፓስታ ቤት አጠገብ ወይም ሚኒሚዲያ ...ከላይ ካለው PDF  ስማችሁን እና ተራ ቁጥራችሁን እያያችሁ በተባለው ቦታ በመገኘት እንድትወስዱ ስንል እናሳውቃለን ።

# ማክሰኞ በቀን 22/4/17ዓ.ም  ቀን 6-8ሰአት
ከተራ ቁጥር 1-200
ምሽት 2-4ሰአት  201-400

# ዕሮብ በቀን 23/4/17ዓ.ም
ቀን 6-8ሰአት 401-600
ምሽት 2-4 ሰአት 601-800

# ሀሙስ በቀን 24/4/17ዓ.ም
ቀን 6-8ሰአት 800-እና ከዚያ በላይ


👉የስም ስህተት ያለባችሁ ተማሪዎች
በ0937842684 text በማድረግ ወይም በቴሌግራም   @abusintu   አሁንም  ቁጥራችሁን   እና ትክክለኛውን ስማችሁን ልካችሁ ማስተካከል ትችላላችሁ ።

ማሳሰቢያ ፦  በቁጥራችሁ መሰረት እና በቀናችሁ ተገኝታችሁ እንድትወስዱ ከዛ ውጪ የምመጣ ተማሪ የማናስተናግድ መሆኑን እንገልፃለን!!
👍1
please share the above information to other students participated in summer voluntery services in WSU.
👍2
እስካሁን ድረስ ሰርቲፊኬታችሁን(CERTIFICATE) ያልወሰዳችሁ ተማሪዎች ነገ ሐሙስ ቀን፡- 24/4/2017 ዓ.ም  ከሰዓት 6፡00-8፡00 LT & ማታ ከ12፡00 LT. ጀምራችሁ ፖስታ ቤት አጠገብ ካለው ሚንሚዲያ በአካል ቀርባችው እንድትወስዱ እናሳስባለን!!

ለበለጠ መረጃ... ሀሳብ፣ጥያቄ፣ጥቆማ ካላችሁ በስልክ ቁጥር 0937842684 ወይም በቴሌግራም @abusintu ማሳወቅ ትችላላችሁ።
Please share this info to other students
👍31
WSU National Volunteer Trainers pinned «እስካሁን ድረስ ሰርቲፊኬታችሁን(CERTIFICATE) ያልወሰዳችሁ ተማሪዎች ነገ ሐሙስ ቀን፡- 24/4/2017 ዓ.ም  ከሰዓት 6፡00-8፡00 LT & ማታ ከ12፡00 LT. ጀምራችሁ ፖስታ ቤት አጠገብ ካለው ሚንሚዲያ በአካል ቀርባችው እንድትወስዱ እናሳስባለን!! ለበለጠ መረጃ... ሀሳብ፣ጥያቄ፣ጥቆማ ካላችሁ በስልክ ቁጥር 0937842684 ወይም በቴሌግራም @abusintu ማሳወቅ ትችላላችሁ። Please…»
ሰላም ውድ ተማሪዎች!!
እስካሁን ድረስ ሰርቲፊኬታችሁን ያልወሰዳችሁ .....

# ከተራ ቁጥር 1--541 ያላቹ እና የኦቶና - ካምፋስ ተማሪ የሆናችው
በ 0937842684 በመደወል (በቴሌግራም @abusintu) ሰርቲፊኬታችሁን መውሰድ ትችላላችሁ

## ከተራ ቁጥር 542--917
ያላቹ ተማሪዎች በ 0945250164 በመደወል መውሰድ የምትችሉ መሆኑን ለመግለጽ እንወዳለን።

ላልሰሙ ተማሪዎች መረጃውን እንድታጋሩ።
👍3