Tutorial for highschool students
174 subscribers
24 photos
25 videos
13 files
98 links
Educational channel
You can dm me at:
t.me/Abboud1088
Download Telegram
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA
የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ስለ ኩረጃ ምን አሉ ?

" ትምህርት እውቀት ሲሆን ሰርተፊኬት ደግሞ ያንን እውቀት የምንለካበት ነው።

በስርቆት ፣ በማጭበርበርና በኩረጃ የሚገኝ ነገር እውቀት ሳይኖር ሰርተፊኬት ማግኘት ነው። ይህ ደግሞ እውቀት አለመኖሩ ብቻ ሳይሆን ሰርተፊኬቱ እውቀት አለህ ስለሚለው ምንም ሳያቅ ሰርተፊኬት በእጁ ስላለው ብቻ እውቀት አለኝ ብሎ የሚያምን የህብረተሰብ ክፍል ይፈጠራል፤ ይህም ህብረተሰቡን በጣም ይጎዳል።

በተለይ በትምህርት ዘርፉ ተንሰራፍቶ የነበረውን ማጭበርበር፣ ስርቆትና ኩረጃ ተማሪዎች ብቻ የሚያደርጉት ቢሆን ኖሮ የልጆቹ ችግር ነው ተብሎ ሊወሰድ ይችላል። ነገር ግን ይህን የሚያደርጉት ፦
- ተማሪዎች፣
- የትምህርት ቤት አስተዳደሮች፣
- የክልል ባለስልጠናት እና ሌሎችም ' የኛ አካባቢ ልጆች እንዲያልፉ ' በሚል የሚያደርጉት በመሆኑ ከፍተኛ የሞራል ውድቀት ውስጥ የተገባበት ነበር።

በመሆኑም ወደፊት ትውልዱን በጥራት ማስተማር አለብን ካልን ከመሰረቱ ችግሩን መፍታትና በኩረጃና በማጭበርበር የሚገኝ እውቀት እንደሌለና ይህም ሀገር እንደሚጎዳ በሁሉም ዘንድ መተማመን መፍጠር ያስፈልጋል።

በዚህም ይህንን ስብራት ለማስተካከል በተወሰደው የለውጥ እርምጃ ተማሪዎች በትምህርት ዘርፉ በቀላሉ አጭበርብሮና ኮርጆ ማለፍ የለም የሚለውን በማወቅ ፦
° በሥርዓቱ ማጥናት፣
° ቤተ መጽሃፍት መግባት፣
° ጊዜያቸውን በአግባቡ መጠቀም፣
° በትርፍ ጊዜያቸው ቲቶሪያል መማርና ለትምህርታቸው በቂ ትኩረት መስጠት  ጀምረዋል።

መምህራንም በአግባቡ ተዘጋጅተው ማስተማርና ተማሪዎችን በሚገባ ማዘጋጀት፣ የትምህርት ቤት ርዕሳነ መምህራንም ሁሉም ተማሪዎች ትምህርታቸውን ተከታትለው ከክፍል ክፍል በትክክል ተመዝነው እንዲያልፉ ማድረግ ጀምረዋል።

በየክልሉ ያለው የትምህርት መዋቅርም በኩረጃ ' የኔ አካባቢ ይህን ያህል አለፈ ' ከሚል የቁጥር ጨዋታ ወጥተው በትክክል የትምህርት ምዘና በየደረጃው በማድረግ ልጆች ባላቸው እውቀት ብቻ ተመዝነው የሚያልፉበት ሥርዓት እየፈጠሩ ይገኛል። ለአብነት ፦ የ6ኛ እና 8ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና በአግባቡ እየተገበሩ ነው።

ይህንን ማስቀጠል ከተቻለ የምዘናና የፈተና አስተዳደር ሥርዓቱን በሚገባ ያስተካክለዋል።

የገጠመውን የሞራል ክስረት በሚገባ አስወግዶ ትምህርት በእውቀትና በችሎታ ብቻ የሚለው በጀመርነው አግባብ ወደ ኋላ ሳይመልሰው ማስረጽ ከቻልን ለምናደርገው የትምህርት ጥራት መሻሻል እንደ መነሻ ይሆናል።

በአጠቃላይ የትምህርት ምዘናና ፈተና አስተዳደር ሥርዓቱን ማስተካከል ከተጀመረ ጀምሮ በተወሰዱ እርምጃዎች ከአሁን በኋላ በሁሉም ዘንድ ግልጽ በሆነ መንገድ በማጭበርበርና በኩረጃ የሚገኝ ነገር እንደሌለ እና ተምሮና ተግቶ በማጥናት ብቻ ውጤት እንደሚገኝ በተማሪዎችና በማህበረሰቡ ዘንድ መተማመን ተፈጥሯል። "

#MoE

@tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA
#MoE

ትምህርት ሚኒስቴር ከ2018 የትምህርት ዘመን ጀምሮ ተማሪዎች ሞባይል ስልክ፣ ታብሌት እና መሰል ኤሌክትሮኒክስ ቁሶችን ይዘው ወደ ትምህርት ቤት እንዳይሔዱ ከልክሏል፡፡

ትምህርት ሚኒስቴር በ2018 የትምህርት ዘመን አጀማመር ላይ ከክልል እና ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊዎች ጋር የበይነ-መረብ ምክክር አድርጓል።

የ2018 ትምህርት ዘመን የመማር ማስተማር ሥራ ሰኞ መስከረም 05/2018 ዓ.ም እንደሚጀመር ተገልጿል።

ተማሪዎች ተንቀሳቃሽ ስልክ፣ ታብሌት እና መሰል ኤሌክትሮኒክስ ቁሶችን ይዘው በትምህርት ቤት መገኘት ክልክል መሆኑን ሚኒስቴሩ አሳስቧል።

በሌላ በኩል፤ ባለፈው ዓመት ከትምህርት ገበታ ውጪ የሆኑ ተማሪዎችን ጨምሮ ሁሉም ዕድሜያቸው ለትምህርት የደረሱ ህጻናት እና ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤት እንዲመጡ ወላጆች፣ መምህራን እና የዘርፉ ባለድርሻዎች የሚጠበቅባቸውን እንዲወጡ ተጠይቋል።

Via @tikvahuniversity