WLS 2016 Grade 12 Batch
92 subscribers
132 photos
14 videos
143 files
63 links
Dear users of this channel✌️ "Education is not preparation for life education is life itself."
wolaita liqa school.
G_12th students 😍
#Class of 2024
Download Telegram
👨‍🏫👩‍🏫 ለ 2017 የመጀመሪያ አመት የዩኒቨርሲቲ ና የኮሌጅ ተማሪዎች በሙሉ!

📚A+ Tutorial Class ተማሪዎችን በሚያስፈልጋቸው ነገር ለመርዳት ዝግጅቱን ጨርሶ ተማሪዎችን በመመዝገብ ላይ ይገኛል። የተለያዩ ግቢና ኮሌጅ ተማሪዎች በሚቀጥሉት ጥቂት ሳምንታት ትምህርት መጀመራቸውን አስመልክቶ በሚኖራቸው Mid-Exam ላይ የሚያስፈልገውን እገዛ ያደርጋል።

🎯ለሁሉም ኮርሶች የሚያስፈልጉ ምቹ ቲቶሪያሎችን ያቀርባል ፤ ቲቶርያሉ በጥቂት ቀናት ውስጥ ይጀምራል።

🎯በየቻፕተሩ የተዘጋጁ ጥያቄዎችን ከሰፊ ማብራሪያዎች ያቀርባል።

🎯ያለፉት አመታትን የለተያዩ ግቢዎች የሚድ ፈተና ጥያቄዎች ይሰራሉ።

እርስዎስ ተመዝግበዋል? ካልተመዘገቡ አሁነኑ ይመዝገቡ! ከተመዘገቡ ላልተመዘገቡት ይህን መልዕክት ያጋሩ።🙌

ለመመዝገብ👇👇
@Aplustutorialsbot

ለጥያቄና አስተያይት👇👇
@Ucan_Scorebot

ይፋዊ የቴሌግራም ቻናላችንን ለመቀላቀል👇
@Aplustutorialofficial

© A+ Tutorial Class.
በተማሪዎች ምገባ ላይ የተደረገዉ ማሻሻያ ለአንድ ተማሪ በቀን ከሚያስፈልግ ወጪ ጋር የሚመጣጠን አይደለም ተባለ‼️

በተማሪዎች ምገባ ላይ ምላሽ መሰጠቱ መልካም ቢሆንም አሁንም በቂ በጀት አለመመደቡን መናኸሪያ ሬዲዮ ያነጋገራቸው ዩኒቨርስቲዎች ገልጸዋል። በነበረው የምግብ ሜኑ ወይም ዝርዝር ላይ ምንም አይነት የሚጨምር ነገር አይኖርም በማለት ከ22 ብር ወደ 1 መቶ ብር ከፍ ማለቱ መልካም ምላሽ ቢሆንም አሁንም ካለው የገበያ ንረት አንጻር በቂ በጀት አይደለም ሲሉ በደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ዲን አቶ አለምነው መልካሙ ለመናኸሪያ ሬዲዮ ተናግረዋል።

በነበረው በጀት ከመጪው ጥር ወር ጀምሮ ለተማሪዎች ምገባ የሚሆን በጀት አልነበረንም ሲሉ የተናገሩት የተማሪዎች ዲኑ ምናልባት አዲሱ ውሳኔ በተወሰነ ሽፋን ሊሰጥ እንደሚችል ገልጸዋል። የገበያው ሁኔታ በየቀኑ እየናረ የተማሪዎች ምግብና አመጋገብ ደግሞ በተለመደ አይነት ሁኔታ እየቀጠለ ነው የነበረው አዲሱ በጀትም ከዚህ የተለየ ገበያውን በመቆጣጠር መፍትሄ ይሆናል ብለን አናምንም ሲሉ አቶ አለምነው ተናግረዋል።

ከ22 ብር ወደ 1 መቶ ብር ማደጉ ነገሩን ያረጋጋዉ እንደሆነ እንጂ በጥራትም ሆነ በምግባ አገልግሎቱ ላይ ለውጥ አያመጣም ሲሉ የወልዲያ ዩኒቨርስቲ የተማሪዎች አገልገሎት ዲን ዶ/ር ዮሃንስ ሲሳይ ገልጸዋል፡፡

ከሶስት ወር በፊት ነሐሴ ወር ላይ ብቻ በተሰራ ዳሰሳ ለአንድ ተማሪ ወጪ በትንሹ 1መቶ 54 ብር ያስፈልግ ነበር ሲሉ ያከሉት ዲኑ አሁን ያለው የገበያ ሁኔታ ደግሞ ከሶስት ወር በፊት ከነበረው እጅግ የተለየና ጭማሪ ያሳየ በመሆኑ የተጨመረው ጭማሪ መልካም ቢሆንም ጠቃሚ ነው ማለት ግን እንደማይቻል ዶ/ር ዮሃንስ ገልጸዋል። ገበያው ውድ ከመሆኑ የተነሳ በርካታ ስራዎች እየተስተጓጎሉ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

ከትምህርት ሚኒስቴር የመጣ ይፋዊ የድጎማ ማሳወቂያ ባይኖርም ዩኒቨርሲቲዎቹ እስካሁን በሰሙት መረጃ መሰረት የተደረገው ድጎማ አሁንም ተጨማሪ ማሻሻያ የሚያስፈልገዉ እና በቀን ለአንድ ተማሪ ይወጣል ተብሎ ከሚታሰበዉ ጋር እንደማይመጣጠን አመላክተዋል፡፡

ትክክለኛ መረጃ የምትገኙበት የ 12ኛ
https://t.me/+esqs-EEENtxlM2Q8
 
            Share share🙏🙏
ለተጨማሪ መረጃ👇👇👇👇
╔═══════════╗
♨️ ♦️ @ethiouniversity1  ♨️
♨️ ♦️ @ethiouniversity1  ♨️
♨️ ♦️ @ethiouniversity1  ♨️
╚═══════════╝
WPS Office-2024-12-19 10.45.zip
12.9 MB
Logic mid exam collection part 1
WPS Office-2024-12-19 10.48.zip
24.8 MB
Logic mid and final exam collection part 2🌟
#Tomorrow we will release #Anthropology's☺️  ppt  and mid Exam. HAVE A NICE TIME💫
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA
#Update

" የምግብ ጥራቱ ወርዷል ፤ መጠኑ ቀንሷል 22 ብር በነበረ ጊዜ ይሻላል ፤ የብሩ መጨመር ምንም ነገር ካላስተካከለ ትርፉ ከፍተኛ ኮስት ሸሪንግ / የወጪ መጋራት እዳ ነው " - ተማሪዎች

ከሰሞኑን በሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች ወጥነት ባለው መንገድ መተግበር የጀመረው የምግብ ሜኑ በተማሪዎች ዘንድ ቅሬታን የፈጠረ ሆኗል።

ምግቡ መጠኑ ቀንሷል፤ ጥራቱም 22 ብር የነበረ ጊዜ ይሻላል የሚል ቅሬታ ነው ተማሪዎች ዘንድ ያለው።

ከዚህ ባለፈ የብሩ መጨመር በተማሪዎች ኮስት ሼሪንግ / ወጪ መጋራት ላይ ከፍተኛ ጭማሪ አድርጎ ተማሪውን ባለዕዳ ከማድረግ ባለፈ አንድም የጥራት መሻሻል አይታይም ፤ ጭራሽ መጠንም ቀንሷል ብለዋል።

በትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አስተዳደርና ልማት መሪ ሥራ አስፈፃሚ የሆኑት ዶ/ር ሰሎሞን አብርሃ  ስለ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የምግብ በጀት (100 ብር) ምን አሉ ?

" የምግብ በጀቱ 100 ብር ሆነ ማለት የግድ የተለየ ለውጥ ይመጣል ማለት አይደለም። የምግብ አይነቱም ሙሉ ለሙሉ አስደናቂ በሆነ መልኩ ይቀየራል ማለት አይደለም፣ ሊቀየርም አይችልም።

ድሮውንም ተማሪዎች በተመደበላቸው 22 ብር ብቻ ሲመገቡ አልቆዩም።

ከፌዴራል መንግሥት የሚመደበው 22 ብር አነስተኛ መሆኑ ስለሚታወቅ ዩኒቨርሲቲዎች በራሳቸው አካሄድ ሲያስተካክሉ ቆይተዋል።

ዩኒቨርስቲዎች ከሚመደብላቸው የተለያየ በጀት እያዟዟሩ በቀን ከ80 እስከ 150 ብር በማውጣት ተማሪዎችን ሲመግቡ ነበር።

የተማሪዎች የምግብ ሜኑ ከመሻሻሉ በፊት አንድ እንጀራን እስከ 24 ብር ድረስ የሚገዛ ዩኒቨርስቲ ነበር። ድሮ ይመደብ የነበረው በጀት አንድ እንጀራ እንኳን በቅጡ የማይገዛ ነበር።

በመሆኑም ይህ አካሄድ የዩኒቨርሲቲዎችን እንቅስቃሴ ስላስተጓጎለና የአሰራር ስርዓታቸው ላይም ችግር ስለፈጠረ፣ የምግብ ሜኑ ሲዘጋጅ ጥናት ተጠንቶ ሀገር አቀፍ የተማሪ ህብረት ተወካዮች ጭምር በአካል በተገኙበት የዩኒቨርሲቲዎች ምግብ ማሻሻያ ተደርጓል።

ተማሪዎች አሁን ካለው ሁኔታ አንፃር ማድረግ ያለባቸው የሚመደብላቸው በጀት በአግባቡ ለእነርሱ መድረሱን እና በቀን የመቶ ብሩ በጀት ተሰልቶ በሳምንት 700 ብር ወጪ መደረጉን፣ እንዲሁም ያንን ወጪ ታሳቢ ያደረገ ሜኑ መቅረብና አለመቅረቡን ማረጋገጥ ነው።

ከዚህ ጋር በተያያዘ የተማሪዎች ህብረት አደረጃጀትም ኃላፊነት በመውሰድ በአግባቡ መከታተል አለበት " ብለዋል።


ቲክቫህ ኢትዮጵያ ይህ የሰሎሞን አብርሃ (ዶ/ር) ንግግር የተወሰደው ለአሐዱ መሆኑን ያሳውቃል።

@tikvahethiopia
Forwarded from Ethio~Campus
Arsi University 🙌 አዲሱ ሜኑ👐

አርሲ ዩኒቨርስቲ ትምህርት ሚኒስቴር ባወጣው መሰረት የ 100 ብር ሜኑ ጀምረዋል 👐🥰

እንደሚታዩት ለአይን የሚያምር እንዲሁም አሪፍ የሆነ ምግብ ማቅረብ ጀምረዋል👏👏 ትንሽ መረቅ ብመርቁበት 🤗

ከተማሪዎችም እንደ አጀማመሩ አሪፍ መሆኑን ገልፀዋል።

👉 በአዲሱ ሜኑ ምግብ ካልተሻሻለ ቅሬታ በፎቶ አድርጋችሁ ላኩልን። እንዲሁም አሪፍ የሆኑ ምግቦችንም ላኩልን።

@freshman_infoo
ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም እና በጤና አደረሳችሁ!

መልካም የገና በዓል
💘1
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#Kenya

ትላንት ምሽት በኢትዮጵያ ደቡብ እና ደቡብ ምዕራብ ክፍሎች በሰማይ ላይ እየተቀጣጠሉ በከፍተኛ ፍጥነት ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ብርሃን ያላቸው የቁስ አካላት ስብስብ በኬንያ ሰሜናዊ ምስራቅ ክፍልም ታይተዋል።

እነዚህ ቁስ አካላት በኬንያ ቱርካና፣ ማርሳቢት፣ ሞያሌ አካባቢ መታየታቸውን የኬንያ የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ገልጸዋል።

ምንም እንኳን ቁስ አካላቱ " የጠፈር ፍርስራሾች ናቸው በገጠሪቱ የሀገሪቱ ክፍል (ኬንያ - ኢትዮጵያ ድንበር) ወድቀዋል ፤ ሲወድቁም ከፍተኛ ድምጽ ተሰምቷል ፤ ከሚቃጠል ነገር ጭስም ታይቷል ሽታም ነበረው " እያሉ ብዙ ተከታይ ያላቸው የኬንያ ፀሀፊዎች X ላይ ቢፅፉም የኬንያ ስፔስ ኤጀንሲ በይፋ የሰጠው ማረጋገጫ የለም።

እስካሁን የኬንያ ስፔስ ኤጀንሲ ፥ ቁስ አካላቱ ኬንያ ውስጥ ስለመውደቃቸው ማረጋገጫ አልሰጠም ስለ ጉዳዩ መግለጫም አላወዋጣም።

ከሰሞኑን በኬንያ ማኩኒ ካውንቲ ሙኩኩ በተባለች ትንሽዬ መንደር ከሰማይ ወርዷል የተባለ 2 ነጥብ 5 ሜትር ስፋት ያለውና 500 ኪሎግራም ክብደት ያለው ቁስ በርካቶችን አስደንግጦ ነበር።

የኬንያ የስፔስ ኤጀንሲ ሰዎች ቁሱ ወደወደቀበት ስፍ በማቅናት ምንነቱን ለማጥናት የሞከሩ ሲሆን ወደ ህዋ የመጠቀ ሮኬት ቁርጥራጭ ሊሆን እንደሚችል ገምተዋል።

ቀለበት ቅርጹ ከሮኬት ከተነጠለ በኋላ የሚፈረካከስ እንደነበር የተገለጸ ሲሆን የየትኛው ሀገር ወይም ኩባንያ ንብረት እንደሆነ የማጣራት ስራ እየተሰራ ነው። እስካሁን መደምደሚያ ላይ አልተደረሰም።

ተቋሙ " እንደዚህ አይነት ቁሶች (በኬንያ የወደቀው ቀለበት) ወደ ምድር ምህዋር ሲመለሱ ራሳቸውን እንዲያቃጥሉ አልያም ወደ ውቅያኖሶች እንዲገቡ ተደርገው የሚሰሩ ናቸው " ሲል ነው ያብራራው።

እንደ ኒውዮርክ ታይምስ መረጃ ከሆነ ባለፉት ስድስት አስርት አመታት በሀገራት መካከል የሚደረግ የህዋ ላይ ፉክክር መጠናከር ከሰማይ ላይ የሚወድቁ ቁሶች እንዲበራከቱ አድርጓል።

ባለፈው አመት ባወጣ የአውሮፓ የጠፈር ኤጀንሲ መረጃ በዝቅተኛ የምድር ምህዋር ውስጥ ከ14 ሺህ ቶን በላይ ቁሶች እንዳሉ ተገምቷል ፤ ከዚህ ውስጥም ከሲሶ በላዩ ለህዋ ምርምር የማያስፈልጉ ቁሳቁሶች ናቸው።

እንደ መረጀው ፥ በየአመቱ ከ110 በላይ የሳተላይት ማምጠቅ ሙከራዎች ይደረጋሉ ፤ በጥቂቱ 10 ሳተላይቶች እና ሌሎች የምርምር ቁሳቁሶች ወደ ትንንሽ ስብርባሪዎች ይቀየራሉ። ይህም ከህዋ ላይ ወደ መሬት የሚወድቁ ነገሮች እንዲበራከቱ አድርጓል።

መረጃው ከኬንያ የማህበራዊ ትስስር መድረኮች፣ ከኒውዮርክ ታይምስ፣ ከቢቢሲ፣ ከአል አይን ፣ ከኬንያ ስፔስ ኤጀንሲ ነው የተገኘው።

@tikvahethiopia
Forwarded from 4-3-3 World News
ናሳ አትስጉ ብሎ ነበር....🪐

የአሜሪካን የጠፈር ምርምር ኢንስቲቲዩት  ፡ የቤት መጠን ያለው አስትሮይድ  2024 YW9 እና አውቶቡስ የሚያህል የሚረዝም   2024 PT5 የተባሉ ሁለት አስትሮይዶች ከምድር አንድ ሚሊየን ኪሎሜትር ርቀው በከፍተኛ ፍጥነት በዛሬው እለት ( Jan 9 ) እንደሚያልፉ ተናግሮ ነበር ።

ናሳ በዚህ መግለጫው እነዚህ አስትሮይዶቹ ምንም እንኳን ለምድር በቀረበ ርቀት የሚጓዙ ቢሆኑም ፡ ስጋት የሚሆኑ  አይደሉምና መረበሽ እንደማያስፈልግ ከትላንት በስትያ አስታውቆ ነበር ።

እናም ትላንት በአንዳንድ ቦታዎች የታየውም ፡ በነዚህ አስትሮይዶች ግጭት የተፈጠረ ፡ እና  ወደምድር ከባቢ አየር የተጠጋ   ሜትሮይት እንደሚሆን ይገመታል ።

@Ethionews433 @Ethionews433
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
[በ40 ምንጭና በተለያዩ አካባቢዎች በሰማይ ላይ እየነደደ የሚጓዘው ምን ይኾን?

የዛሬውን እንግዳ ክስተት በተመለከተ በመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ በፌስቡክ ገፃቸው ካጋሩት ሳይንሳዊ እና ሃይማኖታዊ ምልከታ ሳይንሳዊውን እንደሚከተለው እነሆ👇

💥 ዛሬ ጥር 1/ 2017 ዓ.ም. በሀገራችን በተለያዩ ቦታዎች የታየ በሰማይ እየተቀጣጠለ የሚኼድ በጣም በርካታ ፎቶዎችና ቪዲዮዎች በውስጥ መሥመር እየተላኩልኝ ነበርና ምልከታዬን ለማስቀመጥ እሞክራለኹ።

💥 ከሰማይ ላይ አብርተው ስለሚታዩ ስለሚወድቁ የተፈጥሮና ሰው ሠራሽ አካላት መረዳት ግድ ይላል።
የተፈጥሮ የሕዋ ዐለቶችን አስቀድመን እንመልከት፦
1. አስትሮይድ
2. ሜትዮራይድ
3. ሚትዮር
4. ሜትሮይት
መካከል ያለውን ልዩነት አንድነት መረዳት ያስፈልጋል፡-

1. አስትሮይድ
💥 በዋነኛነት በማርስ እና በጁፒተር መካከል ባለው የአስትሮይድ ቀበቶ ውስጥ የሚገኙት ዐለታማ ሥሪትነት ያላቸው አካላት ናቸው። መጠናቸውን ለመረዳት ለምሳሌ አስትሮይድ ቬስታ መጠኑ 329 ማይል (530 ኪሎ ሜትር) ዲያሜትር ያለው ሲኾን ከታናናሾቹ ውስጥ ከ33 ጫማ (10 ሜትር) በታች የኾኑም ይገኙበታል።  የኹሉም አስትሮይድ አጠቃላይ ክብደት ግን ከምድር ጨረቃ ያነሰ ነው።

👉 በዚኹ አጋጣሚ በኢትዮጵያ አቆጣጠር ዐርብ ሚያዝያ 5/ 2021 ዓ.ም ወይም እንደ ጎርጎርዮሳዊ አቆጣጠር ኤፕሪል 13/ 2029 አፖፊስ የተባለው አስትሮይድ ከምድር በላይ 30,600 ኪሎ ሜትር (19,000 ማይል) ርቀት ላይ የሚያልፍ ሲኾን ቢሊዮኖች በዐይናቸው ያዩታል። መሬትን የመመታት ዕድሉ 2.7 ፐርሰንት ብቻ ነው። (አንድሮሜዳ ክፍል 2 ገጽ 388 - 394 )

2. ሜትዮራይድ
💥 ሜትዮራይዶች በሕዋ ያሉ ትናንሽ ዐለቶች ሲኾኑ መጠናቸው ከከሸዋ ቅንጣት እስከ 1 ሜትር አካባቢ ይደርሳሉ። አንዳንድ ሜትዮራይድ ዐለቶች ሲሆኑ ሌሎቹ ደግሞ ብረታ ብረት ወይም የድንጋይ እና የብረት ውሕዶች ናቸው። ሜትዮራይድ ብዙ ጊዜ ከአስትሮይድ ወይም ከኮሜት ወይም ከሌሎች ፕላኔቶች ጭምር የሚመጡ ናቸው። በአጠቃላይ ሜትዮራይድ ስንል ገና በሕዋ ላይ ያሉትን ነው።

3. ሚትየር
💥 ከላይ እንዳየነው ሜትዮራይድ ወደ ምድር ከባቢ አየር ወይም ወደ ሌላ ፕላኔት በከፍተኛ ፍጥነት ሲገቡ እና ሲቃጠሉ ሚትዮር ይባላሉ።  በሌላ አጠራር “ተወርዋሪ ኮከቦች” ብለን የምንጠራቸው ሲኾን አንዳንድ ጊዜ ሜትየሮች ከቬኑስ የበለጠ ብሩህ ኾነው ሊታዩ ይችላሉ። ያን ጊዜ “የእሳት ኳሶች” ተብለው ይጠራሉ።  ብዙ ተወርዋሪ ከዋክብት በአንድ ላይ በሰዓታት ሲታዩ "ሜትየር ሻወር" በመባል ይታወቃሉ።

4. ሜትሮይት
💥 ሳይቃጠል የምድርን ከባቢ አየር ዐልፎ በምድር ላይ የሚያርፍ የሜትሮይድ ቁራጭ መጠሪያ ነው።  በሰዓት በዐሥር ሺዎች የሚቆጠሩ ኪሎ ሜትሮችን በመጓዝ በኃይለኛ ግፊት ወድቆ ሲበታተን  ብሩህ ነበልባል ይመስላል።
ሜትሮይትስ በሦስት ዋና ዋና ዓይነቶች ይከፈላሉ፡-
1) ድንጋያማ ሜትሮይትስ (በዋነኛነት ከሲልኬት) ማዕድናት የተውጣጡ ናቸው)፣
2) የብረት ሜትሮዮይትስ (በአብዛኛው ከብረት-ኒኬል ውሕዶች የተውጣጡ ናቸው) 
3) ድንጋያማ ብረት ሜትሮይትስ (በግምት እኩል መጠን ያላቸው የሲሊኬት ማዕድናት እና ብረት ኒኬል ይዘዋል)

👉 ሜትሮይቶች ሲታዩ የምድር ዐለቶችን ሊመስሉ ይችላሉ፣ ነገር ግን አብዛኛውን ጊዜ የሚያብረቀርቅ ሊመስል የሚችል የተቃጠለ ውጫዊ ክፍል አላቸው።  ይኸውም በከባቢ አየር ውስጥ በሚያልፉበት ጊዜ የሜትሮይት ውጫዊ ገጽታ ሲቀልጥ የሚፈጠር ነው።

👉በምድር ላይ ከ 50,000 በላይ ሜትሮይትስ ተገኝተዋል.
ከእነዚህ ውስጥ 99.8% የሚሆኑት ከአስትሮይድ የሚመጡ ናቸው።

👉 በየቀኑ 48.5 ቶን የሜትሮይት ቁስ አካል ወደ ምድር ይወድቃል። ይህም በዓመት 17,000 ሚቴዮራይትስ እንደማለት ነው። አብዛኛው ግን በከባቢ አየር ውስጥ ተንኖ ተወርዋሪ ኮከብ ይኾናል።

👉 በቅርብ የተከሰቱ አደገኛ ከሚባሉት የሜትሮይትስ ክስተቶች ውስጥ ኹለቱን በማንሣት ጽሑፌን ልቋጭ፦
1ኛ) በዘመናዊ ታሪክ ውስጥ አንድ ትልቅ ሜትሮይድ ወደ ምድር ከባቢ አየር ውስጥ የገባው እኤአ በ1908 ሲኾን የቱንጉስካ ክስተት በመባል ይታወቃል።  ይህ ሜትዮር በሩሲያ በሳይቤሪያ ላይ የተከሰተ ሲኾን ምድሩን ሳይመታ በፊት በአየር ላይ ጥቂት ማይል ርቀት ላይ ፈነዳ። 

👉 የፍንዳታው ኃይል በመቶዎች የሚቆጠሩ ማይሎች ስፋት ባለው ክልል ውስጥ ዛፎችን ለማውደም የሚያስችል ኃይለኛ ነበር።  ሜትዮሩ 120 ጫማ (37 ሜትር) ስፋት ያለው እና 220 ሚሊዮን ፓውንድ (100 ሚሊዮን ኪሎ ግራም) ይመዝን ነበረ።  በአካባቢው በመቶዎች የሚቆጠሩ አጋዘኖች ሲሞቱ ነገር ግን ማንም ሰው በፍንዳታው መሞቱን የሚያሳይ ቀጥተኛ መረጃ የለም።

2ኛ) እ.ኤ.አ. በ 2013  በቼልያቢንስክ ሩሲያ ሰማይ ላይ ቤትን የሚያህል ሜትሮይድ በሰከንድ ከ11 ማይል (18 ኪሎ ሜትር) በላይ ወደ ከባቢ አየር በመግባት ከመሬት በላይ 14 ማይል (23 ኪሎ ሜትር) ላይ ፈነዳ።  ፍንዳታው ወደ 440,000 ቶን የሚገመተውን የቲኤንቲ ኃይል በመልቀቁ ከ200 ስኩዌር ማይል (518 ስኩዌር ኪሎ ሜትር) በላይ መስኮቶችን የሰባበረ እና ሕንፃዎችን ያበላሽ አስደንጋጭ ኹኔታን ፈጠረ።  በፍንዳታው ይልቁኑ በመስታወት ስብርባሪ ከ1,600 በላይ ሰዎች ቆስለዋል።

💥 ሌላው በሰማይ እየተቃጠሉ ሲሄዱ ሊታዪ የሚችሉት ሰው ሠራሽ ነገሮች
👉 ከአሁን በኋላ የማይሠሩ በጠፈር ውስጥ ያሉ ሰው ሠራሽ  ነገሮች Space debris, space junk, orbital debris በመባል ይታወቃሉ።
ለምሳሌ፡-
👉 የድሮ ሳተላይቶች
👉 የሮኬት ክፍልፋዮች
👉 የፈነዱ ወይም የተጋጩ ተሽከርካሪዎች ወይም የተቆራረጡ ቁርጥራጮች ይገኙበታል።
👉 ከጠፈር ተልእኮ በኋላ የተጣሉ ቁሶች ናቸው።
💥 በግምት ከ10 ሴንቲ ሜትር በላይ ከ36,500 በላይ ቁሶች ሲኖሩ፤ ከ1-10 ሴ.ሜ በላይ 1 ሚሊዮን ቁርጥራጮች እና ከ1 130 ሚሊዮን የሚጠጉ ትናንሽ ቁርጥራጮች ይገኛሉ።

ሊያመጡ የሚችሉት አደጋዎች፡-

1) የሚሠሩ ሳተላይቶችን፣ ዐለም ዐቀፍ የጠፈር ጣቢያ (አይኤስኤስ) ወይም የጠፈር መንኮራኩሮችን በመግጨት ሊጎዳ ይችላል።

👉 አንዳንድ ቁርጥራጮች  ወደ ምድር ከባቢ አየር ውስጥ ከገቡ  መሬት ላይ አደጋ ሊፈጥሩ ይችላሉ።
👉 ለምሳሌ ሰኞ ታኅሣሥ 21/ 2017 ወይም December 30, 2024, በኬንያ፣ ሙኩኩ መንደር ውስጥ ከሮኬት የመለያያ ቀለበት በመባል የሚታወቅ አንድ ትልቅ ብረታማ ነገር የተከሰከሰ ሲኾን  ቀለበቱ በግምት 2.5 ሜትር ዲያሜትር እና 500 ኪሎ ግራም ይመዝናል።  እንደ እድል ሆኖ ግን ምንም ጉዳት አልደረሰም።

✍️ በመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍1