VICTORY OFFICIAL
9.44K subscribers
894 photos
21 videos
84 files
221 links
ለመመዝገብ 👇
@VICTORY_CUSTOMER_SERVICE

የኢንትራንስ ተፈታኝ ተማሪዎቻችን አስተያየት👇 https://t.me/victorystcom_7

☎️ 0914633658
Download Telegram
ትምህርት ሚኒስቴር በ remedial ዘርፍ የምንቀበላቸው ተማሪዎችን እንደሚቀንስ አሳውቋል
3
ይህም የሆነው ያለፈው ተማሪ በመጨመሩ ምክንያት ነው
3
🔔የስራ ማስታወቂያ ፦

ውድ የቪክትሪ ቤተሰቦች በዚህኛው አመት ቪክትሪ አካዳሚ ጥሩ ውጤት ያመጡ በዛ ያሉ ተማሪዎችን ቀጥሮ አብሮ መስራትና ማሰራት ይፈልጋል በመሆኑም ጥሩ ውጤት ያመጣቹ ተማሪዎች ውጤቶቻቹን Screenshoot እያደረጋቹ በInbox በመላክ መወዳደር ትችላላቹ ፣ የ ኢንትራንስ ውጤት ብቻ ሳይሆን ሌሎችንም ክህሎቶችን በዋነኛነት የምንመዝን በመሆኑ ውጤታቹ ዝቅ ያላባቹ ተማሪዎች የሚያስፈልጉትን ዝርዝር ክህሎቶች ከያዛቹ በቪክትሪ ምርጭ ውስጥ የመካተት እድላቹ ሰፊ በመሆኑ በዚህ ሂደት መሳተፍ የምትፈልጉ ተማሪዎች በሙሉ በ Victory customer service በኩል ለአድሚኖቻችን በመላክ የእድሉ ተጠቃሚ መሆን ትችላላቹ።

በዚህ link አድሚኖቻችንን ማግኘትና ማናገር ትችላላቹ👇

@VICTORY_CUSTOMER_SERVICE

ፈጣሪ ይረዳቹ ዘንድ ቪክትሪ መልካም እድልን ለሁላቹ ይመኛል 🙏




© Victory Is A State Of Mind !
9👏1
VICTORY OFFICIAL pinned «🔔የስራ ማስታወቂያ ፦ ውድ የቪክትሪ ቤተሰቦች በዚህኛው አመት ቪክትሪ አካዳሚ ጥሩ ውጤት ያመጡ በዛ ያሉ ተማሪዎችን ቀጥሮ አብሮ መስራትና ማሰራት ይፈልጋል በመሆኑም ጥሩ ውጤት ያመጣቹ ተማሪዎች ውጤቶቻቹን Screenshoot እያደረጋቹ በInbox በመላክ መወዳደር ትችላላቹ ፣ የ ኢንትራንስ ውጤት ብቻ ሳይሆን ሌሎችንም ክህሎቶችን በዋነኛነት የምንመዝን በመሆኑ ውጤታቹ ዝቅ ያላባቹ ተማሪዎች የሚያስፈልጉትን…»
Grade-12 ዝግጁ?...🙌

እስካሁን ውጤት  በፍጥነት የምታዩባቸውን አማራጮች ለመጥቀስ ያክል ፦

@EAESbot
eaes.et
eaes.gov.et
eaes.edu.et
result.neaea.gov.et
SMS 6284

Network አስቸጋሪ ሊሆን ስለሚችል በትዕግስት ጠብቁ እኛም ከዚህ በተጨማሪ ከ አድሚኖች እና የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ጋር በመሆን በዚህ ቻናል ዉስጥ እናንተን ምናግዛችሁ ይሆናል😊

አይዟቹ ፈጣሪ ከጎናቹ አለ ጥሎ አይጥላቹም ቤተሰቦች መልካም ዕድል እኖዳቹኃለን🙏

ሁሉም ተማሪ እንዲጠቀም ፤ አብሮን ያለ ችግር እንዲያይ ሼር አድርጓቸው

ውጤት አብረን የምናይበት አድራሻ ቻናል👇

https://t.me/VictoryTutor_7


©  Victory Is A State Of Mind 🏆
9🔥2
ብዙ ተማሪዎች ዝግጅት ለመጀመር ሲያስቡ 9ኛ፣ 10ኛ፣ 11ኛ እና 12ኛ ክፍል መጻሕፍት ተደርድረው ሲያዩአቸው አእምሯቸው ይደናገጣል። በዛ ላይ "ከ9ኛ ልጀምር ወይስ ከ11ኛ?" የሚለው ጥያቄ ያሰሯቸዋል።

እውነተኛው እና መሬት ላይ ያለው መፍትሔ ይህ ነው፦

"ከየት ልጀምር?" (WHERE TO START)

አጀማመራችሁ በ 3 ደረጃዎች (Steps) የተከፈለ መሆን አለበት፦

1️⃣የመጀመርያው፦ ከ11ኛ ክፍል ጀምሩ

ለዚህ ትልቅ ምክንያት የ11ኛ ክፍል ትምህርት በኢንትራንስ ፈተና ላይ ከፍተኛውን ድርሻ (እስከ 35-45%) ይይዛል ።በተጨማሪም ገና አምና የተማራችሁት ስለሆነ አእምሯችሁ በፍጥነት ለማስታወስ አይቸገርም። ይህም አቅም እና በራስ መተማመን ይሰጣችኋል።

2️⃣ሁለተኛው (ትምህርት ሲጀምር)፦ ከ12ኛ ክፍል ጋር እኩል ተጓዙ

ብዙ ተማሪዎች 12 ክፍል ላይ ክፍለጊዜ ሲቀጡ(ሲፎርፉ) እና በነዛ ጊዜያትላይ 9 እና 10 ሲያነቡ ይስተዋላሉ ይህ ፈጽሞ ስህተት ነው 12 ክፍልን ስትማሩ ለኢንትራንዝ እየተዘጋጃችሁ በማሰብ ምትማሩትን እያንዳንዱን ቻፕተር በደንብ እያጠናችሁ short ኖት በማውጣት መልሳችሁ እንዳዲስ ላለማጥናት እግረመንገዳችሁን ለኢንትራንስ ዝግጅት ምታደርጉበት ትልቅ እድል መፍጠር ትችላላችሁ።

ትምህርት ቤት ሲጀምር የመምህራንን ክፍለ-ጊዜ በፍጹም አትቅጡ። የ12ኛ ክፍልን ትምህርት "ዛሬ የተማራችሁትን ዛሬውኑ" አጠናቁ። የ12ኛ ክፍል ትምህርት ከተከማቸ በኋላ ወደ ኋላ ተመልሶ ማንበብ እጅጉን ይከብዳል።

3️⃣ሶስተኛው (ጎን ለጎን ምታስኬዱት)፦ 9ኛ እና 10ኛ ክፍል

የ9 እና የ10ኛ ክፍል መጻሕፍትን ገጽ በገጽ ማንበብ ጊዜ ማባከን ነው። ይበልጥ የሚያስፈልጉት መሠረታዊ ነጥቦች (Basic Concepts) ብቻ ናቸው። ስለዚህ የ9 እና 10ኛ ክፍልን ይዘት መጀመርያ 11 እና 12 ክፍልን ካያቹ በኋላ መሰረታዊ የሆኑትን እና ህሳባቸው 11 እና 12 ላይ የሌሉትን ነገርግን ጥያቄ ሚወጣባቸውን ለይታችሁ ብቻ አንብቡ።

ምክንያቱም 11 እና 12 ክፍል ላይ ያሉት ቶፒኮች ከገባችሁ የ 9 እና 10 ላይ ያሉትን መረዳት ብዙም አይከብዳችሁም አብዛኞቹ ለ 11 እና 12 መሰረት ሚጣልባቸው ቶፒኮች ስለሆኑ ማለት ነው።

»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»
ከወዲሁ ለኢንትራንስ ዝግጅትታችሁን መጀመር የምትፈልጉ ተማሪዎች ታች ባለው ሊንክ ተቀላቀሉን
@VICTORY_CUSTOMER_SERVICE
11👍1
ውጤት ማየት ተጀምሯል ። መልካም ዕድል ቤተሰቦች

ውጤታቹን ከታች ባለው ቴሌግራም ላይ ላኩልን👇👇👇
@VICTORY_CUSTOMER_SERVICE
1
ውጤት እንዴት ሆነላቹ ቤተሰቦች
🎉10
እጅግ በጣም ብዙ ተማሪዎቻችን በ Inbox በኩል እንዳለፋቹ በስፋት እየገለፃቹልን ትገኛላቹ በጣም ደስ ብሎናል እንኳን ደስ አላቹ ።

ይህንን ያደረገ ልዑል አምላክ የተመሰገነ ይሁን ሁላቹም ፈጣሪያቹንና አምላካቹን ቅድሚያ ከሁሉ በላይ አመስግኑ እርሱ ጥሎ አልጣላቹም🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏
🙏273👍3
Forwarded from #€.,.,¥
2
Forwarded from #€.,.,¥
Alifalew benante erdata tlk wtet amtche amesegnalew
5
እንኳን ደስ አላቹ እንኳን አብሮ ደስ አለን እስካሁን ባለው ሂደት ቪክትሪ ከ 513.75 ወይንም 85 percent የመጣ ሲሆን ይህቺም የምንወዳት ሴት ተማሪ እህታችን ቤተልሔም ተስፋዬ አረጋይ ሆናለች እንኳን ደስ አለን አላቹ 🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏

ሌሎች ቤተሰቦችም እንዲሁ በብዛት እየላካቹ የምስጋና መልዕክት እያስቀመጣቹ ነውና በጣም እናመሰግናለን ልፋታችን በፍሬ በማየታችን በእውነት እናመሰግናለን ፈጣሪ ጨምሮ ይባርካቹ።
ነገ ደግሞ ከዚህ በላይ የምንጠብቃቹ ተማሪዎች አላቹ ውጤቶችን እየተከታተልን ለእናንተ እናደርሳለን መልካም እድል ለሁላቹ ውድ ቤተሰቦቻችን
7👍2
Forwarded from ✨JUST ME✨
Forwarded from ✨JUST ME✨
Igziabiher yimesgen ke inante gar asaktenewal bexam bexam ameseginalew victorywoch thank you.
ውድ የቪክትሪ ተማሪ ቤተሰቦች በጣም የምንወደው ተማሪ ልጃችን ናኦል ፍቃዱ እስካሁን በቪክትሪ ታሪክ መጥቶ የማያውቅ ምርጡን ውጤት ከ 600 ውስጥ 543.17 ወይንም average 90.53 በማምጣት ከፍተኛውን የቪክትሪ ሰንጠረዠ ፉክክር እየመራ ይገኛል እንኳን ደስ አለክ እንኳን ደስ አለን ደስ አላቹ ይህ የልጁና የቪክትሪ ትልቅ የስራ ውጤት ነውና አምላካችንን በእጅጉ እናመሰግናለን !!
ልፋታችንን በተግባር ስለምታሳዩን እናመሰግናለን🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏

ሌሎች እጅግ በጣም ብዙ የምትሆኑ ተማሪዎች የምስጋና እና የደስታ መልዕክታቹን እያጋራችሁን ነውና በጣም እናመሰግናለን በርቱልን በጣም ደስ ብሎናል ኮርተንባቹኃል
👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏


© Victory Is A State Of Mind 🏆
8
🔔ማስታወቂያ ውድ የቪክትሪ ተማሪ የነበራቹ ቤተሰቦች ያመጣቹት ውጤት የት ዩኒቨርስቲ እንደሚያስገባ ማወቅ እንፈልጋለን ባላቹት መሰረት የትኞቹን ዩኒቨርስቲዎች እንደሚያስገባቹ ለእያንዳንዳቹ የኛ ለነበራቹ ተማሪዎቻችን ልንነግራቹ ዝግጅታችንን አጠናቀናል በመሆኑም ከታች ባለው Inbox ለዚህ አላማ ያስቀመጥናቸውን ባለሞያዎች(experts) ውጤታቹን በመላክ ልታገኟቸው የምትችሉትን ዩኒቨርስቲዎች ማወቅ ትችላላቹ👇

@VICTORY_CUSTOMER_SERVICE

ማሳሰቢያ፦ይሄ አገልግሎት የሚሰጠው የኛ ተማሪ ለነበራቹ ተማሪዎች ብቻ ይሆናል




© Victory Is A State Of Mind 🏆
👏21
Forwarded from Wende mak
አኔ ነሐሴ ዉስጥ ነበር victory academy yetekelakelkut አናንተ ጋር በነበርኩበት 1 ዓመት ብዙ tmriyalehu ዉጤቱ ብዙም bayasdestm ግን አግዚአብሔር ይመስገን አና ምን llachhu ፈልጌ ነው አናንተ ጋር ስማር ፅናት, ትግስት ትንሽ አንብበው ጥሩ ዉጤት ማምጣት endemichal ብቻ bzunegerachu አሪፍ ነበር ማለት አችላለሁ sleneberen ቆይታ ከልብ የመነጨ ምስጋናዬን አቀርባለሁ 🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
ለ2019 E.C. የኢንትራንስ ተፈታኞች በሙሉ የተዘጋጀ ወሳኝ ጥሪ ከVictory Academy!

ውድ ተማሪዎች... በዚ ሰአት የማትሪክ ውጤታቹ ላይ ትልቁን ልዩነት የሚፈጥረው ለስንት ሰዓት እንደደከማችሁ ሳይሆን፣ በምን ያህል ብልሃትና ስትራቴጂ እንደተዘጋጃችሁ ነው!

የቀደሙት ዓመታት የፈተና ውጤቶች እንደሚያሳዩት፣ ብዙ ተማሪዎች የሚያንሳቸው መጽሐፍ ማንበብ ሳይሆን እንዴት ማንበብ እንዳለባቸው አለማወቅቸው(ስትራቴጂ) እና የስነ-ልቦና ጥንካሬ አለመኖር ነው።

ይህንን ችግር ለመፍታት፣ Victory Academy ለ2019 E.C. ተፈታኞች በአዲስ መልኩ ልዩ የቱቶሪያል (Tutorial) ፕሮግራም በይፋ መጀመሩ ይታወቃል።

💡 Victory ለኢንትራንስ ሙሉ በሙሉ ብቁ የሚያደርጋችሁ በምን በምን እንደሆነ ያውቃሉ?

Victory ዝም ብሎ ተጨማሪ ትምህርት የሚሰጥበት ቦታ አይደለም፤ ይልቁንም ውጤታማ አጠናንን እና የፈተና ጥበብን የምታጥቁበት የተጠና የስትራቴጂ ማዕከል ነው፦

1️⃣ የላቀ የጥናትና የፈተና ስልቶች (Advanced Study Strategies)

The 80/20 Concept Focus: ከመጽሐፉ ይዘት ውስጥ በከፍተኛ መጠን ፈተና የሚወጣባቸውን ዋና ዋና (Core) ርዕሶች ላይ ያተኮረ ትምህርት።

Active Recall & Pattern Recognition: ጥያቄዎችን ገና በአይን በማየት ብቻ የፈተና አውጪዎችን አስተሳሰብ የመረዳትና በ30 ሰከንድ ውስጥ መልስ የማይሆኑትን እና የሚሆኑትን የመለየት ብልሃት።

The Error Journal System: የተሳሳታችኋቸውን ጥያቄዎች ወደ ጥንካሬ የምትቀይሩበት የራሳችሁ ልዩ የስህተት መዝገብ አዘገጃጀት እና አሰራር።

2️⃣ ሙሉ የስነ-ልቦና እና የትኩረት ዝግጅት (Psychological Readiness)

Exam Anxiety Control: የፈተና ፍርሃት እና የመደናገጥ ስሜትን ሙሉ በሙሉ የሚሰብሩ የስነ-ልቦና ስልጠናዎች ።

Time & Focus Management: ትኩረታችሁ ሳይበታተን፣ የስልችት ስሜት ሳይሰማችሁ በከፍተኛ ፍላጎት የመማርና ሰዓትን በአግባቡ የመጠቀም ጥበብ።

Personal Mentorship: በየሳምንቱ ደረጃችሁን የሚከታተሉ እና ክፍተታችሁን የሚሞሉ የባለሙያ መምህራን እና የዩንቨርስቲ ተማሪዎች ምክር።

3️⃣ Real Exam Simulation

ልክ እንደ እውነተኛው የሀገር አቀፍ ፈተና የተዘጋጁ Model Exams እና የሰዓት ገደብ ልምምዶች ተማሪዎቻችን ፈተናው እለት ምንም አይነት የመረበሽ ስሜት እንዳይሰማቸው ያደርጋል።

»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»
ከወዲሁ ለኢንትራንስ ዝግጅትታችሁን መጀመር የምትፈልጉ ተማሪዎች ታች ባለው ሊንክ ተቀላቀሉን
@VICTORY_CUSTOMER_SERVICE
9
♦️የተሰላ የክለሳ ጊዜ ሰሌዳ♦️

ኢንትራንስ ተፈታኞች ሙሉ በሙሉ ማለት ይቻላል የማያውቁት ወይም አውቀውት እንኳ የማይተገብሩት፣ ነገር ግን የከፍተኛ ውጤት አምጪዎችን (Top Scorers) ውጤት የሚወስን አንድ ትልቅና ውጤታማ ስልት አለ። እሱም፦ "Spaced Repetition with Active Spacing" (የተሰላ የክለሳ ጊዜ ሰሌዳ) ይባላል።

🧠 ይህ ስልት ምንድነው?

አብዛኛው ተማሪ ትልቅ ስህተት ይሰራል፦ አንድን ቻፕተር ዛሬ ያጠናና "አውቄዋለሁ" ብሎ ዘግቶ ያስቀምጠዋል። ከዚያ ከ2 ወይም ከ3 ወር በኋላ ፈተና ሲደርስ ይከፍተዋል። ያኔ አእምሮው ሙሉ በሙሉ ረስቶታል!

"Ebbinghaus Forgetting Curve" በሚባለው የኒውሮሳይንስ ህግ መሰረት፣ አእምሯችን ያጠናነውን ነገር በ24 ሰዓት ውስጥ እስከ 70% የሚሆነውን ይረሳዋል።

ይህንን የነገሮችበቶሎ የመርሳት ችግር የሚሰብረው መፍትሄ መጽሐፉን ደጋግሞ ማንበብ ሳይሆን፣ "አእምሮ መርሳት ሲጀምር በትክክለኛው ሰዓት ደግሞ እንዲያስታውስ ማስገደድ" ነው። ይህንን ለማድረግ

📅 የ3-7-21 የክለሳ ህግ (The Spaced Interval System)

ይህንን ስልት ለመተግበር ተማሪዎች ትልቅ ፕሮግራም ማውጣት አይጠበቅባቸውም። የደብተራቸው ወይም የኖታቸው የመጀመሪያ ገጽ ላይ 3 ቀናት ብቻ መመዝገብ ይበቃቸዋል፦

ቀን 1 (ከ3 ቀን በኋላ)፦ በዚ ቀን ላይ ዛሬ ያጠናችሁትን ቻፕተር ከ3 ቀን በኋላ መጽሐፉን ሳትከፍቱ በባዶ ወረቀት ላይ አእምሮአቹ የሚያስታውሰውን ብቻ ለመጻፍ ምክሩ (ለ15 ደቂቃ ብቻ)።

ቀን 2 (ከ7 ቀን በኋላ)፦ በዚ ቀን ደግሞ ያለፈ ዓመት የማትሪክ ጥያቄዎችን ብቻ ውሰድቹ ስሩ ይህም ይበልጥ አእምሮአቹ ውስጥ እንዲቀመጥ እና በቀላሉ እንዳትረሱት ይረዳቹሃል (ለ20 ደቂቃ)።

ቀን 3 (ከ21 ቀን በኋላ)፦ ጥያቄ በምትሰሩበት ሰአት ከዚ በፊት እንዳወራነው የተሳሳታችሁትን ጥያቄ በተለይም ደግሞ በተደጋጋሚ የምትሳሳቷቸውን ጥያቄዎች 'Error Journal' (የስህተት ደብተር) ላይ አስፍሩአቸው ብለናችሁ ነበር ታዳ በዚኛው ቀን ይህን Error Journal' (የስህተት ደብተር) ብቻ ትከልሳላችሁ።

🎯 አብዛኛው ተማሪ "አዲስ ቻፕተር ጨረስኩ" በሚለው የውሸት እርካታ ስለሚታለል፣ ወደ ኋላ ተመልሶ የቀደመውን በየጊዜው መከለስ ጊዜ ማባከን ይመስለዋል።

ነገር ግን በኢንትራንስ ፈተና አሸናፊ የሚሆነው ብዙ ቻፕተር ያነበበው ሳይሆን፣ ያነበበውን ፈተና አዳራሽ ድረስ ይዞ መግባት የቻለው ተማሪ ብቻ ነው!

💡
"የኢንትራንስ ትልቁ ምስጢር፦ ብዙ ማንበብ ሳይሆን፣ አለመርሳት ነው!

አእምሮአቹ ያጠናውን ነገር በ24 ሰዓት ውስጥ 70% ይረሳዋል። ስለዚህ አዲስ ቻፕተር ለማብዛት ከመሮጣቹ በፊት፣ ዛሬ ያጠናችሁትን የዛሬ 3 ቀን፣ የዛሬ 7 ቀን እና የዛሬ 21 ቀን አእምሮአቹን ጠይቃቹ ማውጣት (Active Recall) ልማድ አድርጉ።

መቼ መከለስ እንዳለባቹ ማወቅ፣ ከማንበብ በላይ ውጤትን ይወስናል!"


»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»»
ከወዲሁ ለኢንትራንስ ዝግጅትታችሁን መጀመር የምትፈልጉ ተማሪዎች ታች ባለው ሊንክ ተቀላቀሉን
@VICTORY_CUSTOMER_SERVICE
4🥰2