ወጥረን የምንሰራው እንኳን ደህና መጣህ እና ደሞ መጣህ የሚለው ልዩነቱ ሰለገባን ነው..🤔
👍29
በጣም ከረጅም ጊዜ በፊት አንድ ማታ ላይ ነው እናቴ በጣም የተቃጠለ ዳቦ ለአባቴ አቀረበችለት፡፡ ነገር ግን አባቴ ዳቦውን በልቶ ወደኔ ዞሮ "የትምህርት ቤት ውሎህ እንዴት ነበር?" አለኝ ምን እንዳልኩት አላስታውስም የማስታውሰው እናቴ ዳቦው ተቃጠለብኝ ብላ ይቅርታ መጠየቋን ነበር ! አባቴ መቼም ልረሳው የማልችለው መልስ ነበር ለእናቴ የሰጣት የኔማር የተቃጠለ ዳቦ እወዳለሁ እኮ አላት
የዛን ቀን ማግስት ወደ መኝታዬ ልሄድ ስል አባቴን አንድ ጥያቄ ጠየኩት "አባዬ ግን አንተ በእውነት የተቃጠለ ዳቦ ትወዳለህ ?" አልኩት እቅፍ አደረገኝና "አየህ ልጄ እናትህ ሁል ጊዜ ስትለፋ ነው የምትውለው በዛ ላይ ደግሞ የተቃጠለ ዳቦ ማንንም አይጎዳም!
ነገር ግን መጥፎ ቃላቶች ናቸው ሰውን የሚጎዱት! ሕይወት በጎዶሎ ነገሮችና ሙሉ ባልሆኑ ሰዎች የተሞላች ናት ! እኔ ደግሞ በምንም ነገር ምርጥ ነኝ ብዬ አላስብም በሕይወቴ የተረዳሁት ነገር ቢኖር የሰውን ጥፋት መቀበልና ልዩነትን በመቻቻል ማሳለፍ ነው! ይህ ደግሞ ዘላቂና ጤናማ ለሆነ ግንኙነት መሰረት ነው ..🙏🙏🙏

❤35
"የመጀመሪያ ባሌ፣ የልጄ አባትና የህይወቴ ትልቅ እቅድ ነበር። አንዲት ልጅ ወልደን ከተለያየን በኋላ ቤተሰቤን ለመደገፍ ወደ ሳውዲና ኦማን ተሰደድኩ። አራት ዓመት ሙሉ በሰው ሀገር ስለፋ እሱ ግን 'ሌላ አላገባም፣ እሷን ነው የምጠብቀው' እያለ ለእናቴ ይነግራት ነበር። ልጄ አባት አልባ ሆና እንድታድግ ስላልፈለግሁ፣ የቀረበልኝን ጥሪ አምኧ ወደ ሀገሬ ተመለስኩ።
ሰርጋችን በደመቀ ሁኔታ እንዲከናወን ተወሰነ። እኔ ለእናቴ አንድ ልጅ ነኝ፤ የሰርግ ቀንዋን ማየት የእሷ ትልቅ ህልም ነበር። ጥሪ ወረቀቶች ተበትነው፣ ድግሱ ተደግሶ፣ እኔም የሙሽርነት ልብሴን አምሬ ለብሼ ጠበቅኩት። የስድስት ወር ነፍሰ ጡር ነበርኩ። ነገር ግን በዚያ ትልቅ ቀን ሙሽራው አልመጣም! 'ስራዬን አልጨረስኩም' ከሚል ባዶ ምክንያት ውጭ ምንም አላለም።
እንግዶች መጡ፣ ተስተናገዱ፤ እናቴ ግን የወሬውንና የጥያቄውን ማዕበል ሁሉ ብቻዋን ተቀበለች። የስብራቷ ስፋት ከእኔ በላይ ነበር። ከወር በኋላ ያው ሰው ምንም እንዳልተፈጠረ ደውሎ 'ምነው ጠፋሽ?' ሲለኝ ያን ያህል ቀላል አድርጎ ማየቱ ልቤን በእጅጉ አሰቃየው።
አካባቢው በሙሉ በሁኔታው ደንግጦ ራሴን እንዳላጠፋ ይፈራ ነበር። ህመሙና ውርደቱ ቢከብድም ህይወት መቀጠል ነበረባት። ወገቤ ሳይጸና፣ ሁለተኛዋን ልጄን ወልጄ በወሯ ሁለቱንም ህፃናት ለእናቴ አስረክቤ ወደ ዱባይ ተሰደድኩ። እንቅልፍ በግማሽ ሰዓት እየለካሁ፣ ህመም ሳይበግረኝ፣ በህገ-ወጥነትም ቢሆን ለሦስት ዓመታት ደክሜ ሠሸሁ። ዓላማዬ አንድ ብቻ ነበር፤ ልጆቼ የእኔን የወደቀ ህይወት እንዳይደግሙትና ተማረው እንዲያድጉ።
አሁን በ2017 ዓ.ም. ወደ ሀገሬ ተመልሻለሁ። ምንም ገንዘብ ባይኖረኝም የልጆቼ በፍቅር የተቀበሉኝ እቅፍ ትልቅ ሀብቴ ነው። እኔም ያደግሁት አባቴን ሳላውቅ በእናትና አያቴ እጅ በመሆኑ፣ የልጆቼ ህይወት የተሻለ እንዲሆን እታገላለሁ።
ዛሬ ላይ የምፈልገው አንዱና ዋነኛው ነገር ወደ አረብ ሀገር ላለመመለስ ነው! እናቴን ማሳረፍና ልጆቼን ሰብስቤ በአንድ ጣሪያ ስር መኖር እፈልጋለሁ። የባልትና ስራዎች (ሽሮና በርበሬ በማዘጋጀት) ውጤታማ መሆን እችላለሁ፤ በዚህ ስራ የሚያግዘኝና የሚያበረታታኝ ደግ ሰው ባገኝ ደስ ይለኛል። በተጨማሪም ያሳለፍኩት ከባድ የህይወት አሰቃቂ ገጠመኝ እስካሁን ስለሚረብሸኝ የሥነ-ልቦና ድጋፍ ያስፈልገኛል።
ብንሰበርም አንወድቅም! ያን ጊዜ ብወድቅ ልጆቼ ዛሬ እዚህ አይደርሱም ነበር።
የሸገር ኢንፎ ሚዲያ

❤11👏2
ልጁን በትከሻው አዝሎ ብዕር ይሸጥ የነበረው ስደተኛ አብዱል ሀሊም አል-አታር ዛሬ የት ደረሰ?
በህይወትዎ ተስፋ የቆረጡበት፣ "ነገስ ምን እሆናለሁ?" ብለው የተጨነቁበት ቀን አለ? እንግዲያውስ ይህ እውነተኛ ታሪክ ጥንካሬንና ተስፋን ይስጥዎት ዘንድ እንመኛለን።🤞
ይህ በምስሉ ላይ የምታዩት ሰው አብዱል ሀሊም አል-አታር (Abdul Halim al-Attar) ይባላል። በሊባኖስ ቤይሩት ጎዳናዎች ላይ እጅግ በሚለበልብ ፀሐይ ውስጥ፣ የ4 ዓመት ህጻን ልጁን በትከሻው ላይ አዝሎ ብዕር (እስክሪብቶ) ሲሸጥ በድንገት ፎቶግራፍ የተነሳ ፍልስጤማዊ-ሶሪያዊ ስደተኛ ነው።💔
ልጁ በትከሻው ላይ ተኝታለች... እሱ ግን ለነገው እንጀራ ሲል የሚወርደውን ከባድ ሙቀት ተቋቁሞ ብዕር ይሸጣል። ይህ ምስል በ2015 ዓ.ም በኢንተርኔት ላይ ሲሰራጭ የዓለምን ህዝብ ልብ ሰበረ።😍
ነገር ግን ታሪኩ እዚህ ላይ አላበቃም! ይልቁንም የአንድ ትልቅ ተአምር መጀመሪያ ሆነ፦
• የፍቅር ማዕበል፡ አንድ አይስላንዳዊ ጋዜጠኛ በከፈተው የገንዘብ ማሰባሰቢያ ገፅ አማካኝነት፣ ካሰበው 5 ሺህ ዶላር በላይ አልፎ፣ ከመላው ዓለም በተሰበሰበ እርዳታ ከ191,000 ዶላር በላይ ሊሰበሰብ ቻለ።💰
• ከጥገኛነት ወደ ቀጣሪነት፡ አብዱል ሀሊም የተሰጠውን ገንዘብ ለራሱ ብቻ አልበላውም። በቤይሩት ከተማ የራሱን ዳቦ ቤት፣ የከባብ ሱቅ እና ሬስቶራንት ከፈተ።💪
• የሌሎች ተስፋ ሆነ፡ በራሱ ድርጅቶች ውስጥ ከ16 በላይ የሚሆኑ አብረውት የተሰደዱ ሶሪያውያንን በመቅጠር የሥራ ዕድል ፈጠረላቸው።
• የቤተሰብ ደህንነት (Family Welfare)፦
የተሰበሰበው ገንዘብ ልጆቹን (ወንድ ልጁን አቡዲን እና ሴት ልጁን ሪምን) ከጊዜያዊ መጠለያ አውጥቶ ደህንነቱ ወደተጠበቀ ባለ ሁለት መኝታ ክፍል አፓርታማ እንዲያዛውር አስችሎታል። በተጨማሪም በመጨረሻ ልጆቹን ወደ ትምህርት ቤት መላክ የቻለ ሲሆን፣ በሶሪያ ውስጥ በችግር ላይ ለሚገኙ ዘመዶቹ እና ጓደኞቹ ወደ 25,000 ዶላር የሚጠጋ ገንዘብ በእጁ ወስዶ አስረክቧል።
አብዱል ሀሊም ከጎዳና ተዳዳሪነት ተነስቶ የብዙዎች መጠለያ እና የስራ አባት መሆን ቻለ። ይሄ ታሪክ የሚያስተምረን አንድ ትልቅ እውነት አለ፦
"አንዳንድ ጊዜ ያሰብከው ብዕር መሸጥ ብቻ ሊሆን ይችላል፤ ፈጣሪ ግን ካንተ ጀርባ የብዙዎችን ህይወት የሚቀይር ትልቅ በር ሊከፍትልህ ይፈልጋል።"
በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ ብትሆኑ ተስፋ አትቁረጡ። ዛሬ የምታልፉበት መከራ የነገው ስኬታችሁ መነሻ ሊሆን ይችላል።
🙏🙏🙏

👏5❤4👍3
እድል ወይስ ስሌት? 14 ጊዜ ሎተሪ ያሸነፈው ሊቅ ግለሰብ ሚስጥር!
ስቴፋን ማንደል (Stefan Mandel) የተባለ ሮማኒያዊ የሂሳብ ሊቅ (Mathematician) በአለም ላይ ሎተሪን 14 ጊዜ ያሸነፈ ብቸኛ ሰው ነው። ስቴፋን ሎተሪን ያሸነፈው በእድል ሳይሆን በሂሳብ ቀመር (Formula) ነበር።
በወቅቱ የሎተሪውን ህግና ቁጥሮች በደንብ ካጠና በኋላ ሁሉንም የቁጥር አማራጮች ሊሸፍን የሚችል በሚሊዮን የሚቆጠሩ የሎተሪ ቲኬቶችን በአንድ ጊዜ በመግዛት አሸናፊ መሆኑን ያረጋግጥ ነበር።
ከአንድ ጊዜ በላይ በተደጋጋሚ ሚሊዮኖችን ሲያሸንፍ የሎተሪ ድርጅቶቹና መንግስት ግራ ገባቸው። በመጨረሻም እሱን ለመከላከል ሲሉ የሀገሪቱን የሎተሪ ህግ ለመቀየር ተገደዱ። ዛሬ ላይ እሱ የተጠቀመበት ዘዴ በአለም ዙሪያ በህግ የታገደ ነው...🤔

👏8❤1
North Korea ግን ምን አይነት ሀገር ነች..🤔
በአንድ ቀን 6 billion dollar hack ..በኢትዮጵያ ስንት ብር ይሆናል..🙆♂️

🥱5🙉3
አእምሮህ የሚያስበውን ብቻ አይደለም… የሚደጋግመውን ይገነባል።
3 ነገሮችን ተጠንቀቅ፦
1. በየቀኑ የምትመለከተውን።
የምታነበው፣ የምትሰማው እና በስልክህ የምታሳልፈው ጊዜ በአስተሳሰብህ ላይ ተፅዕኖ ያሳድራል።
አእምሮህ የሚደጋገምለትን መረጃ የበለጠ ተደራሽ ያደርገዋል።
1. ለራስህ የምትነግረውን።
“አልችልም” ብለህ ደጋግመህ ስትነግረው ችግሩ እውነት መሆኑ ሳይሆን፣ አእምሮህ ያንን እንደ መነሻ ሊወስደው ይችላል።
ስለዚህ “አልችልም” ከማለት ይልቅ “ገና አልቻልኩም፤ ግን መማር እችላለሁ” በል።
1. የምትደጋግመውን ተግባር።
እውቀት ብቻ ለውጥ አያመጣም።
እውቀት → ተግባር → ድግግሞሽ → ልማድ።
ስለዚህ ሕይወትህን መቀየር ከፈለግክ፣ መጀመሪያ የምታስገባውን መረጃ፣ የምትነግረውን ራስ-ንግግር እና የምትደጋግመውን ተግባር ቀይር።
ምክንያቱም የዛሬ ድግግሞሽህ የነገ ማንነትህን እየገነባ ነው።
አስብ። ተማር። እደግ።

❤16