Haileyesus Official News
5.82K subscribers
1.95K photos
150 videos
11 files
731 links
Download Telegram
አምና በዚህ ወቅት የሰንበት ት/ ቤት አባልና የዘጠነኛው ሺ ተከታታይ ድራማ ተዋናይ ሱራፊል ብስራት (አቡ ) በቅድስት ቤተክርስቲያን ስርአተ ህግ ጋብቻውን ፈፅሟል 🥰 አሁን ላይ ለኛ ቀልድ ለራሱ ቁምነገር ጭኗል
congratulations
ዜና እረፍት
ተወዳጇ ተዋናይት ሰላማዊት ደስታ ከእዚህ ዓለም በሞት ተለየች

በፊልም ቲያትር እና በሌሎችም ተወዳጅ ጥበባዊ ሥራዎቿ ዝናን ያተረፈችው አርቲስት ሰላማዊት ደስታ ከእዚህ ዓለም በሞት ተለይታለች።።

አርቲስት ላማዊት ደስታ ባደረባት ህመም ሳቢያ በህክምና ስትረዳ ቆይታ ዛሬ ዓርብ ግንቦት 21 ቀን 2018 ዓ.ም ማረፏን የቅርብ ወዳጇና አብሮ አደጓ ጋዜጠኛ ግርማ ፍስሃ አስታውቋል።

የሽኝት ፕሮግራሙ ነገ ቅዳሜ ግንቦት 22 ቀን 2018 ዓ.ም 3:00 በሀገር ፍቅር ቲያትር የሚከናወን ሲሆን፣ የቀብር ሥነ-ሥርዓቷም በማኅደረ ስብሐት ቅድስት ልደታ ለማርያም እና ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ከቀኑ 7:00 ሰዓት ጀምሮ ይፈፀማል።" ሲል አስታውቋል።

የዝግጅት ክፍላችን በአርቲስት ሰላማዊት ደስታ ዜና እረፍት የተሰማውን ሀዘን እየገለፀ ለቤተሰቦቿ፣ ለሙያ አጋሮቿና አድናቂዎቿ መፅናናትን ይመኛል።

#ዳጉ_ጆርናል
5😢4👏1
የጋና ፓርላማ የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነትን እና ተግባራቱን የሚያስተዋውቅ የትኛውንም እንቅስቃሴ ወንጀል የሚያደርግ ሕግ አጸደቀ። በተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት ውስጥ ተሳትፎ የሚገኝ ማንኛውም ግለሰብ በሦስት ዓመት እስራት እንደሚቀጣ ሕጉ ይደነግጋል።
6
አትሌት ደራርቱ ቱሉ ልጇን ዳረች‼️

ጀግናዋ አትሌት ደራርቱ ቱሉ ወንድ ልጇን ተስፋዬ ፀጋውን ትናንት ድራለች ። የረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ ልጅ
ኢንጅነር ተስፋዬ ፀጋው ከገብሬላ ተስፋዬ ጋር ነዉ የተሞሸረዉ።

ተስፋዬ ከአሜሪካው ፍሎሪዳ ዩኒቨርሲቲ በኢንጅነሪግ በከፍተኛ ማዕረግ የተመረቀ ሲሆን፤ ከተመረቀም በኋለ በኢትዮጵያ የረ/ኮ ደራርቱ ቱሉ ድርጅት ውስጥ ጠቅላላ ስራ አስኪጅ ሆኖ እንያገለገለ ይገኛል።
በጋምቤላ የተሽከርካሪ እንቅስቃሴ ታገደ

በጋምቤላ ክልል በ7ኛ ጠቅላላ ምርጫ ዋዜማ የተሽከርካሪ እንቅስቃሴ ሙሉ በሙሉ መታገዱን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል።

ከዛሬ ግንቦት 23/2018 ዓ.ም ጠዋት ጀምሮ በክልሉ የሚገኙ ማንኛውም ተሽከርካሪ እንቅስቃሴ እንዲያቆሙ የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን አቅጣጫ ሰጥቷል። ዛሬ መተግበር የጀመረው እገዳ እስከ ምርጫው ማግስት ግንቦት 25/2018 ዓ.ም ድረስ የሚቀጥል ሲሆን፣ ለተከታታይ ሦስት ቀናት "የይለፍ ፊቃድ ካልተሰጠው በስተቀር ማንኛውም የመንግሥት፣ የንግድ እና የግል ተሽከርካሪዎች፣ ባጃጅ እና ሞተር ሳይክል በሙሉ እንቅስቃሴ እንዲያቆሙ" መመሪያ መሰጠቱን ኮሚሽኑ ገልጿል።

የተሽከርካሪ እንቅስቃሴ ገደብ መመሪያውን ተግባራዊ በማያደርጉ አሽከርካሪዎች ላይ "ጥብቅ የሆነ ሕጋዊ እርምጃ" እንደሚጠብቃቸው መየክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ዶሮ ካሩ አሳስበዋል።

በልዩ የይለፍ ፈቃድ "በተወሰነ ደረጃ እንቅስቃሴ የሚፈቀድላቸው ለድንገተኛ ሥራ ወይም አገልግሎት (Emergency) ብቻ የሚንቀሳቀሱ የመብራት ኃይል፣ የቴሌኮሙኒኬሽን እና አምቡላንሶች" ናቸው ተብሏል። በውስን ሁኔታ ልዩ ፈቃድ የተሰጣቸውም ተሽካሪዎችም፣ የይለፍ ወረቀት መያዝና ሲጠየቅ የማሳየት ኃላፊነትና ግዴታ አለባቸው ተብሏል።

#Ethiopia #Ethiopian #ኢትዮጵያ #ሀገራዊምርጫ #ጋምቤላ #ምርጫ2018
#AndaftaMedia #አንድአፍታ
2
ሰበር!

በጎንደር የቦምብ ጥቃት!

​በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ካምፓስ ትላንት ምሽት የአርሴናል እና ፒኤስጂ የቻምፒየንስ ሊግ ጨዋታ በፕሮጀክተር ሲተላለፍ በነበረበት ወቅት በተከሰተ የቦምብ ፍንዳታ የተማሪዎች ህይወት ማለፉና በርካቶች መጎዳታቸው ታውቋል።

​ፍንዳታው የተከሰተው የመጀመሪያው አርባ አምስት ደቂቃ ሊጠናቀቅ ሲል ሲሆን፣ በአዳራሹ ውስጥ በነበረው ከፍተኛ መጨናነቅ ምክንያት በተፈጠረ መረጋገጥም ተጨማሪ ጉዳት ደርሷል።

​የተማሪዎች ህብረት አመራሮች እና የከተማው ነዋሪዎች እንደገለጹት፣ በጥቃቱ የሁለት ወይም የሶስት ተማሪዎች ህይወት አልፏል።

የሟቾች አስክሬን ዛሬ ጠዋት ወደ ቤተሰቦቻቸው የተሸኘ ሲሆን፣ ከ30 በላይ የሚሆኑ የቆሰሉ ተማሪዎች በካምፓሱ ሆስፒታል የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው ይገኛል።

​አሁን ላይ ፖሊስ በካምፓሱ ገብቶ የፍንዳታውን መንስኤ እያጣራ ሲሆን፣ በካምፓሱ ውስጥ የሀዘን ድባብ ሰፍኖ ይገኛል።
💔31
የጌዴኦ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በተከሳሽ አቶ ጸጋዬ ታደሰ ላይ ጥብቅ የሆነውን የሞት ቅጣት ውሳኔ በዛሬው ዕለት ማጽደቁ ታወቀ
የፍርድ ሂደቱ ዝርዝር ሁኔታ፦
ፍርድ ቤቱ ግንቦት 17/2018 ዓ.ም በዋለው ችሎት በተከሳሹ ላይ መነሻ ቅጣት በሞት እንዲቀጣ ወስኖ የነበረ ሲሆን የተከሳሽን የቅጣት ማቅለያ እና የአቃቤ ህግን የቅጣት ማክበጃ ለመስማት ለዛሬ ግንቦት 26/2018 ዓ.ም ቀጠሮ መያዙ ይታወሳል።
በዛሬው ዕለት የወንጀል ችሎቱ ተከሳሽ ካቀረባቸው የቅጣት ማቅለያዎች መካከል ሁለቱን የተቀበለ ሲሆን በተመሳሳይ መልኩ ከሳሽ የጌዴኦ ዞን አቃቤ ህግ ካቀረባቸው ልዩ የቅጣት ማክበጃዎች ውስጥ ሁለቱን ፍርድ ቤቱ ተቀብሎታል።
ፍርድ ቤቱ ከተከሳሽ የቀረበውን የቅጣት ማቅለያ እና ከአቃቤ ህግ የቀረበውን ልዩ የቅጣት ማክበጃ ሚዛን እኩል (ተመሳሳይ) ሆኖ አግኝቶታል።
በዚህም ምክንያት ፍርድ ቤቱ ቀደም ሲል የያዘውን መነሻ ቅጣት በማፅናት በአቶ ጸጋዬ ታደሰ ላይ የሞት ውሳኔውን በይፋ አፅድቋል።
የጌዴኦ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የተወሰነውን የሞት ቅጣት ውሳኔ ተከታትሎ እንዲያስፈጽም ለዲላ ከተማ ማረሚያ ተቋም ትዕዛዝ መስጠቱን ከስፍራው የጌዴኦ ዞን ፖሊስ መምሪያ ህዝብ ግንኙነት የላከው መረጃ ያመለክታል።
ሰበር
ህወሃት ለዓለም አቀፍ ማህበረሰብ አስቸኳይ ደብዳቤ ጻፈ

የሕዝባዊ ወያነ ሐርነት ትግራይ (ህወሃት) ከፍተኛ አመራር የፕሪቶሪያውን የሰላም ስምምነት የፌደራል መንግስቱ በይፋ ማፍረሱንና ክልሉን በከበባ ውስጥ ማድረጉን በመጥቀስ፣ አዲስ ሊቀሰቀስ የሚችለውን አስከፊ ጦርነት ለመግታት ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በአስቸኳይ ጣልቃ እንዲገባ ጥሪ አቀረበ።

በትግራይ ክልል ያለውን የፖለቲካ የሥልጣን ክፍተት ለመሙላትና ተቋማዊ ቀጣይነትን ለማረጋገጥ ከ1 ሚሊዮን በላይ የክልሉ ነዋሪዎች የተሳተፉበት ሰፊ ውይይት መደረጉን የገለጸው የህወሃት መግለጫ፣ በዚህም መሠረት በ2012 ዓ.ም የተመረጠው የትግራይ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ወደ ሉዓላዊ ሥልጣኑ እንዲመለስ መወሰኑን ይፋ አድርጓል። ምክር ቤቱ ወደ ሥራው ሲመለስ አካታች የሆነ የሕግ አስፈጻሚና የዳኝነት መዋቅር እንደሚያዋቅር የተገለጸ ሲሆን፣ ተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶች በካቢኔው ውስጥ የ33 በመቶ (አንድ ሶስተኛ) የሥልጣን ድርሻ እንዲኖራቸው ጥሪ መቅረቡም ገልጿል።

በትግራይ ክልል ያለው ሰብአዊና ኢኮኖሚያዊ ቀውስ አሁንም እጅግ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መሆኑን የጠቀሰው ይኸው አለም አቀፍ ጥሪ፣ የፌደራል መንግስቱ በነዳጅ እና በንግድ ዕቃዎች ላይ የጣለው እገዳ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴውን ሙሉ በሙሉ ማሽመድመዱንና ከፍተኛ የዋጋ ንረትን ማስከተሉን ያብራራል። ከዚህ በተጨማሪም የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት በትግራይ ድንበሮች ዙሪያ መጠነ-ሰፊ ወታደራዊ ዝግጅትና ከበባ እያደረገ እንደሚገኝ በመግለጽ፣ ይህ ድርጊት በሕዝቡ ላይ ከፍተኛ የስነ-ልቦና እና የማኅበራዊ ጫና እየፈጠረ መሆኑን ይከሳል።

https://www.facebook.com/61582312059471/posts/122169311115077068/?app=fbl
👍1
መድኃኒያለም በእለተ ቀኑ ታድጎናል!
ይህ ዛሬ 27/09/2018 በአሁን ሰአት መገናኛ የደረሰ የመኪና አደጋ በሰው ላይ የከፋ ጉዳት አልደረሰም።

📷 ትግስት ታንቱ
7👍1
ክፉ ጊዜ ነው!
የሀገርን ሰንደቅ ከፍ ለማድረግ ተማምለው አመታት ስልጠና ሲያደርጉ የነበሩ ወጣት አትሌቶች በቅናት ተገዳደሉ😢

https://www.facebook.com/61582312059471/posts/122169379953077068/?app=fbl
4
ዜና እረፍት!
የቀድሞ የአዲስአበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ የነበሩት አቶ አሊ አብዶ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ።
rip
👎2
"ለኔ ከአርሰናል አርሲ ትቀድማለች!" አርቲስት ሄኖክ ድንቁ

"እሁድ አራት ኪሎ ዘመን ሲኒማ የክለባችን የአርሰናልን ዋንጫ መብላት ምክንያት በማድረግ የእንኳን ደስ ያለን እና የማሊያ ጊቭ አዌይ ፕሮግራም በወቅታዊ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ሀዘን ምክንያት መሰረዜን አስታዉቃለዉ"
Via FastMereja.com
1
ያለ ኢንተርኔት የሚሰራ AI መምህር በኢትዮጵያ ቀረበ

​ትምህርት ሚኒስቴር የሁለተኛ ደረጃ መምህራንን የሥራ ጫና የሚቀንስ፣ ሙሉ በሙሉ ያለ ኢንተርኔት (Offline) በማንኛውም ኮምፒውተር ላይ የሚሠራ “ኤጀንቲክ መምህር ረዳት” (Agentic AI) መተግበሪያ አበልጽጎ በሙከራ ደረጃ ሥራ ላይ አዋለ።

​የሚኒስቴሩ የሥራ ኃላፊዎች( የአይሲቲና ዲጂታል ትምህርት መሪ ስራ አስፈጻሚ ዘላለም አሰፋ (ዶ/ር) ‎የክፍሉ አማካሪ ሙሉነህ አጥናፉ (ዶ/ር)) እንደገለጹት፤ መተግበሪያው በአዲሱ ሥርዓተ ትምህርት (ከ9ኛ-12ኛ ክፍል) መጻሕፍት ላይ ተመስርቶ የበለጸገ ሲሆን፣ የትምህርት ዕቅድ ማዘጋጀት፣ የፈተና ጥያቄዎችን ማመንጨትና የማስተማሪያ ስልቶችን ማቀናጀት ይችላል።

​ቴክኖሎጂው የኢንተርኔት ተደራሽነት በሌላቸው የገጠር አካባቢዎች ጭምር ያለምንም መቆራረጥና ተጨማሪ የወርሃዊ ክፍያ ወጪ የሚያገለግል በመሆኑ፣ በከተማና በገጠር መካከል ያለውን የትምህርት ጥራት ልዩነት ለማጥበብ ከፍተኛ እገዛ ያደርጋል።

በዓለም ባንክ የቴክኒክ ድጋፍ የሚደረግለት ይህ መተግበሪያ በተመረጡ ትምህርት ቤቶች ተሞክሮ አጥጋቢ ውጤት ማሳየቱም ተገልጿል።
1
ነገ በ 29 መብራት የሚጠፋባቸው ቦታዎች!

በነገው እለት የጥገና ሥራ ለማከናወን የሚቋረጥ የኃይል አቅርቦት

ነገ ግንቦት 29 ቀን 2018 ዓ.ም የጥገና ሥራ ለማከናወን ኃይል የሚቋረጥባቸው አካባቢዎች፦

4:30 – 9:00

👉መስቀል ፋላዎር፣ ወንግላዊት፣ ወሎ ሰፈር ጀርባ፣ ጎርጎርዮስ፣ ጎተራ እና አካባቢው፣

ከጠዋቱ 2፡00 – 9፡30

👉ሰበታ ከተማ ፣ አለርት ሆስፒታል፣ ቻይና ቱቦ አካባቢ፣ ኢንዱስቲሪ መንደር እና አካባቢያቸው፣

ከጠዋቱ 12፡00 – 7፡00

👉መቀለ ከተማ 03፣ አይደር ሪፌራል ሆስፒታል፣ አድሽምን፣ አዲሃ አክረም እና ደኤሮ አካባቢ፣

ከጠዋቱ 2፡00 – 12፡00

👉መቀለ ከተማ 05፣ ኮንዶሚኒየም ሰፈር፣ ግብርና ብሮና ማይዱባ እና አካባቢያቸው፣

ከጠዋቱ 2፡00 – 10፡00

👉አዳማ ፖስታ ቤት፣ አዳማ ሆስፒታል፣ ፍራንኮ፣ ፒኮክ፣ 105 አካባቢ፣ አኪሊስያ ሆስፕታል እና አካባቢያቸው፣

ከጠዋቱ 2፡00 – 6፡30

👉በወልድያ መቻሬ፣ አዳጎ፣ አሸዋ ሜዳ፣ አመያመጫ፣ ሁርጌሳ፣ ኡድመን፣ ልብሶ፣ ጊረና፣ መሀለምብ እና አካባቢያቸው፣

ከጠዋቱ 12፡00 - 11፡00

👉የአዳሚ ቱሉ ገንዳ አርባ 132 ኪ.ቮ አግሮ ኢንዱትሪ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር ለመዘርጋት በታወር ቁጥር 11 እና በታወር ቁጥር 12 መካከል በሚገኙ ኩርማ 33 ኪ.ቮ ኢንዱስትሪ ፓርክ 33 ኪ.ቮ እና ቡልቡላ 15 ኪ.ቮ የኤሌክትሪክ መስመሮች ይቋረጣሉ፡፡

ስለሆነም በተጠቀሱት አካባቢዎች የምትገኙ የተከበራችሁ ደንበኞቻችን የጥገና ሥራው ተጠናቆ የኃይል አቅርቦቱ እስኪመለስ ድረስ በትዕግስት እንድትጠብቁን እንጠይቃለን፡፡

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት
2
ጠቅላይ ሚ/ር አቢይ አህመድ (ዶ/ር) በአርሲ ንፁሐን ወገኖቻችን በደረሰዉ ጥ*ቃት የተሰማቸዉን ሀዘን ገልፀዋል።
👎10😁1