This is how #AbiyAhmed’s soldiers raze villages to the ground under the pretext of fighting #OLA. This is how they execute their project of “draining the ocean in order to exterminate the fish.” An episode of burning down residential villages in Gujii Zone., Oromia.
https://www.facebook.com/share/v/dSSLkh6DEWJnaTrh/?mibextid=WC7FNe

Facebook
Log in or sign up to view
See posts, photos and more on Facebook.
Forwarded from KMN
Discussion with #KMN on:
1) Abiy’s destruction of villages in Gujii Zone;
2) Hostage-taking as #AbiyAhmed’s new political currency; and
3)Transition constitutionally or extra-constitutionally? Through (constitutional) care taker government, or victors’ provisional government leading to a Transitional Government, or a Transition through the National Dialogue Commission??? Clarifying the concepts…
https://www.youtube.com/live/xkDR9MDJ8yI?si=z7Z4V1nP-e_YZcDj

YouTube
ከሽግግር ወደ መፈንቅለ መንግሥት?
#KMN #KUSH
"አብይን ያካተተ የሽግግር ሂደት?"--ከምን ወደ ምን?
================================
ከአምባገነናዊ ሥርዓት: በተለይም ከፋሽስታዊ ዘር-አጥፊ ጦርነት በኃላ ለሚደረግ ሽግግር የሚወሰዱ እርምጃዎች ውስብስብና ፈርጀ-ብዙ መሆናቸውን ማንም ይረዳል::
በዚህ ዓይነት አውድ ውስጥ ተሁኖ: ለዘላቂ ሰላምና ለሁለንተናዊ የፖለቲካ መግባባት (comprehensive political settlement) የሚደረግ ድርድርና ውይይት: የራሱ ሂደት አለው::
ሂደቱም ቢያንስ ሶስት እርከኖች (steps) ይኖሩታል:: እነዚህን እርከኖች ለይቶ አለማወቅ: ወይም እርከኖቹን በመዝለል ቅደም ተከተላቸውን ማምታታት: ወይም ሶስቱንም በአንድ መጨፍለቅና እንደ አንድ ሁነት መቁጠር: የሚፈለገውን ሽግግር ለማምጣት እክል ይፈጥራልና: እያንዳንዳቸውን በዝርዝርና በጥልቀት ማየት ይገባል::
1) የመጀመሪያው እርከን: በታጣቂዎች መካከል የተኩስ አቁም ስምምነት (Ceasefire Agreement) ላይ እንዲደርሱ የሚደረግበት ነው:: የተኩስ አቁም ስምምነት ለማድረግ የሚደረግ ውይይት: አፈሙዝ ለማዘጋት በሁለቱም ወገኖች የሚወሰዱ እርምጃዎችን ይመለከታል:: ተመልሶ ወደ መጠቃቃት እንደማይመለሱ መተማመኛ እርምጃዎችን ለይተው: ቅድመ-ሁኔታዎች (ካሏቸው) አስቀምጠው: እስካሁን ያገኙትን "ድል" ሳያስነኩ የቀሩ ድሎችን በሰላማዊ መንገድ እውን ለማድረግ የሚያስችል የጋራ ማዕቀፍ ያስቀምጣሉ:: ለዚህም ነው: አደራዳሪ (facilitator/mediator): ታዛቢ (observer): እና ዋስ (guarantor)የሚያስፈልገው::
በዚህ ሂደት የሚካተቱት ጭብጦች ከሞላ ጎደል የሚከተሉትን ያካትታሉ:-
ሀ)ተኩስ አቁሙ መች ይጀምራል እስከመቼ ይቆያል?
ለ)ማን ተቁስ አቁሙ በስምምነት መሠረት መፈፀም አለመፈፀሙን ይቆጣጠራል? አንዳቸው ስምምነቱን ቢተላለፉ: የጣሰው ወገን እንዴት ይታደባል?
ሐ)በሁለቱ ኃይሎች መካከል ስለሚኖረው ነፃ ቀጣና (buffer zone):
መ)ስለ ትጥቅ አፈታት ሂደት: ስለታጣቂዎች ቅነሳና ተሃድሶ: እንዲሁም ወደ ሰላማዊ ኑሮ መሸጋገር:
ሠ)ስለ ተያዙ:ስለ ታገቱና ስለ ታሰሩ ሰዎች መለቀቅ:
ረ)ለተጋላጭ ሰላማዊ ዜጎች ሊደርስስለሚገባ ሰብዓዊ እርዳታ:
ሰ)ወደ ቀደመው ሁኔታ (status quo ante) ለመመለስ ስለሚወሰዱ እርምጃዎች:
ሸ)ስለ ተፈናቃዮች መመለስና መካስ: ስለ ምርኮኞች መለዋወጥ:
ቀ)ስለከተኩስ አቁሙ ሁኔታ መሳለጥ በኃላ ስለሚፈጠረው የጋራ የትብብር ተቋም (ማለትም የጊዜያዊ መንግሥት):
በ)በውጊያው ሂደት ለተፈፀሙ ወንጀሎች ተጠያቂነት ስለሚሰጥ ዋስትናና ስለሚወሰዱ አስተማማኝና ተጨባጭ እርምጃዎች: (በፊት ተጥለው የነበሩ ውንጀላዎች ስለሚነሱበት ሁኔታ) ወዘተ እና
ሌሎች ተዛማጅ ጭብጦችን ይመለከታል::
ይሄ ስምምነት የሽግግር ሥምምነት ሳይሆን:በዋናነት: መገዳደልን ማቆምን የሚመለከት ነው:: በሁለቱ ወገኖች የሚፈፀሙ የኃይል ተግባራትን የማክሰም ሂደት ነው::
ይህ ሂደት በስኬት የሚገባደድ ከሆነም: ከዚህ የግጭት/ጦርነትና ፖለቲካዊ ክፋት (political evil) ሁኔታ በማያዳግም ለመውጣት መስማማትካለ: ይሄን ለማድረግ የሚያስችል የሽግግር ሂደት ማዕቀፍ (Framework for Transitional Process) ማስቀመጥ ይቻላል:: ይሄንን የሚያመቻች ጊዜያዊ የጋራ መድረክ (በኢትዮጵያ ሁታ ደግሞ: ታጣቂዎቹን ያካተተ አገራዊ ጊዜያዊ መንግሥት) እንዲኖር እስከመስማማት ሊደርስ ይችላል::
2) ሁለተኛው እርከን: የጋራ መድረኩን (ጊዜያዊ መንግሥቱን) ለማቋቋምና በሚቋቋመው ጊዜያዊ መድረክ/ መንግሥት ውስጥ ተዋጊ ወገኖች ያላቸውን የሥራ ድርሻ: መብት: ሥልጣንና ኃላፊነት: የመድረኩ/መንግሥቱ (ውሱን) ኃላፊነት(mandate): የሥራ ጊዜ ላይ ውይይት ተደርጎ ስምምነት የሚደረስበት ነው::
ይህ ሂደት ውጤታማ ከሆነ: በስምምነቱ መሠረት ጊዜያዊ መድረኩ/መንግሥቱ ወደ ሥራ የሚገባበት እርከንነው::ይህ ሁለተኛ እርከን የሽግግር ሂደት: ሙሉ የፖለቲካ መግባባት ለመፍጠር ጥረት የሚደረግበት ሳይሆን: ተኩስ አቁሙን መተግበርና ከአለፈው የጦርነትና የፖለቲካ ክፋት ለመላቀቅ የሚያስችሉ እንቅስቃሴዎች የሚደረጉበት (ማለትም: ሁለንተናዊ ሰላምና መረጋጋት መፍጠር: እስረኞችን መፍታት: የታገዱና የተሰደዱ የፖለቲካ ኃይሎችን መመለስ:ድንበርን መዝጋት: የወንጀል ተጠርጣሪዎችን በሕግቁጥትር ሥር ማዋል: ለዕለትተለት ኑሮ የሚያስፈልጉ የአስተዳደርና የግልጋሎቶች ፍሰትን ማሳለጥ: ቁልፍ ለሆኑ አገራዊና ማህበራዊ የመሠረተ-ልማት አውታሮች አስፈላጊውን የጥበቃ ሽፋን መስጠት: እና የመሳሰሉት የሚፈፀሙበት) እርከንነው::
በተጨማሪም: ወደ እውነተኛ ሽግግር ለመሄድ የሚያስችሉ የዝግጅት እርምጃዎች የሚወሰድበት ወቅት ነው:: ለዚህ የሚያስፈልገው ሁሉን አካታች የሆነ የሽግግር ጉባኤ ለማካሄድ እንዲቻል ለሁሉም የፖለቲካ ኃይሎች ጥሪ የሚደረግበት: ሁሉም ኃይሎች ለመሳተፍ እንዳይችሉ የተቀመጡ ህጋዊና ህጋዊ ያልሆኑ ገደቦች ሁሉ የሚነሱበት: መሠረታዊ የሲቪክና የፖለቲካ መብቶች (በተለይ: የማሰብ: እራስን የመግለፅ: የመናገር: የመፃፍ: የመሰብሰብ: እና የመደራጀት: መብቶች) ያለ ገደብ የሚከበሩበት: የውይይት አጀንዳ የሚለይበት (ቅድመ-ፖለቲካዊና ፖለቲካዊ የሆኑት ተነቅሰው የሚወጡበት): ለመፍትሄ እርምጃዎች ምክንያታዊ የጊዜ ተመን (ሰሌዳ የሚቀመጥበት): ወዘተ ወቅት ነው::
ይህ ሂደት: አገራዊ የሽግግር ጉባኤ ተካሂዶ: የሽግግር መንግሥት ሲቋቋምና ጊዜያዊዉ የጋራ መድረክ (ወይም ጊዜያዊው መንግሥት) ኃላፊነቱን ለሽግግር መንግሥቱ ሲያስረክብና እራሱን ሲያከስም ይጠናቀቃል:: በዚህም: ወደ ሶስተኛውና የመጨረሻው የሽግግር እርከን ለመሄድ እድል ይፈጠራል::
በዚህ በሁለተኛው እርከን በተባባሪነት ሲሳተፍ የቆየው ነባሩና የፖለቲካ ክፋትን ሲተገብር የነበረው የአገሪቱ ቡድን(ፈቃደኛ ሆኖ ከተሳተፈ) ጉዞውን እዚህ ጋ ገትቶ ከፖለቲካው ሂደት እራሱን ያገልላል: ወይም እንዲያገልል ይገደዳል:: (ይሄን በሌላ ፅሁፍ እመለስበታለሁ::)
3) ሶስተኛው እርከን: የሽግግር መንግሥት ተቋቁሞ: አገሪቱን ወደ ሰላማዊና የተደላደለ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ለመምራት የሚንቀሳቀስበት ነው:: የሽግግር መንግሥቱ: ባለፈው የጦርነት: የዘር ማጥፋትና የፖለቲካ ክፋት ዘመንና ወደፊት ሊመጣ ባለው የእፎይታ: የፍትሕና የዴሞክራሲ ዘመን መካከል የሚሆን አገናኝ ድልድይ ነው:: የዴሞክራሲ አዋላጅ ነው::
በዋናነት የዚህ (የሽግግር) መንግሥት ኃላፊነት (mandate): በዋናነት የሚከተሉትን የሚመለከት ይሆናል:-
ሀ) ሰላምን መጠበቅ:
ለ) አንገብጋቢ ለሆኑ ችግሮች ወቅታዊ ምላሽ መስጠት:
ሐ) ዴሞክራሲያዊ አካታችነትንና ተሳትፎን ለማሳለጥ የሚያግዙ ህጎችንና ደንቦችን ማውጣት: ፖሊሲዎችን መቅረፅ: ለዚህ የሚሆኑ እርምጃዎችንም መውሰድ:
መ)ወንጀለኞችን ተጠያቂ ለማድረግና ተጠቂዎችን ለመካስ የሚያስችል የሽግግር ፍትህ ህግ/ፖሊሲ ማእቀፍ ማውጣትና ዓለማቀፋዊ መስፈርትን የሚያሟሉ የሽግግር ፍትህ ተቋማትን ማቋቋም:
ሠ) ሰብዓዊ እርዳታ ለተጎጂዎች ማቅረብ: ተፈናቃዮችን መመለስ:
ረ) ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ የሚጠቅሙ የፀጥታ (የደህንነት: የመከላከያ: የፖሊስ): የሚድያ: ሲቪል ማህበረሰብ: የምርጫ ቦርድ: የፍትህ: ወዘተ ማሻሻያ ፖሊሲዎችን መንደፍና መተግበር:

ሰ) ለከራረሙ: ለአደሩና ለተወሳሰቡ ቅድመ-ፖለቲካዊ የፍትሕ ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት የሚያስችሉ: በሕዝቦች ዘንድ መተማመንን የሚያጠነክሩ የመፍትሔ አቅጣጫዎችን (ለምሳሌ ሕዝበ-ውሳኔ) ከነ ጊዜ ሰሌዳው ማስቀመጥና ተቋማዊ ዝግጅት ማድረግ::
---
እነዚህን እርከኖች በመቀላቀል: ቅደም-ተከተላችውን በማምታታት: ወይም በአንድ ጨፍልቆ "የሽግግር መንግሥት/ የባላደራ መንግሥት" እያሉ ችግሩንና መፍትሔውን ማቀላቀል--ከዚህም ፍሬያማ ውጤት መጠበቅ--አይቻልም::
--
አሁን ባለው ሁኔታ: ብልፅግናን "የሽግግሩ አካል እናድርግ" ማለት: የአብይን የስልጣን ዘመን በማራዘም: የችግሩን እድሜ ማስቀጠል ነው እንጂ ሽግግርን ማማጣት አይደለም::
ብልጥግና ሙሉ በሙሉ በኃይል እንዳይወገድ ከፈለገና ግጭቶችን በሰላማዊ መንገድ መጨረስ ከፈለገ: የተኩስ አቁም ድርድሮችን በመጀመር: አፈሙዝ ለማዘጋት በሚደረግ ሂደት (የሽግግር የመጀመሪያ እርከን ሂደት ላይ) ሊሳተፍ ይችላል::
የተኩስ አቁም አድርጎ: የእሱ አካሄድ ስህተት መሆኑን ተቀብሎ: ወደዴሞክራሲ የሚደረግ ጉዞ ይሻላል የሚለውን ከተቀበለና እራሱንም ለማክሰም--ለአንዳንድ ባለስልጣናቱም ምህረትና ይቅርታን ተደራድሮ--ከተስማማ ደግሞ: የጊዜያዊ መንግሥት ረዳት አካል (junior partner) ሆኖ: የሽግግር መንግስት እስኪቋቋም ባለው ጊዜያዊ የጋራ መድረክ ወይም በጊዜያዊ መንግሥት መሳተፍ ይችላል:: በዚህ ሂደቱ ሁለተኛ እርከን ላይ ተሳታፊ ይሆናል ማለት ነው::
ከዚህ በኃላ ግን ወንጀለኞቹን ለፍትህ አካላት አስረክቦ: እራሱን አክስሞ መቀመጥ እንጂ የሽግግር መንግስቱ አካል ሊሆን አይችልም:: ብልጥግና አብሮን ከተሻገረማ አገሪቷስ ከእርሱ መች ልትሻገር ነው?
አብይን የመፍትሔው አካል አድርጉ የሚለው የልጆች ጨዋታ: የአብይን ፋሽስት መንግሥት በመጠኑ liberalise አድርገን: ሌሎች ኃይሎችንም ጨምረን: ወደ ፊት እንቀጥል እንደማለት ነው::
ፋሽስት liberalise አይደረግም:: በታሪክ እንደታየው: Liberalismን ቀርጥፎ ውጦ ብቻውን ይቀጥላል እንጂ::
ይሄን ብልጥግናን liberalise የማድረግ ጥሪ የአሜሪካ እንደሚሆንይገመታል:: አብይየእነሱ መንግሥት ስለሆነ (ምናልባትም በእነሱ ዓይን ሊብራል ዴሞክራት ስለሆነ) ሰላምን በመዋዋልና ሌሎችን በማካተት የበረታና የጠነከረ እንዲሆን የመፈለግ ዝንባሌ ሊኖራቸው ይችላል::
የኢትዮ-አማራ ልሂቃን የፖለቲካ ኃይሎች "አብይ የሌለበት ሽግግር አይኑር" ማለታቸው የሚያሳየው: በመሠረቱ የአብይ መንግሥት: እነሱ ለኢትዮጵያ ተመራጭ ነው የሚሉት መንግሥት መሆኑን (እና በጉዞው መኃል ላይ ትንሽ ከመስመር የወጣባቸው በመሆኑ: ትንሽ መስተካከል እንዳለበት እንደሚያምኑ) ነው:: አብይ በመሠረቱ የእነዚህ የኢትዮአማራ ልሂቃን መንግስት መሆኑን ግልፅ ያደረገ ሂደት ነው:: (ቀደም ብለው ያለ ገደብ ለአብይ ሲያሸበሸቡ የነበረ መሆኑን ልብ ይሏል:: ሰፊ የዘር ማጥፋት ሲይካሄድ ጭምር ድጋፋቸውን እንዳልነሱት ማስታወስ ያስፈልጋል::
ምክንያታቸው ከላይ ያልነው ካልሆነ ግን: ሌላ ሃሳብ--ከአብይ የተሻለ መፍትሔም--እንደሌላቸው በግልፅ ያሳያል:: የተሻለች ኢትዮጵያን ማየት ሲፈልጉ: ለማየት የሚችሉት: አብይ ያየውን ያህል ብቻ መሆኑን ያሳያል:: And that is tragic. All too familiar to us, but tragic nonetheless.
(ይቀጥላል)

የብሔረ ፖለቲካ አና የዐንቀፅ 39 ትርክት
#KMN #KUSH
ስለ ሕገ-መንግሥት: ፌደራሊዝም: ሕብረ-ብሔራዊነት: እና አገራዊ ማንነት::
ስለ "ብሔር ፖለቲካ": ስለ አንቀጽ39: እና ስለ መመሥረቻ መርሆዎች (Foundational Principles)
With #KMN
https://www.youtube.com/live/-2J4WaPTq0k?si=GJTWoCoDWTJBygnF
ስለ "ብሔር ፖለቲካ": ስለ አንቀጽ39: እና ስለ መመሥረቻ መርሆዎች (Foundational Principles)
With #KMN
https://www.youtube.com/live/-2J4WaPTq0k?si=GJTWoCoDWTJBygnF
Forwarded from KMN
Irra deddeebidhaan Facebook Dr Tsegaye cufamaa ykn Ugguramaa tureera. Ammas page dabalatee hundumtuu waan jalaa cufsiifameef isa haaraa kanaan maatii ta’uudhan hordofaa.
የዶ/ር ፀጋዬ ፌስቡክ በተደጋጋሚ እየተዘጋ እና እየታገደ እንደነበር ይታወቃል አሁንም ስላዘጉበት በዚህ አዲሱ አካዉንታቸዉ ቤተሰብ ሁኑ::
https://www.facebook.com/profile.php?id=61563092909085&mibextid=LQQJ4d
የዶ/ር ፀጋዬ ፌስቡክ በተደጋጋሚ እየተዘጋ እና እየታገደ እንደነበር ይታወቃል አሁንም ስላዘጉበት በዚህ አዲሱ አካዉንታቸዉ ቤተሰብ ሁኑ::
https://www.facebook.com/profile.php?id=61563092909085&mibextid=LQQJ4d
የብሔረ ፖለቲካ አና የዐንቀፅ 39 ትርክት
https://youtube.com/live/-2J4WaPTq0k?feature=share
https://youtube.com/live/-2J4WaPTq0k?feature=share
YouTube
የብሔረ ፖለቲካ አና የዐንቀፅ 39 ትርክት
#KMN #KUSH
#Gofa Disaster claims lives. Help is needed urgently. Condolences to the families affected by the tragedy.💔💔💔