Tsegaye R Ararssa
15.6K subscribers
1.73K photos
256 videos
164 files
2.62K links
TA
Download Telegram
ሕዝብን በመሳደብና በማዋረድ ችግር አይፈታም!
===========
ሰሞኑን #አብይ_አህመድ፣ የጉራጌ ሕዝብ የክልልነት ጥያቄን ለመመለስ እንዳንችል ያደረገን፣ "ጉራጌ ተበታትኖ የሚኖር መሆኑ ነው። አዲስ አበባ ውስጥ ነው ክልል የምንሰጠው? ወይስ ኦሮሚያ ውስጥ ነው? ወይስ የት ነው?" ማለቱን በመገናኛ ብዙሃን ለይ ተከታተልን።

ይሄን ባለበት በዚሁ መድረክ ላይ ስለ ወለኔ ሕዝብም፣ ከፓርቲው ተወካዮች ጥያቄ ቀርቦለት፣ እንዲህ ሲል አደመጥን፦
"እርስዎ ጠቅላይ ሚኒሥትር ጽ/ቤት ተገኝተው፣ 'እኔ ወለኔ ነኝ' ብለው መናገር መቻሎ እራሱ ትልቅ ድል መሆኑን መቀበል ይኖርብዎታል።" (ጥቅሱ ቃል በቃል አይደለም።)

አብይ፣ ክልልነት፣ መብት መሆኑን የማይረዳና ሊረዳና ሊቀበልም የማይፈልግ መሆኑ ግልፅ ነው። ክልልነት፣ እሱ በበጎ ፈቃዱ፣ እንደ ችሮታ፣ ለፈለገው የሚሰጠው፣ ላልፈለገው የሚነሳው ስጦታ እንደሆነ የሚያስብ መሆኑንም፣ ከዚህ በፊት ከሚናገራቸው ነገሮች ተነስተን መገመት አይከብድም። (በአብይ ዓለም፣ ችሮታና ጉቦ እንጂ መብትና ግዴታ አይታወቁምና።)

እንደ አንድ ብሔር የማንነት እውቅና ተሰጥቶት፣ በግልፅ በሕግና በተጨባጭ በሚታወቅ አካባቢ፣ የዞን አስተዳደር መሥርቶ (ከሞላ ጎደል) እራሱን ሲያስተዳድር የነበረን ሕዝብ፣ በዚህ ደረጃ፣ "ተበታትኖ የሚኖር ከመሆኑ የተነሳ" አድራሻው የማይታወቅ ነው ብሎ ማሳነስና ማበሻቀጥ ግን ሕዝቡን መስደብና ማዋረድ ነው።

ይሄ ችግርን አይፈታም። ይልቁንም፣ ችግሩን አወሳስቦ ለትውልዶች የሚተላለፍ ውጥረት ያነግሳል እንጂ።

ይሄ ንቀት ብቻ ሳይሆን የጥላቻ ንግግር ነው። ይሄ፣ ውሎ አድሮ ሕዝብን ለከፋ ጥቃት የሚያጋልጥ ጠንቀኛ ንግግር ነው።

ንግግሩ መታረም አለበት፤ መንግሥት ሕዝቡን ይቅርታ መጠየቅ አለበት።

በተመሳሳይ መልኩ፣ ለወለኔው ተወካይ፣ "እኔን በወለኔነት ማናገርዎ ትልቅ ድልና ዓይነተኛ ስኬት ነው" ብሎ የሕዝቡን የማንነትና የአካባቢ የራስ አስተዳደር ጥያቄ በዚህ ልክ ማሳነስ፣ ታላቅ ስድብ ነው። ንቀት ነው። ማንአለብኝነት ነው። መመፃደቅ ነው። በእኔ-አውቅልሃለሁ ስሜት ሌላውን አኮስሶ መመልከት (patronizing) ነው።

እንዲህ ያለ ንግግርና ተግባር ትውልዱን ምሬት ውስጥ በመጨመር፣ ወደ ማይፈለግ የኃይል እርምጃ እንዲገባ ያስገድዳል። ይሄም ፖለቲካውን (ኢትዮጵያ ውስጥ፣ ፖለቲካ ኖሮም አያውቅ እንጂ) ወደ ብረት እንዲገባ በማድረግ ማሕበረሰባዊ ጦረኝነትን (social militarizationን) ያስፋፋል።

ከዚህም አልፎ፣ አሁን በጥላቻ ቃል የተጀመረውን ንግግራዊ የኅይል ጥቃት (discursive violence) ወደ ለየለት ብሔር-ተኮር ጥቃት (እና ወደ ዘር ማጽዳትና ዘር ማጥፋት ዘመቻዎች) ያሸጋግረዋል።

ለነገሩ፣ ይብላኝለት ለሕዝቡ እንጂ፣ እንደ #አብይ_አህመድ ካለ የክፍለ-ዘመኑ አውራ የዘር ማጥፋት ወንጀል ፈጻሚ መራሔ-መንግሥት፣ ከዚህ ሌላ ምን ይጠበቃል?

#AbiyAhmed_is_a_genocidaire!
#No_to_hate_speech!
#No_to_discursive_violence.
#Apologies_are_due_to_Gurage_and_Wolene_People!