ለፖለቲካ ብለንነው?!?
================
ፖለቲካ ሸፍጥ አይደለም። መዋሸትም አይደለም። (የአብይም መሠረታዊው ችግር እኮ: የራሱ አእምሮ እንኳን የማያስተውለውና የማይቆጣጠረው ውሸትን እያወራ ውሎ ማምሸቱ፣ አምሽቶም ማንጋቱ፣ በውሸት እሽክርክሪት ውስጥ መኖሩ ነው።)
እውነትን በማድበስበስ፣ ከእውነት አቅጣጫ በመታጠፍ (dodge በማድረግ)፣ ውሸትን በማሻሸት (massage በማድረግ) እውነት ለማስመሰል ጥረት ማድረግ፣ ወዘተ ለድል አያበቃም፣ ዘላቂ መፍትሔም አያመጣም። በተለይ የሕዝቦች እውነት፣ ሃቅ፣ እና ፍትሕ ተቀብሮ በመቆየቱ ምክንያት፣ ብዙ መስዋዕትነት ያስከፈለ ትንቅንቅ በሚደረግበት አውድ ውስጥ፣ ከእውነት እየሸሹ መተጣጠፍ ድልን አያጎናጽፍም፣ ፍትህን አያወርስም፣ ፍትሃዊና ዘላቂ ሰላም አያመጣም። ለመቀራረብ ሲባል፣ አቋምን ማቀራረብ ሊሞከር ይቻላል--ተቃራኒ እውነቶችን በማቻቻል (ወይም compromise በማድረግ)። ማቻቻል/ ማመቻመች (Compromise) ግን መዋሸትና መቅጠፍ አይደለም። እኔ ያለኝ እውነትና ሃቅ እንዲወሰዱ የሚጠይቃቸውን እርምጃዎች ሁሉ አሁኑኑ፣ ወይም ሙሉ በሙሉ ይወሰዱ ላለማለት ሲባል: ከባድ የውሳኔ ምርጫ ማድረግ እንጂ።
በደምሳሳው፣ "ፖለቲካ ሸፍጥ/ውሸት ነው" በሚል እሳቤ ላይ ተንተርሶ፣ ፖለቲከኞች ከእውነት እየታጠፉ፣ የፈለጉትን እርምጃ እንደተመቻቸው እየወሰዱ እንዲቀጥሉ ማድረግ፣ ሕዝቡ ተጠያቂነትን የማስገደድ ኃላፊነቱን ጥሎ፣ በሸፍጠኛ ግለሰባዊ አምባ-ገነን ሥርዓት ሥር እንዲኖር መፍቀድ ነው።
ትግላችን ለፍትሕ ከሆነ: "ለፖለቲካ ሲባል" ብለን የምንሸፋፍነውና እያስመሰልን የምንታገልለት: ድብቅ የሆነ ወይም የምናፍርበት: አንዳች ሃቅ የለንም: አይኖረንም!!
#አርነት_በእውነት_እንጂ_በሸፍጥ_አይመጣም!