Siyaasa jechuun kijibuu miti. Dhugaa fi haqa uummataa dabssuu ykn yeroo fi haala laallachaa dhugaa fi haqa sabaa irraa dabuu miti. Keessattuu, biyya dhugaan, haqni fi mirgi keenya nn jalaa awwalame jettee lubbuuf jireenya kee itti kennitee itti falmattu keessatti tooftaan kikkijibuu nama hin baasu. Biyya nagaa, haqa-qabeessa, fi dimokraatowa ta'e keessatti warri hojii siyaasa hojii idilee godhatee (ykn career/professional politician ta'e) kijibuullee baatan yeroo tokko tokko dhugaa dhodhoqsanii bira darbuu danda'u. Biyya akka keenyaa kan dhiigni wareegamtootaa hin qorriin keessatti gaaffii dhugaa fi haaqaa dhodhoksaniituma, ykn irraa dabaniituma, bira kutuun hin danda'amu.
---
ፖለቲካ ሸፍጥ አይደለም። መዋሸትም አይደለም። (የአብይ መሠረታዊው ችግር የራሱ አእምሮ እራሱ የማያስተውለውና የማይቆጣጠረው ውሸትን እያወራ ውሎ ማምሸቱ፣ አምሽቶም ማንጋቱ፣ በውሸት እሽክርክሪት ውስጥ መኖሩ ነው።)
እውነትን በማድበስበስ፣ ከእውነት አቅጣጫ በመታጠፍ (dodge በማድረግ)፣ ውሸትን በማሻሸት (massage በማድረግ) እውነት ለማስመሰል ጥረት ማድረግ፣ ወዘተ ለድል አያበቃም፣ ዘላቂ መፍትሔም አያመጣም። በተለይ የሕዝቦች እውነት፣ ሃቅ፣ እና ፍትሕ ተቀብሮ በመቆየቱ ምክንያት፣ ብዙ መስዋዕትነት ያስከፈለ ትንቅንቅ በሚደረግበት አውድ ውስጥ፣ ከእውነት እየሸሹ መተጣጠፍ ድልን አያጎናጽፍም፣ ፍትህን አያወርስም፣ ፍትሃዊና ዘላቂ ሰላም አያመጣም። ለመቀራረብ ሲባል፣ አቋምን ማቀራረብ ሊሞከር ይቻላል--ተቃራኒ እውነቶችን በማቻቻል (ወይም comprise በማድረግ)። ማቻቻል/ ማመቻመች ግን መዋሸትና መቅጠፍ አይደለም። እኔ ያለኝ እውነትና ሃቅ እንዲወሰዱ የሚጠይቃቸውን እርምጃዎች ሁሉ አሁኑኑ፣ ወይም ሙሉ በሙሉ ይወሰዱ ላለማለት ከባድ የውሳኔ ምርጫ ማድረግ እንጂ።
በደምሳሳው፣ "ፖለቲካ ሸፍጥ/ውሸት ነው" በሚል እሳቤ ላይ ተንተርሶ፣ ፖለቲከኞች ከእውነት እየታጠፉ፣ የፈለጉትን እርምጃ እንደተመቻቸው እየወሰዱ እንዲቀጥሉ ማድረግ፣ ሕዝቡ ተጠያቂነትን የማስገደድ ኃላፊነቱን ጥሎ፣ በሸፍጠኛ ግለሰባዊ አምባ-ገነን ሥርዓት ሥር እንዲኖር መፍቀድ ነው።
#Hanga_kijiba_xireeffannutti_bilisa_bahuuf_hin_deemnu!