ትህትናዊ✍️እይታ Tina's view
235 subscribers
230 photos
6 videos
60 links
ኑ በልባችን እንመንን
ያላችሁን በዚህ አጋሩኝ
https://t.me/tinasview
Download Telegram
«...
አንት የከንፈር ወዳጅ
በግዜ ሳመኝ
ጤፍ አበጥራለሁ
የሰው ግዙ ነኝ

የሰው ግዙ ሆኖ
የሰው ግዙ መውደድ
እሳት በገለባ
እፍ ብሎ ማንደድ!
...
🙄»

ቀጥሉት🤔

https://t.me/Gazetaw

የኔው ሲቀጠል ደግሞ እንዲ ሄዶ'ል

ግዞት ከሌለበት ከሰራ ዓለሜ ና፣
ጓዝ ጉዝጓዙ ፍቅር ከልቤ መዲና ።
መንደድ ቢሉ ማየል ከሳተገሞራ ፣
ክሱት ገጽህ ገዢ ደብርህ ከተራራ፣
አንተን አነግሳለሁ ሲሸ'ኙ ከተራ።

✍🏽ቲኑ ከምናብ ዓለም
02/07/18

ያኑረን!!!
2
ዘዋሪቴ ዘወርዋራ ተሽከርክረሽ ለኪሳራ
ዜማ ቅኔው ተኳኩሎ ከብስባሽ ሲያንሰራራ
የኔ ነፍሥስ
ከሱ እቅፍ ከጎኑስር ሲያሳብበኝ ስጎመራ
ውሉደ ፍቅር በሥሥቱ ያስመለጠኝ ከመከራ
ያስከበረኝ በሙሃባ ማተብ ልቡን ለኔ አጥልቆ
ሲሰራራኝ ሲያበጃጀኝ እኔነቴን ከ'ርሱ አርቆ'
ከወሰደኝ ምን እንዳልሆን
ከወሰድኩት ምን እንዳይሆን

02/07/18


https://t.me/tinasview
እናውራበትን?
1👍1
ውድቅ እንበል እስኪ ስብር ከመንበሩ
መኖር ማዳመቂያ ስንት ገባ ግብሩ
ሞትስ ለከርታታ ልቡን ላስገበረ
ያበጠው በመንገድ ሳይደርስ ከሰረ
እንጃ ምን ሊሳመር ምን ሊዘከር ኖሯል
ሽሽት ከራስ ጉያ ከሰው በላይ ከብሯል

04/07/18
ካስገመገሙን ስር
ትህትና ከልብ ሰፈር

https://t.me/Tinasview23
https://t.me/Tinasview23
https://t.me/Tinasview23
1
አንድ ለቅዳሜ

ከዘመናት እልፍኝ ከታጨቀ ዶሴ
ምን ላገኝ ልመለሰ ከነግሳንግሴ
ኧረ ቀስ
ዳና እየታደነ ምናብ ካልረቀቀ
አላፊ ታስሶ ትልም ካልፀደቀ
ከክታብ ቀሳስሞ እውነት ካልተኖረ
ወደፊት ተንዶ ዛሬ ተቀበረ

ሞሾ እናውርድለት
05/07/18
ትህትና ከሃሳብ ሰፈር

የሙሾ ግዳቹን በዚህ https://t.me/tinasview አድርሱ


https://t.me/Tinasview23
https://t.me/Tinasview23
https://t.me/Tinasview23
ለመኖር ሚሮጥ ሰው ላለመኖር ከቆመ ጋ መላተም የለበትም ወይ ያስቀረዋል ወይ ደግሞ እንቅፋት ነው ሚሆነው። እና ምን ያድርግ ካላቹ የራሱን ሂወት ይኑር ያኔ ምናልባት ለመሞት የቆመው ይንቀሳቀሳል ወይ ደሞ እራሱ ለመኖር ሚሮጠው ይቆማል።
በሰው ከመገፋት በራስ መንገድ መንደረደር የበለጠ ያራምዳል፣ አልያም አፅንቶ ያቆማል።

17/07/18
ትህትና ከምናብ ሰማይ ስር
https://t.me/Tinasview23?direct
እንዲህ ያለ ነገር አይቻለሁ ዓመት በዞረ ቁጥር 😍ያጓጓኛል እያንዳንዱ እለት የተደጎሰ መዝገብ ነው ሰፊና ጥልቅ የተለየ ስጦታ። ትርጉም እንዲሰጠኝ ደጋግሜ ማጣጣም እፈልጋለሁ እናም ያን ለማድረግ ከራሴጋ እሆናለሁ ያንን ሳደርግ የቀኑን ዑደት ሳሰላስል ያተረፍኩትን እዘራና ደግሜ አበቅለዋለሁ።
የጎደለውን ለአምላክና ለነገ አስረክባለሁ።
አሁን ደግሞ ከእለታታ ወደ ዓመት ዳሰሳ ሊቀየር 4 ቀናት ቀርተውታል።
ተመስገን ተመስገን ተመስገን!!!✍🏽❤️❤️❤️
21/07/18
ትህትና
ለራስ የተከተበ ከሰከነ ህሊና ጋር

https://t.me/Tinasview23
https://t.me/Tinasview23
https://t.me/Tinasview23
እግዚያብሔር ይመስገን
ለዚህ ደርሰናል
ሲነጋ 1 እንጨምራለን
የፍሬ ዘመን ያድርግልኝ
አሜን
24/07/26
ማስተዋሉን ያብዛልኝ።
ቅምምም ማለት ልብን ማሰናዳት
ነገን እየጓጉ ሰርክ ደጅ ጥናት
እኖራልሁ ብሎ አርቆ መመኘት
ውልደትን መርቆ ወደሞት መጠጋት
እወድሻልሁኝ የኔ ልበ ቀና
ስርዝ ድልዝ ለበስ ያሳለፍነው ዳና
ዞረው ሲሳሳሙ አርብና ልደትሽ
ሲገርመኝ ይውላል የተሳለው መልክሽ
ከገጽ ቅብ በላይ ይታየኛ ልብሽ
እወድሻለሁ የኔ ልብ የኔ ጀግና
24/07/18
ከመጎምራት ክፍል
ለራስ የተከተበ
🙏🏽✍🏽❤️❤️❤️
1
ስለሁሉም እግዚያብሔርን አመሰግናለሁ
ለሚመጣው እርሱ ያውቃል
መልካም ልደት ለኔ
25/07/18
ጥያቄ አለኝ
ግጥሞቼን በድምጽ ላጋራቹ ወይ ነው?
ሃሳባችሁን በዚህ
https://t.me/tinasview
አሳውቁኝ
ወይም በኢሞጂ ግለጹልኝ
አመሰግናለሁ
🔥1
መልካም አመሰግናለሁ
አሁን በሁልት መንገድ እንደአዲስ እንጀምራለን
እንድጽፈው ምትፈልጉትንም ሃሳብ ማጋራት ትችላላችሁ
መልካም ጊዜ
ጥያቄ
ከራስ ለመራራቅ ከሰው ለመኖር
አስመስሎ ማለፍ ይሰራል ወይ ፍቅር?
ወይስ
መስሎ ተመሳስሎ ከራስ እየራቁ
እስኪገለጥ ድረስ በቁም እያለቁ
ነፍስን ሲኦል ልኮ መኖር ሲሳቀቁ?
እህ
06/08/2018
ትህትና
1
በመቆየት ውስጥ የምናቤን ሃገር ምሰራት ምዳስሳት ምኖርባት ነኝ።
ነኝ ነው ይሆናል አምናለሁ ማመን ብቻ አይደለም ሆኖም አለና ለው፣
በመንገዴ ከመጡት ከሄዱትም የተቀዳ ወዝ አለብኝ ያሁኑ ደግሞ ከጉጉትም በላይ ነው
ለምን
እየደረስኩት ነው እየደረስኩበት
መታደል አይደል ምናብን መኖር
እሰይ ተመስገን ነው። ወዝ ላበረከታቹልኝ በሙሉ አመሰግናለሁ
8/8/18
ስላንተ
አልደርስም ካልኩበት ስበህ
አልቆምም ካልኩበት ተክለህ
ስድህ እንዳልነበር ክንፍን ያስበቀልከኝ
ከጎንህ አጉድለህ ሙሉ ያደረከኝ
ያ'ላተ መኖርን ወደህ አስጀመ/ረሳኽኝ
እወድሃለሁ
19/08/18
https://t.me/tinasview
1
ነገን ማጨላለም
ሲያሻው ከደመና ሲያሻው ከሰው ላብጋ እየተሰወረ
እንባዬን አድርቆ ከእግዜሩ ሰማይ ስር ዝናብ ተቀመረ
ጋራው ሲናፍቀኝ የወረደው ልቤ ከገፄ ተላኮ ሸንተረር ወቀረ
እጠጋበት የለኝ ሰው መሆን ሲረክስ ከርሞ ከነገ ስር እየተቀበረ
ምናብ ብቻ ትርፌ ምናልባት የሚያስብል ሰው ሰው የሸተተ ባገኝ እንደራሴ
ነገን ሲያጨልመው ከድቅድቁ ውላጅ አጥንት ሳይንተራስ ካፈር ሳይታገል የሚዘጋ ዶሴ
ይመጣንደሁ ለኔ እጠብቀዋለሁ ከሰማይ ዳር ዳሩ ከምድር ከርስ ሰጥሜ
ጎኔን አስደግፌ ከሸንተረሬ ስር ሲቃ ካየለበት ማየሰብ ቢያቀምሰኝ ልድን ከህመሜ

20/08/18
ትህትና ከምናብ ዓለም
https://t.me/Tinasview23
6
አጀብ አጀባ
አምነሽ ነበር አሉኝ ሁሉን እኩል ሰፍረሽ ከስንዴ ከንክርዳድ ገለባ ሲከብሽ
መንገድ እንጂ ሰውስ ያለ ግፊት አይከብድ አይቆረቁር አይንሳፈፍ ውልሽ
እናሳ እንዴት ነው አጀባው ሲደራ ማንን ማንን ሰደርሽ
ከቁናሽ ማን ሞላ ማን ፍሬውን ሰጠሽ

22/08/2018
ትህትናዊ ዕይታ
5
ሰውም እንደ ምድር ከርሞ ይታረሳል
ክምር ጉልጓል አፈር ለሞት ይሰለፋል
ስንት ነፍስ ይርከፍከፍ ለዚች ምድር ማራሻ
አንድ አንድ ሲገበር ዘመን መሳለሚያ ዙፋንን ሟሟሻ
ክንፍ አብቅይ ነፍስ ሆይ ብረሪ ምጠቂ
በስጋ ደም ጸበል እንዳትጠመቂ
መርቀቅ ግብርሽ ይሁን ከፍ በይ ካፈሩ ከብስባሽ ተራ
አጋድመው ሲፈጁ ውሉደ አራዊት፤ እንደራሴ ሁኚን በአምላክ ስፍራ።

11/09/2018
ትህትና ከህዝብ ሰፈር
6
ስጋት ላባ ሰራች ሥስት ክንፍ ወለደ
ተወርዋሪ ቀስቴ ከሳት ተዋደደ
ሲምዘገዘግ ሄዶ ደመና ቀደደ
ንፋስ ያሳረገው ፍቅር ተገመደ
እሰይ ደግ አረግን በላባ ከነፍን
አሹ አበጃጀን ተሳስረን ወደቅን
አፈር ተንተርሰን ዘርን አበቀልን
29/10/2026
ያኑረን እንድንበር

ትህትና ከመኖር ዓለም
3