الزواج في الإسلام /ትዳር በኢስላም
22.4K subscribers
391 photos
19 videos
8 files
924 links
﴿وَمِنْ آيَاتِهِ أَنْ خَلَقَ لَكُم مِّنْ أَنفُسِكُمْ أَزْوَاجًا لِّتَسْكُنُوا إِلَيْهَا وَجَعَلَ بَيْنَكُم مَّوَدَّةً وَرَحْمَةً﴾

ለማንኛዉም አስተያየት☞☞ @Tidarbaislam_bot
ለይ ያድርሱን

ለጥያቄ ☞☞ t.me/Hayatbintkedir
Download Telegram
الزواج في الإسلام /ትዳር በኢስላም
ጥያቄና መልስ ቁጥር አስር/⑩ 10) ከሚከተሉት ውስጥ የትኞቹን ማግባት ነው በቁርአን ውስጥ እርም የተደረገው? ? ሀ// እናት ለ// ልጆች ሐ// እህት መ// አክስት ሠ// የወንድም ልጅ ረ// የሚስት እናት ሰ// የሚስት ልጆች ሸ// ሁሉም             ቴሌግራማችን ╰➤ ❝@Tidar_Be_Islam ╭┈─────── ೄྀ࿐ ˊˎ- ╰➤ ❝@Tidar_Be_Islam
ጥያቄና መልስ ቁጥር አስራአንድ/⑪

11) ዒሳ (አሌይሂ ሰላም) ጌታ አለመሆኑን ራሱ የተናገረበት ተከታዩ አያ ምን ሱራ ላይ ይገኛል ???

لَقَدْ كَفَرَ ٱلَّذِينَ قَالُوٓا۟ إِنَّ ٱللَّهَ هُوَ ٱلْمَسِيحُ ٱبْنُ مَرْيَمَ ۖ وَقَالَ ٱلْمَسِيحُ يَٰبَنِىٓ إِسْرَٰٓءِيلَ ٱعْبُدُوا۟ ٱللَّهَ رَبِّى وَرَبَّكُمْ ۖ إِنَّهُۥ مَن يُشْرِكْ بِٱللَّهِ فَقَدْ حَرَّمَ ٱللَّهُ عَلَيْهِ ٱلْجَنَّةَ وَمَأْوَىٰهُ ٱلنَّارُ ۖ وَمَا لِلظَّٰلِمِينَ مِنْ أَنصَارٍۢ

እነዚያ «አላህ እርሱ የመርየም ልጅ አልመሲሕ ነው» ያሉ በእርግጥ ካዱ፡፡ አልመሲህም አለ፡- «የእስራኤል ልጆች ሆይ! ጌታዬንና ጌታችሁን አላህን ተገዙ፡፡» እነሆ! በአላህ የሚያጋራ ሰው አላህ በርሱ ላይ ገነትን በእርግጥ እርም አደረገ፡፡ መኖሪያውም እሳት ናት፡፡ ለበዳዮችም ምንም ረዳቶች የሏቸውም፡፡

ሀ//ሡረቱል በቀራ ቁ፡38
ለ//ሡረቱል መርየም ቁ፡4
ሐ//ሡረቱ አል ዒምራን ቁ፡72
መ// ሡረቱል ኢኽላስ ቁ፡3
ሠ//  መልሱ የለም

            ቴሌግራማችን
#ሼር_ያድርጉ👇👇👇

╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
╭┈─────── ೄྀ࿐ ˊˎ-
╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
الزواج في الإسلام /ትዳር በኢስላም
ጥያቄና መልስ ቁጥር አስራአንድ/⑪ 11) ዒሳ (አሌይሂ ሰላም) ጌታ አለመሆኑን ራሱ የተናገረበት ተከታዩ አያ ምን ሱራ ላይ ይገኛል ??? لَقَدْ كَفَرَ ٱلَّذِينَ قَالُوٓا۟ إِنَّ ٱللَّهَ هُوَ ٱلْمَسِيحُ ٱبْنُ مَرْيَمَ ۖ وَقَالَ ٱلْمَسِيحُ يَٰبَنِىٓ إِسْرَٰٓءِيلَ ٱعْبُدُوا۟ ٱللَّهَ رَبِّى وَرَبَّكُمْ ۖ…
መልስ ቁጥር አስራአንድ/⑪

ሠ // መልሱ የለም የሚለው ነው፡፡

#መልሱ_ሡረቱል_ማኢዳ_ቁ፡72 ነው

لَقَدْ كَفَرَ الَّذِينَ قَالُوا إِنَّ اللَّهَ هُوَ الْمَسِيحُ ابْنُ مَرْيَمَ ۖ وَقَالَ الْمَسِيحُ يَا بَنِي إِسْرَائِيلَ اعْبُدُوا اللَّهَ رَبِّي وَرَبَّكُمْ ۖ إِنَّهُ مَن يُشْرِكْ بِاللَّهِ فَقَدْ حَرَّمَ اللَّهُ عَلَيْهِ الْجَنَّةَ وَمَأْوَاهُ النَّارُ ۖ وَمَا لِلظَّالِمِينَ مِنْ أَنصَارٍ

እነዚያ «አላህ እርሱ የመርየም ልጅ አልመሲሕ ነው» ያሉ በእርግጥ ካዱ፡፡ አልመሲህም አለ፡- «የእስራኤል ልጆች ሆይ! ጌታዬንና ጌታችሁን አላህን ተገዙ፡፡» እነሆ! በአላህ የሚያጋራ ሰው አላህ በርሱ ላይ ገነትን በእርግጥ እርም አደረገ፡፡ መኖሪያውም እሳት ናት፡፡ ለበዳዮችም ምንም ረዳቶች የሏቸውም፡፡ አል_ማኢዳህ 72

            ቴሌግራማችን

╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
╭┈─────── ೄྀ࿐ ˊˎ-
╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
الزواج في الإسلام /ትዳር በኢስላም
☞ትዳር_በኢስላም.☜   ክፍል~አራት /④ት =>ከአንድ በላይ ሚስት በቀደምት ነብያት..   #ነብዩላህ_ያዕቁብ_እና_ሌሎችም    ነብዩ ያዕቁብ አሰ በአንድ ጊዜ 4 ሚስቶች ያገቡ ሲሆን እንደመፅሀፍ ቅዱስ ገለፃ ስማቸውም እንደሚከተለው ነው፣ 1/ #ሊያ 2/ #ራሄል 3/ #ባላ 4/ #ዘለፋ ናቸው።   ☞ ከእነዚህ አራት ሴቶች 12 ልጆችን ያገኙ ሲሆን ከሚስቶቻቸው በጣም ተወዳጅ የነበረችው #የነብዩ_ዩሱፍ_እናት_ራሄል…
☞::::::ትዳር~በኢስላም::::::☜

 
#ክፍል_አምስት/⑤ት

ከአንድ በላይ ሚስት በቀደምት ሀይማኖቶች...

#ከአንድ በላይ ሚስት በአይሁዳዎች እምነት
      ከአንድ በላይ ሚስት በቀደምት ሀይማኖቶች የተፈቀደ እና ወሰን ያልተቀመጠለት ድንጋጌ እንደነበር ከላይ አሳልፈናል። አይሁዶች ከአንድ በላይ ሚስትን የሚፈቅዱ ሲሆን#ቱልሙድ በሚባለው ሰው ሰራሽ መፅሀፋቸው የሚስትን ቁጥር አራት መሆን አለበት የሚል ፅፈዋል። ከላይ እንዳሳለፍነው ቁጥራቸውን 4 ብሎ ያስቀመጥ እንጂ ስለአራቱ ሴቶች በምን ሁኔታ መገባት አለባቸው ኑሯቸው ምን መምሰል እንዳለበት ዝርዝር መመሪያ ያልተካተተበት የጎደለ ድንጋጌ ነው።በዚሁ መፅሀፍ ውስጥ ገንዘብ ያለው ሰው የፈለገውን ያክል ሴቶች ባሮች ገዝቶ በእነሱ ስሜቱን መርካት እንደሚችል ተደንግጓል።
  
#ከአንድ በላይ ሚስት በነሷሯዎች ዘንድ
   እንደሚታወቀው ነብዩ ኢሳ በነብይነት ዘመናቸው ሚስት አላገቡም።ሚስት ላለማግባታቸው የራሱ የሆነ ምክንያት አለው። ነብይ ሆነው ያላገቡ ግን
#እርሳቸው ብቻ አልነበሩም።ነብዩ የህያም በተመሳሳይ አለላገቡም ነበር ፣ይህን የሰሙ ነሷራዎች አከማግባት ፅድቅ ያስገኛል የሚል አስተሳሰብ በመያዝ ይህንም የኢሳ አስተምሮ ነው ብለው ድምዳሜ ላይ በመድረስ ብዙዎቹ  ትዳርን አሻፈረኝ  ብለው ትተውታል። ይህ ግብ ትክክለኛ የኢሳ አስተምህሮት አይደለም።ኢሳ አሰ አይደለም አለማግባትን ሊያበረታቱ ይቅርና እንደውም ከአንድ በላይ ማግባት የመልካም መገለጫ እንደሆነ ለተላኩበት አላማ በምሳሌነት በግልፅ አስቀምጠውታል ከዚህም አልፎ በሰማይ ቤትም ከአንድ ሚስት በላይ እንደሚኖር በዚሁ አስተምሮታቸው ውስጥ ተካቷል ይህን አስተምሮታቸውን ያልተረዱ ወይም #አውቀው_ ሚስጥሩን_የደበቁ..ነሷራዎች ኢስላም በጀነት ከአንድ በላይ ሚስቶችን ለመልካም ሰሪዎች አዘጋጅቷል የሚለው ብስራት መሳለቂያ አድርገው ይዘውታል።በምድር አልበቃ ብሎ በሰማይ ቤትም እንዴት ከአንድ በላይ ሚስት ይፈቀዳል??? የሚል የሰይጣን ጦራቸው በኢስላም ላይ ይቀስራሉ።እውነታው ግን የነሷራ እምነት ከአንድ በላይ ሚስት ማግባትን መቼ ከለከለ???? መፅሀፉን መለስ ብሎ ማንበብ እና  ማገናዘብ የተሻለ ይመስለኛል።በትክክል እምነቱ የሚከለክለው ከሆነ በደረቁ ከመተቸት ጨዋነት በተሞላበት መልኩ ለማሳመን መሞከር የተሻለ ይመስለኛል።
    ☞ የነሷራ እምነት ከአንድ በላይ ሴት ማግባት ሲፈቅድ እስከ ስንት የሚለውን(ቁጥር) ግን ገደብ አላስቀመጠም።ለዚህም 2 ዋና ዋና ማስረጃን ማቅረብ በቂ ነው ብዬ አምናለሁ..

1/ "ኢሳ የተላከበትን አላማ በምሳሌ ሲያስረዳቸው እንዲህ ይላል፣ *በዚያን ጊዜ መንግስተ ሰማያት መብራታቸውን ይዘው ሙሽራውን ሊቀበሉ የወጡ 10 ቆነጃጅትን ትመስላለች።ከእነሱ አምስቱ ሰነፎች  አምስቱም ልባሞች ነበሩ፣ሰነፎቹ መብራታቸውን ይዘው ከእነርሱ ጋር ዘይት አልያዙምና ልባሞቹ ግን ከመብራታቸው በተጨማሪ በማሰሯቸው ዘይት ያዙ። ሙሽራውም በዘገየ ሁሉም እንቅልፍ እንቅልፍ አላቸውና ተኙ። እኩል ሌሊትም ሲሆን እነሆ ሙሽራው ይመጣል፣ ትቀበሉት ዘንድ ውጡ የሚልውካታ ኾነ። በዚያን ጊዜ እነዚያ ቆነጃጅት ሁሉ ተነሱና መብራታቸውን አዘጋጁ።ሰነፎቹም ልባሞቹን መብራታችን ሊጠፋብን ነው ከዘይታችሁ ስጡን አሏቸው። ልባሞቹ ግን መልሰው ምናልባት ለእኛና ለእናንተ ባይበቃስ ይልቅስ ወደሚሸጡት ኼዳችሁ ለራሳችሁ ግዙ አሏቸው።ሊገዙም በሄዱ ጊዜ ሙሽራው መጣ፤ ተዘጋጅተው የነበሩም ከርሱ ጋር ወደ ሰርግ ገቡ ደጁም ተዘጋ6...

አንደኛ ፣ ከዚህ የወንጌል አስተምሮት በግልፅ እንደምንማረው ኢሳ ከአንድ በላይ ሚስት ማግባት ወንጀል እንዳልሆነ በምሳሌው አስቀምጧል።
ከአንድ በላይ  ሚስት ማግባት የማይፈቀድ ቢሆን ኖሮ
#አስር ቆነጃጅት ልጅ አገረድ ሙሽሮች_አንድ ሙሽራ እየጠበቁ.. የሚል ምሳሌ ባልሰጠ ነበር።ምክንያቱም ነብይን ያህል ሰው ኀጢአተ በሆነ ነገር ለህዝቦቹ ምሳሌ ፈፅሞ ሊሰጥ አይችልምና..ከዚህም በተጨማሪ ጀነት ውስጥ ከአንድ በላይ ሚስት የለም ለሚሉ ነሷራዎች ንግግራቸው መሰረተ ቢስ ለመሆኑ ይህ ትልቅ ማስረጃ ነው።

#በዚያን_ጊዜ መንግስተ_ሰማያት መብራታቸውን ይዘው_ሙሽራውን ሊቀበሉ የወጡ_አስር ቆነጃጅትን ትመስላለች የሚለው አባባል በቀጥታ መንግስተ ሰማያት ከአንድ በላይ ሚስት ለመኖሩ ጥቆማ ነው ወይም የሚከለክል ቢሆን ስንት ምሳሌ የሚሆን ነገር እያለ መንግስተ ሰማያት ብለው ባልጀመሩ ነበር።

#ሁለተኛ፣ እንደ መፅሀፍ ቁዱስ ገለፃ፣ ኢሳ ሲመጣ የሙሳን ህግ ለማስቀጠል እንጂ ለማፍረስ እንዳልሆነ ወንጌል ላይ በተደጋጋሚ በግልፅ ተቀምጧል።#የነሷሮች ሀይማኖት ዋና መሰረት የሆነው ይኸው ለሙሳ የወረደው መፅሀፍ ተውራት(ኦሪት) እንደሆነ የሚታወቅ ነው.።

#ከአንድ በላይ ሚስት በቀደምት ህዝቦች ዘንድ...ይቀጥላል

            ቴሌግራማችን

╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
╭┈─────── ೄྀ࿐ ˊˎ-
╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
📌ወንድሜ  ውዷ ባለቤትህ ልታበላት፣ ልታጠጣትና ልታስጌጣት ከምትጓጓው በላይ የዲን እውቀት እንድትማርና እንድትቀስም ልትጓጓላት ይገባል።

📌قَال عَمرُو ابنُ قَيسٍ -رَحمَهُ اللهُ-:
☞አምር ኢብን ቀይስ አላህ ይዘንለትና እንዲህ ብሏል።

☜إنَّ المَرأةَ لَتُخاصِمُ زَوجَهَا يَوم القِيامَة عِندَ اللهِ، فَتقُولُ: إنّهُ كانَ لا يُؤدِّبُنِي وَلا يُعلِّمُني شَيئًا، كَانَ يأْتِينِي بِخُبزِ السُّوق

አንድ ሚስት የውመል ቂያማ ባሏን አላህ ዘንድ ትሞግተዋለች። እንዲህም በማለት ትከሰዋለች።
☞አደብ አያስይዘኝም ነበር
☞ስለዲኔ ምንም አያስተምረኝም ነበር

ነገር ግን ብቻ ከሱቅ ዳቦ እያመጣ ሲመግበኝ ነበር ትላለች።
📚 تَفسِيرُ السَّمعانِي (٤٧٥/٥)

            ቴሌግራማችን

╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
╭┈─────── ೄྀ࿐ ˊˎ-
╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
الزواج في الإسلام /ትዳር በኢስላም
☞::::::ትዳር~በኢስላም::::::☜   #ክፍል_አምስት/⑤ት ከአንድ በላይ ሚስት በቀደምት ሀይማኖቶች... #ከአንድ በላይ ሚስት በአይሁዳዎች እምነት       ከአንድ በላይ ሚስት በቀደምት ሀይማኖቶች የተፈቀደ እና ወሰን ያልተቀመጠለት ድንጋጌ እንደነበር ከላይ አሳልፈናል። አይሁዶች ከአንድ በላይ ሚስትን የሚፈቅዱ ሲሆን#ቱልሙድ በሚባለው ሰው ሰራሽ መፅሀፋቸው የሚስትን ቁጥር አራት መሆን አለበት የሚል…
☞ትዳር_በኢስላ☜

 
#ክፍል_ስድስት/⑥

☞ከአንድ በላይ ሚስት በቀደምት ህዝቦች ዘንድ
 
#በቀደምት_ቻይናውያን_ዘንድ
የቻይና ወንዶች በቀድሞ ዘመን የመጀመሪያ ሚስታቸውን ካገቡ በኃላ በርካታ ልጅ አገረዶችን በመግዛት እንደፈለጉ ይጠቀሙባቸው ነበር።
#በኃላየ ተገቡት ወይም የተገዙት ሴቶች ለመጀመሪያዋሚስት ታዛዥ የመሆን ግዴታ አለባቸው ከሌሎች ሚስቶቹ የሚወለዱት ልጆች ለመጀመሪያዋ ሚስት እንደልጅ ታስበው ያድጋሉ።
☞ የቻይና ሴቶች ለባሎቻቸው ባሪያ በመሆን ራሳቸውን እስከማቃጠል የደረሰ መስዋእትነት ይከፍሉ እንደነበር ታሪክ ያስረዳል። የቻይና ባሎች  የሚፈልጓቸውን ሴቶች በቁጥር ሳይገደቡ በህጋዊ ጋብቻ ያገባል። ባል ከመጀመሪያ ሚስቱም ሆነ ከሌላው ማህበረሰብ ለምን አገባህ የሚል ወቀሳ አልነበረም። እንዳውም ወንዶች ከአንድ በላይ እንዲያገቡ ይበረታቱ ነበር።ከዚህም በተጨማሪ
#ገንዘብ_ያለው_ቻይናዊ_ወንድ_በገንዘቡ_የሚፈልጋቸውን_ሴቶች_በመግዛት_እንደሚስት_እንደሚስት_አድርጎ_ይጠቀምባቸው_ነበር
☞ ይህ የጥንት ቻይናውያን ባህል እና ወግ ሆኖ አልፏል።አሁን ቻይናውያን ከሚፈፅሙት አስፀያፊ ተግባር ጋር ሲነፃፀር ያ ትውልድ የተሻለ ያሰየሚመደቡ የአሁኖቹ ቻይኖች እንደበፊቱ በህጋዊ መንገድ
#ከአንድ_በላይ ሴቶችን ባይዙም ሰለጠን ብለው አንድትን ሴት ለአራትና ለአምስት በአንድ ጊዜ ከሚገናኙት ብልሹ ህዝቦች የሚመደቡ ናቸው።አላፍር ብለው የእነሱን ተግባር እንደመልካም በመቁጠር ያለፉት ህዝቦች ተግባር ሲኮንኑ ይደመጣሉ።መኮነን ያለበትን እንኳ በቅጡ የማያውቁ እንስሶች፣
  
#በቀደምት_ህንዶች_ዘንድ
   በጥንታዊያን ህንዶች ዘእንዲሰጡ እንደቻይናዎቹ ከአንድ በላይ ሚስት ማግባት የተለመደ ተግባር ነው።ለሴቶች የሚሰጠው ግምት ከወንዶች በእጅጉ ያነሰ ነበር፣ሴቶች ሙሉ ማንነታቸውን  ለባሎቻቸው አሳልፈው እንዲሰጡ ይገደዳሉ። የህንድ ወንዶች ከአካባቢያቸው እና ጎሳዎቻቸው እራቅ ብለው በመሄድ የፈለጉት ያክል ሴት ያገቡ ነበር። ከሚስቶቹ መካከል የተሻለችውን በመምረጥ ሌሎቹን ሴቶች እንድትመራ እና እንድታስተዳድር ይደረጋል። በብዛት ይህን ስልጣን የሚሰጣት የመጀመሪያ ሚስት ናት። አንዳንድ የህንድ ወንዶች በሺ የሚቆጠሩ ሚስቶች ያገቡ እንደነበር በታሪክ ተመዝግቧል።
#ሪባ_የሚባለው_የህንድ_ንጉስ_3000_ሚስቶች እንደነበሩት ይነገራል። በጣም የሚገርመው ከጥንታዊ ህንዶች ሴቶች መካከል አንድ ጊዜ ከተገቡ እንዳጋጣሚ ባላቸው ከሞተከዚህ በኃላ አለም በቃኝ ብለቅ እራሳቸውን በእሳት የሚያቃጥሉም ጎሳዎች ነበሩ.በቀደምት ፈረንሳዊያን_ዘእቃ
   ከሁለት ንግስት ሴቶች በስተቀር በአጠቃላይ ፈረንሳይ ለሴት ልጆች ቦታ የምትሰጥ አገር አልነበረችም እነርሱ ዘንድ ሴት ልጅን እንደተራ መገልገያ እቃ ይቆጥራሉ።አንዳንድ ጊዜ ያለምንም ጥፋት የሞት ፍርድ ይፈረድባቸዋል። በፈረንሳይዎች ዘንድ አንድ ወንድ የፈለገውን ያህል ሴት ማግባት ይችላል። ብዙ ሴት ማግባት የወንድነት መገለጫ መሆኑን ማህበረሰቡ የሚያምንበት ተግባር ነው። ከዚህ በጣም የከፋ ው ለመስማት የሚዘገንነው አንድ ስሩት እናቱን ፣ ሴት ልጁን፣ እህቱን እንዲሁም 2 እህትማማቾችን ማግባት የሚችልበት ማህበረሰብ ነበር። ለነገሩ አሁንስ ቢኖን በሙስሊሞች ላይ ጣታቸውን የሚቀስሩት ምእራባዊያን ተግባራቸው ከዚህ የተለየ ነው እንዴ? ሴት ልጆቻቸውን የሚደፍሩ ምእራባዊያን ቁጥራቸው ቀላል ነው ?በቀደምት ግብፆች ዘንድ
   በጥንታዊ ግብፆች ዘንድ ነጠላ ሚስትን አብዛኛው ማህበረሰብ የሚያገባ ቢሆንም ከአንድ በላይ ሚስት ማግባትም እንግዳ አልነበረም። በተለይ የግብፅ ንጉሶች እና የንጉስ ቤተሰቦች በስፋት ይተገብሩት ነበር። ይህ ማለት ግን ተራው ማህበረሰብ ማግባት አይፈቀድለትም ማለት አይደለም።
አንድ ወንድ ሁለት ሴቶችን የሚያገባ ከሆነ ሁለቱን ሴቶች በየግላቸው ራሱን በቻለ ቤት በማኖር ባል በየተራ ሚስቶቹን እየዞረ ይጠይቃል ነገር ግን
#መጀመሪያ መጀመሪያ የተገባችው_ሴት የተለየ ክብር እና ቦታ ትይዛለች
   
#በጥታዊ ግሪኮች_ዘንድ
   ጥንታዊ ግሪኮች ከሴት ልጅ ይልቅ ለወንድ ልጅ ልዩ ክብር ስለነበራቸው
#ሚስት የሚያገቡበት ዋናው_አላማ ወንድባልጅ ለማግኘት እንደሆነ ይነገራል።ሚስቱ መውለድ የማትችል ከሆነ የመፍታት ሙሉ መብቱ የወንድ ነው። ሴቶች ባል ካገቡ በኃላ ከቤት መውጣት አይፈቀድላቸውም ነበር። በእርግጥ ለሴት ልጅ ክብሯ ከቤት አለመውጣቷ ነው።በግሪኮች ዘንድ አንድበእጅጉ የተለመደ ቢሆንም ወንዶቹ እንደሚስታቸው የሚቆጥሯት አንድ ተጨማሪ ሴት በየቦታው ትኖራለች።ከዚህ በተጨማሪ የሴቶች ቁጥር በእጅጉ የጨመረ ስለነበር በአገሩ ህግ ከአንድ በላይ ሚስት ማግባት የሚፈቀድና የሚበረታታ አዋጅ ወጥቶ ነበር፣ለምሳሌ ሶቅራጥስ በህጋዊ መንገድ ያገባቸው ሁለት ሚስቶች ነበሩት።.

  
#በጥንታዊ_ሮማዊያን_ዘንድ
   እንደሌሎች ሀገሮች ሁሉ ጥንታዊ ሮሞች ከአንድ በላይ ሚስት የሚፈቅድ ህግ ነበራቸው። ይህንንም ቤተክርስቲያን ትቀበለው እና ታፀድቀው ነበር። ጊዜው እየረዘመ ሲመጣ ከ1750  ዓ. ል በኃላ ከአንድ በላይ ሚስት ቤተክርስቲያኗ አትደግፍም በማለት የሌላ ህግ በማውጣት መከልከላቸው ይታወቃል።ይህ ክልከላ የፈጣሪ ትእዛዝ የሌለበት ሰው ሰራሽ ፈጠራ ከመሆን ውጭ እንደቁም ነገር ሃይማኖታዊ ሽፋን ተሰጥቶት በማስረጃነት ሊቀርብም ሆነ ሌሎችንም ለመተቸት ከግምት የሚገባ አይደለም.ከአንድ_በላይ_ሚስት_በጥንታዊ_አረቦችጥንታ   አረቦች ያለገደብ የሚበቃቸውን ያህል ሚስት ያገቡ እንደነበር የታሪክ ምሁራን ይናገራሉ።ብዙ ሴቶች ማግባት የሀይለኝነት ፣ የታዋቂነት፣የጀግንነትና የባለፀጋነት መገለጫ አድርገው ይቆጥሩታል።አንድ ወንድ ብዙ ሴቶችን ባገባ ቁጥር ደረጃውም በዛው ልክ እየጨመረ ይሄዳል ተብሎ ይታሰብ ነበር 
#አንዳንዶቹ_ስድስትአ_ንዳንዶቹ_አስር_ሌሎቹ_ደግሞ_እስከመቶ የሚደርሱ ሚስቶች ነበሯቸው።እንደምሳሌ ብንመለከት ፣ የነብዩ ሰአወ አጎት አብዱልሙጠሊብ፣ሱፍያን ቢንሀርብ እና ሶፍዋን ኢብኑ ኡመያህ እያንዳንዳቸው ስድስት ስድስት ነበራቸው ሙጊራህ ኢብኑ ሹዕባህ ሰባት ሚስቶች ነበሯቸው
    ☞ ነብዩ  ﷺ እስልምናን ይዘው ሲመጡ አብዛኛዎቹ የአረብ ንዳቸው ከአስር ያላነሱ ሚስቶች ነበሯቸው።ለምሳሌ ሱዑድ ኢብኑ መዕቀብ ፣ዑርወት ኢብኑ መስኡድ፣ሱፍያን ኢብኑ አብዲላህ እና መስኡድ ኢብኑ አምር እያንዳንዳቸው አስር አስር ሚስቶች ነበሯቸው።

ቀይስ ኢብኑ ሳቢት ሲያወሩ እንዲህ ይላሉ፣ስምንት ሚስቶች በስሬ እያሉ እስልምናን ተቀበልኩ፣ከዛም ወደአላህ መልእክተኛ ዘንድ መጥቼ ይህን ነገርኳቸው እሳቸውም "ከእነሱ ውስጥ አራት ምረጥና ሌሎቹን ፍታ" አሉኝ ይላል.
   ☞ አብደላህ ኢብኑ ኡመር ሲያወሩ በጃሂልያ ይላሉ በጃሂልያ ዘመን ያገባኋቸው አስር ሚስቶች በስሬ እያሉ እኔም ሚስቶቼም እስልምናን ተቀበልን።ከእነርሱ 4 ብቻ እንድመርጥ ነብዩ ﷺ አዘዙኝ"ይላል።

   ☞ ነውፈል ኢብኑ ሙአዊያህ እንዲህ ይላሉ፣ "5 ሚስቶች በስሬ እያሉ እስልምናን ተቀበልኩ፣ከዛም ወደአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዓሌይሂ ወሰለም ዘንድ መጥቼ ጠየኳቸው፣ እርሳቸውም "አንዷን ፍታ ሌሎቹን ያዝ" አሉኝ ይላል።
    በዚያን ጊዜ(በጃሂልያህ ዘመን) በአንድ ወንድ ስር የሚኖሩ ሴቶች መብዛታቸው ብቻ ሳይሆን ከወንዶች በኩል የሚደርስባቸው በደል እጅግ የሚዘገንን ነበር  ወንዶች ያለገደብ
ያገቧቸውን ሴቶች አይደለም በፍትህ ሊያስተዳድሯቸው የሚያስፈልጋቸውን እንኳን መሰረታዊ ነገሮች አያገኙም ነበር የሰው ልጅ መሆናቸው ግምትየሚሰጠው አልነበረም።
ይቀጥላል #ሼር_ያድርጉ
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
☞አራዳ ሙስሊም ሚስቱን ለማስደሰት ብሎ እናቱን አያስቀይምም ፣ የእናቱን መብት ለመጠበቅ ብሎ ሚስቱንም አያስቀይምም ፣ የሚስቱንም ሆነ የእናቱን መብት ገደብ ለይቶ በሚገባ ያውቃል ። ስለዚህ ወንድሜ የእናትንም ሀቅ ሆነ የሚስትህን ሀቅ በግባቡ ተወጣ።

            ቴሌግራማችን

╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
╭┈─────── ೄྀ࿐ ˊˎ-
╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
ሐቂቃ ወንዶቻችን  አደብ  አጥታቹሃል።  ቆይ  ግን  እንደስማቹህ  በፆታችሁስ  ለምን  ወንድ  አትሆኑም!  እኔማኮ  ገርሞ  ይገርመኛል   የምታገባዉ  አንድቷን  ነዉ  አይደል ?  አላህ  ካለልህ  አግብተህ  አይተህ  አቅምህ  ከቻለ  እያደር  እስከተፈቀደልህ  4 ድረስ  ትጨምራለህ።  ከዛ  በፊት  ሳታገባ  የምታወራቸዉ   ያለማካበድ  ከ10  አያንሱም   ኧረ  ወዴት  እያመራህ  ነዉ  አኺ''  ቆይ ግን  ያቺንም  ይችንም  ፍቅሬ  ማሬ  እያልክ  ከጉሮሮ  የማይወርድ  ቃል  መዘባረቅ ምንድን ነው   ጥቅሙ?   ይልቅ  ከቻልክ  ለምን  አግብተህ  አትሰተርም?  ደሞ  በሚዲያ  ጊዜህንም  ካርድህንም  አታባክን  ተዉ  ግን  ወንዶች  ልብ  ግዙ   ሐቂቃ  ይህ  ተግባራችሁ  እጅግ  አስቀያሚ  ነዉ   ያሣፍራል   በቃ  ተሰተሩ   ሴቶች  የመዝረክረካቸዉ  ዋናዉ  ሰበቡ  እናንተ  ናችሁ   እናንተ   ቆፍጠን  ብትሉ  ሤቶቻችንም   አይደርሱም  ነበር   ስለዚህ  እባካቹህ  ከቻላችሁ  አግቡ  ካልቻላችሁ   ሴቶችን  አታጃጅሉ   አላህን  ፍሩ! 

አሁንማኮ   በመካከላችን  መተማመንም  ጠፋ።  መጥፎዎቹ  ከፊታችን  ተሠልፋቹህ  ከኋላ ደህነኞቹን  እንዳናይ  ጋረዳቹህን !


የህልምህ  ንግስቷ  ያቺ  የናፈካት
ጊዜዉ  እከሚደርስ  እስከምታገኛት
ቆጠብ  በልና  በሶብር  ጠብቃት


ተስፋህን  ሠንቀህ እስከዛዉ ግን  ታገስ
ከዚች  ከዛ እያልክ  የትም አትልከስከስ

  ቴሌግራማችን

╰➤ ❝@Tidar_Be_Islam
╭┈─────── ೄྀ࿐ ˊˎ-
╰➤ ❝@Tidar_Be_Islam
الزواج في الإسلام /ትዳር በኢስላም
☞ትዳር_በኢስላ☜   #ክፍል_ስድስት/⑥ ☞ከአንድ በላይ ሚስት በቀደምት ህዝቦች ዘንድ   #በቀደምት_ቻይናውያን_ዘንድ የቻይና ወንዶች በቀድሞ ዘመን የመጀመሪያ ሚስታቸውን ካገቡ በኃላ በርካታ ልጅ አገረዶችን በመግዛት እንደፈለጉ ይጠቀሙባቸው ነበር። #በኃላየ ተገቡት ወይም የተገዙት ሴቶች ለመጀመሪያዋሚስት ታዛዥ የመሆን ግዴታ አለባቸው ከሌሎች ሚስቶቹ የሚወለዱት ልጆች ለመጀመሪያዋ ሚስት እንደልጅ ታስበው…
☞:::::ትዳር በኢስላም:::::☜

 
#ክፍል_ሰባት_⑦ት

     
#ከአንድ_በላይ_ሚስት_በኢስላም

   ባለፈው እንዳሳለፍነው በጃሂሊያ ዘመን (ኢስላም ከመታደሱ በፊት) በአለም ላይ ያሉ ሀገራት ለሴት ልጅ ያላቸው ክብር እና ግምት በእጅጉ የወረደ በመሆኑ ያለምንም የቁጥር ገደብ ብዙ ሴቶች በአንድ ባል ስር እንዲተዳደሩ ይገደዳሉ።በዚህ ድርጊት ምክንያት በሴቶች ላይ የሚደርስባቸው ግፍና በደል ወንዶችን ምንም የሚያስጨንቃቸው አልነበረም።

    የሰው ልጅ አይነታ የሆኑት
#የአላህ_መልእክተኛ_ሰአወ ኢስላምን ለማደስ ከመጡ በኃላ በጃሂልያ ይተገበር የነበረው ፈር የለቀቀው በሴቶች ላይ ይደረግ የነበረው #ግፍና_መከራ ገፈው ጣሉት።ከአንድ በላይ ሚስትን በተመለከተ እስልምና ቁጥርን ብቻ መገደብ ሳይሆን በሚስቶችም መካከል ፍትሀዊነትም ጭምር ትኩረት ሰጥቶ አስተካክሏል

#በፍትህ_ማስተዳደር_ያልቻለ_አንድ_ትብቃው_እሷንም_ማስተዳደር_ያልቻለ_ማስተዳደር_እስኪችል_ድረስ እንዲፆም_እና_እንዲታገስ በማድረግ ከእንግዲህ ሴት ልጅን እንደፈለጉ ማድረግና መጨቆን እንዳከተመለት ለሴት ልጅ ኢስላም ሙሉ የሆነ ዋስትና እንደሰጣት ታወጀ።አዋጁም ከአፅናፍ እስከ አፅናፍ ተስተጋባ።

    ከዚህም በተጨማሪ ሴት ልጅ ውጭ ወጥታ ከወንድ ጋር እንዳትጋፋ የወንዶች ዘለፋ እንዳያገኛት ሂጃቧን ጠብቃ ቤቷ እንፍትሆን በማድረግ እሷን የመንከባከብ ግዴታውን በወንዶች ላይ አደረገ።እየቻለ ቢያስቸግራት ፀቡ ከማንም ጋር ሳይሆን ከአላህ ጋር እንደሆነ ነብዩ ሰአወ አስጠነቀቁ። በኢስላም ውስጥ
#ሴት_ መሆን_መታደል ነው።እንዲሉ በአጠቃላይ እስላም ለሴቶች ምሽግ ነው።ነገር ግን የኢስላም ጠላቶች ኢስላም ከአንድ በላይ በመፍቀዱ የሴቶችን መብት ይጋፋል። የሚል የእብድ ወሬ ሲያናፍሱ ይደመጣሉ።ኢስላም ከአንድ በላይ ሚስት ማግባት ማስገደድ ሳይሆን በአለፉ እምነቶችና ባህሎች ፈር ለቆ የነበረውን ከአንድ በላይ ሴቶችን ማግበስበስ በገደብ እና በፍትህ እንዲሆን ህግ ማሰረቀመጥ እንደሆነ በዝርዝር አሳልፈናል..

እስከ አራት የተፈቀደ ለመሆኑ ማስረጃ

               
#ቁርአናዊ_ማስረጃ
   አላህ ሱብሀነ ወተአላ እንዲህ ብሏል፣

وَإِنْ خِفْتُمْ أَلَّا تُقْسِطُوا فِي الْيَتَامَىٰ فَانكِحُوا مَا طَابَ لَكُم مِّنَ النِّسَاءِ مَثْنَىٰ وَثُلَاثَ وَرُبَاعَ ۖ فَإِنْ خِفْتُمْ أَلَّا تَعْدِلُوا فَوَاحِدَةً أَوْ مَا مَلَكَتْ أَيْمَانُكُمْ ۚ ذَٰلِكَ أَدْنَىٰ أَلَّا تَعُولُوا

በየቲሞችም (ማግባት) አለማስተካከላችሁን ብትፈሩ (ዝሙትንና ከተወሰነላችሁ በላይ ማግባትንም ፍሩ)፡፡ ከሴቶች ለእናንተ የተዋበላችሁን ሁለት ሁለት ሦስት ሦስትም አራት አራትም አግቡ፡፡ አለማስተካከልንም ብትፈሩ አንዲትን ብቻ ወይም እጆቻችሁ ንብረት ያደረጉትን ያዙ፡፡ ይህ ወደ አለመበደል በጣም የቀረበ ነው፡፡ (ሱረቱ አል-ኒሳእ - 3)

    ☞ይህ የቁርአን አንቀፅ፣ በኢስላም ውስጥ ከአንድ በላይ ሚስት ማግባት የሚፈቀድ መሆኑን ግልፅ ማስረጃ ነው።ነገር ግን በሴቶች መካከል በፍትህ ማስተዳደርን ቅድመ መስፈርት አድርጎ ደንግጓል።
#ፍትህ ዋና ቅድመ መስፈርት ለመሆኑ የቁርአን አንቀፁ የወረደበት ሰበብ ማወቅ መልክቱ ግልፅ ያደርገዋል..

    እናታችን አኢሻ ረአ እንዲህ ይላሉ፣ "አንድ ሰው በውስጡ የሚያሳድጋት ብዙ ንብረት ያላት የቲም ሴት ልጅ ነበረችው፣ ንብረቷን ፈልጎ ጥሎሹን በትክክል ሳይሰጣት አገባት።ከዚያ ይቺ የቁርአን አንቀፅ ወረደች.።

   ☞  በሌላ ዘገባ ዑርወት ኢብኑ ዙበይር ወደ እናታችን አኢሻ ዘንድ መጣና ስለ
"وَإِنْ خِفْتُمْ أَلَّا تُقْسِطُوا فِي الْيَتَامَىٰ"
ጠየቃቸው እሳቸውም እንዲህ ብለውታል፣ "የወንድሜ ልጅ ሆይ;አንድ ወንድ ሃላፊ ሆኖ የሚያሳድጋት የቲም ሴት ልጅ ገንዘቧ እንዲሁም መልኳ አስቀንቶት መህሯን በትክክል ሳይሰጣት እንዳያገባት ማለት ነው፣ ይህ ነው የተከለከለው። እሷን ማግባት የሚፈልግ ከሆነ መህሯን ለሌሎቹ እንደሚሰጠው አድርጎ በፍትህ መህሯን ለሌሎች ሚስቶች የሚገባውን ሰጥቶ ያግባት።ነገር ግን ፍትህ ማጓደልን ከፈራ እሷን ትቶ ሌሎችን የሚያስደስቱትን እስከ አራት ማግባት ይችላል ማለት ነው።" ቡኻሪ ዘግበውታል።.

#ይቀጥላል_ኢንሻአላህ_ሼር_ያድርጉ👇👇👇

            ቴሌግራማችን

╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
╭┈─────── ೄྀ࿐ ˊˎ-
╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
☞ሷሊህ መሆን የሚቻለው በምኞት ሳይሆን ሰበብ በማድረስ ነው⇩

ከሰበቦች ሁሉ የመጀመሪያው
#ዱዓ ሲሆን ቀጣዩ ደግሞ #ጥረት ነው
ያረብ ከሷሊዎች አድርገን አሚን

            ቴሌግራማችን

╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
╭┈─────── ೄྀ࿐ ˊˎ-
╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
الزواج في الإسلام /ትዳር በኢስላም
☞:::::ትዳር በኢስላም:::::☜   #ክፍል_ሰባት_⑦ት       #ከአንድ_በላይ_ሚስት_በኢስላም    ባለፈው እንዳሳለፍነው በጃሂሊያ ዘመን (ኢስላም ከመታደሱ በፊት) በአለም ላይ ያሉ ሀገራት ለሴት ልጅ ያላቸው ክብር እና ግምት በእጅጉ የወረደ በመሆኑ ያለምንም የቁጥር ገደብ ብዙ ሴቶች በአንድ ባል ስር እንዲተዳደሩ ይገደዳሉ።በዚህ ድርጊት ምክንያት በሴቶች ላይ የሚደርስባቸው ግፍና በደል ወንዶችን…
☞::::::ትዳር በኢስላም:::::☜

  .
#ክፍል_ስምንት/⑧ት
     
#ከአንድ በላይ ሚስት በኢስላም

#እስከ_አራት_የተፈቀደ_ለመሆኑ_ማስረጃ

               
#ቁርአናዊ_ማስረጃ
   አላህ ሱብሀነ ወተአላ እንዲህ ብሏል፣

وَإِنْ خِفْتُمْ أَلَّا تُقْسِطُوا فِي الْيَتَامَىٰ فَانكِحُوا مَا طَابَ لَكُم مِّنَ النِّسَاءِ مَثْنَىٰ وَثُلَاثَ وَرُبَاعَ ۖ فَإِنْ خِفْتُمْ أَلَّا تَعْدِلُوا فَوَاحِدَةً أَوْ مَا مَلَكَتْ أَيْمَانُكُمْ ۚ ذَٰلِكَ أَدْنَىٰ أَلَّا تَعُولُوا

በየቲሞችም (ማግባት) አለማስተካከላችሁን ብትፈሩ (ዝሙትንና ከተወሰነላችሁ በላይ ማግባትንም ፍሩ)፡፡ ከሴቶች ለእናንተ የተዋበላችሁን ሁለት ሁለት ሦስት ሦስትም አራት አራትም አግቡ፡፡ አለማስተካከልንም ብትፈሩ አንዲትን ብቻ ወይም እጆቻችሁ ንብረት ያደረጉትን ያዙ፡፡ ይህ ወደ አለመበደል በጣም የቀረበ ነው፡፡ (ሱረቱ አል-ኒሳእ - 3)

#ከአንቀፁ_የምንማራቸው_ቁም_ነገሮች

_አንቀፁ አንድ ወንድ ማግባት የሚችለው ከፍተኛው ቁጥር አራት መሆን እንዳለበት ይደነግጋል።ከአራት ሚስት በላይ ከነብዩ ሰአወ  ውጭ ማንኛውም ሰው መጨመር እንደማይፈቀድለት ኢማም አሻፊኢይ ኢጅማእ (የሙስሊም ሊቃውንት የጋራ አቋም)) አለው ይላሉ።ነብዩ ሰአወ ለምን ከአራት በላይ እንደተፈቀደላቸው እና ከአንድ በላይ የማግባታቸው ጥበብ ሌላው ተራው ሰው ከአንድ በላይ ከሚያገባበት ምክንያት የተለየ ነው።ይህን በተመለከተ እራሱን የቻለ ምዕራፍ ስላለው ከማውጫው ላይ በመፈለግ በዝርዝር ማንበብ ጠቃሚ ነው።

_አንቀፁ ከአንድ በላይ ሚስት ማግባት የፈለገ ሰው
#ፍትሃዊነት ቅድመ መስፈርት መሆን እንዳለበት ያስተምራል።በፍትህ ማስተዳደር የማይችል ወይም ፍትሃዊነት ሊጎለኝ ይችላል
ብሎ የሚያስብ ወንድ ከሆነ ከአንድ በላይ ማግባት እንደማይፈቀድለት አንቀፁ ከሚሰጠን ግንዛቤ የተወሰኑት ናቸው።

    ☞ ፍትሃዊነት ሲባል አንድ ሰው ማድረግ በሚችለው
#እንደቀለብ_ልብስ_መኖሪያቤት_እና_አብሮማደርን የሚያካትት ነው።ነገር ግን ከእርሱ ቁጥጥር ውጭ ሆኖ በማይችለው እና ከአቅሙ በላይ በሆነው እንደ #ፍቅር_መስጠት ያሉ ነገሮች ሁሉንም ሚስቶቹን እኩል ላድርግ ቢል ማድረግ አይችልም።ምክንያቱም አላህ በልቡ ላይ #ትወደድ_ያላት_ሴት_እሱ_ዘንድ_የበለጠ_ትወደዳለች።ለዚህ ሲባል አላህ እንዲህ ይላል፣

وَلَن تَسْتَطِيعُوا أَن تَعْدِلُوا بَيْنَ النِّسَاءِ وَلَوْ حَرَصْتُمْ ۖ فَلَا تَمِيلُوا كُلَّ الْمَيْلِ فَتَذَرُوهَا كَالْمُعَلَّقَةِ ۚ وَإِن تُصْلِحُوا وَتَتَّقُوا فَإِنَّ اللَّهَ كَانَ غَفُورًا رَّحِيمًا
በሴቶችም መካከል ምንም እንኳ ብትጓጉ (በፍቅር) ለማስተካከል አትችሉም፡፡ እንደ ተንጠለጠለችም አድርጋችሁ ትተዋት ዘንድ (ወደምትወዷት) መዘንበልን ሁሉ አትዘንበሉ፡፡ ብታበጁም ብትጠነቀቁም አላህ መሓሪ አዛኝ ነው፡፡[ ሱረቱ አል-ኒሳእ - 129 ]

☞ ከቁርአን አንቀፁ የምንማረው ቁምነገር፣ አንድ ሰው በሚስቶቹ መካከል በልብ ላይ ባለው ነገር(ፍቅር) ማስተካከል የማይችል መሆኑን ነው። ነገር ግን የሰው ልጅ የሚችለውን ማስተካከል ጠብቆ መያዝ እንዳለበት ካለፈው የቁርአን አንቀፅ ለማየት ሞክረናል። እንደውም በሚስቶች መካከል ፍትሃዊ መሆን የመጀመሪያ መስፈርት ከሚባሉት ውስጥ ነው።

#ማሳሰቢያ፣ አንዳንድ አዕምሯቸው እንዳያገናዝብ የተዘጋባቸው ሰዎች ከአንድ በላይ ሚስት ማግባት አይቻልም ብለው የሚከራከሩ በኢስላምም ውስጥ ብቅ ብለዋል።ማስረጃ ብለው ያቀረቡት ከላይ ያሳለፍነውን የቁርአን አንቀፅ ነበር።እንደነሱ አባባል የቁርአኑ አንቀፅ "በሴቶች መካከል ምንም እንኳን ብትጓጉ ለማስተካከል አትችሉም" ብለው በመተርጎም * በሴቶች መካከል ማስተካከል ደግሞ ቅድመ መስፈርት ስለሆነ ከአንድ በላይ ሚስት ማግባት አይቻልም* የሚል ድምዳሜ ላይ ደረሱ። #ትርጉሙን_ለስሜታቸው_እንዲመቻቸው_አድርገው_በመተርጎም_እነሱ_ይህን_ይበሉ_እንጂ_ትክክለኛ_የአንቀፆቹ_መልእክት_እንዳሳለፍነው_ነው

    📚 የመጀመሪያው የቁርአን አንቀፅ የሚለው በየቲሞች መካከል ፍትህን እናጓድላለን ብላችሁ ከፈራችሁ ሌሎች ሴቶችን እስከ አራት ማግባት ትችላላችሁ የሚል ሲሆን የሁለተኛው የቁርአን አንቀፅ የሚያስረዳው ደግሞ በሴቶች መካከል ፍቅርን እኩል ማካፈል አትችሉም።ነገር ግን በምትችሉት ነገር ሴቶቻችሁን ችላ ብላችሁ እንዳትተዋቸው የሚል መልክ አዝሏል።
#ትክክለኛውም_የቁርአኑ_መልእክት_ይህ_ነው
  ☞ በሚችለው ነገር በሚስቶቹ መካከል ፍትሃዊ ያልሆነ ወንድ አላህ ዘንድ ትልቅ ቅጣት እንደሚጠብቀው ነብዩ ሰአወ ተናግረዋል።

    ☞አቡ ሁረይራ ባስተላለፉት ሀዲስ ነብዩ ሰአወ እንዲህ አሉ፣ "ሁለት ሚስቶች እሱ ዘንድ ያሉት እና በመካከላቸው ፍትሃዊ ያልሆነ ወንድ የቂያማ ቀን አንድ ጎኑ የተዘነበለ ሆኖ ይመጣል"  (ቲርሚዝይ ዘግበውታል

      ❗️ሙስሊም ሲባል ከዚህም ባለፈ በሁሉም ነገር ላይ በሚችለው አቅሙ በፈቀደው ፍትሃዊ መሆን መለያ ባህሪይው ሲሆን በተለይ ደግሞ በውስጡ ባሉት የኑሮ አጋር ከሆኑት ሚስቶቹ ጋር ሲሆን በእጅጉ ትኩረት የሚሰጠው ነው.።

  
#ይቀጥላል

            ቴሌግራማችን

╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
╭┈─────── ೄྀ࿐ ˊˎ-
╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
☞የባለቤትሽን ቤተሰቦች ትወጃለሽ??  እህቴ
     
  ☞ሙእሚን ሴት፤ የባሏን ቤተሰቦች በተለይም እናቱን ታከብራለች። መልካም ግንኙነትንም ታበለፅጋለች። የባልን እናት እንደጠላት የሚስለውን ያረጀ ግንዛቤ ወደጎን በመተው አላህን ታስደስታለች።  ችግር ቢገጥማት እንኳ ሰብር በማድረግ የባለቤቷን ሀቅ ትሞላለች።
  
መልካም ሚስት ባሏ ለእናቱ መልካም እንዲሰራ ትረዳዋለች፤ እናቱን በመንከባከብና ሀቋን በመሙላት ረገድ ድክመት ካየችበትም ትመክረዋለች እንጂ ለሸይጣን ረዳት አትሆንም!!
    
☞ውዷ እህት! በሚቀጥሉት ቀናት ውስጥ  ለአላህ ብለሽ የባለቤትሽን ቤተሰቦች ጠይቂ። ከዚህ ቀደም የተቀያየምሽውን ሁሉ ይቅር ተባባይ። አላህን እና ባለቤትሽን በማስደሰትሽ የምታገኚው የመንፈስ እርካታ በገንዘብ የማይተመን እንደሆነ ትረጃለሽ።
   
አላህ ላገቡት ያማረ የፍቅር የደስታ ሂወት ያድርግለችው ላለገቡት ኸይረኛውን ይወፍቃችው

‼️ዱንያ አጭር ህይወት ናትና በፅድቅ እናሳልፋት

            ቴሌግራማችን

╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
╭┈─────── ೄྀ࿐ ˊˎ-
╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
ታገስ! አላህ ታጋሾችን ያለ ገደብ ይመነዳል!!
————
ትግስት (ሶብር) እጅግ በጣም ታላቅ ስጦታ ነው!። ትግስት በእርግጥ ጅምሩ መራራና ከባድ ቢሆንም መጨረሻው ደግሞ ከማር የበለጠ ጣፋጭ ነው!።

አንድም ሰው ከትግስት የተሻለ ስጦታ የተሰጠው የለም!። ከአቢ ሰዒድ አል-ኹድሪይ (ረዲየላሁ ዐንሁ) ተይዞ የአላህ መልእክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል:-
የሚታገስ ሰው አላህ ያስታግሰዋል፣ አንድም ሰው ከትግስት የተሻለ ስጦታ አልተሰጠውም!።” [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል]

የትግስት ምንዳ አላህ ዘንድ እጅግ በጣም የላቀ ከመሆኑ አንፃር ታጋሾችን የሚመነዳው ያለ ገደብ ነው። አምላካችን አላህ እንዲህ ብሏል:-

قُلْ يَا عِبَادِ الَّذِينَ آمَنُوا اتَّقُوا رَبَّكُمْ ۚ لِلَّذِينَ أَحْسَنُوا فِي هَٰذِهِ الدُّنْيَا حَسَنَةٌ ۗ وَأَرْضُ اللَّهِ وَاسِعَةٌ ۗ إِنَّمَا يُوَفَّى الصَّابِرُونَ أَجْرَهُم بِغَيْرِ حِسَابٍ

«ጌታችሁ፣ እናንተ ያመናችሁ ባሮቼ ሆይ! ጌታችሁን ፍሩ!፡፡ ለነዚያ በዚህች በቅርቢቱ ዓለም መልካም ለሠሩት መልካም ምንዳ አላቸው፡፡ የአላህ ምድርም ሰፊ ናት፤ (ብትቸገሩ ተሰደዱ)፡፡ ታጋሾቹ ምንዳቸውን የሚሰጡት ያለግምት ነው፣ (ይላል) በላቸው፡፡» አዝ-ዙመር 10

ስለ ትግስት እጅግ በጣም በርካታ የቁርኣን አንቀፆችና ሶሂህ ሀዲሶች አሉ። በግል ጉዳይም ይሁን በጀመዓ ጉዳይ፣ በአኼራ ጉዳይም ይሁን በዱኒያ ጉዳይ በተለያየ መንገድ በሚደርሱ ችግሮችና ፈተናዎች ምንም ያህል ቢበረቱ ዋጥ አድርጎ ታጋሽ ሆኖ በጥንቃቄ ማሳለፍ መጨረሻው ያማረና ገደብ የለሽ ለሆነ ምንዳ ያደርሳል!!።

ብዙ ጊዜ ለእኛ ክፉ መስለው የሚታዩን ስለደረሱብን ወይም ስላመለጡን፣ አለያም ሀብት ንብረት ስለወደመ፣ ደክመን ጥረን ሰበብ አድርሰን ከሰራነው ቤት ስለተፈናቀልን… የምንቆጭባቸውና ትግስት የምናጣባቸው ነገሮች በትግስት ዱዓ እያደረግን አላህ እስልምናን እና ጤናን ጨምሮ ሌሎች ተቆጥረው የማያልቁ ፀጋዎችን እንዳጎናፀፈን እያስተዋልን በማመስገን በጥንቃቄ ስናልፋቸው መጨረሻቸው መልካም ሆነው እናገኛቸዋለን!።

ታዳ አንተ ምን ጨነቀህ?! ታገሽ ብቻ ሁን!፣ አላህ ከታጋሾች ጋር ነውና። አላህ እንዲህ ብሏል:-

يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا اسْتَعِينُوا بِالصَّبْرِ وَالصَّلَاةِ ۚ إِنَّ اللَّهَ مَعَ الصَّابِرِينَ

«እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በመታገስና በሶላት ተረዱ፡፡ አላህ (በእርዳታው) ከታጋሾች ጋር ነውና፡፡» አል-በቀረህ 153

ሸይኽ ሙሀመድ ቢን ሷሊህ አል-ዑሰይሚን (ረሂመሁላህ) እንዲህ አሉ:-
“ትክክለኛው ወርቅ በእሳት ካልተፈተነ አይታወቅም፣ የእንጨቱ (ዌራ) ሽታ አይታወቅም በእሳት ሲቃጠል ቢሆን እንጂ። እንዲሁም አማኝ የሆነ ሰው አይታወቅም በመፈተን ቢሆን እንጂ። ወንድሜ ሆይ! አደራ በትግስት!፣ እርግጥ ነው በዲንህ ትፈተናለህ፣ በእርግጥም ያፌዙብህ ይሆናል…፣ ታገስ እውነተኛ ሁን! መልእክተኞች ኡሉል ዐዝሞች ላይ የደረሰውን ተመልከት (አስታውስ)።

የአላህ መልእክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) መስጂደል ሀረም (መካ) አካባቢ ለአላህ ሱጁድ ላይ ሆነው እያለ፣ ከሰዎች ሁሉ ጠማማ የሆኑት ይመጡና የግመል ፈርስና እንግዴ ልጅ ይጥሉባቸው ነበር፣ ሱጁድ ላይ ሆነው ነው ይህን የሚያደርጉባቸው የነበረው፣ ይህ እጅግ በጣም ከባድና ከመልእክተኞችና ኡሉል ዐዝሞች ያልሆነ ሰው የማይታገስበት ተግባር ነው!። በህፃንና በጨቅላ እድሜዋ የነበረችው ልጃቸው ፋጢማ (ረዲየላሁ ዐንሃ) መጥታ እስክታነሳላቸው ድረስ ሁሉ ይቆይ ነበር፣ እንደዛም ሆኖ ሙሽሪኮች ይስቁ ያላግጡ ነበር።

ታገስ! አላህ ዘንድም ምንዳ አገኝበታለሁ ብለህ አስብ፣ እወቅ! የስቃይህና የችግርህ ማብቂያ ሞት ከሆነና ለአላህ ብለህ ታጋሽ ሆነህ ከሞትክ፣ ከአንድ ሀገር ወደተሻለና መልካም ወደሆነ ሀገር ተሸጋግረሃል።” [ተፍሲር ኢብኑ ዑሰይሚን 3/41☜


የተለያዩ ት/ቶችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችን ⤵️
#join በማድረግ ይቀላቀሉ
            ቴሌግራማችን

╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
╭┈─────── ೄྀ࿐ ˊˎ-
╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
☞ሕይወት ይበልጥ እየተዋበች የምትመጣው ፣ ይበልጥ ኢስላም የህወትህ አካል ሲሆን ነው ።
ስለዚህ በዲናችሁ በርቱ

            ቴሌግራማችን

╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
╭┈─────── ೄྀ࿐ ˊˎ-
╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
الزواج في الإسلام /ትዳር በኢስላም
☞::::::ትዳር በኢስላም:::::☜   .#ክፍል_ስምንት/⑧ት       #ከአንድ በላይ ሚስት በኢስላም #እስከ_አራት_የተፈቀደ_ለመሆኑ_ማስረጃ                 #ቁርአናዊ_ማስረጃ    አላህ ሱብሀነ ወተአላ እንዲህ ብሏል፣ وَإِنْ خِفْتُمْ أَلَّا تُقْسِطُوا فِي الْيَتَامَىٰ فَانكِحُوا مَا طَابَ لَكُم مِّنَ النِّسَاءِ مَثْنَىٰ وَثُلَاثَ…
☞:::ትዳር በኢስላም::::☜

  ክፍል ዘጠኝ/⑨ኝ

  
#ከአንድ_በላይ_ሚስት_የመፈቀዱ_ጥበብ

    አላህ ለወንድ ልጅ ከአንድ በላይ እስከ አራት ሚስት ማግባት እንዲችል ሲፈቅድለት የሰው ልጅ ሊደርስበት የማይችል ሚስጥራዊ ሂክማ አለው።

    በኢስላም ውስጥ አብዛሀኞቹ  በቁጥር የተገደቡ ኢባዳዎች የቁጥራቸውን ሚስጥር ጥራትና ልቅና የተገባው ጌታችን አላህ ሱወ ብቻ ነው የሚያውቀው።የዙህር ሶላት ለምን አራት ሆነ፣የመግሪብ  ሶላት ለምን ሶስት ሆነ፣ሱብሂ ለምን ሁለት ሆነ፣ ለምን 5ወይ6 ወይም አንዳንድ አልሆነም? ሁሉም ሶላቶች ለምን ተመሳሳይ ቁጥር አልኖራቸውም?እና የመሳሰሉት ጥያቄዎች ሊነሱ ይችላሉ።ነገር ግን የእነዚህን የተለያየ ቁጥር ያላቸውን የኢባዳ አይነቶች ሚስጥር የሚያውቃቸው አላህ ብቻ ነው።የሰውነት የአካል ክፍላችን ብዛት ብናስተነትን እና እያንዳንዱን የቁጥር መጠን ለምን ሆነ ብንል፣አይናችን ለምን 2 ሆነ፣ጆሮስ ለምን 2 ሆነ፣የእጅ ጣቶች ለምን 5 ሆኑ፣ለምን 4 ወይም 6 ዘልሆነም?? የሚለውን የብዛቱን ሚስጥር አዋቂው አላህ ብቻ ነው።

   ☞ ከአንድ በላይ ሚስት ያውም ደግሞ 4 የሚለው ቁጥር ለምን ተመረጠ ቢባል መልሱ ሁሉን አዋቂ የሆነው ጌታችን ብቻ የዚህ ሚስጥር ባለቤት ነቅ የሚል ምላሽ ይሆናል።

   ከአንድ በላይ ሚስት ማግባት የራሱ የሆነ ጥበብ መኖሩ እንዳለ ሆኖ ኡለሞች የሚዘረዝሯቸው አስደናቂ ጥበቦች አሉት እነዚህ ጥበቦች እንደሚከተለው አንድ ሁለት እያልን እንዘረዝራለን፣

1/
#የአላህ_መልእክተኛን_ሰአወ_ሱና_ለመከተል_ሲባል

   እንደሚታወቀው የአላህ መልእክተኛ ከዚህ አለም በሞት እስከተለዩ ድረስ ከአንድ በላይ ሚስቶች ነበራቸው።የአላህ መልእክተኛ ከአንዳንድ እሳቸው ብቻ ከሚለዩባቸው ተግባራቸው በስተቀር የእሳቸውን ፈለግ እንድንከተል ታዘናል።ይህንን አስመልክቶ አላህ በቁርአኑ እንዲህ ብሎናል፣

لَّقَدْ كَانَ لَكُمْ فِي رَسُولِ اللَّهِ أُسْوَةٌ حَسَنَةٌ لِّمَن كَانَ يَرْجُو اللَّهَ وَالْيَوْمَ الْآخِرَ وَذَكَرَ اللَّهَ كَثِيرًا

ለእናንተ አላህንና የመጨረሻውን ቀን የሚከጅል ለሆነ ሰው፣ አላህንም በብዙ ለሚያወሳ በአላህ መልዕክተኛ መልካም መከተል አልላችሁ፡፡
(ሱረቱ አል- አሕዛብ - 21)

    ☞የአላህ መልእክተኛ የደነገጉትን መቀበል እና ሃቅ ነው ብሎ ማመን የሙስሊሞች ግዴታ ነው።ከአንድ በላይ ሚስት በሸሪዓ የተፈቀደ እና የተወደደ ነው የሚለውን መቀበል በእያንዳንዱ ሙስሊም ላይ ግዴታ ነው።ከአንድ በላይ ሚስት ማግባት አያስፈልግም ብሎ የጠላ ወይም መሆን አልነበረበትም ብሎ የተቃወመ ከኢስላም እንደሚወጣ የኢስላም ሊቃውንት ይስማማሉ።

     ነብዩ ሰአወ ለዱኒያም  ለአኼራም ለኡመታቸው የተሻለውን ነገር ሳያመላክቱ መጥፎን ነገር ሳያሰረጠነቅቁ አላለፉም። መጥፎውን እና ደጉን የማስተማር ሀላፊነት አላህ አስቀምጦላቸዋል።ነብዩ ሰአወ በንግግራቸው፣በተግባራቸው እና አይተው በማፅደቅ ያስተምራሉ።ከአንድ በላይ ሚስት ማግባት የሚወደድ እና የተሻለ እንደሆነ በተግባራቸው አስተምረውናል።ለሰዎች ሚስጥሩ በግልፅ ያልተገለፀው ከአንድ በላይ ሆኖ መግባትም እንደዚሁ ለሴቶች ትልቅ ጥቅም እንዳለው ያስገነዝባል።ለዚህም በርካታ ምክንያቶች መጥቀስ ይችላሉ።ከእነዚህም ውስጥ ነብዩ ለህዝባቸው ሲያስተምሩ የተሻለውን ወይም የበለጠ ጥቅም የሚያስገኘውን ነው ካልን ለሴቶች ኡመቶቻቸው የሚጎዳ ወይም የበለጠ ጥቅም የማያስገኝ በፍፁም ሊደነግጉ ወይም ሊያመላክቱ አይችሉም።ሌላው እናታችን አኢሻ ረአ ከሁሉም ሴቶች እንደምትበልጥ ነብዩ መስክረዋል።እሷ ከነብዩ ሚስቶች ከዘጠኝ አንዷ ናት ስለዚህ ከአንድ በላይ ሚስት ሆና መግባት ደረጃን የሚቀንስ ከሆነ ከሴቶች ሁሉ የምትበልጠው እናታችን አኢሻ ረአ ለምን በእሷ ላይ ሌላ ተገባባት።በሌላ አነጋገር ከአንድ በላይ ሚስት ሆኖ ሴቶችን ክብር ይቀንሳል ወይም ሴቶችን ከጓደኞቻቸው የበታችነት እንዲሰማቸው ያደርጋል ብሎ ማሰብ አኢሻን ረአ የበታች ነበረች ብሎ እንደማሰብ ይቆጠራል።ይህ አስተሳስብ ደግሞ ከኢስላም ጋር ይጋጫል።

    ☞ ከአንድ በላይ ሚስት ማግባት ከአንድ በላይ ካላገባው ጋር ሲነፃፀር በደረጃ የተሻለ እንደሚሆን ነብዩ ሰአወ በሃዲሳቸው እንዲህ ሲሉ  ተናግረዋል፣

     
#ሰኢድ_ኢብኑ_ጁበይር_ረአ ባስተላለፉት ሀዲስ"አብደላህ ኢብኑ አባስ አግብተሃል?ሲል ጠየቀኝ እኔም አላገባሁም አልኩት፣አግባ ከዚች ኡማ የተሻለው ብዙ ሚስቶች ያሉት ነው"" አለኝ ይላሉ። ሀዲሱን ቡኻሪ ዘግበውታል።

2
#ሳያገቡ_እድሜያቸው_የገፉና_የሚፈቱ_ሴቶች_መኖርና_መበራከት

  እነዚህ ሁለት አይነት ሴቶች በተለያዩ ምክንያቶች ሊኖሩ ይችላሉ።እድሜያቸውን ከገፉ በኃላ ለመጀመሪያ ሚስት የሚፈልጋቸው ወንድ አናሳ ነው።ወይም ደግሞ እንደሚታወቀው ወንዶች ለማግባት መሰረታዊ የሚባል የቤት ወጪን የሚሸፍኑበት ገንዘብ ያስፈልጋቸዋል። ይህን ገንዘብ በልጅነት እድሜያቸው ካላገኙ እስቲሳካላቸው የተወሰነ ጊዜ መጠበቃቸው አይቀሬ ነው።በዚህም የተነሳማግባት ከነበረባቸው እድሜያቸው ከገፉ በኃላ ይሆናል። የእነሱ አለማግባት በእኩያታቸው ያሉ ሴቶች ቶሎ ላያገቡ ይችላሉ።እነዚህ በእድሜያቸው ብዙ ከሄደ በኃላ ሚስት ሊያገቡ የሚያስቡ ወንዶች በእድሜ ከእነሱ ጋር እኩል የሆኑ ሴቶች ሳይሆን ለጋ የሆነችውን ሴት ይመርጣሉ። በዚህም ምክንያት እነዚህን ሴቶች ለመጀመሪያ ሚስትነት የሚፈልጋቸው ወንድ አናሳ ይሆናል ማለት ነው። ያለባል እንዳይቀሩ መፍትሄ ይሆን ዘንድ ከአንድ በላይ መፈቀዱ ኢስላማዊ ጥበብ ነው። በተመሳሳይ የተፈታችንም ሴት ለመጀመሪያ ሚስትነት የሚፈልጓት ወንዶች እጅግ አናሳ ናቸው።ለዚህም መፍትሄው ያለባል ከመቅረት ሁለተኛ ማግባት ነው
  
#ከአንድ_በላይ_ሚስት_የመፈቀዱ_ጥበብ
            3_4_&_5

👇በቀጣይ ርዕሳችን ይቀጥላል ሺንሻአላህ
#ሼር_ያድርጉ

            ቴሌግራማችን

╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
╭┈─────── ೄྀ࿐ ˊˎ-
╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የመልካም ጓደኛና የመጥፎ ጓደኛ  ቱርፋቶች ❗️
መልካም ጓደኛ ወደ መልካም ሲመራህ  መጥፎ ጓደኛ ደግሞ ልክ እንደ እርሱ መጥፎ  ያደርግሃል ። ከመጥፎ ጓደኛህ ጋር ጊዜህን የምታባክን ከሆነ አንተም የእርሱን ስራ ትከተላለህ መልካም የሆነውን ስራ ሁሉ ትረሳለህ ።
ሳታስበውም ሞት ይመጣና ይወስድሃል።
يا ويلتى ليتني لم أتخذ فلانا خليلا
[ ሱረቱ አል-ፉርቃን፣ - 28 ]
«ዋ ጥፋቴ! እገሌን ወዳጅ ባልያዝኩ ኖሮ እመኛለሁ፡፡

لقد أضلني عن الذكر بعد إذ جاءني وكان الشيطان للإنسان خذولا
[ ሱረቱ አል-ፉርቃን፣ - 29 ]

(የእምነት ቃልን) ከመጣልኝ በኋላ ከማስታወስ በእርግጥ አሳሳተኝ» (ይላል)፡፡ ሰይጣንም ለሰው አጋላጭ ነው፡፡

መልካም ጓደኛ ከነፍሳችን ይበልጣል
ኢማም ኢብኑል ቀይም እዳስተላለፉት :-
መልካም ወዳጅ ለአንተ ከነፍስህ የበለጠ ይጠቅምሃል ። ምክንያቱም ነፍስ በመጥፎ  ስታዝ መልካም ወዳጅ ግን በመልካም እንጂ በመጥፎ አያዝህም""!

ያረቢ መልካሞቹን ጓደኞች  አንተ ወፍቀን ።ከሰይጣን ክፋት አንተ ጠብቀን ።   አስሐቡል የሚን የተከበሩ  የቀኝ ጓዶች ብለህ ከምትጠራቸው ባሪያዎችህ አድርገን  ያኢላሂ ።   በመንገድህም ላይ አፅናን አሟሟታችን አሳምርልን አሚን።🤲

            ቴሌግራማችን

╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
╭┈─────── ೄྀ࿐ ˊˎ-
╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
☞«የሴት ልጅ ነፃነት የሚረጋገጠው ጌታዋን ስትታዘዝ ነው። ልጆቿን በጥሩ ተርቢያ ኮትኩታ ስታሳድግ፣ እንደአቅሟ አላህ የጣለባትን በቤቷ ውስጥ የጣለባትን ሀላፊነት ስትወጣ ነው። ሴት ልጅ ለባሏ ቤት ጠባቂ ስትሆን ስለ አጠባበቋም ተጠያቂ ናት።
     📚 ሸይኽ ሳሊህ አልፈውዛን

            ቴሌግራማችን

╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
╭┈─────── ೄྀ࿐ ˊˎ-
╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
🔰 ባሮችህ ረገፉ

በፈለስጢን ምድር - በአላህ ቤት
በመስጂደል አቅሳ - ነብዩ ባረፉበት
በካኃዲዋ እስራኤል - ረገፉ ህፃናት
ቦምብ ዘነበባቸው - እንቅልፋቸውን በተኙበት
ዓለምም ችላ አለው - ይህን የዘር ማጥፋት

ያረቢ የአላህ - ሰማዩ ሰማይህ
ያራህማን ያራሂም - ምድሩም ምድርህ
ድረስላቸው ጌታችን - ጀባሩ ያአላህ
ሙስሊም የሆኑ - ኢባዱ ራህማን ናቸው
ሰው ናቸውና ያራሂም - ካጠፉም ማራቸው
መንገድ ስተው እንደሆን - መንገድ አሳያቸው
ሙስሊሞቹም ያንተ - ህፃኖች ያንተው
ካንተ ውጭ ሌላ መጠጊያም ዬላቸው!

አዎ ወጀለኞች ነን - ነብሳችንን በዳይ
ድንበር አላፊዎች ነን - በሰጧን አታላይ
ለብልጭልጭ ህይወት - በርከክ ባይ
ለዚህች ለቀን ጤዛ - ደሞም ለዱንያ
ላትሆነን መንገድ - ጀነትን መዝለቂያ
እያጠለቀችልን - የአዛብ ሜዳሊያ

ግን አንገሰፅም - ከዚህ ሁሉም ነገር
በኛ ወንጀል የተነሳ - ሙስሊሙ ሲሸበር
ጠላት ተጠራርተው - ሁሉም ባአንድ ሲያብር
እኛ ስንባላ - በጎሳ በብሄር
እኛ ስንከፋፋል - በቋንቋ በዘር
አስክሬኖች በርክተው - አፈር ሲለብስ በዶዘር

እኛ ቆይ የት ገባን - ቆይ የትስ አለቅን!?
ቆይ ምን ዋጠን - ምንስ ላይ ሰመጥን!?
ሙስሊም ረገፈ እኮ - እኛ በቁም እያለን
ጂሃዱስ አይሳካ  - ያአላህ ማለት አቃተን!
የሙስሊም መሣሪያው - ዱዓ ነው እየተባልን፤
ያራህማን ያራሂም - እኛስ ቀሽሞች ነን፤
ሙስሊሞች ነንና - እባክህን ማረን
አዛኝ ነህና - ያአላህ እዘንልን
ውስጣችን ቆሰለ - ደም ዘነበ ከዓይን
ወንድሞቻችን አለቁ - በከሃዲዎች ረገፉብን
እነዛ የሰው አውሬዎች - ያንተን ቤት ደፈሩብን።

ያረቢ የአላህ - ሰማዩ ሰማይህ
ያራህማን ያራሂም - ምድሩም ምድርህ
ያአላህ ያ! ራህማን - ቤቱም ቤትህ
ድረስላቸው ጌታችን - ጀባሩ ያአላህ
ከጭንቅ ጠብቃቸው - ከጭንቅ አውጪ ነህ

ብዙዎች ቆሰሉ - ብዙዎች አለፉ
በህይወት እያሉ - ባሮችህ ደም ተፉ
በዘረጋሃው ምድርህ - ሙስሊሞች ተገፉ
እነዛ አውሬዎች - ሬሳን አሰለፉ
ሴትም አልቀራቸው - ህፃንም ቀጠፉ
ገደልን እያሉ - በደስታም ደነፉ
⭕️ በባረከው ምድርህ  - ባሮችህ ረገፉ
በረሻድ ኢብኑ ሙዘሚል
ቀን: ጥቅምት 20/2016 E.C Oct 31/2023 G.C

ግጥም ለማቅረብ 👇👇
ሀያት ቢንት ኸዲር 👈ለይ ይላኩልን