الزواج في الإسلام /ትዳር በኢስላም
22.4K subscribers
391 photos
19 videos
8 files
925 links
﴿وَمِنْ آيَاتِهِ أَنْ خَلَقَ لَكُم مِّنْ أَنفُسِكُمْ أَزْوَاجًا لِّتَسْكُنُوا إِلَيْهَا وَجَعَلَ بَيْنَكُم مَّوَدَّةً وَرَحْمَةً﴾

ለማንኛዉም አስተያየት☞☞ @Tidarbaislam_bot
ለይ ያድርሱን

ለጥያቄ ☞☞ t.me/Hayatbintkedir
Download Telegram
الزواج في الإسلام /ትዳር በኢስላም
بسم الله الرحمن الرحيم! ☞:::::እህቴ::::::☜ ክፍል አንድ/ ① ያቺን የዱንያ ህይወት ላይ ፈጣ የቀረችን ዐይንን ላናግራት.. አንቺ ዐይን ሆይ! ጀነትን አስታዉሺ! ያቺን ዱንያን ያፈቀረችን፣ ሀሳቧም ግቧም ዱንያ ብቻ የሆነችን ልብ ላናግራት.. አንቺ ልብ ሆይ! ጀነትን አስታዉሺ! ያቺን ዱንያ ላይ መንጠልጠል ያቃጠላትን፣ ደስታዋም ሀዘኗም ከዱንያ ጋር የተያያዘዋን ነፍስን ላናግራት..…
☞:::::::እህቴ::::::::☜

ክፍል ሁለት/ ②

ፊርዖዎን ያቺን ከስሮቿ ወንዞች የሚፈሱባትን፣ ያቺን በቅንጡ ፎቆች የተጌጠችን ዉብን ሀገር ስለሚመራ ይፎክር ነበር። «ታላቁ ጌታችሁ ነኝ!» እያለም ምድር ላይ ጥፋትና ብክለትን ያንሰራፋል።

ነገር ግን ያቺ አማኟ የሙስሊም ሴቶች ምርጥ ሞዴል የነበረችዉ ሚስቱ አሲያ አንዲት የጀነት ቤት እሱ የሚገዛዉን ጨምሮ ዓለም ላይ ካለ ከትኛዉም ሀብት እንደሚበልጥ ዓለምን አስተማረች።

ከሁሉም ግርም የሚለኝ የሳሂሮቹ ጉድ ነዉ። የአላህን ብርሀን ለማጥፋትና በምትኩ ደግሞ ከፊርዖን ዘንድ ምንዳንና ቀረቤታን ፈልገዉ ተደራጅተዉ መጡ። ግን ወዲያዉ አላህ ብርሀኑን ለገሳቸዉና የኢማን ጥፍጥና ወደ ልባቸዉ ዘለቀ። ወዲያዉ እንደአምላክ አጎንብሰዉ ሲያናግሩት የነበረዉን ፊርዖንን አንገታቸዉን ቀና አድርገዉ በሙሳና በሃሩን ጌታ እንደሚያምኑ ነገሩት።

አየሽ! የኢማን በሻሻ ልብን ሲቆጣጠር ዱንያ ላይ ያለዉ የትኛዉም ሀብትና ዝና ተራ እንደሆነ ይገባናል። ዱንያ ላይ ያለ የትኛዉም አካል ዱንያን እንጂ ሌላ ፍርድ እንደሌለዉ እንረዳለን። ከሳሂሮቹ ታሪክን ይሄን ነዉ ምንማረዉ።

ፊርዖን ይመለሱ እንደሆነ ብሎ እጃቸዉን ቆረጠ! ቅጣታቸዉን ሊጨምር እግራቸዉንም ቆረጠ! የተምር ግንድ ላይ ሰቀላቸዉ! «የትኛችን ቅጣቱ አሳማሚና ቀሪ እንደሆነ ትረዳላችሁ!» አላቸዉ። ኢማን ልብ ሲገባ ተዓምር ይሰራልና ፍንክች አላሉም። «ፍረድ! አንተ ምትፈርደዉ ቅርቢቷን ዓለም ብቻ ነዉ!» አሉት።

አጀብ! ጥዋት ኮ ጠንቋዮች ነበሩ! ማታ ግን ሸሂድ ሆነዉ ጌታቸዉን.. የሙሳንና የሃሩንን ጌታ ተገናኙ።

አላሁ አክበር!!

አላህ ነገ ለአማኞች ያዘጋጀዉን ጀነትን በመሻት ዓለም ላይ ያላቸዉን ነገር በሙሉ ሰጡ! ዝናቸዉን፣ ሀብታቸዉን፣ ጊዜያዊ ደስታቸዉን.. ሀታ ነፍሳቸዉን ሳይቀር ሰዉ!! በምትኩም የሰማይና የምድርን ያህል ስፋት ያላትን ጀነትን ወረሱ።

እህቴ! ነፍሴንም አንቺንም በአንድ ነገር ብቻ ነዉ አደራ የምለዉ! ሌላዉ ቢቀር ለዛች ዘላለማዊ ደስታ ስንል ሀራምን እንጠንቀቅ! ዋጂባትን እንፈፅም!

አምስት ወቅትሽን ስገጂ! ወርሽን ፁሚ! የቤተሰብሽን ትዕዛዝ ‛መርሀባ’ በዪ! ነፍስሽን ከሀራም ጠብቂ! ምላስሽን ከወንጀል ቆጥቢ! ወደ መጥፎ ምታዘዋን ነፍስሽን ታገዪ! ሙዚቃን ራቂ! ከወንድ ጋር የሀራም ግንኙነትን አትቅረቢ!

ሁሌም አንድን ነገር ከመስራትሽ በፊት «አላህ ይሄን ነገር ይወደዋል?!» ብለሽ ራስሽን ጠይቂ! ከወደደዉ ተጣደፊበት! ካልወደደዉ ራቂዉ!

ኢንሻ አላህ! እዛኔ የዱንያም የአኼራንም ጀነትን ትወርሺያለሽ!

[[እህቴ! ክስረት ማለት ምን እንደሆነ ታዉቂያለሽ?!

ክስረት ማለት ጀነት የሰማይና የምድርን ያህል ስፋት ኑሯት አንቺ ከዚያ ቦታ ከሌለሽ ነዉ።]]
#ይቀጥላል_ኢንሻአላህ
ቴሌግራማችን

╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam🌸🍃
╭┈─────── ೄྀ࿐ ˊˎ-
╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam🌸🍃
Audio
《الوساءل المفيدة للحياة السعيدة》
የደስታን ህይወት ማስገኛ መንገድ በሚል ርዕስ

👆👂👂👈

🎤 በኡስታዝ ሑሴን ዒሳ
【حفظه الله تعالى】
ቴሌግራማችን

╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam🌸🍃
╭┈─────── ೄྀ࿐ ˊˎ-
╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam🌸🍃
☞☞ምኞትህን የሰው ልጅ ውዴታን
ለማግኘት አታድርግ‥❗️❗️
❗️ የሰው ልጅ ልብ ተገለባባጭ ናት
ዛሬ ወዶህ ነገ ይጠላሃል።
⇨ምኞትህን አላህ በወደደኝ ብለህ
ተመኝና ፈልግ ‥
እሱ ከወደደህ ሁሉም ነገር ይወድሃል
አላህ ከሚዎዳቸዉ ያድረገን አሚን።


ቴሌግራማችን

╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
╭┈─────── ೄྀ࿐ ˊˎ-
╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
#THEY ASKED HER : "WHY DON'T YOU HAVE A BOYFRIEND? "Listen

She replied with confidence and eyes full of love for her Creator:"in my religion it is haram to have a boyfriend and I prefer to die then to anger my creator and disobey him the one who provide for me and love me and gave me life! I would never enter a cursed relation and date the futur husband of another woman while my lord already wrote for me 50000 years ago before I existed if I would get married or not and to whom I would get married so why gain useless sins?!"

They said:"but how will you find a husband if you don't date?"
*
She smiled and replied:"the one meant for me will find me even if I'm hidden inside a mountain..that is called:destiny! And I trust my creator!"

They said :"time has changed so be modern!"

She replied :"but the words of my creator didn't!..they remained the same and I say to him:"I heard and I obey!"

They said:"but everyone is doing it!"

She replied:"should I stop praying if everyone stop praying? Haram remain haram even if the whole world do it! And my Allah said:"if you follow most of people on earth they would turn you away from the truth and lead you astray!"

She added:"I would never shame my father or my brother who are proud of my purity and piety I was raised by a good woman who taught me that I was the futur wife of a pious man how could I cheat on my futur husband?how would I cheat on the man who will make me his and make me take his name and cherish my beauty? My beauty is only for him and I am worth more than being a girlfriend and let a man who is nothing for me have me that easy and touch me that easy as if I was a cheap stone found everywhere!no! I am a pearl in it's shell reserved only for my husband and I will wait for him until Allah send him to me!
@Tidar_Be_Islam
@Tidar_Be_Islam
الزواج في الإسلام /ትዳር በኢስላም
☞:::::::እህቴ::::::::☜ ክፍል ሁለት/ ② ፊርዖዎን ያቺን ከስሮቿ ወንዞች የሚፈሱባትን፣ ያቺን በቅንጡ ፎቆች የተጌጠችን ዉብን ሀገር ስለሚመራ ይፎክር ነበር። «ታላቁ ጌታችሁ ነኝ!» እያለም ምድር ላይ ጥፋትና ብክለትን ያንሰራፋል። ነገር ግን ያቺ አማኟ የሙስሊም ሴቶች ምርጥ ሞዴል የነበረችዉ ሚስቱ አሲያ አንዲት የጀነት ቤት እሱ የሚገዛዉን ጨምሮ ዓለም ላይ ካለ ከትኛዉም ሀብት እንደሚበልጥ…
☞::::::እህቴ::::::☜

ክፍል ሶስት/ ③

..ከዕለታት በአንዱ ቀን አንዲት እህትሽ ወደ ተወዳጁ ነብይ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) በመምጣት.. «አዉድቅ አለብኝ፣ (አዉድቁ በሚጥለኝ ወቅት ደግሞ) ሰዉነቴ ይገለጣል። ዱዓ አድርጉልኝ!» አለች። ያ የነፍስና የልብ ሀኪም የሆኑት ተወዳጁ ነብይም ሁለት ምርጫ ሰጧት፣ አንድም ዱዓ አድርገዉላት መዳን፣ አልያም ታግሳ ጀነትን ማግኘት። አማኞች ዘንድ ከጀነት በላይ ዉድ ነገር አልነበረምና መታገስን መረጠች።

አየሽ! ሙዕሚን ሰዉ ለጀነት ሲል ሁሉንም ይሰጣል። ሙሲባ የተደራረበባቸዉ ሳይቀር የጀነትን ስም ሲሰሙ ሙሲባቸዉን ይረሱታል። ታግሰዉ አላህ ዘንድ ያለዉን ምንዳን ይከጅላሉ።

የሀሪሳን እናት እንመልከታት እስቲ! ልጇን ሀሪሳን በጣም ትወደዋለች። ሀሪሳ በበድር ወቅት ሸሂድ ሆኖ ይቺን ከንቱ ዓለም ተሰናበት። እሷም ወደ ፍጥረቱ ዐይነታ በመሄድ.. «አንቱ የአላህ መልዕክተኛ! (መቼስ) ሀሪሳ ልቤ ዉስጥ ያለዉን ቦታ ታዉቃላችሁ። (እስቲ ስለሱ ንገሩኝ!) ጀነት ዉስጥ ከሆነ እታገሳለሁ፣ አላለቅስም። ካልሆነ ግን በሱ ላይ ማልቀስን እጠናከርበታለሁ።» አለችዉ።

ረሱሉም.. «የሀሪሳ እናት ሆይ! ሞኝ ሆንሽ እንዴ?! (በሽታ አገኘሽ?) እሷ ኮ አንዲት ጀነት አይደለችም። እሷ ጀነቶች ናት። እሱ ደግሞ ላይኛዋ ፊርዶስ ዉስጥ ነዉ።» አሏት።

እህቴ! እዚህ ዓለም ላይ ለአንዲት እናት ልጅን ከማጣት በላይ ትልቅ ህመም የለም። ነገር ግን ያ የሷ ልጅ ወደ አላህ ጉርብትና መሄዱን ያወቀች እንደሆነ ህመሟ እንዳልነበረ ይሆናል። ለምን እንደሆነ ታዉቂያለሽ?!

ምክንያቱም እሱ ፀጋ ዉስጥ ነዉ። እሱ ሀሴት ዉስጥ ነዉ። ከንግዲህ ሀዘንም ጭንቀትም አያገኘዉም። ሀዘንና ሀሳብ ምድር ላይ ላሉ ሰዎች ብቻ ነዉ። የጀነት ሰዎች ሁሌም ደስታ፣ ሁሌም ፌሽታ፣ ሁሌም ራሃ ዉስጥ ናቸዉ።

አላህ ያለ ሂሳብና ያለ ቅጣት ጀነትን ከሚወርሱት ያድርገን!!

ሙሲባችን ሚገራዉና ሀዘናችን ሚጠፋዉ አላህ ላይ ያለን የቂን ሙሉ ሲሆን ነዉ። ልባችንን የኢማን በሻሻ ሲወርሰዉ ነዉ።

ኢማን ልብሽ ዉስጥ ሲገባ ጀነት ዘላለማዊ ደስታ እንደሆነችና ለሷ ነፍስሽን፣ ሀብትሽን፣ ሁልሽን መስጠት እንዳለብሽ ይገባሻል።

ኢማን ልብን ሲቆጣጠር የሀራም ስሜት አንቺን አይገዛሽም፣ ነፍስሽ እንደፈለጋት አታዝሽም፣ ነፍስሽ ላይ ንግስት ሁነሽ ሁሉንም እንደልብሽ ታዢያለሽ። የነፍስሽ ፈቃጅም ከልካይም አንቺ ብቻ ትሆኛለሽ! እዛኔ በልብሽ ዐይን ጀነትን ታዪለሽ!

እዛኔ.. አቤት ደስታሽ!!

ነገር ግን.. ለጊዜያዊ ደስታሽ ባሪያ ሁነሽ፣ ሰላትን በጊዜ መስገድን ተሳንፈሽ፣ ሙዚቃን ማዳመጥ አጠናክረሽ.. በአላህ እስቲ በምን ስራሽ ነዉ ጀነትን የተመኘሺዉ?! አላህ አዛኝ ነዉ አዉቃለሁ! ግን ቢያንስ ሰበብ አያስፈልግም?!

አላህ ምስክሬ ነዉ!
የአላህ ፍቅርና የሀራም ፍቅር በአንድ ልብ ዉስጥ አይሰባሰብም.. አንዱ ሌላዉን ገፍትሮ ሚያወጣዉ ቢሆን እንጂ! ወይ ኢማንሽን አድሺና በልብሽ ጀነትሽን ተመልከቺ.. አልያም የሼይጣን መጫወቻ ትሆኚያለሽ!

[[እህቴ! የአላህ ዕቃ ዉድ ነዉ። የአላህ ዕቃ ለዉዶች ነዉ የተዘጋጀዉ። የአላህ እቃ ነፍሳቸዉን ድል አድርገዉ፣ ከሀራም ነፍሳቸዉን ጠብቀዉ፣ ግዴታ የተደረገባቸዉን በአግባቡ ለሚወጡት ነዉ የተዘጋጀዉ።
:
የአላህ ዕቃ ጀነት ነዉ።]]
#ይቀጥላል_ኢንሻአላህ

           ቴሌግራማችን

╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
╭┈─────── ೄྀ࿐ ˊˎ-
╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
👆👂👂👈 አጠር ያለች መልዕክት ነዉ አዳምጡት

ቴሌግራማችን

╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam🌸🍃
╭┈─────── ೄྀ࿐ ˊˎ-
╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam🌸🍃
አቡ ሁረይራህ (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንዳስተላለፈው፡- የአላህ መልእክተኛ (ሶለላሁ ​​ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ፡- አንድ ሰው #ሚስቱን_ወደ አልጋው ቢጠራት እሷም እምቢ ብትል፣ እሱም ቢያሳልፍ።
በእርሷ የተናደዱ ሌሊት መላአክቶች እስከ ማለዳ ድረስ ይረግሟታል፣ ተስማሙ። ባለቤቷ ወደ ፍላጎቱ ቢጠራት ማዳመጥ እና መታዘዝ የሴቲቱ ግዴታ ነው, ከትክክለኛ ሰበብ በስተቀር.ስለዚህ
#እህቴ_የባልሽን ትዕዛዝ አክባሪ ሁኚ ። ነገ ለአኼራሽም ይጠቀምሽ ዘንድ

        ቴሌግራማችን

╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
╭┈─────── ೄྀ࿐ ˊˎ-
╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
الزواج في الإسلام /ትዳር በኢስላም
☞::::::እህቴ::::::☜ ክፍል ሶስት/ ③ ..ከዕለታት በአንዱ ቀን አንዲት እህትሽ ወደ ተወዳጁ ነብይ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) በመምጣት.. «አዉድቅ አለብኝ፣ (አዉድቁ በሚጥለኝ ወቅት ደግሞ) ሰዉነቴ ይገለጣል። ዱዓ አድርጉልኝ!» አለች። ያ የነፍስና የልብ ሀኪም የሆኑት ተወዳጁ ነብይም ሁለት ምርጫ ሰጧት፣ አንድም ዱዓ አድርገዉላት መዳን፣ አልያም ታግሳ ጀነትን ማግኘት። አማኞች ዘንድ ከጀነት በላይ…
☞::::::እህቴ!::::::::☜

ክፍል አራት/④

ይህ ታሪክ ትዝ ባለኝ ቁጥር ሰዉነቴን ከእግሬ እስከ ፀጉሬ ይነዝረኛል። ገና ሳልፅፈዉ ዐይኔን በእንባ ይሞላዋል። ወላሂ ደስታ ይሁን ሀዘን እንጃ አላዉቀዉም.. ግን ልቤን ድብልቅልቅ ያለ ስሜት ይወርሰዋል።

ዛሬ የማወራዉ ስለዚያች.. በረሱል ምስክርነት የሷ ተዉባ ለሰባ ሰዎች ቢከፋፈል ይበቃ ነበር ስለተባለላት ሴት ነዉ።

ያ አላህ!! ያ ረሱላችን ምስክር በሰጡት በኢማኗ ታላቅነት ልገረም?! ወይስ ያለ አንዳች ግፊት የሰራችዉን በግልፅ ተናግራ ሀድ እንዲቆምባት ረሱሉን በጠየቀቺዉ እዉነተኝነቷ ልገረም?!

ይህ ወሬ በማሰማመር ምናልፈዉና ዝምብለን እንባ ተራጭተን ምናወራዉ ተራ ወሬ አይደለም። ይህ የአላህን ዒቃብ ለሚፈሩት ይገሰፁ ዘንድ የተፃፈ ታሪክ ነዉና ጥሞና ይፈልጋል። እዚች ሴት ላይ ከየትኛዉ ጊዜ በላይ ሙሉ የሆነን ትኩረትን እፈልጋለሁ።

እቺ ታላቅ ሴት አንድ ቀን ወደ ረሱሉ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) በመምጣት.. «አንቱ የአላህ መልዕክተኛ! ዝሙት ሰርቻለሁ አጥሩኝ!» አለች። ረሱሉም መለሷት። በነገታዉም መጣችና «ለምንድን ነዉ ምትመልሱኝ?! ምናልባትም ማዒዝን እንደመለሳችሁት ልትመልሱኝ ፈልጋችሁ ይሆናል። ወላሂ እኔ እርጉዝ ነኝ!» አለች። «(እንደዚያ ከሆነ) ስትወልጂ ተመልሰሽ ነይ!» አሏት። በወለደችም ጊዜ ልጁን ይዛዉ መጣችና «ይሄ እሱ ነዉ! ወልጃለሁ!» አለቻቸዉ። ረሱሉም «ይዘሺዉ ሂጂና (ጡት እስኪጥል) አጥቢዉ!» አሏት። አጥባታዉ በጨረሰች ጊዜ በእጁ ዳቦ አስይዛዉ መጣችና «ይሀዉ የአላህ ነብይ! (ጡት ጥሏል!) እንደምታዩትም ምግብ ጀምሯል።» አለቻቸዉ።

ረሱሉም (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ለአንዱ ሰሀባ ልጁን ሰጡና ጉድጓድ ቆፍረዉ አዘጋጇት። ‛ረጅም’ እንድትደረግ አዘዙ። ኻሊድም መጣና (በትልቅ) ድንጋይ ራሷን ፈነከታት። ደም በደም አደረጋት። ደሟ ኻሊድን ሳይቀር አለበሰዉ። ኻሊድ ሰደባት። ረሱላችንም ኻሊድ መሳደቡን በሰሙ ጊዜ እንዲህ አሉት.. «ኻሊድ ሆይ ተረጋጋ! ያ ነፍሴ በእጁ ባለችዉ ጌታ ይሁንብኝ! እሷ ኮ (ያ ቀረጥ ሚቀበለዉ) ሰዉ ቢቶብት እንኳን አላህ ይቅር የሚለዉን ተዉባ ነዉ የቶበተችዉ።»

በሌላ ዘገባ ሊሰግዱባት ሲዘጋጁ ዑመር ዝሙት ሰርታ ሳለ እንዴት ትሰግድባታለህ?! ሲሏቸዉ እንዲህ አሉት.. «በእርግጥም እቺ ሴት ለ70 የመዲና ሰዎች ተዉባዋ ቢከፋፈል የሚበቃን ተዉባ ነዉ የቶበተችዉ። አንዲትን ነፍሷን ለአላህ ከሰጠች ሴት በላይ ትልቅ ደረጃ ያለዉን ሰዉ አግኝተሃልን?!»

ሱብሀነላህ!
እቺ ሴት ኮ ከአላህ ዉጪ ማንም ባላያት ሁኔታ ላይ ሁና ነዉ ሸይጣን ወስዉሷት ለዝሙት የተዳረገችዉ። ወደ አላህ አልቅሳ፣ ተመልሳ ብትለምነዉና ትክክለኛ ተዉባን ወደሱ ብትመለስ ይበቃት ነበር። ግን የኢማን ለዛ ልብን ሲቆጣጠር እንዲህ ነዉ። በሌሎች ሰዎች ዘንድ ተራ ሚመስለዉ ወንጀል ኢማን ልባቸዉን ለተቆጣጠረ ሰዎች ቀንና ማታ ሀዘንና ቁጭትን ሚያወርስ ነዉ።

አይገርምም! ሲመልሷት እንኳን ተመልሳ ትመጣለች ኮ! እስክትወልድ ብዙ ወራት ነበራት። ከወለደች ብኃላ ጡት እስኪጥል ሁለት አመት ገደማ ያቆያል። ግን በዚህ ሁላ መሃል አንድም ቀን የአላህ ሀድ እንዳይቆምባት ወደኃላ ማለትን አልመረጠችም። በወደቀ ማንነት ጌታዋን መገናኘትን አልፈለገችም።

እቺ ሴት ወደ አላህ ቁርጥን የሆነን መመለስን ለሚሹት ምርጥ ምሳሌ ናት። እርግዝናዋ፣ ዉልደቷ፣ ማጥባቷ አንድኛቸዉም ከተዉባ አላገዷትም። የልጇ ዉብ ዐይኖች እሷ እንደዚያ ስትቀጠቀጥ በእንባ መሞላቱ ከተዉባ አላገዳትም። ልጇን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ተሰናብታ በጠራ ልብ አምላኳን ተገናኘች።

በአላህ ዉዴታ ተፅናንታ የዚያን የድንጋዩን ህመም ተቋቋመች። ወንጀሏን እንዲያፀዳላት በመሻት ልብሷኗ መላዉ ሰዉነቷ ደም እስኪለብስ ፀናች።

ይህ ሁላ ለአላህ ዉዴታ የተከፈለ ዋጋ ነዉ።
:
ይህ ሁላ
#ለጀነት የተከፈለ ዋጋ ነዉ።

እህቴ! ልክ እንደዚች እህትሽ ቁርጠኛ ሁኚ! በተራ ነፍስ አላህን መገናኘትን አትሺ! ከሱ ብኋላ መንሸራተት የሌለዉን ትክክለኛ መመለስን መደ አላህ ተመለሺ!!

[[አንዲት ነፍሷን ለጌታዋ ከሰጠች (ነፍስ) በላይ አላህ ዝንድ ትልቅ ደረጃ ያለዉን ሰዉ ታገኛላችሁ?!]]
#ይቀጥላል_ኢንሻአላህ

     ቴሌግራማችን

╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
╭┈─────── ೄྀ࿐ ˊˎ-
╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
Audio
❗️የወንዶች መገላለጥ

☞የወንዶች መገላለጥ

❗️ቅጥ ያጣው የወንዶች አለባበስ ተዳሶበታል።

🎤አቡ አብዲላህ ኢብኑ ኸይሩ

         ቴሌግራማችን

╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
╭┈─────── ೄྀ࿐ ˊˎ-
╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
°•° እኛ መልካም ሰው ከሆንን የሚያጣን እንጂ የምናጣው አይኖርም መልካም  ሰው ማለት  በውበት  ሳይሆን በመልካም አስተሳሰብና በተግባሩ  ውብ የሆነ  ነዉ።!!  አላህ ሆይ አስተሳሰባችንን ከአንተ ጋር የተወደደ አድርግልን!!_
•°ባለንበት ጊዜ መማር ማወቅ  ሌላ  መተግበር ሌላ  ሆኗል  አሏሁመ እስተአና!!  እውቀት ያለው ሁሉ ፍፁም ሰው እየመሰለን   እውቀት ወደለው እንሮጣለን ነገር ግን  አላህ ያዘነለት ሲቀር      ብዙዎቻችን ከተግባር ዜሮነን ግን ለምን?????? ❗️ለዱኒያ ብለን ወላ አኼራን ናፍቀን ያአላህ ባሮች እስኪ እናስተንትን   !!  አላህ ይዘንልንና!!  አሚን

       ቴሌግራማችን

╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
╭┈─────── ೄྀ࿐ ˊˎ-
╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
الزواج في الإسلام /ትዳር በኢስላም
☞::::::እህቴ!::::::::☜ ክፍል አራት/④ ይህ ታሪክ ትዝ ባለኝ ቁጥር ሰዉነቴን ከእግሬ እስከ ፀጉሬ ይነዝረኛል። ገና ሳልፅፈዉ ዐይኔን በእንባ ይሞላዋል። ወላሂ ደስታ ይሁን ሀዘን እንጃ አላዉቀዉም.. ግን ልቤን ድብልቅልቅ ያለ ስሜት ይወርሰዋል። ዛሬ የማወራዉ ስለዚያች.. በረሱል ምስክርነት የሷ ተዉባ ለሰባ ሰዎች ቢከፋፈል ይበቃ ነበር ስለተባለላት ሴት ነዉ። ያ አላህ!! ያ ረሱላችን ምስክር…
☞::::::እህቴ::::::::☜

ክፍል አምስት/ ⑤

..አንዱን ዓሊም
«እስቲ ስለጀነት ፀጋዎች ንገረንና ጀነትን አስናፍቀን!» አሉት።

እሱም በአንዲት ዐ.ነገር ብቻ ልብን ጀነት ላይ እንድትንጠለል ምታደርግን ንግግር ተናገር። መልካም ስራ መስራት ላደከማቸዉ አሪፍ ብርታት ሚሆንን ንግግር ተናገረ።

«በዉስጧ ረሱሉ አሉ።» አላቸዉ።

አለቀ።
አንድ በልቡ ዉስጥ የረሱሉ ሙሃባ ላለበት ሰዉ በቂ ማነቃቂያ ነዉ።

ምናልባትም «ደክሞኛል፣ ብርታቴ ዝሏል፣ ነፍሲያዬን ቀጥ ማድረግ ከብዶኛል።» ትዪ ይሆናል። የዚህ ታላቅ ዓሊም ንግግር ብርታት ይሆንሻልና ልብሽ ዉስጥ ጥሩ ቦታ አስቀምጪዉ።

እህቴ! ከወንጀል መታቀብ ሲከብድሽም በዚህ ንግግር ዊስዋስን ከላይሽ ላይ ግፈፊ! ዒባዳ መስራት ሲከብድሽም በዚህ ንግግር ተበራቺ!

ጀነት ዉስጥ ረሱሉ አሉ። መርየም፣ አሲያ፣ ኸዲጃ፣ አዒሻ፣ ፋጡማ፣ ማሺጣ.. ሁላቸዉም አሉ። በነሱ ሙሀባ ተጠናከሪ!

ጀነት ዉስጥ ዱንያ ላይ እንደነሱ ለመሆን ምትደክሚላቸዉ መልካም ስብዕናዎች በሙሉ አሉ።

ጀነት ዉስጥ የፀጋዎች ቁንጮ የሆነዉ ታላቁ ኒዕማም አለ። ጀነት ዉስጥ ጀነት ከመግባት በላይ ትልቁ ኒዕማ የዚያን የአላህን ዉብ ፊት ማየት ነዉ። አላህ የሱን ዉብ ፊት ማየትን ይወፍቀን!!

አንቺ የአላህ ባሪያ የሆንሺዉ እህቴ! በአላህና በረሱሉ ፍቅር አአሳስሮ ያስቀመጠሽን የድካም ሰንሰለትን በጣጥሺዉ! አላህ ፅናቱን ይወፍቅሽ!

[[ሲደክምሽ፣ ብርታት ሊሆንሽ ይችላልና ይሄን ፅሁፌን በፈለግሺዉ ሰዓት ልታገኚዉ ምትችዪበት ቦታ አስቀምጪዉ!]]
#ይቀጥላል_ኢንሻአላህ

ቴሌግራማችን

╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
╭┈─────── ೄྀ࿐ ˊˎ-
╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
Audio
🔍 የፕሮፋይላችን ነገር

ምርጥ ምክር👆👂👂

‼️ፕሮፋይላችን ማንነታችንን ይገልፃል።

‼️ፕሮፈሰይላችሁን አስተካክሉ

🎤አቡ አብዲላህ ኢብኑ ኸይሩ

       ቴሌግራማችን

╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
╭┈─────── ೄྀ࿐ ˊˎ-
╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
ነብዩ ﷺ ከባህሪያቸው ውስጥ፦ ከሰዎች ጋር የነበራቸው መስተጋብር ያማረ ነበረ። ሁሌም በፈገግታ የተሞሉ ነበሩ። ቤተሰቦቻቸውን ያጫውቱ እንዲሁም ያዝኑላቸው ነበር። ወጪያቸውንም ሰፋ አድርገው ይሸፍኑ ነበር። ሚስቶቻቸውን ያስቁ ነበር።

اللَّهُمَّ صَلِّ وَسَلِّمْ وبارك عَلَى نَبَيِّنَا مُحَمَّدٍ
اللَّهُمَّ صَلِّ وَسَلِّمْ وبارك عَلَى نَبَيِّنَا مُحَمَّدٍ
اللَّهُمَّ صَلِّ وَسَلِّمْ وبارك عَلَى نَبَيِّنَا مُحَمَّدٍ
         ቴሌግራማችን

╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
╭┈─────── ೄྀ࿐ ˊˎ-
╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
الزواج في الإسلام /ትዳር በኢስላም
🔍 የፕሮፋይላችን ነገር ምርጥ ምክር👆👂👂 ‼️ፕሮፋይላችን ማንነታችንን ይገልፃል። ‼️ፕሮፈሰይላችሁን አስተካክሉ 🎤አቡ አብዲላህ ኢብኑ ኸይሩ        ቴሌግራማችን ╰➤ ❝@Tidar_Be_Islam ╭┈─────── ೄྀ࿐ ˊˎ- ╰➤ ❝@Tidar_Be_Islam
ዉድ እህትና ወንድሞቼ ❗️ፎቶ / ነብስ ያለዉን ነገር ፕሮፋይል የምታደርጉ ሁላ ልታዳምጡት ይገባል👆👂👂 pless ስንቶቻችን ነን ዛሬ ለይ በየቦታዉ ፎቶቻችን የለቀቅነዉ
ሞት ሳይቀድመን እናስተካክል ቶብተን ወደ አላህ እንመለስ ። አላህ ይዘንልን ተዉበታችንንም አላህ ይቀበለን። بارك الله فيكم
ኸልዋ
.....
አሁን ላይ ምንም የማይመስለን ነገር ግን ሓራም ይሆኑ.... ነገሮች እጅግ በዝተዋል።
...
ከነሱም ውስጥ አንዱ ኸልዋ( መገለል) ነው!!
√ኸልዋ (መገለል) ስንል፦ ..አንድ ወንድ ለሱ አጅነብይ የሆነችን ሴት ለብቻዋ ሲያገኛት or ...እሷ ጋር ምንም መህረም(የቅርብ ዘመድ) ሳይኖር ሲገለሉ ማለት ነው።
....
ይሄን ደግሞ ረሱል (ﷺ) ከልክለዋል። ማለትም ሓራም ነው።
رواه ابن عباس (رضي الله انه) انّه سمع النّبيّ ﷺ يخطب ،يقول [لا يَخْلُوَنَّ رَجُلٌ بِامْرَأةٌ إلَا وَمَعَها ذَو مَحْرَمٍ]
ኢብኑ ዓባስ በዘገበው ሃዲስ....
ነብዩ (ሰለላሁ ዓለይህ ወሰለም) ኹጥባ ሲያደርጉ ሰማሁኝ።
ወንድ ልጅ በሴት ልጅ እንዳያገል (ብቻቸውን እንዳይሆኑ)ከሷ ጋር የቅርብ ዘመዷ ቢኖር እንጂ። ብለዋል!
እናም ወንድሞቼ ......ሳናውቅ ብዙ ሃራም ነገሮችን እየሳራን እንዳለን ልንገነዘብ ይገባል
....
ሴቶችን በሃጃ እንኳን ማግኘት ቢኖርብን ..ሸሪዓዊ አዳቦችን በጠበቀ መልኩ መሆን አለብት።
...አላህ (ሱብሃነሁ ወተዓላ) ...

{(وَإذَا سَأَلْتُمُوهُنَّ مَتَاعًا فَسْأَلُوهُنَّ مِنْ وَرَآءِ حِخاب)}🌸
{ዕቃንም (ለመዋስ) በጠየቀችኃቸው ጊዜ ከመጋረጃ ጀርባ ሆናችሁ ጠይቋቸው።} ሱረቱል አህዛብ: 53
በማለት ገልፆልናል።
....ቁርኣንን አንባቢ ብቻ ሳንሆን ተገንዛቢ( በቁርኣን ሰሪዎች ልንሆን ይገባል)


🥀ባረከላሁ ፊኩም።
ቴሌግራማችን

╰➤ ❝@Tidar_Be_Islam
╭┈─────── ೄྀ࿐ ˊˎ-
╰➤ ❝@Tidar_Be_Islam
Don't love someone by make the haram relationship. Haram relationship will involved you to Zina In Islam, there are no love between a man and a woman except a love of life partner ... Nikah is the Halal relationship. it is the right way to show your love, if you cant afford to Nikah. Then you should fasting because fasting will curb your passions . Follow the rules of Islam and In shaa Allah your life will be very simple and wonderful as Islam
join the channel

╰➤ ❝@Tidar_Be_Islam
╭┈─────── ೄྀ࿐ ˊˎ-
╰➤ ❝@Tidar_Be_Islam
الزواج في الإسلام /ትዳር በኢስላም
☞::::::እህቴ::::::::☜ ክፍል አምስት/ ⑤ ..አንዱን ዓሊም «እስቲ ስለጀነት ፀጋዎች ንገረንና ጀነትን አስናፍቀን!» አሉት። እሱም በአንዲት ዐ.ነገር ብቻ ልብን ጀነት ላይ እንድትንጠለል ምታደርግን ንግግር ተናገር። መልካም ስራ መስራት ላደከማቸዉ አሪፍ ብርታት ሚሆንን ንግግር ተናገረ። «በዉስጧ ረሱሉ አሉ።» አላቸዉ። አለቀ። አንድ በልቡ ዉስጥ የረሱሉ ሙሃባ ላለበት ሰዉ በቂ ማነቃቂያ ነዉ።…
☞:::::::::እህቴ::::::::::☜

ክፍል ስድስት/⑥

ዛሬ ከሌሎች ጊዜ ለየት ያለ ትንሽ ጠጠር ያለ ሀሳብ ነዉ የማነሳዉ። ርዕሳችን ስለጀነት ነዉና ምናልባትም ይህ ዛሬ የማነሳዉ ጉዳይ በኛና በጀነት መሃል መጋረጃ ሊሆን ስለሚችልም ወቅታዊም ጉዳይ ስለሆነ ማንሳቱን መረጥኩኝ።

ሀገራችን ካፈራቻችዉ ታላላቅ ስብዕናዎች መሃል አንዱ የሆኑት.. ታላቁ ሼይክ ሙሀመድ አሊ ኣደም እንዲህ ይላሉ..

«ወሳኙ ነገር ‛አሉ! አሉ!’ መብዛቱ አይደለም። ወሳኙ ነገር ማስረጃዉ ጠንካራ መሆኑ ነዉ።»

አብዘሀኛዉ ሰዉ የሆነን ነገር ያደርጋል ማለት ያ ነገር ልክ ነዉ ማለትን አያስይዝም። በሆነ መንገድ ላይ ሚሄዱ ሰዎች መበራከታቸዉ ያ መንገድ ልክ ነዉ ማለትን አያስንዝም።

እቺን ወሳኝ ነጥብ ከያዝን ወደ ጉዳያችን እንግባ።

እንበልና ያ ከልበወለድ የማያወራዉ ተወዳጁ ነብይ ሙሀመድ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ከዛሬ 1400 አመታት በፊት አንድን ነገር ከለከሉ። ነገር ግን ከዉዱ ነብይሽ ህልፈት ከ7 እና ከ6 መቶ አመታት ብኋላ አንድ ሰዉ መጣና «ያ ነብያችሁ ሲከለክሉት የነበረዉ ነገር ኮ ስህተት ነዉ። እኔ መልካምን ነገር አዉቅላችኋለሁ። እኔን ብትከተሉ መልካም ነዉ።» ቢል ትከተዪዋለሽ?!

አላህ አይቀድረዉና አንቺ ምናልባት መዉሊድን እያከበርሽ ከሆነ ያን ከ1400 አመታት በፊት «ዲናችሁን ሞላሁላችሁ!» ብሎ ቁርዓንን ያወረደዉን አላህን፣ እንዲሁም ያን «ትዕዛዛችን ያልሆነን አንድን ነገር የፈፀመ በሱ ላይ ተመላሽ ነዉ።» ብሎ የተናገረዉን የረሱሉን ቃል ጥሰሽ.. ከረሱሉ ህልፈት ብኋላ ከ700 አመታት ብኋላ መጥቶ መዉሊድን ያወጀዉን ሙዘፈርን አስበልጠሻል ማለት ነዉ።

አላህ ምስክሬ ነዉ!
እኔ ላንቺ አሳቢና ተቆርቋሪ ብቻ ነኝ።

ያ.. እንዴት መብላት፣ እንዴት መጠጣት፣ እንዴት መልበስ፣ እንዴት መተኛት፣ እንዴት መሄድ፣ እንዴት ማዉራት.. በተጨማሪም ብዙ ቀላል ሚመስሉ ነገሮችን ያስተማሩን ነብይ መዉሊድም ኸይር ቢሆን ኖሮ ባስተማሩንና ባመላከቱን ነበር። ግን በአስተምህሮታቸዉ ዉስጥ አንድንም መዉሊድን ሚደግፍ ነገር አናገኝም።

ሰሀቦችም፣ ታቢዕዮችም፣ አትባዓ ታቢዒንም አንድኛቸዉም አልፈፀሙትም። ታዲያ ዲን በነብያትና ከነሱ ቀጥሎ በመጡት መልካም ዓሊሞች ይመራል እንጂ.. በንጉስና በመጥፎ ዓሊሞች ይመራል እንዴ?!

እህቴ! የዚህ ዘመን ሰዎች ምንስተካከለዉ የበፊቶቹ በተስተካከሉት ነዉ። እነሱ የተስተካከሉት ደግሞ በቁርዓንና በሀዲስ ነዉ። በቁርዓንና በሀዲስ ማስረጃዎች አደራ እልሻለሁ!!

[[አደራ!
ብዙ ሰዉ መዉሊድን ማክበሩ አያታልልሽ!
አብዘሀኛዉ ሰዉ ነፍሱ ምታጌጥለትን እንጂ ቁርዓንና ሀዲስን አይከተልምና።]]
#ይቀጥላል_ኢንሻአላህ

            ቴሌግራማችን

╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
╭┈─────── ೄྀ࿐ ˊˎ-
╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
☞☞አላህ ሆይ ከጀሀነም እሳትና ወደዛ ከሚወስዱ ስራዎች አንተው ጠብቀን።

☞አቢ ሰኢድ አልኹድርይ رضي الله عنه እንዳስተላለፈው የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል።

«ከጀሀነም ሰዎች ትንሹ ቅጣት የሚቀጣው ሰው፦ ከእሳት የሆኑ ሁለት ጫማዎች ይደረግለታል። ከጫማው ሙቀት የተነሳ ጭንቅላቱ ይንተከተካል።»
📚 رواه مسلم (211 )

قَالَ رَسُولُ اللهِ ﷺ: «يَا أَيُّهَا النَّاسُ تُوبُوا إلَى اللهِ، فَإِنِّي أتُوبُ إلَيْهِ مِئَةَ مَرَّةٍ»

ነቢዩ ( صلى الله عليه وسلم( እንዲህ ብለዋል፡ ‹‹እናንተ ሰዎች ሆይ ወደ አላህ በፀፀት ተመለሱ፡፡ እኔ በየቀኑ ከመቶ ጊዜ ያላነሰ ተውበት አደርጋለሁ፡፡

☞☞ዉድ የሙስሊም እህትና ወንድሞቼ አላህ ከጀሀነም እሳት ይጠብቀን አሚን←←←←←

       ቴሌግራማችን

╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
╭┈─────── ೄྀ࿐ ˊˎ-
╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
الزواج في الإسلام /ትዳር በኢስላም
☞:::::::::እህቴ::::::::::☜ ክፍል ስድስት/⑥ ዛሬ ከሌሎች ጊዜ ለየት ያለ ትንሽ ጠጠር ያለ ሀሳብ ነዉ የማነሳዉ። ርዕሳችን ስለጀነት ነዉና ምናልባትም ይህ ዛሬ የማነሳዉ ጉዳይ በኛና በጀነት መሃል መጋረጃ ሊሆን ስለሚችልም ወቅታዊም ጉዳይ ስለሆነ ማንሳቱን መረጥኩኝ። ሀገራችን ካፈራቻችዉ ታላላቅ ስብዕናዎች መሃል አንዱ የሆኑት.. ታላቁ ሼይክ ሙሀመድ አሊ ኣደም እንዲህ ይላሉ.. «ወሳኙ ነገር…
☞::::::::::እህቴ! ::::::::::☜

ክፍል ሰባት/⑦

ወሳኝ ጥያቄ!
ዲንን የምትወስጂበት ዋና ቦታ የት ነዉ?!

እስከዛሬ የገባኝ ነገር ቢኖር አብዘሀኛዉ ሰዉ ቀላል የሆነን መንገድ ነዉ ሚከተሉት። ከነፍሳቸዉ ጋር የሚገጥምን ነገር ፈተዋ የሚሰጥን ሰዉ ይወዳሉ። አንዳንዱ እንደዉም ነፍሱ ደስ ያለዉን ነገር ፈተዋ ሚሰጥ ሰዉ ከሰማ በደስታ በሮ.. «ሼይክ ማለትማ ይህ ነዉ፣ ያለንበትን ተጨባጭ የተረዳ ታላቅ ዓሊም ማለት ይህ ነዉ፣ የሙስሊሞችን ቁስል ጠንቅቆ ሚያዉቀዉ እሱ ነዉ።» ይላሉ።

ፈተዋዉ የፈለገዉን ያህል ልክ ባይሆንና በደዒፍ ሀዲሶች ቢሞላ እንኳን የነፍሱን ሙራድ ከገጠመ ፈተዋ ማለት ለሱ ያ ነዉ። ሙፍቲ ማለት ያ ሼይክ ነዉ።

አላህ የቂያማ ቀን እያንዳንዳችንን አንድን ጥያቄ ይጠይቃል..
«..መልዕክተኞችን ምን ብላችሁ መለሳችሁ?!»

አላህ ስለ ሸይክ አገሌ አልያም ስለ ሙፍቲ እገሌ አንጠይቅሽም። ቁርዓንና ሀዲስን ስለመከተልሽ ነዉ የሚጠይቅሽ።

ይበልጥ ግልፅ እንዲሆን ጥያቄዬን ልድገመዉ..

ዲንን የምትወስጂበት ዋና ቦታ የት ነዉ?!

እህቴ! ኮፊያ የለበሰ፣ ጥምጣም የጠመጠመ፣ በአላህ ምስጋና ጀምሮ በ‛ወላሁ አዕለም!’ የዘጋ ሁላ ሙፍቲ ይሆናል እንዴ?!

ዓሊም መስሎ ራሱን ያሳየ ሁሉም ሰዉ ዲን ከሱ ሚያዝ ሰዉ ይሆናል እንዴ?!

እህቴ! ዲንሽን ማንም እንደፈለገዉ የሚቀንሰዉና የሚያበላሸዉ ተራ እቃ አታድርጊዉ! እንደመጣለት የሚፈርድን ተራ ሰዉን እንደሼይክ አድርገሽ አትከተዪዉ! አንቺ ብቻሽን ነዉ ምትመረመሪዉ..

«..መልዕክተኞችን ምን ብላችሁ መለሳችሁ?!» ተብለሽ ብቻሽን ነዉ ምትጠየቂዉ። የጠመሙ ዓሊሞችን እንዳትከተዪ አደራ እልሻለሁ።

እስቲ አንዲት ፈገግ ምታረግን ታሪክ ልንገርሽ!! ላነሳነዉ ርዕስም ምርጥ ምሳሌ ይሆናል።

አንድ ገያስ ኢብኑ ኢብራሂም የሚባል ራሱን ዓሊም ሚያስመስል ዉሸታምና ወራዳ ሰዉ ነበር። ሰዉዬዉ ወሬ ይችላል፣ ሀዲሶችን እንደሀፈዘና ብዙ ዒልም እንዳለዉ ይናገራል። በዚህም ብዙ ሰዎች በዙሪያዉ ይሰባሰባሉ።

አንድ ቀን አንድ ሰዉዬ ገያስን በሚያሳፍር ሁኔታ ላይ ተቀምጦ አየዉና «ከሰዎች አታፍርም?! (ተስተካከል እንጂ!)» አለዉ።

ገያስም «ሰዎች የት አሉ?!» አለዉ። ሰዉዬዉም «እነዚህ በዙሪያህ የተሰበሰቡት ሳ?!» አለዉ። ገያስም «እነዚህማ ሰዎች አይደሉም። እነዚህ ከብቶች ናቸዉ። ከፈለክ ላረጋግጥልህ!» አለዉ።

ከዚያም ገያስ ያለዉን ሊያረጋግጥለት ወደ ሰዎቹ ሄደና ስለጀነትና ፀጋዎቿ ይነግራቸዉ ጀመር። ሁሉም አፉን ከፍቶ ያዳምጣል። ልባቸዉ ወደሱ መንጠልጠላቸዉ ባየ ጊዜ አንድን የዉሸትን ሀዲስ ፈጠረና እንዲህ አላቸዉ.. ረሱል (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል.. በምላሱ የአፍንጫዉን ጫፍ የነካ ሰዉ ጀነት ገባ!

ሰዎቹም ይህን በሰሙ ጊዜ ወዲያዉ ምላሳቸዉን እያወጡ አፍንጫቸዉን ለመንካት መሞከር ጀመሩ።

ገያስም ወደሰዉዬዉ ዞረና «ከብት ናቸዉ አላልኩህም ነበር።» አለዉ።

እህቴ! አላህ የጠበቀዉ ሰዉ ሲቀር አብዘሀኛዉ የኛ ዘመን ሰዉ ቁርዓንና ሀዲስን ሳይሆን እንዲህ አይነት ዓሊሞችን በጭፍን ሚከተሉ «ከብቶች» ሆነዋል።

እህቴ መላልሼ አደራ የምልሽ ነገር..
ዲንሽን ማንም ‛ዓሊም ነኝ!’ ባይ ከመሬት ተነስቶ የሚመራዉ ተራ ነገር አድርገሽ አትያዢዉ።

[[አንድ ሰዉ ዓሊም ሚባለዉ ሁለትን ነገር አንድ ላይ ሲይዝ ነዉ። ዒልምና ተቅዋን።

ዒልም ከቁርዓንና ከትክክለኛ ሀዲሶች ማስረጃ የሚያረግበት መሳሪያዉ ሲሆን.. ተቅዋው ደግሞ በፈተዋዉ ዉስጥ አላህን እንዲፈራ፣ በሀብትና በክብር እንዳይታለልና ሀቅን ለመናገር የወቃሽን ወቀሳ እንዳይፈራ ያደርገዋል።

ትክክለኛ ምርጥ የአላህ ዑለሞች በኛ ዘመን አቤት ማነሳቸዉ።
#ይቀጥላል_ኢንሻአላህ

            ቴሌግራማችን

╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
╭┈─────── ೄྀ࿐ ˊˎ-
╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
☞ሱብሀን አላህ ልብ የሚነካ ነገር ነው

#ሼኽ_ናይፍ_እንዲህ_ይለናል

አላህ( سبحانه وتعالى) ሁላችንንም  ይጣራል ማረኝ በሉኝ ምህረትን  ጠይቁኝ ይላል

ከአንድ ወር ግማሽ በፊት እኔና ሸኽ ወሊድ  ሌሎችም ሼኾች  ከጅዳ ወደ ጣኢፍ  ለሙሃደራ  ለመሄድ አስበን መንገድ ላይ ሸኽ ወዲድ እንዲህ አለኝ የናይፍ አንድ እናት አለች ከጣኢፍ  አንድ ሳምንት ሆናት ስታናግረኝ ። እርሱም  አንድ ወንድ ልጅ አላት ። የልጁ እናትም እንዲህ አለችኝ የሸኽ ልጄን መታችሁ ብታውልኝ ዝያራ ብታደርጉለት አለች
። አመኛለሁ አላህ ብታስታውሱን  ከእናንተ ጋር ዳዕዋው ቦታ ብትወስዱልኝ እናንተ አላህን የምትዘክሩበት ቦታ አላህን ከምታስታውሱበት ቦታ  ውሰዱት ልጄ እንዲሰግድ እፈልጋለሁ ልጄ ወደ ጌታው እንዲመለስ እፈልጋለሁ  ልጄ  እደዚህ አይነት ሁኔታ ላይ ሆኖ ቢሞትብኝ አልፈልግም ጌታውን ያውቅ ዘንድ እርዱኝ አለች ።
#ሼኽ_ወሊድም አለኝ የናይፍ ምን ይመስልሃል የዚህችን እናት ቃል ሰምተን ወደ ልጁ ብንሄድ አለኝ ። እኔም አልኩኝ መርሀባ የሼኽ ። ከዛም  ለልጁ  እናት ስልክ ወደልን  ። ልጁን ማናገር እንፈልጋለን አልናት  አናገርነውም ። አልነው ስማ  ወንድሜ  እኛ ከቤታችሁ ቅርብ ነን ። ከጂዳ ወደ ጣኢፍ የዳዕዋ የመጣን ሼኾች ነን  አልነው ። ቦታ ተቀጣጠርን እና ተገናኘን ።
ተሰላለምን ።ካላሰብነው በላይ መልካም ልጅ ሆኖም አገኘነው ። ከጌታው የራቀ ቢሆንም ግን አላህ ሙሉ አካል የሰጠው ሁሉ ነገሩ የተሟላ ነበር ። ከተሰላለምን በኃላም እንዲህ አልነው
። የምንልህ ነገር አለ ። እርሱም እሺ ምንድን ነው አለ ። እኛም አልነው ።

ዛሬ ጣኢፍ  ሙሀደራ አለ እናም ከእኛ ጋር እንድትሄድ እንፈልጋለን አልነው ።እርሱም አለ ስሙኝ መምጣታችሁ ለእኔ ወድጄዋለሁ ። ወላሂ እመጣለሁ ። የእህቴን ልጅ ይዤ አብረን እንመጣለን ሙሀደራውን አብረን እንከታተላለን አለን ።
ወላሂ በሙሀደራው ውስጥ ከ2000 በላይ ህዝብ ነበርና ሙሀደራ በምናደርግ ሰአት ልጁን እረሳነው ። ከሙሀደራው መጨረሻ ላይም ያ ልጅ ቀስ እያለ ወደ እኛ መጣ  አቀፈኝ እና ያለቅስ ጀመር ።ለጌታው  ስጁድም ወረደ ።

ጌታዬን አመሰግነዋለሁ እያለ ስጁድ ላይ ተደፋ ። ወላሂ ከ4 ቀን በፊትም መሞቱን ሰማን እናቱንም አላህ ያፅናሽ አልናት ። ሰው ሁሉ ይሞታል ። ግን ይሄ ልጅ እንዴት ሞተ የሚለው ነገር ። እናቱም አለች ወላሂ ከሙሀደራው  ወዲህ  የእናቱን ሀቅ ሲወጣ ነበር  አለች ።

ኡምራም አድርጎ መጣ አለች ። ከዛም የሱቢህ ሰላትን ሰገደ  ከመካ ወደ ጣኢፍ እየመጣ ከቤቱ ሲደርስ ሞተ ። አላህ  አዛኝ ነው አላህ መሀሪ ነው አላህ የባሮቹን መክፈር አይወድም ።
አላህ ምህረትን ይሻልናል አላህ ጀነትን ይወፍቀናል ። አላህ ለምንድን ነው ጥሩኝ ምህረትን ጠይቁኝ ያለው እኛ ምህረትን እናገኝ ዘንድ ነው ""!
የረብ የአላህ አንተ ተገዢዎች ሆነን እንጂ አትግደለን ። አላህ መጨረሻችንን ያሳምርልን አሚን ።

            ቴሌግራማችን

╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
╭┈─────── ೄྀ࿐ ˊˎ-
╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
በጁሙዓ ለሊት እና ቀን ላይ ሰለዋት አብዝታችሁ አውርዱብኝ ፣በእኔ ላይ አንድ ጊዜ ካወረዳችሁ አላህ በእናንተ ላይ አስር ጊዜ ያወርዳል ረሱል ﷺ
      اللهُمّ صَلِّ وسَلّم على نبيّنا محمد ﷺ

ቴሌግራማችን

╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
╭┈─────── ೄྀ࿐ ˊˎ-
╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam