መልካም እረኛ
572 subscribers
381 photos
4 videos
20 files
86 links
"እንደ ኢየሱስ ያለን መልካም እረኛን ይፈልጉታል"
~ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

"በጎቼ ድምፄን ይሰማሉ እኔም አውቃቸዋለሁ ይከተሉኝማል" ዮሐ 10:27

ጥያቄ ወይ አስተያየት ካለዎት በዚህ አድራሻ ይላኩልን:- @The_Good_Shepherdbot
Download Telegram
ቅዱሳን አንተን ባወቁበት መጠን አውቅህ ዘንድ እሻለሁ የቅዱሳኑ ንፅህና ግን በእኔ ዘንድ የለም። እጠጋለው ኀጢአቴም ዳግመኛ ታርቀኛለች እጠጋለው ኀጢአቴም ዳግመኛ ታርቀኛለች።አቤቱ ጌታዬ ሆይ አደከመቺኝ አንተን በፍፁም ንፅህና አፈልግህ ዘንድ ከለከለቺኝ።ደክሞኝም ፈፅሜ እንዳልተውህ ያቀመስከኝ የፍቅርህ ጣዕም ትዝ ይለኛል። አቤቱ ተጨነኩ አንተስ እስከመቼ ዝም ትላለህ? እስከመቼስ ለፈቃዴ ትተወኛለህ?...

አቤቱ አንተን እንደወደዱህ እንደ ቅዱሳንህ ከፈቃዴ እንድሰዋልህ ቅድስት የምትሆን በጎ ጭካኔንን አስጨክነኝ።

“ከፈቃዴ እሠዋልሃለሁ”
— መዝሙር 54፥6
ልቤ

ልቤ እርጋታ የለውም ። ልቤ የረገጠውን መልሶ ይረግጣል ። ቍርጥ ውሳኔ አጥቶ ከኃጢአት እየዋለ ከጽድቅ ያረፍዳል ። ልቤ ሸካራ ነው ፤ ቂምን አርግዞ በቀልን ይወልዳል ። ልቤ ልፍስፍስ ነው ፣ ከሚሰደብበት ቦታ ቆሻሻ መጣያ ሆኗል ። ልቤ ዓለም ነው ፣ ልቤ የወፍ ጎጆ ነው ። ሰፋ ስለው የሚጠብብ አስጨናቂ ነው ። ልቤ ሁሉን ካልወደድሁ ብሎ በስሜት ይነሣሣል ፣ መልሶ ራሱንም መጥላት ይጀምራል ። ልቤ በልቤ ውስጥ ባይሆን ኖሮ አብዷል ተብሎ በተያዘ ፣ ወፈፌ ተብሎ የተዘለፈ ነበር ። አካሌ ጨምቶ ልቤ ይወራጫል ። ወንበር ላይ ተቀምጬ ልቤ ዓለምን ይዞራል ። ውስንነት ከብዶት ልቤ ምሉዕ በኵለሄ ልሁን ይላል ። አንድ ቀን በልደት የጀመረ ፣ አንድ ቀን በሞት የሚያበቃ መሆኑን ረስቶ ልቤ አልፋ ኦሜጋ ልሁን ይላል ። ልቤን ለልብ አምላክ እከሰዋለሁ ። ስንዴና እንክርዳድን ያበቀለ እርሻ መሆኑን እናገራለሁ ።

ልቤ የሚያሳዝነው ያስቀዋል ፣ የሚያስቀው ያስለቅሰዋል ። ልቤ ሞገደኛ ነው አብዮት ያስነሣል ፣ ልቤ ደካማ ነው በድቃቂ ሳንቲም ይደለላል ። ልቤ ሰማይን ያስሳል ፣ ቁራሽ መሬት ለማግኘት ዘመን ላመጣው ያደገድጋል ። ልቤ ሞቱን በሟቾች መቃብር ላይ ያለቅስለታል ፣ ከቀብር ሲመለስ ወደ ግፍ ተግባሩ ይመለሳል ። ልቤ መቀበልን ሽቶ መስጠትን ይጠላል ። ሌላው እንዲወደው እየተመኘ ፣ ሌላውን ለመውደድ ዳተኛ ይሆናል ። ልቤ ጉራማይሌ ነው ። ወጥ መልክ እያጣ ያናውጠኛል ። አድራሻዬን ተናግሬ እንዳልወጣ ያዘባርቀኛል ። ልቤ እንደ ሰዓቱ ፣ ልቤ እንደ ዜናው ፣ ልቤ እንደ ወቅቱ ነው ። ሰማይ ላይ የሄደው ልቤ በዚያው ቅጽበት ጭቃ ሲያላቁጥ አገኘዋለሁ ። በልቡ ላይ የበላይ የሆነ ይህን አቤቱታ መስማት አይሆንለትም ። ልቡን ልቡ ያደረገ አይቼም አላውቅም ። ልቤ እየቀደሰ ይረክሳል ፣ እየዘመረ ይስታል ፣ እየጸለየ ይባክናል ። ራሱ ከፍቶ ፣ በሌሎች መክፋት ልቤ ይደነቃል ። የእርሱን ምሰሶ ትቶ በሰው ጉድፍ ይሳለቃል ። ልቤ ሞኝ ነው ፣ አያገኘኝም ብሎ የጨው ተራራ ሲናድ ይስቃል ።

ልቤ ራሱ ጠፍቶት የሰውን ልብ አውቃለሁ ይላል ። ልቤ እገሌ ጎሣ ሲነግሥ “ደብቄ ነው እንጂ እኔ እኮ ከዚህ ዘር ነኝ” ለማለት ይከጅላል ። ልቤ ሆዳምነት በልጦበት ካሸነፉት ሰፈር ሲወለድ ይኖራል ። ሁልጊዜ የሚወለድ ማደግ ግን ያቅተዋል ። ልቤ ረቂቁ ፣ ግዙፉን ዓለም የሚንጠው እርሱ ነው ። የሚታየው ከማይታዩት የተሠራ ነው ። የሚታየው ጥፋት ፣ የማይታዩ ልቦች ውጤት ነው ። አካል ያጠፋል እንጂ አይከፋም ፤ ልቤ ይከፋል ፣ አካሌ ያጠፋል ። ልቤ ሰማይ ተቆልፎበት ምነው በሞትኩኝ ይላል ። ልቤ ሰውን ሁሉ እወዳለሁ እያለ አንድን ሰው ማፍቀር አቅቶታል ። ልቤ ስለ ዓለም አቀፋዊነት እያወራ ፣ መንደር አቀፍነት ወጥሮታል ። ልቤ ሩቅ አገር ካለው ጋር እየተወዳጀ ጎረቤቱን አኩርፏል ። ልቤ መንታው ፣ ልቤ ባለማመን የምታሰቃየኝ ፣ ልቤ እስስቱ ፣ ልቤ የጌታ ሳይሆን የቀን ሎሌ ነህ ።

ልቤ ወንዙ ፣ ልቤ ነሆለሉ ፣ ልቤ ባሕር ፣ ልቤ የሚዋልል ፣ ልቤ የውኃ ላይ ኩበት ፣ ልቤ ተቀምጬ የሚሮጥ ፣ ጽሞናን ጠልተህ በጫጫታ የምትደበቅ ፣ ለገዳይም ለሟችም እኩል የምታጨበጭበው እውቀት አልባ የምትሆነው እስከ መቼ ነው ? እግዚአብሔር ሲመራህ እንቢ ብለህ ሰው እንዲነዳህ የፈቀድከው ፣ ባሰመሩልህ ስትቀየስ የምትኖር የመስኖ ውኃ የሆንከው ፣ ልቤ ዕረፍትህን ናፍቄአለሁ ።

ልቤ እርሱ እያሞገሰ ፣ ካህናት ለምን አያወግዙም የሚለው ፣ እውቀትና መረጃን ያምታታው ፣ ሰልጥኛለሁ ብሎ ኃጢአትን የሚያቆነጀው ለሞትም ለምጽአትም ያልተዘጋጀው ልቤ እርሱ ነው ።

ተኝቶ እያደረ ስጸልይ ነጋ የሚለው ልቤ ግብዙ ፣ ሙሴን እየተወ ፈርዖንን የሚጋብዝ ፣ ኢየሱስን ትቶ በርባንን የሚናፍቅ ፣ ሚዛንን ጥሎ የሚደንስ ልቤ እርሱ ነው ።

ከጥንት ጀምሮ የልብ ባለመድኃኒት የሆንከው የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ልቤን ጠብቀው ! አሜን!!!

ዲ.አ.መ
ተፃፈ ነሐሴ 9 ቀን 2015 ዓ.ም.
በውስጤ ያለችው የኃጢአት ፍቅር ለአንተ ካለኝ ፍቅር ስትበልጥ ይሰማኛል አንተንም እንዳላይ የልቦናዬን አይን የምትጋርድ እርሷ ናትና አቤቱ እንድወድህ ግድ በለኝ ፈቃዴን አልሻውምና። ከኃጢያት ከምትለየዋ ከአንተ ፍቅር አድርሰኝ።
መልክህን ማየት ተለል ተለል ያደርገኛል።ፍቅርህም ያዝለኛል፤ አንተን መዘከር ያቃጥለኛል። ሁል ጊዜ ስራ ለመስራት ያነቃቃኛል ።አቤቱ ፍቅርህ በልቦና ፈጥኖ አደረ በሰውነቴ ተሰራጨ።ሕዋሳቴን ጸጥ አደረጋቸው።

አረጋዊ መንፈሳዊ ድርሳን ፳፩
ቅዱሳን አንተን ባወቁበት መጠን አውቅህ ዘንድ እሻለሁ የቅዱሳኑ ንፅህና ግን በእኔ ዘንድ የለም። እጠጋለው ኀጢአቴም ዳግመኛ ታርቀኛለች እጠጋለው ኀጢአቴም ዳግመኛ ታርቀኛለች።አቤቱ ጌታዬ ሆይ አደከመቺኝ አንተን በፍፁም ንፅህና አፈልግህ ዘንድ ከለከለቺኝ።ደክሞኝም ፈፅሜ እንዳልተውህ ያቀመስከኝ የፍቅርህ ጣዕም ትዝ ይለኛል። አቤቱ ተጨነኩ አንተስ እስከመቼ ዝም ትላለህ? እስከመቼስ ለፈቃዴ ትተወኛለህ?...

አቤቱ አንተን እንደወደዱህ እንደ ቅዱሳንህ ከፈቃዴ እንድሰዋልህ ቅድስት የምትሆን በጎ ጭካኔንን አስጨክነኝ።

“ከፈቃዴ እሠዋልሃለሁ”
— መዝሙር 54፥6
"ሲዖልን ማራኪ ማድረግ እንደማይቻል ዲያብሎስ ጠንቅቆ ያውቃል ስለዚህ ያለው አማራጭ ወደሲዖል የሚወስደውን መንገድ በቀላሉ የሚለመድ ሳቢ ውብና ማራኪ አድርጎ ማሳየት ነው።

መንገዱ የተመቸ ሁሉ መዳረሻውም ምቹ ላይሆን ይችላልና በሕይወት መንገድ ላይ አለን የምንል መንፈሳዊ ተጓዦች ቆም ብለን እንደቃሉ መመራት አለመመራታችንን እናስብ።"

~ ታላቁ ቅዱስ ባስልዮስ

ተቀላቀሉ:-
https://t.me/orthodoxy_life
የቅዱስ አንብሮስ የንስሐ ጸሎት

"ቁስሌን የሚፈውስልኝ ጌታ ኢየሱስ ሆይ አንተን ብቻ እከተላለሁ ፡፡ በአንተ ካለው የእግዚአብሔር ፍቅር ምን ይለየኛል? መከራ ፣ ጭንቀት ወይስ ረሃብ? በምስማር እንደ ተያዘ እኔ በፍቅር ሰንሰለቶችህ ታስሬአለሁ። ጌታዬ ኢየሱስ ሆይ ኃጢአቶቼ በበረታው ጎራዴህ ከእኔ ቁረጥ ፡፡ በፍቅርህ እስራት ጠብቀኝ በእኔ ውስጥ ያለውን የተበላሸውን ነገሬ አስወግድ ፡፡ በፍጥነት ወደ እኔ ና የበዛውን ፣ የተሰወረውንና የደበቀውን መከራዬን ፍጻሜ አበጅለት ፡፡ አንተ የቆሸሸውን በውስጤ ያለውን አፅዳ፡፡

በኃጢአቶቻችሁ ውስጥ ሰካራም ሀሳቦችን የምታወጡ ፤ እናንተ ምድራዊ ሰዎች ሆይ ስሙኝ ፈዋሼን አጊንቻለሁ ፡፡ እርሱ በሰማያት ተቀምጧል በፈውሱ ምድርን ሞልቷል። እርሱ ብቻ ህመሜን ሊፈውስ የሚችለው። እሱ ብቻ ነው። እርሱ ብቻ ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰወረውን የሚያውቅ ፣ የልቤን ሀዘን ፣ የነፍሴን ፍርሃት ሊያስወግድ የሚችል። ክርስቶስ ጸጋ ነው ፣ ክርስቶስ ሕይወት ነው ፣ ክርስቶስ ትንሣኤ ነው! አሜን"

ትርጉም፡ ብስራት ገብርኤል
[ምንጭ ፦ A Prayer of Repentance and Conviction by St. Ambrose of Milan]


ተቀላቀሉ መልዕክቱን ለሌሎች ያካፍሉ!
እውነተኛ ፍቅር!

“የትእዛዝ ፍጻሜ ግን ከንጹሕ ልብና ከበጎ ሕሊና ግብዝነትም ከሌለበት እምነት የሚወጣ ፍቅር ነው” 1ጢሞ. 1፡5 ።

እውነተኛ ፍቅር ከምን ይመነጫል የሚል አጭር ትረካ ያድምጡ!

https://youtu.be/csuxjF8ISvM?si=emPEbprwz8Yp7jV5
እንኳን ለመድኃኔዓለም ወርሃዊ በዓል አደረሳችሁ!

"ዋላ ወደ ውኃ ምንጭ እንደሚናፍቅ፥ አቤቱ፥ እንዲሁ ነፍሴ ወደ አንተ ትናፍቃለች። "
(መዝ 42 :1)

የናፍቆት ጉልበት እንድታደምጡ በመድኃኔዓለም ስም ተጋብዛችኋል!!
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://youtu.be/16AgUauwoKg?si=pu9j6lqhBPVuClXv
❝ሰማይንና ምድርን የፈጠርኽ ፥ ተስፋ የሚያደርጉኽን የማተው ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ዘንዶውን ድል እንዳደርግ ራሱንም እንድቀጠቅጥ ስለአደረከኝ አመሰግንሃለኹ ! ለባሪያዎችኽ ዕረፍት ስጣቸው፣ የጠላቶቻችን ግፍ የመጨረሻ ሰለባ ተጠቂ ነኝና ይኽን ዕረፍት ስጠኝ ! ለቤተክርስትያንኽ ሰላምን ስጣት ፥ ከዲያብሎስ ጨቋኝነት ንጠቃት። አሜን።
« ቅዱስ ቴዎዶጦስ ዘዕንቆራ»
የኤጲፋንዮስ ቅዳሴ

(ክፍል አንድ)

እግዚአብሔር በገናንነቱ ገናና ነው፤ በቅድስናው የተቀደሰ ነው፤ በምስጋናው የተመሰገነ ነው፤ በክብሩም የከበረ ነው፡፡

ከመቼ ወዲህ የማይሉት ቀዳማዊ ነው፤ እስከዛሬ የማይሉት ማእከላዊ ነው፣ እስከዚህ የማይሉትም ደኃራዊ ነው፡፡

ለአነዋወሩ ጥንት የለውም፤ ለአኳኋኑም ፍጻሜ የለውም፤ ለዘመኑ ቁጥር የለውም፤ ለውርዝውናውም ማርጀት የለበትም፤ ለኃይሉም ጽናት ድካም የለበትም፤ ለመልኩ ጥፋት የለበትም፡፡ ለፊቱ ብርሃንም ጨለማ የለበትም፡፡
ለጥበቡ ባሕር ድንበር የለውም፤ ለትእዛዙም ይቅርታ መስፈርት የለውም፤ ለመንግሥቱ ስፋት ዐቅም ልክ የለውም፣ ለአገዛዙም ስፋት ወሰን የለውም፡፡

በኅሊና የማያገኙት ሥውር ነው፤ በልቡናም የማይረዱት ምጡቅ ነው፤ አንሥርት የማይደርሱበት ረጅም ነው፤ ዓሣዎች የማይዋኙበት ጥልቅ ነው፡፡
ከተራሮች ራስ ይልቅ ከፍ ያለ ነው፤ ከባሕር ጥልቅነት ይልቅ ጥልቅ ነው፤ ነገሥታት የማይነሳሱበት ጽኑ ነው፤ መኳንንት የማይቃወሙት አሸናፊ ነው፡፡

የጥበበኞችን ምክር የሚያጠፋ ጥበበበኛ ነው፤ የሚመክሩትን ሰዎች አሳባቸውን የሚያስረሳ ዐዋቂ ነው፤ የጸኑ ልጓሞችን የሚፈታ ኃያል ነው፤ የኃጥአንን ጥርሶች የሚያደቅ፣ የትእቢተኞችንም ክንድ የሚቀጠቅጥ ብርቱ ነው፡፡

የግብዞችን ፊት የሚያዋርድ ክቡር ነው፤ የዝንጉዎችን ብርሃን የሚያርቅ ከሃሊ ነው፡፡
ባልንጀራ የሌለው አንድ ነው፤ ዘመድ የሌለው ሥሉጥ ነው፤ ሰማያት ይጠፋሉ፤ የብስም ትጠፋለች፤ ሁሉም እንደ ልብስ ያረጃል፡፡ እርሱ ግን እስከ ዘለዓለሙ እርሱ ነው፡፡

የባሕር መመላለሷ ድንቅ ነው፤ ድንቅስ በልዕልናው እግዚአብሔር ነው፤ የሚመስለው የለም፤ ከፍጥረትም ሁሉ ከአማልክትም ልጆች ሁሉ የሚተካከለው የለም፡፡ እርሱ ብቻ አምላክ ነው፤ እርሱም ብቻ ጌታ ነው፤ ፈጣሪም እርሱ ብቻ ነው፤ ሠሪም እርሱ ብቻ ነው፡፡

ስላሰበው ጥበብ እረዳት አይሻም፤ ስለ ወደደውም ሥራ መካር አይሻም፡፡ ሳይሆን ቀድሞ እንደ ሆነ አድርጎ፤ ያልተደረገውንም እንደ ተደረገ አድርጎ ሁሉን ያውቃል፡፡

ሳይጠይቅ ኅሊናን ይመረምራል፤ ሳይመረምር ልቡናን ይፈትናል፤ ያለመብራት በጨለማ ያለውን ያያል፡፡

ጻድቁን ጽድቅን ሳይሠራ ያውቀዋል፤ ኃጥኡንም ኃጢአት ሳይሠራ ያውቀዋል፤ ልበኞችን ከአባታቸው ወገብ (አብራክ) ሳይወጡ ያውቃቸዋል፤ ኃጥአንንም ከእናታቸው ማኅጸን ያውቃቸዋል፡፡
የሚሸሸገው የለም የሚሰወረውም የለም፤ ከእርሱም የሚሰወር የለም፤ ሁሉ በእርሱ ዘንድ የተገለጸ ነው፤ በዓይኖቹም ፊት ሁሉ የተዘረጋ ነው፡፡ ሁሉ በመጽሐፉ የተጻፈ ነው፤ በኅሊናውም ሁሉ የተጠራ ነው፡፡

ቁጥር የሌላቸው ታላላቆችን፣ መመርመር የሌለባቸውን የተደነቁ፣ የከበሩ ሥራዎችን ይሠራል:: ሥራው ካየነው ይልቅ እጹብ ነው፤ ኃይሉም ከሰማነው ይልቅ ድንቅ ነው፤ ጌትነቱም ከነገሩን ይልቅ ድንቅ ነው፡፡

ከጨለማ ለይቶ ብርሃንን ፈጠረ፣ ደመናውን መለየት ያውቃል፡፡ ውኃውን እንደወደደ ይከፍለዋል፤ የተመረጡትን በደመና ይሠውራል፡፡
ምድርን ፈጠራት መጠኗንም አዘጋጀ፤ ፍጻሜዋንም እንደምንም ተከለ፤ ማዕዘኗንም አጸና፡፡

ባሕርን ከእናቷ ሆድ በወጣች ጊዜ በበሮች አጠራት፡፡ ልብሷንም ደመና አደረገላት፤ በጉም ጠቀለላት፤ ወሰን አደረገላት፤ በውስጧም መዝጊያዎችንና ቁልፎችን አደረገላት፡፡ ‘‘እስከዚህ ድረሺ፤ ከወሰንሽም አትተላለፊ፤ ማዕበልሽ በውስጥሽ ይመላለስ (ይነቃነቅ) እንጂ’’ አላት፡፡
በበላይዋ ላይ የንጋት ብርሃን ተዘጋጀ፤ የአጥቢያ ኮከብም ትእዛዙን ዐወቀ፡፡ እርሱ ከምድር ጭቃን ነሥቶ ሕያው የሆነውን ፈጠረ፡፡ በምድርም ላይ እንዲነጋገር አደረገው፡፡ እርሱ እስከ ዓለም ዳርቻ ደረሰ፡፡ በጥልቅ ፍለጋም ተመላለሰ፡፡

ከግርማው የተነሳ የሞት ደጆች ይከፈታሉ፤ የሲኦል በሮችም ባዩት ጊዜ ይደነግጣሉ፡፡ ከሰማይ በታች ያለውን ስፋቱን፣ ከሰማይ በላይ የሚሆነውንም እርሱ ያውቀዋል፡፡

በእርሱ ትእዛዝ ዋግ ከመዝገቡ ይወጣል፡፡ ከሰማይ በታች ያለ አዜብ (ነፋስ ) ይመላለሳል፡፡ ዝናምን በምድረበዳ ያጸናዋል፣ ሰው በሌለበትና የሰው ልጅ በማይኖርበት ይዘንም ዘንድ፡፡

እርሱ የውኃውን መፍሰሻ ወሰነ፤ ክረምትንም በያመቱ ይከፍታል፤ በጋውንም ኋላ በጊዜው ጊዜ ያመጣዋል፡፡ደመናውንም በቃሉ ይጠራዋል ውኃም እየተንቀጠቀጠ ይመልስለታል፡፡

ብልጭልጭታውንም እርሱ ይልከዋል፤ እርሱም ይሄዳል፤ ‘‘ምንድር ነው?’’ እያለ ይመልስለታል፡፡ እርሱ ደመናን በጥበቡ ይቆጥረዋል፡፡ ሰማይን (ጠፈርን ) ወደ ምድር ያዘነብለዋል፡፡
እርሱ ብቻ የአርያምን ኃይል ለበሰ፤ በምስጋናና በክብር ተጌጠ፡፡

እሳታውያን ኪሩቤል፣ ብርሃን የለበሱ ሱራፌልም እርሱን ያመሰግናሉ፡፡ በማያርፍ ቃል፣ ዝም በማይል፣ በማይደክምም አንደበት ሁሉም ተባብረው ተሰጥዎ ባለበት ባንድ ቃል ‘‘የጌትነትህ ምስጋና በሰማይ በምድር የመላ ፍጹም አሸናፊ ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እግዚአብሔር’’ ይላሉ፡፡

ፍጹም አሸናፊ እግዚአብሔር የጌትነትህ ምስጋና በሰማይና በምድር የመላ ነው፡፡

ሁሉ ከእርሱ ነው፣ ሁሉም ስለእርሱ ነው፣ ሁሉም የእርሱ ነው፣ ሰማይ በእርሱ ነው፣ ከሰማያት በላይ ያለ ሰማይም የእርሱ ነው፣ የአርያም ስፋት የክብሩ ዙፋን ነው፣ የምድርም ስፋት የእግሩ መመላለሻ ናት፡፡

ፀሐይ የእርሱ ነው፣ ጨረቃም ከእርሱ ነው፣ ከዋክብትም የእጁ ሥራ ናቸው፣ ደመናት መልክተኞቹ፣ ነፋሳትም ሠረገላዎቹ ናቸው፣ እሳትም የቤቱ ግርግዳ ነው፡፡

የቤቱ ጠፈር ውኃ ነው፣ የዙርያውም ጸፍጸፍ የበረድ ሰሌዳ ነው፣ ድንኳኖቹ ብርሃናት ናቸው፡፡ የመሰወሪያ መጋረጃውም የብርሃን መብረቅ ነው፤ መመላለሻውም በአየር ነው ::

የመናገሩ ድምፅ በብልጭልጭታ ያለ ነው፡፡ የነጎድጓዱ ቃል በሠረገላዎች አለ፡፡ ባሕር ባሪያው ናት፣ የወንዝ ፈሳሾች ተገዥዎቹ ናቸው፡፡ ቁር አስሐትያም ፈቃዱን የሚሠሩ ናቸው፡፡

ከምድር ዳርቻ ደመናውን ያወጣል፣ መብረቅንም በዝናም ጊዜ አደረገ፣ ዝናምንም እንደ መሽረብ ነጠብጣብ ያፈሳል፣ ጉምን እንደ አመድ ይበትነዋል፣ በረድንም እያጠቃቀነ ያወርዳል፣ ለእንስሳም ሣሩን ያለመልማል፡፡

እንዳሰበ ያደርጋል፣ እንደ ጀመረም የጀመረውን ይፈጽማል፣ እንደወደደም ያከናውናል፡፡ ያሳዝናል፣ ደስ ያሰኛል፤ ያደኸያል፣ ባለጸጋም ያደርጋል፡፡

ያዋርዳል፣ ያከብራል፤ ይገድላል፣ ያድናልም፤ ድውይ ያደርጋል፣ ይፈውሳልም፤ ይኮንናል፣ ያጸድቃልም፡፡
የወደደውን ይምራል፣ ሊያስጨንቀው የወደደውን ያስጨንቃል፣ የሚምረውን ይምረዋል፡፡ ይቅር የሚለውን ይቅር ይለዋል፡፡
<<Kaleessa isan wajjiin fannifame, Hardha isaan wajjiin kabajame. Kaleessa isa wajjiin awwaalame hardha isa wajjiin du'aa ka'e. Kanaafuu isa nuuf jedhee du'e kaa'eef kennaa yaa keenninu. Yeroo kanan isiniin jedhu kennaa warqee yookiin albuudota mimmiidhagoo yookiin meeshota qaqqaalii harka namaatiin hojjataman yookiin kan kennaa garboonni addunyaa kanaa mootota isaaniitii kennan sana isinitti fakkaata ta'a. Garuu isaa kanaa miti. Ofii keessaniifi laphee keessan qalbii keessanis gooftaadhaaf kennaa. Kabaja nuuf keenname yaa hubannu; isa nu uumeefis galata yaa galchinu. Humna iccitii gooftaan keenya nuuf du'eef yaa hubannu.>>

Qulqulluu Gorgoriwoos
(Jaarraa 2ffaa keessa kan barreefame)
Forwarded from መልካም እረኛ
ወደ አንተ እንደተዘረጉ ያረጁ እጆች የተቀደሱ ናቸው።
"የማርን ጥፍጥና ማርን ቀምሶ ለማያውቅ ሰው በመቅመስ እንጂ በቃላት ማስተማር እንደማይቻል ሁሉ የእግዚአብሔርን መልካምነት በቃላት በጠራ መልኩ ማስተማር አይቻልም። ራሣችን ወደ እግዚአብሔር መልካምነት ዘልቀን መግባት ይኖርብናል እንጂ።"

ቅዱስ ባስልዮስ
"ክብርና ሥልጣን፥ ሀብትና ንብረት፥ በዚህ ዓለም ላይ የምናገኛቸው ብልጽግናዎች ኹሉ ጸንተው የሚኖሩ አይደሉም። ኹሉም ከወራጅ ውኃ በፈጠነ ፍጥነት የሚያልፉ ናቸው እንጂ ከእነዚህ አንዱስ እንኳን ዘላለማዊ የለም። የሙጥኝ ብሎ ሊልዛቸው የሚሞክር ሰው እንኳን በፍጹም ሊያቆያቸው አይችልም፤ የሚቀረው ባዶውን ነው። መንፈሳዊ ነገሮች ግን እንደዚህ አይደሉም፤ የዚህ ተቃራኒ ናቸው እንጂ፦ እንደ ጽኑ ዐለት የማይንቀሳቀሱ ናቸው፤ ሕልፈት ውላጤ የለባቸውም። ታዲያ ጸንቶ የሚኖረውን እጠፋ እጠፋ በሚለው፥ የማይነቃነቀውን በሚንገዳገደው፥ ዘላለማዊውን በጊዜያዊው ፥ የማያልፈውን በሚያልፈው ፥ ዘላለማዊ ደስታ የሚሰጠውን ዘላለማዊ ስቃይ በሚሰጠው መቀየራችን እንደ ምን ያለ ሞኝነት ነው?"

ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ
አንኳን ሰ2017 ዓ ም ለጌታችን፣ ለአምላካችንና ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረስዎ!

“ስብሐት ለእግዚአብሔር በሰማያት ወሰላም በምድር ሥምረቱለሰብእ፤ በሰማያት ምስጋና ተደረገ በምድርም እርቅ ተወጠነ ‹‹ሰላም ሆነ፡፡›› (ሉቃ. ፪፥፲፬)

በዚህ ዓለም ላይ የሰው ልጆች ነጻነትን ፣ ምድርም ሰላምን ይፈልጋሉ ፤ የምድር ገዥዎች አነዚህን ጸጋዎች እናመጣለ አያሉ ተስፋ የሚሰጡ ቢሆንም በተግባር ማረጋገጥ ስላልቻሱ የሰው ልጆች በሕሊና እስር፣ ምድርም በሁከት አያለፉ ነው ።

አኛ ግን አውነተኛውን ነጻነት አርሱም ለአግዚአብሔር ክብር መኖርን ፤ አውነተኛውን ሰላም ከራስ ጋር መስማማትን አናገኝ ዘንድ በዳዊት ከተማ መድኅን ክርስቶስ ተወልዶልናል።

መልካም በዓለ ልደት ይሆንልዎ ዘጓድ ምኞታችንን ስገልጽ በአክብሮት ነው!

በክርስቶስ ፍቅር!
አንድ ቀን አለ

ለዘመናት የጠበቅነው ወረፋ የሚደርስበት ፣ ስማችን ተጠርቶ የምንሸለምበት ፣ አደባባዩን የምንወርስበት ፣ ጥላቻን በፍቅር የምንለውጥበት ፣ ርግማኑ ቀርቶ ምርቃት የሚዘንብበት አንድ ቀን አለ ። ስህተታችን የሚታረምበት ፣ ውድቀታችን በትንሣኤ የሚለወጥበት ፣ ቀና ብለን የምንሄድበት ፣ በሕሊናችን ፊት ነጻነት የምናገኝበት ፣ ተስፋ ለቆረጡብን ተስፋ የምንሆንበት አንድ ቀን አለ ። የገፉን የሚያፍሩበት ፣ ስድብ የተለማመዱብን ምን ሆኜ ነበር? የሚሉበት ፣ የከሰሱን የሚመሰክሩበት ፣ ሞታችንን የተመኙ ዕድሜ ይስጣችሁ ብለው የሚመርቁበት አንድ ቀን አለ ። ያልተረዳናቸውን ሰዎች የምንረዳበት ፣ ስህተት የመሰለን እውቀታቸውን የምናከብርበት ፣ የእነርሱ መኖር ለእኛ በጣም የሚያስፈልግበት ፣ የወዳጅን ዋጋ የምናውቅበት አንድ ቀን አለ ። ያለፋን ኑሮ የሚሸነፍበት ፣ የተጫነን ደመና የሚገፈፍበት ፣ ሞት ሞት ያሰኘን ትግል ገለል የሚልበት ፣ የተሰናበትነውን ፍቅር ሰላምታ ሰጥተን የምንጀምርበት አንድ ቀን አለ ። ያስተማሩንን የምናመሰግንበት ፣ ያሳደጉንን የምናኮራበት ፣ ልጅነታችንን ያልናቁትን የምናከብርበት ፣ ልጄ ላሉን ልጅ የምንሆንበት አንድ ቀን አለ ። እንደ ኒቆዲሞስ በጨለማ ተምረን በገሀድ የምንሸኝበት ፣ ፍርሃታችንን የምንታዘብበት ፣ ከሰፈር ፍርድ የምንወጣበት ፣ የሰውን ሰውነቱን አቃለን ተስፋ ቢስ ባደረግንበት የምንጸጸትበት አንድ ቀን አለ ። ረሀባችን ዳርቻ ፣ ጥማታችን ድንበር የሚያገኝበት ፣ የሰው ያለህ እንዳላልን በሰው የምንከበብበት አንድ ቀን አለ ።

ትዕግሥቱን ቸል ብለን ፣ ቃሉን ተጋፍተን ፣ ፍርድ እንደሌለ ራሳችንን አሞኝተን የተጓዝንበት መንገድ የሚቀጣበት አንድ ቀን አለ ። የተሰጠንን መብት ያባከንበት ፣ በረከታችንን ያድፋፋንበት ፣ ሥራችንን ያቃለልንበት ምርጫ የሚዳኝበት አንድ ቀን አለ ። በፈረድንበት ፍርድ የምንገኝበት ፣ “የወረወርሁት አንካሴ መልሶ ለራሴ” ብለን እያለቀስን የምንማርበት አንድ ቀን አለ ። የሚወዱንን መለየት አቅቶን የሚጠሉንን ለማሳመን የሮጥንበት ፣ የወደድነውን አጥተን የጠላነውን የምንቀላውጥበት አንድ ቀን አለ ። የማይሞቱ መስለውን ያሳዘናቸው ወላጆቻችን ፣ ሲፈልጉን የራቅናቸው ወዳጆቻችን ምነው ዛሬ ባገኘኋቸው ብለን የምናጣበት አንድ ቀን አለ ። ተባብረን ምስኪኑን ያጠቃንበት ፣ አድማው ፈርሶ እርስ በርስ የምንበላላበት አንድ ቀን አለ ። ሥልጣን አገኘሁ ብለን ደጉን የገፋንበት ፣ አውርቶ አደሮችን ያከበርንበት እንደ ሥዕል የሚመጣበት ፣ እየተገረፍን የምንማርበት አንድ ቀን አለ ።

በቁመናቸው ያልሰማናቸውን ፣ ጥበባቸውን ጋርደው ያለፉትን ፣ ምነው ባልተማርሁ ብለው የተጸጸቱትን አዋቂዎች መቃብራቸውን ይቅርታ የምንጠይቅበት አንድ ቀን አለ ። ወገን ለይተን ያሳደድናቸውን ፣ ዘረኛ ሆነን ያፈረስናቸውን ፣ ሕፃናትን ሳይቀር የጠላንበትን ያንን ክፉ አእምሮአችንን የምንወቅስበት አንድ ቀን አለ ። የማንሞት መስሎን የገደልንበትን ፣ የማናጣ መስሎን የቀማንበትን ፣ የማንዋረድ መስሎን ያዋረድንበትን ፣ የማያልፍ መስሎን ሰባሪ ቃል የተናገርንበትን በእጥፍ የምንሸከምበት አንድ ቀን አለ ። ትዕግሥተኛው አምላክ ፈራጅ ነው ፣ ፈራጁም መሐሪ ነው ።

አልገባ ያለን እውቀት እንደ ቀትር በነፍሳችን ላይ የሚበራበት ፣ የተሰወረ ጥበብ ገንዘባችን የሚሆንበት ፣ መጋረጃው ተቀዶ እግዚአብሔርን ፊት ለፊት የምናይበት አንድ ቀን አለ ። ፈርተን እንዳላነጋን በዕረፍት የምንተኛበት ፣ ተሸማቀን እንዳልተሰማራን በእምነት የምንወጣበት ፣ እንዳላቀረቀርን ቀና የምንልበት አንድ ቀን አለ ። እግዚአብሔር እኛን የሚጎበኝበት ፣ ከተራብንበት ቤት የምንጠግብበት ፣ የተሸከሙንን የምንሸከምበት ፣ ያከበሩንን የምናከብርበት ፣ የዋሉልንን የምናደንቅበት አንድ ቀን አለ ። ቀን የእግዚአብሔር ባሪያ ነው ። ቀኑን ለእኛ የሚያስገዛበት ፣ ያለፉ ወራቶች የሚካሱበት አንድ ቀን አለ ። ሃምሳ ዓመት ዘርተን ያላጨድነውን በሃምሳ ደቂቃ የምናጭድበት ፣ እግዚአብሔር ሲዋጋ በዝማሬ የምንቆምበት አንድ ቀን አለ ። እንደ ሰው የምንቆጠርበት ፣ ተሸልመን በጸጋው የምንከብርበት አንድ ቀን አለ ። እዚች ቀን ለመድረስ አንደበታችንን እንጠብቅ ። ይህችን ቀን ለማየት ከፈለግን የነቢዩን ምክር እንስማ፡- “ሕይወትን የሚፈቅድ ሰው ማን ነው ? በጎንም ዘመን ለማየት የሚወድድ ? አንደበትህን ከክፉ ከልክል ፥ ከንፈሮችህም ሽንገላን እንዳይናገሩ ። ከክፉ ሽሽ መልካምንም አድርግ ሰላምን እሻ ተከተላትም ።” (መዝ. 33 ፡ 12-14) ።

ዲ.አ.መ
ታኅሣሥ 4 ቀን 2018 ዓ.ም.

https://t.me/orthodoxy_life
ከማር የሚጣፍጥ፣ ከሽቶ የሚወደድ ስም፤ ኢየሱስ!

በዚህ ዓለም ላይ እንደ ኢየሱስ ስም ያለ ጣፋጭና ኃያል ስም የለም። ይህ ስም የነፍስ መድኃኒት፣ የልብ ሰላም ነው!

ምድራዊ ማር ምላስን ብቻ ያጣፍጣል፤ "ኢየሱስ" የሚለው ስም ግን መራራውን ሕይወታችንን ወደ ጣፋጭነት ይለውጣል። በኀዘን ለተሰበረ ልብ ብርታትን፣ ለደከመች ነፍስ ኃይልን ይሰጣል።

ምድራዊ ሽቶ መዓዛው ውሎ ያድራል፤ የጌታ ስም ግን ለዘላለም የማይጠፋ፣ የኃጢአትን ሽታ አስወግዶ ቅድስናን የሚያለብስ የሕይወት መዓዛ ነው።

ሙሽራይቱ ቤተክርስቲያን ሳትጠራው ውላ አታድርም "ስምህ የሚጣፍጠው ኢየሱስ" ትለዋለች። ዛሬ ደግሞ በትንቢቱ መሠረት በቤተ መቅደስ "ኢየሱስ" ተብሎ የተጠራበት ዕለት ነው

ዕፍረት ዘተሰውጠ ስምከ/ ስምህ እንደሚፈስ ሽቱ ነው መኃ 1÷3

መ/ር ብርሃኑ ተክለያሬድ