Isaiah 48 Apologetics
4.81K subscribers
60 photos
11 videos
22 files
247 links
✟ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! ✟

"14 The grace of the Lord Jesus Christ, and the love of God, and the communion of the Holy Ghost, be with you all. Amen."
(2Corinthians 13:14)

📌 ሌላኛው ቻናላችን:- @ovadiah
Download Telegram
✍️ በእስላማዊ ምንጮች መሠረት አለም ሁሉ ለመሐመድ እንደተፈጠረና፥ በመጨረሻውም ቀን በአላህ ዙፋን ላይ እንደሚቀመጥ ያውቁ ኖሯል?

ትክክለኛው የሙስሊሞች አምላክ መሐመድ ነው የምንለው በምክንያት ነው...!

https://answeringislamblog.wordpress.com/2021/10/08/muhammads-enthronement-and-mediation/
<<የመስዋዕቱ ልጅ ኢስሐቅ ወይስ ኢስማኢል?>>
የኡስታዙ ድርሳነ ባልቴት(ተረተረት)

ኢድ አል አድሃ(عيد الأضحى) ኢድ(عيد) ማለት በአል፣ ድግስ ወይም ለመታሰቢያነት የሚከበር ነገር ማለት ሲሆን አድሃ (أضحى) ወይም ቁርበን (قربان) ወይም ደግሞ የእብራይስጡ አቻ ቃል ቆርባን(קׇרְבָּן) ማለት "መስዋዕት/መባ" ማለት ነው። ኢድ አል አድሃ ሁለተኛው የሙስሊም ወገኖቻችን ክብረ በአል ነው። በዚህም ክብረ በአል ሙስሊም ወገኖቻችን ለመስዋዕትነት የሚሆነውን የበግ፣ የግመል፣ የፍየል ወየም የጠቦትን...ወዘተ የመሳሰሉትን የእንስሳትን ደምን ያፈሳሉ። የበአሉ እርሾ ወይም ጅማሮ በቁርአን ውስጥ የኢብራሂም(ዐሰ) ልጁን ለአምላኩ ለመሰዋት የታዘዘበትን ቀን ለማሰብ ሲባል የሚከበር በአል ነው። በቁርአን ላይ አላህ በሱረቱ አልሷፍፋት (የተሰላፊዎቹ ምዕራፍ) ላይ ስለ ተሰላፊዎች እምነት በሚናገርበት ክፍል በቁጥር 83 ላይ ከአማኞች መካከል የሆነው ኢብራሂም (ዐሰ) አንደኛው እንደሆነ ይናገራል። በዛው ክፍል በቁጥር 100 ላይ ደግሞ ኢብራሂም (ዐሰ) አንድን ጸሎትን ሲጸልይ እንመለከታለን፦

♦️As-Saffat 37:100
ጌታዬ ሆይ! #ከመልካሞቹ_የሆነን ( #ልጅ) #ስጠኝ፡፡(رَبِّ هَبْ لِى مِنَ ٱلصَّٰلِحِينَ)

የኢብራሂምም አምላክም ታጋሽ በሆነ ወጣት ልጅም ባሪያውን አበሰረው። ኢብራሂም (ዐሰ) ከባዱ ፈተና የሚጀምረው በቁጥር 102 ላይ ነው። አምላኩ የሰጠው ልጅ ለስራ በደረሰ ጊዜ ኢብራሂም (ዐሰ) በራዕይ አንድ ልጁን እንደሚያርድ ሁኖ ያልማል። እርሱም ለልጁ ስለ ራዕዩ ምን እንደሚያስብ በጠየቀው ጊዜ <<..የታዘዝከውን ሥራ..>> ብሎ ሲፈቅድለት እንመለከታለን።

<<አሁን ዋናው ጉዳይና ጥያቄ ያ ለኢብራሂም (ዐሰ) የተበሰረው የመስዋዕቱ ልጅ ማነው❗️የሚለው ንግርት ነው>>

የዘመናችን የሙስሊም ኡስታዞች ሽንጣቸውን ገትረው በመከራከር በቁርአኑ ላይ የመስዋዕቱ ልጅ #ኢስማኢል ለማስመሰል የቁርአኑን አያህ የማይቀባቡት ነገር የለም። ከሁሉም በላይ ደግሞ #አጃኢብ የሚያስብለው ጥርት እና ጥንፍፍ ብሎ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተነገረለትን የቃል ኪዳን ልጅ ይስሐቅን በእስማኤል ተክተውና አንሻፈው የመስዋዕቱ ልጅ እስማኤል እንደሆነ መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል ማለታቸው ነው። "...ጅልና ወረቀት..." እንደሚሉት አበው በእኛ ዘንድ የሙስሊም ኡስታዞቻቸው የጅል ዜማ መስማቱ የተለመደ ነው። ሲጀመር ኡስታዞቹ የማይሆን የማይሆን የሙግት ነጥቦቻቸውን እየሰካኩ ለሙስሊሙ ተደራሲያን እየፈተፈቱ ሲያጎርሷቸው እኛንም (የክርስቲያኑን ማህበረሰብ) ለማታለል መጣጣራቸው ሳስብ ይገርመኛል። ለማንኛውም የኡስታዞቻቸውን ድርሳነ ባልቴት ወይም የአሮጊቶች ተረት የሆነውን የሙግት ሐሳባትን በሁለት ጎራዎች ከፍለን ስለ መስዋዕቱ ልጅ ማንነት እንመለከታለን፦

<< የቁርአናዊ ሙግት >>
በመጀመሪያ ኢስማኢል ነብይ መሆኑ ለመስዋዕትነት የተዘጋጀው ልጅ እርሱ ነው የሚያስብለን አንድምታ የለም። ምክንያቱም እንዲሁ ኢስሐቅም ነብይ መሆኑን ቁርአናቸው ይነግረናል(Al-'Ankabut 29:27)።[1] ስለዚህ ስለ ኢስማኢል ነብይነት መጥቀስና ማጠቃቀስ ጉንጭ ማልፋት ካልሆነ በስተቀር ለሙግቱ እንብዛም ውጤት የለውም። ለማንኛውም ኡስታዞቹ ያነሷቸውን ዋና ዋና ነጥቦችን እንመለከታቸዋለን።

<< #ነጥብ_አንድ_ቀጠሮ_አክባሪው>>
የሙስሊም አቃብያነ እምነት ዘቦች ነን የሚሉት የዘመናችን አብዱሎች በሱረቱ መርየም 54 ላይ የተጠቀሰውን ክፍል ከሱረቱ አልሷፍፋት 102 ጋር በማጣመር የተሳሳተ ምስስሎሽን (wrong analogy) በመፍጠር ለመስዋዕትነት የቀረበው ኢስማኢል መሆኑን ለማሳየት ሞክረዋል። ነገር ግን በክፍሉ ላይ አውዳዊ ምልከታ ስናደርግ ሙግታቸው የሚያስኬድ ሁኖ አናገኘውም፦

♦️Maryam 19:54
በመጽሐፉ ኢስማዒልንም አውሳ፡፡ እርሱ ቀጠሮን አክባሪ ነበረና፡፡ መልክተኛ ነቢይም ነበር፡፡(وَٱذْكُرْ فِى ٱلْكِتَٰبِ إِسْمَٰعِيلَۚ إِنَّهُۥ كَانَ صَادِقَ ٱلْوَعْدِ وَكَانَ رَسُولًا نَّبِيًّا )

በዚህ ክፍል ላይ አላህ የኢብራሂምን ልጅ ኢስማኢልን ሲያመሰግነው እንመለከታለን። ኢስማኢል የአረቦች ሁሉ አባት ነበር። በተጨማሪም እርሱ ለቃለ ማሐላው እውነተኛና ታማኝ እንደነበር የሙስሊም ሊቃውንት ይናገራሉ።[2] የክፍሉን አውደ ሕታቴ ለመረዳት ቁጥር 55ን መመልከቱ አስፈላጊ ነው፦

♦️Maryam 19:55
ቤተሰቦቹንም በሶላትና በዘካ ያዝ ነበር፡፡ እጌታውም ዘንድ ተወዳጅ ነበር፡፡(وَكَانَ يَأْمُرُ أَهْلَهُۥ بِٱلصَّلَوٰةِ وَٱلزَّكَوٰةِ وَكَانَ عِندَ رَبِّهِۦ مَرْضِيًّا )

ኢስማኢል በጌታው ዘንድ ተወዳጅ የሆነበትና ከላይ ደግሞ አላህ ኢስማኢልን እንዲያስቡ ለምእመናን ሲናገር በኢስማኢል የግብር ጉዳር ረገድ መሆኑ ግልጽ ነው። ኢስማኢል ለአላህ ለሆኑ ስራዎች ላይ ታማኝና አክባሪ ነብይ መሆኑን ከክፍሉ አውድ መረዳት እንችላለን። እንደውም የእንግሊዘኛው ትርጉም ቁጥር 54ን የሚገልጸው <<he was true to his promise>> ለቃለ መሐላው እውነተኛ ወይም ታማኝ እንደሆነ በሚያሳይ መልኩ ነው።

And mention in the Book, Ishmael. Indeed, #he_was_true #to_his_promise, and he was a messenger and a prophet./English - Sahih International (Maryam 19:54)/

በተጨማሪም ኢብን ጁረይጅ ስለ ኢስማኢል ሲናገሩ፦
"He did not make any promise to his Lord, except that he fulfilled it./የሚፈጽመውን ካልሆነ በቀር ኢስማኢል ምንም አይነት ቃለ መሐላ ለጌታው አይገባም "Ibn Jurayj

ስለዚህ ኢስማኢል ለቃለ መሐላው እውነተኛ፣ ታማኝና አክባሪ መሆኑን
የሱረቱ መርየም ቁጥር 54 አውዳዊ አንድምታው ፍንትው አድርጎ ያሳያል። ቀጠሮ ከሚለው ፍታቴ ይልቅ ቃለ መሐላ ወይም ቃልኪዳን(promise) እንደሆነ የክፍሉ ዙሪያ ገባ ይነግረናል። <<ቀጠሮውን አክባሪ>> የሚለው ኃይለቃል በተጨማሪም የማያስኬደው በመጀመሪያ አላህ በሱረቱ አልሷፍፋት 102 ላይ ራዕይን ያሳየው ለኢብራሂም (ዐሰ) እንጂ ለልጆቹ ለኢስሐቅ ወይም ለኢስማኢል ፈጽሞ አይደለም።

فَلَمَّا بَلَغَ مَعَهُ ٱلسَّعْىَ قَالَ يَٰبُنَىَّ إِنِّىٓ أَرَىٰ فِى ٱلْمَنَامِ أَنِّىٓ أَذْبَحُكَ فَٱنظُرْ مَاذَا تَرَىٰۚ قَالَ يَٰٓأَبَتِ ٱفْعَلْ مَا تُؤْمَرُۖ سَتَجِدُنِىٓ إِن شَآءَ ٱللَّهُ مِنَ ٱلصَّٰبِرِينَ
ከእርሱ ጋርም ለሥራ በደረሰ ጊዜ «ልጄ ሆይ! እኔ በሕልሜ እኔ የማርድህ ሆኜ አያለሁ፡፡ ተመልከትም፤ ምን ታያለህ?» አለው፡፡ «አባቴ ሆይ! የታዘዝከውን ሥራ፡፡ አላህ ቢሻ ከታጋሾቹ ሆኜ ታገኘኛለህ» አለ፡፡

በተጨማሪም አላህ የመስዋዕቱን ቀጠሮ የሰጠው ለአባቱ ለኢብራሒም(ዐሰ) እንጂ ለልጁ አልነበረም። ምክንያቱም የራዕዩና የትእዛዙ አክባሪ አባቱ እንጂ ልጁ አይደለም። በተጨማሪም በቀጠሮው ቀን ለመሰዋት ልጁን የወሰደው አባትየው እንጂ ልጁ አይደለም። ስለዚህ ለመስዋዕትነት የተቀጠረው ኢስማኢል የቀጠሮው አክባሪ ነበር የሚለው አንድምታ ኪስ ወለድ እንጂ አውዳዊ አለመሆኑን ለመረዳት አያዳግትም።
<< #ነጥብ_ሁለት_የኢብራሒም_ጸሎት >>
ሌላው የሙግት ነጥብ ብለው የሚያቀርቡት ደግሞ "ኢስማኢል/إِسْمَٰعِيْل" ማለት "አምላክ ይሰማል" ማለት ስለሆነ ኢብራሒም ደግሞ በቁጥር 100 ላይ ወደ አላህ በጸለየው መሰረት ልጅን ሰጠው የሚል ነበር። ነገር ግን ከአውዱ ተነስተን ስንመለከት አላህ ለኢብራሒም በጸሎቱ መሰረት የተሰጠው ልጅ ኢስሐቅ እንጂ ኢስማኢል እንዳልሆነ እንረዳለን። ሲጀመር ኢስሐቅ(إسحاق) ወይም በእብራይስጥ ይሽሐቅ(יִשְׂחָק) ደስታ፣ ሳቅ ወይም ብስራት ማለት ነው። በቁጥር 100 ላይ ነብዩ ኢብራሂም(ዐሰ) <<ጌታዬ ሆይ! ከመልካሞቹ የሆነን (ልጅ) ስጠኝ(رَبِّ هَبْ لِى مِنَ ٱلصَّٰلِحِينَ)>> ብሎ ከጸለየ በኋላ፤ በቁጥር 101 ላይ ጌታውም <<ታጋሽ በሆነ ወጣት ልጅም አበሰርነው (فَبَشَّرْنَٰهُ بِغُلَٰمٍ حَلِيمٍ)>> ብሎ ሲናገር እንመለከታለን። አስተውሉ! የጌታው መልስ ላይ << #አበሰርነው>> የሚለውን ቃል ከኢስሐቅ ጋር እንጂ ከኢስማኢል የስም ትርጉም ጋር ፈጽሞ የሚገናኝ አይደለም። እንደውም ስለ ልጁ ማንነት በዛው ሱራ በቁጥር 112 ላይ ግልጽ አድርጎ የብስራቱ ልጅ ኢስሐቅ እንደሆነ ይነግረናል << #በኢስሐቅም #አበሰርነው፡፡ ከመልካሞቹ የሆነ ነቢይ ሲሆን(وَبَشَّرْنَٰهُ بِإِسْحَٰقَ نَبِيًّا مِّنَ ٱلصَّٰلِحِينَ) >>
በተጨማሪ በሱረቱ ሁድ 11፡69-71 ያለውን ክፍል ስንመለከት በቁጥር 101 ላይ <<ታጋሽ በሆነ ወጣት ልጅም አበሰርነው>> የሚለው ንግግር ለኢስሐቅ መሆኑን ግልጽ የሚያደርግ ክፍል ነው።

11:69 - መልክተኞቻችንም ኢብራሂምን #በ(ልጅ) #ብስራት በእርግጥ መጡት፡፡ ሰላም አሉት፡፡ ሰላም አላቸው፡፡ ጥቂትም ሳይቆይ ወዲያውኑ የተጠበሰን የወይፈን ስጋ አመጣ፡፡
11:70 - እጆቻቸውም ወደ እርሱ የማይደርሱ መኾነቸውን ባየ ጊዜ ሸሻቸው፡፡ ከነሱም ፍርሃት ተሰማው፡፡ «አትፍራ እኛ ወደ ሉጥ ሕዝቦች ተልከናልና» አሉት፡፡
11:71 - ሚስቱም የቆመች ስትኾን (አትፍራ አሉት) ሳቀችም፡፡ #በኢስሐቅም አበሰርናት፡፡ ከኢስሐቅም በኋላ (በልጁ) በያዕቁብ (አበሰርናት)፡፡

#ነጥብ_ሶስት_ከኢስሐቅ_ሌላ_አካል
በዚህኛው የሙግት ሐሳብ ላይ ደግሞ
በቁጥር 112 <<በኢስሐቅም አበሰርነው፡፡ ከመልካሞቹ የሆነ ነቢይ ሲሆን>> በሚለው ክፍል ላይ በኢስሐቅም ስለሚል "-ም" የምትለው ጥገኛ ምእላድ ከኢስሐቅ ተጨማሪ ሌላ አካል እንዳለ ያመለክታል የሚል ሙግት ነው። ነገር ግን ይሄ ሐሳብ ፈጽሞ የሚያስኬድ አይደለም። አብዱሉ በክፍሉ ላይ ሁለት ልጅ የተባሉ አካላት እንዳሉ ይናገራል። <<የመጀመሪያው ታጋሽ በሆነ ወጣት ልጅም ሲሆን ሁለተኛው በኢሥሐቅ>> ብሎ ከፋፍሎ እንመለከታለን። እንደዛ ከሆነ የሙግቱ ሃሳብ አጠያያቂ ይሆናል። ምክንያቱም በእርሱ ሎጂክ ከሄድን በቁጥር 101 ላይ አላህ ለኢብራሒም <<ታጋሽ በሆነ #ወጣት #ልጅም አበሰርነው (فَبَشَّرْنَٰهُ بِغُلَٰمٍ حَلِيمٍ )>> በሚለው አንቀጽ ላይ #ወጣት_ልጅም በሚለው ኃይለ ቃል ይሰመርበት "-ም" የምትለው ምእላድ አሁንም በእነርሱ ሎጂክ ኢስማኢል ነው ብለው ከሚያምኑት አካል ሌላ ከእርሱ በፊት የተጠቀሰ አካል አለ እያሉን እንደሆነ አንባቢ ልብ ይበለው። ያ አካል መቼም ኢስሐቅ ነው እንዳይሉ በእነርሱ አባባል ገና በቁጥር 112 ላይ ዘግይቶ የተጠቀሰ መሆኑ ግልጽ ነው። በቁጥር 112 ላይ << #በኢስሐቅም>> ሲል ከእርሱ በፊት የተጠቀሰው አካልን (ወጣት ልጅ) የሚያመለክት ከሆነ በቁጥር 101 ላይ << #ወጣት_ልጅም>> ሲለን ማንን ይገልጻል እያሉን እንደሆነ ጥያቄውን ለአብዱሎቹ ትተነዋል። ነገር ግን "-ም" የምትለው ጥገኛ ምእላድ ከተጨማሪ አካል ከመግለፅ ባሻገር አንድን ነገር ትኩረት(emphasis) ለመስጠት እንደምትገባ መረዳት ይኖርብናል።

በመጨረሻም የሙስሊም አቃብያነ እምነት ተሟጋቾች ለመስዋዕትነት የቀረበው ኢስማኢል መሆኑን እንኳን በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ለማረጋገጥ ይቅርና በራሳቸው መጽሐፍ በቁርአኑ ላይ ማረጋገጥ ፈጽመው አይችሉም። ጥንታዊያን ሙስሊም ሊቃውንት ለመስዋዕት በቀረበው ልጅ ማንነት ዙርያ ስምምነት የላቸውም፡፡[3] እውቅ ጥንታዊ የሙስሊም ሊቃውንቶች ለምሳሌ ኢብን ቁጠይበኽ እና አል ጠበሪ የመሳሰሉ የሙስሊም ሊቃውንቶች ሱራ 37፡100-107 በሚያብራሩበት አንድምታ ላይ የመስዋዕቱ ልጅ ይስሐቅ መሆኑን ጽፏል።[4] ሌሎች የቁርአን እውቅ ሙፈሲሮችም እንደ ኢብን አባስ[5] እና እንደ ሁለቱ ጃለሎችም[6] ያሉ የሙስሊም ሊቃውንቶች ለመስዋዕት በቀረበው ልጅ ማንነት ዙርያ ግልጽ የሆነ እና ተመሳሳይ አቋም የላቸውም። አንዳድ ሐዲሳትም ጭምር ለመስዋዕትነት የቀረበው ልጅ ኢስሐቅ እንደሆነ ይናገራሉ፦

“ሙሐመድ ኢብን አል-ሙንተሸር እንዳስተላለፈው አላህ ከጠላቶቹ ቢታደገው ራሱን ለመሰዋት ስዕለት የተሳለ አንድ ሰው ነበረ፡፡ ኢብን አባስን ለምክር በጠየቀው ጊዜ መስሩቅን እንዲያማክረው ነገረው፡፡ እርሱን ባማከረ ጊዜ እንዲህ የሚል ምላሽ ሰጠው፡- ‹‹ራስህን አትሰዋ ምክንያቱም አማኝ ከሆንክ አማኝ ነፍስ ትገድላለህና ከሃዲ ከሆንክ ደግሞ ወደ ገሃነም ትፈጥናለህና፤ ነገር ግን በግ በመግዛት ለድኾች ስትል መስዋዕት አድርግ ምክንያቱም ይስሐቅ ካንተ የተሻለ ሆኖ ሳለ በበግ ተዋጅቷልና፡፡›› ጉዳዩን ለኢብን አባስ ባወጋው ጊዜ ‹‹እኔም ልነግርህ የፈለኩት ውሳኔ ይኸው ነበር›› በማለት መለሰለት፡፡”------(ሚሽካት አል-መሳቢህ)[7]

ለተጨማሪ ማብራሪያ እና ማጣቀሻ ከእውነት ለሁሉ ድረገጽ ላይ( http://www.ewnetlehulu.org/am/our-answers/hasentaju/ch5_2/) ይመልከቱ።

ስለዚህ የሙስሊም አቃብያነ እምነት ነን ባይ ኡስታዞች በባዶው ወደ መጽሐፍ ቅዱስ ዘለው ከሚገቡ ይልቅ መጀመሪያ ከቁርአናቸው በመነሳት ሙግታቸውን በማረቅ፣ በማረምና ወጥነት በማስያዝ ቢጀምሩ የተሻለ ይመስለኛል። በክፍል ሁለት መጽሐፍ ቅዱሳዊ ሙግት ብለውያነሷቸውን አስቂኝ የሙግት ነጥቦች ምልከታና ትችቶችን ከእርምታዊ ማብራሪያዎች ጋር የምንቃኝ ይሆናል። ለማንኛውም ለመላው የሙስሊም ተከታዮች የ1443ኛው ኢድ አል አድሓ በዓልን ከቀድሞው የሞኝነትና ሐሰተኛ አስተምህሮ ተላቅቃችሁ እውነትን ከመጽሐፍ ቅዱስ እንድትማሩ እንጋብዛችኋለን🙏
Jonathan(Yeshua Apologetics)
🔖ማጣቀሻዎችና ማስፈንጠሪያ
[¹] Lives of the Prophets, L. Azzam, Isaac and Jacob^ Storie
[²] Tafsir ibn Kathir 19:54
[³] Gibb and Kramers. A Shorter Encyclopaedia of Islam; p. 175
[⁴] Al-Tabari. The History of al-Tabari, Vol. II, Prophets and Patriarchs, trans. William M. Brenner [State University of New York Press, Albany 1987], p. 89)
[⁵] anwîr al-Miqbâs min Tafsîr Ibn ‘Abbâs; Online Edition:
http://altafsir.com/Tafasir.asp?tMadhNo=0&tTafsirNo=73&tSoraNo=37&tAyahNo=102&tDisplay=yes&UserProfile=0
[⁶] Tafsir al-Jalalayn; Online Edition: http://altafsir.com/Tafasir.asp?tMadhNo=0&tTafsirNo=74&tSoraNo=37&tAyahNo=107&tDisplay=yes&UserProfile=0
[⁷] Mishkat Al-Masabih English Translation With Explanatory Notes by Dr. James Robson, Volume I [Sh. Muhammad Ahsraf Publishers, Booksellers & Exporters, Lahore-Pakistan, Reprint 1990], p. 733
📜 የጳውሎስ መልእክት 📜

እግዚአብሔር ሀሳቡን ከገለጠባቸው መንገዶች አንዱ በሰዎች ባህል፣ ስርዓት፣ ቋንቋና ትውፊት በመጠቀም ነው። የመልእክቱም ተቀባዮች/ነብያቶች ፣ሐዋርያት፣ መልእክተኞችና ወንጌላውያን.....ወዘተ/ የተገለጠላቸውን መልእክትና አምላካዊ አስተምህሮ በራሳቸው ቋንቋና ባህል በተለያየ መንገድ አብራርተው ለተደራሲያኖቻቸው የእግዚአብሔርን ሀሳብ በሚገባ ገልጠዋል። ከእነዚህም አንዱ ሐዋርያው #ጳውሎስ(ፓውሎስ/Παῦλος) ነው። ሐዋርያው ጳውሎስ የእግዚአብሔርን ሐሳብ በመልእት መልኩ አስተላልፏል። ስለዚህም መልእክቶቹ የመጽሐፍ ቅዱስ አካል ሊሆኑ ችለዋል። የሐዋርያው ጳውሎስን መልእክቶች ስንመለከታቸው እያንዳንዳቸው ጥቅል ስነ መለኮታዊ መገለጦችን የያዙ ናቸው። የጳውሎስ መለኮታዊ መልእክቶች ጥልቅ ሲሆኑ እግዚአብሔር ሃሳቡን በጳውሎስ በኩል ለሰዎች ሁሉ ሲያስተላልፍ ጳውሎስ የተገለጠለትን ጥልቅ መለኮታዊ ሃሳብን ለተደራሲዎቹ ለማስረዳት ከግል ሰላምታ ጀምሮ ተደራሲዎቹን በጸሎት ወደ እግዚአብሔር እስከማቅረብ ድረስ አስፍሯል። በዚህም ክርስቲያናዊ ሰላምታ መልእክትና የእርስ በርስ/የአንድ አካል/ መመጋገብና መግባባት ምን መምሰል እንዳለበት የሚያስረዳ ነው። ቅዱስ ጳውሎስ <በገዛ እጄ> ሲል የራሱ ልበ ወለዳዊ ጽሑፍ ማለቱ ሳይሆን እግዚአብሔር አምላክ መልእክቱን በራሱ ቅዱስ ጳውሎስ አማካኝነት ሀሳቡን ማስተላለፉን የሚናገር ነው። ይሄም ማለት የደብዳቤዎቹ ጸሐፊ ቅዱስ ጳውሎስ መሆኑን ያሳያል፦
“እኔ ጳውሎስ ይህን ሰላምታ በገዛ እጄ ጽፌአለሁ።”
— 1ኛ ቆሮንቶስ 16፥21
“በገዛ የተጻፈ የእኔ የጳውሎስ ሰላምታ ይህ ነው። እስራቴን አስቡ። ጸጋ ከእናንተ ጋር ይሁን።”
— ቆላስይስ 4፥18

በመሆኑም መልእክቶቹ ወደ እያንዳንዳችን የተላኩ የእግዚአብሔር መልእክታት ናቸው። ጳውሎስም በመልእክታቱ መጀመሪያ ላይ "...ሐዋርያ የሆነ..." ወይም "...የኢየሱስ ክርስቶስ ባርያ የሆነ..." የሚሉ ቃላቶችን መጠቀሙ መልእክቱ የግሉ ሳይሆን መለኮታዊ መሆኑን አስቀድሞ መናገሩ እንመለከታለን። ሐዋርያ(አፖስቶሎስ/ἀπόστολος) ማለት "#በጌታ #የተላከ_መልእክተኛ" ማለት ሲሆን "ባሪያ (ዱሎስ/δοῦλος)" ማለት ደግሞ በፈቃዱ ራሱን ለጌታው ያስገዛ፤ ለጌታው ክብር የሚኖር የራሱ ቃል የሌለውና ጌታ እንዲህ ብሏል የሚል ነው። በዚህ ረገድ መልእክቱን ለማስተላለፍ የራሱ ቋንቋ፤ ባህልና ስርአት የመጠቀም ነጻነት ጳውሎስ ከጌታ ዘንድ ቢኖረውም መልእክቱና አስተምህሮቱ ከእግዚአብሔር መለኮታዊ መልእክት የሚንጻረር ወይም ያፈነገጠ መልእክት አያስተላልፍም። አንዳንድ ጊዜም ሐዋርያቶች በነጻ ማለትም ለአገልግሎታቸው ምንም ክፍያ ሳያገኙ የእግዚአብሔርን ወንጌል ያለ ደመወዝ በመስበክ ያገለግላሉ። እዚህ ጋር ልብ ማለት ያለብን #የእግዚአብሔርን #ወንጌል እንጂ የየራሳቸውን ወንጌል የሚያስተላልፉ አገልጋዮች አይደሉም። በግሪኩ ቶው ቴው(τοῦ #θεοῦ) የሚለው ቃል በባለቤትነት አመልካች ሙያ መምጣቱን አንባቢ ልብ ይሏል።
“ወይስ #የእግዚአብሔርን_ወንጌል (τοῦ #θεοῦ εὐαγγέλιον) ያለ ደመወዝ ስለ ሰበክሁላችሁ፥ እናንተ ከፍ እንድትሉ ራሴን እያዋረድሁ ኃጢአት አድርጌ ይሆንን?”
— 2ኛ ቆሮ 11፥7

አንዳንድ ጸረ-ክርስቶሳውያን የጳውሎስ መልእክተኛነትን እና ሐዋርያነትን በመካድ መልእክቶቹንም መለኮታዊነታቸውን በመሸምጠጥ የጳውሎስ ልቦለዳዊ ጽሁፎች በማለት የአላዋቂነታዊ ፈርጅን ያስቀምጣሉ። ከሳሾቹ አንድ ያላስተዋሉት ነገር ቢኖር የሐዋርያትነት አገልግሎት ምን እንደሚመስል አለማወቅ ላይ ነው። ሐዋርያነት ከጌታ የተቀበሉት ሙሉ ስልጣን እና ሹመት ነው/ሐዋ 1:17፤ ሐዋ26:16፤ ገላ2:8/። ተግባራቸውም በጌታ ዘንድ የተላኩትን መልእክት በራሳቸው ባህል እና ስርዓት ወይም በራሳቸው የመገለጥ ነጻነት ተጠቅመው ማስተላለፍ ነው። በመሆኑም ሐዋርያው ጳውሎስ እንደ ሐዋርያነቱ በሐዋርያዊ ስልጣን መሰረት መልእክታትን ለተደራሲያን አስተላልፏል።

እነዚሁ ጸረ-ክርስቶሳውያን የሚገርመው ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ መልእክተኛ አይደለም በማለት ከራሳቸውም አስተምህሮ ጋር የሚጋጭ የአላዋቂነት ወይም ለእውነታው እንቅፋትና መጋረጃ ለመሆን በሚፍጨረጨሩበት ጊዜ ከራሳቸው አስተምህሮት ጋር መጋጨታቸውን ያስተዋሉ አይመስሉኝም። ሆኖም ግን በታዋቂው ሙፈሲር ኢማም ኢብኑ ከሲር ተፍሲር ላይ #የአላህ_ባርያ እና #መልእክተኛም እንደነበር መስክረውልናል። ስለዚህ መልእክተኛ ከሆነ ከፈጣሪው መልእክት እና ትእዛዛት የሚያስተላልፍ ባሪያ ብቻ ነበር።

"...ከደማስቆ ሰዎች መካከል በመሲሁ ያመነ ዲና የተባለ ሰው ነበር። ጳውሎስ ከተባለ አይሁዳዊ ሸሽቶ ከትልቁ ቤተ ክርስቲያን አጠገብ በሚገኝ መቃብር ውስጥ ተሸሽጎ ነበር። ጳውሎስም መሲሁን እጅግ የሚጠላና ክፉ ሰው ነበር። የአጎቱ ልጅ (የአላህ ምህረት በእርሱ ላይ ይሁን) በመሲሁ በማምኑ ምክንያት ጸጉሩን ላጭቶት በከተማው መካከል እስኪሞት ድረስ በድንጋይ ወገረው። ከዚያም መሲሁ ወደ ደማስቆ እንዳቀና በሰማ ጊዜ በቀሎውን አዘጋጅቶ ሊገድለው ወደ ደማስቆ ወጣ። ኮኩባ በተባለ ቦታ የመሲሁን ተከታዮች ተገናኘ። በዚህን ጊዜ መልአክ ከሰማይ መጥቶ በክንፉ ፊቱን በጥፊ መታው። ይህንንም ሲመለከት መሬት ላይ ወደቀ። በመሲሁም አመነ። ወደ መሲሁ በመምጣት በእርሱ አመነ ላደረጋቸው ነገሮች ይቅርታ ጠየቀው። መሲሁም ተቀበለው። ፈጣሪ የማየት ብርሃኑን እንዲመልስለት ዓይኖቹን እንዲዳስስለት መሲሁን ለመነው። እርሱም በከተማችን በደማስቆ በስተምስራቅ ወደሚገኘው ገበያ ሂድ። እርሱ ይጸልይልሃል አለው። ሰውዬውም ጸለየለት ዓይኑም ተመለሰለት።
#ከዚህ_በኋላ_ጳውሎስ(ሰላም በእርሱ ላይ ይሁንና) በመሲሁ ላይ #ታላቅ እምነት ኖረው። #በዚህም_ምክንያት_የአላህ_ባርያ_እና_መልእክተኛ_ነው።..."
🖋ኢብን ከሲር ቀሰሱል አንቢያ ቅጽ 1 ገጽ 575

http://islamport.com/w/tkh/Web/2908/87.htm

Jonathan(Yeshua Apologetics)
ከዚህ በፊት ስለ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በእስልምና ምልከታ የተጻፉ ጠቃሚ ጽሑፎች
♦️ሐዋሪያው ጳውሎስ በእስልምና (ክፍል 1)
https://t.me/TheTriune/685

♦️ሐዋሪያው ጳውሎስ በእስልምና (ክፍል 2)
https://t.me/TheTriune/686

♦️ሐዋሪያው ጳውሎስ በእስልምና (ክፍል 3)
https://t.me/TheTriune/687
🚩 ክርስቶስ "አምላክ ነኝ" አላለምን?

የክርስቶስን አምላክነት በማይቀበሉ ወገኖች በስፋት ከሚነሱት ጥያቄዎች መካከል ቀዳሚው "የቱ ጋር ነው ክርስቶስ በራሱ አንደበት "እኔ አምላክ ነኝ" ያለው?" የሚለው ነው። ይህን ጥያቄ የሚያነሱ ወገኖች ክርስቶስ አንድም ጊዜ በራሱ አንደበት አምላክ ነኝ ብሎ አያውቅም ሲሉ ይሰማሉ። ክርስቲያኑም ይህንን ጥያቄ በተለያየ መልኩ ሲመልሰው ኖሯል

ነገር ግን እነዚህ ወገኖች ይህን አቋም ሲያራምዱ፥ አንድ የተሳሳተ ቅድመ ግንዛቤ ይዘው ነው። እርሱም ክርስቶስ አንድም ጊዜ በራሱ አንደበት አምላክ ነኝ ብሎ አያውቅም የሚለው ነው። እነዚህ ወገኖች አንድም ጊዜ ክርስቶስ በራሱ አንደበት አምላክ ነኝ ብሎ እንደማያውቅ በምን አወቁ?

ክርስቶስ በራሱ አንደበት አምላክ ነኝ አለማለቱን እንዴት እንዳወቁ ሲጠየቁ፥ መልሳቸው "በራሱ አንደበት አምላክ ነኝ ያለበት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ የለም" የሚል መልስ ይሰጣሉ። ማለትም፥ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አምላክ ነኝ ያለበት ቦታ ስላልተዘገበ፥ ብሎ አያውቅም የሚል ነው።

▶️ ይህ ግን እጅግ የተሳሳተ ቅድመ ግንዛቤ ነው። ምክንያቱም በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ (በተለይ በወንጌላት) ያልተዘገቡ፥ ነገር ግን ክርስቶስ የተናገራቸው ብዙ ነገሮች አሉ። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስላልተዘገበ፥ የሆነ ነገር አልተባለም ወይንም አልተዘገበም ማለት አይደለም። ክርስቶስ በምድር ሳለ የተናገራቸው፥ ነገር ግን በወንጌላት ያልተዘገቡ ነገሮች አሉና። ለምሳሌ፦

"እንዲሁ እየደከማችሁ ድውዮችን ልትረዱና እርሱ ራሱ። #ከሚቀበል ይልቅ #የሚሰጥ ብፁዕ ነው እንዳለ የጌታን #የኢየሱስን ቃል ልታስቡ ይገባችሁ ዘንድ በሁሉ አሳየኋችሁ።"
(የሐዋርያት ሥራ 20:35)

በዚህ ስፍራ ሐዋርያው ጴጥሮስ "ከሚቀበል ይልቅ የሚሰጥ ብፁዕ ነው" የሚለውን የጌታ የኢየሱስ ቃል ሲያሳስባቸው እንመለከታለን። በዚህ ቦታ ላይ ሐዋርያው ክርስቶስ ተናግሮታል ያለው ቃል በወንጌላት ተዘግቦ አይገኝም። ነገር ግን የእርሱ ሐዋሪያ የሆነው ጴጥሮስ እንደ እርሱ ቃል ጠቅሶታል። ይህ ክርስቶስ በወንጌላት ያልተዘገቡ ብዙ ነገሮችን እንደተናገረ ያሳያል። ሌላ ምሳሌ፦

"ከእርሱም የሰማናት ለእናንተም የምናወራላችሁ መልእክት። #እግዚአብሔር #ብርሃን #ነው ጨለማም በእርሱ ዘንድ ከቶ የለም የምትል ይህች ናት።"
(1ኛ የዮሐንስ መልእክት 1:5)

በዚህም ስፍራ፥ ሐዋርያው ዮሐንስ ከክርስቶስ የሰማውን መልእክት እንደሚያወራ ይናገራል። እርሱም፥ እግዚአብሔር ብርሃን እንደሆነና ጨለማ በእርሱ ዘንድ እንደሌለ ነው። በአራቱ ወንጌላት፥ ክርስቶስ ይህን ቃል ሲናገር አንመለከትም። ነገር ግን የእርሱ ሐዋርያ ከእርሱ የሰማው እውነተኛ መልእክት መሆኑን ተናገረ። ይህ ክርስቶስ በወንጌላት ላይ ያልተዘገቡ ብዙ ነገሮችን እንደተናገረ ያረጋግጣል።

"ኢየሱስም በዚህ መጽሐፍ #ያልተጻፈ ሌላ ብዙ ምልክት በደቀ መዛሙርቱ ፊት #አደረገ፤"
(የዮሐንስ ወንጌል 20:30)

በዚህም ቦታ ሐዋርያው ዮሐንስ ጌታ ኢየሱስ በዚህ መጽሐፍ (በዮሐንስ ወንጌል) ያልተጻፈ ሌላ ብዙ ምልክት እንዳደረገ ዘግቦልናል። ይህ ክርስቶስ በወንጌላት ያልተጻፉ ብዙ ነገሮችን እንዳደረገና እንደተናገረ ያረጋግጣል። ሁሉም የክርስቶስ ስራዎችና ንግግሮች አልተዘገቡም

"ኢየሱስም #ያደረገው ብዙ ሌላ ነገር ደግሞ አለ፤ ሁሉ በእያንዳንዱ #ቢጻፍ ለተጻፉት መጻሕፍት ዓለም ራሱ ባልበቃቸውም ይመስለኛል።"
(የዮሐንስ ወንጌል 21:25)

በዚሁ ስፍራም ሐዋርያው ዮሐንስ በምዕራፍ 20 ላይ የተጻፈውን ይደግመዋል። ክርስቶስ በወንጌል ላይ ያልተጻፉ ብዙ ነገሮችን አድርጓል። እርሱ የእግዚአብሔር ልጅ መሆኑን እንድናምን የሚበቃን ተጽፏል (ዮሐ 20:31) በተረፈ ግን ሌሎች ብዙ ስራዎቹና ንግግሮቹ አልተጻፉም። ይህ ክርስቶስ በወንጌላት ያልተጻፉ ብዙ ነገሮችን እንደተናገረ ያረጋግጣል

✏️ ስለዚህ ክርስቲያን ያልሆኑ አካላት፥ ወንጌላት ላይ ክርስቶስ በራሱ አንደበት አምላክ ነኝ ማለቱ ስላልተዘገበ ብቻ አላለም ማለት አይችሉም። ስላልተዘገበ ብቻ አላለም ማለት አይደለም። ክርስቶስ በወንጌላት ያልተዘገቡ ብዙ ነገሮችን ተናግሯልና

ተቺዎቹ ክርስቶስ አምላክ ነኝ ማለቱን አናውቅም ማለት ይችላሉ እንጂ፥ በእርግጠኝነት አላለም ማለት አይችሉም። አለማለቱን የሚያረጋግጥ ምንም አይነት ማስረጃ የለም። አለማለቱን የሚያሳይ ማስረጃ እስከሌለ ድረስ፥ አፋቸውን ሞልተው አላለም ማለት አይችሉም። በወንጌላት አለመዘገቡ፥ ላለማለቱ ማስረጃ አይደለምና።

መጽሐፍ ቅዱስ ወይ ቃል በቃል "ክርስቶስ አምላክ ነኝ አላለም" እስካላለ ድረስ ወይንም ደግሞ ብሎ እንደማያውቅ እስካላስተማረ ድረስ ወይንም ደግሞ ሊል እንደማይችል ከመጽሐፍ ቅዱስ ማረጋገጥ እስካልተቻለ ድረስ አምላክ ነኝ ብሎ አያውቅም ማለት አይቻልም። ይህ አይነቱ ማስረጃ እስካልቀረበ ድረስ፥ የሚቻለው አናውቅም ማለት ብቻ ነው።

♦️ ይህ የኢ-ክርስቲያናዊያንን ሙግት በይበልጥ ያደክመዋል። ምክንያቱም የክርስቶስ አይን እማኝ የሆኑት ሐዋርያት እግዚአብሔር መሆኑን መስክረዋል፥ ነቢያትም በትንቢታቸው የሚመጣው መሲህ አምላክ መሆኑን ተንብየዋል። ከሁሉም በላይ ደግሞ ክርስቶስ ራሱ፥ አምላክ ብቻ ያሉት ባህሪያት እንዳሉት ተናግሯል፥ መለኮት ብቻ ሊሰራቸው የሚችላቸውን ስራዎች ሰርቷል፥ እግዚአብሔር ብቻ ያሉት ስሞች እንዳሉት ተናግሯል። ይህ ከበቂ በላይ ማስረጃ ነው

ክርስቲያን ያልሆኑ ወገኖች ለተቃውሟቸው የሚያነሱት ሙግት በራሱ አንደበት አምላክ ነኝ ብሎ አያውቅም የሚል ነበር። ነገር ግን አሁን እንዳየነው፥ እንደዛ ማለቱን አናውቅም ማለት እንጂ አምላክ ነኝ ብሎ አያውቅም ማለት አይችሉም። ይህ የእነርሱን ተቃውሞ እጅግ ደካማ ያደርገዋል። ባለማወቅ ላይ የተመሰረተ ሙግት ነውና።

▶️ ስለዚህ የትኛውም የክርስቶስ ተቃዋሚ "ክርስቶስ አምላክ ነኝ ማለት አለማለቱን አናውቅም" እንጂ ማለት የሚችለው፥ አፉን ሞልቶ "አምላክ ነኝ ብሎ አያውቅም" ማለት አይችልም
🚩 እግዚአብሔር በፍጡር ምሏልን? (ክለሳ)

መጽሐፍ ቅዱስ እግዚአብሔር በየትኛውም ፍጡር እንደማይምል ያስተምራል።

"እግዚአብሔርም ለአብርሃም ተስፋ በሰጠው ጊዜ። በእውነት እየባረክሁ እባርክሃለሁ እያበዛሁም አበዛሃለሁ ብሎ፥ #ከእርሱ_በሚበልጥ_በማንም_ሊምል_ስላልቻለ#በራሱ_ማለ፤"
(ወደ ዕብራውያን 6:13-14)

ይህ የሆነበት ምክንያት፥ ማንም ከእርሱ ስለማይበልጥ እግዚአብሔር መኃላን ሲምል በራሱ ነው። እንጂ በየትኛውም ፍጡር አይደለም።

ነገር ግን ሙስሊሞችና ሌሎች የመጽሐፍ ቅዱስ ተቺዎች፥ እግዚአብሔር በፍጡር ምሎ ያውቃል በማለት ተቃውሞ ያነሳሉ፦

"እግዚአብሔር #በያዕቆብ_ክብር እንዲህ ብሎ #ምሎአል። ሥራቸውን ሁሉ ለዘላለም ምንም አልረሳም። "
(ትንቢተ አሞጽ 8:7)

አሞጽ 8:7 በመጥቀስ የያዕቆብ ክብር ፍጡር ነው፥ ስለዚህ እግዚአብሔር በእርሱ መማሉ በፍጡራን መማሉን ያሳያል ለማለት ይሞክራሉ። ይህ ፈጽሞ ስህተት ነው።

✍️ ምክንያቱም "የያዕቆብ ክብር" የሚለው ስያሜ የራሱ የእግዚአብሔር ስም ነው። በያዕቆብ ክብር እምላለሁ ሲል፥ እያመለከተ ያለው ራሱን ነው። ይህ ማለት እግዚአብሔር በራሱ ነው እየማለ ያለው ማለት ነው

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ፥ እግዚአብሔር በተደጋጋሚ ራሱን ከእስራኤል ሕዝብ ጋር በተያያዘ ስያሜ ሲጠራ እንመለከታለን። ለእስራኤል እርሱ የሆነውን ነገር፥ እንደ ስያሜ ያውለዋል

ለምሳሌ

"የአባቴ የአብርሃም አምላክ #የይስሐቅም #ፍርሃት ከእኔ ጋር ባይሆንስ ዛሬ ባዶ እጄን በሰደድኸኝ ነበር፤ እግዚአብሔር መከራዬንና የእጆቼን ድካም አየ፥ ትናንትም ገሠጸህ።"
(ኦሪት ዘፍጥረት 31:42)

"የአብርሃም አምላክ የናኮርም አምላክ የአባታቸውም አምላክ በእኛ መካከል ይፍረድ። ያዕቆብም በአባቱ #በይስሐቅ #ፍርሃት ማለ።"
(ኦሪት ዘፍጥረት 31:53)

በነዚህ ስፍራዎች፥ ያዕቆብ እግዚአብሔርን "የይስሐቅ ፍርሃት" በማለት ይጠራዋል። የይስሐቅ ፍርሃት ማለት ይስሐቅ ይፈራው የነበረው አምላክ ማለት ነው። እግዚአብሔር የይስሐቅ ፍርሃት ተብሎ መጠራት፥ ለይስሐቅ ምን እንደሆነለት ያሳያል። ይፈራው የነበረው አምላኩ ነው። በዚህ ስፍራ የይስሐቅ ፍርሃት የተባለው ሌላ አካል ሳይሆን ራሱ እግዚአብሔር ነው

ሌላ ምሳሌ

"ረድኤታችን ከእግዚአብሔር ከንጉሣችንም #ከእስራኤል #ቅዱስ ነውና።"
(መዝሙረ ዳዊት 89:18)

"ፈጣሪሽ ባልሽ ነው፥ ስሙም የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ነው፤ #የእስራኤልም #ቅዱስ ታዲጊሽ ነው፥ እርሱም የምድር ሁሉ አምላክ ይባላል።"
(ትንቢተ ኢሳይያስ 54:5)

በነዚህ ስፍራዎችም እግዚአብሔር የእስራኤል ቅዱስ ተብሎ ሲጠራ እንመለከታለን። እስራኤል የሚያመልከው ቅዱሱ እርሱ ነው። ከእስራኤል ጋር በተያያዘ "የ" እስራኤል ቅዱስ ተብሎ የተጠራው እግዚአብሔር እንጂ ሌላ አካል አይደለም።

" #የእስራኤል #ታዳጊ ቅዱሱም፥ እግዚአብሔር፥ ሰዎች ለሚንቁት ሕዝብም ለሚጠላው ለገዥዎች ባሪያ እንዲህ ይላል። ስለ ታማኙ ስለ እግዚአብሔር ስለ መረጠህም ስለ እስራኤል ቅዱስ ነገሥታት አይተው ይነሣሉ፥ መሳፍንትም አይተው ይሰግዳሉ።"
(ትንቢተ ኢሳይያስ 49:7)

በዚህ ቦታም እንዲሁ፥ እግዚአብሔር የእስራኤል ታዳጊ ተብሎ ተጠርቷል። ታዳጊነቱ ለእስራኤል ስለሆነ፥ "የ" እስራኤል ታዳጊ ተብሏል። ይህ እግዚአብሔር ከሰዎች ጋር በተያያዥነት እንደሚጠራ የሚያሳይ ተጨማሪ ማስረጃ ነው።

"ነገር ግን ቀስቱ እንደ ጸና ቀረ፤ የእጆቹም ክንድ በያዕቆብ አምላክ እጅ በረታ፥ በዚያው በጠባቂው #በእስራኤል #ዓምድ፥"
(ኦሪት ዘፍጥረት 49:24)

በዚሁ ስፍራም፥ በተመሳሳይ መልኩ እግዚአብሔር "የእስራኤል ዓምድ" ተብሎ ተጠርቷል። ይህ ማለት እስራኤል የሚመካበት፥ የተመሰረተበት ዓለቱ እርሱ ነው ማለት ነው። እግዚአብሔር ከእስራኤል ጋር በተያያዥነት ስለሚጠራ፥ "የ" እስራኤል ዓምድ ተባለ

♦️ ልክ በዚህ አኳሃንም፥ እግዚአብሔር "የእስራኤል ክብር" ተብሎ ተጠርቷል። የእስራኤል ክብራቸው፥ የሚመኩበት ሞገሳቸው እርሱ ነውና

#የእስራኤል #ክብር የሆነው እግዚአብሔር አይዋሽም፤ አይጸጸትምም፤ እርሱ ይጸጸት ዘንድ ሰው አይደለምና።”
— 1ኛ ሳሙኤል 15፥29 (አዲሱ መ.ት)

“He who is the #Glory of #Israel does not lie or change his mind; for he is not a man, that he should change his mind."”
— 1Sam 15:29 (NIV)

ይህ በግልፅ እንደሚያሳየው፥ እግዚአብሔር የእስራኤል ክብር ተብሎ ይጠራል። እግዚአብሔር ከእስራኤል ጋር በተያያዥነት ከሚጠራባቸው ስያሜዎች መካከል አንዱ "የእስራኤል ክብር" ነው።

ስለዚህ በአሞጽ 8:7 ላይ በያዕቆብ ክብር እምላለሁ ሲል፥ በራሴ እምላለሁ ማለት ነው። ምክንያቱም እውነተኛው የእስራኤል ክብር እርሱ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ፥ በተደጋጋሚ የእስራኤል ክብር እግዚአብሔር መሆኑን ይናገራልና

"ከዚያ በኋላ እግዚአብሔር የዘላለም ብርሃንሽ፥ #አምላክሽም #ክብርሽ #ይሆናልና ፀሐይ በቀን ብርሃን አይሆንልሽም፥ የጨረቃም ብርሃን በሌሊት አይበራልሽም። "
(ትንቢተ ኢሳይያስ 60:19)

"ታበጥራቸዋለህ፥ ነፋስም ይጠርጋቸዋል፥ ዐውሎ ነፋስም ይበትናቸዋል፤ አንተም በእግዚአብሔር ደስ ይልሃል፥ በእስራኤልም ቅዱስ #ትመካለህ (shall #glory)"
(ትንቢተ ኢሳይያስ 41:16)

"የእስራኤልም ዘር ሁሉ በእግዚአብሔር ይጸድቃሉ፥ #ይመካሉም ይባላል (shall #glory)"
(ትንቢተ ኢሳይያስ 45:25)

➣ ስለዚህ እግዚአብሔር በያዕቆብ ክብር እምላለሁ ሲል፥ በራሴ እምላለሁ ማለት ነው።

ይህንንም ከራሱ ከአሞጽ መጽሐፍ ማረጋገጥ ይቻላል። በአሞጽ መጽሐፍ ውስጥ፥ በተደጋጋሚ በራሱ ሲምል እንመለከታለን።

" #ጌታ #እግዚአብሔር። የያዕቆብን ትዕቢት ተጸይፌአለሁ፥ አዳራሾቹንም ጠልቻለሁ፤ ስለዚህ ከተማይቱንና የሚኖሩባትን ሁሉ አሳልፌ እሰጣለሁ ብሎ #በራሱ #ምሎአል፥ ይላል የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር።"
(ትንቢተ አሞጽ 6:8)

" #ጌታ #እግዚአብሔር። እናንተን በሰልፍ ዕቃ፥ ቅሬታችሁንም በመቃጥን የሚወስዱበት ቀን፥ እነሆ፥ በላያችሁ ይመጣል ብሎ #በቅዱስነቱ #ምሎአል።"
(ትንቢተ አሞጽ 4:2)

✍️ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ፥ ጌታ እግዚአብሔር በራሱ መማሉ የተለመደ ነው፦

"እንዲህም አለው። #እግዚአብሔር#በራሴ_ማልሁ ይላል፤ ይህን ነገር አድርገሃልና፥ አንድ ልጅህንም አልከለከልህምና"
(ኦሪት ዘፍጥረት 22:16)

"የሠራዊት ጌታ #እግዚአብሔር እንዲህ ሲል #በራሱ_ምሎአል። በእውነት ሰዎችን እንደ አንበጣ እሞላብሻለሁ፥ እነርሱም ጩኸት ያነሡብሻል።"
(ትንቢተ ኤርምያስ 51:14)

"ቃሌ ከአፌ በጽድቅ ወጥታለች፥ አትመለስም። ጕልበት ሁሉ ለእኔ ይንበረከካል፥ ምላስም ሁሉ በእኔ ይምላል ብዬ #በራሴ_ምያለሁ።"
(ትንቢተ ኢሳይያስ 45:23)

"ነገር ግን ይህን ቃል ባትሰሙ፥ ይህ ቤት ወና እንዲሆን #በራሴ_ምያለሁ፥ ይላል #እግዚአብሔር።"
(ትንቢተ ኤርምያስ 22:5)

"ባሶራ መደነቂያና መሰደቢያ መረገሚያም እንድትሆን #በራሴ_ምያለሁ፥ ይላል #እግዚአብሔር፤ ከተሞችዋም ሁሉ ለዘላለም ባድማ ይሆናሉ።"
(ትንቢተ ኤርምያስ 49:13)

"እናንተ በግብጽ ምድር የምትኖሩ ይሁዳ ሁሉ፥ ስለዚህ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ፤ በግብጽ ምድር ሁሉ በሚኖር በይሁዳ ሰው ሁሉ አፍ ስሜ ከእንግዲህ ወዲህ። ሕያው እግዚአብሔርን! ተብሎ እንዳይጠራ፥ እነሆ፥ #በታላቅ_ስሜ_ምያለሁ፥ ይላል #እግዚአብሔር።"
(ትንቢተ ኤርምያስ 44:26)
"ነገር ግን የሰበሰቡት ይበሉታል እግዚአብሔርንም ያመሰግናሉ፥ ያከማቹትም በመቅደሴ አደባባይ ላይ ይጠጡታል ብሎ #በቀኙና_በኃይሉ_ክንድ_ምሎአል።"
(ትንቢተ ኢሳይያስ 62:9)

ይህ በማያሻማ ሁኔታ እግዚአብሔር በማን እንደሚል ግልፅ ያደርግልናል። የሚምለው በራሱ ነው። በአሞጽ 8:7 ላይ ለየት ያለ አገላለጽን ለራሱ ማዋሉ በሌላ አካል ይምላል አያስብለውም።

እግዚአብሔር ራሱን የያዕቆብ ክብር ብሎ መጥራቱ፥ የያዕቆብ መመኪያና ክብር ሃብታቸው ወይ ሃይላቸው ሳይሆን እርሱ ራሱ መሆኑን ለመግለጽ ነው። እራሱን የያዕቆብ ክብር ብሎ ሲጠራ፥ እያመለከተ ያለው ይህንን ነው። እንጂ በፍጡር እየማለ አልነበረም። በአውዱም ውስጥ መሃላው የተደረገው በፍጡር ነው የሚል አንዳች ነገር የለም። ጌታ በራሱ እንጂ በፍጡር አይምልምና

ጌታ ይርዳን!
🚩 መሲሁ፦ እስራኤልን ወደ ምድሩ የሚመልሰው አምላክ

መምጣቱ የተተነበየለት መሲሕ በስጋ የተገለጠው አምላክ መሆኑን መጽሐፍ ቅዱስ በስፋት ያስተምራል። ከእግዚአብሔር ቃል መሠረታዊ አስተምህሮዎች አንዱ የመሲሑ መለኮትነት ነው። በዚህም ምክንያት ለእግዚአብሔር ብቻ በሚውሉ ስያሜዎች ተጠርቶ እንመለከታለን። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ መሲሁ፥ ሃያል አምላክ (ኢሳ 9:6-7) እግዚአብሔር ጽድቃችን (ኤር 23:5-6) ዘላለማዊ ዙፋን ያለው አምላክ (መዝ 45:6-7) በሰማይ ያለው ጌታ (መዝ 110:1) በደመናት ላይ የሚሄደው የሰው ልጅ (ዳን 7:13-14) ተብሎ ተጠርቷል።

▶️ መሲሁ በእነዚህ ሁሉ ስያሜዎች ሊጠራ የቻለው፥ በስጋ የመጣው አምላክ በመሆኑ ነው። ዛሬም መጽሐፍ ቅዱስ መሲሁን እግዚአብሔር ብሎ ከጠራባቸው ቦታዎች አንዱን ለመመልከት እንሞክራለን።

" #በአምላካቸው_በእግዚአብሔር #አበረታቸዋለሁ፥ በስሙም ይመካሉ፥ ይላል እግዚአብሔር።"
(ትንቢተ ዘካርያስ 10:12)

በዚህ ስፍራ፥ እግዚአብሔር በመጨረሻው ዘመን የሚሆነውን ነገር በነቢዩ ዘካሪስ አማካኝነት ሲናገር እንመለከታለን። ትንቢተ ዘካርያስ በመጨረሻው ዘመን ስለሚከሰቱ ነገሮች አብዝቶ የሚናገር መጽሐፍ ሲሆን፥ በዚህ ስፍራም እየተናገረ ያለው በዘመን መጨረሻ ስለሚሆነው ነገር ነው

የዘካርያስ 10 አውድ በመጨረሻው ዘመን እስራኤላውያን እንዴት ከተበተኑበት ቦታዎች ሁሉ ተሰብስበው ወደ እግዚአብሔር ወደ ሰጣቸው ምድር እንደሚመለሱ የሚተነብይ ክፍል ነው። በዚያ ክፍል እግዚአብሔር የእስራኤልን ሕዝብ ካሉበት የአለም ዳርቻ በሙሉ ሰብስቦ ለአባቶቻቸው ሊሰጣቸው ወደማለላቸው ምድር እንደሚመልሳቸው ቃል ይገባላቸዋል። እግዚአብሔር ለአብርሃም፥ ለይስሐቅና ለያዕቆብ የከነዓንን ምድር ለዘሮቻቸው ለዘለአለም እንደሚሰጣቸው ቃል ገብቶላቸዋል (ዘፍ 13:15 ዘፍ 26:4 ዘፍ 48:4) በዘካ 10 ተተንብዮ የምንመለከተው የዚህ ቃል ፍጻሜ ነው

✍️ እግዚአብሔር ለእስራኤል ሕዝብ የገባው ይህ ቃል ኪዳን የሚፈጸመው መሲሁ ተመልሶ ሲመጣ እንደሆነ መጽሐፍ ቅዱስ ያስተምራል

መሲሁ ለኃጢአታችን ሞቶ (ኢሳ 53:9) ተነሥቶ (ኢሳ 53:11 መዝ 16:10) ወደ አባቱ ካረገ (መዝ 110:1 ዳን 7:13-14) በኋላ፥ ጊዜው ሲደርስ ተመልሶ ይመጣል (ዘካ 14:5) ተመልሶ ከመጣ በኋላ፥ በዳዊት ዙፋን ላይ ይቀመጣል (ኢሳ 9:6-7 መዝ 132:11) በዚያ ዙፋን ላይ ተቀምጦም አለምን ሁሉ ለዘላለም ይገዛል (መዝ 72:11 ዘካ 9:9-10)

እስራኤላውያንም ከተበተኑበት የአሕዛብ ምድሮች በሙሉ የሚሰበሰቡት በዚሁ ጊዜ ነው። መሲሁ ተመልሶ መጥቶ ዙፋኑን በሚመሰርትበት ጊዜ ነው የእስራኤል ሕዝብ እግዚአብሔር ለአባቶቻቸው እንደሚሰጣቸው ወደማለላቸው ምድር በሙላት የሚመለሱት፦

"12 ለአሕዛብም ምልክትን ያቆማል፥ #ከእስራኤልም የተጣሉትን #ይሰበስባል#ከይሁዳም የተበተኑትን ከአራቱ የምድር #ማዕዘኖች #ያከማቻል።"
(ትንቢተ ኢሳይያስ 11:12)

በዚህ ስፍራ፥ መሲሁ በአራቱ የምድር ማዕዘኖች የተበተኑትን የእስራኤል ልጆች እንደሚሰበሰብ ተተንብዮ እንመለከታለን። ኢሳያስ 11 በጣም ታዋቂ መሲሃዊ ትንቢት ሲሆን፥ የመሲሁ ማንነትና ስራ በስፋት የተዘገበበት ክፍል ነው። ከእሴይ ዘር የሚበቅል በትር እንደሆነ (ቁ.1) የእግዚአብሔር መንፈስ በእርሱ ላይ እንደሆነ (ቁ.2) በአሕዛብ ላይ በጽድቅ እንደሚፈርድ (ቁ.3) ክፉዎቸን በእስትንፋሱ እንደሚያጠፋ (ቁ.4) ግዛቱ ፍጹም ሰላማዊ እንደሚሆን (ቁ.6-8) በዘመኑም ምድር ሁሉ እግዚአብሔርን በማወቅ እንደምትሞላ (ቁ.9) የሚተነብይ አስደናቂ መሲሃዊ ትንቢት ነው።

በዚሁ ትንቢት ላይ ነው፥ እንግዲህ ወደ አራቱም አቅጣጫ የተበተኑትን የእስራኤል ልጆች እንደሚያከማች የተነገረው። ይህ ማለት፥ መሲሁ አለምን ሁሉ ለመግዛት ወደ ምድር ሲመለስ ከሚያደርጋቸው ነገሮች መካከል አንዱ ይህ ነው ማለት ነው። በአለም ዙሪያ የተበተኑትን አይሁዳውያን እግዚአብሔር ለአባቶቻቸው ሊሰጣቸው ወደማለላቸው ምድር ይመልሳቸዋል ማለት ነው። ይህ በምድር ሁሉ የተበተኑትን የእስራኤል ልጆች ወደ ራሳቸው ምድር የሚመልሰው መሲሁ መሆኑን ያረጋግጣል።

"5፤ እነሆ፥ ለዳዊት #ጻድቅ_ቍጥቋጥ የማስነሣበት ዘመን ይመጣል፥ ይላል እግዚአብሔር፥ እርሱም እንደ #ንጉሥ_ይነግሣል፥ ይከናወንለታልም፥ በምድርም ፍርድንና ጽድቅን ያደርጋል። 6፤ በዘመኑም ይሁዳ ይድናል እስራኤልም ተዘልሎ ይቀመጣል፥ የሚጠራበትም ስም። #እግዚአብሔር_ጽድቃችን ተብሎ ነው። 7፤ ስለዚህ፥ እነሆ። የእስራኤልን ልጆች ከግብጽ ምድር ያወጣ ሕያው እግዚአብሔርን! ዳግመኛ የማይባልበት ዘመን ይመጣል፥ ይላል እግዚአብሔር፤ 8፤ ነገር ግን። #የእስራኤልን_ቤት ዘር #ከሰሜን አገርና #ካሰደድኋቸውም_አገር ሁሉ #ያወጣና #የመራ ሕያው እግዚአብሔርን! ይባላል፤ #በምድራቸውም_ይቀመጣሉ።"
(ትንቢተ ኤርምያስ ምዕራፍ 23:5-8)

➣ በዚህ ስፍራ፥ መሲሁ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ተመልሶ ሲመጣ የሚሆነውን ነገር እናነባለን። መሲሁ ይመጣል፥ እንደ ንጉሥም ይነግሳል። በሚነግስበት ሰአትም "እግዚአብሔር ጽድቃችን" ተብሎ ይጠራል። መሲሁ "እግዚአብሔር/ያሕዌ" ተብሎ መጠራቱ ሰው ብቻ አለመሆኑን ነገር ግን እግዚአብሔርም መሆኑን ያረጋግጣል። ምንም እንኳ ለዳዊት የተነሳ ቁጥቋጦ (የዳዊት የሥጋ ዘር) ቢሆንም ሰው ብቻ አይደለም። እግዚአብሔርም ነው።

ቀጥሎም መሲሁ በሚነግስበት ሰአት ምን እንደሚሆን በቁ.7-8 እናነባለን። በዚያ ዘመን (መሲሁ በሚገዛበት ዘመን) እስራኤልን ከግብፅ ያወጣ መባሉ እንደሚቀርና እስራኤልን ከአሕዛብ ምድር ያወጣ እንደሚባል ይናገራል። ይህ ማለት መሲሁ ተመልሶ በሚመጣበት ጊዜ የእስራኤል ሕዝብ ወደ ምድሩ ይመለሳል ማለት ነው። ከተበተኑበት አገራት በሙሉ ስለሚመለሱ እነርሱን ወደ ምድራቸው የመለሰ እግዚአብሔር ተብሎ ይጠራል። ለዚያም ነው ቁ.8 "ወደ ምድራቸው ይመለሳሉ" የሚለው። ከተበተኑበት ምድር በሙሉ በመሲሁ የንግስና ዘመን ስለሚመለሱ ወደ ምድራቸው ይመለሳሉ ተብሏል።

"13 #ከአሕዛብም ዘንድ #አወጣቸዋለሁ #ከአገሮችም #እሰበስባቸዋለሁ፥ ወደ ገዛ አገራቸውም አመጣቸዋለሁ፤ በእስራኤልም ተራሮች ላይ በፈሳሾችም አጠገብ በምድርም ላይ ሰዎች በሚኖሩበት ስፍራ ሁሉ አሰማራቸዋለሁ።
23 በላያቸውም አንድ #እረኛ አቆማለሁ እርሱም ያሰማራቸዋል፥ እርሱም #ባሪያዬ #ዳዊት ነው፤ ያሰማራቸዋል እረኛም ይሆናቸዋል። 24 እኔም እግዚአብሔር አምላክ እሆናቸዋለሁ #ባሪያዬም #ዳዊት በመካከላቸው አለቃ ይሆናል፤ እኔ እግዚአብሔር ተናግሬአለሁ።"
(ሕዝቅኤል 34:13-24)

በዚሁ ሥፍራም እግዚአብሔር በመሲሁ ዘመን የሚሆነውን ነገር ሲናገር እንመለከታለን። ከአሕዛብ ዘንድ እንደሚያወጣቸው ከአገሮችም እንደሚያመጣቸውና በእስራኤል ተራሮች ላይ እንደሚያኖራቸው ቃል ይገባላቸዋል። የክፍሉ ሙሉ አውድ በዚያ ዘመን እግዚአብሔር ስለሚያደርግላቸው ነገር ይናገራል። በክፍሉ እግዚአብሔር የእስራኤልን ሕዝብ በበጎች በመመሰል በእስራኤል ተራሮች እንደሚያሰማራቸው የደከመውን እንደሚያጸና የባዘነውን እንደሚፈልግ መንጋውንም እንደሚያድን ቃል ይገባላቸዋል።
በዚያም ሰአት በላያቸው አንድ እረኛን እንደሚያቆም ቃል ይገባል። ያም እረኛ ባሪያው ዳዊት ነው። በዚህ ስፍራ "ዳዊት" ተብሎ የተጠራው መሲሁ ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ መሲሁ ብዙ ስሞች አሉት። ከነዚህ ስሞች መካከል አንዱ ዳዊት ነው። እግዚአብሔር ለዳዊት ከሆዱ ፍሬ በዙፋኑ ላይ እንደሚያስቀምጥ ቃል ስለገባለት (2 ሳሙ 712) ከእርሱ የዘር ሀረግ የሚወለደው ክርስቶስ "ዳዊት" ተብሎ ተጠርቷል። (ሆሴ 3:4 ኢሳ 55:3-5) መሲሁ ተመልሶ በመጣ ጊዜ ለእስራኤል ሕዝብ እረኛ ይሆናል። በመካከላቸው ይነግሳል እረኛቸውም ይሆናል

ይህ እንደሚያረጋግጠው መሲሁ ተመልሶ በመጣ ጊዜ ከሚሆኑት ነገሮች አንዱ የተበተኑት እስራኤላውያን ወደ ምድራቸው መመለስ ነው። መሲሁ እንደ እረኛ በሚነሳላቸው ሰአት እግዚአብሔር በመሲሁ አማካኝነት ወደ ምድራቸው ይመልሳቸዋል። ለዚያም ነው በክፍሉ እግዚአብሔር እንደ በጎች እረኛ እንደተመሰለው ሁሉ መሲሁም እረኛ ተብሎ የተጠራው። ልክ እንደ አባቱ ሕዘቡን ወደ ምድራቸው ይመልሳቸዋልና

"10፤ እግዚአብሔር እንዲ ይላል። እናንተ። ያለ ሰውና ያለ እንስሳ ያለች ባድማ ናት በምትሉአት በዚህች ስፍራ፥ የሚቀመጥባቸው በሌላ፥ ያለ ሰውና ያለ እንስሳ ባድማ በሆኑ #በይሁዳ #ከተሞችና #በኢየሩሳሌም #አደባባይ፥ 11፤ የሐሤት ድምፅና የደስታ ድምፅ፥ የወንድ ሙሽራ ድምፅና የሴት ሙሽራ ድምፅ። እግዚአብሔር ቸር ነውና፥ ምሕረቱም ለዘላለም ነውና የሠራዊትን ጌታ እግዚአብሔርን አመስግኑ የሚሉ ድምፅ፥ ወደ እግዚአብሔርም ቤት የምስጋናን መሥዋዕት የሚያመጡት ድምፅ እንደ ገና ይሰማል። #የምድርን #ምርኮ #ቀድሞ #እንደ #ነበረ #አድርጌ #እመልሳለሁና፥ ይላል እግዚአብሔር። 12፤ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል። ባድማ ሆኖ፥ ያለ ሰውና ያለ እንስሳ ባለው በዚህ ስፍራ በከተሞችም ሁሉ መንጎቻቸውን የሚያሳርፉት #የእረኞች #መኖሪያ #ይሆናል። 13፤ በደጋው ላይ ባሉ ከተሞች በቈላውም ባሉ ከተሞች በደቡብም ባሉ ከተሞች፥ በብንያምም አገር በኢየሩሳሌምም ዙሪያ ባሉ ስፍራዎች፥ በይሁዳም ከተሞች መንጎቹ በተቈጣጣሪው #እጅ #እንደ #ገና #ያልፋሉ፥ ይላል እግዚአብሔር። 14፤ እነሆ፥ ስለ እስራኤል ቤትና ስለ ይሁዳ ቤት የተናገርሁትን #መልካም #ቃል የምፈጽምበት #ዘመን #ይመጣል፥ ይላል እግዚአብሔር። 15፤ #በዚያም_ዘመን በዚያም ጊዜ ለዳዊት #የጽድቅን #ቍጥቋጥ #አበቅልለታለሁ፤ እርሱም ፍርድንና ጽድቅን በምድር ያደርጋል። 16፤ በዚያም ዘመን ይሁዳ ይድናል ኢየሩሳሌምም ተዘልላ ትቀመጣለች፤ የምትጠራበትም ስም። #እግዚአብሔር #ጽድቃችን ተብሎ ነው።
(ትንቢተ ኤርምያስ ምዕራፍ 33:10-16)

በዚህም ሥፍራ ነቢዩ ኤርምያስ መሲሁ ተመልሶ ሲመጣ የሚሆነውን ነገር ሲተነብይ እንመለከታለን። በምርኮና በመበታተናቸው ምክንያት ባድማ የሆኑት የይሁዳ ከተሞችና የኢየሩሳሌም አደባባዮች ሰዎች እንደሚሞሉ ይናገራል። ለዚያም ነው በቁ.11 "የምድርን ምርኮ እንደ ቀድሞ አድርጌ እመልሳለሁ" የሚለው። ቀጥሎም ባድማ የነበሩት ከተሞች የእረኞች መኖሪያ እንደሚሆኑ ሕዝቡም በተቆጣጣሪው እጅ እንደሚያልፉ ይናገራል። ቀጥሎም በቁ.14 ለእስራኤል ቤትና ለይሁዳ ቤት የተናገረው መልካም ቃል የሚፈጸምበት ዘመን ይመጣል ይላል። ይህ ማለት በተደጋጋሚ ስለ መሲሁ የገባላቸው ቃል ይፈጸማል ማለት ነው። መሲሁ ተመልሶ ሲመጣ ይሆናል አላቸው  ነገሮች በሙሉ የሚሆኑበት ዘመን ነው ማለት ነው።

ከዚያም በቀ.15 "በዚያም ዘመን በዚያም ጊዜ ለዳዊት የጽድቅን ቁጥቋጦ አበቅልለታለሁ" ይላል። ይህ ማለት፥ እስራኤል ወደ ምድሩ በተመለሰ ጊዜ ይህ የጽድቅ ቁጥቋጦ ይበቅላል ማለት ነው። በዚህ ሥፍራ "ቁጥቋጦ" ተብሎ የተጠራው መሲሁ ነው። መሲሁ በመጽሐፍ ቅዱስ ከተጠራባቸው ስሞች መካከል፥ አንዱ ቁጥቋጦ ነው። (ዘካ 3:8 ኢሳ 11:1 ኢሳ 4:2 ኢሳ 11:10) ያ ቁጥቋጦ (መሲሁ) በዚያ ዘመን ፍርድንና ጽድቅን በምድር ላይ ያደርጋል።

ይህ ማለት እስራኤል ወደ ምድሩ የሚመለስበትና የሚድንበት ዘመን መሲሁ ፍርድንና ጽድቅን በምድር ላይ በሚያደርግበት ዘመን ነው ማለት ነው። መሲሁ ሊነግስና ሊፈርድ ተመልሶ በሚመጣበት ሰአት እስራኤል ዳግም በምድሩ መኖር ይጀምራል። እግዚአብሔርም የገባላቸው ቃል ኪዳን ይፈጸምላቸዋል። ይህ በማያሻማ ሁኔታ እንደሚያረጋግጠው መሲሁ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ተመልሶ በሚመጣበት ሰአት እስራኤል ከተበታተኑበት ምድር በሙሉ ይሰባሰባሉ

"21፤ አንተም እንዲህ ትላቸዋለህ። ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል። እነሆ፥ #የእስራኤልን #ልጆች ከሄዱባቸው #ከአሕዛብ መካከል #እወስዳለሁ #ከስፍራም ሁሉ #እሰበስባቸዋለሁ ወደ ገዛ #ምድራቸውም #አመጣቸዋለሁ፤ 22፤ በምድርም ላይ #በእስራኤል #ተራሮች ላይ አንድ ሕዝብ አደርጋቸዋለሁ፥ አንድ ንጉሥም በሁላቸው ላይ ይነግሣል፤ ከዚያ ወዲያ ሁለት ሕዝብ አይሆኑም፥ ከዚያ ወዲያም ሁለት መንግሥቶች ሆነው አይለዩም። 23፤ ከዚያ ወዲያም በጣዖቶቻቸውና በርኵሰታቸው በመተላለፋቸውም ሁሉ አይረክሱም፥ ኃጢአትም ከሠሩባት ዓመፅ ሁሉ አድናቸዋለሁ አነጻቸውማለሁ፤ ሕዝብም ይሆኑኛል እኔም አምላክ እሆናቸዋለሁ። 24፤ ባሪያዬም ዳዊት #ንጉሥ ይሆናቸዋል፤ ለሁሉም አንድ እረኛ ይሆንላቸዋል፤ በፍርዴም ይሄዳሉ ትእዛዜንም ይጠብቃሉ ያደርጓትማል። 25፤ አባቶቻችሁም #በኖሩበት ለባሪያዬ ለያዕቆብ #በሰጠኋት #ምድር #ይኖራሉ፤ እነርሱና ልጆቻቸው የልጅ ልጆቻቸውም ለዘላለም ይኖሩባታል፤ ባሪያዬም ዳዊት ለዘላለም አለቃ ይሆናቸዋል።"
(ትንቢተ ሕዝቅኤል ምዕራፍ 37:21-25)

በዚሁ ሥፍራም እግዚአብሔር መሲሁ በሚነግስበት ዘመን የሚሆነውን ነገር ሲናገር እንመለከታለን። መሲሁ በዳዊት ዙፋን ላይ ሊቀመጥ ተመልሶ በመጣ ጊዜ እግዚአብሔር የእስራኤልን ሕዝብ ከሄዱበት ከአሕዛብ መካከል እንደሚወስዳቸው፥ ከስፍራም ሁሉ እንደሚሰበስባቸው፥ ወደ ገዛ ምድራቸውም እንደሚመልሳቸው ቃል ይገባል። በምድርም በእስራኤል ተራሮች ላይ አንድ ሕዝብ ያደርጋቸዋል።

በዚያም ጊዜ አንድ ንጉሥ በሁላቸው እንደሚነግሥና (ቁ.22) ያም ንጉም ባሪያው ዳዊት (መሲሁ) እንደሆነ (ቁ.24) ይናገራል። ይህ መሲሁ ኢየሱስ በዳዊት ዙፋን ላይ ሊቀመጥ ተመልሶ በሚመጣ ጊዜ አንድ ንጉሥና አንድ እረኛ እንደሚሆንላቸውና እነርሱም ከተበተኑበት የአሕዛብ ምድሮች እንደሚመለሱ ያረጋግጣል። ለዚያም ነው ቀጥሎ፥ አባቶቻችሁ በኖሩበት ለባሪያዬ ለያዕቆብ በሰጠሁት ምድር ይኖሩበታል የሚለው። መሲሁ በዳዊት ዙፋን ላይ ተቀምጦ ሊገዛ በሚመጣበት ሰአት የእስራኤል ሕዝብ ከተበተነበት የአሕዛብ አገሮች በሙሉ ተሰብስቦ አባቶቹ በኖሩባት ምድር መኖር ስለሚጀምር ነው።

"3፤ እነሆ፥ የሕዝቤን የእስራኤልንና የይሁዳን ምርኮ #የምመልስባት ዘመን #ይመጣልና፥ ይላል እግዚአብሔር፤ ለአባቶቻቸውም ወደ #ሰጠኋት #ምድር #እመልሳቸዋለሁ፥ እነርሱም ይገዙአታል። 8፤ #በዚያ #ቀን #እንዲህ #ይሆናል፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፤ ቀንበርን ከአንገትህ እሰብራለሁ፥ እስራትህንም እበጥሳለሁ፥ ከእንግዲህ ወዲህም #ለሌላ #አትገዛም፤ 9፤ ለአምላካቸው ለእግዚአብሔርም #ለማስነሣላቸው #ለንጉሣቸው #ለዳዊትም #ይገዛሉ እንጂ ሌሎች አሕዛብ እንደ ገና አይገዙአቸውም። 10፤ እነሆ፥ #አንተን #ከሩቅ #ዘርህንም #ከምርኮ አገር #አድናለሁና ባሪያዬ #ያዕቆብ ሆይ፥ አትፍራ፥ ይላል እግዚአብሔር፥ አንተም እስራኤል ሆይ፥ አትደንግጥ፤ ያዕቆብም ይመለሳል ያርፍማል ተዘልሎም ይቀመጣል፤ ማንም አያስፈራውም።"
(ትንቢተ ኤርምያስ ምዕራፍ 30:3-10)
በዚሁ ሥፍራም እግዚአብሔር በነቢዩ ኤርምያስ አማካኝነት፥ መሲሁ አለምን ሁሉ ሊገዛ ተመልሶ ሲመጣ የሚሆነውን ነገር ሲናገር እንመለከታለን። ለአባቶቻቸው ወደ ሰጣቸው ምድር እንደሚመልሳቸው ይናገራል። ይህ ማለት፥ ከተበተኑበት አገራት በሙሉ ወደ ምድራቸው እንደሚመለሱ ያሳያል።

በዚያም ዘመን፥ ሌሎች አሕዛብ እንደማይገዟቸውና ለአምላካቸው ለእግዚአብሔር ለሚያስነሳላቸው ለንጉሳቸው ለዳዊት (መሲሁ) ይገዛሉ። ከላይ እንደተነጋገርነው፥ መሲሁ በመጽሐፍ ቅዱስ ከተጠራባቸው ስሞች መካከል አንዱ ዳዊት ነው። በዚያ ዘመን ሌሎች አሕዛብ አይገዟቸውም ማለት ደግመው ወደ ምርኮ አይሄዱም ማለት ነው። ደግመው ከምድራቸው አይፈልሱም ማለት ነው። እግዚአብሔር ለአባቶቻቸው በማለላቸው ምድር ለአምላካቸው ለእግዚአብሔርና ለልጁ ለመሲሁ ለኢየሱስ ክርስቶስ ይገዛሉ ማለት ነው።

ይህ በሚገባ መሲሀ ሊገዛ ሲመለስ፥ እስራኤል በምርኮ ከተበተኑባቸው ስፍራዎች በሙሉ እንደሚመለሱ ያረጋግጣል። ለዚያም ነው በቁ.9 ለእግዚአብሔርና ለመሲሁ እንደሚገዙ ከተናገረ በኋላ፥ በቁ.10 ላይ "ባሪያዬ ያዕቆብ አንተን ከሩቅ፥ ዘርህንም ከምርኮ አገር አድናለሁ" የሚለው። መሲሁ በሚነግስት ዘመን፥ እስራኤል ከምርኮ አገር በእግዚአብሔር ይድናሉ። ከምርኮ አገር ወደ ሀገራቸው ይመለሳሉ። ይህ መሲሁ፥ ሊነግስ ተመልሶ በሚመጣበት ጊዜ የአይሁድ ሕዝብ በሙሉ እግዚአብሔር ወደ ማለለት ምድር እንደሚመለስ ያረጋግጣል። ከምርኮ የሚድኑበት ዘመን ለእርሱና ለአባቱ የሚገዙበት ዘመን ነውና

♦️ ታዲያ ይህ ከዘካ 10 ጋር እንዴት ይገናኛል? መሲሁስ በስጋ የመጣው አምላክ መሆኑን እንዴት ያረጋግጣል?

ከላይ በብዙ ማስረጃዎች እንዳረጋገጥነው፥ መሲሁ በዳዊት ዙፋን ላይ ሊነግስ ተመልሶ በመጣበት ጊዜ፥ ከሚሆኑት ነገሮች አንዱ የእስራኤል ሕዝብ ከምርኮ መመለሱ ነው። መሲሁ ተመልሶ ሲመጣ፥ እግዚአብሔር በእርሱ አማካኝነት ለአባቶቻቸው ወደ ሰጠው ምድር ይገባሉ

የዘካ 10 አውድ ይህ ነው። ዘካ 10 እንዴት በዘመን መጨረሻ እስራኤል ወደ ምድራቸው እንደሚመለሱ የሚናገር ክፍል ነው

"6፤ ወድጃቸዋለሁና የይሁዳን ቤት አበረታለሁ፥ የዮሴፍንም ቤት አድናለሁ፤ አደላድላቸዋለሁም፤ #እመልሳቸዋለሁ፤ እኔም አምላካቸው እግዚአብሔር ነኝና፥ እኔም እሰማቸዋለሁና እንዳልጣልኋቸው ይሆናሉ። 7፤ የኤፍሬምም ሰዎች እንደ ኃያላን ይሆናሉ፥ ልባቸውም የወይን ጠጅ እንደ ጠጣ ሰው ደስ ይለዋል፤ ልጆቻቸውም አይተው ደስ ይላቸዋል፥ ልባቸውም በእግዚአብሔር ሐሤት ያደርጋል። 8፤ ተቤዥቼአቸዋለሁና በፉጨት ጠርቼ #እሰበስባቸዋለሁ#ቀድሞም #በዝተው እንደ ነበሩ #ይበዛሉ። 9፤ #በአሕዛብም መካከል #ብዘራቸው እንኳ በሩቅ አገር ሳሉ ያስቡኛል፥ ከልጆቻቸውም ጋር በሕይወት ይኖራሉ፥ #ይመለሱማል። 10፤ #ከግብጽም #ምድር #እመልሳቸዋለሁ#ከአሦርም #እሰበስባቸዋለሁ፤ ወደ ገለዓድና ወደ ሊባኖስ ምድር #አመጣቸዋለሁ፥ የሚበቃም #ቦታ #አይገኝላቸውም። 11፤ እርሱም በጭንቅ ባሕር ያልፋል፥ የባሕርንም ሞገድ ይመታል፥ የወንዙም ጥልቅ ሁሉ ይደርቃል፤ የአሦርም ትዕቢት ይዋረዳል፥ የግብጽም በትረ መንግሥት ይርቃል። 12፤ በአምላካቸው #በእግዚአብሔር #አበረታቸዋለሁ፥ በስሙም ይመካሉ፥ ይላል እግዚአብሔር።"

በዚሁ ሥፍራ እግዚአብሔር በዘመን መጨረሻ የሚሆነውን ነገር ይናገራል። እንደሚመለሱ (ቁ.6) በፉጨት እንደሚጠራቸው፥ እንደ ቀድሞም እንደሚበዙ (ቁ.8) ይናገራል። ይህ ማለት እንደ ቀድሞ በብዛት ወደ ምድራቸው ይመለሳሉ ማለት ነው። ቀጥሎም በአሕዛብ መካከል ቢዘራቸውም እንኳን፥ ከልጆቻቸው ጋር በሕይወት እንደሚመለሱ ቃል ይገባላቸዋል (ቁ.9) ይህ ማለት በአሕዛብ መካከል ቢበተኑም እንኳ፥ ከነ ልጆቻቸው ወደ ምድራቸው ይመለሳሉ ማለት ነው። ከዚያም በቁ.10 ከግብፅ ምድር እንደሚመልሳቸው፥ ከአሦርም እንደሚሰበስባቸው ወደ እስራኤልም ምድር እንደሚመልሳቸው ይናገራል። ይህ ማለት ከተበተኑበት ሥፍራ ሁሉ ወደ ገዛ ምድራቸው ይመጣሉ ማለት ነው።

✏️ ከላይ በብዙ ማስረጃዎች እንዳረጋገጥነው፤ ይህ የሚሆነው መሲሁ ተመልሶ በሚመጣበት ጊዜ ነው። መሲሁ በሚመለስበት ዘመን ይህ ይፈጸማል

በዘካ 10:12 ግን አስገራሚ ነገር እንመለከታለን። እስራኤል ወደ ምድራቸው በሚመለሱበት በዘመን መጨረሻ፥ እግዚአብሔር "በ" አምላካቸው በእግዚአብሔር እንሚያበረታቸው ይናገራል። በዚያ ዘመን፥ እግዚአብሔር የእስራኤልን ሕዝብ በእግዚአብሔር ያበረታቸዋል፥ እነርሱም በስሙ ይመካሉ

✍️ ከላይ ግን በብዙ ማስረጃዎች እንዳየነው፥ ወደ ምድራቸው በሚመለሱበት ዘመን እግዚአብሔር የሚያስነሳላቸው (ኤር 33:15-16 ሕዝ 34:23-24) እነርሱም የሚገዙለት (ኤር 30:9) ንጉስ (ኤር 23:5-6) እረኛ (ሕዝ 37:25) መሲሁ ነው። በእርሱ አማካኝነት ነው ወደ ምድራቸው የሚመልሳቸው፥ በእርሱ አማካኝነት ነው የሚጠብቃቸው።

በዘካ 10:12 ግን በዚያ ዘመን እግዚአብሔር "በ" እግዚአብሔር የእስራኤልን ሕዝብ እንደሚያበረታቸው ይናገራል። በእርሱ አማካኝነት እንደሚያበረታቸውና እንደሚያጸናቸው እየተናገረ ነው።

♦️ በሌላ ቋንቋ፥ በዘካ 10:12 እግዚአብሔር "እግዚአብሔር" በማለት የጠራው መሲሁን ነው!

መሲሁ በእግዚአብሔር "እግዚአብሔር/ያሕዌ" ተብሎ መጠራቱ በስጋ የመጣው አምላክ መሆኑን በማያሻማ መልኩ ያረጋግጣል። በመጽሐፍ ቅዱስ መሲሁ በብዙ ቦታዎች አምላክ ብቻ በሚጠራባቸው ስሞች ተጠርቷል። ዘላለማዊ ዙፋን ያለው አምላክ (መዝ 45:6-7) በሰማይ ያለው ጌታ (መዝ 110:1) ኃያል አምላክ (ኢሳ 9:6-7) እግዚአብሔር ጽድቃችን (ኤር 23:5-6) አወጣጡ ከዘላለም የሆነ (ሚክ 5:2) ተብሏል። በዚህ ስፍራም እግዚአብሔር ተብሎ የተጠራው እርሱ ነው።

እስራኤል ወደ ምድራቸው ከተመለሱ በኋላ የሚገዛቸው፥ የሚጠብቃቸው መሲሁ ነው። እግዚአብሔር በእነርሱ ላይ እንዲነግስ፥ እረኛም እንዲሆን ያስነሳው መሲሁን ነው። እርሱን ስላስነሳው፥ በእርሱ አማካኝነት ያበረታቸዋል፥ ያጸናቸዋል።

"በ" አበረታቸዋለሁ ማለት መካከለኝነት የሚያመለክት ቃል ነው። "በ" ማለት በእርሱ አማካኝነት ስራውን ይሰራል ማለት ነው። አንድ አካል፥ በሌላ አካል አማካኝነት ስራውንና ፈቃዱን መፈጸሙን ለማመልከት የሚጠቀመው ቃል ነው። አንድ አካል ሌላን አካል ልኮ ወይንም አስነስቶ ስራውን ሲሰራ፥ "በ" እርሱ ሰራ ይባላል። ለምሳሌ፦

" #በአንቺም ሰረገላውንና በላዩ የሚቀመጠውን እሰባብራለሁ፤ #በአንቺም ወንድንና ሴትን እሰባብራለሁ፤ በአንቺም ሽማግሌውንና ብላቴናውን እሰባብራለሁ፤ #በአንቺም ጐልማሳውንና ቆንጆይቱን እሰባብራለሁ፤"
(ትንቢተ ኤርምያስ 51:22)

በዚህ ሥፍራ እግዚአብሔር ባቢሎንን "መዶሻዬ" በማለት ሲጠራት እንመለከታለን (ቁ.20) ቀጥሎም በአንቺ ወንድና ሴትን፥ ሽማግሌና ብላቴናን፥ ጎልማሳውንና ቆንጆይቱን እንደሚሰብር ይናገራል። ይህ ክፍል ስለ እስራኤል ምርኮ የሚናገር ክፍል ነው። እስራኤልን እንዲማርኩና እንዲያጠፉ እግዚአብሔር ባቢሎንን ስለላካቸው፥ በእስራኤል ላይ ስላስነሳባቸው "በ" አንቺ እሰባብራለሁ አለ። "በ" አንቺ እሰራለሁ ማለቱ ሌላ አካልን ተጠቅሞ አላማውን መፈጸሙን የሚያረጋግጥ ነው።
"22፤ ስለዚህ፥ #ኦሖሊባ ሆይ፥ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል። ነፍስሽ ከእነርሱ የተለየች ውሽሞችሽን #አስነሣብሻለሁ፥ በዙሪያሽም በአንቺ ላይ አመጣቸዋለሁ። 23፤ እነርሱም #የባቢሎን ሰዎች #ከለዳውያንም ሁሉ፥ ፋቁድ፥ ሱሔ፥ ቆዓ፥ ከእነርሱም ጋር አሦራውያን ሁሉ፥ መልከ መልካሞች ጐበዛዝት፥ አለቆችና ሹማምቶች ሁሉ፥ መሳፍንቶችና አማካሪዎች ሁሉ፥ በፈረስ ላይ የተቀመጡ ናቸው።"
(ትንቢተ ሕዝቅኤል ምዕራፍ 23:22-23)

▶️ ስለዚህ እግዚአብሔር "በ" እግዚአብሔር አበረታቸዋለሁ ማለቱ ሌላ እግዚአብሔር የሆነ አካል እንዳለ ያረጋግጣል። ያም አካል መሲሁ ነው። እግዚአብሔር በእግዚአብሔር/በመሲሁ ያበረታቸዋል። በላያቸው እንዲነግስ (ኤር 23:5-6) እረኛ እንዲሆን (ሕዝ 34:23-24) ያስነሳው፥ ያቆመው እርሱን ነውና። ያስነሳው እርሱን ስለሆነ፥ የሚያበረታቸውም በእርሱ ነው

ከዚህ በፊት በብዙ ማስረጃዎች እንዳየነው፥ እግዚአብሔር መለኮታዊ ልጅ አለው (ምሳ 30:3-4 ዳን 3:25-28) ያም ልጁ እግዚአብሔር ነው (ዘፍ 31:10-13 ዘጽ 24:1 ዘጽ 24:10) እግዚአብሔር ብቻ የሚያደርገውን ነገር ማድረግ ይችላል (ዘፍ 16:10 ዘካ 3:3-4) ተመልኳልም (ኢያ 5:13-15 መሳ 6:15-21) ከእግዚአብሔርም ጋር በባህርይ/መለኮት አንድ ነው (ዘጽ 23:21) በእግዚአብሔር ቢላክም (2 ዜና 32:21-22) እርሱ ራሱ መለኮት ነው (ሆሴ 1:7)

መሲሁ፥ በስጋ የተገለጠው የእግዚአብሔር ልጅ ነው። የእግዚአብሔር ልጅ በስጋ ተገልጦ መሲሁን ሆነ። ለዚያም ነው፥ ሰው መሆኑ ተገልፆ እንኳ እግዚአብሔር ተብሎ የተጠራው። ሁለቱ ባህሪያት አሉትና። በተጨማሪም በአካል ከእግዚአብሔር የተለየ ቢሆንም እንኳ፥ እግዚአብሔር ተብሎ ተጠርቷል። ልጁ ነውና። መለኮት ስለሆነ እግዚአብሔር ተብሎ ይጠራል፥ ልጁ ስለሆነም ከእርሱ የተለየ አካል ነው። ለዚያ ነው ልኮታል፥ አስነስቶታል የተባለው። ይህ መሲሁ በስጋ የተገለጠው አምላክ መሆኑን ከማረጋገጥ ባሻገር፥ አንዱ አምላክ ከአንድ በላይ አካላት መሆኑን ያረጋግጣል።

▶️ መደምደሚያ

ከላይ በብዙ ማስረጃዎች እንዳረጋገጥነው፥ መሲሁ ተመልሶ በመጣ ጊዜ የእስራኤልን ሕዝብ ከተበተኑበት አገራት በሙሉ ወደ ምድራቸው ይመልሳቸዋል። እግዚአብሔርም በእነርሱ ላይ እንዲነግስ፥ እረኛቸውም እንዲሆን ያስነሳዋል። ያም እርሱ ያስነሳውን መሲህ፥ እግዚአብሔር ብሎ በመጥራት በስጋ የተገለጠው አምላክ መሆኑን ያረጋግጣል። በተጨማሪም እግዚአብሔር "በ" እግዚአብሔር/መሲሁ አበረታቸዋለሁ ማለቱ፥ አንዱ መለኮት ከአንድ በላይ አካል መሆኑን ያሳያል።

መሲሁ ኢየሱስ ክርስቶስ ተመልሶ በመምጣት በዳዊት ዙፋን ላይ የሚቀመጠው፥ ለእስራኤል ሕዝብ ንጉሥና እረኛ እንዲሆን አባቱ እግዚአብሔር አብ ያስነሳው፥ የእስራኤልንም ሕዝብ ከተበታተኑበት አገራት ወደ ምድራቸው የሚመልሳቸው አምላክ ነው!

ጌታ ይርዳን!
<<አንድያ ልጅ የሆነው አምላክ>>
("ሞኖጌኔስ ቴዎስ" ለዮሐንስ ወንጌል እንግዳ (ጭማሬ) ነውን?)

#ክፍል_2
በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ
✟አሐዱ አምላክ✟

“ከቶውንም #እግዚአብሔርን ያየ ማንም የለም፤ ነገር ግን በአብ እቅፍ ያለው አንድያ ልጁ የሆነው #አምላክ(ሞኖጌኔስ ቴዎስ/μονογενής θεός) እርሱ ገለጠው።”— ዮሐንስ 1፥18 (አዲሱ መ.ት)

የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባባዌ ህያሴ ጥናት እጅጉን ሰፊና ጥልቅ የሆነ ዘርፈ ብዙ መስክ ሲሆን በሊቃውንቶች መካከል ብዙ ሙግቶችን እና ውይይቶች ሲደረጉበት ይስተዋላል። ከዚህ በፊት እንዳየነው የመጽሐፍ ቅዱስን ከበኩረ ጽሑፋት የአወራረድ ሰንሰለት ወይም አሁን በእጃችን ላይ ካለውና ከጥንታዊ እደ ክታባት መካከል ያለውን ወጥነት (consistency)፣ ጸሓፊው ያስተላለፈውን መልእክት እንዳለ በታማኝነት የመተላለፉ ስርዓት ወይም ሎሌነት (fidelity) እና የአተረጓጎም ሆነ የአቀዳዱ ትክክለኛነትን (accuracy) የምንመረምርበት ከ5,500 በላይ ጥንታዊ የግሪክ እደ ክታባት ሲኖሩን ከ10,000 የሚበልጡ የላቲን ብቻ የጥንታዊ ቅጂዎች አሉ። ሌሎች ጥንታዊ የሲሪያክ፣ ኮፕቲክ፣ የቩልጌት፣ አርሜኒያን እና የግእዝ (Ethiopic version) የመሳሰሉትን ጨምረን ከ25,000 በላይ ማኑስክሪፕቶች በቂ ማረጋገጫዎቻችንና ማስረጃዎችን እንዳሉን ተመልክተናል። በተጨማሪም የቀደምት የቤተክርስቲያን አባቶችን (Ante-Nicene Fathers) ጹሑፋት ለዚሁ ጥናት እንደ አንኳር ጥሬ እቃነት የሚውሉ ማስረጃዎቻችን ናቸው።

ታዳ በምንባባዌ ሕያሴ(Textual Criticism) ጥናት ውስጥ ብዙ የቃላት፤ የሐረጋት እና በአረፍተ ነገር አኳያ መጠነኛ ልዩነቶችን ልናስተውል እንችላለን። እነዚህን ልዩነቶች የምንፈታበትን የዚሁ ጥናት ክፍል በሆነው የምንባቤያዊ ሕያሴ ቀኖና (Canon of Textual Criticism) ወደ ድምዳሜ ሊወስዱን የሚችሉ የጥናት መንገዶች አሉ። የመጀመሪያው መንገድ ብዙ ለዘብተኛም ሆኑ አጥባቄያነ የነገረ መለኮት የምንባባዌ ሕያሴ ሊቃውንት የሚጠቀሙበት ምክንዮአዊ ኤክሌክቲዝም (Reason Eclecticism) የሚባለው ክፍለ ጥናት ነው።

ኤክሌክቲኮስ/ἐκλεκτικός የሚለው የጽርዕ(ግሪክ) ቃል ኤክሌክቶስ/ἐκλεκτός "አነሳ ወይም መረጠ" ከሚለው ግስ የመጣ ሲሆን "የተሻለውን መምረጥ" የሚል ትርጓሜን ይሰጠናል። [1] ምክንዮአዊ ኤክሌክቲዝም (Reason Eclecticism) በአመክንዮአዊና በብዙ አውደ ጥናት አሰሳ መሰረት የቀደምት በኩረ ጽሑፋትን የምናጠናበት የምንባባዌ ሕያሴ ዘርፍ ሲሆን በበኩረ ጽሑፋቱ ውስጥ ለሚገኙት ልዩነቶች በተለያዩ አቅጣጫዎች መርምሮ የተሻለ ማስረጃዎችን ለጽሑፉ የሚያቀርብ አውደ ጥናት ነው።[2] ይህን ጥናት ሶስት ሕያሴያዊ ክፍሎችን ይይዛል፦

1)ውስጣዊ ሕያሴ (Internal Criticism)
2)ውጫዊ ሕያሴ(External Criticism) እና
3)የቃላት አገባባዊ ሕያሴ(Verbal Criticism) ናቸው።[3]

ሐሳቡን እያሰፋን ላለመሄድ(ከርዕሱ ጋር አያይዘን ለመመልከት እንሞክራለን) ወደ ዋናው አርዕስት ስንገባ "ሞኖጌኔስ ቴዎስ/μονογενής θεός" የሚለው ነባቤ ቃል በውጫዊ ሕያሴ(External Criticism) መመዘኛ መሰረት ሚዛን ደፍቶ እናገኘዋለን። ውጫዊ ሕያሴ (External Criticism) የምንለው ውጫዊ ማስረጃዎችን በመሰብሰብ ከጊዜ ምደባ (scriptural dating)፤ ከእደ ክታቡ ምንጭ (The Source of The scripture) እና ከጎንዮሽ ምልከታ (corresponding scripture analysis) ተነስቶ ሕያሴ የሚሰጥበት መንገድ ነው። "ሞኖጌኔስ ቴዎስ/μονογενής θεός" የሚለው ነባቤ ቃል ከሚደግፉ (ከሚያካትቱ) ግንባር ቀደም በኩረ ጹሑፋት መካከል P⁶⁶ እና P⁷⁵ የሚባሉት ደንገል ቅጠል ናቸው። P⁶⁶ እና P⁷⁵ ደንገል ክታባት አንዳዶች የሶስተኛውና የአራተኛው መቶ ክፍለ ዘመን ክታብ ናቸው ቢሉም (Nongbri) አሳማኝና በብዙሃኑ ሊቃውንቶች ዘንድ ተቀባይነት ያለው በአማካይ P⁶⁶ በ100-200 አ.ም (Martin, Hunger) እና P⁷⁵ ደግሞ በ175-225 አ.ም (Edward D. Andrews, Martin, Kasser) አካባቢ የነበረ ክታብ እንደሆነ መዛግብት ይመሰክራሉ።[4] በተጨማሪም በይዘታቸውም ሆነ በእድሜ መደባቸው ታላቅ ኮዴክስ ከሚባሉት መካከል ኮዴክስ ቫቲካነስ/Codex-B* (c. 300-325)፤ በኮዴክስ ሳይናቲከስ/Codex-א* (c. 330–360) እና Codex C* - Eprhraemi Rescriptus (5th C.) በእነዚህ ደንገል ክታባት ውስጥ "ሞኖጌኔስ ቴዎስ/μονογενής θεός" የሚለው ነባቤ ቃል እናገኛለን። ስለዚህ ከላይ ካየናቸው እደ ክታባት "ሁዮስ/υἱός" የሚለው ነባቤ ቃል የያዘ በእድሜ ዘመን በላጭ የሆነ አንድም ማኑስክሪፕት አናገኝም። ስለዚህ ከመጽሐፍ በቅዱስ ጥንታዊ እደ ክታባት መካከል "ቴዎስ/θεός" የሚለውን ነባቤ ቃል የያዙት ቀደምትና በእድሜ ታላቅ መሆናቸውን እንመለከታለን። በተጨማሪም በብዛት ደረጃ አንዳንዶች "ሞኖጌኔስ ቴዎስ" የሚለው ነባቤ ቃል የያዙት ጥንታዊ እደ ክታባት በቁጥር አነስተኛ እንደሆኑ በመናገር ሲሞግቱ ይስተዋላሉ። ነገር ግን በክፍል አንድ ላይ በተወሰነ መጠኑ የዘረዘርናቸውን ማስረጃዎች ይመልከቱ።[5] በተጨማሪም ሁሉም ባይሆኑም አንዳንድ የግዕዝ (Ethiopic Version) ቅጂዎች "ሞኖጌኔስ ቴዎስ" ብለው ያሰፈሩ እደ ክታባት እንዳሉ ተመልክተናል።[6] ይሄ ሁሉ ማስረጃዎች የሚያሳዩን "ሞኖጌኔስ ቴዎስ" የሚለው ነባቤ ቃል ለዮሐንስ ወንጌል #እንግዳ ወይም #ጭማሬ ተቀጥያ ነው ለሚለው ተራ ክስ መና የሚያስቀሩ እውነታዎች ናቸው።
በቅዱስ ዮሐንስ ወንጌል(1፥18) ላይ ውስጣዊ ሕያሴ (Internal Criticism) ስናደርግ ብርሃነ አለም ቅዱስ ዮሐንስ በአብዛኛው በስነ ጽሑፋዊ ይዘቱ "ሞኖጌኔስ ሁዮስ/μονογενὴς υἱός" የሚለውን ነባቤ ቃል መጠቀሙ (ዮሐ 3፥16፣ ዮሐ 3፥18፣ 1ኛ ዮሐ 4፥9) በተጨማሪም በዮሐንስ ወንጌል 1:18 ላይ ከሌላው ክፍሎች ተለይቶ መገኘቱ "ሞኖጌኔስ ቴዎስ/μονογενής θεός" የሚለውን ነባቤ ቃል በልዩነት የሚገኝ (Hapax legomenon) ስለሆነ ቃሉ ጭማሬያዊ ተቀጥያ ነው ብሎ ሕያሴ መስጠት እጂጉን ደካማ እና አንዳንድ ተመሳሳይ የሆኑ ይዘት ያላቸውን ቃላት አደጋ ላይ የሚጥል ሙግት ነው። ለምሳሌ፦ " #ሴባዞማይ/σεβάζομαι" የሚለው የግሪክ ቃል በሮሜ 1፥25 ላይ ብቻ የሚገኝ ሲሆን የሐዋርያው ብርሃነ አለም ቅዱስ ጳውሎስን መልዕክታት የስነ ጽሑፍ ቅርጽ በተመለከትን ጊዜ አምልኮ የሚለውን ቃል ለመግለጽ ከተጠቀመባቸው ቃላት የተለየ (Hapax legomenon) እንኳን በመልእክቶቹ በአዲስ ኪዳን የግሪክ ቃላት ውስጥ አንድ ጊዜ ብቻ በሮሜ 1፥25 ውስጥ የሚገኝ በይዘቱ ነጠላ የሆነ ቃል ነው፦

“ይህም የእግዚአብሔርን እውነት በውሸት ስለ ለወጡ በፈጣሪም ፈንታ የተፈጠረውን ስላመለኩና (ἐσεβάσθησαν) ስላገለገሉ ነው፤ እርሱም ለዘላለም የተባረከ ነው፤ አሜን።”
— ሮሜ 1፥25

በተጨማሪም የጎፈር እንጨት(עֲצֵי-גֹפֶר) በዘፍጥረት 1:6 ላይ፤ አይብ ወይም ወተት(גבינה) ተብሎ የተተረጎመው የእብራይስጥ ቃል ወዘተ እነዚህና መሰል ብዙ በሌላው መጽሐፈ ምንባባት ላይ ያልተጠቀሱ ልዩ ቃላቶች (Hapax legomenon) ናቸው። እነዚህን እና መሰሎቻቸውን የጭመራ ተቀጥያ ቃላት ናቸው ማለት እንደማንችል ሁሉ በዮሐንስ ወንጌል ላይ "ሞኖጌኔስ ቴዎስ" የሚለውን ነባቤ ቃል ቅዱስ ዮሐንስም(በሌላ ቦታ) ሆነ ሌሎች የቅዱሱ መጽሐፍ ጸሐፊያን ስላልተጠቀሙት እንግዳ የሆነ እና በዋናው ጽሑፍ ላይ ጭማሪ ነው የሚያስብለን አንዳች ምክንያት የለም።

በተጨማሪም ብዙ (ቢያንስ በቁጥራቸው ከአሰር በላይ ሊሆን ይችላል) ቀደምት የቤተ ክርስቲያን አበው "ሞኖጌኔስ ቴዎስ/μονογενής θεός" የሚለውን ነባቤ ቃል በጽሑፋቸው ውስጥ ተጠቅመውበታል። በክፍል አንድ ላይ ያነሳናቸውን አበው ይመልከቱ።[7]
ለምሳሌ ያክል ለመናፍቃን ምላሽ በመስጠት የሚታወቀው እና ቀደምት የቤተ ክርስቲያን የነገረ መለኮት መምህር የነበረው የአሌክሳንድርያው ቀለሜንጦስ (150 – c. 215 AD) ብርሃነ አለም ቅዱስ ዮሐንስ በወንጌሉ(1:18) ላይ አንድያ ልጅ የሆነ አምላክ ብሎ እንደከተበ ገልጾልን እንመለከታለን፦

<<...And John the apostle  says: No man has seen God at any time. #The_only_begotten  #God, who is in the bosom of the Father, He has declared Him, John 1:18 — calling invisibility and ineffableness the bosom of God.>>[8]

በተጨማሪ ያክል ለመጥቀስ የአሌክሳድሪያው ቀለሜንጦስ ተማሪ እንደነበር የሚታሰበው አርጌንስ (c. 185 – c. 253) አስተማሪውን በመከተል በዮሐንስ ወንጌል ላይ በሰጠው ማብራሪያ ዮሐ 1:18 "አንድያ ልጅ የሆነ አምላክ" መሆኑን ገልጾልን እንመለከታለን፦

<<...Accordingly John came to bear witness of the light, and in his witness-bearing he cried, saying, ‘He that comes after me exists before me; for He was before me; for of His fullness we have all received and grace for grace, for the law was given by Moses, but grace and truth came through Jesus Christ. No one has seen God at any time; the #only_begotten #God, who is in the bosom of the Father, He has declared Him.’ This whole speech is from the mouth of the Baptist bearing witness to the Christ...>>[9]

እነዚህን እንደ ክለሳ አየናቸው እንጂ ብዙ ቀደምት የቤተ ክርስቲያን አበው "ሞኖጌኔስ ቴዎስ/μονογενής θεός" የሚለውን ነባቤ ቃል በክታባቸው ላይ አስፍረውት እንመለከታለን። ስለዚህ "ሞኖጌኔስ ቴዎስ" ለዮሐንስ ወንጌል እንግዳ (ጭማሬ) ነው ብሎ ማሰብ የቤተ ክርስቲያን አበውን አስተምህሮ እና የቤተ ክርስቲያንን ታሪካዊ ትውፊት መቃወም እንደሆነ መረዳት ይኖርብናል። "ሞኖጌኔስ ቴዎስ" ለዮሐንስ ወንጌል #እንግዳ ወይም #ጭማሬ ተቀጥያ ነው ከተባለ ለምን አንድ የጥንት ቤተ ክርስቲያን አበው ይህን ሐሳብ ከመጥቀሱ ይልቅ ሐሳቡን አንስቶ ማብራሪያ አልሰጠም? ተጨማሪ ነው ካልንስ ቀደምት የቤተ ክርስቲያን አበው ተጨማሪ ወይም እንግዳ መሆኑን ከእኛ በፊት ሳያውቁ ቀርተው ይሆን በክታባቸው ውስጥ ያካተቱት? ጥያቄውን ለተሟጋቾች ትቼዋለሁ። በተጨማሪም አንዳንዶቹ ተሟጋቾች ከላይ ከጠቀስናቸውና አንዳንድ ቀደምት የኒቂያ አበው "ሞኖጌኔስ ሁዮስ/μονογενὴς υἱός" የሚለውን ነባቤ ቃል በጽሑፎቻቸው እንደሚጠቀሙት ይናገራሉ። በእርግጥ አንዳንድ አበው ሁለቱንም መገለጫዎች ሲጠቀሙት አንዳንዶቹን ደግሞ ስንመለከት ከሁለቱ አንድኛውን ሲጠቀሙት ይስተዋላሉ። ነገር ግን ተሟጋቾቹ ሊያስብላቸው የሚችለው <<ግልጸት ጎደል ወአሻሚ ሐሳብ>> እንጂ ለዮሐንስ ወንጌል #እንግዳ ወይም #ጭማሬ ተቀጥያ ነው የሚያሰኝ ማስረጃ ፈጽሞ የላቸውም። ነገር ግን በመግቢያው ጽሑፍ ላይ እንደዚህ አይነት ችግር ሲያጋጥመን ምን አይነት ዘዴዎችን እንደምንጠቀም ተመልክተናል። አብዛኛውን ይሄን ሙግት ማለትም "ሞኖጌኔስ ቴዎስ/μονογενής θεός" እንግዳ ወይም ጭማሬ ተቀጥያ ነው የሚሉት በክርስትና ወገን ያሉ ሙህራን መኖራቸውም እንዳለ ሆነው ነገር ግን ሙግቱን በግርግር መልኩ የሚያውለበልቡት (የሚያራግቡት) ጸረ ስላሴያውያን ወገን የሆኑ አርዮሳውያን፤ ሰባልዮሳውያን እና በሌሎች ሰዎች እውቀት እውቀት ላይ የሚንጠለጠሉ ባጭሩ አላዋቂ የሙስሊም ኡስታዝ ተብዬ ተሟጋቾች ላይ በይበልጡን ይስተዋላል። በመጨረሻም የዮሐንስ ወንጌል 1:18 "ሞኖጌኔስ ሁዮስ/μονογενὴς υἱός" ሆነ "ሞኖጌኔስ ቴዎስ/μονογενής θεός" በትርጉም አላማውና ውጤቱ አንድ አይነት ነው። እርሱም ለሰባልዮሳውያን ወልድ ከአብ የተለየ ማንነት እንዳለውና ለአርዮሳውያንና ለሙስሊም ተሟጋቾች ደግሞ ወልድ ከአብ ጋር አንድ አይነት ባህሪዎት (ሞኖጌኔስ/μονογενής )፤ ምንነትና በኑባሬያዊ መገኘቱ አብሮ እኩል፣ አብሮ አንድ መሆኑን በግልጽ ሁኔታ ይናገራል።
Jonathan(Yeshua Apologetics)
🔖ማጣቀሻዎች
[¹] Henry George Liddell, Robert Scott, A Greek–English Lexicon
[²] Daniel B. Wallance "Textual Criticism of New Testament",
Textual Criticism: Reasoned Eclecticism page 2
[³] Verbal Criticism አንዳንድ ሙህራን በውስጣዊ ሕያሴ (Internal Criticism) ስር ያካትቱታል።
[⁴] Karyn L. Berner, Papyrus Bodmer ll, P⁶⁶ & P⁷⁵: A re-evolution of the Correctors & corrections, M.A thesis, Wheaton College,lll(1993)
[⁵] https://t.me/TheTriune/864
[⁶] Hort, in Note C of his 1876 dissertation, described 19 Ethiopic Manuscripts of John
[⁷] https://t.me/TheTriune/864
[⁸] The Stromata, Book V chapter 12
[⁹] Contra Celsum, Book II chapter 71

📌(Remark)
በአንደኛው መቶ ክፍለ ዘመን ይኖር የነበረው ቀደምት ሐዋርያዊ አበው ቅዱስ አግናጥዮስ ዘአንጾኪያ "ሞኖጌኔስ ሁዮስ/μονογενὴς υἱός" የሚለውን ሐሳብ ቢጽፍም "...አንድ ልጅ የሆነ እግዚአብሔር (አምላክ) ቃል..." የሚልን ነባቤ ቃል በመልእክቱ ላይ እንዳካተተ እንመለከታለን፦

<<... #μονογενὴς #θεὸς ὁ λόγος/one son, God the Word...>>/Epistle of Ignatius to the Philippians chapter 2./

ሞኖስ/μόνος ማለት #አንድ ወይም #ብቸኛ ማለት ነው። አንዳድ የእንግሊዝኛ ትርጉሞች በዚሁ መልክ የሚተረጉሙ አሉ፦
<<No one has ever seen God. The only(one) Son, God, who is at the Father's side, has revealed him.>>
(-NAB Translation)
Eusebius of Caesarea  (c. 260-339)/De ecclesiastica theologia Book 1, chapter 9 ΤΗΣ ΕΚΚΛΗΣΙΑΣΤΙΚΗΣ ΘΕΟΛΟΓΙΑΣ 3.6.3 page 57/
Basil (c.330-379).  In De Spiritu Sancto chapter 8:17