❤10
🚩 ነገረ ሥላሴ በብሉይ ኪዳን
▶️ በብሉይ ኪዳን ላይ የተመሰረቱ ጽሑፎች ናቸው
1) አምልኮተ-ክርስቶስ በብሉይ ኪዳን (ክፍል 1)
https://t.me/TheTriune/1340
2) አምልኮተ-ክርስቶስ በብሉይ ኪዳን (ክፍል 2)
https://t.me/TheTriune/1343
3) አምልኮተ-ክርስቶስ በብሉይ ኪዳን (ክፍል 3)
https://t.me/TheTriune/1346
4) ኢሳያስ 9:6 እና የመሲሁ አምላክነት (ለአይሁዳውያን የተሰጠ ምላሽ)
https://t.me/TheTriune/669

Telegram
Isaiah 48 Apologetics
🚩 አምልኮተ-ክርስቶስ (ክፍል 5)
ባለፉት ተከታታይ ክፍሎች ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንደሚመለክ ከእግዚአብሔር ቃል እያየን ነበር። እንደ መጽሐፍ ቅዱስ አስተምህሮ ኢየሱስ አምልኮ የሚገባው አምላክ ነው። ዓለም ሳይፈጠር የነበር (ዮሐ 17:5 ዕብ 1:2) ፍጥረትን ሁሉ የፈጠረ (ቆላ 1:13-17 ዕብ 1:10-12) በኋላ ላይ ግን በስጋ የመጣ (ሮሜ 8:3 ፊሊ 2:7) አምላክ (ዮሐ 1:1 ዕብ 1:8)…

❤2
🚩 ነገረ ሥላሴ በብሉይ ኪዳን
▶️ የመሲሁ እርገት እና ዳግም ምጽአት በብሉይ ኪዳን
https://t.me/TheTriune/1001 (ክፍል 1)
https://t.me/TheTriune/1003 (ክፍል 2)
https://t.me/TheTriune/1008 (ክፍል 3)
https://t.me/TheTriune/1010 (ክፍል 4)
https://t.me/TheTriune/1012 (ክፍል 5)
https://t.me/TheTriune/1020 (ክፍል 6)
https://t.me/TheTriune/1023 (ክፍል 7)
▶️ የመሲሁ እርገት እና ዳግም ምጽአት በብሉይ ኪዳን
https://t.me/TheTriune/1001 (ክፍል 1)
https://t.me/TheTriune/1003 (ክፍል 2)
https://t.me/TheTriune/1008 (ክፍል 3)
https://t.me/TheTriune/1010 (ክፍል 4)
https://t.me/TheTriune/1012 (ክፍል 5)
https://t.me/TheTriune/1020 (ክፍል 6)
https://t.me/TheTriune/1023 (ክፍል 7)
Telegram
Isaiah 48 Apologetics
🚩 የመሲሁ እርገትና ዳግም ምጽአት በብሉይ ኪዳን (ክፍል 1)
በክርስቶስ መሲህነት ላይ አይሁዳውያን ረቢዎች ከሚያነሷቸው ተቃውሞዎች መካከል አንዱ የመሲሁ እርገትና ዳግም ምጽአት ነው። እነዚህ ወገኖች የመሲሁን እርገትና ዳግም ምጽአት ፈጽሞ አይቀበሉም። ለምን?
መሲሁ ወደ እግዚአብሔር እንደሚያርግና ተመልሶም ወደ ምድር እንደሚመጣ የማይቀበሉበት ምክንያት መሲሁ በመጣ ጊዜ አለምን ሁሉ በመግዛት የሰላምና…

❤8
🚩 ሮሜ 9:5 ክርስቶስ አምላክ ነው አይልምን? (ለኡስታዙ የተሰጠ ምላሽ) 👇
#like #share #repost 👇
https://vt.tiktok.com/ZSVBH46dj/
#like #share #repost 👇
https://vt.tiktok.com/ZSVBH46dj/
🔥8
🚩 የዳንኤል 9 ማብራሪያ
https://t.me/TheTriune/980 (ክፍል 1)
https://t.me/TheTriune/982 (ክፍል 2)
https://t.me/TheTriune/985 (ክፍል 3)
https://t.me/TheTriune/980 (ክፍል 1)
https://t.me/TheTriune/982 (ክፍል 2)
https://t.me/TheTriune/985 (ክፍል 3)
Telegram
Isaiah 48 Apologetics
🚩 በእንተ ዳንኤል 9 (ክፍል 1)
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በነቢያት እንደሚመጣ የተተነበየለት እውነተኛው መሲሕ መሆኑን ከሚያረጋግጡት ዋነኛ የብሉይ ኪዳን ትንቢቶች መካከል አንዱ ዳንኤል 9 ነው። ዳን 9:24-27 የሚመጣው መሲሕ የሚመጣበትን ጊዜና መጥቶ ምን እንደሚያደርግ የሚናገር አስደናቂ ትንቢት ነው። በትንቢቱ መሰረት መሲሁ ሁለተኛው ቤተ መቅደስ ከመፍረሱ በፊት ይመጣና፥ ይገደላል ምንምም አይቀረውም።…

❤1
Isaiah 48 Apologetics
🚩 የዕብራውያን መልእክት ጸሐፊ (ክፍል 25) ባለፉት ተከታታይ ክፍሎች የዕብራውያን መልእክት ጸሐፊ ሐዋሪያው ጳውሎስ ለመሆኑ ከራሱ ከዕብራውያን መልእክት ውስጠ-ጽሑፋዊ (inter-textual) ማስረጃዎችን ማቅረብ ጀምረን ነበር። ሙስሊሞች ሆኑ ሌሎች ከክርስትና ውጪ ያሉ አካላት የዕብራውያን መልእክት ጸሐፊ ስለማይታወቅ መጽሐፉ የመጽሐፍ ቅዱስ አካል መሆን የለበትም፥ የእግዚአብሔርም ቃል ሊሆን አይችልም…
🚩 እግዚአብሔር ቢረዳን "የዕብራውያን መልእክት ጸሐፊ" የሚለውን ጽሑፍ የምንጨርስ ይሆናል!
🔥5❤3
🚩 የዕብራውያን መልእክት ጸሐፊ (ክፍል 26)
ባለፉት ተከታታይ ክፍሎች የዕብራውያን መልእክት ጸሐፊ ሐዋሪያው ጳውሎስ ለመሆኑ ከራሱ ከዕብራውያን መልእክት ውስጠ-ጽሑፋዊ (inter-textual) ማስረጃዎችን ማቅረብ ጀምረን ነበር። ሙስሊሞች ሆኑ ሌሎች ከክርስትና ውጪ ያሉ አካላት የዕብራውያን መልእክት ጸሐፊ ስለማይታወቅ መጽሐፉ የመጽሐፍ ቅዱስ አካል መሆን የለበትም፥ የእግዚአብሔርም ቃል ሊሆን አይችልም ብለው ሊሟገቱ ይሞክራሉ።
ነገር ግን ባለፉት ክፍሎች ለማሳየት እንደሞከርነው ይህ ፍጹም ስህተት የሆነ አመለካከት ነው። የዕብራውያን መልእክት ጸሐፊ ሐዋሪያው ጳውሎስ ለመሆኑ ከምሁራንና ከቤተክርስቲያን ታሪክ ብዙ ማስረጃዎችን ማምጣት ይቻላል። በተጨማሪም ከራሱ ከዕብራውያን መልእክት ጸሐፊው ራሱ ሐዋሪያው ጳውሎስ መሆኑን የሚያረጋግጡ ማስረጃዎችንም ማቅረብ ይቻላል
▶️ እግዚአብሔር ቢፈቅድ በዚህም ክፍል ላይ ካለፉት ክፍሎች በመቀጠል የዕብራውያኑ ጸሐፊ ራሱ ሐዋሪያው ጳውሎስ መሆኑን የሚያረጋግጡ ተጨማሪ ውስጠ-ጽሑፋዊ (inter-textual) ማስረጃዎችን ማቅረብ እንቀጥላለን፦
53) ጢሞቴዎስን ወንድማችን ብሎታል
" #ወንድማችን_ጢሞቴዎስ እንደ ተፈታ እወቁ፥ ቶሎ ብሎም ቢመጣ ከእርሱ ጋር አያችኋለሁ" (ዕብ 13:23)
በዚህ ስፍራ ላይ የዕብራውያን ጸሐፊ ጢሞቴዎስን ወንድማችን ብሎ ሲጠራው እንመለከታለን። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ሐዋርያው ጳውሎስ የጢሞቴዎስ መንፈሳዊ አባት እንደሆነና ጢሞቴዎስም መንፈሳዊ ልጁ እንደሆነ ተገልጿል። ሐዋርያው ጳውሎስ በመልእክቱ ጢሞቴዎስን በእምነት እውነተኛ ልጁ እንደሆነ (1ጢሞ 1:2) ልጁ እንደሆነ (1ጢሞ 1:18) በጌታ የሚወደውና የታመነው ልጁ እንደሆነ (1ቆሮ 4:17) ተናግሯል። እንደ መጽሐፍ ቅዱስ አስተምህሮ አንድ ሰው ሌላን ሰው ወንጌል መስክሮ፥ አስተምሮ ወደ ክርስቶስ ካመጣው የዚያ ሰው መንፈሳዊ አባት ይባላል (ፊሊ 1:10-11) ስለዚህ ሐዋርያው ጳውሎስም ጢሞቴዎስን ወደ ክርስትና ስላመጣው መንፈሳዊ አባቱ ሆኗል። ከዚህ መረዳት የተነሳ አንዳንዶች ሐዋርያው ጳውሎስ ጢሞቴዎስን ልጄ ይለዋል እንጂ ወንድሜ አይለውም ይላሉ። ይህ ፈጽሞ ስህተት ነው። ምክንያቱም እያንዳንዱ ክርስቲያን የእግዚአብሔር ልጅ ነው (ዮሐ 1:12) በዚህም ምክንያት እያንዳንዱ ክርስቲያን ወንድም እና እህት ነው (ማቴ 23:8) ስለዚህ በዚህ ምክንያት ሐዋርያው ጳውሎስ ጢሞቴዎስን ወንድማችን ቢለው አይገርምም። ሲቀጥል ሐዋርያው ጳውሎስ በመልእክቱ ላይ ጢሞቴዎስን ወንድማችን ብሎታል። ይህ ሐዋርያው ጳውሎስ ጢሞቴዎስን ወንድማችን አይለውም የሚለው እሳቤ ስህተት መሆኑን ከማሳየት በላይ የዕብራውያን ጸሐፊ እርሱ ለመሆኑ ጠቋሚ ማስረጃ ነው፦
"ስለ እምነታችሁም እንዲያጸናችሁና እንዲመክራችሁ #ወንድማችንን የእግዚአብሔርንም አገልጋይ ከእኛ ጋርም አብሮ በክርስቶስ ወንጌል የሚሠራውን #ጢሞቴዎስን ላክነው" (1ተሰ 3:2)
በዚህ ስፍራ ላይ ሐዋርያው ጳውሎስ ጢሞቴዎስን ወንድማችን ብሎ ሲጠራው እንመለከታለን። በቁ.1 ላይ ወደ ፊት እንታገስ ዘንድ ባልተቻለን ጊዜ በአቴና ብቻችንን ልንቀር በጎ ፈቃዳችን ሆነ ይላል። በዚህ ቦታ ላይ ሐዋርያው ጳውሎስ እየተናገረ ያለው ሐዋርያት ሥራ 17 ላይ ስለተከሰተው ክስተት ነው። በአንፊጶልና በአጶሎንያ ካለፉ በኋላ ወደ ተሰሎንቄ መጡ በዚያም የአይሁድ ምኩራብ ነበር። በዚያም ሐዋርያው ጳውሎስ ከመጻሕፍት በመጥቀስ ጌታ ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ መሆኑን እየጠቀሰ ከእነርሱ ጋር ይነጋገር ጀመር፥ የተወሰኑ ሰዎችም ከእነርሱ ጋር ይተባበሩ ጀመር (ሐዋ 17:1-4) ከዚያም አይሁድ ኢያሶንንና በኢያሶን ቤት የነበሩትን ወንድሞች ከኢያሶን ቤት አውጥተው ወደ ሕዝብ አለቆች በመውሰድ የቄሣርን ትዕዛዝ እንደሚቃወሙና ኢየሱስ የሚባል ሌላ ንጉሥ አላቸው ብለው ከሰሷቸው፥ የሕዝቡም አለቆች ሕዝቡ ይህንን በሰሙ ጊዜ ታወኩ ከኢያሶንና ከሌሎቹ ዋስ ተቀብለውም በዋስ ለቀቋቸው (ሐዋ 17:5-9) ወዲያውም ወንድሞች ጳውሎስና ሲላስን ወደ ቤርያ ሰደዷቸው እነርሱም ወደ አይሁድ ምኩራብ ገቡ። እነርሱም በተሰሎንቄ ከነበሩት ይልቅ ልበ ሰፊዎች ስለነበሩ እለት እለት መጻሕፍትን እየመረመሩ ቃሉን በሙሉ ፈቃድ ተቀበሉ። ስለዚህም ከእነርሱና ከግሪኮችም ቀላል የማይባሉ ሰዎች አመኑ። በተሰሎንቄ የነበሩት አይሁድ ጳውሎስ በቤርያ የእግዚአብሔርን ቃል እንደሰበከ ባወቁ ጊዜ ወደዚያው መጥተው ሕዝቡን አወኩ።
በዚያም ጊዜ ወንድሞቹ ወዲያው ጳውሎስን እስከ ባህር ድረስ ይሄድ ዘንድ ሰደዱት ሲላስና ጢሞቴዎስም በዚያው ቀሩ። ጳውሎስን የሸኙት ግን ወደ አቴና አደረሱት፥ እንደሚቻላቸውም በፍጥነት ወደ እርሱ ይመጡ ዘንድ ወደ ሲላስና ወደ ጢሞቴዎስ ትዕዛዝ ተቀብለው ሄዱ (ሐዋ 17:10-15) ስለዚህ ጢሞቴዎስ በተሰሎንቄ ቀርቶ ነበር። ሐዋርያው ጳውሎስ 1ተሰ 3:2 ላይ "ስለ እምነታችሁ እንዲያጸናችሁና እንዲመክራችሁ...ጢሞቴዎስን ላክነው" ብሏል። "እኛ" ብሎ በብዙ መደብ የሚናገረው ራሱንና ሲላስን/ስልዋኖስን አካትቶ እንደሆነ ከመልእክቱ መግቢያ መረዳት እንችላለን (1ተሰ 1:1) ከሐዋርያት ሥራ 17 እንደምንረዳው ደግሞ ሐዋርያው ጳውሎስ ወደ አቴና ሲሄድ ጢሞቴዎስ እና ሲላስ በተሰሎንቄ ቀርተው ነበር። ስለዚህ ከተሰሎንቄ መልእክት መግቢያና ከሐዋ 17:14 እንደምንረዳው ጢሞቴዎስን ወደ ተሰሎንቄ ክርስቲያኖች የላኩት ሐዋርያው ጳውሎስና ሲላስ ናቸው ማለት ነው። ይህ ሐዋርያው ጳውሎስ በ1ተሰ 3:2 እየተናገረ ያለው ስለ ሐዋርያት 17 ክስተት መሆኑን ያሳያል። ከዚያም ባሻገር በ1ተሰ 3:2 ላይ ልክ እንደ ዕብ 13:23 ላይ ጢሞቴዎስን ወንድማችን ብሎ መጥራቱ የዕብራውያን ጸሐፊ እሱ ለመሆኑ ጠቋሚ ውስጠ-ጽሑፋዊ (Inter-Textual) ማስረጃ ነው።

❤5
"በእግዚአብሔር ፈቃድ የኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያ የሆነ #ጳውሎስ_ወንድሙም_ጢሞቴዎስ፥ በአካይያ አገር ሁሉ ከሚኖሩ ቅዱሳን ሁሉ ጋር በቆሮንቶስ ላለች ለእግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን" (2ቆሮ 1:1)
በዚህ ስፍራ ላይ ሐዋርያው ጳውሎስ ጢሞቴዎስን በሶስተኛ መደብ ወንድሜ ብሎ ሲጠራው እንመለከታለን። ሐዋርያው ጳውሎስ ይህንን መልእክት ለቆሮንቶስ እና ለአካይያ ክርስቲያኖች የጻፈው በመቄዶንያ በነበረበት ጊዜ ነው። በ2ቆሮ 2:12-13 ላይ እንዴት ስለ ክርስቶስ ወንጌል ወደ ጢሮአዳ በመጣ ጊዜ ለጌታ ስራ ምንም በር ቢከፈትለትም ወንድሙን ቲቶን ስላላገኘው መንፈሱ እረፍት እንዳልነበረውና ከእነርሱ ተሰናበቶ ወደ መቄዶንያ እንደወጣ ይናገራል። ስለዚህ በዚህ ቦታ ላይ እንዴት ወደ መቄዶንያ እንደሄደ ለቆሮንቶስ እና ለአካይያ ክርስቲያኖች እያብራራ ነው ማለት ነው። ቀጥሎም እንዲሁ በ2ቆሮ 7:5 ላይ ወደ መቄዶንያ በመጡ ጊዜ በሁሉ ነገር መከራን እንደ ተቀበሉ እንጂ ሥጋቸው እረፍት እንዳልነበረው ደግሞም በውጭ ጠብ በውስጥ ፍርሃት እንደነበር ይገልጻል። ስለዚህ በዚህ ቦታ ላይም ወደ መቄዶንያ ከሄደ በኋላ የገጠመውን ነገር ለቆሮንቶስ እና ለአካይያ ክርስቲያኖች ማብራራቱን ይቀጥላል።
ከዚያም በመቀጥል በ2ቆሮ 8:2 ላይ ወንድሞች ሆይ ለመቄዶንያ አብያተክርስቲያናት የተሰጠውን የእግዚአብሔርን ጸጋ እናስታውቃችኋለን በማለት የመቄዶንያ አብያተክርስቲያናት ያሉበትን መንፈሳዊና ሁኔታ ለቆሮንቶስ እና ለአካይያ ክርስቲያኖች ይገልጽላቸዋል። ቀጥሎም በ2ቆሮ 9:1-2 ላይ ለቅዱሳን ስለሚሆነው አገልግሎት ሊጽፍላቸው እንደማያስፈልግ ለዚህም ምክንያቱ በጎ ፈቃዳቸውን በማወቁ ስለዚያም አካይያ ከአምና ጀምሮ ተዘጋጅቷል ብሎ ለመቄዶንያ ሰዎች በእነርሱ እንደሚመካ ቅንዓታቸውም የሚበዙትን እንዳነሳሳ ይናገራል። ስለ አካይያ ክርስቲያኖች ለመቄዶንያ ክርስቲያኖች መናገሩ ለቆሮንቶስ እና ለአካይያ ክርስቲያኖች ከመቄዶንያ ሆኖ እየጻፈ እንደሆነ የሚያሳይ ነው። ሐዋርያው ጳውሎስ ከመቄዶንያ ሆኖ እየጻፈ መሆኑ በሐዋ 20:1 ተረጋግጧል። በዚያ ክፍል ላይ ሁከቱ ከቀረ በኋላ ደቀመዛሙርቱን አስመጥቶ እንደመከራቸው ተሰናብቷቸውም ወደ መቄዶንያ ይሄድ ዘንድ እንደ ወጣ ተገልጿል። ይህ ወደ ቆሮንቶስ ክርስቲያኖች ከመቄዶንያ ሆኖ እንደጻፈ ከማሳየት ባሻገር በ2ቆሮ 1:1 ላይ ልክ እንደ ዕብ 13:23 ጢሞቴዎስን ወንድሜ ብሎ መጥራቱ የዕብራውያን ጸሐፊ እሱ ለመሆኑ ጠቋሚ ውስጠ-ጽሑፋዊ (Inter-Textual) ማስረጃ ነው።
"በእግዚአብሔር ፈቃድ የኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያ የሆነ #ጳውሎስ_ጢሞቴዎስም_ወንድሙ" (ቆላ 1:1)
"የክርስቶስ ኢየሱስ እስር #ጳውሎስ_ወንድሙም_ጢሞቴዎስ፥ ለተወደደውና አብሮን ለሚሠራ ለፊልሞና" (ፊል 1:1)
በቆላሲስ እና በፊሊሞና መልእክቶቹ መግቢያ ላይ ሐዋርያው ጳውሎስ ጢሞቴዎስን በሶስተኛ መደብ ወንድሜ ብሎ ሲጠራው እንመለከታለን። ሐዋርያው ጳውሎስ የቆላሲስ መልእክትን የጻፈው በሮም እስር ቤት ሳለ ነው። በቆላ 4:3 ላይ በዚያን ጊዜም ስለ እርሱ ደግሞ የታሰርሁበትን የክርስቶስን ምስጢር እንድንነግር እግዚአብሔር የቃሉን ደጅ ይከፍትልን ዘንድ ስለ እኛ ደግሞ ጸልዩ ይላል። ስለዚህ ይህን መልእክት በጻፈበት ጊዜ ታስሮ ነበር ማለት ነው። እንዲሁም በቆላ 4:18 ላይ በገዛ እጄ የተጻፈ የእኔ የጳውሎስ ሰላምታ ይህ ነው ካለ በኋላ እስራቴን አስቡ ጸጋ ከእናንተ ጋር ይሁን በማለት መልእክቱን ይዘጋል። ይህ የቆላሲል መልእክትን ታስሮ በነበረበት ጊዜ እንደጻፈው ያረጋግጣል። የፊልሞናን መልእክትም የጻፈው እንዲሁ ታስሮ በነበረበት ወቅት ነው። መልእክቱን ሲጀምር የክርስቶስ ኢየሱስ እስር ጳውሎስ በማለት በወቅቱ ታስሮ እንደነበር ይገልፃል። ከዚያም ፊሊ 1:9 ላይ እንደምናነበው ይልቁንም እንዲህ የሆንሁ እኔ ጳውሎስ ሽማግሌው አሁን ደግሞ የኢየሱስ ክርስቶስ እስር የሆንሁ ስለ ፍቅር እለምናለሁ በማለት መልእክቱን ሲጽፍ ታስሮ እንደነበር ይናገራል።
ይቀጥልና በቁ.10 ላይ አስቀድሞ ስላልጠቀመህ አሁን ግን ለእኔም ለአንተም ስለሚጠቅም በእስራቴ ስለ ወለድሁት ስለ ልጄ ስለ አናሲሞስ እለምንሃለሁ በማለት መልእክቱን የጻፈው በታሰረበት ወቅት መሆኑን ያረጋግጥልናል። ከዚያም በቁ.13 ላይ አንተም ልቤ እንደሚሆን ተቀበለው እኔስ በወንጌል እስራት ስለ አንተ እንዲያገለግለኝ ለራሴ ላስቀረው እፈቅድ ነበር በማለት ይህን መልእክት ታስሮ በነበረበት ጊዜ እንደጻፈው ያረጋግጣል። ሐዋርያው ጳውሎስ ታስሮ የነበረው በሮም እንደሆነ መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል። በሐዋ 28:16 ላይ እንደምናነበው ወደ ሮሜ በገቡ ጊዜ ጳውሎስ ከሚጠብቀው ወታደር ጋር ለብቻው ይቀመጥ ዘንድ እንደተፈቀደለት የሐዋርያት ስራ ጸሐፊው ሉቃስ ይነግረናል። ስለዚህ ሐዋርያው ጳውሎስ ታስሮ የነበረው በሮም ነው ማለት ነው። ይህ የቆላሲስ መልእክቱን በሮም ታስሮ በነበረበት ጊዜ እንደጻፈው ያረጋግጣል። ስለዚህ ከሁለቱ መልእክቶች ሐዋርያው ጳውሎስ እነዚህን መልእክቶች በሮም ታስሮ በነበረበት ጊዜ እንደጻፈው ከመረዳት ባሻገር በቆላ 1:1 እና በፊል 1:1 ላይ ልክ እንደ ዕብ 13:23 ጢሞቴዎስን ወንድሜ ብሎ መጥራቱ የዕብራውያን ጸሐፊ እሱ ለመሆኑ ጠቋሚ ውስጠ-ጽሑፋዊ (Inter-Textual) ማስረጃ ነው።
▶️ ይቀጥላል

❤15🔥3
🚩 እንኳን ለአዲሱ ዓመት በሰላም አደረሳችሁ! 2019 ዓ/ም
"በቸርነትህ ዓመትን ታቀዳጃለህ፥ ምድረ በዳውም ስብን ይጠግባል" (መዝ 65:11)

👏24❤12
🚩 ሁለት መንፈስ አለን?
በነገረ መንፈስ ቅዱስ ዙርያ ለእህታችን የተሰጠ ወንድማዊ ምላሽ
በብዙ ትማሩበታላችሁ!
#share #like #repost 👇
https://vt.tiktok.com/ZSqtt2KLp/
በነገረ መንፈስ ቅዱስ ዙርያ ለእህታችን የተሰጠ ወንድማዊ ምላሽ
በብዙ ትማሩበታላችሁ!
#share #like #repost 👇
https://vt.tiktok.com/ZSqtt2KLp/
❤7
🚩 አምልኮተ ክርስቶስ (የራዕይ 7 ማብራሪያ) (ክፍል 1)
መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔር ልጅ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አምልኮ የሚገባው መለኮት መሆኑን በስፋት ያስተምራል። የእግዚአብሔር ቃል ወልድ አምላክ እንደሆነ (ዕብ 1:8 ዮሐ 1:1 1ዮሐ 5:20) ከአባቱ ከእግዚአብሔር አብ ጋር በመለኮታዊ ባህርይ አንድ እንደሆነ (ዮሐ 10:27-30 ፊል 2:6 ዕብ 1:3) ዓለም ሳይፈጠር እንደነበር (ዮሐ 17:5 ዕብ 1:2) ዘላለማዊ እንደሆነ (ራዕ 1:17-18 ራዕ 22:13-16) የሁሉ ፈጣሪ እንደሆነ (ዮሐ 1:3 ቆላ 1:13-17 1ቆሮ 8:6 ዕብ 1:8-12 ዕብ 1:2) በሁሉ ስፍራ እንደሚገኝ (ማቴ 18:19-20 ዮሐ 3:13 ኤፌ 4:10 ራዕ 1:13/20) መንፈስ እንደሆነ (1ቆሮ 15:45 2ቆሮ 3:14-18) በኋላም ጊዜው በደረሰ ጊዜ ሰው ሆኖ እንደመጣ (ዮሐ 1:14 ሮሜ 8:3 ዕብ 2:11-14) ያስተምራል።
ይህ የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ እውነተኛ መለኮት መሆኑን በሚገባ ያሳያል። እንደ መጽሐፍ ቅዱስ አስተምህሮ ክርስቶስ ኢየሱስ እውነተኛ መለኮት ከሆነ አምልኮ ይገባዋል ማለት ነው። ስለዚህ በእግዚአብሔር ቃል ውስጥ ጌታ ኢየሱስ ሲመለክ ማየት አለብን ማለት ነው። ለእውነተኛ አምላክ አምልኮ ስለሚቀርብ ማለት ነው። ዛሬ እግዚአብሔር ቢፈቅድ የእግዚአብሔር ልጅ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በእውነተኛ አምልኮ የተመለከበትን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ለመመልከት የምንሞክር ይሆናል።
ክፍሉ እነሆ፦
"በታላቅም ድምፅ እየጮሁ። በዙፋኑ ላይ #ለተቀመጠው_ለአምላካችንና #ለበጉ #ማዳን ነው አሉ" (ራዕይ 7:10)
በዚህ ስፍራ ላይ ሐዋርያው ዮሐንስ ከእግዚአብሔር የተቀበለውን ራዕይ ሲያይ እንመለከታለን (ራዕ 1:1) በራዕ 7:9 ላይ ከዚያ በፊት ያየውን ራዕይ ካየ በኋላ አንድ እንኳ ሊቆጥራቸው የማይችል ከሕዝብና ከነገድ ከወገንም ከቋንቋም ሁሉ እጅግ ብዙ ሰዎችን ነጭ ልብስ ለብሰው የዘንባባንም ዝንጣፊዎች በእጆቻቸው ይዘው በዙፋኑና በበጉ ፊት ቆመው ይመለከታቸዋል። ከዚያም በቁ.10 ላይ በታላቅ ድምፅ እየጮሁ በዙፋኑ ላይ ለተቀመጠው ለአምላካችንና ለበጉ ማዳን ነው ሲሉ ያያቸዋል። እግዚአብሔር አምላክ በልጁ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ አንድያ ልጁን ወደ ዓለም ስለላከው (ዮሐ 3:16) እጅግ በጣም ብዙ ሰዎች በልጁ በኢየሱስ አምነው በዚህ መልኩ የእግዚአብሔርን መንግስት ወርሰው ታይተዋል። ከዚያም በቁ.13 ላይ ከሽማግሌዎቹ አንዱ ተመልሶ ለሐዋርያው ዮሐንስ እነዚህ ነጩን ልብስ የለበሱ እነ ማን ናቸው? ከወዴትስ ወጡ? ይለዋል።
ሐዋርያው ዮሐንስን ያናገረው ሽማግሌ ከሀያ አራቱ ሽማግሌዎች አንዱ ሲሆን (ራዕ 4:4) ልብስ ደግሞ ሕይወትን ወይም ማንነትን ሊያመለክት ይችላል። ለምሳሌ የታላቁ ሊቀ ካህን የኢያሱ ኃጢአተኛ ሕይወት ወይም ማንነት በአደፈ ልብስ ተመስሏል (ዘካ 3:1-4) ስለዚህ ነጭ ልብስ ከኃጢአት የነጻ ወይም ከኃጢአት የጸዳ ሕይወትን ወይም ማንነትን ያመለክታል። ከዚያም በቁ.14 ላይ ሐዋርያው ዮሐንስ ጌታ ሆይ አንተ ታውቃለህ ብሎ ይመልስለታል። ሽማግሌውም እነዚህ ከታላቁ መከራ የመጡ ናቸው ልብሳቸውንም አጥበው በበጉ ደም አነጹ ይለዋል። በጉ የዓለምን ኃጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ የተባለው ጌታ ኢየሱስ ነው (ዮሐ 1:29) ልብሳቸውን በበጉ ደም አነጹ ማለት ደግሞ በደላቸው በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ ደም ነጽቷል ማለት ነው። የልጁም የኢየሱስ ክርስቶስ ደም ከኃጢአት ሁሉ ያነጻልና (1ዮሐ 1:7) እነዚህ ሰዎች በፊት ኃጢአተኛ የነበሩ ሰዎች ቢሆኑም ንስሐ በመግባት በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ ደም ከኃጢአታቸው ነጽተዋል።
ከዚያም ሸማግሌው ይቀጥልና ስለ እነዚህ ሰዎች እንዲህ ይላል፦
"ስለዚህ በእግዚአብሔር ዙፋን ፊት አሉ፥ ሌሊትና ቀንም በመቅደሱ #ያመልኩታል፥ በዙፋኑም ላይ የተቀመጠው በእነርሱ ላይ ያድርባቸዋል" (ራዕይ 7:15)
በቁ.15 ላይ እንደምናነበው እነዚህ ሰዎች በእግዚአብሔር ዙፋን ፊት አሉ፥ ሌሊትና ቀንም በመቅደሱ ያመልኩታል፥ በዙፋኑ የተቀመጠው በእነርሱ ላይ ያድርባቸዋል። ስለዚህ በቁ.13-14 ላይ ያሉት ሰዎች ቁ.9 ላይ ያሉት እንደሆኑ በዚህ እርግጠኞች መሆን እንችላለን። ቁ.15 ላይ ሰዎቹ በእግዚአብሔር ዙፋን ፊት እንዳሉ ተገልጿል፥ ቁ.9 ላይም ሰዎቹ በዙፋኑ ፊት እንዳሉ ተገልጿል። ቁ.13 ላይ ነጭ ልብስ እንደለበሱ ተነግሯል፥ ቁ.9 ላይም ነጭ ልብስ እንደለበሱ ተነግሯል። ስለዚህ በቁ.15 ላይ ያመልኩታል የተባሉት ሰዎች በቁ.9 ላይ ያሉት ራሳቸው ሰዎች ናቸው ማለት ነው። በቁ.15 ላይ #ያመልኩታል ተብሎ የተተረጎመው የግሪክ ቃል "λατρεύουσιν" ወይም "ላትሬኦሲን" የሚለው ቃል ሲሆን ለአምላክ የሚቀርብን እውነተኛ አምልኮ የሚያመለክት ቃል ነው (Strong's G3000) በሌሎች የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎችም ጥቅም ላይ የዋለው ይህንኑ ለማመልከት ነው (ማቴ 4:10 ዘዳ 6:13 LXX)
✍️ አምልኮ እንዴት ይፈጸማል/ይተገበራል?
አምልኮ ተግባር ወይም action ነው። ስለዚህ ይህ ተግባር የሚፈጸምበት ወይም የሚተገበርበት መንገድ አለ ማለት ነው። አንድ አካል አመለከ ሲባል እንዴት አመለከ? አምልኮን እንዴት ፈጸመ ወይም ተገበረ? ተብሎ መጠየቅ አለበት። አምልኮ ተግባር ወይም action እስከሆነ ድረስ በተለያዩ መንገዶች ይከናወናልና። እንደ መጽሐፍ ቅዱስ አስተምህሮ አምልኮ የሚተገበርባቸው ወይም የሚፈጸምባቸው ብዙ መንገዶች አሉ።
ለምሳሌ፦
1) መሥዋዕት በመሰዋት
"24 ፈርዖንም ሙሴን ጠርቶ። ሂዱ እግዚአብሔርን #አገልግሉ፤ ነገር ግን #በጎቻችሁንና_ከብቶቻችሁን ተዉ፤ ልጆቻችሁ ደግሞ ከእናንተ ጋር ይሂዱ አለው። 25 ሙሴም። አንተ ደግሞ ለአምላካችን ለእግዚአብሔር #የምንሠዋው_መሥዋዕትንና የሚቃጠል መሥዋዕትን ትሰጠናለህ። 26 አምላካችንን እግዚአብሔርን #ለማገልገል ከእነርሱ እንወስዳለንና #ከብቶቻችን ከእኛ ጋር ይሄዳሉ፥ አንድ ሰኮናም አይቀርም፤ አምላካችን የምናገለግለው ምን እንደሆነ ከዚያ እስክንደርስ አናውቅም አለ" (ዘጽ 10:24-26)
በዚህ ቦታ ላይ አምልኮ ከሚከናወንባቸው መንገዶች አንዱ መስዋዕት መሰዋት እንደሆነ እንመለከታለን። በቁ.24 ላይ ፈርዖን ሙሴን ሂዱ እግዚአብሔርን አገልግሉ ነገር ግን በጎቻችሁን እና ከብቶቻችሁን ተው ሲለው ሙሴ አንተ ለአምላካችን ለእግዚአብሔር የምንሰዋውን መስዋዕት ትሰጠናለህ አምላካችን እግዚአብሔርን ለማገልገል ከእነርሱ እንወስዳለንና ከብቶቻችን ከእኛ ጋር ይሄዳሉ አለው። ስለዚህ እግዚአብሔር ከሚመለክባቸው መንገዶች አንዱ መስዋዕት መሰዋት እንደሆነ ከዚህ እንረዳለን።
በዚህ ስፍራ ላይ "ማገልገል" ተብሎ የተተረጎመው የሰብዓ ሊቃናቱ የግሪክ ቃል "λατρεῦσαι" ወይም "ላትሬኡሳይ" የሚለው ቃል ሲሆን ራዕይ 7:15 ላይ ያለው ራሱ ቃል ነው (Strong's G3000) በሌሎች የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ላይም አምልኮ ተብሎ ተተርጉሟል (ዘዳ 10:20 LXX ሉቃ 4:8) በዋናው ዕብራይስጥ ደግሞ "עֲבֹד" ወይም "ኤቬድ" የሚለው ቃል ሲሆን (Strong's H5647) በሌሎች የብሉይ ኪዳን ክፍሎች ላይ አምልኮ ተብሎ የተተረጎመው የዕብራይስጥ ቃል ነው (1ሳሙ 7:4) ስለዚህ ከዘጽ 10:24-26 እንደምንረዳው መስዋዕት መሰዋት አምልኮ የሚተገበርበት ወይም የሚፈጸምበት አንዱ መንገድ ነው።

❤13
2) ጾምና ጸሎት
"እርስዋም ሰማኒያ አራት ዓመት ያህል መበለት ሆና በጣም አርጅታ ነበር፤ #በጾምና_በጸሎትም ሌሊትና ቀን #እያገለገለች ከመቅደስ አትለይም ነበር" (ሉቃ 2:37)
በዚህ ስፍራ ላይ አምልኮ ከሚፈጸምባቸው መንገዶች አንዱ ጾምና ጸሎት መሆኑን እናያለን። ከአሴር ወገን የሆነችው የፋኑኤል ልጅ ነቢይቱ ሐና ነበረች። እርሷም ከድንግልናዋ ጀምራ ከባልዋ ጋር ሰባት ዓመት ኖራ ነበር (ሉቃ 2:36) እርሷም ሰማንያ አራት ዓመት ያህል መበለት ሆና በጣም አርጅታ ነበር፥ በጾምና በጸሎትም ሌሊትና ቀን እያገለገለች ከመቅደስ አትለይም ነበር (ሉቃ 2:37) ስታገለግል ወይም ስታመልክ የነበረው በመጾምና በመጸለይ ነው። በዚህ ቦታ ላይ "ስታገለግል" ተብሎ የተተረጎመው ቃል "λατρεύουσα" ወይም "ላትሬኡሳ" ሲሆን (Strong's G3000) ራሱ ራዕ 7:15 ላይ ያለው ቃል ነው። በሌሎች የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ላይም አምልኮ ተብሎ ተተርጉሟል (ኢያ 24:14 LXX 2ጢሞ 1:3) ይህ ጾምና ጸሎት አምልኮ ከሚፈጸምባቸው መንገዶች አንዱ መሆኑን ያሳያል።
3) ስግደት
"በባቢሎን አውራጃ ሥራ ላይ የሾምሃቸው ሲድራቅና ሚሳቅ አብደናጎም የሚባሉ አይሁድ አሉ፤ ንጉሥ ሆይ፥ እነዚህ ሰዎች ትእዛዝህን እንቢ ብለዋል፤ አማልክትህን #አያመልኩም፥ ላቆምኸውም ለወርቁ ምስል #አይሰግዱም" (ዳን 3:12)
በዚህ ቦታ ላይ አምልኮ ከሚተገበርባቸው መንገዶች አንዱ ስግደት እንደሆነ እንመለከታለን። ሲድራቅ ሚሳቅና አብድናጎ የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ላቆመው የወርቅ ምስል አለመስገዳቸውን ያዩ ከለዳውያን (ዳን 3:8) ወደ ንጉሡ ቀርበው በባቢሎን አውራጃዎች የሾማቸው ሲድራቅ ሚሳቅ አብድናጎ የሚባሉ አይሁድ እንዳሉና ትዕዛዙን እንቢ እንዳሉ፥ የእርሱንም አማልክት እንደማያመልኩ ላቆመውም የወርቅ ምስል እንደማይሰግዱ ነገሩት። ስለዚህ ስግደት አምልኮ ከሚተገበርባቸው መንገዶች አንዱ እንደሆነ ከዚህ እንረዳለን።
በዚህ ቦታ ላይ "አያመልኩም" ተብሎ የተተረጎመው የሰብዓ ሊቃናቱ የግሪክ ቃል "λατρεύουσιν" ወይም "ላትሬኡሲን" ሲሆን (Strong's G3000) ራሱ ራዕይ 7:15 ላይ ያለው ቃል ነው። በሌሎች የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ላይም አምልኮ ተብሎ ተተርጉሟል (ዘጽ 23:25 LXX ሐዋ 7:7) በዋናው አረማይክ ደግሞ "פָלְחִין" ወይም "ፕላኺን" ሲሆን (Strong's H6399) በሌሎች ክፍሎች ላይ አምልኮ ተብሎ የተተረጎመ ቃል ነው (ዳን 6:16) ይህ አምልኮ ግን የተተገበረው በስግደት ነው። ስለዚህ ስግደት አምልኮ ከመተግበርያ መንገዶች አንዱ ነው ማለት ነው።
4) የቤተ መቅደስ አገልግሎት
"ይህም እንደዚህ ተዘጋጅቶ ሳለ፥ ካህናት #አገልግሎታቸውን እየፈጸሙ ዘወትር በፊተኛይቱ #ድንኳን ይገቡባታል" (ዕብ 9:6)
በዚህ ስፍራ ላይ አምልኮ ከሚፈጸምባቸው መንገዶች አንዱ የቤተ መቅደስ አገልግሎት እንደሆነ እንመለከታለን። የዕብራውያን ጸሐፊ ሐዋርያው ጳውሎስ ስለ ቀደሙት የብሉይ ኪዳን ካህናት ሲናገር ካህናቱ አገልግሎታቸውን እየፈጸሙ ዘወትር በፊተኛይቱ ድንኳን ይገቡባታል ይላል። የብሉይ ኪዳኑ መቅደስ ቅድስትና ቅድስተ ቅዱሳን ተብሎ ይከፈል የነበረ ሲሆን ቅድስት በሚባለው ወይም በዕብ 9:6 ፊተኛይቱ በተባለው ድንኳን ውስጥ ካህናት ይገቡና ያገለግሉ ነበር። በቅድስተ ቅዱሳን ወይም በዕብ 9:7 ሁለተኛይቱ በሚባለው ድንኳን ውስጥ ግን ሊቀ ካህናቱ ብቻ በዓመት አንድ ጊዜ ይገባባታል። ይህ የቤተ መቅደስ አገልግሎት አምልኮ ከሚፈጸምባቸው መንገዶች አንዱ መሆኑን ያሳያል።
በዚህ ቦታ ላይ "አገልግሎታቸው" ተብሎ የተተረጎመው የግሪክ ቃል "λατρείας" ወይም "ላትሬያስ" የሚለው ሲሆን (Strong's G2999) ራሱ ራዕ 7:15 ላይ ያለው ቃል ነው። በሌሎች የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ላይም አምልኳዊ የሆነን አገልግሎት ለማመልከት ጥቅም ላይ ውሏል (ሮሜ 12:1 1ዜና 28:12-13 LXX) ስለዚህ በዕብ 9:6 ላይ የተነገረው የካህናቱ አገልግሎት አምልኮ ነው። ይህ አምልኮ ግን ይፈጸም የነበረው በቤተ መቅደስ አገልግሎት ነው። ስለዚህ ከዚህ የቤተ መቅደስ አገልግሎት አምልኮ ከሚፈጸምባቸው መንገዶች አንዱ እንደሆነ እንረዳለን።

❤7🔥2
🚩 አምልኮተ ክርስቶስ (የራዕይ 7 ማብራሪያ) (ክፍል 2)
ባለፈው ክፍል ላይ የእግዚአብሔር ልጅ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በስጋ የመጣው መለኮት እንደሆነ እና በዚህም ምክንያት አምልኮ እንደሚገባው መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚያስተምር መመልከት ጀምረን ነበር። ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ እውነተኛ መለኮት ከሆነ አምልኮ ስለሚገባው ማለት ነው። ለዚህ እውነታ ማሳያ ይሆን ዘንድ ራዕ 7:9-15 በመጥቀስ እንዴት እግዚአብሔር በዚያ ክፍል ላይ እንደተመለከ እና በሌሎች የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎችም አምልኮ የሚከናወንባቸውን መንገዶች ለመመልከት ሞክረን ነበር።
ዛሬ እግዚአብሔር ቢፈቅድ ከዚያ በመቀጠል እንዴት በራዕይ 7:9-15 ክርስቶስ ከእግዚአብሔር ጋር በአንድነት እንደተመለከ ለማየት እንሞክራለን፦
ባለፈው ክፍል ለማየት እንደሞከርነው በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ብዙ አምልኮ የማከናወኛ መንገዶች አሉ። መስዋዕት መሰዋት፥ ጾምና ጸሎት፥ ስግደት፥ የቤተ መቅደስ አገልግሎት እነዚህ ሁሉ አምልኮ የመፈጸሚያ መንገዶች ናቸው። ከእነዚህ መንገዶች በተጨማሪ ግን ሌላ አምልኮ የመፈጸሚያ መንገድ አለ። እርሱም መለኮታዊ ባህርያትን መስጠት ወይም attribution ነው። ይህም ለእግዚአብሔር መለኮታዊ ባህርያትን መንገር ወይም እነዚያ መለኮታዊ ባህርያት የእርሱ መሆኑን መመስከር ማለት ነው።
ለምሳሌ፦
"የእግዚአብሔርን ስም እጠራለሁና፤ #ለአምላካችን ታላቅነትን #ስጡ" (ዘዳ 32:3)
በዚህ ቦታ ላይ እግዚአብሔር የእስራኤል ልጆች እንዲዘምሩት ያስጻፈውን መዝሙር እንመለከታለን (ዘዳ 31:22) በዚህ መዝሙር ላይ "ለአምላካችን ታላቅነትን ስጡ" ይላል። ምን ማለት ነው ለአምላካችን ታላቅነትን ስጡ ማለት? መጽሐፍ ቅዱስ እግዚአብሔር ቀድሞውኑም ታላቅ መሆኑን ያስተምራል (ዘዳ 3:24 ዘዳ 5:24 ዘዳ 11:2) ታዲያ ታላቅነትን ስጡ ማለት ምን ማለት ነው? ስንል ይህን ባህርይ ለእርሱ ንገሩ ማለት ነው። ታላቅ እንደሆነ፥ ታላቅነት የእርሱ እንደሆነ መስክሩ ማለት ነው። ይህንኑ ጽንሰ ሀሳብ በመከተል በብሉይ ኪዳን ውስጥ ቅዱሳን እግዚአብሔር ታላቅ መሆኑን የመሰከሩት ለዚያ ነው። ይህ አምልኮ ከሚፈጸምባቸው መንገዶች አንዱ በመሆኑ ማለት ነው፦
" #እግዚአብሔርን ከእኔ ጋር #ታላቅ አድርጉት፥ በአንድነትም ስሙን ከፍ ከፍ እናድርግ" (መዝ 34:3)
"አቤቱ፥ በሰማይና በምድር ያለው ሁሉ የአንተ ነውና #ታላቅነትና ኃይል፥ ክብርም፥ ድልና ግርማ ለአንተ ነው፤ አቤቱ፥ መንግሥት #የአንተ_ነው፥ አንተም በሁሉ ላይ ከፍ ከፍ ያልህ ራስ ነህ" (1ዜና 29:11)
" #እግዚአብሔር_ታላቅ እንደ #ሆነ፥ ጌታችንም ከአማልክት ሁሉ እንዲበልጥ አውቄአለሁና" (መዝ135:5)
✍️ ይህ ከራዕይ 7:9-15 ጋር እንዴት ይገናኛል?
በራዕይ 7:9-15 ላይ ሲከናወን የምንመለከተው አምልኮ የተከናወነው በዚህ መንገድ ነው። በራዕይ 7:15 ላይ እነዚያ ነጭ ልብስን የለበሱት ሰዎች እግዚአብሔርን እንደሚያመልኩት ተገልጾ ነበር። በራዕይ 7:9-15 አውድ መሰረት እነዚያ ሰዎች እግዚአብሔርን እንዴት ነው የሚያመልኩት ከተባለ መልሱ ለእርሱ መለኮታዊ ባህርይን በመስጠት ወይም በattribution ነው። በራዕይ 7:10 ላይ እንደምንመለከተው ማዳን የእግዚአብሔር መሆኑን ይመሰክራሉ፦
"በታላቅም ድምፅ እየጮሁ። በዙፋኑ ላይ ለተቀመጠው #ለአምላካችንና ለበጉ #ማዳን ነው አሉ" (ራዕይ 7:10)
ስለዚህ በቁ.15 ላይ ያመልኩታል ሲል በአውዱ መሰረት የሚያመልኩት በዚህ መንገድ ነው። እርሱን የሚያመልኩት ይህን መለኮታዊ ባህርይ ለእርሱ በመስጠት ወይም attribute በማድረግ ነው። እግዚአብሔር በተለያዩ መንገዶች ሊመለክ የሚችል ሲሆን እነዚህ ነጭ ልብስን የለበሱ ከሕዝብ ከነገድ ከቋንቋ የተዋጁ ሰዎች እርሱን የሚያመልኩበት መንገድ ይህ ነው። ማዳን የእርሱ መሆኑን በመመስከር ወይም መለኮታዊ የሆነውን የአዳኝነት ባህርይ ለእርሱ በመስጠት ወይም attribute በማድረግ ማለት ነው።
♦️ አስተውሉ! በቁ.15 ላይ እነዚህ ሰዎች እግዚአብሔርን ያመልኩታል ተብሏል። ስለዚህ በአውዱ መሰረት ይህን አምልኮ እንዴት ፈጸሙት? እንዴትስ ተገበሩት? የሚለው ጥያቄ ወሳኝ ጥያቄ ነው። አምልኮ ተግባር ወይም action ስለሆነ ይህ ተግባር እንዴት እንደተከናወነ መታወቅ አለበት። በአውዱ መሰረት በቁ.15 ላይ ያለው አምልኮ የተከናወነው በቁ.10 ላይ ባለው መንገድ ነው። ትክክለኛው አውዳዊ መረዳት ይህ ነው።
በብሉይ ኪዳንም እግዚአብሔር አምላክ የተመለከው በዚሁ መንገድ ነው። የእግዚአብሔር ቅዱሳን እግዚአብሔርን ካመለኩበት መንገዶች አንዱ ማዳን የእርሱ መሆኑን በመመስከር ነው፦
" #ማዳን_የእግዚአብሔር_ነው፥ በረከትህም በሕዝብህ ላይ ነው" (መዝ 3:8)
"እኔ ግን በምስጋና ቃል እሠዋልሃለሁ፤ የተሳልሁትንም እከፍላለሁ። #ደኅንነት_ከእግዚአብሔር ዘንድ #ነው" (ዮናስ 2:10)
" #ከእግዚአብሔር ዘንድ ምሕረት፥ #በእርሱም ዘንድ ብዙ #ማዳን ነውና እስራኤል በእግዚአብሔር ይታመን" (መዝ 130:7)
"እነሆ፥ #የእግዚአብሔር_እጅ_ከማዳን አላጠረችም፥ ጆሮውም ከመስማት አልደነቈረችም" (ኢሳ 59:1)
ስለዚህ በራዕ 7:10 ላይም ለእግዚአብሔር ቀርቦ የምንመለከተው አምልኮ ይህ ራሱ አምልኮ ነው። በቁ.15 ላይ "አምልኮ" ወይም "λατρεύουσιν/ላትሬኦሲን" የተባለው ይህ attribution ነው። ማዳን የእርሱ መሆኑ መመስከሩ ወይም መለኮታዊ ባህርይ የሆነው የአዳኝነት ባህርይ ለእርሱ መሰጠቱ በአውዱ መሰረት እግዚአብሔር የተመለከበት መንገድ እንደሆነ እንረዳለን።

❤3
✍️ ነገር ግን በቁ.10 ላይ ማዳን የእርሱ ነው የተባለው ለማን ጭምር ነው?
ከላይ በማስረጃ እንዳየነው በቁ.10 ላይ ማዳን ለእግዚአብሔር ተነግሯል ወይም ማዳን የእርሱ እንደሆነ ተመስክሯል። ይህ በአውዱ ላይ ቃል በቃል አምልኮ ተብሏል (ቁ.15) ደግሞም በብሉይ ኪዳን እግዚአብሔር የተመለከበት አምልኮ ነው። ታዲያ ግን ይህ አምልኮ ለእግዚአብሔር ሲቀርብ ከማን ጋር በአንድነት ቀረበ?
"በታላቅም ድምፅ እየጮሁ። በዙፋኑ ላይ ለተቀመጠው ለአምላካችንና #ለበጉ #ማዳን ነው አሉ" (ራዕይ 7:10)
ይህ በአውዱ ላይ አምልኮ የተባለው ደግሞም በብሉይ ኪዳን አስተምህሮ መሰረት አምልኮ የሆነው attribution ለእግዚአብሔር ሲቀርብ ከበጉ ጋር በአንድነት ነው! ማዳን ለእግዚአብሔርም ለበጉም እንደሆነ ተመስክሯል! ስለዚህ በጉ ከእግዚአብሔር አብ ጋር በአንድነት ተመልኳል ማለት ነው። ይህ በጉ ወይም ልጁ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ከእግዚአብሔር አብ ጋር በመለኮት አንድነት እንደሚመለክ የሚያሳይ ተጨባጭ ማስረጃ ነው!
♦️ አስተውሉ! በቁ.15 ላይ ነጭ ልበሱን የለበሱት ሰዎች እግዚአብሔርን ያመልኩታል ተብሏል። እነዚህ ሰዎች እግዚአብሔርን እንዴት እንደሚያመልኩት በቁ.10 ላይ ተገልጿል። በቁ.10 ላይ ግን እግዚአብሔርን ሲያመልኩት ከበጉ ጋር በአንድነት ነው። ለእግዚአብሔር የሰጡትን አምልኳዊ attribution ያቀረቡት ከበጉ ጋር በአንድነት ነው። ስለዚህ በጉ ከእግዚአብሔር አብ ጋር በአንድ አምላክነት በዚህ አምልኮ ተመልኳል ማለት ነው። ይህ በጉ ወይም ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ ከአብ ጋር በመለኮት እንደሆነ፥ በመለኮት አንድ ስለሆነም ከአብ ጋር በአንድነት እንደሚመለክ በሚገባ ያረጋግጣል። ከአምላክ ውጪ ሊመለክ የሚገባው ማንም የለምና።
በራዕይ 7:10 ላይ እንደተገለጸው ማዳን የበጉ ወይም የእግዚአብሔር ልጅ የኢየሱስ ክርስቶስ ነው፦
" #የሰው_ልጅ የጠፋውን ሊፈልግና #ሊያድን መጥቶአለና አለው" (ሉቃስ 19:10)
" #ልጅም ትወልዳለች፤ እርሱ ሕዝቡን #ከኃጢአታቸው_ያድናቸዋልና ስሙን #ኢየሱስ ትለዋለህ" (ማቴ 1:21)
"ዛሬ በዳዊት ከተማ #መድኃኒት እርሱም #ክርስቶስ ጌታ የሆነ ተወልዶላችኋልና" (ሉቃ 2:11)
"ስለ እነርሱም #ሊያማልድ ዘወትር በሕይወት ይኖራልና ስለዚህ ደግሞ በእርሱ ወደ እግዚአብሔር የሚመጡትን ፈጽሞ #ሊያድናቸው ይችላል" (ዕብ 7:25)
"ዓለም #በልጁ_እንዲድን ነው እንጂ፥ በዓለም እንዲፈርድ እግዚአብሔር ወደ ዓለም አልላከውምና" (ዮሐ 3:17)
"እኛም አይተናል አባትም #ልጁን የዓለም #መድኃኒት ሊሆን እንደ ላከው እንመሰክራለን" (1ዮሐ 4:14)
" #መዳንም በሌላ በማንም የለም፤ #እንድንበት ዘንድ የሚገባን ለሰዎች የተሰጠ #ስም ከሰማይ በታች ሌላ የለምና" (ሐዋ 4:12)
"ያን መንፈስም፥ በጸጋው ጸድቀን በዘላለም ሕይወት ተስፋ ወራሾች እንድንሆን፥ #በመድኃኒታችን_በኢየሱስ_ክርስቶስ በእኛ ላይ አትርፎ አፈሰሰው" (ቲቶ 3:6-7)
"እንዲሁ ወደ ዘላለሙ ወደ ጌታችንና #መድኃኒታችን ወደ #ኢየሱስ_ክርስቶስ መንግሥት መግባት በሙላት ይሰጣችኋልና" (2ጴጥ 1:11)
✍️ በመጽሐፍ ቅዱስ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ አዳኝ መሆኑ በተደጋጋሚ ተገልጿል። ስለዚህ ይህ መለኮታዊ የሆነው የአዳኝነት ባህርይ የእርሱ ባህርይ ነው ማለት ነው። ስለዚህ ራዕይ 7:10 ላይ እንደምንመለከተው ማዳን እንደ attribution ከአባቱ ከእግዚአብሔር አብ ጋር በአንድነት ሊነገርለት ወይም ሊመሰከርለት ይችላል ማለት ነው። ይህ ደግሞ ከአብ ጋር በመለኮት አንድነት የተመለከበት አምልኮ ነው።
▶️ መደምደሚያ
በነበሩን ተከታታይ ክፍሎች እግዚአብሔር አምላክ በራዕይ 7:9-15 ላይ እንዴት እንደተመለከ ለማየት ሞክረናል። እግዚአብሔር አምላክ መስዋዕት፥ ስግደት፥ ጾምና ጸሎት፥ የቤተ መቅደስ አገልግሎት በመሳሰሉት የማምለኪያ መንገዶች እንደሚመለክና ከእነዚህም አምልኮ ከሚከናወንባቸው መንገዶች አንዱ attribution እንደሆነ ለማየት ሞክረናል። በራዕይ 7:10 ላይም ማዳን ለእርሱ attribute ተደርጎለት በዚሁ መንገድ እንደተመለከና ይህ ራሱ attribution በራዕይ 7:15 ላይ አምልኮ ተብሎ እንደተጠራ፥ በብሉይ ኪዳንም ሲመለክ የነበረበት መንገድ እንደሆነ ለመመልከት ሞክረናል።
ነገር ግን ይህ በራዕይ 7:10 ላይ ማዳን የበጉም ወይም የልጁ የኢየሱስ ክርስቶስ እንደሆነ ተመስክሯል። በሌሎች የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎችም ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ አዳኝ መሆኑ ተገልጿል። ስለዚህ ለእግዚአብሔር የቀረበው ይህ አምልኮ ለበጉም ወይም ለልጁ ጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስም በመለኮት አንድነት የቀረበ አምልኮ ነው ማለት ነው። ስለዚህ እግዚአብሔር አምላክ የሚመለከው ከልጁ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር በአንድ አምላክነት ነው ማለት ነው። ይህ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ከአብ ጋር አንዱን መለኮት እንደሆነ፥ ከአብ ጋር አንድ መለኮት በመሆኑም ከአብ ጋር በአንድነት እንደሚመለክ በማያሻማ አኳሃን ያረጋግጣል።
ይህን ጌታ አውቃችሁት ያልዳናችሁ አውቃችሁት ትድኑ ዘንድ የዘወትር ጸሎታችን ነው!
ጌታ ይርዳን!

❤10🔥2
👍7❤5🔥2
🚩 እሬቻ
"1 በመካከልህም ነቢይ ወይም ሕልም አላሚ ቢነሣ፥ ምልክትም ተአምራትም ቢሰጥህ፥ 2 እንደ ነገረህም ምልክቱ ተአምራቱም ቢፈጸም፥ እርሱም። ሄደን #የማታውቃቸውን ሌሎች #አማልክት እንከተል #እናምልካቸውም ቢልህ" (ዘዳ 13:1-2)
ሰሞኑን እሬቻ የተሰኘው በአል በአዲስ አበባ ሲከበር ነበር። ይህ በአል ሃይማኖታዊ በአል ሲሆን የኦሮሞ ሕዝብ ወንጌልን ሰሞቶ ወደ ክርስትና ከመምጣቱ በፊት የነበረበት ግልጽ ጣዖት አምልኮ ነው። በክርስቶስ ኢየሱስ ወንጌል አማካኝነት የእስራኤልን አምላክ ከማወቁ በፊት የነበረበት ጣዖታዊ ባዕድ አምልኮ ነው
የእግዚአብሔር ቃል እንደሚናገረው ከግብፅ ምድር የወጡት እስራኤላውያን ካወቁት አምላክ ከእግዚአብሔር/ከያሕዌ በቀር ሌሎች አማልክትን ማምለክ እግዚአብሔር የሚጸየፈው ጣዖት አምልኮ ነው። በእሬቻ በአል የሚመለከው ዋቃና ሌሎቹ ጣዖታት (አቴቴ፥ ቦርንትቻ ወዘተ...) በሙሉ እስራኤል ያላወቃቸው እርኩሳን ጣዖታት ናቸው (ዘዳ 29:17 1ነገ 11:7) እነዚህን ጣዖታት ማምለክ በጣዖት አምላኪነት ያስጠይቃል፥ የእግዚአብሔርንም ቁጣ በምድር ላይ ያመጣል
✍️ መጽሐፍ ቅዱስ ከእስራኤል አምላክ ከእግዚአብሔር ውጪ የሆኑ አማልክት በሙሉ አጋንንት እንደሆኑ ይናገራል፦
"17 #እግዚአብሔር ላልሆኑ #አጋንንት፥ #ለማያውቋቸውም #አማልክት" (ዘዳ 32:17)
"አይደለም፤ ነገር ግን #አሕዛብ የሚሠዉት #ለአጋንንት እንዲሆን እንጂ #ለእግዚአብሔር እንዳይሠዉ እላለሁ፤ ከአጋንንትም ጋር #ማኅበረተኞች #እንድትሆኑ #አልወድም" (1ቆሮ 10:20)
ስለዚህ አንድ ሰው በማወቅም ሆነ ባለማወቅ ወደዚህ በአል ከሄደና ተሳታፊ ከሆነ በአምልኮተ አጋንንት እየተሳተፈ ነው። አጋንንትን እያመለከ ነው። የእግዚአብሔር ቃል "..የአጋንንት ማህበርተኞች እንድትሆኑ አልወድም.." እያለ አንድ ሰው ወደዚህ ባዕድ አምልኮ ሄዶ ከተባበረ የእርኩሳን መናፍስት ማህበርተኛ እየሆነ ነው። እግዚአብሔርን ያልሆኑ ሰይጣናትን በቀጥታ እያመለከ ነው
በክርስቶስ ኢየሱስ የሚያምኑ ክርስቲያኖች ከጣዖታት ጋር #በምንም_አይነት መንገድ ሕብረት ሊኖራቸው አይችልም፦
" #ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስም #ከጣዖት ጋር ምን #መጋጠም አለው? እኛ የሕያው እግዚአብሔር ቤተ #መቅደስ ነንና እንዲሁም እግዚአብሔር ተናገረ እንዲህ ሲል። በእነርሱ እኖራለሁ በመካከላቸውም እመላለሳለሁ፥ አምላካቸውም እሆናለሁ እነርሱም ሕዝቤ ይሆናሉ።" (2ቆሮ 6:16)
➢ ከላይ የተገለጸው አይነት ጣዖት አምልኮ ሁሉ ደግሞ የዘላለምን ሞት እንደሚያስከትል መጽሐፍ ቅዱስ አስረግጦ ይነግረናል፦
"ዳሩ ግን የሚፈሩና የማያምኑ የርኵሳንም የነፍሰ ገዳዮችም የሴሰኛዎችም የአስማተኛዎችም #ጣዖትንም_የሚያመልኩ የሐሰተኛዎችም ሁሉ ዕድላቸው #በዲንና_በእሳት በሚቃጠል ባሕር ነው፤ ይኸውም #ሁለተኛው_ሞት_ነው" (ራዕ 21:8)
"ውሻዎችና አስማተኞች ሴሰኛዎችም ነፍሰ ገዳዮችም #ጣዖትንም_የሚያመልኩት ውሸትንም የሚወዱና የሚያደርጉ ሁሉ #በውጭ_አሉ" (ራዕ 22:15)
"20 መዳራት፥ #ጣዖትን_ማምለክ፥ ምዋርት፥ ጥል፥ ክርክር፥ ቅንዓት፥ ቁጣ፥ አድመኛነት 21 መለያየት፥ መናፍቅነት፥ ምቀኝነት፥ መግደል፥ ስካር፥ ዘፋኝነት፥ ይህንም የሚመስል ነው። አስቀድሜም እንዳልሁ፥ እንደዚህ ያሉትን የሚያደርጉ #የእግዚአብሔርን መንግሥት #አይወርሱም" (ገላ 5:20-21)
"9 ወይስ ዓመፀኞች የእግዚአብሔርን መንግሥት እንዳይወርሱ አታውቁምን? አትሳቱ፤ ሴሰኞች ቢሆን ወይም #ጣዖትን_የሚያመልኩ ወይም አመንዝሮች ወይም ቀላጮች ወይም ከወንድ ጋር ዝሙት የሚሠሩ 10 ወይም ሌቦች ወይም ገንዘብን የሚመኙ ወይም ሰካሮች ወይም ተሳዳቢዎች ወይም ነጣቂዎች የእግዚአብሔርን #መንግሥት #አይወርሱም" (1ቆሮ 6:9-10)
"ይህን እወቁ፤ አመንዝራም ቢሆን ወይም ርኵስ ወይም የሚመኝ እርሱም #ጣዖትን_የሚያመልክ በክርስቶስና በእግዚአብሔር #መንግሥት ርስት #የለውም" (ኤፌ 5:5)
▶️ የዚህ አስከፊ እርኩሰት ውጤት የዘላለም ሞት በመሆኑ፥ መጽሐፍ ቅዱስ በተደጋጋሚ ከጣዖት አምልኮ እንድንሸሽ አዝዞናል፦
"ልጆች ሆይ፥ #ከጣዖታት ራሳችሁን #ጠብቁ" (1ዮሐ 5:21)
"ስለዚህ፥ ወዳጆቼ ሆይ፥ #ጣዖትን ከማምለክ #ሽሹ" (1ቆሮ 10:14)
"ሕዝብም ሊበሉ ሊጠጡም ተቀመጡ ሊዘፍኑም ተነሡ ተብሎ እንደ ተጻፈ ከእነርሱ አንዳንዶቹ እንዳደረጉት #ጣዖትን #የምታመልኩ #አትሁኑ" (1ቆሮ 10:7)
"ነገር ግን #ከጣዖት ርኵሰትና ከዝሙት ከታነቀም ከደምም #ይርቁ ዘንድ እንድንጽፍላቸው እቈርጣለሁ" (ሐዋ 15:20)
"አምነው ስለ ነበሩ አሕዛብ ግን #ለጣዖት ከተሠዋ ከደምም ከታነቀም ከዝሙትም #ነፍሳቸውን #እንዲጠብቁ ፈርደን እኛ ጽፈንላቸዋል" (ሐዋ 21:25)
" #ለጣዖት ከተሠዋ፥ ከደምም፥ ከታነቀም፥ ከዝሙትም #ትርቁ ዘንድ ከዚህ ከሚያስፈልገው በቀር ሌላ ሸክም እንዳንጭንባችሁ እኛና መንፈስ ቅዱስ ፈቅደናልና፤ ከዚህም ሁሉ ራሳችሁን ብትጠብቁ በመልካም ትኖራላችሁ። ጤና ይስጣችሁ" (ሐዋ 15:28-29)
▶️ እሬቻ ባህል አይደለም። እሬቻ በባህል ስም የሚካሄድ ጣዖት አምልኮ ነው። በባህልና በሌሎች ሰበቦች ስም እግዚአብሔር በልጁ ወንጌል ብርሃን ካዳነንና ካላቀቀን ጣዖት አምልኮ ጋር ተመልሰን መቆራኘት፥ ተቆራኝተንም በዚህ እርኩሰት ረክሰን ነፍሶቻችንን ማጣት የለብንም!
ቃሉ እንደሚለው እግዚአብሔርን #ብቻ እናምልክ!
"ሳሙኤልም የእስራኤልን ቤት ሁሉ። በሙሉ ልባችሁ ወደ እግዚአብሔር ከተመለሳችሁ እንግዶችን አማልክትና አስታሮትን ከመካከላችሁ አርቁ፥ ልባችሁንም ወደ #እግዚአብሔር አቅኑ፥ እርሱንም #ብቻ #አምልኩ፤ ከፍልስጥኤማውያንም እጅ ያድናችኋል ብሎ ተናገራቸው" (1ሳሙ 7:3)
"ያን ጊዜ ኢየሱስ። ሂድ፥ አንተ ሰይጣን ለጌታህ #ለአምላክህ ስገድ እርሱንም #ብቻ #አምልክ ተብሎ ተጽፎአልና አለው" (ማቴ 4:10)
♦️ በክርስቶስ ስም የእሬቻን ጣዖት አምልኮ #እንቢ በሉት! Say #No to irecha Idol Worship in the name of Christ!

❤35👍7👏1
🚩 የዕብራውያን መልእክት ጸሐፊ (ክፍል 27)
ባለፉት ተከታታይ ክፍሎች የዕብራውያን መልእክት ጸሐፊ ሐዋሪያው ጳውሎስ ለመሆኑ ከራሱ ከዕብራውያን መልእክት ውስጠ-ጽሑፋዊ (inter-textual) ማስረጃዎችን ማቅረብ ጀምረን ነበር። ሙስሊሞች ሆኑ ሌሎች ከክርስትና ውጪ ያሉ አካላት የዕብራውያን መልእክት ጸሐፊ ስለማይታወቅ መጽሐፉ የመጽሐፍ ቅዱስ አካል መሆን የለበትም፥ የእግዚአብሔርም ቃል ሊሆን አይችልም ብለው ሊሟገቱ ይሞክራሉ።
ነገር ግን ባለፉት ክፍሎች ለማሳየት እንደሞከርነው ይህ ፍጹም ስህተት የሆነ አመለካከት ነው። የዕብራውያን መልእክት ጸሐፊ ሐዋሪያው ጳውሎስ ለመሆኑ ከምሁራንና ከቤተክርስቲያን ታሪክ ብዙ ማስረጃዎችን ማምጣት ይቻላል። በተጨማሪም ከራሱ ከዕብራውያን መልእክት ጸሐፊው ራሱ ሐዋሪያው ጳውሎስ መሆኑን የሚያረጋግጡ ማስረጃዎችንም ማቅረብ ይቻላል
▶️ እግዚአብሔር ቢፈቅድ በዚህም ክፍል ላይ ካለፉት ክፍሎች በመቀጠል የዕብራውያኑ ጸሐፊ ራሱ ሐዋሪያው ጳውሎስ መሆኑን የሚያረጋግጡ ተጨማሪ ውስጠ-ጽሑፋዊ (inter-textual) ማስረጃዎችን ማቅረብ እንቀጥላለን፦
54) አዲስን መሰረት አለመመስረት
"ስለዚህ የክርስቶስን ነገር መጀመሪያ የሚናገረውን ቃል ትተን ወደ ፍጻሜ እንሂድ፤ #መሠረትን_ደግመን_አንመሥርት፥ እርሱም ከሞተ ሥራ ንስሐና በእግዚአብሔር እምነት፥ ስለ ጥምቀቶችና እጆችንም ስለ መጫን ስለ ሙታንም ትንሣኤ ስለ ዘላለም ፍርድም ትምህርት ነው" (ዕብ 6:1-2)
በዚህ ስፍራ ላይ የዕብራውያን ጸሐፊ አዲስን መሰረት ስላለመመስረት ሲናገር እንመለከታለን። በበፊተኛው ምዕራፍ ላይ የዕብራውያን ጸሐፊ የዕብራውያን ክርስቲያኖችን እንዳልበሰሉ ይነግራቸዋል። በክርስትና ከቆዩበት ጊዜ አንጻር አስተማሪዎች መሆን ሲገባቸው እነርሱ ግን ገና ለወተት ማለትም ስለ እግዚአብሔር ቃል ላለው የመጀመሪያው ትምህርት እንጂ ለጠንካራ ምግብ ወይም ጠለቅ ላለው የነገረ እግዚአብሔር ትምህርት እንዳልደረሱ ይነግራቸዋል (ዕብ 5:12-14) ይህን ካለ በኋላ ነው በቀጣዩ ምዕራፍ ላይ ስለዚህ የክርስቶስን ነገር መጀመሪያ የሚናገረውን ቃል ትተን ወደ ፍጻሜ እንሂድ አዲስ መሰረትም አንመስርት ያለው። ይህ ማለት ስለ ክርስቶስ ማንነት ከመጀመሪያውና ከቀላሉ ትምህርት ተሻግራችሁ ወደ ላቀው ወደ ረቀቀው መረዳት እለፉ ማለት ነው። ሰዎቹ በመንፈሳዊ አረዳዳቸው ለጋ እንደነበሩ በበፊተኛው ምዕራፍ ላይ ስለገለጸ በቀጣዩ ምዕራፍ ላይ ከዚህ ለጋ ከሆነ መንፈሳዊ አረዳድ ወጥታችሁ ወደ ፍጻሜው ማለትም ወደ በለጠውና የበሰሉ ክርስቲያኖች ወዳላቸው መረዳት ኑ ማለት ነው። ነገር ግን ወደ ተሻለው መረዳት ሲመጡ አዲስ መሰረት በመመስረት አይደለም። ማለትም ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን አስመልክቶ ያለውን መሰረታዊውን የክርስትና ትምህርት ትቶ ሌላ ትምህርትን በመፍጠር ወይም በማስተማር አይደለም። የጌታን ማንነት አስመልክቶ በአረዳዳቸው መብሰልና መጨመር ያለባቸው ቀድሞ በተመሰረቱበት መሰረት ላይ ሆነው ነው። የዕብራውያን ጸሐፊ አዲስ መሰረት መመስረት እንደሌለበት መናገሩ ጸሐፊው ሐዋርያው ጳውሎስ ለመሆኑ ውስጠ-ጽሑፋዊ (Inter-Textual) ማስረጃ ነው።
ሐዋርያው ጳውሎስ አዲስ መሰረት መመስረት እንደሌለበት በመልእክቱ ገልጿልና፦
" #ከተመሠረተው_በቀር_ማንም_ሌላ_መሠረት ሊመሠርት #አይችልምና፥ እርሱም ኢየሱስ ክርስቶስ ነው" (1ቆሮ 3:11)
በዚህ ስፍራ ላይ ሐዋርያው ጳውሎስ ከተመሠረተው መሠረት በቀር ማንም ሌላ መሠረት ሊመሠርት እንደማይችልና ይህም መሠረት ኢየሱስ ክርስቶስ እንደሆነ ሲናገር እንመለከታለን። በቁ.4 ላይ አንዱ እኔ የጳውሎስ ነኝ ሁለተኛውም እኔ የአጵሎስ ነኝ ቢል ሥጋውያን መሆናችሁ አይደለምን ይላል። ከቁ.1-3 ላይ የቆሮንቶስ ክርስቲያኖች ለጽኑ መብል ያልደረሱ ወተት ሊጋቱ የሚገባቸው በመንፈሳዊ ደረጃቸው ገና መሆናቸውን ወይም ሥጋውያን መሆናቸውን ከገለጸ በኋላ ይህ ሥጋዊነት ምን እንደሚመስል በቁ.4 ላይ ይናገራል። እርሱም "እኔ የእከሌ ነኝ እኔ የእከሌ ነኝ" ብለው መከፋፈላቸው ነው። ጌታ ኢየሱስን በመከተል ፈንታ ሰውን አይቶ መከፋፈል የሥጋዊነት ምልክት መሆኑን ይገልጻል። ከዚያም በቁ.5 ላይ አጵሎስ ምንድነው? ጳውሎስስ ምንድነው? በእነርሱ እጅ ያመናችሁ አገልጋዮች ናቸው፥ ለእያንዳንዳቸውም ጌታ እንደሰጣቸው እንደሚያገለግሉ ይገልጻል። ከዚያም በቁ.6-7 ላይ እርሱ እንደተከለ አጵሎስ እንዳጠጣ ነገር ግን ያሳደገው እግዚአብሔር እንደነበርና የሚያሳድግ እግዚአብሔር እንጂ የሚተክል ቢሆን ወይም የሚያጠጣ ቢሆን አንዳች አይደለም ይላል። ይቀጥልና በቁ.8 ላይ የሚተክልና የሚያጠጣ አንድ ናቸው ነገር ግን እያንዳንዱ እንደ ራሱ ድካም መጠን የራሱን ደመወዝ ይቀበላል ይላል።
ይህ ማለት የሚተክልም የሚያጠጣም ሁለቱም ከእግዚአብሔር የስራቸውን መጠን የሚከፈላቸው አገልጋዮች ናቸው እንጂ የእምነት መሰረት አይደሉም ማለት ነው። ከዚያም በቁ.9 ላይ የእግዚአብሔር እርሻ ናችሁ የእግዚአብሔር ሕንጻ ናችሁ እኛም ከእርሱ ጋር የምንሰራ ነንና ይላል። ከዚያም በቁ.10 ላይ የእግዚአብሔር ጸጋ እንደተሰጠኝ መጠን እንደ ብልሃተኛ የአናጺ አለቃ መሠረትን መሠረትሁ ሌላውም በራሱ ያንጻል። እያንዳንዱ ግን በእርሱ ላይ እንዴት እንዲያንጽ ይጠንቀቅ ይላል። መሠረትን መሰረትሁ ሲል መሰረታዊውን የክርስትና ትምህርት ለእናንተ በሕንጻ ለተመሰላሁት ክርስቲያኖች አስተማርሁ ማለት ነው። ሌላውም በራሱ ያንጻል ማለት በዚያ በተመሰረተው መሰረት ላይ ከፍ ያሉ ተጨማሪ የክርስትና ትምህርቶችን ያስተምራል ማለት ነው። እያንዳንዱ በእርሱ ላይ እንዴት እንዲያንጽ ይጠንቀቅ ማለት ደግሞ ከመሰረቱ ውጪ የሆነን ትምህርት አለማስተማሩን ይጠንቀቅ ማለት ነው። ለዚያ ነው ቀጥሎ በቁ.11 ላይ ከተመሰረተው በቀር ማንም ሌላ መሠረት ሊመሰርት አይችልም እርሱም ክርስቶስ ነው ያለው። አንድ ጊዜ ከተማሩት ነገረ ክርስቶስ ውጪ የሆነን ሌላ ነገረ ክርስቶስ እንደ እምነት መሰረት መስበክ አይቻልም። በ1ቆሮ 3:11 ላይ የምንመለከተው ይህ ሀሳብ በዕብ 6:1-2 ላይ ያለው ራሱ ሀሳብ መሆኑ የሁለቱም መልእክቶች ጸሐፊ ራሱ ሐዋርያው ጳውሎስ ለመሆኑ ውስጠ-ጽሑፋዊ (Inter-Textual) ማስረጃ ነው።
♦️ 1ቆሮንቶስ 3:1-11 እና ዕብራውያን 5:12-14 እና ዕብ 6:1-2 ከፍተኛ ቁርኝት ያላቸው ክፍሎች ናቸው። በሁለቱም ቦታዎች የአማኞች አለመብሰል ተገልጿል (1ቆሮ 3:1-3 ዕብ 5:12-14) አማኞቹ ስላልበሰሉ በወተት ስለተመሰለው የመጀመሪያው የክርስትና ትምህርት ተነግሯል (1ቆሮ 3:2 ዕብ 5:13) ደግሞም አዲስ መሰረት መመስረት እንደሌለበት ተገልጿል (1ቆሮ 3:11 ዕብ 6:1-2) የሁለቱም ክፍሎች መዋቅር (structure) አንድ አይነት መሆኑ የሁለቱም ክፍሎች ጸሐፊ ራሱ ሐዋርያው ጳውሎስ ለመሆኑ የማይታበል ማስረጃ ነው።

❤4