University of Ethiopia
637 subscribers
126 photos
128 files
203 links
MOE / STAR ACADEMY

ይህ በአይነቱ ልዩ የሆነ ቻናል የተዘጋጀው በ ማህበረሰቡ ጥያቄ መሰረት ሲሆን በውስጡም ለተለያዩ የክፍል ደረጃዎች የሚሆኑ ኖቶች፣pdf፣ሞዴል ፈተናዎች፣ማትሪክና የተለያዩ መረጃዎችን ያገኛሉ።

📚Freshma tutorial በዮኒቨርስቲ ተማሪዎች የተቋቋ
ad service: 📚 MOE በተለየ መልኩ

መረጃዎች በፍጥነት እንዲደርሶት ቻናላችንን #UNMUTE ያድርጉ
Download Telegram
University of Ethiopia
Photo
#Update

የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተናን ከ50 በላይ ያመጡት ከተፈታኞች ውስጥ 3.3 በመቶ መሆናቸውን ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል።

ፈተናውን በትክክል ከወሰዱት 896,520 ተማሪዎች ውስጥ ከግማሽ በላይ ያመጡት፤ 29,909 መሆኑን ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ተናግረዋል።

ሚኒስትሩ ይህን ያሉት በትላንትናው ዕለት ይፋ የተደረገውን የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ውጤትን አስመልክቶ ዛሬ በሰጡት መግለጫ ላይ መሆኑን ኢትዮጵያ ኢንሳይደር ዘግቧል።

@Temihert
Hello students
Remedial Exam Tentative Schedule‼️

የ Remedial ተማሪዎች በማዕከል የሚዘጋጀውን ፈተና ለመፈተን ጊዜያዊ የሆነ Program ነው።

━━━━━━━━━

#ለፈጣን እና ታማኝ መረጃ

👇👇👇👇👇👇

#Share
#Share

@Temihert
Channel name was changed to «Exam waiting.........»
ሀገረ አቀፍ ፈተናዎች . . .

እንደ ትምህርት ሚኒስቴር እና ሀገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት መረጃ :

የሬሜዲያል ፈተና ፦

- በልዩ ሁኔታ የሬሜዲያል ፕሮግራም ተጠቃሚ የሆኑ ተማሪዎች ፈተና ዛሬ ሰኔ 30/ 2015 ዓ/ም ተጠናቋል።

(አሁን ላይ ያልተፈተኑ የግል ተማሪዎች ወደፊት በሚገለፅ ጊዜ በመስከረም 2016 ዓ/ም እንደሚፈቱ የትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል)

- በ2016 ዓ/ም ፍሬሽማን ፕሮግራም ለመከታተል ብቁ ሆነው የሚገኙ በተቋማት የውስጥ ፈተና 30 ከመቶ፣ በማዕከል የተዘጋጀው ፈተና 70 ከመቶ ተደምሮ በድምሩ 50 ከመቶና ከዚያ በላይ ያስመዘገቡ ይሆናሉ።

ለመጀመሪያ ጊዜ ለመንግስት እና ለግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተመራቂ ተማሪዎች የሚሰጠው የመውጫ ፈተና ፦

- መውጫ ፈተና ከሐምሌ 3 እስከ ሐምሌ 8 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ ይሰጣል። ውጤት ሐምሌ 10 ይገለፃል። (የጤና ተማሪዎች መውጫ ፈተና ዛሬ ተካሂዷል)

- በዘንድሮው ዓመት 169 ሺህ በላይ ተማሪዎች የከፍተኛ ትምህርት መውጫ ፈተና ይወስዳሉ።

- ለ208 የመመረቂያ ፕሮግራሞች የሚውሉ የፈተና ዓይነቶች ተዘጋጅቷል።

- ሃምሳ (50) በመቶና በላይ ያመጡ ተማሪዎች ያልፋሉ።

- ፈተናውን ያላለፉ ተማሪዎች መልሰው መላልሰው የሚወስዱበት ዕድል አለ። የመጀመሪያው ዙር ፈተና መንግሥት በራሱ መንገድ የሚያስኬደው ሲሆን ከዛ በኃላ ግን ልክ የ12ኛ ክፍል ፈተናን በግል እንደሚፈተኑት መውጫ ፈተና ላይም ተፈታኞች ዝግጁ ነን በሚሉ ሰዓት / በተዘጋጁ እና ይሄን ፈተና አልፋለሁ ብለው እራሳቸውን አብቅተው በሚመጡበት ሰዓት መፈተን ይችላሉ። ተፈትነው ሲያልፉ #ዲግሪያቸውን የሚወስዱበት አሰራር አለ።

- የመውጫ ፈተና ሙሉ በሙሉ #በኦንላይን ይሰጣል።

- የተፈታኝ ተመራቂ የተማሪዎች ስም ዝርዝር ተልኮ ወደ ዳታ ማዕከል ገብቷል።

- ለተማሪዎች ለፈተና የሚሆን ልዩ የመታወቂያ ቁጥር ይሰጣቸዋል ፤ በተሰጣቸው ቁጥር መሠረት በኦንላይን መፈተን እንዲችሉ የሚረዳ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራ ተከናውኖ ፤ የሞዴል ፈተና እየወሰዱ ነው።

ለ2ኛ ጊዜ በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ የሚሰጠው የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ፦

- ብሔራዊ ፈተናው ከሐምሌ 19 እስከ 30 ቀን 2015 ዓ/ም ድረሰ በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ይሰጣል።

- ለብሔራዊ ፈተናው የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች ከሐምሌ 16 ቀን ጀምሮ ለዚሁ ሥራ ብቻ ዝግጁ ይሆናሉ።

- የ2015 ዓ.ም ብሔራዊ የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ ፈተና ለመውሰድ ከ869 ሺህ በላይ ተፈታኞች በኦንላይን መመዝገባቸውን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል፡፡

- ፈተናው ለመውሰድ 869 ሺህ 765 ተፈታኞች በኦንላይን ተመዝግበዋል።

- ለፈተናው የተመዘገቡት 503,812 የሶሻል ሳይንስ እንዲሁም 365,954 የተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኞች ናቸው።

- የፈተና አስፈጻሚዎች፣ ሱፐርቫይዘሮች እና የፈተና ጣቢያ ኃላፊዎች ምልመላ ቅድመ ዝግጅት ሥራዎች ተከናውኗል።
Share share🙏🙏
@Temihert
@Temihert
የስራ እድል ለምትፈልጉ ብቻ

በየትኛውም የትምህርት ደረጃ ላይ ያላችሁ

በየትኛውም አከባቢ የምትኖሩ

ሌላ ስራ እየሰራችሁ ተጨማሪ ስራ ለምትፈልጉ

ከትምህርታችሁ ጋር ማስኬድ የምትችሉትን ስራ ለምትፈልጉ

ስልጠና ወስዳችሁ እራሳችሁንም ሌሎችንም እያሳደጋችሁ የተሻለ ቦታ መድረስ ለምትፈልጉ

ደግነት ለራስ ነው ስለዘህ ለወዳጅዎ ያካፍሉ
በ ትንሹ ለ 10 ሰው ያካፍልሁ
ስላካፈልሁ አምሰግናልሁ

ፍላጎት ያላችሁ ጥቂት ሰዎች ብቻ 👉

ቀድሞ የመጣ ቀድሞ ይስተናገዳል
👇👇👇👇👇
https://t.me/Amnole12
#MoE

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ደርሶት የተመለከተውና ለሁሉም የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የተላከ አንድ ደብዳቤ የሬሜዲያል ውጤት አያያዝን በተመለከተ አቅጣጫ አስቀምጧል።

ይህ ደብዳቤ በሐምሌ 11 /2015 ዓ/ም በትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ ተፈርሞ ለሁሉም የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የተላከ ነው።

በዚህም ደብዳቤ ፤ ዩኒቨርሲቲዎች የሬሚዲያል ኘሮግራም ማጠቃለያ ላይ በተከታታይ ምዘና በየተቋማቸው የተደረገው ምዘና 30% ፤ ከማዕከል የተዘጋቸው የማጠቃለያ ፈተና ከ70% እንዲያዝ ከዚህ በፊት የተላከው ሴርኩላር እንደተጠበቀ ሆኖ እንደሚቀጥል ይገልጻል።

ከዚህ ባለፈ የታሪክና የፊዚክስ ኮርሶች ሳይካተቱ ከአጠቃላይ 50 እና ከዚያ በላይ ያስመዘገቡ በየተቋሙ (ዩኒቨርሲቲዎቹ) የ2016 ፍሬሽማን ተማሪዎች እንደሚሆኑ ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።

በዚሁ መሠረት 150 ከ 300 እና 200 ከ 400 እና ከዚያ በላይ ያስመዘገቡ ተማሪዎች ዝርዝር ለትምህርትና ሥልጠና ባለሥልጣን እንደዚሁም ለትምህርት ሚኒስቴር አካዳሚክ ጉዳዮች መሪ ሥራ አስፈጻሚ እንዲላክ ማሳሰቢያ ተላልፏል።



https://t.me/Temihert
በ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎች ምዝገባ እየተካሔደ ነው።


ተፈታኝ ተማሪዎችን የመመዝገብ ሥራ ከየካቲት 3/2016 ዓ.ም ጀምሮ እስከ የካቲት 30/2016 ዓ.ም እንደሚከናወን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ገልጿል።

ምዝገባ የጀመሩ አካባቢዎች መኖራቸውን የጠቆሙት ኃላፊው፤ ምዝገባ ያልተጀመረባቸው አካባቢዎች በቀጣይ ምዝገባውን እንደሚያካሒዱ የአገልግሎቱ ም/ዋ/ዳይሬክተር ተፈራ ፈይሳ ገልጸዋል።

በመደበኛ እና በማታ መርሐግብር የመልቀቂያ ፈተናውን የሚወስዱ ተማሪዎች ምዝገባ በትምህርት ቤቶች ይከናወናል የተባለ ሲሆን በግል፣ በርቀት እና በበይነ መረብ ተምረው የሚፈተኑ ተማሪዎች ምዝገባ በክ/ከተማ፣ በልዩ ወረዳ እና በወረዳ የትምህርት ጽ/ቤቶች እንደሚካሔድ ም/ዋ/ዳይሬክተሩ ተናግረዋል።

በ2016 ዓ.ም የሚሰጠውን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ መልቀቂያ ፈተና ከ870 ሺህ በላይ ተማሪዎች እንደሚፈተኑ ይጠበቃል።
@Temihert