TechIn2
1.22K subscribers
1.47K photos
1 video
120 files
500 links
Technology & Innovation Institute (TechIn2), Ethiopia

የቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኢኒስቲትዩት

ጠቃሚና ወቅታዊ የሆኑ የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ፈጠራ፣ ጤና እና ሰብአዊ-ኣቅም ግንባታ(Human Development)መረጃዎችንና ምክሮችን በየእለቱ እናደርሶታለን።
Download Telegram
የሃር ምርት በኢትዮጵያና ፤ ፈተናዎቹ
==================
በኢትዮጵያ ለሺህ አመታት የተለያዩ ባህላዊና ሀይማኖታዊ ክዋዜዎች ውስጥ የራሱን ድርሻ ይይዛል፡፡ በኢትዮጵያ ሃርን ማምረት ከተጀመረም ሁለት አስርት ዓመታትን አስቆጥሯል፡፡ ምንም እንኳን በነዚህ ጊዜያት ውስጥ ዓመታዊ ምርቱ ከጊዜ ወደ ጊዜ በፍጥነት በማሻቀብ ላይ ቢሆንም ኢትዮጵያ ለሃር እርሻ ምቹ ከሚያደርጓት የአየር ንብረትም ሆነ ሌሎች ገፀ-በረከቶቿ አንፃር ግን የሚመረተው የሃር መጠን አነስተኛ እንደሆነ የመረጃዎች ጥቆማ ነው፡፡ በጥሬ እቃነትም ሆነ ያለቀለት የሃር ምርትን ወደ ባህር ማዶ ልኮ ይህ ነው የሚባል ገቢ ለሐገራችን ማስገባት አልተቻለም፡፡ የተለያዩ መረጃዎችን ያየን እንደሆነ በምርትም ሆነ ለምርት በሚያስፈልጉ ግብዓቶች ላይ ያሉ ድክመቶችን መገንዘብ ይቻላል፡፡ ለምሳሌ ለኤሪ የሃር ትሎች ምግብነት የሚውለው የጉሎ ቅጠል (castor) ምርት በሐገራችን 1,300 ኪ.ግ በሄክታር ሲሆን ይህን ህንድ ውስጥ በሄክታር 2,500 ሆኖ እናገኘዋለን፡፡ ለኤሪ ብቻ ሳይሆን ለመልበሪ ሃር ምግብ በሚሆኑ ዕፅዋትም ተመሳሳይ የልዩነት ደረጃ ይስተዋላል፡፡ በሃር ቅርፊቶቹ ረገድም በኢትዮጵያ ያሉት የሃር ትሎች ከተቀረው ዓለም ያነሰ ነው፡፡
ለዚህ ዘርፍ ጠንክሮ አለመውጣት የተለያዩ ምክንያቶች ይሰነዘራሉ፡፡ ከነዚህ ውስጥ ቀዳሚው ኢትዮጵያ ያለው በዘርፉ የሰለጠነ የሰው ኃይል እጥረት ነው፡፡ የሃር ግብርና ለሀገራችን አዲስ ከመሆኑ አንፃር በተለይ የሃር ትሎቹን ከማራባት አንስቶ ሃሩን ነጥሎ እስከማውጣት ያሉት የምርት ሂደቶች ለኛ እንግዳ የሆኑ ስልተ-ምርቶችን ይይዛሉ፡፡ ይህ የዕውቀት ክፍተት በትምህርትና ስልጠና መሟላት እስካልቻለ ድረስ በዘርፉ አጥጋቢ የሆነ ፍሬ ማግኘት አዳጋች ነው፡፡
ሁለተኛው የሃር ትሎቹ ከሚመገቧቸው እዕዋት ጋር የተገናኘ ነው፡፡ ውጤታማ የሃር ግብርናን ለማከናወን ትሎቹ የሚመገቧቸው እፅዋት ከፍተኛ የቅጠል ምርት የሚሰጡ፣ ተባይን የሚቋቋሙና የላቀ የመላመድ ብቃት ያላቸው መሆን ይገባቸዋል፡፡ በተጨማሪም በተለይ የሃር ምርት እንቅስቃሴው ባለበት ስፍራ ዕፅዋቶቹም የሚተከሉበት ስፍራ በስፋት እንዲኖር ያስፈልጋል፡፡ ሆኖም ይህ የመሬት አቅርቦት እጥረት እንዳለበት ለመረዳት ይቻላል፡፡ በተክሎቹ ዙሪያ የሚታዩት ሌሎቹ ክፍተቶች ዕፅዋቱን በተገቢው መልኩ ከማልማናት እና የዕፅዋት ዝርያዎቹን በተገቢው መልኩ አባዝቶ በቀላሉ ከምርት ስፍራው አቅራቢያ ከማድረስ አኳያ ነው፡፡
ሌላው ተጠቃሽ ክፍተት ከሃር ትሎቹ ጋር በተያያዘ ያለው ነው፡፡ ቀዳሚው የተሸሻሉ የሃር ትል ዝርያዎችን እና እንቁላሎቻቸውን በዓይነት በአይነት አባዝቶ ከምርት ስፍራዎቹ በአግባቡ ማቅረብ እንዲሁም በሃር ትሎቹ ላይ በመከሰት ጉዳት እያደረሱ ላሉት በሽታዎች መፍትሄ ማበጀት አለመቻሉ ነው፡፡ ይህን ያደርጉ ዘንድ ቅድሚያውን መውሰድ የነበረባቸው የትምህርት፣ ምርምር እና ስልጠና ተቋማትን ጨምሮ ሌሎችም አካላት ሚናቸውን በአግባቡ መወጣት አለመቻላቸው አንደኛው የክፍተቱ መንስኤ ነው፡፡
በጠቅላላው ለዘርፉ ተብሎ የተዘጋጀ ግልፅ ስትራቴጂ አለመኖር እንደ ዋና ችግር መቀመጥ ይገባዋል፡፡ ከዓመታት በፊት ኢትዮጵያን ጨምሮ በምስራቅ አፍሪካ ሀገራት የሃር ምርት ላይ ትኩረቱን አድርጎ የተሰራ አንድ ጥናት እንዳመላከተው የሃር ምርትን ተንተርሶ የውጪ ምንዛሬን ለማግኘት ከመጎምዠት ያለፈ በቂ የፖሊሲ አቅጣጫና ተግባራዊ ስራ አልተሰራም፡፡ ከነዚህ መሰራት የነበረባቸው ወሳኝ ተግባራት ውስጥ ሚዲያና ሌሎች መንገዶችን ተጠቅሞ ዘርፉን በህብረተሰቡ ውስጥ ከማስረፅ አንስቶ በቂ የምርምር እና ስርፀት፣ የሀገር ውስጥ ገበያ ትስስርን የማጎልበት፣ የሃር ትሎቹን ከማራባት ጀምሮ የሃር ምርቱን ለገበያ እስከሚደርስ ድረስ ባሉት ምዕራፎች ዘርፉ የሚጠይቃቸውን ቴክኖሎጂዎች የማሰራጨት እንዲሁም አስፈላጊ ስልጠናና የዕውቀት ክፍተትን የሚደፍኑ እንቅስቃዎች ላይ የተሰሩት ስራዎች አነስተኛነትን በግንባር ቀደምነት መጥቀስ ተገቢ ነው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በመሰረተ ልማት በተለይም በውሃና የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት ረገድ እንዲሁም በዘርፉ ላይ በስፋት ከተሰማሩት ሀገራት ጋር የሚደረገው የልምድ ልውውጥ አናሳነት ላለው የምርት ውስንነት ተጠቃሽ መንስኤዎች ናቸው፡፡
ምንጭ፡ ቴክ ሳይንስ ቅፅ ፲፮ (ሙሉ መፅሐፉን ከዲጂታል ቤተ መፅሐፍታችን/ library.techin.gov.et ማግኘት ይችላሉ)
የሁለት ሜትር ርቀር ኮሮናን ለመከላከል ላይበቃ ይችላል
===================
ሰሞኑን ከጤና ባለሙያዎች ሲነገር እንደሰማነው የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል 2 ሜትር/ ሁለት የአዋቂ እርምጃ ርቀትን መጠበቅ አስፈላጊ ነው፡፡ የዓለም ጤና ድርጅትን ጨምሮ የተለያዩ የጤና ተቋማትና ባለሙያዎች እንደሚገልፁት ዋነኛው የቫይረሱ መተላለፊያ መንገድ ቫይረሱ ያለባቸው ሰዎች ሲያስነጥሱና ሲያስሉ ከአፋቸው በሚወጣው ነጠብጣብ አማካኝነት ነው፡፡ በዚህ መሰረት ከሄድን የሁለት ሜትር ርቀትን መጠበቅ እጅን በተደጋጋሚ በደንብ መታጠብ ጋራ ተዳምሮ የበሽታውን ስርጭት ለመግታት ወይም ለመቀነስ በቂ ነው፡፡ ሆኖም አዲስ የወጣ ጥናት የሁለት ሜትር ርቀት በቂ ላይሆን እንደሚችል ጠቁሟል፡፡
ቫይረሱ በአየር ላይ የመንሳፈፍ ብቃቱ የጨመረ (airborne) ከሆነ ሰዎች በሚተነፍሱበትና በሚያወሩበት ወቅት በሚሰራጩ እጅግ አነስተኛ ነጠብጣቦች አማካኝነት ሊተላለፍ ይችላል፡፡ ሆኖም የተለያዩ ሁነቶች ሊወስኑት ይችላል፡፡ ለምሳሌ በቤት ውስጥ መሆንና አለመሆን፣ ጮክ ብሎ ማውራት፣ ጭንብል ማድረግ አለማድረግ፣ አየር በደንብ በሚዘዋወርበት ክፍል ውስጥ መሆን አለመሆን እና የቫይረሱ የመንሳፈፍ ብቃት፡፡
ሰዎች በሚተነፍሱበት፣ በሚያወሩበት፣ በሚዘፍኑበት፣ በሚያስሉበትና በሚያስነጥሱበት ወቅት በመጠናቸው የተለያዩ ጠብታዎች ከአፋቸው ይወጣል፡፡ እነዚህ ጠብታዎች በመጠናቸው አነስተኛና ከፍ ያሉ ተብለው ይመደባሉ፡፡ ታድያ ባለሙያዎችን ስጋት ውስጥ የከተተው ከ5 እስከ 10 ማይክሮ ሜትር ገደማ ዲያሜትር ያላቸው አነስተኞቹ ጠብታዎች ናቸው፡፡ ተለቅ ያሉት ጠብታዎች ብዙ ቫይረስና መሰል ቅንጣቶችን መሸከም ስለሚችሉ ከሰዎች ጋራ ሲገናኙ የማስያዝ እድላቸው ከፍ ያለ ነው፡፡ ሆኖም በዚህ መጠን ያሉ ጠብታዎች ክብደታቸው ስለሚጨምር ከአንድና ሁለት ሜትር በላይ ወደፊት ሳይጓዙ ከመሬት እንደሚወድቁ ይታመናል፡፡ እነዚህ ጠብታዎች ሰዎች በሚያስሉና በሚያስነጥሱበት ወቅት ከአፍ በመውጣት በቅርብ ያለ ሰውን ይበክላሉ፡፡ በተጨማሪም ሰዎች በሚያስሉበት ሰዓት አፋቸውን በሸፈኑበት መዳፋቸው ሌሎችን ሲጨብጡ፤ ወይም እቃ ሲነኩና ሌሎች ሰዎች እቃውን ነክተው ምግብ ሲበሉ፣ አይናቸው ሲያሻሹ፣ ወዘተ በበሽታው እንደሚጠቁ ይታመናል፡፡
ሰዎች ሲያወሩ ወይም ሲተነፍሱ የሚለቀቁ በ
መጠናቸው እጅግ አነስተኛ በሆኑ ጠብታዎችም ግን ሰዎችን የመበከለ፤ አቅም አላቸው፡፡ እነዚህ ጥቃቅን ጠብታዎች ግን ከአየር የሚመጣባቸውን ግፊት መቋቋም ስለማይችሉ ብዙውን ጊዜ ወደሰዎች ከአንድ ሜትር በላይ መቅረብ ሳይችሉ በዙርያቸው እንዲንዲዘዋወሩ ይገደዳሉ፡፡ ሆኖም ከአፍ የሚወጡት በአይን ከሚታይ እጅግ ጥቃቅን መጠን እስካላቸው ጠብታዎች ሁሉ ልክ ባልተረጋጋ አየር ምክንያት እንደሚፈጠሩ ደመናዎች በአየር ላይ ሊሰባሰቡ ይችላሉ፡፡ እነዚህ የጠብታዎች ስብስብ የሆኑ ያልተረጋጉ ደመናዎች ታድያ በውስጣቸው ያለው ሙቀት፣ እርጥበት እና አለመረጋጋት በአየር ላይ ለመጓዝ የሚበቃ ግፊትን ከሳል፣ ትንፋሽ፣ ማስነጠስ ወዘተ..ያገኛሉ፡፡ በዚህም መሰረት ነጠብጣቦቹ እስከ ስምንት ሜትር በአየር ላይ መጓዝ እንደሚችሉ በጆርናል ኦፍ አሜሪካን ሜዲካል አሶሴሽን የወጣው ጥናት ያሳያል፡፡ ታድያ ጠብታዎች ያን ያህል መጓዝ ከቻሉ ቫይረሶችም በእነርሱ ላይ ተሳፍረው ሊጓዙ ይችላሉ፡፡
በኒው ኢንግላንድ የህክምና ጆርናለ ላይ የወጣ ሌላ ጥናት በበኩሉ እጅግ ጥቃቅን ጠብታዎች የኮሮና ቫይረስን ተሸክመው ለሰዓታት በአየር ላይ ሊቆዩ እንደሚችሉ አውቋል፡፡ ይህ ግን በጥንቃቄ በተቀመረ ቤተ ሙከራ ውስጥ ነጠብጣቦቹን ከሰው ልጆች አተነፋፈስ በተለየ መልኩ በሚለቁ ማሽኖች የተሰራ በመሆኑ ጥችትን አስተናግዷል፡፡ ሆኖም መሰል ጥቃቅን ነጠብጣቦች ሁሌም በዙርያችን ያጋጥሙናል፤ ቫይረሱም በነዚህ ነጠብጣቦች ላይ የመቆየት እድል ሊኖረው ይችላል፡፡
መዝፈንም በተመሳሳይ ቫይረሱን የማሰራጨት ዕድል አለው፡፡ በአሜሪካኗ የዋሽንግተን ግዛት ውስጥ በአንድ ቦታ ተሰባስበው የነበሩ ድምፃዊያን ለዚህ አንድ ምሳሌ ናቸው፡፡ ድምፃዊያኑ ሲሰባሰቡ በመሀላቸው የ2 ሜትር ርቀትን ጠብቀው ነበር፡፡ ሆኖም ሲያቀነቅኑ እንደሆነ በሚታመን መልኩ 45 የቡድኑ አባላት በኮሮና ሲያዙ 2ቱ ሞተዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ሰዎች ከ2 ሜትር በላይ ተራርቀው ሲያወሩ ድምፃቸውን ከፍ ሊያደርጉ ይችላሉ፡፡ ይህ ደግሞ ከአፍ የሚወጡ ጠብታዎችን ስለሚያበዛ ስጋቱን ከፍ ያደርገዋል፡፡
ምንጭ፡ Science News
ቴክ-ሳይንስ የቴሌቪዥን ፕሮግራም
========================
በነገው ፕሮግራማችንም ለእርሰዎ እና ልጆችዎ ትምህርት የሚሰጡትን
• የአዕምሮ ህመም፤ ክፍል አንድ
• ስለ ስማርት ከተማ (ስማርት ሲቲ)
• በተመራማሪ ታሪክ ዶ/ር ሄዋን ደምሴን (ክፍል ሁለት)
• እንዲሁም ብላቴናት ዝግጅቶቻችን ነገ ቅዳሜ በ10 ሰዓት በ MOE TV ከእርሰዎ ዘንድ ይደርሳሉ (Nilesat/12520/
V/27500)፡፡
ሲጠበቅ የነበረው የኮቪድ-19 መድሃኒት ውጤት ሳያሳይ ቀረ
==========================
በጥቂት ወራት ዕድሜው መላውን ዓለም ያዳረሰውንና እስካሁኑ ሰዓትም ከ2.7 ሚሊዮን ሰዎችን አጥቅቶ ከ191 ሺህ በላይ የሚሆኑትን ህይወት ለወሰደው ኮቪድ-19 ኢትዮጵያን ጨምሮ የተለያዩ ሀገራት እና ተቋማቶቻቸው መድሀኒትና ክትባት የማግኘት ሩጫ ላይ ናቸው፡፡ ታድያ ለኮሮና ቫይረስ ተብለው ሲዘጋጁ ከነበሩት መድሃኒቶች መካከል በቀዳሚነት የሚቀመጠው ሬምዲሲቪየር የተባለው መድሃኒት በመጀመሪያ ሙሉ ሙከራው ውጤት ሳያሳይ ቀርቷል፡፡ ሬምዲሲቪየርን የወሰዱና ያልወሰዱ 237 ታማሚዎችን ያሳተፈው የመድሀኒቱ ሙከራ ሳይሳካ ሲቀር ሙከራውም በሚያስከትላቸው የጎንዮሽ ጉዳቶች ምክንያት እንዲቋረጥ ተደርጓል፡፡
የመድሀኒቱ ያለመሳካት ዜና በዓለም የጤና ድርጅት የክሊኒካል ሙከራዎች የመረጃ ቋት (ዳታቤዝ) ላይ ተለጥፎ የነበረ ቢሆንም በኋላ እንዲነሳ ተደርጓል፡፡ የድርጅቱ ቃል አቀባይ ታሪክ ጃስሬቪች ሪፖርቱ በስህተት ያለጊዜው መጫኑን ተናግረዋል፡፡ “ለዓለም የጤና ድርጅት በበሚፅፉ ሰዎች የተዘጋጀው ሰነድ በስህተት በድርጅቱ ድረ-ገፁ ላይ የተጫነ ሲሆን ስህተቱ እንደታወቀ እንዲወርድ ተደርጓል” ብለዋለ ቃል አቀባዩ፡፡ አክለውም ፅሁፉ ግምገማ እየተደረገበት መሆኑንና የዓለም የጤና ድርጅትም አስተያየት ከመስጠቱ በፊት ውጤቱን እየተጠባበቀ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
ጊላድ ሳይንስ በተባለው የአሜሪካን ኩባንያ የተዘጋጀው ይህ መድሃኒት ከዚህ ቀደምም በኢቦላ ላይ የተሞከረ ፀረ ቫይረስ መድሀኒት ነው፡፡ በዚያ ወቅትም በተመሳሳይ ውጤት ሳያሳይ ቀርቶ ነበር፡፡ በኮቪድ-19 ላይ የሚሰራ መድሃኒትን ለማግኘት በሚደረገው ሩጫ ብዙ ሀኪሞች የሙከራው ውጤትን ሳይጠብቁ ለታማሚዎች ሬምዲሲቪየርን ሲሰጡ ቆይተዋል፡፡ ለመድሀኒቱ በነበረው ከፍተኛ ተስፋ የተነሳም መድሀኒቱ በዓለም ዙርያ እጥረት ሲከሰትበት ለከሮና መፍትሄ ሊሆኑ ይችላሉ የተባሉ መፍትሄዎች በመሞከር ቀዳሚ የሆነው የኦክስፎርድ ማዕከል ተመራማሪዎችም መድሀኒቱን ማግኘት ባለመቻላቸው ምክንያት ጥናት ሊያደርጉበት አልቻሉም ነበር፡፡ በቻይና ተደረገው ሙከራ ታድያ ችኮላዎችን ሊገታ ይችላል፡፡ ሆኖም አምራች ግን አሁንም ቢሆን መድሃኒቱ ውጤታማ ሊሆን እንደሚችል የሚያሳዩ ምልክቶች መኖራቸውንና በተለይም የከፋ ምልክት በማይታይባቸው የበሽታው ታማሚዎች ዘንድ ጥቅም ሊኖረው እንደሚችል ገልጿል፡፡
በሙከራው በዘፈቀደ የተመረጡ 158 ታማሚዎች መድሀኒቱን እንዲወስዱ ታጭተው የነበረ ሲሆን ሌሎች 79 ታማሚዎች ደግሞ ፍቱንነት የሌለው መድሀኒትን (Placebo) ተሰጥቷቸዋል፡፡ በውጤቱም በሁለቱም ቡድኖች መካከል የድህነት ውጤት ልዩነት ሳይታይ ቀርቷል፡፡ ሬምዲሲቪየርን ከወሰዱት መካከል 14 በመቶው ህይወታቸው ሲያልፍ በአንፃሩ ካልወሰዱት ውስጥ 13 በመቶው ሞተዋል፡፡ በጥናቱ በሆስፒታል ተኝተው ህክምና በሚከታተሉ ታማሚዎች ላይ መሞከሩንና መድሃኒቱም ምንም አይነት ከቫይረሱም ሆነ ህክምና ጋር የተያያዘ ውጤት አለማሳየቱ በዓለም የጤና ድርጅት ድረ-ገፅ ላይ የወጣው ፅሁፍ አሳይቷል፡፡ መድሀኒቱን እንዲወስዱ ከታጩት 158 ታማሚዎች መካከልም 18ቱ ብቻ እንዲወስዱት ከተደረገ በኋላ ባመጣው ጉዳት ምክንያት መሰጠቱ እንዲቆም ሆኗል፡፡ በአጭሩ በተፃፈው ሪፖርት ውስጥ በጎንዮሽ ጉዳቱ ላይ ዝርዝር መረጃ አልቀረበም፡፡
ከአንድ ሳምንት በፊት ራሱ ጊላድ በ125 ታማሚዎች ላይ ባደረገው የሬምዲሲቪየር ሙከራ በቺካጎ የሚገኙ ሀኪሞችን ቀልብ ስቦ ነበር፡፡ የሙከራው አካል የነበሩት ሁሉም ታማሚዎች በአንድ ሳምንት ውስጥ ከሆስፒታል ድነው ወጥተዋል፡፡ ሆኖም በቻይናው ሙከራ እንደተደረገው ፍቱንነት የሌላቸው መድሃኒቶች ስላልቀረቡ ታማሚዎቹ ድነው የወጡት በሬምዲሲቪየር ምክንያት መሆን አለመሆኑን ተመራማሪዎች ሊያረጋግጡ አልቻሉም ነበር፡፡
ሬምዲሲቪየር እጅጉን ተስፋ ተጥሎበት የነበረና ከዶክተር እስከ ፖለቲከኛው ለኮሮና ለታማሚዎች እንዲሰጥ በስፋት ሲገፋ ቆይቷል፡፡ በተመሳሳይ ፀረ-ወባ የሆነው የክሎሮኩዊን መድሀኒት መራዛማነቱ ያነሰ አምሳያ የሆነው ሀይድሮክሲክሎሮኩዊን ለኮሮና ታማሚዎች ለመስጠች ችኮላ ነበረ፡፡ ይህም ያስከተለው የጤና ጉዳት እንዳለ ሆኖ፤ መድሀኒቱ ያስፈልጋቸው የነበሩ ሉፐስ የተባለ የሰውነት የበሽታ የመከላከል አቅምን የሚያጠቃ በሽታ ታማሚዎች እጥረት እንዲያጋጥማቸው አድርጓል፡፡ ታድያ በመድሃኒቶች ላይ ስርዓቱን የጠበቀ ሙከራ እንዲደረግ የሚሹ ተመራማሪዎች ይህ ካልተደረገ በስተቀር ከዚህ ቀደም የተሞከሩ መድሀኒቶችን እንኳን እንዲህ እንደኮሮና ገና በደንብ ላልታወቁ በሽታዎች የመጠቀምን ጉዳት ለማሳያነት እንደሚጠቀሙበት ይገመታል፡፡
ምንጭ፡ The Guardian
ውድ ተከታታዮቻችን መዘናጋት ዋጋ ያስከፍለናልና ዛሬም ከሰዎች ጋራ ያሎትን አካላዊ ርቀት ይጠብቁ፤ እጅዎንም በየጊዜው በደንብ ይታጠቡ፤ ሌሎችም በባለሙያ የተነገሩ የጥንቃቄ እርምጃዎችን ይውሰዱ፡፡
የኮሮናቫይረስን ለመዋጋት አፍሪካውያን የተገበሯቸው 5 አስገራሚ ፈጠራዎች
****************************************
በአለማችን የታሪክ ምዕራፍ እጅግ አስጨናቂ ሁኔታዎችና ከስተቶች ለፈጠራ በር መክፈታቸው አይቀሬ ጉዳይ ነው፡፡ ኮቪድ 19 በአለም ላይ በደቀነው ከፍተኛ አደጋ ምክንያት ከዚህም ከዚያም ሁኔታውን ቀላል ለማድርግ የሚያግዙ ፈጠራዎች በመሰራት ላይ ናቸው፡፡ በአህጉራችን አፍሪካም የአደጋውን መጠን ለመቀነስ እና የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት ልዩ ልዩ ፈጠራዎች በመተግበር ላይ ናቸው፡፡ ለምሳሌ ኮ ክሬሽን ሃብ እና ቬንቸርስ ፕላትፎርም ሃብ የተሰኙ የፈጠራ ሃሳብ አጋዦች ከኮቪድ 19 ጋር የተያያዙ የፈጠራ ሃሳብ ያላቸውን ሰዎች በገንዘብ እና በክህሎት በመደገፍ ላይ ይገኛሉ፡፡ ሌሎች በየሃገሩ የሚገኙ መንግስታዊ እና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማትም ለዚሁ አለማ እየተጉ የሚገኙ ናቸው፡፡ ታዲያ በዚህ ሁኔታ በተለያዩ የአፍሪካ ምድሮች ተሰርተው በመተግበር ላይ ያሉ እና ሁላችንም ልናውቃቸው የሚገቡ ፈጠራዎች ይገኛሉ፡፡
1.ቻትቦትስ (Chatbots) እና ስለራስ ማወቂያ ፈጠራዎች
እንዲህ ያሉት ፈጠራዎች የብዙሃኑን ጤና ካለበት ለመጠበቅ እና የቫይረሱን ቀላል ምልከቶች ከቤት ሆኖ ለመለየት የሚያገለግል ሲሆን፤ የሰዎችን ጭንቀት ለመቀነስና በምርመራ ማዕከሎች የሚኖረውን አጥረት ለማገዝ በእጅጉ የሚረዳ ነው፡፡ ለምሳሌ በናይጄሪያ COVID-19 Triage Tool በሚል ሰዎች በኦንላይን ስለጤናቸው ሁኔታ እንዲረዱ እና በቫይረሱ ተይዘው ከሆነ በሚታይባቸው ምልክተቶች መሰረት ምን አይነት እርምጃ መውሰድ እንደሚገባቸው ልዩ ልዩ ጤና ምክሮች የሚያገኙበት ነው፡፡ ከዚህ መሳሪያ በተጓዳኝ COVID-19 tracker የተሰኘው መገልገያም ተጠቃሚዎች የኮቪድ 19 ምልክቶች ሲታዩባቸው በሚቀርቡላቸው ጥያቄዎች መሰረት ወደ ለይቶ ማቆያ እና የምርመራ ማዕከል እንዲያቀኑ የሚያግዝ ፈጠራ ነው፡፡ ይህ አሰራር በደቡብ አፍሪካም በዋትአፕ Chatbots አማካኝነት የሚከናወን ሲሆን፤ ተጠቃሚዎች በቫይረሱ ዙሪያ የሚያዩትን ምልክቶች በመናገር መውሰድ የሚገባቸውን ቀላል ህክምናዎች እና ሌሎች ምክሮችን የሚያገኙበት ነው፡፡ ፈጠራው ከሚሰጠው ጥቅም አንፃር 3.5 ሚሊዮን ተጠቃሚዎች ጋር ሁለት ወር ባለሞላ ጊዜ ውስጥ ተደራሽ ሊሆን ችሏል፡፡
2.የህክመና መሳሪያዎችን በ 3D ማተሚያ መሽን መስራት
በዚህ የፈጠራ ዘርፍ ላይ ለአፍሪካ የጤና ባለሙያዎች በእጅጉ የሚያግዝ የሰውነት መሸፈኛ መሳሪያ እና የፊት መሸፈኛ ጭምብል በ3D ማተሚያ ቴክኖሎጂ አማካኝነት በአፍሪካውያን የተሰራ ሲሆን፤ እንደቬንትሌተር ያሉ ሌሎች የህክመና መሳሪያዎችም በተለያዩ የአህጉሪቱ ክፍሎች እየተሰሩ ይገኛል፡፡ ለአብነት በአፍሪካ የአርተፊሻል ኢንተለጀንስ ዘርፍ ቀዳሚ የሆነቸው የጅኋንስበርጓ ናትሊ ራፍል ወረርሽኙ ከተከሰተበት ጊዜ አንስቶ በ3D ማተሚያ አማካኘነት በየቀኑ መቶ የህክምና ባለሙያዎች ማስክ በማምረት ከሃገሯ አልፋ ለሌሎች የአፍሪካ ሃገራት ምርቶችን የምታቀርብ ናት፡፡
3.የኮቪድ 19 የቀጥታ (Real-time) መረጃ መከታተያ
የቫይረሱ ስርጭት ከፍተኛ እየሆነ ሲመጣ ዜጎች ትክከለኛ መረጃን በፍጥነት እንዲገኙ እና ራሳቸውን ከሁኔታዎች ጋር እንዲያናብቡ በአፍሪካ በብዙ ቦታዎች የተሰሩት መሰል ፈጠራዎች ትልቅ ግልጋሎት እንደነበራቸው የሚታወቅ ነው፡፡ ለምሳሌ በጋና comprehensive real-time tracker በሚል በተዘጋጀው አህጉርአቀፍ የኮቪድ 19 የቀጥታ መከታተያ አማካኘነት ዜጎች ስለቫይረሱ አጠቃላይ መረጃ እንዲኖራቸው ከማድረጉም ባለፈ ለፖሊሲ አውጪዎች እና የመንግስት አካላት ትክክለኛ ውሳኔ እንዲሰጡ እና ትንበያቸውን ምክንያታዊ ለማድረግ በእጅጉ አግዛል፡፡ ይህ ፈጠራ በሃገራቸን ኢትዮጵያም ከወራት በፊት መተገብር እንደጀመረ የሚታወቅ ነው፡፡
4.የሳንባ X-ray መመርመሪያዎች
ይህ የፈጠራ ሃሳብ የሳንባ X-ray ምርመራዎችን ከኦንላይን ሲስተሞች ጋር በማዛመድ የኮቪድ 19 ምርመራን ለማካሄድ የሚውል ሲሆን፤ መሰል ችግሮች የሚታዩባቸው ሰዎች የ X-ray ውጤታቸውን በምስል በመላክ በቫይረሱ መተቃት አለመጠቃታቸውን የሚያውቁበት ነው፡፡ በቱኒዚያ መሰል ስርዓቶችን በማበልፀግ ጥቂት ምልከቶችን የሚሳዩ ሰዎች በሳንባ X-ray ምስላቸው አማካኘነት ለቫይረሱ የመጋለጥ እድላቸውን በቤት ሆነው ለማወቅ ችለዋል፡፡ ይህ የፈጠራ ሃሳብ በኬንያም T-sense በተሰኘ ሲስተም አማካኘነት ሰዎች የልባቸውንና የሳንባቸውን ድምፅ ወደ መስል በመቀየር የመተንፈሻ አካል ችግር እንዳለባቸው እንደሌለባቸው ለመለየት የሚያስችል ግሩም ፈጠራ ሆኖ ቀርቧል፡፡
5.የኮቪድ 19 መመርመሪያ ኪቶች
የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በአፍሪካ ከተከሰተ ወዲህ በየሃገራቱ የሚደረጉ የኮቪድ 19 ምርመራዎች እጅግ አነስተኛ እንደሆኑ ይታወቃል፡፡ ለምሳሌ በናይጄሪያ 200 ሚሊዮን የሚጠጋ ህዝብ ባለበት ሁኔታ የቫይረሱ ምርመራ የተደረገለት ህዝብ ከ8ሺ አያልፍም፡፡ ታዲያ ይህ ሁኔታ ለሌሎች አማራጮችን ለመመልከት ግድ ብሏል፡፡ ይህ የፈጠራ ዘርፍ በናይጄሪያ ብዙ ሙከራዎች ሲደረጉበት የቆየ ግሩም ቴክኖሎጂ ሲሆን፤ ሞባይልን ብቻ መሰረት በማድረግ ከታከሉበት የሴንሰር መተግበሪያዎች ጋር በማጣመር የኮቪድ 19 ምርመራን ለማከናውን የሚረዳ ነው፡፡
ምንጭ፡ Techpoint.Africa
ኮቪድ 19 ለምን ከሴቶች ይልቅ ወንዶች ላይ በረታ
አዲሱ ጥናት የሚለው አለ
*******************************
ስለኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ብዙ ያልታወቁ ጉዳዮች ይገኛሉ፡፡ ከቫይረሱ መነሻ መላምቶች አንስቶ ስለመተላለፊያው መንገድ እና ሌሎቹም ተያያዥ ጉዳዮች ተጨማሪ ጥናቶችን የሚፈልጉ ናቸው፡፡ ታዲያ ከእነዚህ መልስ ያልተገኘላቸው ጥያቄዎች ውስጥ ቫይረሱ ከሴቶች ይልቅ በእጥፍ ወንዶች ላይ የሚበረታበት ምከንያት ምንድን ነው የሚለው ሌላኛው ያልተፈታ እንቆቅልሽ ነው፡፡
በዚህ ጉዳይ ላይ መረጃዎችን ሲያጠናቅር የነበረው የምርምር ቡድን ለአብነት ያስቀመጣቸው ማሳያዎች ቫይረሱ ከሴቶች ይልቅ ወንዶች ላይ እንደሚበረታ በግልፅ የሚያሳዩ ናቸው፡፡ ለምሳሌ በኮሮናቫረስ በእጅጉ በተመታችው በኒው ዮርክ ከተማ በቫይረሱ ከተያዙ 100,000 ወንዶች መካከል 146 የሚጠጉት ህይወታቸው ሲያልፍ፤ በአንጻሩ በቫይረሱ ከተያዙት 100,000 ሴቶች መካከል 84 የሚሆኑት ብቻ ህይወታቸውን አተዋል፡፡ ይህ የሞት ልዩነት ሲመዘገብ ከፍተኛ መጠን ያላቸው ወንዶች በሆስፐታል ህክምና ሲደረግላቸው የቆዩ መሆኑ ጉዳዩን ይበልጥ አስገራሚ ያደርገዋል፡፡ ይህ ጥንቅር በቫይረሱ በጽኑ ታመው የትንፋሽ ማገዣ የተደረገላቸው ሰዎች በአብዛኛው ወንዶች መሆናቸውን እንዲሁ የሚያሳይ ሲሆን፤ በሌሎች እንደ ቻይና፣ ጣልያን እና ደቡብ ኮሪያ ባሉ ሃገራትም ተመሳሳይ ስታቲክስ እንዳለው ለማውቅ ተችሏል፡፡ ታዲያ የምርምር ቡድኑ ይህ እንዴት ሊሆን ቻለ ለሚለው ጥያቄ ከተለያዩ ጎኖች በማየት ጉዳዪን ለማብራራት ይሞክራል፡፡
በዚህ አለምአቀፍ ጥናት የህንዱ ካስቱርባ ሆስፖታል፣ አልበርት አንስታይን የጤና ኮሌጅ እንዲሁም ሞንቴፊዮሪ የጤና ኢንስቲትዩት በዋናነት የተሳተፉ የምርምር ቡድኑ አባላት ሲሆኑ የምርምር ፅሁፉ አጠቃላይ ዝርዝር ደግሞ
Medrxiv.org በተባለው አለምአቀፍ ጆርናል ላይ ታትሟል፡፡ የጥናቱ ይዘት በሁለቱም ፆታዎች በኩል የሚኖረውን የኮቪድ 19 በሽታን ለይቶ የመከላከል አቀም (viral clearance) እና ቀደሞ ምላሽ የመስጠት ሁኔታን በማብራራት ሴቶች ከወንዶች ባነሰ ጊዜያት ውስጥ እንዴት ለቫይረሱ ፈጣን ምላሽ እንደሚሰጡ የሚያሳይ ነው፡፡ በጥናቱ 48 የሚሆኑ ፍቃደኛ ወንዶች እና 20 ሴቶች ሲሳተፉ አማካይ እደሜ ጣሪያቸው 37 ነበር፡፡ ተመራማሪዎች የሁለቱንም ፆታዎች የደም ናሙና ከመረመሩ በኋላ በቫይረሱ መያዛቸውን በማረጋገጥ እና የትኞቹ ተጠቂዎች በፍጥነት ለቫይረሱ ምላሽ በመስጠት ወደማገገም ይሄዳሉ የሚል ነበር፡፡
ታዲያ በውጤቱ መሰረት ሁሉም ሴቶች ከወንዶቹ በመቅደም ቫይረሱን ከሰውነታቸው ለመፅዳት አጭር ጊዜ እንዳስፈለጋቸው እና ቢያንስ አንኳን የሶስትና የአራት ቀን ልዩነት በመካከላቸው እንደነበረ በጥናታቸው አረጋግጠዋል፡፡ ይህ ውጤት የሁለቱንም ፆታዎች በሽታ የመከላከል ስርዓትና ፈጣን ምላሽ የመስጠት አቅም (immune system response) በስፋት እንዲጠና መንገድ የሚከፍት ቢሆንም በወንዶች በኩል ቫይረሱን ከሰውነት ለማስወገድ የሚታየው ችግር ከሌሎች ማህበራዊና አካባቢያዊ ችግሮች የሚቀዳ ሊሆን እንሚችል ጥናቱ የጠቆመው አብይ ጉዳይ ነው፡፡ ለምሳሌ በአብዛኛው የማህበረሰብ የአኗኗር ሂደት ውስጥ ከመተንፈሻ አካል ጋር የተያያዙ ችግሮችን የሚያስከትሉ አጉል ሱሶች እና የህይወት ልምምዶች በወንዶች እንደሚተገበሩ ይታወቀል፡፡ አንደማሳያ ብንወስድ እንኳን ሲጋራ ማጨስ፣ የአልኮል መጠጦች ማዘውተር እንዲሁም ሌሎች ተያያዥ ችግሮች ከሴቶች ይልቅ ወንዶች ላይ በስፋት መታየታቸው ውጤቱን ከባድ እንደሚያደርገው ይገመታል፡፡
ምንጭ፡ Bigthink እና Medrxiv.org
CDC በጤና መመሪያው ላይ ያካተታቸው የኮቪድ 19 ስድስት ምልክቶች ምንድን ናቸው?
=============================
የአሜሪካው የበሽታ መቆጣጠሪያ እና መከላከያ መዕከል (CDC) በይፋዊ ድረ-ገፁ በሚያወጣቸው የጤና መመሪዎች ወይም (Guidelines) አማካኝነት በኮቪድ 19 ዙሪያ ቀድመው ከሚታወቁት የትኩሳት፣ ደረቅ ሳል እና የትንፋሽ መቆራራጥ ምልክቶች በተጨማሪ ሌሎች ተያያዥ የበሽታው ምልከቶች ሊኖሩ እንደሚችሉ አስታውቋል፡፡ ተቋሙ በመመሪያው ይፋ ያደረጋቸው እነዚህ የኮቪድ 19 ተያያዥ ምልክቶች አንዳንዶቹ ቀድመው በተለያዩ የጤና ኤክስፐርቶች ሲጠቆሙ የነበሩ እና በቫይረሱ ከተያዙ ሰዎች ላይ ሲስተዋሉ የነበሩ ምልክቶች ናቸው፡፡
የአሜሪካ የበሽታ መቆጣጠሪያ እና መከላከያ መዕከል (CDC) ይፋ ካደረጋቸው የበሽታው ተያያዥ ምልክቶች ውስጥ ብርድ፣ የጡንቻ ህመም፣ ከቅዝቃዜ ጋር የተያያዘ ተደጋጋገሚ የሰውነት ማንቀጠቀጥ፣ ራስ ምታት እና የጉሮሮ ህመም ዋናዎቹ ሲሆኑ ከዚህ በተጨማሪም ሽታንና ጣዕም የመለየት ችግርም በመጀመሪያዎቹ ቀናት ላይ ሊታዩ የሚችሉ የበሽታው ቀላል ምልክቶች እንደሆኑ አስታውቋል፡፡ እነዚህ ምልክቶች በሁሉም ሰው ላይ የመታየት እድላቸው ሙሉ ለሙሉ የተረጋገጠ ባይሆንም ከበሽታው ቀላል ምልክቶች መካከል በዋናነነት የሚመደቡ በመሆናቸው እና በተለያየ መልኩ ሰዎች ላይ የመታየት እድል ስለሚኖራቸው በጥንቃቄ ማየቱ ጥቅም እንዳለው CDC አስታውቋል፡፡
የኮሮናቫይረስ አዲስ ወረርሽኝ ከመሆኑ እንፃር እና በበሽታው ላይ የሚደረጉ ተጨማሪ ጥናቶች ገና በሂደት ላይ በመሆናቸው እነዚህ የተጠቀሱት ተያያዥ ምልክቶች አካታች ወይም (inclusive) ናቸው ማለት ባይቻልም እንደሰዎቹ የእድሜ ሁኔታ እና ሌሎች መመዘኛዎች ተመስረቶ ቫይረሱ በያዘው ሰው ላይ ከ2 እስከ 14 ባሉት ቀናት የመታየት እድል አላቸው፡፡ ይህ ሁኔታ በተለይም ከወጣቶች እና ታደጊዎች ጋር በተያያዘ አብዛኞቹ በቫይረሱ የተጠቁ ሰዎች ቀድመው ሲጠቀሱ የነበሩ የህመም ስሜቶች ሳይሰማቸው እና ምልክቶች ሳይታይባቸው ቀናትን ሊያስቆጥሩ በመቻላቸው ሁኔታውን ከዚህ ጉዳዩ ጋር ይበልጥ ተያያዥ እንደሚያደርገው የጤና ባለሙያዎች እምነት ነው፡፡
ይሁንና አንደተቋሙ ማብራሪያ እነዚህ የተጠቀሱ የበሽታው ምልክቶች ቀላል ከሚባሉት መካከል የሚመደቡ በመሆናቸው በዙሪያችን ካሉ የጤና ባለሙያዎች ጋር በመመካከር መወሰድ የሚገቡ ጥንቃቄዎችን መወሰን እንደሚቻል እና አደጋውን ቀድሞ ለመከላከል እድል እንደሚሰጥ በመመሪያው ገልጿል፡፡ በበሽታው ዙሪያ ምናልባትም አስጊ ሁኔታ ሊባል የሚችለው እና በአፋጣኛ የሃኪም እገዛ የሚያስፈልገው አተነፋፋስ ላይ ችግር ካለ፣ በደረት አካባቢ ፅኑ የሚባል ህመምና ግፊት ካለ፣ በከንፈርና ፊት ላይ የቀለም ለውጥ ካስተዋልን እንዲሁም ከመኝታ ለመነሳት ስንቸግር ወይም ግራ የመጋባት ስሜት ሲኖረን አፋጣኝ እርምጃዎችን ማድረግ እንደሚገባ CDC በመመሪያው አሳስቧል፡፡
ለበለጠ https://www.cdc.
የልብ ችግር ለኮሮናቫይረስ መባባስ ዋና ምክንያት ሊሆን ይችላል
==============================
የኮቪድ 19 ወደከባድ የጤና ችግር እንዲያመራ እንደ ሳምባ ነቀርሳ፣ የደም ግፊት እና የልብ በሽታ ያሉ ተያያዥ የጤና እክሎች ትልቅ ሚና እንደሚኖራቸው በተደጋጋገሚ ሲነሳ ቆይቷል፡፡ በተለይም ደግሞ ከሳምባ ጋር ተያያዥነት ያላቸው አንደአስም እና ሌሎች የመተንፈሻ አካላት በሽታዎች ቫይረሱ ይበልጥ አቅም እንዲያገኝ በማድረግ የጤናችንን ሁኔታ አደጋ ውስጥ እንዲገባ ምከንያት ይሆናሉ፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ ከሰሞኑ የወጡ ዘገባዎች አንደሚያሳዩት የልብ ችግር ከሳምባ ጋር ተያያዥነት ካላቸው በሽታዎች ይልቅ ለኮሮናቫይረስ መባባስ ቁልፍ ሚና ሊኖራቸው እንደሚችል ያመላከተ ነው፡፡ በዚህ ሪፖርት እንደተጠቀሰው ከሳምባ ጋር ተያያዥነት ያላቸው በሽታዎች ለኮቪድ 19 መባባስ ስድስት በመቶ ብቻ አስተዋፅኦ ሲያደርጉ፤ የልብ በሽታ ግን 10 በመቶ ለሚሆኑት የኮሮናቫይረስ ከባድ ኬዞች ዋና ምክንያት እንደነበረ በሪፖርቱ ተገልጿል፡፡ እነዚህ የእስታቲክስ ውጤቶች በቻይና፣ በጣልያን፣ በእንግሊዝ እና በአሜሪካ ከተሰበሰቡ የታካሚዎች የጤና ማህደር የተገኘ ሲሆን በሌሎች አካባቢዎችም ተመሳሳይ አዝማሚያ ሊኖረው እንደሚችል ይገመታል፡፡
የኮቪድ 19 በልብ በሽታ ምክንያት ይበልጥ ከባድ ሊሆን እንደሚችለው ሁሉ ከዚህ በፊት የልብ ችግር የሌለባቸው ሰዎች በቫይረሱ የተነሳ ብቻ ለዚህ በሽታ ሊጋለጡ እንደሚችሉ ይህ ሪፖርት የሰበሰባቸው መረጃዎች ያሳያሉ፡፡ ይህ ደግሞ የሚሆነው በቫይረሱ ከባድ አደጋ የተነሳ በልብ ዙሪያ ማዮካርዲቲስ (myocarditis) የሚባል ከባድ የእብጠት ምላሽ (inflammatory response) ሊፈጠር በመቻሉ ነው፡፡ ይህም የልብን ኤሌክትሪካል ኮንዳክሽን በመሻሻል በሰውንት ውስጥ የሚረጨውን የደም ሁኔታ ጫና ውስጥ እንዲገባ ያደርጋል፡፡ ይህም በጠቅላለለው እንደሳምባ ያሉ የሰውነት አካላት የኦክስጂን እጥረት እንዲያጋጥማቸው በማድረግ የአተነፋፋፍ ስርዓቱን ከባድ ሊያደርገው ይችላል፡፡ ይህ የልብ ችግር በዚህ መልኩ የሚጎዳበት ምክንያት በትክክል ማወቅ ባይቻልም ተመራማሪዎች ግን በጉዳዩ ዙሪው ያሉትን ተያያዥ እውነታዎች ለመረዳት በጥረት ላይ መሆናቸውን ይናገራሉ፡፡
ከዚህ በፊት እንደሚታወቅው H1N1 በሚባላው የመተንፈሻ አካል በሽታ አብዛኞቹ ተጠቂዎች ከልብ ጋር የተያያዘ ችግር የታየባቸው ቢሆንም አሁን ባለው አጠቃላይ የኮሮናቫይረስ ምርመራ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ለልብ እና ለሌሎች የጤና ችግር የሚጋለጡ ባለመሆናቸው አደጋውን ዝቅተኛ እንደሚያደርገው የጤና ባለሙያዎች ያስረዳሉ፡፡
ምንጭ፡ The Conversation
ለብዙ ሚሊዮኖች በዓመቱ መጨረሻ ሊቀርብ ይችላል የተባለው ክትባት በክሊኒካል ሙከራ ላይ ይገኛል
================================
የጀርመን ኩባንያ ከአሜሪካው የመድሃኒት አምራች Pfizer ጋር በጋራ የሚሰሩት የኮቪድ 19 ክትባት በሰዎች ላይ የሚያደርገውን ሙከራ መጀመሩን ሲ ኤን ኤን ዘግቧል፡፡ በፈረንጆቹ የዓመቱ መጨረሻ ለሚሊዮኖች ሊደርስ ይችላል ተብሎ የሚጠበቅው እና ትልቅ ግምት ከተሰጣቸው የክትባት መድሃኒቶች መካካል አንዱ የሆነው ይህ ክታባት በጀርመን ማይንዝ ከሳምንት በፊት በፈቃደኛ ሰዎች ላይ ሙከራ ማድረግ የጀመረ ሲሆን፤ በአሜሪካም ከአንድ ሳምንት በኋላ ሙከራ እንደሚጀመር በዘገባው ተገልጿል፡፡
በጀርመን ማይንዝ መቀመጫውን ያደረገው BioNTech የተባለው ይህ ኩባንያ በጠቅላለው እድሜያቸው ከ18 እስከ 55 የሚገመት 200 የሚጠጉ ፍቃደኛ ሰዎችን በክልኒካል ሙከራው ላይ ያሳተፈ ሲሆን፤ እስካሁን 12 የሚሆኑ ፍቃደኛ ሰዎች BNT162 የተሰኘውን ክትባት በተለያየ ዶዝ ማግኘታቸውን አስታውቋል፡፡ ይሁንና ለሁሉም የጥናቱ ተሳታፊዎች ሙከራው እስከሚደረግ እና የክትባቱ ደህንነት ከኢሚዩኖጄኔሲቲ አቅሙ ጋር ተመርምሮ አስኪረጋገጥ ስለሙከራው አጠቃላይ ውጤት ምንም መረጃ ማቅረብ እንደማይቻል ኩባንያው ያስረዳል፡፡
የክትባት መድሃኒቶችን ፍቃድ የሚሰጠው የጀርመን ፌደራል ኢኒስቲትዩት ለመጀመሪያ ጊዜ በሰዎች ላይ የክሊኒካል ሙከራ እንዲያደረግ ፍቃድ የሰጠው ይህ ኩባንያ አብሮት ከሚሰራው የአሜሪካ መድሃኒት አምራች ድርጅት ጋር በጋራ በመሆን በፈረንጆቹ 2020 መጨረሻ ወር ላይ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ክትባቶችን ለማምረት በእቅድ ላይ ነው፡፡ የክትባት መድሃኒቱ በሂደት የማስፋፊያ ፕሮግራሙን በስኬት የሚያጠናቅቅ ከሆነ እና ከመንግስት አካላት የተሟላ ፍቃድ የሚያገኝ ከሆነ በ2021 በመቶ ሚሊዮን የሚቆጠሩ የክትባት ምድሃኒቶችን ወደ ምርት ለማስገባት ሰፊ እቅድ እንዳለው በዘገባው ተገልጿል፡፡
CNN
ኮቪድ 19ኝን በመከላከል ረገድ ከሩቅ ምስራቅ ሀገራት ስኬት የተገኙ ትምህርቶች
====================
በአሁኑ ሰዓት የኮቪድ-19 ስርጭትን ለመግታት መደረግ ያለባቸው የጥንቃቄ ስራዎች በግልፅ ቢቀመጡም በዓለም ላይ ያሉ ሀገራትና መንግስታት እነዚህን እርምጃዎች ተግብረው ህዝባቸውን ከቫይረሱ ለማስጣል ፈታኝ ሆኖባቸዋል፡፡ የቫይረሱን መነሳት ቻይና ለዓለም ጤና ድርጅት ያሳወቀችበት ዕለት (ታህሳስ 21) ሀገራት የጥንቃቄ እርምጃዎችን እንዲወስዱ የማንቂያውን ደውል ደውሏል፡፡ ታድያ በዚህ ጊዜ በቀደሙት ዓመታት ውስጥ ሳርስ እና መርስ በተባሉ የኮሮና ቫይረስ ቤተሰቦች ተጠቅተው የነበሩት ደቡብ ኮርያ፣ ታይዋን እና ሆንግ ኮንግ ፈጥነው ወደ እርምጃ ለመግባት የመጀመሪያዎቹ ነበሩ፡፡ ሌላው ዓለም ግን ቫይረሱ በፍጥነት መስፋፋት እስከሚጀምርበት ሰዓት ድረስ ተገቢውን እርምጃ ሳይወስድ ቀርቷል፡፡ የሩቅ ምስራቅ ሀገራቱ የቫረሱን ስርጭት ለመግታት ከተጓዙባቸው እርምጃዎች ተከታዮቹን አባይት ነጥቦች መረዳት ይገባል፡፡
• የመጀመሪያው ቫይረሱ የት የት እንደሚገኝ ማወቅና ስርጭቱን ባለበት መግታት ነው፡፡ ይህም የመመርመር፣ መከታተል እና መለየት ስራን፤ ማለትም ምርመራን በስፋት ማከናወን፣ በሳምንት ውስጥ ቫይረሱ ከተገኘባቸው ሰዎች ጋራ ግንኙነት የነበራቸውን ሰዎች መለየትና በለይቶ ማቆያዎች ውስጥ በግዴታ ማስገባትን ይጠይቃል፡፡ መንግስታቱ ለዚህ ተግባር ወታደሮችን በማሰልጠን አሰማርተዋል፡፡ ምንም እንኳን መመርመር በራሱ መፍትሄ ባይሆንም የቫይረሱን ሰርጭት መቆጣጠር ከማይቻልበት ደረጃ ከመድረሱ በፊት ለመግታትና በህክምና ተቋማት፤ ከፍ ሲልም በምጣኔ-ሐብቱ ላይ ቀውስ ሳይፈጠር ነገሮችን ለመቆጣጠር ትልቅ መሳርያ ነው፡፡
• ሁለተኛው እርምጃ ለቫይረሱ ከፍተኛ ተጋላጭነት ያላቸውን የጤና ባለሙያዎች ደህንነት መጠበቅ ነው፡፡ ይህ እርምጃ ባለሙያዎቹ የቫይረሱን ምርመራ ከማንም አስቀድሞ እንዲያገኙ በማድረግ ብቻ ሳይወሰን አስፈላጊው የመከላከያ መሳርያ ሁሉ በአስቸኳይ እንዲደርሳቸው ማድረግን ይጨምራል፡፡ በፍጥነት ማምረት እማይቻሉትን እንደ መተበንፈሻ ማሽን፣ አልጋ እና ኦክስጅን ያሉትን መሳርያዎች አቅርቦት በሽታውን ከፊት ሆነው እየተዋጉ ላሉት ለነዚህ የጤና ባለሙያዎች ማቅረብ ላይም ትኩረት መሰጠት ይኖርበታል፡፡
• ሶስተኛው የትኛው የሀገሪቱ ክፍል በበሽታው ስርጭት በስፋት እየተጠቃ መሆኑን ሰዎች ተጠጋግተው የሚኖሩባቸው ስፍራዎች ለቫይረሱ በከፋ ተጋላጭ መሆን አለመሆናቸውን የሚለይ ስርዓት መዘርጋት ነው፡፡
• የድንበር ቁጥጥር፤ በተወሰኑ ሀገራት ላይ የጉዞ እገዳን ማድረግ ቫይረሱን በመከላከል ረገድ ያለው ውጤታማነት አነስተኛ በመሆኑ ከየትኛውም ሀገራት የሚመጡ ተጓዦችን ወደ ለ14 ቀናት ወደ ለይቶ ማቆያዎች ማስገባት በቫይረሱ ተጠቂ የሆኑትን ለመለየት ሁነኛ መንገድ ተደርጎ ተወስዷል፡፡
• አምስተኛው ህዝቡ በመከላከል ፖሊሲዎቹ ላይ እምነቱን ያሳድር ዘንድ ግልፅነት እና እውነተኝነት ላይ የተመሰረተ የመረጃ ልውውጥን ማድረግ ነው፡፡ እነዚህ ወቅቶች በህዝቡ ዘንድ አለመረጋጋት ያለባቸው በመሆኑ መንግስታተት በመከላከያ ፖሊሲዎቹ ዙርያ ቀጥተኛና ዘላቂነት ያለው መረጃን ማድረስና በሚወስዷቸው እርምጃዎች ዙርያ ግልፀኝነትን ማስፈን ይኖርባቸዋል፡፡
• በስድስተኛነት የተቀመጠው የትኛውም እርምጃ ነገሮች በፍጥነት ቀድሞ ወደነበሩበት የማይመልሳቸው መሆኑን ማወቅ ነው፡፡ ይህ የህዝቡ ዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ በመከላከያ እርምጃዎች የታጀበ ማድረግን ያካትታል፡፡ በዋነኝነትም፤ አካላዊ ርቀትን በሚቻለው መጠን መተግበር፣ ወደማንኛውም የህዝብ መገልገያ ህንፃዎችና ቢሮዎች የሚገቡ ሰዎችን ሙቀት መለካትን እንዲሁም ሰው በሚሰበሰብባቸው ስፍራዎች ሁሉ የፊት ጭምብሎችን ማድረግ ይገኙበታል፡፡
• ሰዉ በቤት እንዲቆይ ማስገደድ ሌላኛው እርምጃ ነው፡፡ ሰውን በቤት እንዲቆይ ማስገደድን አስቀድሞ መተግበር የቫይረሱን ስርጭት ለመቀነስ ይረዳሉ፡፡ ሆኖም ይህ በራሱ ሁነኛ መፍትሄ አይሆንም፤ በምጣኔ ሐብቱ ላይ ከፍተኛ ጉዳት የሚያደርስ እርምጃ ስለሆነ ሁሌ መተግበርም የለበትም፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ ግን ለመንግስታት ጊዜን መስጠቱና የጤና መሰረተ-ልማታቸውን ለማጎልበት ዕድል እንደሚሰጣቸው እሙን ነው፡፡
• የመጨረሻው ከላይ የተጠቀሱት እርምጃዎች ሁሉ የአጭር ጊዜ ስትራቴጂ ከሞሆን ስለማያልፉ በየጊዜው በሚወጡ ሳይንሳዊ ግኝቶች ላይ የተመሰረቱ እርምጃዎችን ከመውሰድ ጎን ለጎን ሀገራት የራሳቸውን ሁነኛ መፍትሄ መመፈለግ ይኖርባቸዋል፡፡
ምንጭ፡ The Guardian