TechIn2
1.23K subscribers
1.47K photos
1 video
120 files
500 links
Technology & Innovation Institute (TechIn2), Ethiopia

የቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኢኒስቲትዩት

ጠቃሚና ወቅታዊ የሆኑ የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ፈጠራ፣ ጤና እና ሰብአዊ-ኣቅም ግንባታ(Human Development)መረጃዎችንና ምክሮችን በየእለቱ እናደርሶታለን።
Download Telegram
ረጋ ዘይት እስከሁን?

በሚረጋ ዘይት ውስጥ ያለው የተከማቸ ስብ አላስፈላጊ ለሆነ ክብደት መጨመር እና ለሌሎች ተያያዥ ጉዳቶች ከመዳረጉም በላይ ኒውክለስ አኩንቢን የተባለው የአዕምሯችን ክፍል ውስጥ ብግነት( inflammation) እንዲፈጠር ምክኒያት እንደሚሆን የሰሞኑ የ ሞንትሪያል ዩኒቨርሲቲ ጥናት አመለከተ፡፡

ኒውክለስ አኩንቢን በአዕምሯችን ውስጥ የሚገኝ ክፍል ሲሆን ተግባሩ ስሜታችን፣ እና ሁኔታችንን መቆጣጠር ነው፡፡ እናም የዚህ የአዕምሮ ክፍል መጎዳት አሊያም መቆጣት አዕምሯችን ስሜታችን ላይ ያለውን ቁጥጥር እንዲያጣ እና ግለሰቡ ለጭንቀት እና ለውጥረት እንዲዳረግ ከማረጉም በላይ የሰውነትን የኬሚካል ዑደት ይረብሸዋል፡፡

በሞንትሪያል ዩኒቨርስቲ ውስጥ በ አይጥ ላይ በተደረገው ጥናትም የረጋ ዘይት (palm oil ) ይህንን ቀውስ ሊያስከትከል እንደሚችል ተረጋግጧል፡፡ በተመሳሳይ እዛው አይጦቹ ላይ የተሞከረው ሌላኛው (monounsaturated fat)የተሰኘው የዘይት ዓይነት ማለትም ከ ኦሊቭ ፍሬ የምናገኘው ዘይት በ አይጦቹ ላይ ምንም ዓይነት ጉዳት ሲያደርስ አልታይም፡፡

አጥኚዎቹ እንደገለጡት ከሆነ ይህንን ዘይት ከተጠቀሙ በኋላ በሰውነት ላይ የታየው የኬሚካል ዑደት መረበሽ ልክ የስኳር በሽተኛ ሰውነት ውስጥ እንደሚከሰተው ዓይነት ነው፡፡ ማለትም የቅድመ ስኳር በሽታ ምልቶች ሁሉ ይታያሉ እንደማለት ነው፡፡

ብዙ ጥናቶች እንደዚህ ያለ ዘይት የማይመገቡ ህዝቦች የሚኖሩበት አከባቢ የ ድብርት እና ጭንቀት በሽታዎች ያን ያህል እንደማይታዩ ያሳዩ ሲሆን በዚህ ጥናት ደግሞ በውፍረት በሽታ(obesity) እና በ ዱባቴ (depression) መሀከል ያለው ትስስር ሊታወቅ ችሏል፡፡

በሰውነት ውስጥ የሚኖር የአላስገላጊ ስብ ክምችት እና የውፍረት መጨመር መንስዔ ከዚህ ከታጨቀ ዘይት አመጋገብ (saturated fat) ጋር የሚገናኝ በመሆኑ እና ይህ የዘይት ዓይነት ደግሞ በአዕምሮ ላይ የሚያደርሰው ጉዳት ለጭንቀት እና ለ ውጥረት እንዲሁም ለመደበት ስለሚዳግ በውፍረት እና በ መደበት መካከል ተያያዠ ችግር ሊፈጠር ችሏል፡፡

ጥናቱ ብዙ ብዙ ጠቃሚ የሆኑ መረጃዎችን የያዘ ቢሆንም ስቲክ ኢትዮጲያ ግን ለዛሬ ብታውቁት እና ብታሰምሩበት ያለውን የረጋ ዘይት ጉዳት እንካችሁ ብሏል፡፡
በስተመጨረሻም የሰው ልጅ የሚበላውን ነውና ወደ ሰውነታችን ስለሚገቡ ነገሮች ሁሉ ጠንቃቃ እይታ ይኑረን እያለ መልም ቀን ይመኝላችኋል፡፡
ምንጭ፡- sciencedaily

መረጃው ጠቃሚ ነውና እናካፍል፡፡
ዛሬ በታሪክ ውስጥ
ልክ በዛሬው እለት 1929 ፋሺስት ጣልያን ኢትዮጵያንን በ ሙስታርድ ጋዝ ጨረሶ ነበር፡፡
ለመሆኑ ሙስታርድ ጋዝ ምንድነው?
ሙስታርድ ጋዝ ወይም ሰልፈር ሙስታርድ (Cl-CH2CH2)2S በጋዝ ደረጃ ከለር የሌለው ነገር ግን በሌላ ደረጃ ደማቅ ቢጫ ወይም ጎመኔ ከለር ያለው ኬሚካል ነው፡፡
ሙስታርድ ጋዝ በቆዳ፣ በአይን እና በእስትንፋስ ላይ ችግር የሚፈጥር ጋዝ ነው፡፡ ሙስታርድ ጋዝ በትንፋሽ፣ እንዲሁም በዓይን እና በሰውነት ንክኪ ወደ ሰውነታችን በቀላሉ ሊገባ ይችላል፡፡
ሙስታርድ ጋዝ ወደ ሰውነትችን ከገባ እነዚህን ጉዳቶች ይፈጥራል
• ዓይናችን፡- ቀይ መሆን፣ ማቃጠል፣ መጉረብረብ፣ መመረዝ እና አስከ መጥፋት ድረስ ሊፈጠርበት ይችላል
• ቆዳችን፡- እከክ የሚመስል ቀይ መሆን እናም ከዛ በኋላ ወደ ቢጫ ውሀ መቋጠር ይቀየራል
• የመተንፈሻ አካለችን ላይ ፡- ማስነጠስ፣ ማሳል፣ ከአፍንጫ ደም መፍሰስ፣ የጉሮሮ መጎርነን፣ የትንፋሽ መቆራረጥ፣ የአስም በሽታ መፈጠር ሊያጋጥመው ይችላል፡፡
• የምግብ መፈጨት ሥርዓታችን ላይ ፡- የሆድ ህመም፣ ማስመለስ፣ ማስቀመጥ፣ ትኩሳት እና ማቅለሽለሽ ያጋጥመዋል
ከዚህ በተጨማሪ ሙስታርድ ጋዝ የሰው ልጆችን ዲ.ኤን.ኤ( DNA) በመጉዳት ለተለያዩ ካንሰሮች የመጋለጥ ዕድላቸውን ይጨምራል፡፡
ለሙስታርድ ጋዝ የተጋለጡ እርጉዝ ሴቶች ጉዳት የተፈጠረበት ልጅ ወይም በካንሰር የተጠቃ ልጅ የመውለድ እድላቸው የጎላ ነው፡፡
ሙስታርድ ጋዝ በመጀመሪያ ጥቅም ላይ የዋለው በመጀመሪያው የዓለም ጦርነት ሲሆን እ.ኤ.አ በ1993 የተባበሩት መንግስታት የኬሚካል የጦር መሳሪያ ኮንቬንሽን የሙስታረድ ጋዝንና የሌሎች የኬሚካል መሳሪያዎችን በጦረነት ላይ መጠቀም አግዷል፡፡
ከብር ለሀገራቸው ብለው በየካቲት 12 /1929 በሙስታርድ ጋዝ ላለቁት ወገኖቻችን፡፡
ለወገኖቻቸን ክብር ይህን ማስታወሻ ሼር እናድርግ፡፡
የጡት ካንሰር

የጡት ካንሰር ማለት ከቁጥጥር ውጪ የሆነ የጡት ሕዋሳት ዕድገት ማለት ነው፡፡ ብዙ ጊዜ በዚህ በጽሽታ የሚጠቁት ሴቶች ቢሆኑም በወንዶች ላይም የመከሰት ዕድል አለው፡፡

የጡት ካንሰር በዓለማችን በሴቶች ላይ ከሚከሰቱ የካንሰር ዓይነቶች በሁለተኛ ደረጃ ላይ የሚገኝ ሲሆን በአብዛኛው ከ50 ዓመት በላይ በሆኑ ሴቶች ላይ የመከሰት ሰፊ ዕድል አለው፡፡ የካንሰር ሕዋሳት ቀድሞ የሚሰራጨው ብብታችን ስር ወደ ሚገኘው አካባቢ ሲሆን ይህም የብብት ስር እብጠትን ሊያስከትል ይችላል፡፡

የጡት ካንሰር ቅድሚያ ካልተደረሰበትና ሕክምና ካላገኘ ወደ ጉበት እንዲሁም ወደተለያዩ የሰውነት ክፍሎች በመሰራጨት እስከ ሞት ሊያደርስ የሚችል በሽታ ነው፡፡

የጡት ካንሰር መንስዔዎች

የጡት ካንሰር መነሻ መንስዔዎች በእርግጠኝነት የሚታወቁ ባይሆንም የተካሄዱ ጥናቶችን መሰረት በማድረግ ለሕመሙ ተጋላጭነትን የሚጨምሩ ሁኔታዎች በከፊል እንደሚከተለው ቀርበዋል

• ዕድሜ፡- በጡት ካንሰር የመጠቃት ዕድል በእያንዳንዱ 10 ዓመት የሕይወት ዘመን በእጥፍ የሚጨምር ሲሆን በአብዛኛው ከ50 ዓመት በላይ በሆኑ ሴቶች ላይ ይከሰታል፡፡
• በዘር፡- ይህ የካንሰር ዓይነት በዘር የመተላለፍ ባህሪ ያለው ሲሆን በካንሰር ሕመሙ የተጠቃው የቤተሰብ አባል እናት፣ እህት ወይንም ሴት አያት ከሆኑ የመተላለፍ ዕድሉ ከፍተኛ ይሆናል፡፡
• ከዚህ ቀደም የጡት ካንሰር ሕመም የነበረባቸው
• በቶሎ ልጅ አለመውለድ ወይም የመጀመሪያ ልጃቸውን ዕድሜያቸው ከ30 ዓመት በላይ ከሆኑ በኋላ የወለዱ ሴቶች
• ጡት ያለማጥባት
• ደረታቸው ለብዙ ጊዜ ለጨረር የተጋለጡ ሴቶች
• ከፍተኛ የአልኮል መጠን ያላቸውን መጠጦች ማዘውተር
• ሲጋራ ማጨስ

የጡት ካንሰር ሕመም ምልክቶች

1. በጡት ላይና በአካባቢው የሚወጣ እባጭ፡- አብዛኛውን ጊዜ የጡት ካንሰር ሕመም ምልክት የሚሆነው ሕመም የለሽ የሆነ እባጭ ነው፡፡ ይህ እባጭ አብዛኛውን ጊዜ ወደ ሰውነት የሚሰራጭ የካንሰር ዓይነት ሊሆን ይችላል፡፡ ነግር ግን ወደ ሕክምና ተቋም በመሄድ ማረጋገጥ ተገቢ ነው፡፡

2. የጡት መጠንና ቅርጽ መለያየት፡- አንዱን ጡት ከሌላኛው ጡት ጋር በማነጻጸር የቅርጽ እና የመጠን ልዩነት ካስተዋሉ ወደ ሕክምና በመሄድ ማረጋገጥ ተገቢ ነው፡፡

3. በተወሰነ የጡት ቆዳ ላይ የመጠንከር ስሜት መከሰት

4. የጡት ጫፍ ወደ ውስጥ መገልበጥ ፡- ይህ ዓይነት የጡት ጫፍ ወደ ውስጥ መገልበጥ ከልጅነት (ቀድሞ የነበረ) ወይም ተፈጥሯዊ የሆነውን የጡት ጫፍ መገልበጥ አያካትትም፡፡

5. የሕመም ስሜት፡- አልፎ አልፎ በጡት አካባቢ የሕመም ስሜት ሊኖር ይችላል፡፡ ነገር ግን የጡት አካባቢ ሕመም በአብዛኛው የካንሰር ሕመም ቀዳሚ መገለጫ ወይም ምልክት ላይሆን ይችላል፡፡

የማይሞት መረጃ ስለሆነ ተጠቅመን ሌሎችን ለመጥቀም እንትጋ፡፡ ሼር
ምን ጊዜዎትን በመቀመጥ ያሳልፋሉ?
አብዝቶ መቀመጥ ለአእምሯችንለምንድነው አደገኛ የሚሆነው?

በብዙ የህይወት መንገዶች አእምሯችንን መጠቀም በምንፈልግበት ቦታ በትምህርት ቤት፣ በስራ ቦታ፣ በፈተና እና በተለያዩ ቦታዎች መቀመጥን እናዘወትራለን፡፡ በቅርቡ በወጣ ጥናት ረዘም ላለ ጊዜ መቀመጥ የአእምሮ ነዳጅ (brain’s fuel) አቅርቦት ላይ ተጽኖ ከማሳደር ባሻገር በአእምሮም ጤና ላይ አሉታዊ ተጽኖ ሊያመጣ ይችላል፡፡
አእምሯችን ጉሉኮስ የተራበ አካል ነው፡፡ ምንም አንኳ የሰውነታችንን ክብደት 2% ብቻ የሚሸፍን ቢሆንም 20% የኛን ሀይል/ኢነርጂ የሚጠቀመው እርሱ ነው፡፡ ይህ ሀይል ደግሞ በአብዛኛው የመጀመሪ ደረጃ የአዕምሮ ነዳጅ በሆነው ጉሉኮስ መልክ የሚገኝ ነው፡፡ የዚህ ሀይል ስርጭት ከተቋረጠ የአዕምሯችንን ሴሎች ሊጎዳ ይችላል፡፡ ስለዚህ የጉሉኮስ በበቂ ደረጃ መኖር ከአይምሮ ጤንነት ጋር ቀጥተኛ ዝምድና አለው፡፡
አይሞሯችን ለከፍተኛ ጉሉኮስ መጠንም ይሁን ለአነሰተኛ ጉሉኮስ መጋለጥ ( dementia) ዲሜንሺያ ለተሰኘው ህመም የመጋለጥ አደጋን ይጨምርበታል፡፡ ይህም የሚጠቁመው በተገቢው መንገድ ጉሉኮስን መቆጣጠር ለአእምሮ ጤና እጅግ አስፈላጊ አስፈላጊመሆኑን ነው፡፡
አብዝቶ መቀመጥ ከሚያመጠው የጤና እክል ውስጥ፡-
• በለጋ ዕድሜ ለሞት የመጋለጥ (early death) አደጋን ከፍ ያደርገወል
በግምት 60-75 መጠነኛ የአካል ብቀት እንቅስቃሴ ማድረግ በቀን ስምንት ሰዓት በመቀመጥ የሚመጣን በለጋ አድሜ ለሞት የመጋለጥ አደጋን ለማጥፋት ይረዳል፡፡
• አብዝቶ መቀመጥ የጉሉኮስ መጠንን በማዛባት ለአእምሮ ጤና ችግር ያጋልጥል
አብዘኛው ጥናቶች መቀመጥ በመቀነስ በተወሰነ መጠን መራመድ ከምግብ በኋላ ጉሉኮስ መጠንን ይቆጣጠራል፡፡
• አብዝቶ መቀመጥ በአእምሯችን የደም ስርጭትን ሊቀንስ ይችላል
ከመቀመጥ ይልቅ መራመድ በአእምሯችን የተሻለ የደም ዝውውር እንዲኖር ይረዳል፡፡ የአእምሮ የደም ዝውውር ለአእምሮ የሚቀርበውን የጉልኮስ መጠን በመቆጣጠር አእምሮ ጤና ላይ አወንታዊ ተጽኖ ይፈጥራል፡፡ በአእምሮ የደም ዝውውር መቀነስ የአእምሮ ስራ በፍጥነት እንዲቀንስ የማድረግ እና ከመርሳት በሽታ (Alzheimer’s disease) ጋር ሊያያዝ ይችላል፡፡
ስለዚህ ምን እናድርግ ካለችሁን
አብዝቶ መቀመጥ ስለሚያመጣው የአእምሮ ጤና ጉደት ሁሉንም የሚያስማማ አንድ የሆነ ጥናት ባይኖርም አብዝቶ መቀመጥ የጉሉኮስ መቆጣጠር መጠን በመቀነስ የአእምሮ ጤናችን ላይ እክል ስለሚፈጥር
• ከምግብ በኋላ የመቀመጥ መጠናችንን ብንቀንስ መልካም ነ
• ከምሳ በኋላ የእግር ጉዞ ማድረግ
• ከራት በኋላ በተለያየ መንገድ እንቅስቃሴ ማድረግ(ለምሳሌ፡- የተበላበትን እቃ በማጠብ ሊሆን ይችላል)
• ጠዋት ወደ ስራ ስንሄድ ወይም ከስራ በኋላ በእግር መጓዝ
የምንቀመጥበትን ሰዓት በመቀነስ የአዕምሯችንም ሆነ የአካላችንን ጤና እናስጠብቅ፡፡ ሼር ማድረግ አይዘንጉ፡፡
ምንጭ፡- የአለም የኢኮኖሚ ፎረም ከ the Conversation ጋር በጋራ
ትኩስ ሻይ መጠጣት ለምግብ ቧንቧ ካንሰር ያጋልጣል

በ አሜሪካን ኮሌጅ ኦፍ ፊዚሻን የወጣው ጥናት እንሚያሳየው ትኩስ ሻሂ የሚጠቀሙ በጨማሪም ሲጋራ የሚያጨሱና አልኮል የመጠጡ ሰዎች በ ጎሮሮ ካንሰር የመጠቃት እድላቸው ከፍተኛ ነው፡፡
ረዥም ጊዜ የፈጀው ይህ ጥናት አራት መቶ ሀምሳ ሺህ ተሳፊዎች ነበሩት፡፡

የጎሮሮ ካንሰር በአብዘኃኛው የታዳጊ አገራት ሰዎችን በተለይም ወንዶችን የሚያጠቃ በሽታ እንደሆነ የከዚህ በፊት ጥናቶች ያመለክታሉ፡፡ ቻይና ከፍተኛ የ ጎሮሮ ካንሰር የሚያጠቃቸው ሰዎች የሚበዙባት አገር ስትሆን ከጊዜ ወደጊዜም ይህ በሽታ በአገሪቷ ውስጥ እየጨመረ መጥቷል፡፡

በጥናቱም 450 ሺህ የሚጠጉ እድሜቸው ከ 30 – 70 የሚሆኑ ሰዎች ላይ ተካሂዶ የነበረ ሲሆን ጥናቱን ለማጠናቀቅ 9 ዓመት ገደማ ፈጅቷል፡፡

የጥናቱ ውጤት እንደሚያሳየው ከሆነ 3ቱ በሃሪ ያላቸው ማለትም አልኮል የሚጠቀሙ ፣ ሲጋራ የሚያጨሱ እና ትኩስ ሻሂ የሚጠጡ ሰዎች 3ቱ በሃሪ ከሌለባቸው ሰዎች ይልቅ በ አምስት እጥፍ በጎሮሮ ካንሰር የመያዝ እድል ኖሯቸዋል፡፡ አጥኚዎቹ እንዳሉት ከሆነ የሲጋራ እና የመጠጥ ኬሚካሎች ከትኩስ ሻሂ እንፋሎት ጋር የሚኖራቸው ውህድ ለጎሮሮ ጤናማ ሁኔታን አይፈጥርም፡፡

በመጨረሻም ሳይንቲስቶቹ አልኮል የሚጠቀሙ እና ሲጋራ የሚያጨሱ ግለሰቦች ትኩስ ሻሂ ከመጠጣት ቢታቀቡ በጎሮሮ ካንሰር የመያዝ እድላቸው እንደሚቀንስ ጠቁመዋል፡፡

ማሳሰቢያ፡- ትኩስ ሻይ መጠቀም ለብቻው ለጎሮሮ ካንሰር አያጋልጥም፡፡ አልኮሆል እና ሲጋራ እስካልተጨመረበት ድረስ፡፡ ሼር

ምንጭ ፡-sciencedaily and others
በቀን ምን ያህል ጨው መውሰድ ይኖርብናል?

ይህ ጥያቄ በየጊዜው የሚነሳ እና ሳይንቲስቶችን የሚያጨቃጭቅ አጀንዳ ነው፡፡ ጨው 40 በመቶ ሶዲየም እና 60 በመቶ ክሎሪን ሲሆን 100 በመቶ ደግሞ ጣፋጭ ነው!!

ሰው ለመኖር ምን ያህል ጨው መውሰድ አለበት ሲባል ምን ያህል ሶዲያም መውሰድ አለበት እንደማለት ነው፡፡ በቱሌን ዩኒቨርሲቲ የ global public health ፕሮፌሰር የሆኑት ዶ/ር ፖል ዌልተን ከ ሊቭ ሳይንስ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ እንደገለጡት ከሆነ ሶዲየም በ ሴሎች በስተውጪ የሚገኝ እጅግ ጠቃሚ ኤሌክትሮላይት ነው፡፡

ኤሌክትሮላይቶች ማለት በጣም ጥቃቅን የሆኑ ንጥረ-ነገሮች ሲሆኑ በውሃ ውስጥ በመዋሃድ ፖዘቲቭ ወይንም ኔጌቲቭ የሆኑ ኤሌክትሪኮች ያመነጫሉ፡፡ የእነዚህ ንጥረ ነገሮች በተመጣጣኝ ሁኔታ መኖር ጤናችን ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ ያሳድራል፡፡ የደም ግፊት፣ የነርቮች ጤናም ሆነ የጡንቻዎች በተገቢው ሁኔታ መስራት ከእነዚህ ኤሌክትሮላይቶች ጋር ቀጥተኛ ዝምድና አለው፡፡

ይሁንና አሜሪካን ውስጥ በተጠናው ጥናት መሰረት አሜሪካዊያን ከተገቢው በላይ ሶዲየም እንደሚጠቀሙ ተረጋግጧል፡፡ አንድ አሜሪካዊ ሊወስደው የሚገባው የሶዲየም መጠን በቀን በአማካኝ 2300 ሚሊገራም ሆኖ ሳለ ጥናቶች የሚያሳዩት እስከ 3400 ሚሊገራም ድረስ እንደሚጠቀሙ ነው፡፡

እንደዚህ ያለ የበዛ የጨው አጠቃቀም ለ ደም ግፊት እና ለድንገተኛ የልብ ድካም እንደሚያጋልጥ የተለያዩ ጥናቶች ጠቁመዋል፡፡

ስለዚህ ለመኖር በቀን ምን ያህል ጨው ብንመገብ ይበቃል?
ዶ/ር ፖል እንደተናገሩት ከሆነ አንድ አሜሪካዊ በ ቀን ውስጥ 1500 ሚሊ ግራም ጨው ቢመገብ ይበቃዋል ብለዋል፡፡ ይህ መጠን ማለት የደም ግፊት ያለባቸው ሰዎች የመጨረሻው በቀን ውስጥ ሊመገቡት የሚችሉት የጨው መጠን ማለት ነው፡፡ ወይንም Center for Disease Control and Prevention (CDC) ከ 3 አመት በታች ያለ ህፃን ልጅ ሊመገበው የሚገባው የጨው መጠን ብሎ ካስቀመጠው የጨው መጠን ጋር እኩል እንደማለት ነው፡፡

እንደ American Heart Association (AHA) ያሉ ተቋሞች ደግሞ እንደውም ከዚህ በጣም ያነሰ ቢሆን ጥሩ ነው ይላሉ ፡፡ ማለትም 500 ሚሊገራም እና ከዛ በታች፡፡ ማለትም ሩብ የሻሂ ማንኪያ ጨው እንደማለት ነው፡፡

እንዲህ ያለው የጨው አጠቃቀም አንደ አሜሪካን ላሉ በፋብሪካ ውስጥ ፕሮሰስ ተደርጎ የወጣን ምግብ ለሚመገቡ አገራት እጅግ በጣም ሩቅ ሊሆን የማይችል ዓይነት ምክር ነው፡፡ ምክኒያቱም አንድ አሜሪካዊ በቀን ይመገበዋል ከተባለው የሶዲየም መጠን ማለትም (3400 ሚሊግራም) 71 በመቶ የሚሆነው የሚመጣው ከእነዚህ በፋብሪካ ፕሮሰስድ ሁነው ከሚመጡት ምግቦች ነው፡፡

ስለዚህ ከእንደዚህ ያለ ነገር እራስን ለመታደግ ተፈጥሯዊ የሆኑትን ምግቦች በቤት ውስጥ እያዘጋጁ መመገብ ይኖርባቸዋል፡፡

በአንዳንድ ሁኔታ ደግሞ ሰዎች ሊኖራቸው ከሚገባ ያነሰ የሶዲየም መጠን ይኖራቸዋል፡፡ ይህም የሚሆነው ሶዲየሞች ከሰውነታቸው በፍጥነት ስለሚወገድ እና የወጣው ደግሞ ስለማይተካ ነው፡፡

ይህ የሶዲየሞች ሙሉ ለሙሉ በውሃ ውስጥ ቀልጦ መጥፋት እና ከሰውነት መወገድ የመድከም፣ የተደጋጋሚ እራስ ምታት እና አንዳንዴም ለህይወት አስጊ የሚሆንበት ሁኔታ እንዲፈጠር ያደርጋል፡፡

ይህ ከፍተኛ የአካል እንቅስቃሴ የሚያደርጉ በተለይም ሯጮች ላይ ይከሰታል፡፡ ለዛም መፍትሄው sport drinks የተሰኙ ተጨማሪ ኤሌክትሮላይቶችን የያዙ ፈሳሾቸን መጠጣት ነው፡፤
የምንመገበው ስለኛ ብዙ ያወራል፡፡

ወደ ውስጣችን ስለሚገባው ሁሉ ግድ ይኑረን፡፡ ሼር

ምንጭ፡- Live Science
አባት ላልተወለደው ልጅ የአዕምሮ እድገት ኃላፊነቱን ይወሰዳል

በሜሪ ላንድ የህክምና ዩኒቨርሲቲ ወስጥ በተደረገው ጥናት መሰረት የአባት የ ስሜት እና የአዕምሮ ሁኔት የሚወለደው ልጅ የአዕምሮ ሁኔታ ላይ ተፅዕኖ እንደሚያሳደድር ታወቀ፡፡

በአይጦቹ ላይ በተደረገው ጥናት መሰረት አባት ውጥረት እና ጭንቀት ውስጥ በሚሆንበት ጊዜ የወንዴ ዘሩ (sperm) ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ እንደሚያሳድር እና ያ ደግሞ ለሚወለደው ልጅ የአዕምሮ እድገት እንቅፋት እንደሚሆን ለማረጋገጥ ተችሏል፡፡

እስከ ዛሬ ልጅ ከመወለዱ በፊት ስለሚኖረው እድገትእና ጤና ሲወራ ሳይንቲስቶች ትኩረት የሚሰጡት የእናት አመጋገብ፣ የአዕምሮ ሁኔታ፣ እና የመሳሰሉት ጉዳይ ላይ ብቻ ነበር፡፡ ይሁንና በ ኒውሮሳይንቲስቷ የተመራው ይህ የ ሜሪላንድ ዩኒቨርሲቲ ጥናት የተለየ ነገር ይዞ ብቅ ብሏል፤ አባትም ላልተወለደው ልጅ የአእምሮ ሁኔታ ታላቅ ሚና እንሚኖረው አስረግጧል፡፡

ኒውሮሳይንቲስቷ አይጦቹ ላይ ባደረገችው ጥናት ውስጥ እንደታየው ጭንቀት microRNA የተሰበኘውን የወንዴዘር ክፍል ይጎዳዋል፡፡ ይህ ክፍል ጂኖች ወደ ግልጋሎት ሰጪ ፕሮቲንነት እንዲቀየሩ የሚያደርገው ወሳኝ ክፍል ነው፡፡

ጥናቱ ለ ትልቅ እውቀት በር ከፋች እንደሚሆን ይገመታል፡፡ ህፃናት እንክብካቤ ሚያስፈልጋቸው ገና ሳይጠነሰሱ ጀምሮ በመሆኑ እያንዳንዱ ጥሩ ያልሆነ አከባቢ የወደፊት እድገታቸውን እና ህይወታቸውን የመወሰን ትልቅ ስልጣን ይኖረዋል፡፡

ወላጅነት ኃላፊነት ነው፡፡ ደስተኛ እና ጤነኛ ቤተሰብ መሆን ልጆች ላይ የሚታይም የማይታይ ም ተፅዕኖ ያሳድራል፡፡

ስለዚህ ስቲክ ኢትዮጲያም ስለ ራሳችን እና ስለ ስሜታችን ግድ እንዲኖረን በመሆን ልጆቻችንን ከማይወጡት ዘልዓለማዊ ቀውስ እንታደግ እያለ መልካም ቀን ተመኝቷል፡፡

እጅግ ጠቃሚ ነውና መረጃውን ሼር ማድረግ አንዘንጋ

ምንጭ፡- sciencedaily
አድዋ ትልቅ የአሸናፊነት ስነልቦና መገለጫ!!
ለመሆኑ የአሸናፊነት ስነልቦና ማለት ምን ማለት ነው?
አሸናፊነት ሌላውን ስለመጣል አይደለም አሸናፊነት ያሰብነው ስኬት ላይ ስለ መድረስ ነው፡፡ ግባችን ደስታን ፣ ሰላምን ፣ ነፃነትን አሊያም ሌላን ማግኘት ሊሆን ይችላል፡፡ ይህ ሁሉ በአድዋ ተገኝቷል፡፡ አሸናፊነት ከኛ ጋር አብሮ የሚያድግ እና የራሱ የሆኑ በሀሪያት ያሉትም ነው፡፡
የአሸናፊነት ስነልቦና ባሕርያት
• ግልፅ እይታዎች (Self-Projection)
(Self-Projection) ማለት ማሳከት ስለምንፈልገው ነገር የሚኖረን ግልፅ አዕምሯዊ ስዕል ማለት ነው፡፡ አሸናፊ ለመሆን ከፈለግን ስለመጨረሻ ግባችን እና ስለምንሄድባቸው አቅጣጫዎች አዕምሯዊ ስዕል ያስፈልገናል፡፡ ለምሳሌ፡- በአሻናፊነታችን ውስጥ ልናሳካው የምንፈልገው ትልቁ ዓላማ ነፃነትን መቀዳጀት ከሆነ ነፃነትን በስነ ልቦናችን በደንብ አድርገን መሳል ኖርብናል፡፡ ነፃ ስንሆን ስለምናደርጋቸው ድርጊቶች እና ስለምንኖረው ህይወት ጥልቅ ዓይነ-ህሊና ሊኖረን ይገባል፡፡ ዛሬ ላይ በአዕመሯችን ውስጥ ያንን ቀን ለመኖር መሞከር ይኖርብናል፡፡
• ሊታዩ የሚችሉ ግቦችን/መዳረሻዎች ማስቀመጥ
ስለ ግባችን የሚኖረን ግልፅ እይታ (Self-Projection) የመጀመሪያው እርከን ነው ፡፡ ብቻውን በቂ አይደለም ፡፡ ስለዚህ ቀጣዩን እርከን መጀመር ይኖርብናል፡፡ የራሳችን የሆነ መዳረሻዎች/ ግቦች ሊኖሩን ይገባል፡፡ ማለትም አዕምሯችን ውስፅ ያለውን ስዕል ወደ ምድር ማውረድ እንድንችል የሚረዱን ስልታዊ አካሄዶችን መቀየስ፡፡
• በድርጊቶቻችን ጥሩ ጎኖች ላይ ማተኮር
ሁሌ ስለውድቀታቸን የምናስብ ከሆነ ነገሮችን ለማድረግ ፈሪና ጭንቀታም እንሆናለን ግባችንንም ማሳካት አንችልም፡፡ ድረጊታቸንን ስንጀምር ውጤቱ ጥሩ እንደሚሆን እርግጠኛ መሆን ይኖርብናል፡፡ ብወድቅ ባይሳካ የሚሉት ነገሮች ላይ ትኩረት ሰጥተን መጨነቅ የለብንም፡፡ ስለ ግባችን የሚኖረን ቀና አስተሳሰብ ለግባችን መሳካት ከምንለፋው ልፋት ያላነሰ ሚና ይጫወታል፡፡
• የባለቤትነት ስሜት መሰማት
የምናደርገው ነገር የግላችን እንደሆነ አድርገን ማሰብ አለብን፡፡ የምለፋውም ሆነ የምንታገለው ከኛ ውጭ ያለ አካል ስለፈለገው ሳይሆን ለኛ ስለሚያስፈልገን እንደሆነ ማመን ይኖርብናል፡፡ ለምሳሌ የሀገራችንን ነፃነት የምናስጠብቀው የመንግስት ፍላጎት ስለሆነ ሳይሆን ነፃነት ለኔ ያስፈልገኛል የሚል ስሜት ስላለን መሆን ይኖርበታል፡፡
• ራስን ማወቅ
ማንም ሰው ፍፁም አይደለም ፡፡ ማሸነፍ ማለት ፍጹም መሆን ማለት አይደለም ጉድለቶችን እየሞሉ መሄድ ነው፡፡ ጉድለታችንን በማወቅ እነሱን ለመሙላት ማሰብ ይኖርብናል፡፡
• በራስ መተማመን
አሸናፊ ለመሆን ከፍተኛ የሆነ በራስ መተማመን ያስፈልጋል፡፡ እኛ ለራሳችን ያልታየን እና ያልተሰማን ሌሎች ሰዎች ስለ እኛ ሊታያቸወ እና ሊሰማቸው የሚችልበት ሁኔታ ጠባብ ነው፡፡
• የራስ ስነ-ስርዓት
አሸናፊ ለመሆን ብዙ ግዜ አጭር መንግድ እንፈልጋለን ነገር ግን ማሻነፍ አቋራጭ መንገድ በመፈልግ የሚገኝ አይደልም ይልቁንም ጠንካራ በሆነ የመስራት ልማድ ቢሆን እንጂ፡፡
እናም የኛ አባቶች በትልቅ የአሸናፊነት ስነ ልቦና አሸነፉ ስንል እነዚህ የአሸናፊነት ባህሪያት ስላቸው ነው፡፡
“በትልቅ የአሸናፊነት ስነ ልቦና ደም ከፍለው ሀገራችንን ላቆዩልን ጀግኖች አባቶቻችን ክብር እና ምስጋና ይሁንልን"
ሼር
ምንጭ፡- Denis Waitley , Psychology of Winning
እጅ ለእጅ መያያዝ ህመም እንደሚያስታግስ ተረጋገጠ
የኮሎራዶ እና የሃይፋ ዩኒቨርስቲ ተመራማሪዎች በአንድነት ባደረጉት እና በሰሞኑ በ National Academy of Sciences (PNAS) ሊታተም በበቃው ጥናት መሰረት ፍቅር ልብ እና ስሜት ላይ ብቻ ሳይሆን አዕምሮ ላይ እራሱ ከባድ ተፅዕኖ እንደሚያሳድር ተረጋገጠ፡፡
አፍቃሪ ለተፈቃሪው ህምም የሚኖረው የእዝነት ደረጃ እና የአካል ንክኪ የታማሚው ሰው አዕምሮ ውስጥ (brain waves synchronization) ማለትም የአዕምሮ ሞገድ ቅንብር እንዲፈጠር ምክኒያት ይሆናል ብለዋል፡፡ አዲስ የአዕምሮ ሞገድ መፈጠር ደግሞ ህመምን የማባረር ትልቅ ሀይል አለው፡፡
የዚህ ምርምር የበላይ ተጠሪ የሆኑት ዶ/ር ፓቨል ጎልድስተን በጥናታቸው ውስጥ "በዚህ ዘመን የተለያዩ የመገናኛ ዘዴዎች የተፈጠሩ ቢሆንም አካላዊ ንክኪዎች ግን ቀንሰዋል ይሁንና የሰው ለሰው ንክኪዎች በሰው ልጆች ላይ ከባድ ተፅዕኖ ያሳድራሉ " ብለዋል ፡፡
ዶ/ር ጎልድስተን ይህንን ጥናት ለማጥናት መነሻ የሆናቸውን ምክኒያት ሲናገሩ እንዳሉት ከሆነ ባለቤታቸው ምጥ ላይ ሆና ጊዜ እጇን በምይዛት ጊዜ ህምሙ ቀለል ይልላት ነበር ብለዋል፡፡ ይህ መነሻ ሃሳብ እውነት የአካል ንክኪ ህመምን ከመቀነስ አንፃር ሚና ይኖረው ይሆን የሚል ጥናትን ሊወልድ ችሏል፡፡
ምርምሩም እንዲህ ነበር የተካሄደው፡-
እድሜያቸው ከ 23-32 የሚሆኑ የሃይፋ ዩኒቨርሲቲ ጥንድ ተማሪዎችዎችን መለመሉ፡፡ ጥንዶቹ በፍቅር አንድ አመት እና ከዛ በላይ አብረው የነበሩ ሲሆን ሁሉም (EEG) የተሰኘው የአዕምሮ መመርመሪያ መሳሪያ ውስጥ በመግባት የአዕምሯቸው ሞገድ ምን እንደሚመስል እንዲታይ ተደረገ፡፡
ከዛም ፍቅረኞቻቸው አጠገባቸው ሲኖሩ ፣ አጠገባቸው ሳይኖሩ እና አጠገባቸው ኑረው በተጨማሪ እጅ ለእጅ ሲያያዙ የሚኖረው የአዕምሮ ሞገድ ቅንብር ሊያይ እንደሚችል ሊያጠኑ ሞክረዋል፡፡
በጥናቱ ወቅት የሴቶቹን ምልምሎች እጅ በትንሹ በግለት እንዲጎዳ በማድረግ ህመም እንዲሰማቸው ካደረጉ በኋላ ፍቅረኞቻቸው እጆቻቸውን ሲይዟቸው የአዕምሮ ሞገዳቸው ላይ የሚፈጠር ለውጥ ሊኖር እንደሚችል ለመረጋገጥ በሞከሩበት ጊዜም አስደናቂ የሆነ ውጤት ሊያገኙም ችለዋል፡፡
በጥናቱ መሰረትም ፍቅረኞቻቸው አጠገባቸው በሚሆኑበት ጊዜ የተለየ የአዕምሮ ሞገድ የሚፈጠር እንደሆነ ያረጋገጡ ሲሆን አጠገባቸው ሁነው በተጨማሪም እጅ ለእጅ ሲያያዙ ደግሞ የአዕምሮ ሞገድ ቅንብራቸው በብዙ እጥፍ የሚጨምር ሆኖ ተገኝቷል፡፡ ያ ደግሞ በከፍተኛ ሁኔታ ህመማቸው እንይሰማቸው አድርጓቸዋል፡፡
ሳይንሳዊ በሆነ መልኩ ሊገለፅ ሲሞከር ይህ ሁኔታ የሚያስረዳው ፡-ህመም የአዕምሮ ሞገድ ቅንብርን የሚረብሽ ስሜት እንደሆነና ተፈቃሪዎች በአፍቃሪቸው በሚነኩበት እና እጃቸው በሚያዝበት ወቅት የተረበሸው ሞገድ ዳግም ከህመም በፊት እንደነበረው በመመለስ ታማሚው ህመሙ እንዲቀንስለት ምክኒያት ይሆናሉ፡፡ ልክ እጃቸው ሲላቀቅ ህመሙ ዳግም የአእምሯቸውን ሞገድ መረበሽ ይጀምራል፡፡
ሼር
ቃላት ለፍቅረኛችን ህመም የተሰማንን እዝነት ሊገልፁ ይችላሉ ንክኪዎች ግን በርግጥ ህመሙን ይፈውሳሉ!!
ምንጭ፡- sciencedaily
እርድ ያልተወራለት ተክል
እርድ አብዘኃኛውን ግዜ በህንድ እና በደቡብ ምስራቅ አሲያ ውስጥ ከፍተኛ ተቀባይነትን ያተረፈ ተክል ነው፡፡ እነዚህ ህዝቦች እርድን ከቀለም ፋይዳው ባለፈ ለብዙ የህክምና እና የስነውበት መጠበቂያነት ይጠቀሙበታል፡፡ በዓለም ላይ እርድን በተመለከተ የተደረጉ ብዙ ጥናቶች ያሉ ሲሆን ሁሉም ለሰውነት እና ለአዕምሮ ትልቅ ፋይዳ እንዳለው አረጋግጠዋል፡፡ በአገራችንም በተለይ በምስራቅ ኢትዮጲያ አከባቢ እርድ በውበት ጥቅሙ በከፍተኛ ደረጃ ተቀባይነትን አትርፏል፡፡
ከእርድ በራካታ የጤና ጥቅሞች ውስጥ 3ቱን ብቻ ብናይ፡-
1- ከሰውነት ውስጥ መርዛማ ውህድን ያስወግዳል
ድሮ ድሮ ህንዳዊያን ብቻ ይጠቀሙበት የነበረው የእርድ የህክምና ፋይዳ ዛሬ የምዕራባዊያኑን ዓይን መሳብ ጀምሯል፡፡ እርድ በውስጡ ኩርኩሚን የተሰኘ ንጥረ ነገር ያለ በመሆኑ የሰውነትን ብግነት (anti-inflammatory)የመቀነስ እና መርዛማ የሆኑ ውህዶችን ከሰውነታችን የማስወገድ(antioxidant.) አቅም አለው፡፡ ይሁንና ሰውነታችን የዚህን ንጥረ ነገር ፋይዳ በቀላሉ ለመውሰድ የሚቸገር በመሆኑ ከ ቆንዶ በርበሬ ጋር አብሮ ቢወሰድ የአወሳሰድ መጠኑ በ 2000 % ያድጋል፡፡
2- ተፈጥሯዊ ብግነት(inflammation) ይፈጥራል
በእርድ ውስጥ የሚገኘው ይህ ኩርኩሚን የተሰኘው ንጥረ-ነገር ወደ ሰውነታችን የሚገቡ ወራሪ አካላትን የመዋጋት በሀሪ ያለው ሲሆን የተጎዱ አካላትን በአዲስ የመተካትም አቅም ተስተውሎበታል፡፡ ያ በመሆኑ በሰውነታችን ላይ የተወሰነ ብግነት (inflammation) እንዲፈጠር ምክኒያት ይሆናል፡፡ ያልበዛ የሰውነት ብግነት በሰውነታችን ውስጥ መፈጠሩ ሰውነት በራሱ አካላት እንዳይጠቃ የማድረግ በሀሪ ስላለው እንደ ካንሰር፣ የልብ በሽታ፣ አልዛይመር እና ለመሳሰሉት ለዘላቂ በሽታዎች የሚኖርን ተጋላጭነት ይቀንሳል፡፡
3- የአዕምሮ በሽታ ተጋላጭነትን ይቀንሳል
Brain-Derived Neurotrophic Factor (BDNF) የተሰኘው ይህ ሆርሞን የአዕምሮ ኒውሮኖችን የመተካካት እና የመባዛት በሀሪን ያጎለብታል፡፡ በመሆኑም እንደ አልዛይመር እና ዱባቴ ያሉ የአዕምሮ ህመሞች የሚከሰቱት በዚህ ሆርሞን መመናመን ምክኒያት ነው፡፡ እርድ ይህንን የአዕምሮ ሆርሞን የመጨመር እና እንዳይመናመን የማድረግ አቅም ያለው በመሆኑ የአዕምሮ በሽታዎች እንዳከሰቱ ከፍተኛ እስተዋፅዖ ያበረክታል፡፡
"እርድ ከመከላከል ባለፈ የማከም በሀሪ ያለው በመሆኑ በተለያዩ ላብራቶሪዎች ውስጥ እንደ ካንሰር ያሉ በሽታዎችን የማዳን ኃይል እንዳለው ሊስተዋል ችሏል፡፡"
ሼር
ምንጭ ፡- healthline