TechIn2
1.22K subscribers
1.47K photos
1 video
120 files
500 links
Technology & Innovation Institute (TechIn2), Ethiopia

የቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኢኒስቲትዩት

ጠቃሚና ወቅታዊ የሆኑ የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ፈጠራ፣ ጤና እና ሰብአዊ-ኣቅም ግንባታ(Human Development)መረጃዎችንና ምክሮችን በየእለቱ እናደርሶታለን።
Download Telegram
የኢትዮጵያ ብሄራዊ የኮሮናቫይረስ ህክምና መመሪያ ታትሞ ለንባብ ቀርቧል
==========================
በኢትዮጵያ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን በመቆጣጠር ሂደት ውስጥ ለፖሊሲ አውጭዎች፣ ለህብረተሰብ ጤና ባለሙያዎች እንዲሁም ለሌሎች የህክምና አገልግሎቶች በሁሉም ደረጃ የሚያገለግል ስታንዳርዳይዝ የህክምና መመሪያ በትናትናው ዕለት ታትሞ ቀርቧል፡፡
ይህ ብሄራዊ መመሪያ ሃገሪቱ በዘርፉ ያላትን የተገደበ የቴክኖሎጂ አቅም እና የሰው ግብረሃይል ከግምት ውስጥ በማስገባት ሀብቱን በውጤታማነት እና ብቃት ለመጠቀም እንዲያስችል በሁሉም መልኩ የሚረዳ ነው፡፡ በስራው ላይ ከመላው ሃገሪቱ የተወጣጡ ከፍተኛ ልምድ ያላቸው የጤና ባለሙያዎች የተሳተፉበት ሲሆን በዋናነትም የጤና ሚኒስቴር ባደራጀው ብሄራዊ የኮቪድ 19 አማካሪ ኮሚቴ አማካኘንት ስራው ሲተገበር እንደነበር ተገልጿል፡፡
መመሪያው በወረርሽኙ ዙሪያ አሁን ያለውን እና በቀጣይ ወራት የሚኖረው አጠቃላይ መረጃ በመዳሰስ ለውሳኔ እነደሚረዳ የጠቆመው ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በዚህ አጭር ጊዜ ውሰጥ ይህን ስራ ለማጠናቀቅ ጊዜያቸውን እና እውቀታቸውን ሳይሰስቱ ሲንቀሳቀሱ የነበሩትን ባለሙያዎች አመስግኗል፡፡
መመሪያውን ከስር ባለው ሊንክ ማግኘት ይቻላል
http://www.moh.gov.et/ejcc/sites/default/files/2020-04/COVID%2019%20Handbook%20for%20health%20professionals%20FMOH%202020.pdf
ቻይና በኮሮናቫይረስ አነሳስ ላይ ትኩረታቸውን ያደረጉ ምርምሮችን እያገደች ነው
*******************************
የኮሮናቫይረስ ለመጀመሪያ ጊዜ የተከሰተባት ቻይና በቫይረሱ አነሳስ ላይ ትኩረታቸውን ያደረጉ የምርምር ውጤቶች እንዳይታተሙ ጥብቅ ቁጥጥር እያደረገች ነው፡፡ እንደመረጃው ከሆነ ከማዕከላዊ መንግስት በተሰጠ ማሳሰቢያ መሰረት ሁለት ዩኒቨርስቲዎች ከዚህ በፊት በድረገፃቸው ለጥፈውት የነበረውን የምርምር ፅሁፍ ማንሳታቸውን ሲ ኤን ኤን ዘግቧል፡፡
በአዲሱ ፖሊሲ መሰረት በኮቪድ 19 ላይ የሚደረጉ ማንኛቸውም ምርምሮች ወደህትመት ከመሄዳቸው በፊት ሌላ ተጨማሪ ግምገማ እንዲደረግባቸው የሚያዝ ሲሆን፤ በቫይረሱ አነሳስ ላይ ትኩረት የሚያደርጉ የምርምር ውጤቶች ደግሞ በጥብቅ ምርመራ ወይም (scrutiny) እንዲያልፉና የማዕከላዊ መንግስት ባለስልጣናት እንዲያፀድቋቸው የሚያስገድድ ነው፡፡ ሃገሪቱ ለዚህ እርምጃ እንደምክንያት ያቀረበችው በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ አነሳስ ወይም አጀማመር ላይ እየበረከቱ የመጡትን ትርክቶችን ለመቆጣጠር እንደሆነ የሃገሪቱ ባለስልጣናት ተናግረዋል፡፡
በቻይና ከጥር ወር አንስቶ አያሌ የጥናት ውጤቶች እና የምርምር ፅሁፎች በታወቁ አለምአቀፍ ጆርናሎች ሲታተሙ እንደነበር ያስታወሰው ዘገባው በቫይረሱ አነሳስ ዙሪያ ያተኮሩ ምርምሮች ያለምንም የመንግስት ጣልቃገብነት ወደ ህዝብ ሲደርሱ እንደነበረና ምንም አይነት እገዳዎች ሲጣሉ እንዳልነበር አወስቷል፡፡
የቻይና ተመራማሪዎች የተወሰደው እርምጃ በቫይረሱ ዙሪያ የሚደረጉ ሳይንሳዊ ምርምሮች በፍጠነት እንዳይደረጉና እድገታቸው እንዲቀንስ አስተዋፅ ያደርጋል ቢሉም፤ የሃገሪቱ መንግስት ግን በቫይረሱ አነሳስ ላይ የሚፈጠሩ አመለካከቶችን እና ትርክቶችን ለመቆጣጠር እርምጃው አስፈላጊ እንደሚሆን አስታውቋል፡፡
CNN
ቢያንስ 70 የሚሆኑ የኮሮናቫይረስ ክትባቶች በመሰራት ላይ ናቸው፤ ሶስቱ ደግሞ በክሊኒካል የሙከራ ሂደት እያለፉ ይገኛል
======================
የዓለም ጤና ድርጅት ባወጣው ሪፖርት እንዳስታወቀው አሁን ላይ ቢያንስ ቁጥራቸው 70 የሚሆኑ የኮሮናቫይረስ ክትባቶች ወይም (vaccines) በመሰራት ላይ ሲሆኑ፤ ሶስቱ ደግሞ የመጀመሪያዎቹ እጩ በመሆን የክሊኒካል ሙከራ በማለፍ ላይ እንደሚገኙ በዘገባው አመላክቷል፡፡ እነዚህ ከፍተኛ የምርምር ሂደት የሚያስፈልጋቸው ክትባቶች ውጤታማነታቸው እና ደህንነታቸው ተረጋግጦ ወደህዝቡ ለመድረስ ከሚወስዱት የረዥም ጊዜ የሙከራ ሂደት አንፃር እና ከሚጠይቁት ከፍተኛ በጀት አኳያ ብዙ ጊዜ ቢያስፈልጋቸውም ቫይረሱ በደቀነው ከፍተኛ አደጋ የተነሳ ብቻ ስራዎች በፍጥነት እንዲካሄዱ እኝሁ የጤና ባለስልጣናት ያሳስባሉ፡፡
የአለም ጤና ድርጀት በስሩ ከሚገኙ ተቋማት ጋር በመሆን ከትልልቅ የፋርማሲ ኢንዱስትሪዎች እና ከተለያዩ የባዮቴክ ኩባንዎች ጋር የሚያከናውኗቸው እነዚህ የተናጥል እና የጋራ ፕሮጀክቶች በመደበኛው ሂደት በትንሹ ከአምስት እስከ አስር ዓመት የሚፈልጉ ቢሆንም እነዚህ የመድሃኒት አምራቾች ግን አንዳንድ ሂደቶችን በማለፍ በአንድ አመትና ከዛ በጣረ ጊዜያት ውስጥ ስራዎች እንዲጠናቀቁ ከፍተኛ ጥረት በማድረግ ላይ ይገኛሉ፡፡
የአለም ጤና ድርጅት በሪፖርቱ እንደሚያመለክተውም በዚህ ሁኔታ በማለፍ በክሊኒካል የሙከራ ሂደት እያለፉ የሚገኙ እና በመጀመሪያ እጩነት የተካተቱ ሶስት ክትባቶች ያሉ ሲሆኑ፤ አነሱም በቻይናው የባዮቴክ ኩባንያ CanSino እና በአሜሪካ መቀመጫቸውን ባደረጉት ሁለት የባዮቴክ ኩባንያ Inovio Pharmaceuticals እና Moderna የሚሰሩ ክትባቶች መሆናቸውን አስታውቋል፡፡ እነዚህ ኩባንዎች ባገኙት ፈቃድ መሰረት ሌሎች ሂደቶችን በማለፍ ሙከራዎቻቸውን በሰዎች ላይ ማድረግ የጀመሩ ሲሆን፤ ከቤጂንግ የባዮቴክኖሎጂ ኢኒስቲትዩት ጋር በትብብር የሚሰራው CanSino ደግሞ ከሁለቱ ኩባንያዎች በተሻለ ፌዝ ሁለት ወደሚባለው የክሊኒካል ሙከራ እንደተሻገረም በሪፖርቱ ተገልጿል፡፡
እነዚህ እንቅስቃሴዎች በዚህ መልኩ ይደረጉ እንጂ ክትባቶቹን በዚህ ፍጥነት እንዲደርሱ ማድረጉ አደጋ ሊኖረው እንደሚችል የሚከራከሩም አሉ፡፡ በተለይ በአሜሪካ ብሄራዊ የአልርጂና ተላላፊ በሽታዎች ኢኒስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር የሆኑት ዶክተር አንቶኒ ፉቺ መስል ስራዎችን በብርቱ የሚቃወሙ ናቸው፡፡ እሳቸው እንደሚሉት ሁለትና ከዛ በላይ አመት የሚስፈልጋቸውን መሰል ስራዎች በአጭር ጊዜ ውስጥ ለመስራት መሞከር በመጨረሻው ውጤት ላይ አደጋ ሊያስከትል እንደሚችል ስጋታቸውን ይጋልፃሉ፡፡ ይሁንና ቫይረሱ ከደቀነው ሁለንተናዊ አደጋ አንፃር ክትባቶቹ በሚቻለው አቋረጭ መንገድ ወደምርት መግባታቸው እጅግ አስፈላጊ እንደሚሆን ብዙዎች የሚስማሙበት ነው፡፡
ምንጭ፡ Bloomberg
የውድድር ጥሪ ለፈጠራ ባለሙያዎችና ተመራማሪዎች በሙሉ
==============================
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር በCOVID-19 ቫይረስ መከላከል ላይ የተለያዩ የመፍትሔ ሃሳብና ፈጠራ ያላቸውን ተመራማሪዎችን እንዲሁም የፈጠራ ባለሙያዎችን አወዳድሮ በመደገፍ ሀገራችን ላይ የተጋረጠዉን ከፍተኛ አደጋ ለመዋጋት የፈጠራ ዉጤቶች በስፋትና በፍጥነት ተመርተው ጥቅም ላይ የሚዉሉበትን ሂደት ማመቻቸት ይፈልጋል።
በአሁኑ ሰዓት የኢትዮጵያ መንግስትና ህዝብ በፍጥነት እየተንሰራፋ እና ከፍተኛ ስጋት የሆነ የመጣዉን የ COVID-19 ቫይረስን ለመከላከልና ለመቆጣጠር እንዲሁም ስርጭቱን ለመግታት ከፍተኛ የሆነ እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ መሆኑ ይታወቃል፡፡
በመሆኑም የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከተለያዩ አጋር ተቋማትና ድርጅቶች ጋር በጋራ በመሆን መፍትሄ ለማበጀት የሚያስችሉ ሃገር በቀል የሆኑ የፈጠራ ሃሳቦችን አወዳድሮ በቀጥታ ወደ ተግባር ለማስገባት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ በኮሮና ቫይረስ መከላከልና መቆጣጠር ላይ ሃሳብና ፈጠራ ያላችሁ በተቋማችን ድህረ ገፅ www.techin.gov.et/announcement ላይ እስከ ሚያዚያ 16፣ 2012 ዓ.ም ድረስ አስፈላጊውን መረጃ በማስገባት መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።
ይህ የዉድድር ፕሮግራም COVID-19 Solution Challenge የሚል ስያሜ ተሰጥቶት ከUNITED NATIONS DEVELOPMENT PROGRAMME (UNDP) ጋር በመተባበር እየተኪያሄደ የሚገኝ ነው።
ለበለጠ መረጃ በ 0111265762 ይደውሉ
ማሳሰቢያ፡ -በአካል መገኘት አስፈላጊ አይደለም
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር
ለማሽተትና ለመቅመስ መቸገር የመጀመሪያው የኮሮናቫይረስ ምልክት ሊሆን እንደሚችል አንድ ጥናት አረጋገጠ
===================================
ቀደም ብለው ከተረጋገጡት የኮቪድ 19 ምልክቶች በተጨማሪ በቅርቡ በተለያዩ ሚዲያዎች ለማሽተትና ለመቅመስ መቸገር ሌላኛዎቹ የኮሮናቫይረስ ቀላል ምልክቶች ሊሆኑ እንደሚችሉ ሲዘገብ ቆይቷል፡፡ ነግር ግን እነዚህ ምልክቶች በቫይረሱ የተጠቃ ሰው ለመጀመሪያ ጊዜ የሚያሳያቸው ቀላል ምልክት ስለመሆናቸው በምርምር ባለመረጋገጡ የተነሳ ተማራመሪዎች ተጨማሪ ጥናቶችን ማካሄድ የግድ ብሏቸዋል፡፡
ይህ አዲስ ጥናት በፈረንጆቹ ሚያዚያ 12 ፎረም ኦፍ አለርጂ ኤንድ ራይኖሎጂ በተሰኘ አለምአቀፍ ጆርናል የታተመ ጥናት ሲሆን፤ ለማሽተትና ለመቅመስ መቸገር ቀደም ብለው ከሚታዩ የኮሮናቫይረስ ቀላል ምልክቶች የመጀመሪያዎቹ ስለመሆናቸውም የሚያትት ነው፡፡ የጥናት ቡድኑ እንደሚለው ከሆነ ለማሽተት የሚቸገሩ ሰዎች እንዲሁ ጨዋማ ነገሮች እና ጣፋጭነት ያላቸውን የተለያዩ ጣእሞች የመለየት አቅም ሊኖራቸው ቢችልም፤ የተለየ ፍሌቨር ያላቸውን ነገሮች ለመለየት እንደሚከብዳቸው ያስረዳል፡፡ ይህም ሁሉም ለማሽተት የሚቸገሩ ሰዎች በተመሳሳይ መልኩ ጣዕም የመለየት ችግር እንዲታይባቸው ያደርጋል፡፡
በጥናቱ ላይ 1,480 የሚጠጉ ከጉንፋንና መሰል በሽታዎች ጋር የተያያዙ ምልክቶች የታዩባቸው ታካሚዎች የተሳተፉ ሲሆን፤ በኮቪድ 19 መያዛቸውን ለማረጋገጥም በሳንዲያጎ የጤና ማዕከል ምርመራ ተደርጎላቸው ነበር፡፡ ታዲያ በውጤቱ መሰረት 102 የሚሆኑት ታካሚዎች የኮሮናቫይረስ ሲገኝባቸው ከእነዚህ ውስጥ ደግሞ 59 የሚሆኑት የማሽተት ችግር እንደታየባቸው አጥኙዎቹ ገልፀዋል፡፡ በዚህ ጥናት ላይ በኮሮናቫይረስ ተጠቅተው የማሽተትና የመቅመስ ችግር የታየባቸው ታካሚዎች 68% እና 71% የሚሆኑት ሲሆኑ፤ በአንፃሩ በኮሮናቫይረስ ካልተያዙት 1300 በላይ ታከሚዎች ውስጥ የማሽተትና የመቅመስ ቸግር የታየባቸው 16% እና 17% የሚሆኑት ብቻ ናቸው፡፡ ይህ ደግሞ ሽታን እና ጣዕምን የመለየት ችግሮች ከሌሎች በሽታዎች በተለየ በኮሮናቫይረስ ላይ በቀዳሚነት የሚታዩ ምልክቶች እንዲሆኑ ያደርጋቸዋል፡፡
ከዚህ ጋር አያይዘው የጥናቱ ዋና መሪ ዶ/ር ካሮል ያን እንደሚሉት በጥናታችን ውጤት መሰረት የማሽተትና የመቅመስ ችግር የታየባቸው ሰዎች ከሌሎች በሽታዎች ይልቅ በኮቪድ 19 ስለመጠቃታቸው 10 እጥፍ የሚያረጋግጡበት ጉዳይ ነው ብለዋል፡፡ እንደሳቸው ሃሳብ ከሆነ የማሽተትና የመቅመስ ችግሮች በቫይረሱ ተጠቂዎች ላይ ከ2 እስከ 4 ሳምንታት በሚቆየው የማገገሚያ ጊዜ ውስጥ ቀድመው የሚጠፉ የበሽታው ምልክቶች ቢሆኑም፤ በመጀመሪያው ሳምንት ላይ ግን በጉልህ (profoundly) የሚታዩ ምልክቶች መሆነቸውን ማወቅ ያስፈልጋል ይላሉ፡፡ በመሆኑም ቫይረሱን በመከላከል ሂደት ውስጥ ብዙዎች እንዲህ ያሉ ቀላል ምልክቶች ሲመለከቱ ቸል ብሎ ከማለፍ ይልቅ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ እና የጤና በለሙያዎችም መሰል ምልክቶች የሚታዩባቸውን ሰዎች እንደሌሎቹ የበሽታው ምልክቶች በመቁጠር ምርመራ እንዲደርጉ ምክራቸውን ይለግሳሉ፡፡
ምንጭ፡ Live Science
የኮሮና መድሃኒትን ፍለጋ ለአራት ወራት በቤተሙከራ ብቻውን ያሳለፈው ተመራማሪ ጥረት
===================
የኮቪድ-19 ወረርሺኝ መነሳቱ ከታወጀበት ጊዜ አንስቶ በዓለማችን የተለያዩ ጥጎች የሚገኙ ተመራማሪዎች ክትባት እና መድሃኑቱን ለማግኘት ከፍተኛ መሰዋዕትነት እየከፈሉ ይገኛሉ፡፡ ለዛሬም የቫይረሱ መነሻ እንደሆነች በምትገመተው ዉሀን ከተማ ውስጥ መድሀኒት ፍለጋ ለአራት ወራት የደከመውን ተመራማሪ ቃል ይዘንልዎ መጥተናል፡፡
“ከጥር አንስቶ ለኮቪድ-19 የሚሆን መድሃኒትን ፍለጋ እያንዳዱን ቀናት በቤተ-ሙከራ ውስጥ አሳልፌያለው፡፡ በሙያዬ የስትራክቸራል ባዮሎጂስት እና ፋርማኮሎጂስት ነኝ፤ ኑሮዩም የወረርሺኙ ማዕከል በሆነችው ዉሀን፤ ቻይና በሚገኘው ኋንዦሆንግ የሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ካምፓስ ውስጥ ነው፡፡ በወርሀ ጥር ከተማዋ በተዘጋችበት ወቅት ባልደረቦቼ የቻይና አዲስ ዓመትን ለማክበር ሄደው (ከከተማ ወጥተው) ስለነበረ መመለስ አልቻሉም፡፡ አሁን በቤተ-ሙከራችን መስራት የምችለው ብቸኛው ሰው እኔ ነኝ፡፡
የመድሀኒት ፍለጋ ጉዞዬን የጀመርኩት ከኮምፒውተሬ ነበር፡፡ ከባልደረቦቼ ጋራ በመሆን ከሳርስ-ኮቭ-2 ቫይረስ ላይ የተወሰዱ ሞዴል ፕሮቲኖችን በመጠቀም በሺዎች የሚቆጠሩ ፍቃድ የተሰጣቸው መድሃኒቶችን መርምረናል፤ በፕሮቲኖቹ ተጣብቀው ቫይረሶቹ ህዋሳቶአችን (cells) እንዳያጠቁ የሚከላከሉትን ለማግኘት፡፡
ፍለጋዬን በቤተ ሙከራዬ አሸጋግሬዋለሁ፡፡ አሁን ፕሮቲኖች ኤክስፕረስ የሚያደርጉ (ህዋሳትን ማጣመር፣ ማሻሻል እና መቆጣጠር) ህዋሳትን እያሳደኩና በክሮሞቶግሪፊ ማሽኑ ውስጥ (ምስሉ ላይ በስተግራ የሚታየው) እያጣራዋቸው ነው፡፡ ፕሮቲኖችን ከተለያዩ መድሃኒቶች ጋራ ስቀላቅላቸው፤ ሌላ ማሽንን በመጠቀም መድሀኒቱ በፕሮቲኖቹ ላይ መጣበቅ አለመጣበቃቸውን አያለሁ፡፡ ሳደርግ እንደምታዩኝ በፕሮቲን-መድሃኒት ጥምረቱ ላይ የሚገኘውን ክሪስታል በማይክሮስኮፕ አማካኝነት እመለከታለሁ፡፡ በመቀጠልም በክሪስታል መልክ የሆነውን አካል በፈሳሽ ናይትሮጅን ውስጥ አቀዝቅዤ (ወደ በረዶ) ከታች በስተ ግራ በሚገኘው ሳጥን ውስጥ እከታቸዋለው፡፡
አሁን በዚህ ያለው መዘጋት (የከተማ) ስላበቃ፤ የክሪስታል አካላቱን መድሀኒት እና ፕሮቲኖች እንዴት እንደሚጠያበቁ ከሚመረምሩ አጥኚዎች ዘንድ ለመላክ አስቤያለሁ፡፡ በሻንጋይ የሚገኙ ተባባሪዎቼ የመድሀኒቶቹን የማዳን አቅም የህዋሳት እና አይጥ ኮቪድ-19 ሞዴሎችን በመፈተሸ ላይ ናቸው፡፡
በ20 ዲ.ሴ ሙቀት እንዲቆይ በተደረገውና ጠረኑ እስከ ህዋሳቴ ዘልቆ ገብቶ በሚሰማኝ በዚህ ክፍል ውስጥ በቀን ከአንድ እስከ ስምንት ሰዓት እቆያለሁ፡፡ ሴት ልጅ እና ሚስቴ ከእኔ ጋራ ይኖራሉ፡፡ ወንድ ልጄ ግን ከአያቶቹ ጋራ በሌላኛው የዉሀን ሰፈር ይኖራል፡፡ ከጥር መጀመሪያ አንስቶ እስካሁን አይቼው አላውቅም፡፡
ከዩኒቨርሲቱው ጋራ የተሳሰሩ አስር ሆስፒታሎች አሉ፤ ሁሉም ከፊት ሆነው ወረርሺኙን የመዋጋት ስራ እየሰሩ ናቸው፡፡ የድርሻዬን እንደምወጣ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡”
ምንጭ፡ Nature
ውድ ተከታታዮቻችን መዘናጋት ዋጋ ያስከፍለናልና ዛሬም ከሰዎች ጋራ ያሎትን አካላዊ ርቀት ይጠብቁ፤ እጅዎንም በየጊዜው በደንብ ይታጠቡ፤ ሌሎችም በባለሙያ የተነገሩ የጥንቃቄ እርምጃዎችን ይውሰዱ፡፡
ኮቪድ-19 ከሞቱ ሰዎችም ሊተላልፍ እንደሚችል ጥናት አመላከተ
========================
ከቀናት በፊት የወጣ ጥናት በታይላንድ ባንኮክ የሚሰራ አንድ የሬሳ መርማሪ በቅርብ ለሞተ ሰው ሬሳ እንደተላለፈበት በተገመተ የኮሮና ቫይረስ መያዙን አመላክቷል፡፡ የሬሳ መርማሪው በኋላ ለሞት የተዳረገ ሲሆን ይህም የሬሳ ክፍል ውስጥ በሚሰሩ የህክምና ባለሙያዎች ላይ ሲከሰት የመጀመሪያው ሆኗል፡፡
የግለሰቡ በቫይረሱ መያዝ በተዘገበበት ወቅት ረዳት ነርሱን ጨምሮ በሀገሪቱ የነበሩ የታማሚዎች ቁጥር 272 ብቻ የነበረ መሆኑና አብዛኛዎቹም ከውጪ ሀገራት ገና መግባታቸው ስለነበረ ከሚሰራበት ሆስፒታል ውጪ በቫይረሱ የመያዙን ዕድል የጠበበ ያደርገዋል፡፡ እንደ ጥናቱ ከሆነ በሬሳ ክፍል የሚሰሩት የህክምና ባለሙያዎች ከታማሚዎቹ የባዮሎጂካል ቅንጣት/ሳምፕል አሊያም ሬሳ ጋራ ካላቸው ግንኙነት ውጪ ከቫይረሱ የመገናኘታቸው ዕድልም የጠበበ ነው፡፡
ትኩስ ሬሳ ኮቪድ-19ኝን ማስተላለፉ አስገራሚ እንዳልሆነባቸው የሚናገሩት በዴቪድ ጄፈን የህክምና ትምህርት ቤት ፕሮፌሰር የሆኑት ዶ/ር ኦቶ ያንግ መሟቾች ከህልፈታቸው በኋላ ቢያንስ ለሰዓታት ከፍ ሲልም ከቀናት በኋላ በሽታውን ሊያስተላልፉ እንደሚችሉ ያስረዳሉ፡፡
ቫይረሱ በሟቾች ሬሳ ውስጥ ለምን ያህል ጊዜ እንደሚቆይ በግልፅ አይታወቅም፡፡ በአለም የጤና ድርጅት መረጃ መሰረት መሰረት ሰዎችን ለህልፈት የሚዳርጉ ደቂቀ አካላት በሟቾች ሰውነት ውስጥ ያላቸው ቆይታ የአጭር ጊዜ እንደሆነ ያሳያል፤ በዚህ ረገድ ከፍተኛ ስጋት ካለባቸው እንደኮሌራና ኢቦላ ካሉት በሽታዎች ውጪ፡፡ ከተጠቂው ግለሰብ ሞት በኋላ ከሚተላለፉት ውስጥ በደም ንክኪ ይተላለፋሉ ብሎ ድርጅቱ ካስቀመጣቸው መካከል ሄፒታይተስ ቢ እና ሲ እንዲሁም ኤች አይ ቪ ቫይረሶች፣ የሳንባ ነቀርሳና የጨጓራና ሆድ ህመመ ኢንፌክሽኖች ይገኙበታል፡፡
የኮሮና የሟች ሰውነት ውስጥ የሚቆይበት ጊዜ መጥፎነቱ ለሬሳ ምርመራ ክፍል የህክምና ሰባለሙያዎች ብቻ አይደለም በቀብር ማስፈፀም ዙርያ ለሚሰሩም ጭምር እንጂ፡፡ ለምሳሌ የሪፖርቱን መውጣት ተከትሎ የቀብር ቦታዎች በኮሮና ምክንያት ለሞቱ ሰዎች ምንም አይነት የቀብር አገልግሎት እንደማይሰጡ አስታውቀዋል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ የፎረንሲክ መርማሪዎች በቫይረሱ ምክንያት የሞቱ ሰዎችን በሚመረምሩበት ወቅት የጥንቃቄ እርምጃዎችነ ሊወስዱ እንደሚገባ ጥናቱ ጠቁሟል፤ ለምሳሌ የመከላከያ ልብስ፣ የጭንቅላት መሸፈኛ እና የፊት ጭምብልን መጠቀም፡፡ በማከልም በቀዶ ህክምና ክፍል የሚደረጉት የፅዳት እርምጃዎች በሙሉ በሬሳ ምርመራ ክፍሎችም ሊከወኑ እንደሚገባ አስቀምጧል፡፡
ምንጭ፡ Scientific American
የሃር ምርት በኢትዮጵያና ፤ ፈተናዎቹ
==================
በኢትዮጵያ ለሺህ አመታት የተለያዩ ባህላዊና ሀይማኖታዊ ክዋዜዎች ውስጥ የራሱን ድርሻ ይይዛል፡፡ በኢትዮጵያ ሃርን ማምረት ከተጀመረም ሁለት አስርት ዓመታትን አስቆጥሯል፡፡ ምንም እንኳን በነዚህ ጊዜያት ውስጥ ዓመታዊ ምርቱ ከጊዜ ወደ ጊዜ በፍጥነት በማሻቀብ ላይ ቢሆንም ኢትዮጵያ ለሃር እርሻ ምቹ ከሚያደርጓት የአየር ንብረትም ሆነ ሌሎች ገፀ-በረከቶቿ አንፃር ግን የሚመረተው የሃር መጠን አነስተኛ እንደሆነ የመረጃዎች ጥቆማ ነው፡፡ በጥሬ እቃነትም ሆነ ያለቀለት የሃር ምርትን ወደ ባህር ማዶ ልኮ ይህ ነው የሚባል ገቢ ለሐገራችን ማስገባት አልተቻለም፡፡ የተለያዩ መረጃዎችን ያየን እንደሆነ በምርትም ሆነ ለምርት በሚያስፈልጉ ግብዓቶች ላይ ያሉ ድክመቶችን መገንዘብ ይቻላል፡፡ ለምሳሌ ለኤሪ የሃር ትሎች ምግብነት የሚውለው የጉሎ ቅጠል (castor) ምርት በሐገራችን 1,300 ኪ.ግ በሄክታር ሲሆን ይህን ህንድ ውስጥ በሄክታር 2,500 ሆኖ እናገኘዋለን፡፡ ለኤሪ ብቻ ሳይሆን ለመልበሪ ሃር ምግብ በሚሆኑ ዕፅዋትም ተመሳሳይ የልዩነት ደረጃ ይስተዋላል፡፡ በሃር ቅርፊቶቹ ረገድም በኢትዮጵያ ያሉት የሃር ትሎች ከተቀረው ዓለም ያነሰ ነው፡፡
ለዚህ ዘርፍ ጠንክሮ አለመውጣት የተለያዩ ምክንያቶች ይሰነዘራሉ፡፡ ከነዚህ ውስጥ ቀዳሚው ኢትዮጵያ ያለው በዘርፉ የሰለጠነ የሰው ኃይል እጥረት ነው፡፡ የሃር ግብርና ለሀገራችን አዲስ ከመሆኑ አንፃር በተለይ የሃር ትሎቹን ከማራባት አንስቶ ሃሩን ነጥሎ እስከማውጣት ያሉት የምርት ሂደቶች ለኛ እንግዳ የሆኑ ስልተ-ምርቶችን ይይዛሉ፡፡ ይህ የዕውቀት ክፍተት በትምህርትና ስልጠና መሟላት እስካልቻለ ድረስ በዘርፉ አጥጋቢ የሆነ ፍሬ ማግኘት አዳጋች ነው፡፡
ሁለተኛው የሃር ትሎቹ ከሚመገቧቸው እዕዋት ጋር የተገናኘ ነው፡፡ ውጤታማ የሃር ግብርናን ለማከናወን ትሎቹ የሚመገቧቸው እፅዋት ከፍተኛ የቅጠል ምርት የሚሰጡ፣ ተባይን የሚቋቋሙና የላቀ የመላመድ ብቃት ያላቸው መሆን ይገባቸዋል፡፡ በተጨማሪም በተለይ የሃር ምርት እንቅስቃሴው ባለበት ስፍራ ዕፅዋቶቹም የሚተከሉበት ስፍራ በስፋት እንዲኖር ያስፈልጋል፡፡ ሆኖም ይህ የመሬት አቅርቦት እጥረት እንዳለበት ለመረዳት ይቻላል፡፡ በተክሎቹ ዙሪያ የሚታዩት ሌሎቹ ክፍተቶች ዕፅዋቱን በተገቢው መልኩ ከማልማናት እና የዕፅዋት ዝርያዎቹን በተገቢው መልኩ አባዝቶ በቀላሉ ከምርት ስፍራው አቅራቢያ ከማድረስ አኳያ ነው፡፡
ሌላው ተጠቃሽ ክፍተት ከሃር ትሎቹ ጋር በተያያዘ ያለው ነው፡፡ ቀዳሚው የተሸሻሉ የሃር ትል ዝርያዎችን እና እንቁላሎቻቸውን በዓይነት በአይነት አባዝቶ ከምርት ስፍራዎቹ በአግባቡ ማቅረብ እንዲሁም በሃር ትሎቹ ላይ በመከሰት ጉዳት እያደረሱ ላሉት በሽታዎች መፍትሄ ማበጀት አለመቻሉ ነው፡፡ ይህን ያደርጉ ዘንድ ቅድሚያውን መውሰድ የነበረባቸው የትምህርት፣ ምርምር እና ስልጠና ተቋማትን ጨምሮ ሌሎችም አካላት ሚናቸውን በአግባቡ መወጣት አለመቻላቸው አንደኛው የክፍተቱ መንስኤ ነው፡፡
በጠቅላላው ለዘርፉ ተብሎ የተዘጋጀ ግልፅ ስትራቴጂ አለመኖር እንደ ዋና ችግር መቀመጥ ይገባዋል፡፡ ከዓመታት በፊት ኢትዮጵያን ጨምሮ በምስራቅ አፍሪካ ሀገራት የሃር ምርት ላይ ትኩረቱን አድርጎ የተሰራ አንድ ጥናት እንዳመላከተው የሃር ምርትን ተንተርሶ የውጪ ምንዛሬን ለማግኘት ከመጎምዠት ያለፈ በቂ የፖሊሲ አቅጣጫና ተግባራዊ ስራ አልተሰራም፡፡ ከነዚህ መሰራት የነበረባቸው ወሳኝ ተግባራት ውስጥ ሚዲያና ሌሎች መንገዶችን ተጠቅሞ ዘርፉን በህብረተሰቡ ውስጥ ከማስረፅ አንስቶ በቂ የምርምር እና ስርፀት፣ የሀገር ውስጥ ገበያ ትስስርን የማጎልበት፣ የሃር ትሎቹን ከማራባት ጀምሮ የሃር ምርቱን ለገበያ እስከሚደርስ ድረስ ባሉት ምዕራፎች ዘርፉ የሚጠይቃቸውን ቴክኖሎጂዎች የማሰራጨት እንዲሁም አስፈላጊ ስልጠናና የዕውቀት ክፍተትን የሚደፍኑ እንቅስቃዎች ላይ የተሰሩት ስራዎች አነስተኛነትን በግንባር ቀደምነት መጥቀስ ተገቢ ነው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በመሰረተ ልማት በተለይም በውሃና የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት ረገድ እንዲሁም በዘርፉ ላይ በስፋት ከተሰማሩት ሀገራት ጋር የሚደረገው የልምድ ልውውጥ አናሳነት ላለው የምርት ውስንነት ተጠቃሽ መንስኤዎች ናቸው፡፡
ምንጭ፡ ቴክ ሳይንስ ቅፅ ፲፮ (ሙሉ መፅሐፉን ከዲጂታል ቤተ መፅሐፍታችን/ library.techin.gov.et ማግኘት ይችላሉ)
የሁለት ሜትር ርቀር ኮሮናን ለመከላከል ላይበቃ ይችላል
===================
ሰሞኑን ከጤና ባለሙያዎች ሲነገር እንደሰማነው የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል 2 ሜትር/ ሁለት የአዋቂ እርምጃ ርቀትን መጠበቅ አስፈላጊ ነው፡፡ የዓለም ጤና ድርጅትን ጨምሮ የተለያዩ የጤና ተቋማትና ባለሙያዎች እንደሚገልፁት ዋነኛው የቫይረሱ መተላለፊያ መንገድ ቫይረሱ ያለባቸው ሰዎች ሲያስነጥሱና ሲያስሉ ከአፋቸው በሚወጣው ነጠብጣብ አማካኝነት ነው፡፡ በዚህ መሰረት ከሄድን የሁለት ሜትር ርቀትን መጠበቅ እጅን በተደጋጋሚ በደንብ መታጠብ ጋራ ተዳምሮ የበሽታውን ስርጭት ለመግታት ወይም ለመቀነስ በቂ ነው፡፡ ሆኖም አዲስ የወጣ ጥናት የሁለት ሜትር ርቀት በቂ ላይሆን እንደሚችል ጠቁሟል፡፡
ቫይረሱ በአየር ላይ የመንሳፈፍ ብቃቱ የጨመረ (airborne) ከሆነ ሰዎች በሚተነፍሱበትና በሚያወሩበት ወቅት በሚሰራጩ እጅግ አነስተኛ ነጠብጣቦች አማካኝነት ሊተላለፍ ይችላል፡፡ ሆኖም የተለያዩ ሁነቶች ሊወስኑት ይችላል፡፡ ለምሳሌ በቤት ውስጥ መሆንና አለመሆን፣ ጮክ ብሎ ማውራት፣ ጭንብል ማድረግ አለማድረግ፣ አየር በደንብ በሚዘዋወርበት ክፍል ውስጥ መሆን አለመሆን እና የቫይረሱ የመንሳፈፍ ብቃት፡፡
ሰዎች በሚተነፍሱበት፣ በሚያወሩበት፣ በሚዘፍኑበት፣ በሚያስሉበትና በሚያስነጥሱበት ወቅት በመጠናቸው የተለያዩ ጠብታዎች ከአፋቸው ይወጣል፡፡ እነዚህ ጠብታዎች በመጠናቸው አነስተኛና ከፍ ያሉ ተብለው ይመደባሉ፡፡ ታድያ ባለሙያዎችን ስጋት ውስጥ የከተተው ከ5 እስከ 10 ማይክሮ ሜትር ገደማ ዲያሜትር ያላቸው አነስተኞቹ ጠብታዎች ናቸው፡፡ ተለቅ ያሉት ጠብታዎች ብዙ ቫይረስና መሰል ቅንጣቶችን መሸከም ስለሚችሉ ከሰዎች ጋራ ሲገናኙ የማስያዝ እድላቸው ከፍ ያለ ነው፡፡ ሆኖም በዚህ መጠን ያሉ ጠብታዎች ክብደታቸው ስለሚጨምር ከአንድና ሁለት ሜትር በላይ ወደፊት ሳይጓዙ ከመሬት እንደሚወድቁ ይታመናል፡፡ እነዚህ ጠብታዎች ሰዎች በሚያስሉና በሚያስነጥሱበት ወቅት ከአፍ በመውጣት በቅርብ ያለ ሰውን ይበክላሉ፡፡ በተጨማሪም ሰዎች በሚያስሉበት ሰዓት አፋቸውን በሸፈኑበት መዳፋቸው ሌሎችን ሲጨብጡ፤ ወይም እቃ ሲነኩና ሌሎች ሰዎች እቃውን ነክተው ምግብ ሲበሉ፣ አይናቸው ሲያሻሹ፣ ወዘተ በበሽታው እንደሚጠቁ ይታመናል፡፡
ሰዎች ሲያወሩ ወይም ሲተነፍሱ የሚለቀቁ በ
መጠናቸው እጅግ አነስተኛ በሆኑ ጠብታዎችም ግን ሰዎችን የመበከለ፤ አቅም አላቸው፡፡ እነዚህ ጥቃቅን ጠብታዎች ግን ከአየር የሚመጣባቸውን ግፊት መቋቋም ስለማይችሉ ብዙውን ጊዜ ወደሰዎች ከአንድ ሜትር በላይ መቅረብ ሳይችሉ በዙርያቸው እንዲንዲዘዋወሩ ይገደዳሉ፡፡ ሆኖም ከአፍ የሚወጡት በአይን ከሚታይ እጅግ ጥቃቅን መጠን እስካላቸው ጠብታዎች ሁሉ ልክ ባልተረጋጋ አየር ምክንያት እንደሚፈጠሩ ደመናዎች በአየር ላይ ሊሰባሰቡ ይችላሉ፡፡ እነዚህ የጠብታዎች ስብስብ የሆኑ ያልተረጋጉ ደመናዎች ታድያ በውስጣቸው ያለው ሙቀት፣ እርጥበት እና አለመረጋጋት በአየር ላይ ለመጓዝ የሚበቃ ግፊትን ከሳል፣ ትንፋሽ፣ ማስነጠስ ወዘተ..ያገኛሉ፡፡ በዚህም መሰረት ነጠብጣቦቹ እስከ ስምንት ሜትር በአየር ላይ መጓዝ እንደሚችሉ በጆርናል ኦፍ አሜሪካን ሜዲካል አሶሴሽን የወጣው ጥናት ያሳያል፡፡ ታድያ ጠብታዎች ያን ያህል መጓዝ ከቻሉ ቫይረሶችም በእነርሱ ላይ ተሳፍረው ሊጓዙ ይችላሉ፡፡
በኒው ኢንግላንድ የህክምና ጆርናለ ላይ የወጣ ሌላ ጥናት በበኩሉ እጅግ ጥቃቅን ጠብታዎች የኮሮና ቫይረስን ተሸክመው ለሰዓታት በአየር ላይ ሊቆዩ እንደሚችሉ አውቋል፡፡ ይህ ግን በጥንቃቄ በተቀመረ ቤተ ሙከራ ውስጥ ነጠብጣቦቹን ከሰው ልጆች አተነፋፈስ በተለየ መልኩ በሚለቁ ማሽኖች የተሰራ በመሆኑ ጥችትን አስተናግዷል፡፡ ሆኖም መሰል ጥቃቅን ነጠብጣቦች ሁሌም በዙርያችን ያጋጥሙናል፤ ቫይረሱም በነዚህ ነጠብጣቦች ላይ የመቆየት እድል ሊኖረው ይችላል፡፡
መዝፈንም በተመሳሳይ ቫይረሱን የማሰራጨት ዕድል አለው፡፡ በአሜሪካኗ የዋሽንግተን ግዛት ውስጥ በአንድ ቦታ ተሰባስበው የነበሩ ድምፃዊያን ለዚህ አንድ ምሳሌ ናቸው፡፡ ድምፃዊያኑ ሲሰባሰቡ በመሀላቸው የ2 ሜትር ርቀትን ጠብቀው ነበር፡፡ ሆኖም ሲያቀነቅኑ እንደሆነ በሚታመን መልኩ 45 የቡድኑ አባላት በኮሮና ሲያዙ 2ቱ ሞተዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ሰዎች ከ2 ሜትር በላይ ተራርቀው ሲያወሩ ድምፃቸውን ከፍ ሊያደርጉ ይችላሉ፡፡ ይህ ደግሞ ከአፍ የሚወጡ ጠብታዎችን ስለሚያበዛ ስጋቱን ከፍ ያደርገዋል፡፡
ምንጭ፡ Science News