TechIn2
1.22K subscribers
1.47K photos
1 video
120 files
500 links
Technology & Innovation Institute (TechIn2), Ethiopia

የቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኢኒስቲትዩት

ጠቃሚና ወቅታዊ የሆኑ የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ፈጠራ፣ ጤና እና ሰብአዊ-ኣቅም ግንባታ(Human Development)መረጃዎችንና ምክሮችን በየእለቱ እናደርሶታለን።
Download Telegram
photo_2020-01-17_16-54-18.jpg
119.9 KB
የኢኖቬሽን ስታርታፕ እና ኢንኩቤሽን ፕሮግራም ጥሪ
=*=*=*=*=*=*=*=*=*=*=*=*=*=*=*=*=*=
የቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት ለሚያካሂደው የቴክኖሎጂ እና ቢዝነስ ኢንኩቤሽን ፕሮግራም ተመዝጋቢዎችን መቀበል መጀመሩን ያበስራል፡፡ ከአመልካቾች መካከል የተመረጡት ለስድስት ወራት ቆይታ ባለው በዚህ ፕሮግራም ላይ ተሳታፊ የሚሆኑ ሲሆን በቆይታቸውም የስራ ቦታ፣ የምክር እና ስልጠና አገልግሎቶችን ከኢንስቲትዩቱ ሲቀርብላቸው ከአማካሪዎች፣ የፋይናንስ አገልግሎት ሰጪዎች፣ ባለሀብቶች፣ የንግድ ባለቤቶች እና የኢኖቬሽን ሀብ ጋርም ትሰስር የሚፈጠርላቸው ይሆናል፡፡

መሳተፍ የምትፈልጉ ሁሉ ከታች በተቀመጠው ሊንክ አማካኝነት እስከ መጋቢት 4/ 2012 ዓ.ም ድረስ መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

https://forms.gle/RHdfBrCJUNdR5oaY7

ዕድሉ እንዳያመልጥዎ፤ ይፍጠኑ!!!
ቢግ ዳታ እና የ4ተኛው የኢንዱስትሪ አብዮት ጅማሮ
************************
ዓለማችን ባሳለፈቻቸው የመጨረሻዎቹ አራት ምዕተ ዓመታት ውስጥ አራት የተለያዩ የኢንዱስትሪ አብዮቶችን አሳልፋለች፤ በማሳለፍ ላይም ነች፡፡ የመጀመሪያው የኢንዱስትሪ አብዮት እ.አ.አ በ1700 መጨረሻ እና በ1800 መጀመሪያ በእንግሊዝ ተጀምሮ ወደ ተለያዩ የአለም ክፍሎች የተሰራጨ ሁነት ነው። ታድያ በዚህ አብዮት ልዩ መገለጫነት የሚወሳው በእንፋሎት የሚሰሩ መሳሪያዎች መፈጠር ነው። በሁለተኛው ማለትም በ19ኛው እና በ20ኛው ክፍለ ዘመን መካከል በነበረው የኢንዱስትሪ አብዮት ኤሌትሪክን በመጠቀም ምርቶችን በስፋት ማምረት ተጀምሯል። ሶስተኛውን እና አራተኛው የኢንዱስትሪ አብዮቶች ከመጀመሪያ ሁለቱ አብዮቶች በመለየት የኢንፎርሜሽን አብዮቶች ተብለው ይታወቃሉ። ሶስተኛው የኢንዱስትሪ አብዮት (የመጀመሪያው የኢንፎርሜሽን አብዮት) በ20ኛው ክፍለ ዘመን መጨረሻ የፈነዳ ሲሆን ኮምፕዩተር እና ኢንተርኔትን መሰረት ያደረጉ እውቀቶች መምጣት የጀመሩበት ጊዜ ነበር። አራተኛው የኢንዱስትሪ አብዮት (ሁለተኛው የኢንፎርሜሽን አብዮት) ከ21ኛው ክፍለ ዘመን መጀመሪያ እስከ አሁን ያለንበት ጊዜ የቀጠለ አብዮት ሲሆን በዚህ አብዮት ውስጥ እንደ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ፣ ኢንተርኔት ኦፍ ቲንግስ፣ ክላውድ ኮምፒዩቲንግ እንዲሁም ርእሳችን የሆነውም ግዙፍ ዳታ (big data) የዚህ አብዮት ፍሬዎች ናቸው።
ግዙፍ ዳታ ከበይነ መረብ፣ ከተለያዩ ማህበራዊ መገናኛዎች፣ ሴንሰሮች ወዘተ… የሚገኙ ያልተዋቀሩ እና በከፊል-የተደራጁ ዳታዎች ግዙፍ ስብስብ ነው። እነዚህ ዳታዎች የፔታባይት ወይም የኤክሳባይት ማካማቻ የሚያስፈልጋቸው በመሆኑ ለመደበኛ ዳታቤዝ ይበዛሉ። ግዙፍ ዳታን ከመደበኛ ዳታ ጋር ስናነጻጽር የግዙፍ ዳታ መጠን ከፔታባይት(1015) እስከ ዜታባይት(1021) የሚደርስ ሲሆን የመደበኛ ዳታ መጠን ከጊጋባይት(109) እስከ ቴራባይት(1012) ነው። በሌላ ንፅፅር ግዙፍ ዳታ ያልተደራጁ የታጨቁበት ሲሆን መደበኛ ዳታ ከዚህ በተራኒ ተደራጅተው ተቀመጡበት ነው።
ግዙፍ ዳታ የሚገለጽባቸው አራት ባህሪያት አሉት። እነሱም መጠን(volume)፣ አይነት(variety)፣ ፍጥነት(velocity) እና ትክክለኛነት(veracity) ናቸው። አንድ ዳታ ግዙፍ ዳታ ለመባል ከፍ ያለ መጠን ያላቸው (ከፔታባይት እስከ ዜታባይት)፣ አይነታቸው የተለያየ (ምስሎች፣ ጽሁፎች፣ ተንቀሳቀሽ ምስሎች..)፣ በተለያየ ፍጥነት የገቡ እና ትክክለኛነታቸው የተረጋገጠ ዳታዎች ስብስብ መሆን ይኖርበታል።
ይህ ግዙፍ ዳታ የሚሰበሰበው ከሴንሰሮች፣ መተግበሪያዎች፣ ከሶፍትዌር ኤጀንቶች፣ ከግለሰቦች እና ከድርጅቶች ሊሆን ይችላል። ይህን የተሰበሰበ ግዙፍ ዳታ ጥቅም ላይ ለማዋል ወይም ትርጉም እንዲሰጥ ለማድረግ የትንተና(analysis) ስራ መሰራት ይኖርበታል። የግዙፍ ዳታ ትንተና ለመስራት ከሚረዱ ሶፍትዌሮች መካከል ሃዱፕ(Hadoop) አንዱ ነው። ሶፍትዌሩ ከመምጣኔ-ሐብት፣ ፖለቲካ፣ ቢዝነስ እንዲሁም አየር ንብረት ጋራ የተያያዙ ትንበያዎችን ለመስራት ይረዳል። ድርጅቶች እንደ ፌስቡክ እና ትዊተርን ከመሰሉ የማህበራዊ መገናኛዎች ዳታዎችን በመሰብሰብ እና በመተንተን የደንበኞቻቸውን ፍላጎት ለማወቅ ይሞክራሉ። የቀድሞ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማም እ.ኤ.አ በ2012 የፕሬዝዳንትነት ምርጫ የምረጡኝ ቅስቀሳቸውን ሲያደርጉ የግዙፍ ዳታ ትንተናን ድምጽ ለማሰባሰብ ተጠቅመዋል።
ይህ ቴክኖሎጂ ወደ ሀገራችን ገና እየገባ ያለ ከመሆኑ አንጻር በድርጅቶችም ሆነ በግለሰቦች ደረጃ ጥቅም ላይ ሲውል ማየት አልተለመደም። ሆኖም እንደ የቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት ያሉ ተቋማት ቴክኖሎጂውን የማላመድ እና ወደ ስራ የማስገባት ስራ እየሰሩ ይገኛሉ፡፡
ምንጭ፡ The Conversation እና Enterprise Big Data Framework
ውድ ተከታታዮቻችን የዩትዩብ ቻናላችንን ከታች በተቀመጠው ሊንክ አማካኝነት በመቀላቀል አስተማሪ ምስሎችን በየጊዜው ያግኙ=> https://www.youtube.com/channel/
UC6jvUOLRSkVEQtc5Annfwvg
ቻይና ቴክኖሎጂን በመጠቀም ፒጃማ ለብሰው አደባባይ የሚወጡ ሰዎችን አሸማቀቀች
**
የቤት ውስጥ ልብስ (ፒጃማ) ቤት ውስጥ በምንሆንበት ሰዓት ምቾት የሚሰጠን ነገር ነው፡፡ ሆኖም ግን አንዳንድ ሰዎች ህዝብ በሚሰበሰብበት/አደባባይ ፒጃማ ለብሰው ሲወጡ ይስተዋላሉ፡፡ ይህንን ድርጊት የቻይና ከተማ የሆነችው የሱዡዋን ከተማ አስተዳደር ከህዝብ የወጣ/ከባህል ውጭ አንዳንዴም የስልጣኔ ጉድለት ሲሉ ይገልፁታል።
ይህን ህዝባዊ ያልሆነ ባህሪ ምንነት ኒዩ ወርክ ታይምስ ሲተረጉመው ሰዎች በህሊናቢስነት ከማህበረሰቡ የተለየ ባህሪ ሲያሳዩ ወይም ድርጊት ሲፈፅሙ ማለት ነው ብሎታል፡፡ አያይዞም ፒጃማ ለብሶ አደባባይ መውጣትን ብዙ ሰዎች እንደቀላልና ትኩረት የሚፈልግ ትልቅ ጉዳይ ሊሆን እንደማይገባው የተናገሩ ሲሆን አደባባዮች የሁሉም እንደመሆናቸው መጠን የህዝብ ክትትል የሌለባቸውና ከተፅዕኖ ነፃ የሆኑ ሊሆኑ እንደሚገባ እንደሚያምኑ ዘግቧል፡፡
ያም ሆነ ይህ የሱዡዋን ከተማ ማኔጅመንት ቢሮ ነዋሪዎቹ መሰል አለባበስን ተቀባይነት የሌለው ነው በማለት ፒጃማ በመልበስ ወደ አደባባይ የሚወጡ ነዋሪዎች እንዲሸማቀቁ ለማድረግና ድርጊቱን ለመቀነስ በሚል ሰኞ ዕለት የሰባት ሰዎችን ፎቶ ከነአለባበሳቸው እና ማንነታቸው በማህበራዊ ሚዲያ (ዊ-ቻት) ላይ በመልቅቀ እስከ ማክሰኞ ድረስ እንዳቆየው የቻይና ዘ-ፔፐር አሳታሚ ዘግቧል፡፡
ከዚህ ጋር በተያያዘ ኒው ዮርክ ታይምስ እንደገለፀው የሰዎቹ ፎቶ የሚወሰደው የሲሲቲቪ ካሜራዎችን በመጠቀም ሲሆን የተወሰደውን ፎቶ የፊት ገፅታ በመለየት ስማቸውን ጨምሮ ማንነታቸውን የሚለይ እንደሆነ ዘግቧል፡፡
ምንጭ: cnet
ጭንቀት ጸጉር መሸበት ላይ አስተዋፅኦ እንዳለው በጥናት ተረጋገጠ፡፡
ለረጅም ጊዜ የጸጉር ሽበት ከጭንቀት ጋር ተያያዥነት እንዳለው ይገመት ነበር፡፡ የሃርቫርድ ዩኒቨርስቲ (Harvard University) ተመራማሪዎች ይህ ሁኔታ እንዴት እንደሚፈጠር ሳይንሳዊ የሆነ ትንታኔ ለመስጠት ተዘጋጅተዋል፡፡
ጭንቀት ሰውነታችን በማምለጥ ወይም መጋፈጥ (Fight or Flight) ምላሽ የሚሰጠውን የነርቫችን ክፍል ስራውን እንዲጀምር ያደርጋል፡፡ ይህ ደግሞ በሰውነታችን ጸጉር የሚበቅልበት ክፍል ላይ የሚገኙ ሴሎችን(Cells) በማይመለስ መልኩ ለጉዳት ያጋልጣል፡፡
ተመራማሪዎቹ የዚህን ጉዳይ ትክክለኛነት ለማረጋገጥ ጥናታቸውን የጀመሩት የጭንቀት እና የጸጉር ሴሎች ምን አይነት ትስስር እንዳለቸው ለማወቅ በመሞከር ነበር ሆኖም ትስስሩን ማግኘት እንደሚታሰበው ቀላል አልነበረም፡፡ ይህም ጭንቀት የሁሉም የሰውነታችን ክፍል ላይ የሚያመጣው ችግር ስለሚኖር የትኛው የሰውነት ክፍልና የትኛው ሴል ከጸጉር መሸበት ጋር እንደሚያያዝ ለማወቅ የሰፋ ጥናት ጠይቋል፡፡
ይህንንም ችግር ለማወቅ ሳይንሳዊ ዘዴዎችን በመጠቀም የተለያዩ ሰውነታቸን ውስጥ የሚካሄዱ ሂደቶችን አጥንተዋል፡፡ አጥጋቢ የሆነውንም ውጤት ያገኙት በጸጉራችን ያሉ ጉበኖች(Follicles) ላይ ሲሆን በዚህ ውስጥ ያሉ ስቴም ሴሎች በውስጣቸው የጸጉር ቀለም ለውጥ ሊያስከትሉ የሚችሉ ፒግመንት (Pigments) ሴሎችን ይይዛሉ፡፡
ስለዚህም ከነርቮቻችን የሚለቀቁ ኬሚካሎች(Chemicals) በስቴም ሴል(Stem Cells) ውስጥ ያሉትን ፒግመንቶች(Pigments) ከመጠን በላይ እንዲመነጩ በማድረግ የስቴም ሴሎች (Stem Cells) እጥረት እንዲከሰት ያደርጋል፡፡ ይህ ደግሞ ሴሎቹ ራሳቸውን የሚተኩበትን አቅም ስለሚያሳጣ መመለስ በማይችሉበት መልኩ የጸጉር ቀለምን የሚያመነጩት ስቴም ሴሎች አቅማቸው እንዲዳከም ምክንያት ይሆናል፡፡
ስለዚህም በተፈጥሮና በተለምዶ ለመኖራችን አስፈላጊ ተብሎ የሚነገረው የሰውነታችን ማምለጥ ወይም መጋፈጥ ምላሽ የሚያመነጫቸው ሆርሞኖች ስቴም ሴሎች ላይ የሚያመጡት ዘላቂ የሆነ ጉዳት የጸጉር ቀለማችን ያለጊዜው እንዲቀይርና እንዲሸብት ዋነኛ ምክንያት እንደሆነ ታይቷል፡፡
ጭንቀትን ከጸጉር መሸበት ጋር ለማያያዝ ተመራማሪዎቹ ከሙሉ የሰውነት ለውጦች ተነስተው ወደ ግለሰብ የሰውነት አካላት፣ ሴሎችና የተለያዩ ሂደቶችን በማጥናት በመጨረሻ የሚያገናኛቸውን ቦታ ማግኘት ችለዋል፡፡ ይህንንም የጥናት መንገድ ጭንቀት ሌሎች የሰውነት ክፍሎች ላይ የሚያመጣውን ለውጦች ለማጥናት እንደሚጠቀሙበት ይናገራሉ፡፡
science daily
5ኛው የሚጥል ህመም ሳምንት በኢትዮጵያ
*****************************************
**********************
በህክምና ስሙ ኢፕለፕሲ በአገራችን ደግሞ በተለምዶ የሚጥል በሽታ እየተሰኘ የሚጠራው ይህ በሽታ በአገራችን ሊሰጠው የሚገባውን ያህል ትኩረት ያላገኘ በሽታ ነው፡፡ ይህንን በተመለከተ የተደረገው የአገራችን ጥናት እንደሚያመለክተው ከ1.5 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ የበሽታው ተጠቂ ያሉ ሲሆን ከነሱ ውስጥ የህክምና እርዳታ እያገኙ ያሉት 5 በመቶ የሚሆኑት ብቻ ናቸው፡፡
እንደ ባለሞያዎች ገለፃ ይህም የሆነበት ምክኒያት ማህበረሰቡ ስለበሽታው ባለው የተሳሳተ አመለካከት እና አናሳ ግንዛቤ ነው፡፡ ከዛም በተጨማሪ በአገራችን በህመሙ ዙሪያ ባለው ልማዳዊ አመለካከት የተነሳ ህመሙ ያለባቸው ሰዎች የሚገለሉ እና አድሎ የሚደርስባቸው እንዲሆኑ አድርጓቸዋል፡፡
ኢፒለፕሲ በማዕከላዊ የነርቭ ሲስተም ( central nervous system) መዛባት ምክኒያ የሚከሰት ኒውሮሎጂካል በሽታ ነው፡፡ በሽታው የመጣል፣ የማፈራገጥ፣ ያልተለመዱ በሃሪዎችን የማሳየት እና እራስን የማሳት ጠባይ እንዳለው ባለሞያዎች ይናገራሉ፡፡
ኢፕለፕሲ ፆታ እና ዘር የማይለይ በሽታ ነው፡፡ የበሽታው ምልክቶች እንደየሁኔታው እና እንደየሰው ሊለያይ የሚችል ሲሆን አንዳንዱ ሰው ሲጥለው ለተወሰነ ጊዜ ምንም ዓይነት እንቅስቃሴ ሳያሳይ እራን ሊስት የሚችል ሲሆን አንዳንድ ሰው ላይ ደግሞ እጅና እና እግርን የማፈራገጥ ባህሪ ያሳያል፡፡
አንድ ሰው አንድ ግዜ ስለወደቀ እና እራሱን ስለሳተ በሽታው አለበት ተብሎ የሚጠረጠር ባይንም ከአንድ ጊዜ በላይ ምክኒያቱ ባልታወቀ መልኩ እራሱን ከሳተ ግን ወደ ህክምና መስጫ ተቋም ሂዶ ምርመራ እንዲያደርግ ባለሞያዎች ይመክራሉ፡፡
በሽታው በህክምና እርዳታ የሚድን ሲሆን የህክምናው ሁኔታ እንደ በሽታው ዓይነት እና ጥልቀት የሚለያይ መሆኑን ባለሞያዎች ያስረዳሉ፡፡ አብዘኃኛውን ግዜ በሽታውን በመድሃኒት ብቻ መቆጣጠር የሚቻል ሲሆን አንዳንድ ጊዜ ቀዶ ጥገና የሚያስፈልግበት ሁኔታ ይኖራል፡፡ በሽታው አንዳንድ ሰው ላይ የዕድሜ ልክ ሁኖ የሚቀጥል ሲሆን አንዳንድ ሰዎች ላይ ደግሞ ከእድሜ ጋር አብሮ የሚጠፋ ይሆናል፡፡
ኬርኤፕለፕሲ ኢትዮጵያ የሚጥል ህመም በአገራችን እያደረሰ ያለውን የማህበራዊ እና የኢኮኖሚያዊ ችግር ጥልቀት በመመልከት በህመሙ የሚሰቃዩ ኢትዮጵያውያንን የጤና ሁኔታ ለማሻሻል የህክምና እድሎችን የማመቻቸት ፣ስለህመሙ በህብረተሰቡ ውስጥ ያለውን የተሳሳተ አመለካከት ለማስተካከል እና በሽታው እንይከሰት ቀድሞ የመከላከል ግንዛቤን ለመፍጠር በሚል በጎ ዓለማ በ2008 ዓ.ም በወርሀ ጥቅምት ተመሰረተ፡፡
ይህ ተቋም ከዚህ በፊት ለ4ጊዜ ብሄራዊ የሚጥል ሀመም ሳምንት የተሰኘ ለአንድ ሳምንት የሚቆይ ታላቅ የግንዛቤ ማስጨበጫ ፕሮግራሞችን ያዘጋጀ ሲሆን እነሆ ዘንድሮም ለ5ኛ ጊዚ ብሄራዊ የሚጥል ህመም ሳምንት ከየካቲት 2/2012- የካቲት 8/2012 ድረስ የሚቆይ እና የተለያዩ መንግስታዊ እና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማትን ያሳተፈ የመድረክ ውይይት እና የእግር ጉዞ ፕሮግራም አዘጋጅቶ ለመላው ኢትዮጵያዊ እና ከጉዳዩ ጋር ቀጥተኛም ሆነ ቀጥተኛ ያልሆነ ትስስር ያላቸውን አካላት ጋብዟል፡፡
ፕሮግራሙ የተለያዩ ውይይቶችን፣ጉብኝቶችን እና ስልጠናዎችን ያካተተ ሲሆን በስተመጨረሻም የካቲት 8/2012 በእግር ጉዞ ይጠናቀቃል፡፡የእግር ጉዞው መነሻ የሚሆነው ከ6ኪሎ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ዋናው በር መግቢያ አካባቢ ሲሆን በ4ኪሎ አደባባይ ተደርጎ መልሶ መድረሻው እዛው 6ኪሎ እንደሚሆን አስታውቃዋል፡፡
እርሶም ተጋብዘዋል እንዳይቀሩ!
በቅርብ ቀን
=======
ሳምንታዊው የቴክ-ሳይንስ ፕሮግራም ዳግም ወደ ቴሌቪዥን መስኮትዎ ሊመለስ ነው፡፡ የብላቴናት፣ የቴክ ታሪክ፣ ሳይንስና ቴክኖሎጂ እንዲሁም ግለ ታሪክ መሰናዶዎቻችን ከዜናና ጥቆማዎች አዋደን በቅርቡ ከእርስዎ ዘንድ ለማድረስ ዝግጅታችንን በማጠናቀቅ ላይ ነን፡፡ እርሰዎ ጣቢያውን ወደ MOE ቴሌቪዥን ያዙሩት ሰፊውን የሳይን ዓለም እኛ እናስቃኝዎታለን፡፡
ከ427 በላይ ቻይናውያን ያለቁበት የኮሮና ቫይረስ እጅግ አሳሳቢ ሆኗል
**************
የብዙ ቻይናውይን ህይወት በመቅጠፍ ላይ የሚገኘው የኮሮና ቫይረስ ዛሬ ደግሞ ኤዢያ ታይምስ ይዞት በወጣው መረጃ መሰረት የሟቾች ቁጥር ከ427 በላይ መሻገሩ ተነግሯል፡፡ ከችግሩ አሳሳቢነት አንፃር ብዙ ጎረቤት ሃገሮች ከቻይና ጋር የሚያዋስናቸውን ድንበር ለመዝጋት የተገደዱ ሲሆን፤ ሌሎች ሃገራትም ወደቻይና የሚደረጉ ማንኛውም በረራዎችን ለማቆም እንደተገደዱ ተገልጿል፡፡
በሃገረ ቻይና እንዲሁ ቫይረሱ ለመጀመሪያ ጊዜ በተስፋፋባቸው ግዛቶች ምንም አይነት የመግባትና የመውጣት አንቅስቃሴ እንዳይደረግ ቢታገድም የስርጭቱ መጠን ከሚታሰበው ባላይ አሳሳቢ አየሆነ እንደመጣ ለማወቅ ተችሏል፡፡ በተለይም ቫይረሱ በሁቤይ ግዛት ከምተገኘው ዉሃን ከተባለቸው ከተማ ለመጀመሪያ ጊዜ ከተነሳ በኋላ አሁን ላይ 20,661 የሚሆኑ ቻይናውያን ቫይረሱ እንዳለባቸው መታወቁ እና በአለም አቀፍ ደረጃም በ24 ሃገራት ውስጥ መስፋፋቱ አደጋው ከፍተኛ አንዲሆን አስችሏል፡፡
ቫይረሱ በሃገራቸው በሚኖሩ ዜጎች ላይ መታያቱን ያረጋገጡት የጂ 7 ሃገራትም (ካናዳ፣ ፈረንሳይ፣ ጀርመን፣ ጣልያን፣ ጃፓን፣ እንግሊዝ እና አሜሪካ) በችግሩ ላይ በትብብር በመስራት ምላሽ ለመስጠት መዘጋጀታቸውን የጀርመን የጤና ሚኒስቴር ጄንስ ፋህን በትላንትናው ዕለት ተናግረዋል፡፡
የኮሮና ቫይረስ አስካሁን ድረስ ምንም አይነት ፈዋሽ መድኃኒት ወይም ክትባት ያልተገኘለት ሲሆን በዋናነት የመተንፈሻ አካላትን በማጥቃት ሰዎችን በአጭር ጊዜ ውስጥ ለሞት የሚዳርግ በሽታ ነው፡፡ የኮሮና ቫይረስ እንደአውሮፓውያኑ በ2003 በቻይና ከተከሰተው “ሳርስ” በሽታ ጋር የመተንፈሻ አካልን በማጥቃት በኩል ተመሳሳይ ቢመስልም፤ የስርጭት መጠኑ እና የሚያደርሰው ጉዳት ግን እጅግ ከፍተኛ መሆኑ የሚለየው ጉዳይ ነው፡፡
Asia Times
ቨርቹዋል ሪያሊቲ ሰዎችን የመታደግ ስራውን ቀጥሏል
****************
ምናባዊ ምስለ-እውነታ ወይም ቨርቹዋል ሪያሊቲ ያለ ምንም ጭስ፣ ያለ ምንም ውሀ እንዲሁም ያለ ምንም ብክነትና ቆሻሻ በውስጡ በያዛቸው አስደናቂ ቴክኖሎጂዎች በመታገዝ ብቻ የእሳት አደጋ ሰራተኞችን ማሰልጠን ስለመቻሉ እየተነገረ ይገኛል፡፡ የቨርቹዋል ሪያሊቲ የእሳት አደጋ ሰራተኞች በስልጠና ወቅት በብዛት ተጋላጭ የሚሆኑበትን አደገኛ ሁኔታዎችን አስመስሎ በመፍጠር የእሳት አደጋ መከላከል አገልግሎት ስልጠናን ማዘመን እንዳስቻለ ተገልጿል፡፡
እንደሚታወቀው አውስትራሊያ ባለፉት አስርት አመታት ውስጥ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ በአስከፊ እሳት አደጋ መጎዳቷ የሚታወስ ሲሆን፤ በአደጋውም ከ2.3 ሚሊዮን ሄክታር በላይ በቃጠሎ እንደወደመ እና ወደ ግማሽ ቢሊዮች የሚጠጉ እንስሳት ላይም ጉዳት እንደደረሰ የሚታወቅ ነው፡፡ ሳይንቲስቶችም የአየር ንብረት ለውጡን ለጉዳቱ መባባስ በምክንያትነት ያስቀመጡ ሲሆን፤ በካሊፎርኒያም ተመሳሳይ ተፅዕኖዎችን እንደተመለከቱ ገልፀዋል፡፡
ታዲያ እነዚህን የመሰሉ የእሳት አደጋዎች በብዛት እየተፈጠሩ ከመሆናቸው ጋር ተያይዞ የእሳት አደጋ ሰራተኞች ችግሩን ለመቋቋም ወደሚያስችላቸው አዳዲስ ቴክኖሎጂዎች ፊታቸውን እያዞሩ ይገኛሉ፡፡ በተለይም በአውስትራሊያ እና አሜሪካ የሚገኙ አንዳንድ የእሳት አደጋ ዲፓርመንቶች የእሳት አደጋ ባለሙያዎችን ለማሰልጠን የቨርቹዋል ሪያሊቲ (ምናባዊ ምስለ-እውነታ) ቴክኖሎጂን መጠቀም ጀምረዋል፡፡
አውስትራሊያ ላይ መቀመጫውን ያደረገው ፍሌም ሲስተምስ የተባለው ኩባንያ ለእሳት አደጋ ሰራተኞች ይህን የምናባዊ ምስለ-እውነታ ማሰልጠኛ ቴክኖሎጂ ያበለፀገ ሲሆን ሰልጣኞች የጆሮ ማዳመጫና የቪ.አር መነፅር በማድረግ ብቻ በእውኑ አለም ሳይገኙ እንዲሰለጥኑ በማድረግ የእውነተኛ-የህይወት ሁኔታዎች ውስጥ ጠልቀው እንዲገቡ እና ይበልጥ ዝግጁ እንዲሆኑ መደረጉን ተነግሯል፡፡
ቴክኖሎጂው ምናባዊ ጭስ፣ እሳት፣ ውሀ እንዲሁም የእሳት ማጥፊያ ፎም በተለያዩ ሁኔታዎች እንደ ቤት ቃጠሎ፣ የአውሮፕላን ቃጠሎ ወይም የዱር ቃጠሎ ምስለ-መልክ ይፈጥራል፤ ሰልጣኞችም የእያንዳንዱን ሁኔታ የሙቀት መጠን አስመስሎ የሚፈጥር ሙቀትን የሚያመነጭ ልብስ እንዲለብሱ በማድረግ እንዲሁም የእሳቱን ቅርበት እና አቅጣጫ በመወሰን ግለሰቡ ላይ በምን ያህል መጠን ተፅዕኖ እንደሚኖረው በሚወስን ሶፍትዌር ቁጥጥር ይደረግበታል፡፡
የቨርቹዋል ሪያሊቲ ቴክኖሎጂን በእሳት አደጋ ስልጠና ላይ መጠቀም አካባቢያዊ ተፅዕኖዎችን የሚቀንስ ሲሆን ከዚህ በፊት የተለመደው የስልጠና አሰጣጥ ከሚቃጠሉ ንጥረ ነገሮች ጭስንና ሌሎች በካዮችን ወደ አየር እንዲለቀቁ የሚያደርግ፣ ለስልጠናው ሲባል ብቻ መጠኑ ብዙ የሆነ ውሀን የሚጠይቅና ይህም በብዛት ድርቅ ለሚያጠቃቸው አካባቢዎች በራሱ ችግር የሚፈጥረውን ሁኔታ እንደሚያስቀር ታምኖበታል፡፡ እንዲሁም በስልጠና ወቅት የሚጠቀሙት የእሳት ማጥፊያ ኬሚካል ፎምም በእሳት አደጋ ሰራተኞች ላይ የጎንዮሽ የጤና ጉዳት ከማስከተሉ ባሻገር የኬሚካሉ ፍሳሽ ለአፈርና ውሀ መበከል አይነተኛ አስተዋፅዖ ከማድረጉ አንፃር፤ አዲሱ የቨርቹዋል ሪያሊቲ ቴክኖሎጂ አየርን የሚበክሉትን እነዚህን ኬሚካል ፎሞች እና ጭስን መጠቀም ሳያስፈልገው፣ ውሀንም መጠቀም ሳይጠይቅ ለእሳት አደጋ ሰራተኞች በተሻለ ሁኔታ ስልጠና እንዲያገኙ ማስቻሉ በዘገባው ተገልጿል፡፡
ምንጭ፡ ሲ.ኤን.ኤን
ከተወለደ 30 ሰዓት ብቻ የሆነው ህፃን በኮሮና ቫይረስ ተጠቅቷል
#########################
በቻይና አዲስ የተወለደ ህፃን ባልታሰበ ሁኔታ የቫይረሱ ተጠቂ መሆኑ እያነጋገረ ይገኛል፡፡ በየካቲት ሁለት ቫይረሱ በተስፋፋበት ዉሃን ከተማ ወስጥ በሚገኝ በአንድ ሆስፒታል የተወለደው ይህ ህፃን በ30 ሰዓቱ በቫይረሱ መጠቃቱ እጅግ ድንጋጤን እንደፈጠረ ተነግሯል፡፡ የህፃኑ እናት ልጇን ከመውለዷ በፊት በተደረገላት ምርመራ ምንም እንኳን ቫይረሱ እንዳለባት የተረጋገጠ ቢሆንም የተወለደው ህፃን ግን በምን መልኩ ቫይረሱ ሊተላለፍበት እንደቻለ አለመታወቁን የሆስፒታሉ አዋላጆች ተናግረዋል፡፡
የሃገሪቱ የዜና አውታር ዢንዋ እንደዘገበው ህፃኑ በሚወለድበት ጊዜ ምንም አይነት ችግር እንዳልነበረ ጠቅሶ በሰዓታት ልዩነት ውሰጥ ግን በቫይረሱ እንዴት ሊጠቃ እንደቻለ ግልፅ አለመሆኑን በትላንትናው ዕለት ይፋ አድረጓል፡፡ የተወለደው ህፃን አሁን ላይ በመልካም ጤንነት ላይ እንደሚገኝ የዘገበው ዢንዋ እሰካሁን ቫይረሱ ካለባቸው ውስን ህጻናት ውስጥም በእድሜ ትንሹ እንደሆነ ገልጿል፡፡
ውሃን በሚገኘው የህፃናት ሆስፒታል ያሉት ሃኪሞች ቫይረሱ ከእናት ወደ ልጅ የተላለፈበትን ምክንያት በግልፅ ለማወቅ ቢቸገሩም ምናልባት ገና በማህፀን እያለ ቫይሩሱ ተላልፎበት ይሆናል የሚል ግምት አላቸው፡፡ ይሁንና ሌሎች የጤና ባለሙያዎች ህፃኑ ከተወለደ በኋላ ከእናቱ ጋር በሚኖር የቅርብ ንክኪ በቫይረሱ ሳይያዝ እንዳልቀረ ግምታቸውን አስቀምጠዋል፡፡ በተለይም ዜንግ ሊንግሆንክ የተባሉት ሃኪም እንደገለፁት ይህ ሁኔታ የኮሮና ቫይረስ ከእናት ወደ ልጅ በከፍተኛ ሁኔታ የመተላለፍ እድል እንዳለው ተረድተን ተገቢውን ጥንቃቄ እንድንወስድ የጠቆመን ነው ብለዋል፡፡
የኮሮና ቫይረስ አሁን ላይ ከ49 እስከ 50 ባሉት የእድሜ ክልሎች ላይ በስፋት ቢስተዋልም አልፎ አልፎ ግን ህፃናት ላይ የመታየት እድል እንዳለው ተጠቁሟል፡፡ ቫይረሱ አሁን ባለው ዘገባ የስርጭት መጠኑ ጨምሮ 28 የሚጠጉ ሰዎችን የያዘ ሲሆን በጠቅላለውም 560 የሚሆኑት ደግሞ ህይወታቸውን ያጡ ሆነዋል፡፡
ቢቢሲ
ባዮሜትሪክስ ቴክኖሎጂ ምንድን ነው?
*************************
ባዮሜትሪክስ የሚለው ቃሉ ቀጥታ ከግሪክ የተወሰደ ሲሆን “ባዮ” ማለት ህይወት፣ “ሜትሪክስ” ደግሞ መለካት ወይም ልኬት ማለት ነው። ሁለቱ ቃላት በአንድነት ሲነበቡ ደግሞ የህይወት መለኪያ/ልኬት የሚለውን ትርጉም ይሰጣሉ። ባዮሜትሪክስ የአንድን ነገር ተፈጥሯዊ ባህሪ ማለትም የዲ ኤን ኤ አደራደር፣ የዓይን ቀለምና ምጣኔ፣ የእጅ አሻራ፣ የድምፅ ሞገድ፣ የልብና ነርቭ መንገድ እንቅስቃሴ የሚያጠና የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ነው። ወይም ደግሞ ባዮሜትሪክስ የአንድን ሰው ማንነት በግልጥ በሰውነት ገፅታው ወይም በውስጣዊ ሥነ ህይወታዊ ባህሪው መረጃ ላይ በመመስረት ስለ ሰውየው አጠቃላይ ሁኔታ ማውራት የሚያስችል የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ነው። እነዚህ ባህሪያት በቀላሉ የማይረሱ፤ የማይጋሩና የማይሰረቁ መሆናቸው ልዩ የሚያደርገው ጉዳይ ነው፡፡
የባዮሜትሪክስ ቴክኖሎጂ በጥንት ጊዜ ከክስቶስ ልደት በፊት ከ500BC ጀምሮ የባቢሎናውያን የንግድ ልውውጦች የጣት አሻራዎችን ሸክላ ላይ በማስቀመጥ ይጠቀሙ የነበረ ቢሆንም በትክክል በዘማናዊ ቴክኖሎጂ መልክ ይዞ ግን በስፋትና በረቀቀ መልኩ አገልግሎት መስጠት የተጀመረው እኤአ ከ1981 በኋላ ስለመሆኑ ይነገራል፡፡ በዚህም መሰረት ባዮሜትሪክስ ቴክኖሎጂ አሁን ካለንበት የቴክኖሎጂ ጣሪያ ላይ ደርሶ የረቀቁ ወንጀሎች ሲፈፀሙ የሰዎችን ማንነት ለማወቅ የሚጠቅም የአሻራ ቴክኖሎጂ በመሆን በስፋት አገልግሎት ላይ እየዋለ ይገኛል፡፡
በአሁኑ ጊዜ ባዮሜትሪክስ ትልቅ ፋይዳ ያለው የቴክኖሎጂ ውጤት ሲሆን፤ አስፈላጊነቱም ከጊዜ ወደ ጊዜ በከፍተኛ ደረጃ እየጨመረ የመጣውን የዓለም የደህንነት ጥያቄ በመመለስ ከፍተኛ አስተዋፅኦ እያበረከተ ይገኛል። በተለይም በትምህርት ተቋማት፣ ህክምና ተቋማት፣ በታላላቅ ኢንዱስትሪዎች፣ መንግስታዊ በሆኑና ባልሆኑ ድርጅቶች፣ በደህንነት ተቋማት እና በሌሎችም ተቋማት ውስጥ ከፍተኛ ሚና በመጫወት ላይ ይገኛል።
የባዮሜትሪክ ቴክኖሎጂዎች መገለጫዎች
* ዩኒቨርሳሊቲ፡ በአለም ላይ ያለ እያንዳንዱ ሰው የራሱ የሆነ ልዩ ባህሪ ሊኖረው ይገባል
* ልዩነት፡ በአጠቃላይ ሁለት ሰዎች አንድ ዓይነት ባሕርይ የላቸውም ፡፡ ሆኖም ተመሳሳይ የሆኑ መንትዮች ለመለየት ከባድ ናቸው ፡፡
* ዘላቂነት፡ የሰዎች የባዮሜትሪክስ ባህሪ ከጊዜ ጋር ልዩነት ሊኖራቸው አይገባም ለምሳሌ ፣ የአንድ ሰው ፊት ከእድሜ ጋር ሊለወጥ ቢችልም በቴክኖሎጂው የመለየት እድሉ ሰፊ ነው።
* ተቀባይነት፡ በሁሉም አለማት ላይ ተመሳሳይ መሆኑና ሁሉም የተቀበሉት መሆኑ
* አስቸጋሪነት፡ ይህም ማለት ሰዎች ለመሸወድ ወይም ለማጭበርብር የማይሞክሩት መሆኑ
ባዮሜትሪክ ቴክኖሎጂ ከሚሰጣቸው አገልግሎቶች መካከል፡-
1. የጣት አሻራ ቴክኖሎጂ
2. የፊት ገፅታን የሚለይ ቴክኖሎጂ
3. የአይን እይታ ቴክኖሎጂ
4. የድምፅ ቴክኖሎጂ የሚሉት ከብዙዎች መካከል ጥቂቶች ናቸው፡፡
የባዮሜትሪክስ ጠቀሜታ
* የወንጀል ድርጊት ከመፈፀሙ በፊትና ከተፈፀመ በኋላ የሰዎችን ማንነት ለመለየት የሚያገለግል ቴክኖሎጂ ሲሆን ለምሳሌ አንድ ሰው የተለያዩ አለማትን በሚዞርበት ወይም በሚጎበኝበት ወቅት በሚዳረስባቸው ቦታዎች በሚገኙ የኢሚግሬሽን ጣቢያዎች ላይ የጣት አሻራ እንዲሰጥ ይጠየቃል ይህም በሀገር እና ግለሰብ ላይ የሚደርሱ ጉዳቶችን ወይም የወንጀል ድርጊቶችን ለመቆጣጠር ያስችላል፡፡
* በበርካታ የመንግስትና የግል ድርጅቶች፣ ባንኮች እና የገንዘብ ተቋማት እንደ ሰዓት መቆጣጠሪያ ይጠቅማል
* የባዮሜትሪክ ሥርዓቶች ሰዎችን በፍጥነት፣ በቋሚነት እና በአስተማማኝ ሁኔታ በመለየት ከፍተኛ ጥቅም ይሰጣሉ
ምንጭ፡ biometricupdate.com እና Si Tech Bufe
ስኪዞፍሬኒያ (Schizophrenia)
***************
ስኪዞፍሬኒያ ከሁለት የግሪክ ቃላት ጥምረት የተገኘ ቃል ሲኾን በደምሳሳው “የተበታተነ አእምሮ” የሚል ትርጉምን የያዘ ነው፡፡ ብዙ ሰዎች ይህን በሽታ በቅጡ አይረዱትም፡፡ ስኪዞፎርኒያ “እብደት” ነው ብለው የሚያስቡ ሰዎች አሉ፡፡ ይህ ስህተት ነው፡፡ ስኮዞፎርኒያ በቤተሰብ እንክብካቤ ማጣት የሚመጣ ደዌ ነው ብለው የሚያስቡ ሰዎች አሉ፤ ይህም ትክክል አይደለም፡፡
በሽታው በአንድ ሰው ሰነፍ ኾኖ መገኘት ወይም ደግሞ ስኬታማ ባለመኾኑ ምክንያት የሚመጣም አይደለም፡፡ ስኪዞፍሬኒያ አእምሮ በሚፈጥራቸው ባዕድ ምስሎች የመሰቃየት በሽታ ነው፡፡ ከፍ ሲልም በአእምሮ አስተካክሎ የማሰብ ችሎታ ባለመኖሩ ከውጭው ዓለም ጋር መግባባት መቸገር ማለት ነው፡፡
በሽታው በዓለም አቀፍ ደረጃ ሥር የሰደደ ሲሆን በተለይ በታዳጊ አገሮች በስፋት የሚስተዋል ነው፡፡ የአገራችንን ትተን እንደ ታላቋ ብሪታኒያ ባሉ ያደጉ አገሮች እንኳ ከ100 ሰዎች አንዱ በዚህ በሽታ የተጠቃ ኾኖ እናገኘዋለን፡፡ ይህን ቁጥር ወደኛ ብንመነዝረው ስኪዞፎርኒያ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን እያሰቃየ የሚገኝ በሽታ እንደኾነ መገመት እንችላለን፡፡
ስኪዞፍሬኒያ የብቸኝነት ሕመም ከመሆኑም ባለፈ ከውጭው ዓለም ጋር የመግባባት አቅምን የሚያሳጣ ነው፡፡ በሽታው አስተሳሰባችንን ክፉኛ ስለሚበታትነው እውነታንና እውነት ያልኾነን ነገር የምንለካበትን ሚዛን ያስተናል፡፡ በዚህም የተነሳ ብዙ ሰዎች ስኪዞፍሬኒያ “የመቀወስ” በሽታ ነው ብለው ለመደምደም ይገደዳሉ፡፡ በእርግጥ እስኪዞፎርኒያ የአእምሮ መታወክ አድርገን እንድንመለከተው የሚያደርገን ነገሮችን በጠራ መልኩ ለማየትና ለማገናዘብ መቸገርን ስለሚያስከትል ነው፡፡ ኾኖም በሐኪም እገዛና በቤተሰብ ክትትል በሂደት ማገገም የሚቻልበትና ሙሉ በሙሉ ሊድን የሚችል በሽታ መኾኑን መረዳት ያሻል፡፡
የስኪዞፍሬኒያ ተጠቂዎች ከሚታይባቸው ዋና ዋና ምልክቶች መካካል ሁሉም ሰዎች ሰለኔ እያወሩ ነው ብሎ ማሰብ፣ ራስን መጣል፣ ለነገሮች ምንም ግድ ማጣት፣ ለዓለም ችግሮችና ሰማያዊ ጥያቄዎች ለሁሉም መልስ ለመስጠት መሞከር፣ መንገድ ላይ ሰዎች ይጠቋቆሙብኛል ብሎ መስጋት እና ከቤተሰብና ከጓደኞች መገለል በሽታው የሚያሳያቸው ምልክቶች ናቸው፡፡
የስኪዞፍሬኒያ ምልክቶች ከሰው ሰው የተለያየ ባሕሪ ሊኖራቸው ቢችልም ታካሚው ምን ሁኔታ ላይ ሲኾን የተሻለ ስሜት እንደሚሰማው ለመረዳት መሞከር መልካም ተግባር ነው፡፡ በሽታው ከምንም በላይ የሰዎችን እንክብካቤ ስለሚሻ ከህክምና በተጨማሪ በዚህ ላይ ትኩረት ማድረግ ትልቅ እርዳታ ይኖረዋል፡፡
ምንጭ፡ www.alodokter.com