የሳይንስ ሊቃውንት የዉሀ ፍሰትን መቀነስ የሚያስችል የመፀዳጃ ቤት አንሸራታች የማጣሪያ ሽፋን ፈጠሩ።
*********************
በአሜሪካ የሚገኝ የተመራማሪዎች ቡድን በዓለም ዙሪያ ቆሻሻ ለማስወገድ ሲባል የሚባክንን ከፍተኛ መጠን ያለው ውሃ ለመቆጠብ የሚያግዝ እጅግ በጣም አንሸራታች የመጸዳጃ ቤት ሽፋን እንዳገኙ ገልፀዋል ፡፡ የፔን ስቴት ዩኒቨርሲቲ ተመራማዎች እንደተናገሩት ከሆነ ሽፋኑ ቆሻሻን ለማስወገድ ተብሎ ከሚወጣው ውሃ 90 በመቶውን ለመቀነስ ይረዳል ፡፡
በተጨማሪም ይህ ሽፋን ባክቴሪያ በሽንት ጎድጓዳ ሳህኖች ውስጥ እንዳይሠራ ለመከላከል የሚረዳ ሲሆን ይህም በባክቴሪያ ሳቢያ ሊከሰቱ የሚችሉ በሽታዎችን የማስቀረት አቅም ይኖረዋል ሲሉ ተናግረዋል ፡፡ ሽፋኑ ቴፍሎን(Teflon) ከተባለዉ ታዋቂው ሽፋን የበለጠ አንሸራታች እንደሆነ የሚነገር ሲሆን በተጨማሪም እንደ ቴፍሎን ቶሎ የሚበከል ባለመሆኑ በየ50 ዙር እንድንቀይረው አንገደድም፡፡
በዓለም ላይ በቀን ዉስጥ 141 ቢሊዪን ሊትር ዉሃ የመጸዳጃ ቤት ቆሻሻን ለማስወገድ የሚውል ሲሆን ይህ ግኝት በተገቢው መንገድ ስራ ላይ መዋል ከቻለ የዓለምን ከፍተኛ የሆነ የውሃ ብክነትን ሊያስቀር ይችላል ሲሉ ተመራማሪዎቹ ተስፋቸውን ገልጸዋል፡፡ አክለውም ተመራማሪዎቹ በጽሁፋቸዉ በአለም ላይ በቀን ውስጥ የመጸዳጃን ቤት ቆሻሻን ለማስወገድ የሚውለዉ ንጹህ ዉሃ በ አፍሪካ ካለዉ አጠቃላይ የውሃ ፍጆታ በ6 እጥፍ የበለጠ ነዉ ሲሉ አስነብበዋል፡፡በዩኒቨርሲቲ ውስጥ ተባባሪ ፕሮፌሰር የሆኑት ፕሮፌሰር Tak-Sing Wong ፣ እንደተናገሩት ቡድኑ ባክቴሪያን እና ሌሎች መሰል ተዋሲያን እንዲፀዱ የሚያድርግ ፈሳሽ መሰል ውህድም አበልፀገዋል ፡፡
https://wonderfulengineering.com/scientists-have-created-an-ultra-slippery-coating-for-your-toilet-that-wont-let-poop-stick/

Wonderful Engineering
Scientists Have Created An Ultra-Slippery Coating For Your Toilet That Won't Let Poop Stick
A team of researchers in the US claims that it has developed an ultra-slippery toilet coating that would help with saving huge amounts of water.
TECHIN weekly seminar
===================
You are invited to join us today @TECHINhall in our head office Located behind Lycée Guebre-Mariam School.
Issues for this week:
• Developing prototype cereal crop-land identification using knowledge-based system
• Challenge and opportunities of technology absorption from assembly to manufacturing in Ethiopia. Case on automotive industry.
Presenters:
Tekalign Abdissa and Yohannes Degefu
#TECHINtalk
#TECHIN #weeklyseminar

በምርምር ስራዎች የታጀበው የዛሬው የቴክኢን ሴሚናር
=====================
ዛሬ በተካሄደው የዚህ ሳምንት የሴሚናሩ ቆይታ እንደወትሮው ሁሉ ሁለት ተመራማሪዎች ስራዎቻቸውን ለታዳሚው አቅርበዋል፡፡ በቀዳሚነት ከመድረኩ የቀረበው በአቶ ተካልኝ አብዲሳ አማካኝነት የተሰራውና ኢትዮጵያዊያን አርሶ አደሮችን ለመጥቀም የተሰራው ዲጂታል ስርዓት ነበር፡፡ በሰርቶ ማሳያነት (Prototype) የቀረበው ይህ ስርዓት ገበሬዎች ባሉበት አካባቢ ያለውን የአፈር አይነት በማስገባት ብቻ ዝርዝር መረጃን የሚሰጣቸው ሲሆን ከገበሬዎቹ ምርጫ ጋራ በተወዳጀ መልኩም ምን ቢዘሩ ውጤታማ እንደሚሆኑ የመጠቆም ችሎታ አለው፡፡ ለየት ባለ መልኩም ጤፍ እና ስንዴን ጨምሮ በሀገራችን በስፋት በሚመረቱት የሰብል ምርቶች ዙሪያ መስራቱ በኢትዮጵያ ያለውን የእነዚህን ወሳኝ ምግቦች ምርት ለማሳደግ ድርሻው ከፍ ያለ እንደሚሆን ታምኖበታል፡፡ በቀጣይም ይህን ድርሻውን ይወጣ ዘንድ በስልክ መተግበሪያ መልኩ ለማቅረብ ስራዎች እየተከናወኑ ይገኛል፡፡
የዕለቱ ሁለተኛ ርዕሰ ጉዳይ የነበረው በኢትዮጵያ የአውቶሞቲቭ ማምረቻ ኢንዱስትሪው ላይ የሚታዩትን ተግዳሮቶች የቃኘው የአቶ ዮሐንስ ደገፉ ጥናት ነበረ፡፡ የአውቶሞቲቭ ማምረቻ ዘርፉ እንቅስቃሴ ማድረግ ከጀመረ ቢሰነባብትም ከዕድሜው አኳያ ያለውን አነስተኛ እድገት ያሰስረዱት አቶ ዮሐንስት ችግሮቹንም በዝርዝር ጠቁመዋል፡፡ እንደጥናቱ ከሆነ ከ100 በላይ ተቋማት በተሽከርካሪ ምርት ለመሰማራት ጥያቄ ቢያቀርቡም ከነዚህ ውስጥ ወደመሬት ወርደው ስራ የጀመሩት አምስቱ ብቻ ሲሆኑ እነዚህ ተቋማትም ሙሉ በሙሉ በሚባል መልኩ ከውጪ የሚያስገቧቸውን ግብአቶች ገጣጥሞ ለገበያ ከማቅረብ የዘለለ ተሳትፎ እያደረጉ አይገኙም፡፡ በመጨረሻም ተመራማሪው ለኢንዱስትሪው ዕድገት ይበጃሉ ያላቸውን ምክረ ሀሳቦች ወደ መድረኩ የገፉ ሲሆን ከእነዚህም መካከል የፖሊሲ ማስተካከያዎችን ማድረግ እና በዘርፉ ልምድ ካላቸው የባህር ማዶ ተቋማት እና ባለሙያዎች ጋራ በትብብር መስራት ይገኙበታል፡፡
ከተሳታፊዎች በኩል የተለያዩ ጥያቄዎች በሁለቱም ርዕሰ ጉዳዮች የቀረበ ሲሆን ተመራማሪዎቹም በተነሱት ጥያቄዎች ላይ ማብራሪያዎችን ሰጥተው አልፈዋል፡፡
የቴክኢን ሴሚናር በየሳምንቱ ሐሙስ ከሰዓት የሚደረግ ሲሆን በተመራማሪዎች የተሰሩ የተለያዩ ጥናት እና ምርምሮች የሚቀርቡበት እና ለማንኛውም ሰው ክፍት የሆነ ዝግጅት ነው፡፡

እየተዘጋጀ ባለው ብሄራዊ የልማት አመላካች ፖርታል ላይ ውይይት ተደረገ
***************************************
የቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት ከብሄራዊ ፕላን ኮሚሽን ጋር በትብብር እያከናወኑት በሚገኘው ብሄራዊ የልማት አመላካች ዳሽቦርድ ላይ ውይይት አካሂደዋል፡፡ በጋራ እየተሳተፉበት በሚገኘው በዚህ ፕሮጀክት ለማሳያ በቀረበው ፕላትፎርም ላይ ሰፊ ምክክር የተደረገ ሲሆን፤ በዋናነትም ከቴክኒካል ጉዳዮች አንፃር ፕላትፎርሙ ሊያሟላቸው በሚገቡ ግብዓቶች ላይ እና በቅርፅ ደረጃ ምን ምን ይጨመሩበት በሚሉት ሃሳቦች ላይ ሰፊ ውይይት ተደርጎበታል፡፡
ከዚያ ባለፈ በፈፃሚ አካላት ዙሪያ የተዘጋጁትን ጠቋሚ መረጃዎች በተለይም እንደ (KPI) ያሉ መመዘኛዎችን በተቀናጀ እና በተደራጀ መልኩ በየተቋማቱ ለመተግበር እና ለህዝቡም ግልፅ እና ተደራሽ ለማድርግ ፕላትፎርሙን ከሚያበለፅጉት የቴክኢን ተመራማሪዎች በተጨማሪ ተወካይ አመራሮችም በየጊዜው እርስ በእርስ በመገናኘት ስርዓቱን የማሻሻል እና የማሳደግ ስራ እንደሚሰራም በውይይቱ ተገልጿል፡፡
ይህ ፕሮጀክት የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ስርዓትን መሰረት በማድረግ ወሳኝ የልማት አመላካች መረጃዎችን በተለያዩ የሴክትር አይነቶች በመሰብሰብ፣ በማደራጀት፣ እና በማቅረብ መረጃን በአንድ ማዕከል ለማስተዳደር የሚያስችል ሲሆን፤ በሁሉም ደረጃም የዘመነ የሪፖርት፣ የቁጥጥር፣ የክትትልና የግምገማ ስርዓትን ለመዘርጋትም በእጅጉ የሚያግዝ ነው፡፡
ፕሮጀክቱ በተለይም ተዓማኒና ወጥነት ያለው መረጃን ለአለም አቀፍ ተቋማት በየወቅቱ ተደራሸ የሚሆንበትን ሁኔታ ለመፈጠር የሚያግዝ ከመሆኑም ባለፈ ፖሊሲዎች፣ ስትራቲጅዎች እና ውሳኔዎች ቀልጣፋ እንዲሆኑ ማስቻሉ በሃገር ደረጃ ጠቃሚ የሚያደርገው ጉዳይ ነው፡፡

የቻይና ተመራማሪዎች አዲስ ኤክሶፕላኔት አገኙ
***************
የቻይና ስነ ፈለክ ተመራማሪዎች ከኛው ስርዓት ፀሀይ ውጪ የሆነች አዲስ ኤክሶፕላኔት ማግኘታቸውን ይፋ አድርገዋል። ተመራማሪዎቹ ያገኟት ይህች ፕላኔት “ወንግሹ” የሚል ስያሜ የተሰጣት ሲሆን በምህዋር የምትዞራት ኮከብ ደግሞ “ዢሂ” የሚል ስያሜ አግኝታለች፡፡ እነዚህ ስያሜዎች ቀድመው ከተገኙት ኤክሶፕላኔቶችና ከዋክቦቶቻቸው በተለየ የቻይናን ቀደምት ስያሜዎች ያገኙ ሲሆን አነዚህም የጨረቃ አምላክ ወይም የጸሃይ አምላክ የሚል ትርጉም እንዳላቸው ተነግሯል።
የዢሂ መጠን ከኛዋ ፀሐይ ሁለት እጥፍ የሚበልጥ ሲሆን የወንግሹ መጠን ደግሞ በቻይና ብሔራዊ የሥነ ፈለክ ምርምር ተቋም ብያኔ መሰረት ከስርዓት ጸሃይችን ትልቋ ፕላኔት ጁፒተር በ2.7 እጥፍ እንደምትበልጥ ተነግሯል። ኤክሶፕላኔት ወንግሹ እኛ ካለንበት ምድር 440 ያህል የብርሃን አመት ርቃ የምትገኝ ቢሆንም ተመራማሪዎች ግን እንደ ሃብል ባሉ ግዙፍ የቴሌስኮፕ አይነቶች በግልፅ ልትታይ እንደመትችል አስቀምጠዋል፡፡
እንደሚታወቀው ኤክሶፕላኔቶች ወይም ውጫዊ አለማት ከስርዓተ-ፀሀያችን (solar system) ውጭ ያሉ ፕላኔቶች ሲሆኑ፤ ልክ እንደምናውቃቸው በፀሀያችን (ኮከብ) ዙሪያ እንደሚዞሩት 9ኙ ፕላኔቶች ሁላ ውጫዊ አለማትም በኮከባቸው ዙሪያ የሚዞሩ ናቸው። እስካሁን በተረጋገጠ መልኩ ወደ 2000 የሚጠጉ ውጫዊ ፕላኔቶች የተገኙ ሲሆን፤ የተጣራ መረጃ እስኪገኝ ተብለው የተቀመጡ ሌሎች ብዙ ፕላኔቶችም አሉ። ጋማ ሴፌይ ኤቢ ለመጀመሪያ ግዜ የተገኘችው ውጫዊ ፕላኔት ስትሆን የተገኘችበትም አመት እ.ኤ.አ በ 1998 ነበር። በግዜው በእርግጠኝነት ፕላኔት መሆኑዋ ያጠራጠረ ቢሆንም በ 2003 እንደገና በተደረገ ጥናት ጋማ ሴፌይ የተባለች ኮከብን የምትዞር ውጫዊ ፕላኔት መሆኗ ሊረጋገጥ ችሉዋል።
ተመራማሪዎች በጥቅሉ በትሪሊዮን የሚቆጠሩ ውጫዊ ፕላኔቶች ሊኖሩ እንደሚችሉ ሳይንሳዊ መላምት ያስቀምጣሉ።
ምንጭ፤ www.xinhuanet.com/english/
2019-12/21/c_138648892.htm

english.news.cn
Xinhua – China, World, Business, Sports, Photos and Video | English.news.cn
Xinhuanet is a comprehensive service-oriented news information portal and the most influential online media in China. As the main communication platform of all-media news information products created by Xinhua News Agency, Xinhuanet releases global news information…
በ 10 ሰኮንድ ጥርስን የሚያፀዳው Y-Brush ቴክኖሎጂ መነጋገሪያ ሆኗል
***********************
ባለፈው ዓመት Y-Brush የተባለው አምራች ድርጅት የተለመደውን የጥርስ ብሩሽ በግሩም ቴክኖሎጂ የሚተካ አዲስ ምርት እንደሚያመጣ ቃል ገብቶ ነበር፡፡ ታዲያ ይህ ድርጅት በቃሉ መሰረት ጥርስን በ 10 ሰከንዶች ውስጥ ብቻ ለማፅዳት የሚያስችል አስደናቂ ቴክኖሎጂ ይዞ ብቅ ብሏል፡፡
ቴክኖሎጂው በጥርስ ብሩሽ ምርቶች ዙሪያ እነ Oral-B እና Colgate ያላቀረቡትን አስገራሚ ይዘት እና ውጤታማነት በምርቶቹ ማካተቱ፤ አዲስ አብዮትን የፈጠረለት ሲሆን በማንኛውም የጥርስ ሳሙና በመጠቀምም ከመደበኛው ብሩሽ በበለጠ ምንም አይነት የጎንዮሽ ጉዳት ሳያስከትል መገልገል እንደሚያስችል ተገልጿል፡፡
የጥርስ ብሩሹ በተዘጋጀለት እጅግ አነስተኛ ሞተር አማካኘነት የትራፒዞይድ ቅርፅ ይዞ ያለውን የአፋችንን አምሳያ በከፍተኛ ፍጥነት እየተርገበገበ የሚቦረሽ ሲሆን፤ በአጭር ሰኮንዶች ውስጥም በተመሳሳይ ጊዜ የጥርሳችንን የላይኛውንና የታችኛውን ክፍል በማፅዳት ሃጫ በረዶ እንደሚያስመስል ተነግሮለታል፡፡
ከዚህ በፊት እንደ Oral-B እና Colgate ያሉ አምራች ድርጅት ስማርት ቴክኖሎጂን የተላበሰ የጥርስ መቦረሻ ምርት ለገበያ ሲያቀርቡ ይዘው ከመጡት የምርት ይዘት አንጻር ከ100 እስከ 180 የአሜሪካን ዶላር የሚለጥፉበት ቢሆንም፤ አዲሱ Y-Brush ቴክኖሎጂ ግን ይዞት ከቀረበው አስገራሚ ገፅታ አኳያ የተቆረጠለት 125 ዶላር እጅግ አነስተኛ መሆኑ ተነግሯል፡፡
ቢቢሲ

ትችትን እንዴት እናስተናግድ
*****************
የበላያችን ወይም አለቃችን በስራችን ላይ አሉታዊ ነገር ተናግሮን ይቅርና ፌስቡክ ላይ ፖስት ያደርግነው ፕሮፋይል ፒክቸር እንኳን ሁለት ላይክ ብቻ ሲያገኝ ጥሩ ስሜት አይስማንም፡፡ እንዴት እንዲሂ ሊሆን ይችላል ብለን ረሳችንን በመጠየቅ እንባዝናለን፡፡ ይሁንና በስራችንም ሆነ በግል ህይወታችን ስኬታማ የመሆን ትልቅ ጉጉት ካለን ትችትን በተገቢው ሁኔታ ማስተናገድ እና ሲቀጥልም በፀጋ መቀበል ያስፈልገናል፡፡
ትችት ምንድነው
ትችት ሰዎች ለሆነ ድርጊት ወይም ሁኔታ የሚሰጡት አስተያየት ሲሆን ጥሩ ወይም መጥፎ ሊሆን ይችላል፡፡ ትችት ሁሉም ቦታ አለ፡፡ በቤተሰ፣ በጓደኛ፣ በስራ ቦታ እና በፍቅረኛ ሊሆን ይችላል፡፡ ሰዎች በተለያየ ምክንያት ትችት ሊሰነዝሩ ይችላሉ፡፡ ቤተሠብ ጓደኛ በቀና አስተሳሰብ የተሠማቸውን ለመግለፅ ወይም እንድንሻሻል በማሠብ አለቆች ሠራተኞች የበለጠ እንዲሰሩ ለማድረግ ትችትን ሊሰነዝሩ ይችላሉ፡፡ በተቃራኒው ደግሞ በቅናት፣ በጥላቻ፣ ስህተት ፈላጊ በመሆን እና የተሻሉ እንደሆኑ ለማሣየት ሲባል ትችት ያለቦታው ሊመጣ ይችላል፡፡
ጥሩ ያልሆኑ ትችቶች ሰዎች ለራሣቸው የሚሰጡትን ግምት በመቀነስ የበታችነት ስሜት እንዲሰማቸው ያደርጋሉ፡፡ ጥሩ ያልሆኑ ትችቶች መብሰልስል፣ ጭንቀት፣ ድብርት “ለምን እንደዚህ ተባልኩ?” እያሉ እንቅልፍ ማጣት ሊያስከትሉ ይችላሉ፡፡ ትችትን በመፍራት አቅም እያላቸው መስራት የሚያቆሙም አይጠፉም፡፡ ትችት የማይቀር ነገር በመሆኑ ብዙ መጨነቅ አይገባንም፡፡ የሚሰነዘሩብንን ትችቶች በሚገባ ለማስተናገድ የሚረዱ የተወሰኑ ነጥቦች እናንሳ፤
ማዳመጥ እና በተረጋጋ ሁኔታ መመለስ
ለትችት ምላሽ ከመስጠታችን በፊት ጠቃሚ ነው አይደለም የሚለውን መለየት አለብን፡፡ ጓደኛችን አብረን ከተዝናናን በኃላ ‘’ገንዘብ ታባክናህ’’ ቢለን ሊሠማን ይችላል፡፡ ነገር ግን ያመለከተው ነገር ራሣችንን እንድንለውጥ የሚያግዘን ሊሆን ይችላል፡፡ ምላሽ ለመስጠት ከመፍጠናችን በፊት ማዳመጥና ምን ለማለት እንደሆነ መረዳት ጥሩ ነው፡፡ የተሰጠን ትችት ጠቃሚ ከሆነ በአክብሮት አመስግነን መቀበል፤ አሉታዊ ከሆነም በአክብሮት ምላሽ መስጠት ራሳችንን ለማጠንከር ትክከለኛው መንገድ ነው፡፡
በግል አለመውሰድ
ሰዎች የሚሰጡት ትችት ስለኛ ከሚናገረው ይበልጥ ስለእነሱ እንደሚናገር ማወቅ አለብን፡፡ በተጨማሪም አንድ ድርጊት ላይ ያለን ድክመት ስለማንነታችን እንደማይናገር ማወቅ አስፈላጊ ነው፡፡ ሂሣብ ላይ ቀሽም መሆናችን ቢነገረን ይህ የሚያሳየው ሂሳብ ላይ ቀሽም እንደሆንን እንጂ እኛ ቀሽም እንደሆንን አይደለም፡፡ አንዳንዴ ትችት ደካማ ጎን ላይ በማተኮር ራሣችንን እንድንጠራጠርና ያሉንን ብዙ ብቃቶች እንድንዘነጋ ያረገናል፡፡ በመሆኑም ትችትን በግል አለመውሰድ ለራሣችን ያለንን ግምት እንዳንቀነስ ይረዳናል፡፡
ጠንክሮ መቀጠል
ጠቃሚ ትችትን ተቀብሎ መቀጠል ራሣችንን እንድናሻሽል ይረዳል፡፡ አሉታዊ ትችት የአንድ ሰው አመለካከት ብቻ እንደሆነ መረዳት ያስፈልጋል፡፡ መድረስ ያሰብንበትን አላማ ላይ እንዳንደርስ አሉታዊ ትችቶች እንዲገድቡን መፍቀድ የለብንም፡፡ ትልልቅ ፈጠራ የሰሩ ሰዎች መጀመሪያ ሀሣባቸውን ሲናገሩ “ዋው የሚገርም ትልቅ ሀሣብ ነው” አልተባሉም፡፡ በተቃራኒው “ይህ የማይሆን ነገር ነው፡፡” እና “አትጃጃል ጊዜህን አታጥፋ፡፡” ነው የተባሉት፡፡ ስለዚህም ሼክስፒር እንዳለው የመስታወት ያህል ጥራት የበረዶ ያህል ንጣት ቢኖረንም ሰዎች ከሚሰነዝሩብን ትችት ማምለጥ ስለማንችል፤ የሚያደርሰውን ተፅእኖ መቋቋም እና ራሣችንን ለማሻሻል መጠቀም ትልቁ ነጥብ ነው፡፡
ምንጨ፡ mental wellness

የኤሌክትሪክ ኃይልን ሳይጠቀም ሰውነትን የሚያቀዘቅዘው መሳሪያ
******************
መሃንዲሶች የኤሌክትሪክ ኃይል ሳያስፈልጋቸው በቆዳ ላይ (on-skin) የሚደረጉ የኤሌክትሮኒክስ የግል አየር ማቀዝቀዣዎችን ወይም (air conditioners) ዲዛይን ማድረጋቸውን አስታውቀዋል፡፡
በሚስሪ ዩኒቨርስቲ በሚገኙ መሐንዲሶች የተነደፈው ይህ “ተለባሽ አየር ማስተካከያ” (air conditioning) በተለይ ወታደሮች ይህን በቆዳ ላይ ያለ መሳሪያ በመጠቀም በጦር ሜዳ ሙቀትን ለመቀነስ እና ቅዝቃዜን ለመፈጠር እንደሚገለገሉበት የተናገሩ ሲሆን፤ ከዚያ ባለፈም የሙቀት ስትሮክ (heat stroke) ወይም ከፍተኛ ድካም እንዳይከሰትባቸው ይረዳቸዋል ብለዋል፡፡ መሣሪያው የደም ግፊትን፣ የልብን ኤሌክትሪክ እንቅስቃሴ እና የቆዳ ድርቀትን (skin hydration) ለመቆጣጠር የሚስችሉ በርካታ የጤና አጠባበቅ መተግበሪያዎች እንደተገጠሙለትም ተነግሯል።
በአሁን ጊዜ ጥቅም ላይ ከሚውሉት ተመሳሳይ ምርቶች ወይም ሌሎች ተዛማጅ ጽንሰ-ሀሳቦች በተቃራኒ ይህ መሳሪያ አየር እንዲገባ የሚያስችል እና በውሃ የማይበላሽ ሲሆን፤ በፓሲቭ ኩሊንግ (passive cooling) ሂደት ለሰውነት የግል አየር ማስተካከያ (air conditioning) አገልግሎትን ይሰጣል፡፡ ፓሲቭ ኩሊንግ (passive cooling) እንደ ፋን ወይም ፓምፕ የኤሌክትሪክ ኃይልን የማይጠቀም ስለሆነ ለተጠቃሚው ምቾትን የመስጠት ሁኔታው የተሻለ እንደሆነ መሀንዲሶቹ ይናገራሉ፡፡
በአሁኑ ጊዜ መሣሪያው አነስተኛ ገመድ ያለው ፓች (wired patch) ቢሆንም፤ ለወደፊቱ ግን ተመራማሪዎቹ የገመድ አልባ ሥሪትን ለመንደፍ ከአንድ እስከ ሁለት ዓመት ይወስዳል ብለዋል፡፡ በተጨማሪም አንድ ቀን ይህን ቴክኖሎጂ በስማርት ልብስ ምርቶች ላይ የመተግበር ሃሳብ እንዳላቸውም ጠቅሰዋል፡፡ ይህም በአሁኑ ጊዜ መሳሪያው በተደረገበት ቦታ ብቻ የሚያቀዘቅዘው ውስን የሆነውን ችሎታ በማስቀረት የመሣሪያውን የማቀዝቀዝ አቅም በመላው አካል ላይ ለማድረስ ያስችላል ብለዋል።
ይህ መሳሪያ በሙቀት ወቅት ሰዎች ለመቀዝቀዝ የሚጠቀሙትን የኤሌክትሪክ አጠቃቀምን ለመቀነስ ከመርዳቱም ባለፈ አንገብጋቢ በሆነው የዓለም ሙቀት መጨመር ላይ ትልቅ እገዛ ሊኖረው ይችላል ተብሎ ይታመናል።
ምንጭ፡ Techxplore.com